- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 899
- 1/48двое суток
- 2 176
- 1/72трое суток
- 2 347
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
ለውድ አባላት በሙሉ፣ የማህበራችን የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ሐምሌ 04 ቀን 2018 ዓ.ም በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል። በዕለቱ ጥሪያችንን አክብራችሁ የተገኛችሁ የልደታ ክፍለ ከተማ ኅብረት ሥራ ማህበር ተወካዮች፣ የንብ ባንክ አመራሮች እና ሰራተኞች፣ እንዲሁም ውድ አባላት በሙሉ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን። በተለይም ይህ ስብሰባ እንዲሳካ ላደረጉልን የስብሰባ አዳራሽ አገልግሎት እና በእለቱ የሻይና ቡና ፕሮግራም ድጋፍ ላደረጉልን ለንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ በማህበሩ ስም ልዩ ምስጋና እናቀርባለን። በስብሰባው ላይ በተነሱት አጀንዳዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎ፦ 1. የ2016 ዓ.ም እና የ2017 ዓ.ም. የኦዲት ሪፖርት ፀድቋል። 2. የ2016 ዓ.ም እና የ2017 ዓ.ም የትርፍ ትርፍ ክፍፍል ተሰልቶ ወደ እጣ እንዲዞር ተወስኗል። 3. የ2018 ዓ.ም. የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቧል። 4. የ2019 ዓ.ም. እቅድ ፀድቋል። 5. የ2018 ዓ.ም. ዓመታዊ የኢንስፔክሽን ሪፖርት ቀርቧል። 6. የማህበሩ ቁጥጥር ኮሚቴ ዓመታዊ ሪፖርት ቀርቧል። 7. በመተዳደሪያ ደንባችን ላይ አነስተኛ የብድር መድህን ህይወት ሽፋን (የሞት) 1.2% ከተበዳሪው ላይ እንዲቆረጥ ተወስኗል። ይሁን እንጂ፣ የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲከሰቱ የመድህን ዋስትናው ተፈፃሚነት አይኖራቸውም፦ o ለሶስት ተከታታይ ወራት ክፍያ ሳይፈጸም ቢሞት (ወይም ሶስት ወራት ኃላፊነት የማይወጣ ከሆነ)፣ o አባሉ ስለመሞቱ በ15 ቀናት ውስጥ ወኪል ህጋዊ ማስረጃ ካላቀረበ። ማሳሰቢያ፡ ይህ መዋጮ ብድር ሲወስዱ እየተቆረጠ አባላት ከወሰዱት ብድር ጋር ተነጻጽሮ፣ የማህበሩ የመክፈል አቅም ታይቶ ለቀጣይ ጠቅላላ ጉባኤ የሚቀርብ ይሆናል፤ የአነስተኛ የብድር መድህን ህይወት ሽፋን(ሞት)ተግባራዊ የሚደረግበት ጊዜም በቀጣይ ውይይት የሚወሰን ይሆናል። 8. አባላት የሂሳብ ደብተር ለማስሞላት የሚያባክኑትን ጊዜ ለመቀነስ እና የማህበሩን ሶፍትዌር ስራ ለማቀላጠፍ፣ የየራሳችሁን መረጃ በድጋሚ በዚህ ሊንክ https://docs.google.com/forms/d/1-2SFqqxEC8sKCN4_OIQmxNBYRf4Zy94UMawnW9nmiBQ/preview ተጠቅማችሁ እንድትመዘገቡ በጥብቅ እናሳስባለን። አባል የሆናችሁበትን ቀን፣ ወር እና ዓመተ ምህረት የማታውቁ አባላት "Today" የሚለውን በመጠቀም መሙላት የምትችሉ ሲሆን፣ ማህበሩ ማስተካከያውን የሚያደርግ ይሆናል። 9. የማህበሩ መስራችና ስራ አስኪያጅ ለሆኑት አቶ ሲሳይ ሁንዴ ለ10 ወራት ተከፍሎ የሚያልቅ በወር 30 ብር (በድምሩ 300 ብር) መዋጮ ተደርጓል። ይህም ገንዘብ ጉባኤው ለቦርዱ በሰጠው ኃላፊነት መሰረት አጠቃላይ የአፈፃፀም ሪፖርቱ በቀጣይ ጉባኤ የሚቀርብ ይሆናል። 