tgindex
ጠበቃ ጌታሁን አያልቅበት⚖️

ጠበቃ ጌታሁን አያልቅበት⚖️

Статистика

ማንኛውም የህግ ምክር እና ጠበቃ ሲፈልጉ @Lawyer_Getahun @Getsh_bot ☎ 0910551429

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
3
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
am
В каталоге с
15 авг.
Подписчики
1 244
мало замеров
Замеров пока мало
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
578
22 постов
Вовлечённость
46,5%
к подписчикам
Постов в день
0,4
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
254
1/48двое суток
291
1/72трое суток
313

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ✅ ለግንዛቤ - የቤት ካርታ ቢጠፋብን ምን ማድረግ ይኖርብናል? የቤት ወይም የቦታ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ማጣት ለማንኛውም ባለቤት ወይም ባለሀብት ትልቅ ጭንቀት ነው። በኣዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የመኖሪያ ቤቶችዎን የሚያስተዳድሩ፣ ለኢንቨስትመንት ቦታ የያዙ ወይም ደንበኞችዎን በሪል እስቴት ግብይት ውስጥ የሚያግዙ ከሆነ፣ የካርታ ምትክ የማውጣቱን ሕጋዊ ሂደት በደንብ ማወቅ አስፈላጊ ነው። ካርታ ቢጠፋብዎ፣ የኣዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጠፋውን ካርታ ውድቅ (እንድመክን) በማድረግ አዲስ ምትክ ካርታ ለመስጠት የሚከተሉትን ጥብቅ የአስተዳደር ሂደቶች እንድታልፉ ይጠይቃል። በክፍለ ከተማው የሪኮርድና ማህደር ክፍል ምትክ ካርታ ለማውጣት የሚያስፈልጉት ዋና ዋና ደረጃዎች የሚከተሉት ናቸው፦ 1. የይዞታው ሁኔታ እና እገዳ የሌለበት መሆኑን ማረጋገጥ ምትክ ካርታ የማውጣት ጥያቄ ከመጀመሩ በፊት፣ ክፍለ ከተማው የሪኮርድና ማህደር ክፍል የቦታው ማህደር ላይ ማንኛውም ዓይነት እገዳ፣ የሕግ ክርክር ወይም የባንክ ዕዳ የሌለበት መሆኑን ከመዝገቡ ማረጋገጥ አለበት። 2. የፖሊስ ማስረጃ ማቅረብ ባለይዞታው ካርታው እንደጠፋበት ወዲያውኑ ካርታው በጠፋበት ወይም ንብረቱ በሚገኝበት ወረዳ ለሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ማመልከት አለበት። ፖሊስ ጣቢያው ካርታው መ his መጥፋቱን የሚገልጽ ኦፊሴላዊ የፖሊስ ማስረጃ ይሰጣል። 3. የማህደር እና የሰነድ ሁኔታዎችን ማሟላት አመልካቹ በክፍለ ከተማው ፕሮጀክት / መሬት ልማት ጽሕፈት ቤት በስሙ የተከፈተ ንቁ ማህደር ሊኖረው ይገባል። ሂደቱን ለማስቀጠል የሚከተሉት አስፈላጊ ናቸው፦ ወቅቱ ያላለፈበት፣ የታደሰ ብሔራዊ መታወቂያ / የነዋሪነት መታወቂያ። ከማህደሩ ጋር ለማስተያየት እንዲረዳ የጠፋው ካርታ ኮፒ (ካለ)። የይዞታውን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ እና ምትክ ለማግኘት የሚቀርብ ሕጋዊ የማመልከቻ ደብዳቤ። 4. የ20 ቀን ጋዜጣ ማስታወቂያ ማውጣት ማጭበርበርን እና የሶስተኛ ወገን አላስፈላጊ ጥያቄዎችን ለመከላከል፣ የካርታው መጥፋት በፍርድ ቤት ወይም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ላይ በይፋ ማስታወቂያ መውጣት አለበት። ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የ20 ቀናት የምጠባበቂያ ጊዜ ይጀምራል። በነዚህ 20 ቀናት ውስጥ ምንም ዓይነት ተቃዋሚ ወይም መብት ጠያቂ ካልቀረበ ሂደቱ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ይሸጋገራል። 5. የጠፋውን ካርታ ማመከን እና ምትክ ማግኘት የ20 ቀናት የማስታወቂያ ጊዜ ያለተቃውሞ ካበቃ በኋላ፦ 1. ክፍያ መፈጸም፦ በወረዳው፣ በክፍለ ከተማው ወይም በክፍለ ከተማው ገቢዎች ጽሕፈት ቤት አስፈላጊውን የአገልግሎት እና የሌሎች ክፍያዎችን መፈጸም። 2. ካርታውን ማመከን፦ ለወደፊቱ አላስፈላጊ አጠቃቀምን ለመከላከል ባለሥልጣኑ የጠፋውን ዋና ካርታ በማዕከላዊ መዝገብ ላይ በሕግ ውድቅ (እንዲመክን) ያደርገዋል። 3. ምትክ ካርታ መስጠት፦ በሕግ ጸደቀ ምትክ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ለባለይዞታው ይዘጋጃል። ለሪል እስቴት ባለሙያዎች እና ባለቤቶች የሚሆን መልእክት የንብረት ሰነዶችን በጥንቃቄ መያዝ በጣም ወሳኝ ነው። ሁልጊዜም የካርታዎን፣ የቦታ ፕላንዎን እና የተከፈሉ ደረሰኞችን ግልጽ ኮፒዎች (በፎቶ እና በዲጂታል) ይያዙ። ካርታ ቢጠፋብዎ እንኳ ሂደቱን ወዲያውኑ መጀመር የንብረት መብትዎን ያስከብራል፤ ንብረትዎንም ለባንክ እና ለግብይት ዝግጁ ያደርገዋል። ©kidus @ethiolawyer1 @ethiopianattorney

