ALFARUK MULTIMEDIA®
Статистика✨ ቀደምቱ አል-ፋሩቅ ኦዲዮ ቪዥዋል ፕሮዳክሽን በአዲስ አቀራረብ ተመለሰ! ✨ ጥራት ያላቸውን ፊልሞች፣ ሙሃደራዎችን፣ ነሺዳዎችን እና መንዙማዎችን ይዞላችሁ ቀርቧል። 📌 የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ 👉 [Join Channel] (https://t.me/ethioalfa) ▶️ የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ፡ 👇👇👇 https://www.youtube.com/channel/UCDIi
- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 4
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Видео
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 494
- 1/48двое суток
- 566
- 1/72трое суток
- 610
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በአልፋሩቅ መልቲሚዲያ ኘሮዳክሽን የተለቀቀው ይህ አዲስ ነሺዳ የነቢያችን (ﷺ) ውበትና ፍቅር የፈሰሰበት፣ የልብን ስሜት የሚኮረኩር እውነተኛ የመንፈስ ድግስ ነው። የአለማቱ እዝነት (ﷺ) መወለድ የነቢያችን (ﷺ) ወደዚች አለም መምጣት የጨለማው ዘመን ማብቂያ፣ የእዝነትና የብርሃን መውጫ ነበረ። ነሺዳው የሳቸውን ታላቅነት፣ ለሰዎች ሁሉ የተላኩት የፍቅርና የሰላም መሪ መሆናቸውን በሚነካ መልኩ በማስታወስ ልባችንን በውዴታና በጉጉት እንዲሞላ ያደርጋል። የሳቸውን መወለድና ታላቅ ባህሪ ሲያወሳ አእምሮን በፍቅር ያንሳፍፋል፤ አይንንም የእንባ ዘንበል ያደርጋል። የሙአዝ ሀቢቢ የተለየ ስጦታ የሙአዝ ሀቢቢ ድንቅና ማራኪ ድምፅ ደግሞ ይህንን ታላቅ መልእክት ወደ እያንዳንዱ ልብ በቀጥታ የሚያደርስ ድልድይ ሆኗል። ድምፁ ውስጥ ያለው ጥልቅ ስሜት፣ ቅንነትና መንፈሳዊ ልስላሴ አዳማጩን ከውጫዊው አለም ውካታ አላቆ ወደ ታላቁ ነቢይ (ﷺ) የፍቅር ውቅያኖስ ያጠልቃል። የኡስታዝ ሰኢድ ድንቅ ስንኞች የኡስታዝ ሰኢድ ጥልቅና ልብ የሚያቀልጡ ስንኞች ለስራው ልዩ ግርማ ሞገስ ሰጥተውታል። እያንዳንዱ ቃል በጥንቃቄ ተመርጦ፣ በፍቅርና በእውቀት ተጠምቆ የተፃፈ በመሆኑ መንፈስን ያረሰርሳል፤ ነፍስንም በኢማን ብርሃን ያድሳል። ይህ ስራ የዜማና የቃል ቅንብር ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም የነቢያችንን (ﷺ) መንገድ እንድንከተል፣ በሱናቸው እንድንታደስና በፍቅራቸው እንድንመሰጥ የሚያደርግ ጥሪ ነው። በእውነት መንፈስን የሚያረጋጋና ልብን ሙሉ በሙሉ የሚማርክ ድቅስ ስራ ነው። ተለቋል🔥ተለቋል🔥ተለቋል🔥ተለቋል 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/f4a13FEn_u0?si=dkrCyrJd0bV8b_Wv
