የመምህራን ገጽ (Teachers page)❤️
Статистикаትምህርት ነክ የሆኑ ወቅታዊ ፣ትክክለኛ እና አስተማማኝ መረጃ የሚያገኙበት ገጽ
- Последний пост
- 28 июл.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 803
- 1/48двое суток
- 2 066
- 1/72трое суток
- 2 228
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
Share Addis Ababa የትምህር ማሻሻያ ዩኒቨርሲቲ ምደባ.xlsx
ቢሮ ለ1884 መምህራን የማስተማር ስነ-ዘዴ /PGDT/ ስልጠና በክረምት መርሀ ግብር ለመስጠት የሚያስችል የጋራ ስራ ውል ስምምነት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ትምህርት ቋንቋዎች ጥናት ኮሌጅ ጋር ተፈራረመ፡፡ (ሀምሌ 10/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለ1884 መምህራን የPGDT/የማስተማር ስነ-ዘዴ/ ስልጠና በክረምት መርሀ ግብር ለመስጠት የሚያስችል የጋራ ስራ ውል ስምምነት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ትምህርት ቋንቋዎች ጥናት ኮሌጅ ጋር ተፈራርሟል፡፡ በፊርማ መርሀ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ትምህርት ቋንቋዎች ጥናት ኮሌጅ ጋር ያደረገው የጋራ ስራ ውል ስምምነት ለ1884 መምህራን በክረምት በርሀ ግብር የPGDT ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ስምምነቱ በከተማ አስተዳደሩ የሚሰጠውን ትምህርት ጥራት ለማረገገጥ እና የተማሪዎችን ውጤትና ስነ ምግባር ለማጎልበት ትልቅ ሚና እንዳለው የጠቀሱት ሀላፊው ስልጠናው ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ በሚያወጣው የስልጠና መስጫ መርሀ ግብር መሰረት ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ቢሮ ያመቻቸዉን ይህንን የ PGDT ስልጠና እድል መምህራን በመጠቀም ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ የሚናቸዉን ሊወጡ ይገባል ያሉት ሀላፊው ስምምነቱ በ2019 የትምህርት ዘመን በከተማ አስተዳደሩ ለሚሰጠው ትምህርት የቅድመ ዝግጅት ስራ አካል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ትምህርትና ቋንቋዎች ጥናት ኮሌጅ ዲን ዶ/ር የቆየሰው ደሴ በበኩላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ የሚሰጠዉን ትምህርት ስኬታማና ጥራቱ የተረጋገጠ እንዲሆን እየሰራቸዉ የሚገኙ ስራዎች አስደሳች መሆናቸውን ጠቅሰው በክረምት መርሀ ግብር ላይ የሚሰጠው የ PGDT ስልጠና ስኬታማ እንዲሆን በትኩረት የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc
без подписи
የክረምት ትምህርት የአዲስ አበባ መምህራን ዝርዝር User Name
без подписи
የክረምት ት/ት እድል በተመለከተ
без подписи
ትምህርት ሚኒስቴር በክረምት የመምህራን የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና አዲስ ማዕቀፍ አዘጋጅቷል። ማዕቀፉ መምህራን በክረምት ስልጠና ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ የሚሸጋገሩበት መሆኑ ተገልጿል። ሚኒስቴሩ በቀን 06/11/2018 ዓ.ም ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ፣ ከአጠቃላይ ትምህርት ሥርዓተ ትምህርት ለውጥ ጋር ተያይዞ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ በክረምት የመምህራን የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ማስገባት መቋረጡን አስታውሷል፡፡ ይሁን እንጂ በቀጣይ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት በተዘጋጀ የስልጠና ማዕቀፍ፣ በክረምት የመምህራን የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑን ገልጿል። በ2018 ዓ.ም የክረምት ስልጠናውን ለመስጠት ስምንት አሰልጣኝ ዩኒቨርሲቲዎች መመረጣቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል። ለክረምት ስልጠናው የተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች፦ 1. ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ 2. ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 3. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ 4. መቐለ ዩኒቨርሲቲ 5. ጅማ ዩኒቨርሲቲ 6. ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ 7. ጎንደር ዩኒቨርሲቲ 8. አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተቋማት እና የስልጠናው አሰጣጥ አግባብነት ከትምህርት ሚኒስቴር እስከሚገለጽ ድረስ ከላይ ከተገለፁት ዩኒቨርሲቲዎች በስተቀር በክረምት መምህራን የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና መስጠት የማይቻል መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳስቧል። ከ2011 ዓ.ም በፊት ስልጠና ጀምረው ያላጠናቀቁ መምህራን ከዚህ በፊት በተሰጠው ውሳኔ መሰረት እንዲያጠናቅቁ እንዲደረግ በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተላከው ደብዳቤ ይገልጻል።