  • ✅ የፌደራል ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት የነሐሴ ወር 2018 ዓ.ም የመኪና ሀራጅ ሽያጭ ላይ የቀረቡ ንብረቶችን ማስታወቅያ ለምትፈልጉ በሙሉ ከተያያዘው ፋይል መመልከት ትችላላችሁ። @Lawyer_Getahun @ethiolawyer1

  • ✅መረጃ ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ በአዲስ አበባ እና ሸገር ከተማ ላይ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን ቢያንስ 150000 ዶላር እንደሚያስፈልገው የሚደነግግ መመሪያን የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አወጣ። አንድ የውጭ አገር ዜጋ በኢትዮጵያ የቤት ባለቤት ለመሆን የማኅበረሰብ ሞራል እና መሰል ጉዳዮች ላይ ገደብ የሌለበት መሆን እንዳለበት ተደንግጓል።በመመሪያው መሠረት የውጭ አገር ዜጋ ማለት፤ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነ የውጭ ዜጋን ሳይጨምር ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሌለው ወይም የሌላ አገር ዜግነት ያለው ማንኛውም ሰው ማለት ነው። የውጭ አገር ዜጎች የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበትን አሠራር ለመወሰን የወጣው መመሪያ ከቀናት በፊት በተጠናቀቀው ሐምሌ ወር የጸደቀ ነው።በመመሪያው መሠረት ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን ሊያሟላ የሚገባው ለአንድ መኖሪያ ቤት የሚያስፈልግ ዝቅተኛ የገንዘብ መጠን ተዘርዝሯል። በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በሸገር ከተማ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን ቢያንስ 150000 የአሜሪካ ዶላር ያስፈልገዋል።ሸገር ከተማን ሳይጨምር በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በትግራይ፣ በሲዳማ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በሶማሌ ክልል፣ በሐረሪ ክልል ወይም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን ደግሞ ዝቅተኛው የገንዘብ መጠን 120000 የአሜሪካ ዶላር ማቅረብ ነው። ከሌሎቹ ክልሎች የውጭ አገር ዜጋ የቤት ባለቤት ለመሆን ዝቅተኛ ገንዘብ የሚጠየቀው በአፋር፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በጋምቤላ ክልል ሲሆን የገንዘቡ መጠን ደግሞ 100000 ዶላር እንደሆነ ተደንግጓል። አንድ የውጭ አገር ዜጋ በኢትዮጵያ ሊኖረው የሚችለው የቤት መጠን አንድ ብቻ ነው።በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ፈቃድ ወስዶ እያለማ ያለ ባለሀብት ግን ይህ ዝቅተኛ የገንዘብ መጠን ሳይገድበው የአንድ ቤት ባለቤት መሆን ይችላል። በመመሪያው መሠረት ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ የተጠቀሰውን ለአንድ ቤት የሚያስፈልግ ገንዘብ የሚያስቀምጥበት የባንክ ሂሳብ እንዲከፈትለትና ገንዘቡን በውጭ ምንዛሬ እንዲያስቀምጥ የሚፈቅድ ደብዳቤ ከሚመለከተው መሥሪያ ቤት በማጻፍ በመረጠው ባንክ ገቢ ማድረግ አለበት። አንድ የውጭ አገር ዜጋ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን የሚያስችል ፈቃድ የሚያገኘው፤ የጸና ፓስፖርት ካለው፣ የወንጀል ታሪክ የሌለው ስለመሆኑ ከሚኖርበት አገር ማረጋገጫ ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ ከቻለ ነው። በተጨማሪም ከሀገር ሰላም፣ ደህንነት፣ ጸጥታ፣ የሕዝብ ጥቅም፣ የማኅበረሰብ ሞራል እና መሰል ጉዳዮች ላይ ገደብ የሌለበት መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃም ማቅረብ አለባቸው ይላል መመሪያው። ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ በመንግሥት ቀጥተኛ ድጎማ ለዜጎች በሚሠሩ የጋራ መኖሪያ ሕንፃዎች ውስጥ የመኖሪያ ቤት ባለቤት መሆን አይችልም፤ ይህም የቤት ባለቤት በሚሆኑ የውጭ ዜጎች ላይ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበትን አግባብ ለመደንገግ በወጣ አዋጅ የተጣለ ገደብ ነው። በአዋጁ መሠረት የውጭ አገር ዜጋ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን ከሀገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋም ወይም ምንጭ ገንዘብ መበደር ወይም ካፒታል ማሰባሰብ አይችልም። በኢትዮጵያ የቤት ባለቤት የሆኑ የውጭ ዜጎችን መብት በተመለከተ ደግሞ መመሪያው ሲዘረዝር ለኢትዮጵያውያን የተሰጡ የንብረት መብቶች ይኖራቸዋል፤ ለግለሰቦች ማከራየት ይችላሉ፣ ለንግድ ዓላማ ማከራየት ግን አይቻልም። ለራሱ እና ለቤተሰቡ የመኖሪያ ፈቃድ፣ የመግቢያ ቪዛና ኢትዮጵያ መመላለስ እንዲችሉ የሚያደርግ አግባብነት ባለው አካል የሚሰጥ እስከ አምስት ዓመት የሚያገለግል የብዙ ጊዜ መመላለሻ ቪዛ የማግኘት መብት አላቸው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣው መመሪያ እና አሠራር መሠረት ከመኖሪያ ቤቱ በሕጋዊ መንገድ የሚያገኘውን የኪራይ ወይም የሽያጭ ገቢ በወቅቱ ተመን በውጭ ምንዛሪ ወደ ውጭ አገር የማስተላለፍ መብት አለው ይላል አዋጁ። መመሪያው ታትሞ በፍትሕ ሚኒስቴር ድህረ ገጽ ላይ ከተጫነበት ቀን ጀምሮ ሥራ ላይ ይውላል ይላል።በፍትሕ ሚኒስቴር ድህረ ገጽ ላይ የተጫነው ባለፈው እሁድ ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ነው። ©ሸገር @ethiolawyer1 @ethiopianattorney