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በፍቅር የታመመ ልብ… ከሀበሻ ምድር እስከ ጦይባ! ✨ አንድ ወረቀት፣ ጥቂት የሠርዶ ቀለም እና በጥልቅ ናፍቆት የታሰረ ልብ… ይህ በቃላት ለመግለፅ የሚያቅት፣ በስሜት እንጂ በጽሁፍ ተተርጉሞ የማያልቅ የፍቅር ጥግ ነው! "ጌታዬ እንዴት ነሁ… ምነው ባየንሁ?" የኡስታዝ ሰኢድ አህመድ ድንቅና ስሜት ቀስቃሽ ግጥም በማዲህ መሀመድ አሚን በሚገርም ዜማ በጣፋጭ ድምፅ ሲታጀብ—ሩህ ቀድማ ወደ መዲና ትበራለች! እግር ሀበሻ ምድር ቢሆንም፣ ቀልብ ግን የጦይባን አየር መተንፈስ ይጀምራል። ✨ ያንን ውበት ማን በነገረው? ከሰማይ ጨረቃ ይልቅ የሚያበራውን ያንን ሙሉ ጀማል… ጠላትን እንኳ ሳይቀር በምህረት እና በእዝነት የሚያረክሰውን ያንን መልካም ጧይባ… ግንድ እና ድንጋይ ሳይቀር ነቢይነትዎን የመሰከሩለትን ያንን ድንቅ ሀይባ… እስኪ እንዴት ብሎ ዝም ይበል? ናፍቆቱ እኮ አቅም አሳጥቶ ልብን ይዘርፋል! መሬቱ፣ ዳመናው፣ ዛፉ፣ እንስሳቱ ሁሉ ላንቱ ሰገዱ፤ ጨረቃ እንኳን ለሁለት ተከፈለች… ታዲያ የሰው ልጅ ልብ እንዴት አይንሰቀሰቅ? እነዚያ አሺቆች፣ እነዚያ ሶሃባዎች እኮ በፍቅርዎ ሰክረው ነው «እየሞቱ የኖሩት፣ እየኖሩም የሞቱት»! የሲዲቅ ፍቅር፣ የኡመር ጀግንነት፣ የኡስማን ልግስና፣ የዐሊይ ወኔ፣ የሀምዛ አንበሳነት፣ የቢላል ናፍቆት… ሁሉ የዚያ ታላቅ ኑር ነፀብራቅ ነበር። "ያዙት ወዳጅሁን ዘርግተሁ እጅሁን… ራህመት መሙላቱን አውቃሁ ልብሁን፤ ያስክኑልኝ አሁን ሳይገለኝ ሁብሁ!" በኡስታዝ ሰኢድ አህመድ ግጥም ተፅፎ፣ በማዲህ መሀመድ አሚን ድንቅ አዜብ የቀረበው ይህ ልብ የሚነካ መንዙማ በአልፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን (Al-Faruk Multimedia Production) ይፋ ሆኖ ተለቋል! 👇 አሁኑኑ ገብታችሁ በመመልከት የረሱልን (ﷺ) የፍቅር ማዕበል አብራችሁን ተካፈሉ፦ [https://youtu.be/DiuZ0XciVNI?si=MWQ1lljFOdIneud5] #አልፋሩቅ_መልቲሚዲያ #ኡስታዝ_ሰኢድ #መሀመድ_አሚን #መንዙማ #ናፍቆት #ጦይባ #መዲና #የፍቅር_መንገድ #ሶለዋት
ተለቀቀ🔥ተለቀቀ🔥ተለቀቀ🔥ተለቀቀ🔥 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://youtu.be/DiuZ0XciVNI
ዛሬ ምሽት ይጠብቁን....
ኸሚስ ምሽት ይጠብቁን
ቁረተል ዓይኔ የሐበሾች የፍቅር ልሳን! ከጥንት ከጠዋቱ የተዘረጋ የፍቅር መረብ ሐበሾች ዘንድ አለ። ይሄ ፍቅር ብዙዎችን በዝምታ አርምሞ ውስጥ ዱሏል። የርካቶችን የልብ አታሞ እየደለቀ በትዝታ ሲያከንፍ ሰንብቷል። ናፋቂና አፍቃሪዎችን በቃላትና በስንኝ ሲያናግር ኖሯል። ሐበሻ ለፍቅር ርቀት ያልገደባት፣ ከጥንት እስከ ዛሬ ናፍቆት የወለዳቸው ቅኔዎች የሚከረርባት አንባ ነች። ይሄ ኑባሬ ቀደምቶቻችን ያሰመሩትን ቀኖና ይዞ እስካሁ እየተጓዘ ነው። ቀደምቶቻችን ተወዳጁን ሰይዳችንንﷺ ቁረተል ዓይኔ ሲሉ አወድሰዋል። ያይኔ ማረፊያ ሲሉ ዘክረዋል። ይሄ ትውልድም ይህንኑ የውዳሴ መንገድ አጥብቆ ይዞታል። የአበው ውርስ አድርጎ ተቀብሎ ከዘመኑ ጋር እያራመደ ይገኛል። አሁንም ሐበሾች በየ ጊዜው ቁረተል ዓይኔ እንላለን። የዘመኑ ጥበባዊ አንድምታን ተከትሎ በተለያዩ ገጣሚያን ቀለም እየተቀዳ በማዲሆቻችን ልሳን ውዱ ነቢ ሲወደሱ ይኖራሉ። ታላቁ የውልደታቸው ወር ወርሃ ረቢዕም ድባቡን ማሸብረቅ ጀምሯል። እኛም በተለያዪ ቀለማት፣ በተለያዪ ማዲሆቻችን ልሳን…አሽረፈል ኸልቅንﷺ ቁረተል ዓይኔ እንላለን!! በቅርቡ ከሚለቀቁ ቁረተል ዓይኔዎች ውስጥ አንዱ በገጣሚያችን ዛሒድ ኢቅባል ተፅፎ በድምፀ መረዋው ማዲህ አንዋር አል ቡርዳ የተዘከረው ቁረተል ዓይኔ ነው። በቅርብ ቀን ለታዳሚያን ይደርሳል!