10. ለቀድሞ የቦርድ አባላት፣ ለሰራተኞች፣ ለት/ቤቶች፣ ለማህበራት እንዲሁም ለንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በእለቱ የሽልማትና የእውቅና መርሃ ግብር ተካሂዷል። በስብሰባ ላይ አለመገኘት የሚወሰኑ ቅጣቶች፦ · ሀ. ለመጀመሪያ ጊዜ ቀርቶ ሳይገኝ ሲቀር፡ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ይቀጣል። · ለ. ለሁለተኛ ጊዜ ቀርቶ ሳይገኝ ሲቀር፡ ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) ይቀጣል። (ይህ ደንብ ጥሪ ተደርጎላቸው ባልተገኙ አባላት ላይ ሁሉ ተፈፃሚ ይሆናል) ጠቅላላ ጉባኤ ሐምሌ 04/2018 ዓ.ም
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ለውድ አባላት በሙሉ https://docs.google.com/forms/d/1-2SFqqxEC8sKCN4_OIQmxNBYRf4Zy94UMawnW9nmiBQ/preview ተጠቅማችሁ እንድትመዘገቡ :: አባል የሆናችሁበትን ቀን ወር እና ዓመተ ምህረት የማታውቁ አባላት Today የሚለውን እንድትጠቀሙ እና ማህበሩ ማስተካከያ የሚሰራ ይሆናል::
ለውድ አባላት እንደሚታወቀው ሰኔ 20/2018 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ ስብስባ ለማካሄ መጠራቱ ይታወቃል:: ሆኖም ጥሪያችንን አክብራችሁ የተገኛችሁ አባላት ምስጋናችን የላቀ ሲሆን በዕለቱ ምእላተ ጉባዔው ስላልተሟላ ለሐምሌ 04/2018 ዓ.ም በድጋሚ አራት ኪሎ በሚገኘው ቱሪስት ሆቴል ጎን ወይም ብርሀንና ሠላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ህንፃ አዳራሽ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ የሚካሄድ ስለሆነ ውድ አባላት በሰዓቱ እንድትገኙ እያሳሰብን በማይገኝ አባል ላይ በማህበሩ ደንብ መሰረት ቅጣቱ ተፈፃሚ የሚደረግ ይሆናል:: የማህበሩ ቦርድ
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው ዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ! በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የጤና ይሁንላችሁ። ኢድ ሙባረክ! ዘውትር ይቆጥቡ /ለቁምነገር ተበደሩ /በጊዜው ይክፈሉ !
ለመላው እስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢድ አል አድሀ በዓል በሠላም አደረሳችሁ! የኢድ አል አድሀ በዓል ልዩ ብድር መበደር የምትፈልጉ 11/09/2018 ዓ. ም ጀምሮ እስከ 14/09/2018 ዓ.ም ድረስ በአካል በመምጣት መበደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን::
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ:: በዓሉ የሠላም የፍቅር እና የደስታ ይሁንላችሁ:: መልካም በዓል!
📢 ለውድ አባላት በሙሉ >> የ2018 ዓ.ም የፋሲካ ልዩ ብድር ነገ መጋቢት 25/2018 ዓ.ም የመጨረሻው ቀን መሆኑን እንገልፃለን። ስለሆነም ብድሩን ያልወሰዳቹና መውሰድ የምትፈልጉ መጥታችሁ መበደር የምትችሉ መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን:: >> ውድ አባላት መልዕክቱን ሼር እንድታደርጉልን የተለመደው ትብብራችሁን እንጠይቃለን::