  • ✅ለግንዛቤ - በፍርድ ቤት እግድ የተጣለበትን የማይቀሳቀስ ንብረት (ቤት) የገዛ ሰው፣ ውሉ በመንግሥት አካል ዘንድ ስለተመዘገበ ብቻ "ተገቢውን ጥንቃቄ ያደረገ መልካም እምነት ያለው ገዢ" (prudent purchaser) ተብሎ በሕግ ጥበቃ ሊደረግለትና የንብረቱ ባለቤት ሊሆን አይችልም። ሰበር በመዝገብ ቁጥር 186626 ላይ የሰጠው ውሳኔ ። የውሳኔው ዋና ዋና ነጥቦች፦ የገዢው የማጣራት ግዴታ፦ ማንኛውም የማይቀሳቀስ ንብረት የሚገዛ ሰው ውል ከመዋዋሉና ከመመዝገቡ በፊት፣ በንብረቱ መዝገብ ላይ የፍርድ ቤት እግድ፣ የዕዳ ወይም የቀደመ የሦስተኛ ወገን መብት መኖር አለመኖሩን የመርመርና የማጣራት የሕግ ግዴታ አለበት። የምዝገባ ገደብ፦ ውል ባለሥልጣን ፊት መመዝገቡ ወይም መጽደቁ ብቻውን፣ በሕግ የተጣለን እግድ ወይም የትዳር አጋርን ፈቃድ ማጣት የሚያስቀር/የሚያጸና ሕጋዊ ሽፋን ሊሆን አይችልም። ውጤት፦ ገዢው አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሳያደርግ እግድ ያለበትን ንብረት ቢገዛ፣ ውሉ ሕጋዊ ውጤት አይኖረውም ውድቅ ይሆናል)፤ የንብረቱም ባለቤት መሆን አይችልም። ሰበር መ/ቁ 186626 የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም @ethiolawyer1 @ethiopianattorney T.me/Lawyer_Getahun

  • 4 авг.507104

    ✅ ለግንዛቤ - የዋስትና ገንዘብ እንዴት ማስመለስ ይቻላል አንድ በወንጀል የተጠረጠረ ሰው የዋስትና ገንዘብ እንዲያሲዝ የሚደረግበት መሠረታዊ ዓላማው ፍርድ ቤት በፈለገው ጊዜ ሁሉ ለመቅረብ የሚችል መሆኑን መተማመኛ እንዲሆን ነው። - በፍርድ ቤት የተያዘን የዋስትና ገንዘብ ተመላሽ እንዲደረግ ለማድረግ 1ኛ በሁለት ፍርድ ቤቶች የዋስትና ገንዘብ ከተያዘ የቀድሞ እንዲመለስ በመጠየቅ ብዙውን ጊዜ በጊዜ ቀጠሮ ላይ ያሉ ባለጉዳዮች በዋስትና እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ መደበኛ ክስ ሲቀርብ መደበኛ ክሱን እያስተናገደ ያለው ፍርድ ቤት አዲስ የዋስትና ገንዘብ እንድታስዙ ሊያደርግ ይችላል። እንዲህ በሆነ ጊዜ በቀድሞው ፍርድ ቤት የተያዘው የዋስትና ገንዘብ ተመላሽ እንዲደረግ መጠየቅ ይቻላል። 2ኛ የወንጀል ምርመራ መዝገቡን ዓቃቤ ሕግ የዘጋው ከሆነ ፖሊስ ያደረገውን ምርመራ መነሻ በማድረግ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ግለሰቡ የተጠረጠረበት ወንጀል እና የተደረገው ምርመራ በቂና በሕግ አግባብ የሚያስጠይቅ መሆን እና አለመሆኑን መርምሮ አግባብነት የለውም ብሎ ሲያምን በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 42 መሠረት መዝገቡን የዘጋው ከሆነ የተሰጠውን ውሳኔ በመያዝ የዋስትና ገንዘብ እንዲመለስ መጠየቅ ይቻላል። 3ኛ በክሱ ላይ ነፃ ወይም ጥፋተኛ ከተባለ በኋላ የዋስትና ገንዘብን በተመለከተ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይሰጥበታል #የዋስትና ገንዘብ የሚታዘዝበት ዋነኛው ምክንያት ፍርድ ቤት ለሚሰጣቸው ቀጠሮዎች መተማመኛ ከሆነ መዝገቡ የመጨረሻ ውሳኔ ከተሰጠው የዋትናው ገንዘብ ተመላሽ እንዲሆን ትዕዛዝ ይሰጥበታል።                         ©ቴዎድሮስ @ethiolawyer1 @ethiopianattorney