የሐበሻ ቀዬ 3 በቅርብ ቀን ይጠብቁን
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የአልፋሩቅ ሱፐርአፕ (Al Faruk SuperApp) ሁሉንም አገልግሎቶች በአንድ ላይ አጠቃሎ የያዘ በመሆኑ አጠቃቀሙ በጣም ቀላል እና ምቹ ነው። መተግበሪያውን በአግባቡ ለመጠቀም የሚከተሉትን ጥቂት ደረጃዎች መከተል በቂ ነው። #muslimtiktok #foryoupage #alfaruk_multimedia_production #alfaruk #viralvideo @Alif Videography
ይህ ፊልም الخوافي والقوادم በሚል ርዕስ የተሰራ የግልፅና የህቡዕ ወይም የውጪና የውስጥ ድጋፍ የሚል ትርጉም ያለው በሁለቱ የነብዩ ክቡራን አጎቶች ሰይዱና አል ዓባስ እና ሰይዱና ሐምዛ የህይወት ገድል ዙርያ የሚያጠነጥን ድንቅ ፊልም ነው። ፊልሙ ሐምዛ ቀድመው ሰልመው ለነብዩ ይሰጡ የነበረውን ድጋፍ፤ አል ዓባስ ዘግይተው ቢሰልሙም ከእስልምና በፊት እንኳን ሁለንተናዊ ድጋፋቸው ለነብዩ እንደነበርና በቀዳሚው የእስልምና ዘመን ያበረከቱትን አስተዋፅዖ ያስቃኛል። አል ፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽንም ይህንን ታሪካዊ ፊልም ለአማርኛ ተናጋሪው ማህበረሰብ በማድረስ ላይ ያለውን ሃላፊነት በመረዳት፣ ለታሪኩ እውነትነት እና ለኢስላማዊ እሴቶች ቅድሚያ በመስጠት በጥንቃቄ አስተርጉሞ አቅርቧል። ፊልሙን በምናዘጋጅበት ጊዜ፣ የፊልሙን ስሜት እና ጥልቀት ለመጠበቅ የተለየ ትኩረት ተሰጥቷል። ዓላማችንም ይህንን ውድ የታሪክ ቅርስ ተደራሽ ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ ተመልካቾቻችን የታሪኩን መልክ በትክክል ተረድተው እንዲማሩበት ጭምር ነው። በመሆኑም የምንግዜም አገልጋያችሁ አል ፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን ይህንን ታሪካዊ ፊልም በአማርኛ አስተርጉሞ በአቻ የትወና ትርጉምና በላቀ ጥራት ወደናንተ ሲያቀርብ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል። ዕሮብ ምሽት 12:00 ላይ ይጠብቁን። መልካም ጊዜ!
የአልፋሩቅ ሱፐርአፕ (Al Faruk SuperApp) ሁሉንም አገልግሎቶች በአንድ ላይ አጠቃሎ የያዘ በመሆኑ አጠቃቀሙ በጣም ቀላል እና ምቹ ነው። መተግበሪያውን በአግባቡ ለመጠቀም የሚከተሉትን ጥቂት ደረጃዎች መከተል በቂ ነው፦
ጽህና፣ እምነትና ተአምር፡ የዓለም ሴቶች ሁሉ አርአያ፣ የጽናትና የትሕትና ተምሳሌት! በቅዱሳን ቁርኣን የተመሰከረላት ሴት ማናት ? ወዳያው በአእምራቹ ማን ከሰተች? ። ከዚህ ቀጥሎ አንድ ጥቆማ ብነግራቹ ወዲያው ታውቃታላቹ በሰሙ የቁርኣን ሱራ የተሰየመላት ። አዎ አሁን እንደምታውቋት ተሰፋ አድርጋለሁ ? ቅድስት መርየምን ያላቹ ራሳቹን ሸልሙ እና ምን ልላቹ ነው የመርየም ታሪክ ከልጅነት እስከ ተአምረኛው የልደት ጉዞ ድረስ በታላቅ ጥበብ የተሰነደው ድንቅ ፊልም አሁን በአልፋሩቅ ቀርቧላቹሃል ። አል ፋሩቅ መልቲ ሚዲያ ፕሮዳክሽን ይህን በአለማቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያገኘ ተከታታይ ፊልም በአማርኝ ሲያቀርብ በታላቅ ደስታ ነው። እና የቅድስቷን መርየምን ታሪክ ማውቅ የወዴታ ግዴታ ነው ብያለሁ ።