መሠረት ሚድያ)- በመንግስት መሬት አቅራቢነት በተጀመረው የመምህራን የመኖሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት ላይ በቅርቡ ይፋ እጅግ ከፍተኛ እና የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ እየተደረገ መሆኑን ለሚድያችን እየደረሱ ያሉ መረጃዎች ያሳያሉ። ከእነዚህም ውስጥ አንዱ በሆነው በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) ስር በሚገኘው የመምህራን ማህበር የመኖሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት ላይ በቅርቡ ይፋ የተደረገው እጅግ ከፍተኛ እና የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ በአባላቱ መካከል ከፍተኛ ቅሬታንና ውጥረትን መፍጠሩ ተሰማ። የፕሮጀክቱ ተሳታፊ የሆኑ መምህራን ለመሠረት ሚድያ እንደገለጹት ቀደም ሲል ከተስማሙበት የዋጋ ተመን ውጭ በአሁኑ ወቅት ከ134% እስከ 238% የሚደርስ ያልተጠበቀ ጭማሪ ተጭኖባቸዋል።  ይህ ጉዳይ የመምህራኑን አቅም ያላገናዘበና የወቅቱን የገበያ ሁኔታ ሰበብ በማድረግ የተፈጠረ ህገ-ወጥ አሰራር ነው በሚል በፅኑ እየተኮነነ ይገኛል። ሰሞኑን በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ ውስጥ ከመምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት እና ከዩኒቨርሲቲው ተወካዮች ጋር በጉዳዩ ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ቢሆንም ምንም ዓይነት አዎንታዊ የለውጥ ውጤት ሳይገኝ መበተኑን የኮሚቴው አባላት ገልጸዋል።  በስብሰባው ላይ የቀረበው አዲስ የዋጋ ዝርዝር (Bill of Quantities) እንደሚያሳየው ሙሉ በሙሉ ያለቀለት (Full Finish) የአንድ ብሎክ ባለ 10 ፎቅ (G+10) ህንፃ ግንባታ በትንሹ 923,457,635 ብር የተመደበለት ሲሆን እንደ ኮንዶሚኒየም ፊኒሺንግ ያላለቀው ደግሞ ያለታክስ በትንሹ 498,868,530 ብር ሆኖ ቀርቧል። ይህ አዲስ ተመን መምህራን በህዳር ወር ላይ ከከፈሉት የ25 በመቶ ቅድመ ክፍያ አንጻር ሲሰላ በ3 እጥፍ ገደማ ጭማሪ ያሳየ ነው። የማህበሩ ኮሚቴ ተወካይ በስብሰባው ዙሪያ ሲናገሩ "በፊት 25% ክፈሉ ተብለን ተበድረን ስንከፍል ህዳር ላይ የነበረው ዋጋ አሁን በ3 እጥፍ ጨምሯል። 'ካልከፈላችሁ ግንባታው አይሰራም' የሚል አስገዳጅ አቅጣጫ ነው የተሰጠን። ነገር ግን እንደ ኮሚቴ ባደረግነው ውይይት መሠረት አንድም የማህበሩ አባል ያላመነበትን እና ያልተስማማበትን ሰነድ ላይ በጭራሽ እንደማንፈርም ተስማምተናል" ብለዋል። ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በተጨማሪ ጭማሪው በሌሎች ተቋማትም ይፋ እየተደረገ ነው።  ከጉዳዩን በተመለከተ ሌላኛው መረጃ አቅራቢ መምህር እንደገለጹት ግንባታው ገና ከመሬት ሳይነሳ እና ኮንትራክተሮቹ አፈር ከመቆፈር ውጭ ምንም ዓይነት መዋቅራዊ ስራ ሳይሰሩ "ብር ካልተጨመረልን አንሰራም" በሚል ስራ ማቆማቸውን ገልጸዋል። መምህሩ አክለውም"የመምህሩ ደሞዝ ምን ያህል አነስተኛ እንደሆነ እየታወቀ የተወሰኑ የመንግስት አካላት ከኮንትራክተሮቹ ጋር በመመሳጠር እኛን ወደ ከባድ ችግር ውስጥ ከትተውናል። የ25 በመቶ ቅድመ ክፍያውን ራሱ ከተለያዩ ቦታዎች ተበድረን ነው የከፈልነው፣ አሁን ግን ዋጋው በብዙ እጥፍ ጨምሯል እየተባለ ግራ ተጋብተናል" ሲሉ ተናግረዋል። በከፍተኛ ቁጭት ውስጥ የሚገኙ ሌላኛው መምህር የዋጋውን ዝርዝር በማነፃፀር እንዲህ ብለዋል: "ከ8 ወራት በፊት የአንድ ካሬ ሜትር የኮንስትራክሽን ዋጋ 35,000 ብር ነው ተብለን ነበር የቆጠብነው። አሁን ግን ያለምንም በቂ ምክንያት ዋጋውን ወደ 82,000 ብር በላይ አሳድገውታል። ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው መንግስት መሬቱን በነፃ እንደሰጠ የተነገረን ሲሆን ይህ አሁን የተጠየቅነው 82,000 ብር ለአንድ ካሬ ሜትር ግንባታ ብቻ የተሰላ መሆኑ ነው" ሲሉ ምሬታቸውን ገልጸዋል። የማህበሩ አመራሮች በሰጡት ምላሽ የተገነነውን የዋጋ ዝርዝር (BOQ) ለአባላቱ እንደሚልኩና አባላቱ በጥልቀት ተመልክተው የተደጋገሙ ወይም የተጋነኑ ክፍታቶች ካሉ መሠረታዊ የህንፃውን ጥራት ሳይነኩ ማስተካከያ (Recommendation) ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጸዋል። ከዚያ ባለፈ ግን ዋጋውን የመቀነስ አቅም እንደሌላቸውና ለቀጣይ ከበላይ አመራሮች ጋር የሚነጋገሩበት ጊዜ እንደሚመቻች አስታውቀዋል። ይሁን እንጂ መምህራኑ የወቅቱን የዋጋ ግሽበት ያላገናዘበና አግባብነት የሌለው የዋጋ ጭማሪ በመሆኑ መንግስት እና የሚመለከታቸው ከፍተኛ አካላት አስቸኳይ ጣልቃ ገብነት እንዲያደርጉና መፍትሄ እንዲሰጧቸው በፅኑ እየጠየቁ ይገኛሉ። | መሠረት ሚድያ |
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
የ2019 ዓ.ም የትምህርት ካላንደር
без подписи
የተከለሰ የትምህርት ካላንደር