  • ✅መረጃ - በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በክረምት በተረኛ ችሎት የሚሰሩ ጉዳዬችን ይመለከታል የፌደራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/13 አንቀጽ 38 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት ከመደበኛ የፍርድ ቤት የስራ ጊዜ ውጭ አስቸኳይ ጉዳዬች እንደሚስተናገዱ በተደነገገው መሰረት እንዲሁም ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በሆኑበት ወቅት ለዳኞች ተራ ወጥቶ በሚደርሳቸዉ ተራ መሰረት መደበኛ የፍርድ ቤቱ የስራ ጊዜ የማይጠብቁ አስቸኳይ ጉዳዬች በፍርድ ቤቶች እየታዩ እልባት የሚሰጥበት የአሰራር ስርዓት ተዘርግቶ ሲሰራ የነበረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት መሰረታዊ የመብት ጥሰት የሚያስከትሉ በባህሪያቸው ጊዜ የማይሰጡ መደበኛ የፍርድ ቤቱ የስራ ጊዜ እስኪጀመር አፋጣኝነታቸው ታይቶ ዉሳኔ ካልተሰጠባቸው የመብት መጣስን ሊያስከትል የሚችሉ እና ሊካስ የማይችል ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ ጉዳዮችን አይቶ መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በሚሆኑባቸው ጊዜ ማለትም ከነሃሴ 01 ቀን እስከ መስከረም 30 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ በተረኛ ችሎት በወንጀል እና በፍታብሄር ጉዳዮች መደበኛ የፍርድ ቤት የስራ ጊዜን የማይጠብቁ ጉዳዮች አስቸኳይ ጉዳዮች ሲቀርቡ የሚታዩ ይሆናል በዚሁ መሰረት፡- በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በክረምት የሚሰጡ የዳኝነት አገልግሎቶች በፍታብሄር ከሚቀርቡ ጉዳዮች ፡- ➢ አስቸኳይ የእግድ አቤቱታዎች ➢ የልጅ ቀለብ ➢ አካል ነጻ ለማውጣት ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎች ➢ እንቅስቃሴን ገዳቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎች ➢ ሰራተኞች በአሰሪዎቻቸው ላይ የሚያቀርቡት የደመወዝ ክፍያ የሚመለከቱ አፈጻጸም ጉዳዮች ➢ ከግልግል ዳኝነት ትዕዛዞች ጋር ተያይዞ አስቸኳይ የማህተም አገልግሎት ጥያቄዎች (ለእግድ, መጥሪያ ለማድረስ..) ➢ አንገብጋቢ እና ጊዜ የማይሰጡ መደበኛ የፍርድ ቤቱን የስራ ጊዜ መጠበቅ የማይችሉ በተረኛ ችሎቱ ዳኛ የሚወሰኑ ሌሎች የፍታብሄር ጉዳዮች በወንጀል ከሚቀርቡ ጉዳዮች፡- ➢ ዋስትና ➢ አመክሮ ➢ አርቲዲ (እስረኛ ያለባቸው የሚቀርቡ የወንጀል መዛግብት ) ➢ በተሰብሮ የሚቀርቡ አቤቱታዎች ➢ ጊዜ ቀጠሮ(አራዳ ምድብ ችሎት) ➢ ለመሰየም የሚቀርብ አቤቱታ ➢ እስረኛ ያለባቸው መዝገቦች ➢ አንገብጋቢ እና ጊዜ የማይሰጡ መደበኛ የፍርድ ቤቱን የስራ ጊዜ መጠበቅ የማይችሉ በተረኛ ችሎቱ ዳኛ የሚወሰኑ ሌሎች የወንጀል ጉዳዮች ባጠቃላይ ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በሚሆንባቸው ጊዜያት መደበኛ የፍርድ ቤቱን የስራ ጊዜ የማይጠብቁ ጊዜ የማይሰጡ እና አጣዳፊ የሆኑ የወንጀል እና የፍታብሄር ጉዳዮች በተረኛ ችሎት የሚስተናገዱ መሆኑን ተገልጿል። ©federal first instance court @ethiolawyer1 @ethiopianattorney

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • ✅ ለግንዛቤ - በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1196(1) መሠረት በሕጋዊ መንገድ የተሰጠ የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያለው ሰው የንብረቱ ባለቤት ለመሆኑ የሕግ ግምት የሚወሰድ በመሆኑ፣ ይህ ግምት ሊፈርስ የሚችለው ካርታው ከሕግ ውጪ መሰጠቱ ወይም ሰነዱን የመስጠት ሥልጣን በሌለው አካል የተሰጠ መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ሲሆን፣ ከዚህ ውጪ በሰው ምስክርነት ወይም ገንዘብ አውጥቻለሁ በሚል ክርክር ብቻ ሊፈርስ አይችልም። - ​የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ አቶ ብርሃኑ ከበደ እና ም/ኢ/ር ጥሩነሽ ዱባለ፣ መዝገብ ቁጥር 132 (ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም) ​በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 40 (1 እና 2) መሠረትም የንብረት ባለቤትነት መብት የሚጠበቀው በሕጋዊ መንገድ በተያዘ ይዞታ ላይ ሲሆን ብቻ ነው። በመሆኑም በጋብቻ ውስጥ ባልና ሚስት በወላጅ ስም በተመዘገበ ይዞታ ላይ ገንዘብና ጉልበት በማፍሰስ ቤት ቢገነቡ እንኳ፣ ይዞታውም ሆነ በይዞታው ላይ የተገነባው ቤት የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ሊሆን አይችልም። ​በቤቱ ግንባታ ላይ በትዳር ዘመን በባልና ሚስት የተደረገ የገንዘብ ወጪ ወይም አስተዋጽኦ ካለ፣ ግምቱን ከመጠየቅ ውጪ በሌላ ሰው ስም ባለው ይዞታ ላይ ያረፈውን ቤት የጋራ ንብረታችን ነው ብለው የክፍፍል ጥያቄ ማቅረብ አይችሉም። ​ስለሆነም፣ በጋብቻ ውስጥ በወላጆች ስም ባለው መሬት ላይ የሚገነባ ቤት የባልና ሚስት የጋራ ሀብት ሳይሆን የባለይዞታው ንብረት እንደሆነ የሚቆጠር ሲሆን፣ በፍቺ ጊዜ የትዳር አጋሮች መብት የሚጠበቀው ያወጡትን ገንዘብ በድርሻቸው ተመላሽ እንዲደረግላቸው በመጠየቅ እንጂ የንብረቱን/የቤቱን ክፍፍል በመጠየቅ አይደለም። @Lawyer_Getahun @ethiolawyer1 @ethiopianattorney

  • ✅ ለግንዛቤ የውርስ ክፍፍል ከተጠናቀቀ በኋላ አዲስ ንብረት ቢገኝስ? የሕግ መፍትሔው ምንድን ነው? ብዙ ጊዜ ወራሾች የውርስ ንብረታቸውን ተከፋፍለው ከጨረሱ በኋላ፣ ቀደም ሲል ያልታወቁ ወይም ያልተካተቱ አዳዲስ የሟች ንብረቶች (መሬት፣ ቤት፣ ገንዘብ...) ሲገኙ ይታያል። በዚህ ጊዜ "ቀደም ብለን ተከፋፍለናልና በቃ" ወይንስ "አዲስ የክፍያ ሥርዓት መጀመር ይቻላል?" የሚለው አከራካሪ ነጥብ ነው። የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 153231 (ቅጽ 23) ላይ ለዚህ ጉዳይ አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል። የጉዳዩ ፍሬ ነገር አመልካቾች እና ተጠሪ የሟች ወራሾች ሲሆኑ፣ ቀደም ሲል በነበራቸው ክርክር የውርስ ንብረት ክፍያ አከናውነው ነበር። ሆኖም አመልካቾች "ቀደም ሲል በክፍያው ያልተካተቱ እና ተጠሪ ደብቆ የያዛቸው አዳዲስ ይዞታዎች ስላሉ ዳግም ይከፈለን" ሲሉ ክስ አቀረቡ። ተጠሪ በበኩሉ "ጉዳዩ ቀደም ሲል ውሳኔ አግኝቷል (Res Judicata)፣ ዳግም መጠየቅ አይቻልም" በማለት ተከራክሯል። የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ችሎቱ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1103 እና 1104ን መሠረት በማድረግ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ወስኗል፦ 1. አዲስ ሀብት ከተገኘ ክፍያ ይፈጸማል፦ የውርስ ንብረት ክፍያ ከተደረገ በኋላ፣ በክፍያው ውስጥ ያልገቡ አዲስ ሀብቶች ከተገኙ አዲስ የክፍያ ሥርዓት መፈጸም ይቻላል። 2. ከዚህ ቀደም በነበረ ውሳኔ አይታገድም፦ አዳዲስ ንብረቶች መገኘታቸው እየታወቀ "ቀደም ሲል ክርክር ተደርጎበታል" በሚል ምክንያት ወራሾችን መከልከል ፍትሃዊ አይደለም። ንብረቱ በቀድሞው መዝገብ ካልተካተተ "ታይቷል" ሊባል አይችልም። 3. መረጃ መደበቅና ስህተት፦ ወራሾች ንብረቱ መኖሩን ሳያውቁ የቀሩት በሌላኛው ወራሽ መረጃ በመደበቁ (ተንኮል) ወይም በሌላ ስህተት ከሆነ፣ መብታቸውን በሕግ መጠየቅ ይችላሉ። በአጠቃላይ የውርስ ክፍያ ተፈጽሟል ማለት ጉዳዩ አከተመ ማለት አይደለም። በስህተት፣ በመዘንጋት ወይም በተንኮል ያልተካተቱ ንብረቶች ካሉ ሕጉ ድርሻ እንዲጠየቅ መብት ይሰጣል። • በውርስ ክፍፍል ሰነድ ላይ "ከዚህ በኋላ በማንኛውም የሟች ንብረት ላይ ጥያቄ የለንም" የሚል ቃል ቢኖር እንኳ፣ ያ የሚሠራው በወቅቱ በታወቁት ንብረቶች ላይ ብቻ ነው። ተደብቀው በቆዩ አዳዲስ ንብረቶች ላይ የወደፊት መብትን አያሳጣም። @Lawyer_Getahun @ethiolawyer1 @ethiopianattorney

  • ✅ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ - "በወንጀል የተከሰሰ ሰው ጥፋተኛ ነው ሊባል የሚችለው ዐቃቢ ህግ ተከሳሹ ወንጀሉን ስለመፈፀሙ ከተከሳሹ በላይ ስላስረዳ ብቻ ሳንሆን ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ ስለ ተከሳሹ ድርጊት ሲያስረጃ ብቻ ነው" የፌዴሬሽን ምክር ቤት በ2018 ዓ.ም. ሰኔ 29 ቀን ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ፣ በወንጀል ፍትሕ ዘርፍ ከተሰጡ እጅግ ወሳኝ የሕገ መንግሥት ውሳኔዎች መካከል ሊመደብ የሚችል ውሳኔ አሳልፏል። ምክር ቤቱ የሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ያቀረበውን ምክረ ሐሳብ በመቀበል ፣ አቃቤ ሕግ ሊያሟላው የሚገባው ዝቅተኛ የማስረጃ መስፈርት ከተከሳሹ ንጹሕ ሆኖ የመገመት ሕገ መንግሥታዊ መብት አንጻር መታየት እንዳለበት በግልጽ አስቀምጧል። ንጹህ ሆኖ የመገመት መብት ዐቃቤ ህግ እያንዳንዱን የወንጀል ክስ አላባውያን ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ እንዲያስረዳ ግዴታ ይጥልበታል። የጥፋተኝነት ፍርድ ሊሰጥ የሚችለው የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተከሳሽ መከላከያ የተሻለ ይመስላል በሚል ወይም ተከሳሹ ድርጊቱን አለመፈጸሙን ወይም ንጹሕነቱን ማረጋገጥ አልቻለም በሚል ምክንያት አይደለም ሲል ወስኗል። ስለዚህ ከዚህ በሗላ የዓቃቤ ህግ ምስክሮች የተሻለ አስረድተዋል ተከሳሹ የዓቃቤ ህግን ማስረጃ አላስተባበለም ተከሳሹ የተከሰሰበትን ወንጀል ስለመፈፀሙ ዓቃቤ ህግ በበቂ  ያስረዳ(የተመሰከረበት) ስለሆነ በሚሉ ምክኒያቶች ብቻ ተከሳሹን ጥፋተኛ ማለት እንደማይገባ እና ከማናቸውም ጥርጣሬ በፀዳ መልኩ ወንጀሉን ስለመፈፀሙ ዓቃቤ ህግ የማስረዳት ግዴታ ያለበት መሆኑን በሙሉ ድምፅ አቋም ተይዞ ዉሳኔ ተሰጥቶበታል። የውሳነው ሙሉ ክፍል ከተያያዘው ዶክመንት ማየት ይቻላል። @lawyer_getahun @ethiolawyer1 @ethiopianattorney

  • ✅ ለመረጃ - በክረምት በከፊል የሚዘጉና የማይዘጉ ፍ/ቤቶች ዝርዝር I) በከፊል የሚዘጉ:- 1. የፌደራል ፍ/ቤቶች:- -ከነሐሴ 1/2018 ዓ.ም - መስከረም 30/2019 ዓ.ም በከፊል ዝግ ይሆናሉ:: [በፌደራል ፍ/ቤቶች ዐዋጅ ቁጥር 1234/2012 አንቀጽ 38(2) መሠረት] 2. የኦሮሚያ ክልል:- -ከሐምሌ 21/2018 ዓ.ም - መስከረም 20/2019 ዓ.ም በከፊል ዝግ ይሆናሉ:: [በክልሉ ፍ/ቤቶች ዐዋጅ ቁ.216/2011 አ. 44(1)+በደንብ ቁ.7/2012 አ. 80(1) መሠረት] 3. የአማራ ክልል:- -ከነሐሴ 1/2018 ዓ.ም - መስከረም 30/2019 ዓ.ም በከፊል ዝግ ይሆናሉ:: [በክልሉ ፍ/ቤቶች ዐዋጅ ቁ. 282/2014 አ.41 መሠረት] 4. የትግራይ ክልል:- -ከሐምሌ 7/2018-መስከረም 7/2019 ዓ.ም በከፊል ዝግ ይሆናሉ:: 5. የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል:- -ከሐምሌ 21/2018 ዓ.ም - መስከረም 20/2019 ዓ.ም በከፊል ዝግ ይሆናሉ:: 6. የሲዳማ ክልል:- -ከሐምሌ 21/2018 ዓ.ም - መስከረም 21/2019 ኦዓ.ም በከፊል ዝግ ይሆናሉ::] [በክልሉ ዐዋጅ ቁ.40/2016 አ.52(2)] 7. የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል:- -ከነሐሴ 1/2018 ዓ.ም -መስከረም 30/2019 ዓ.ም በከፊል ዝግ ይሆናሉ:: [በዐዋጅ ቁ.6/2016 አ. 59] 8. የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል:- -ከነሐሴ 1/2018 ዓ.ም - መስከረም 30/2019 ዓ.ም በከፊል ዝግ ይሆናሉ:: [በክልሉ የፍ/ቤቶች ዐዋጅ ቁ. 1/2016 አ. 59(2)] 9. የሸሪዓ ፍ/ቤቶች:- -ከነሐሴ 1/2018 ዓ.ም - መስከረም 30/2019 ዓ.ም (የኒካ፣ “ጋብቻ” እና ቀለብ ጉዳዮችን ከማስተናገድ በስተቀር) ዝግ ናቸው:: 10. የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል:- -ነሐሴ 1/2018 ዓ.ም - መስከረም 30/2019 ዓ.ም በከፊል ዝግ ይሆናሉ:: 11. የሱማሌ ክልል -ከሐምሌ 1/2018 ዓ.ም - ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም ድረስ ዝግ ሆነው ይቆያሉ። (የሶማሌ ክልል ፍ/ቤቶች ዐዋጅ ቁ. 206/2013 አንቀጽ 35(2) Il) የማይዘጉ 1. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍ/ቤቶች:- -አይዘጉም—መደበኛ ሥራቸውን ይቀጥላሉ! IIl) መረጃ ያልተገኘ 1. የአፋር ክልል :-NA 2. የሐረሪ ክልልል :-NA 3. የጋምቤላ ክልል:- NA 4 የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፍ/ቤት 5. የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን: NA 6. የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ይግባኝ ሰሚ አስተዳደራዊ ፍ/ቤት: NA ©hailu hassen @ethiolawyer1 @ethiopianattorney

  • ✅መረጃ - አዲስ የሞተር ተሽከርካሪዎች የባለቤትነት ታክስ ሊጣል ነው ​ኢትዮጵያ በ2020/21 የበጀት ዓመት የሚተገበር አዲስ የሞተር ተሽከርካሪዎች የባለቤትነት ታክስ ለማስተዋወቅና የገቢ ክፍፍል ሥርዓት ለመዘርጋት እየተዘጋጀች ነው። የቀረበው የሕግ ረቂቅ እስከ ታህሳስ 2019 ዓ.ም ድረስ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚቀርብ ሲሆን፥ ገቢው በፌዴራልና በክልሎች መካከል የሚከፋፈል ይሆናል። ​የገንዘብ ሚኒስቴር እርምጃው የሀገር ውስጥ ገቢን ለማሳደግ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጿል። ሆኖም የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ታክሱ በተለይ አነስተኛ ገቢ ባላቸውና ተሽከርካሪዎቻቸውን ለዕለት ተዕለት ሥራ በሚጠቀሙ ዜጎች ላይ ተጨማሪ የኢኮኖሚ ጫና እና የዋጋ ንረት እንዳያስከትል ስጋታቸውን ገልጸዋል። ​የመንግሥት አካላት የሕግና የአሠራር ዝግጅቶችን እያጠናቀቁ ሲሆን፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ እና የገቢ ክፍፍል ቀመሩ አፈጻጸሙን ይወስናሉ። ©ካፒታል @Lawyer_Getahun @ethiolawyer1 @ethiopianattorney

  • ✅ለግንዛቤ - የብሔራዊ ባንክ አዲሱ ውሳኔ፤ ከንግድ ውጪ ላለነውስ ምን ይዞ መጣ? - የብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ባንኮች የሚያበድሩበትን ጣሪያ ሙሉ ለሙሉ የተነሳ መሆኑን አስቀምጧል፡፡ በተጨማሪ የውጪ ንግድ ወጪን ሊቀንስ የሚችልም እርምጃ ወስዷል ፡፡ ይህ በሌላ ሀገር ቢሆን ኖሮ ነጋዴው እቃ ወደ ሀገር የሚያስገባበት ወጪ የቀነሰለት በመሆኑ በቀጣይ ከውጪ የሚመጡ እቃዎች ላይ አነስተኛም ቢሆን ቅናሽ ያስከትላል ፡፡ እኛ ሀገር በሚገርም ሁኔታ ኢኮኖሚው በተለየ ሁኔታ ነው የሚሰራው እስከ አሁን ባለው አካሄድ የፖሊሲ ለውጡ የዋጋ መቀነስን አያመጣም ለነጋዴው ግን ወጪው ቀነሰለት በመሆኑ ተጨማሪ ትርፍ ማስገኘቱ የማይቀር ነው:: - እኛስ ባለችን አቅም ምን ማድረግ እንችላለን ፡- => ከገንዘብ አስቀማጮች አንጻር - ያው ግዜው አስቸጋሪ በመሆኑ ሁሉም ነገር ከእጅ ወደ አፍ ነው ፡፡ ነገር ግን በየትኛውም መልኩ ሊቀመጥ የሚችል ገንዘብ ከተገኘ ከአሁን በፊት እንዳለው ዝም ብሎ ማስቀመጡ አይመከርም ፡፡ አንደኛው አማራጭ የመንግስት ግምዣ ቤት ሰነድን(Treasury Bill) መግዛት ነው ፡፡ አሁን ብዙ የኢንቨስመንት ባንኮች ያሉ በመሆኑ ሰው ባለው አቅም ከ28 ቀን ጀምሮ እስከ አንድ አመት የሚሆናቸው የግምጃ ቤት ሰነዶችን መግዛት ይችላል ፡፡ የዚህ ትልቁ ጥቅም ምንም አይነት ግብር የሌለበት(Tax free ) መሆኑ ፡፡ - የአዲሱ የግብር ለውጥ በአስቀማጩ ላይ ያመጣው ጫና -በቀድሞው ህግ መሰረት ባንክ የተቀመጠ ገንዘብ የሚጣልበት ግብር 5% የነበረ ሲሆን አሁን ወደ 10% ከፍ ብሏል ፡፡ ገንዘብ ስናስቀምጥ ባንኮች ይከፍሉት የነበረው ወለድ 7% ነው አሁንም ያው ነው ፡፡ ይህ ማለት የህጉ ለውጡ ያመጣው ጫና ሙሉ ለሙሉ ያረፈው አስቀማጮች ላይ ነው ፡፡ ታዲያ አስቀማጩስ ለምን ዝም ይባላል - በብሄራዊ ባንክ መመሪያ DIRECTIVE NO.NBE/INT/13/2026 መሰረት ከአሁን በፊት ተቀምጦ የነበረው ዝቅተኛው የማስቀመጫ ወለድ ተነስቷል፡፡ ባንኮች በራሳቸው የፈለጉትን መጠን እንዲከፍሉ ፍቃድ አግኝተዋል ፡፡ ስለዚህ አሁን መደራደር ይቻላል፤ ከአሁን በፊትም በተወሰነ መልኩ መደራደር ይቻል ነበር፤ ግን የገንዘብ መጠኑ ከፍተኛ መሆን ይኖርበታል፡፡ - ስለዚህ ያለችን ብር ትንሽ ብትሆንም ከማስቀመጣችን በፊት መደራደር ይመከራል ፤ ገንዘብ አስቀምጥ ስትባል በስንት ወለድ? ማለት መልመድ ይኖርብናል፡፡ => ለባንክ ሰራተኞች - ባንኮች ለሰራተኞቻቸው የሚሰጡት የዝቅተኛ ወለድ(Discounted Interest rate) ላይ የገቢዎች ሚኒስቴር ግብር እየጣለ ነው ፡፡ ለዚህ ግብር መሰረቱ ደግሞ የ 15% NBE Policy Rate ነው፡፡ አሁን ይህ መጠን በ1% ከፍ ማለቱ የሚከፈለውንም ግብር በዚሁ ልክ ከፍ ያደርገዋል ፡፡ ይህ በአመት 12% ማለት ነው ስለዚህ ጫናው ቀላል አይሆንም ፡፡ ©yosef alemu @Lawyer_Getahun @ethiolawyer1 @ethiopianattorney

  • ✅መረጃ - የአዲስ አበባ ታክሲዎች ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት ክፍያ እንዲሰበስቡ ተወሰነ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የታክሲ አሽከርካሪዎች ከተወሰነው ታሪፍ በላይ እንዲሚያስከፍሉ ከማኅበረሰቡ የሚነሳውን ቅሬታ ለመፍታት ክፍያው ከመነሻው እንዲሰበሰብ የሚያስገድድ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋቱን አስታውቋል። አሽከርካሪዎች በታሪፍ መመሪያው መሠረት ብቻ ከመነሻው የትራንስፖርት ክፍያ እንዲሰበስቡ ለማስቻል ተቆጣጣሪዎች በመነሻ መጫኛ ቦታዎች ላይ ተመድበው ሥራ መጀመራቸውን የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራው ተናግረዋል። ይህ አሠራር በጉዞ ወቅት "ሒሳብ ጨምሩ" በሚል ከአሽከርካሪዎች የሚነሳውን አግባብነት የሌለው ጥያቄ ለመግታት የጎላ ፋይዳ እንደሚኖረው ታምኖበታል። ይሁን እንጂ አዲሱ አሠራር ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ አንዳንድ ተግዳሮቶች መፈጠራቸውን የቢሮው ኃላፊዎች ጠቁመዋል። በከተማዋ በሚገኙ መነሻዎች ላይ ክፍያውን አስቀድሞ በመሰብሰብ ሂደት የተወሰነ ጊዜ እየወሰደ መሆኑ በማኅበረሰቡ በኩል ቅሬታ መፍጠሩ ተገልጿል። በተመሳሳይ አንዳንድ አሽከርካሪዎች መንገድ ከጀመሩ በኋላ ታሪፍ የመጨመር አዝማሚያዎችን እያሳዩ መሆናቸውን ቢሮው አስታውቋል። ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ ማኅበረሰቡ የጉዳዩን ፋይዳ በመገንዘብ ተገቢውን ትብብር እንዲያደርግና ህገ-ወጥ አሽከርካሪዎችን በተመለከተ ጥቆማዎችን በመስጠት የዜግነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ አቶ ዳኛቸው አሳስበዋል። በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም ያለ ረዳት በሚጭኑ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ሲገለጽ መቆየቱ የሚታወስ ቢሆንም፤ ቢሮው በአሁኑ ወቅት ትኩረቱን አዲሱ የአሠራር ሥርዓት ላይ ማድረጉን አመልክቷል። ይሁን እንጂ የረዳት አጠቃቀምን በተመለከተ ግልጽና ወጥ የሆነ የአሠራር ሥርዓት እንደሚያስፈልግ አቶ ዳኛቸው ገልጸዋል። @lawyer_getahun @ethiolawyer1 @ethiopianattorney

  • ✅መረጃ በአዲስ አበባ በሚገኙ የአልጋ አገልግሎት በሚሰጡ የሆቴል ፔንሲዮን እና እንግዳ ማረፊያ ተቋማት ላይ አዲስ የ5 በመቶ ታክስ እንዲያስከፍሉ የሚያስገድድ ደንብ ወጣ። በወጣው አዲስ ደንብ ቁጥር 204/2018 መሠረት፣ በከተማዋ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ - ሆቴሎች፣ - ሪዞርቶች፣ - ሎጆች፣ - ፔንሲዮኖች እና - እንግዳ ማረፊያዎች ላይ የ5 በመቶ የመኝታ አገልግሎት ታክስ ተጥሏል። ይህ ታክስ የሚሰላው ተቋማቱ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት ከመኝታ አገልግሎት ብቻ ከሚያገኙት ጥቅል ገቢ ላይ እንደሆነ ተገልጿል። አዲሱ አሰራር የመኝታ ክፍል አገልግሎትን ብቻ የሚመለከት ሲሆን፣ እንደ ምግብና መጠጥ ያሉ ሌሎች መስተንግዶዎችን አያካትትም። በአዲስ ነጋሪ ጋዜጣ ላይ የወጣው መረጃ እንደሚያመላክተው፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የክፍል ብዛታቸውንና የዋጋ ዝርዝራቸውን ለገቢዎች መሥሪያ ቤት የማሳወቅ፣ በቅርንጫፍ ቢሮዎች ተመዝግበው ሕጋዊ ደረሰኝ የመቁረጥ እንዲሁም የተገልጋዮችን መረጃ የሚይዝ ራሱን የቻለ መዝገብ የማደራጀት ግዴታ ተጥሎባቸዋል። የሪፖርት አቀራረብን በተመለከተ የደረጃ «ሀ» ግብር ከፋዮች በየወሩ፣ የደረጃ «ለ» ግብር ከፋዮች ደግሞ በየሩብ ዓመቱ ሪፖርት እንዲያደርጉ ደንቡ ያዝዛል። የታክስ ክፍያውን በተባለው ጊዜ ገቢ የማያደርጉ ወይም የሐሰት መረጃ የሚያቀርቡ አካላት በወንጀል እንደሚጠየቁ የጠቀሰው መመሪያው፣ ክፍያ ያዘገዩ ተቋማት ግን የባንክ ወለድና ተጨማሪ የ15 በመቶ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አስታውቋል። © ahadu ሙሉ መመሪያውን ከተያያዘው ፋይል መመልከት ትችላላችሁ @Lawyer_Getahun @ethiolawyer1 t.me/ethiopianattorney

  • የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የወንጀል ሕግ ትርጉም ውሳኔዎች ስብስብ (በየጉዳዮች የተደራጀ ልዩ እትም) አትሞ አውጥቷል። ‎ ‎ይህንን ህትመት 4 ኪሎ በሚገኘው በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት እንዲሁም ልደታ ፍርድ ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ በሚገኘው የብርሃንና ሰላም ሽያጭ መደብር የሚያገኙ ሲሆን ሶፍት ኮፒውን እዚሁ አያይዘናል። ©የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 📞 0910551429 @lawyer_Getahun

  • ✅ለመረጃ በአዲስ አበባ የቤት ኪራይ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆኖ ተወሰነ ፤ የውል እድሳት ምዝገባም ከዛሬ ሐምሌ 1 ጀምሮ ይካሄዳል፡፡ ከዚህ ቀደም በወጣው የቤት ኪራይ ቁጥጥር አዋጅ መሠረት፣ ለ2019 በጀት ዓመት የሚተገበረው ፍትሐዊ የቤት ኪራይ ዓመታዊ ጭማሪ ጣሪያ 11.5% ሆኖ መጽደቁን የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ዛሬ ባወጣው መረጃ አስታውሷል። ይህንን ተከትሎ በመላው ከተማዋ የሚገኙ የግል መኖሪያ ቤቶች የአከራይ-ተከራይ አዲስ የውል እድሳት ምዝገባ ከዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት በይፋ መተግበር ይጀምራል ብሏል። የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ወልደጊዮርጊስ በጉዳዩ ዙሪያ ጥናቱ ይፋ በተደረገበት ወቅት በሰጡት ምላሽ በስራ ላይ ያለው ደምብ በየዓመቱ ጥናት እየተደረገ የዋጋ ማስተካከያ ተመን ማውጣት እንዲቻል ይፈቅዳል ብለዋል፡፡ ቤቶች የሚከራዩት ለገቢ ምንጭነት እንደመሆኑ ተከራዩ የኑሮ ጫና ውስጥ እንደሚያልፍ ሁሉ ለአከራዩም የገቢ ምንጩ፤ ለአንዳንዶችም መጦሪያቸው ነው፤  ለዚህም ነው እስከ 20 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ አከራዮች እንዳሉ በጥናታችን ብናገኝም የኑሮውን ሁኔታ አገናዝበን ሁለቱም የማይጎዱበት ነው በሚል ነው 11.5 እንዲሆን የወሰንነው የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።  ማን ምን ያህል ጨመረ የሚለውን ከወርሃዊ የኪራይ ክፍያችሁ አገኘዋለሁ የሚለው ቢሮው አሰራሬን ማዘመን ላይ እበረታለሁ ብሏል። ©sheger @Lawyer_Getahun @ethiolawyer1

  • 3 июл.888101

    ✅ የፌደራል ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት የሐምሌ ወር 2018 ዓ.ም የሀራጅ ሽያጭ ላይ የቀረቡ ንብረቶችን ማስታወቅያ ለምትፈልጉ በሙሉ ከተያያዘው ፋይል መመልከት ትችላላችሁ። 📞 0910551429 @Lawyer_Getahun