Ethio Universities Digital Network-EUDN
Статистикаበዚህ ቻናል ሁሉንም ትምህርታዊ ጉዳዮች በአንድ ላይ ያገኛሉ ✅ከሁሉንም ዩኒቨርስቲዎች የተሰሙ አዳዲስ መረጃዎች ✅ከት/ሚኒስቴር ወቅታዊ መረጃዎች ✅የት/ት እድሎችን ✅ለ12ኞች እና ለአዲስ ግቢ ገቢ ተማሪዎች መረጃዎችን ✅Exit መረጃ ✅ለተመራቂያን እና ለሁሉም የሚወጡ የስራ ማስታወቂያዎችን ♦️ሌሎችንም ፈጣን እና ጠቃሚ ጉዳዮች 👉ለጥቆማ እና Promotion👇👇 @EthioTag_Bot
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 8
- Всего постов
- 138
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Образование (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 110
- 1/48двое суток
- 126
- 1/72трое суток
- 135
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
без подписи
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ተማሪዎች አፍሪካን ወክለው ለዓለም አቀፍ የምስለ-ችሎት ፍጻሜ አለፉ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በአህጉራዊው የዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ህግ እና የግልግል ዳኝነት (arbitration) የምስለ-ችሎት ውድድር (FDI Moot) የዞኑ አሸናፊ በመሆን አፍሪካን ወክለው ለዓለም አቀፉ ፍጻሜ ማለፋቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፉበት በዚህ ፈታኝ ውድድር ከናይጄሪያ፣ ከኬንያ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ 14 ቡድኖችን በመበለጥ ከሰብ-ሳሃራን አፍሪካ አንደኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቀዋል። በዚህ ውድድር ላይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ወክለው የተሳተፉት ፦ ➡ ባምላክስራ ፋሲል (የ3ኛ ዓመት የህግ ተማሪ) ➡ ቃልኪዳን ሰብስቤ (የ4ኛ ዓመት የህግ ተማሪ) ➡ ዲቦራ ታደሰ (የ4ኛ ዓመት የህግ ተማሪ) እና ➡ ናሆት ግርማ (የ5ኛ ዓመት የህግ ተማሪ) ናቸው። ለዚህ አህጉራዊ ውጤት ያበቃቸው ዋና ምክንያት ምንድን ነው ? " ለዚህ ውጤት ያበቃን ቀደም ሲል በቪስ ሙት (Vis Moot) የነበረን ልምድ ነው። ከቡድናችን አራት አባላት መካከል ሦስቱ በዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ውድድር ላይ ለአንድ አመት ተወዳድረዋል። ይህ ልምድ በጣም ጠቅሞናል። አሁን ላይ የተወዳደርንበት ጉዳይ ከአለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ህግ እና የግልግል ዳኝነት ጋር የተያያዙ ውስብስብ ጥያቄዎችን ያካተተ ነበር። ከዋና ዋናዎቹ የስነ-ስርዓት ክርክሮች መካከል ከሳሹ ቀደም ሲል አቤቱታውን ለሌላ አካል አቅርቦ ስለነበር አሁን እንዳይከለከል የሚለው እና የክስ ማገጃ ትእዛዝ መሰጠት አለበት ወይ ? የሚሉት ይገኙበታል። የፍሬ-ነገር ክርክሩ በበኩሉ ፍትሃዊ እና እኩል እንክብካቤ እንዲሁም ንብረት መውረስን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን አካቷል። በውድድሩ ወቅት የገጠመን ትልቁ ፈተና ከዳኞቹ ለሚቀርቡ ዝርዝር እና ያልተጠበቁ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ነው " ብለዋል። የተወዳዳሪዎቹ መሪ የሆኑትና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞው የህግ ተማሪ፣ የህግ ባለሙያ ቦርጋ ደለሳ፥ ተማሪዎቹ እስካሁን ያለምንም ድጋፍ ለዚህ ድል የበቁ ቢሆንም፣ በመጪው ኦክቶበር (October) ወር በቻይና በሚካሄደው የመጨረሻ ፍጻሜ ላይ ለመሳተፍ ከፍተኛ የገንዘብ እና የተቋማት ድጋፍ ይፈልጋሉ ብለዋል። በተለይም ፦ - ለዓለም አቀፍ ጉዞ፣ - ለእንግዳ ማረፊያ፣ - ለቪዛ፣ - ከምዝገባ ጋር የተያያዙ ወጪዎች እና ለዝግጅት ድጋፍ የሚያስፈልግ በመሆኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት (በተለይም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን) የሕግ እና የንግዱ ማኅበረሰብ፣ እንዲሁም ሌሎች ድርጅቶች ትብብር እንዲያደርጉላቸውና እውቅና እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል። ይህ እድል የነዚህ አራት ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን፣ ኢትዮጵያን እና የአፍሪካን የሕግ ትምህርት በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስተዋወቅና ለመወከል የሚሰጥ ትልቅ ዕድል መሆኑን ገልጸዋል። ተወዳዳሪዎቹን ማግኘት የምትፈልጉ፣ የቡድኑ መሪ የሆኑትን የህግ ባለሙያ ቦርጋ ደለሳን በስልክ ቁጥር +251925494142 ማግኘት ትችላላችሁ። Addis Ababa
без подписи
#AREB የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2019 የትምህርት ዘመን በክልሉ በሚገኙ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ለሚገቡ ተማሪዎች የምዝገባ ጥሪ አድርጓል፡፡ የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ አዳሪ ትምህርት ቤት - ደሴ፣ የክቡር ዶ/ር ሐዲስ አለማየሁ - ደብረማርቆስ፣ እንዲሁም አዲስ የተገነቡ የደብረ ታቦር እና የሰቆጣ አዳሪ ትምህርት ቤቶች አዲስ ተማሪዎችን ተቀብለው ለማስተማር ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በመሆኑም በ2018 ዓ.ም በክልሉ ከሚገኙ የመንግሥት እንዲሁም የግል ትምህርት ቤቶች ተምራችሁ፣ ክልላዊ ፈተና የወሰዳችሁና የተቀመጡ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተማሪዎች በትምህርት ቤቶቹ ምዝገባ እንድታደርጉ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ጥሪ አስተላልፏል፡፡ መሰፈርቶች ● የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና አማካይ ውጤት ለሴቶች 80% እና ለወንዶች 82% ● የ7ኛ እና የ8ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት አማካይ ውጤት ለሴቶች 83% እና ለወንዶች 85% የምዝገባ ጊዜ 👇 ከነሐሴ 06-15/2018 ዓ.ም የምዝገባ ቦታ 👇 በአማራ ክልል በሚገኙ በሁሉም የወረዳ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤቶች የመግቢያ ፈተና በዞን ዋና ከተሞች ነሐሴ 25/ 2018 ዓ.ም ይሰጣል ተብሏል፡፡ (ተጨማሪ መረጃ ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ፡፡) ለተጨማሪ መረጃ ✅Share Share🇪🇹 🛜JOIN👉ETHIO UNIVERSITIES DIGITAL NETWORK
የትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ የሚተገበሩ 11 አዳዲስ የሙያ ትምህርት ዓይነቶችን ይፋ አደረገ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ጋር በመተባበር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁለተኛው ዙር የሚተገበሩ 11 የሥራና ተግባር የሙያ ዓይነቶችን ይፋ በማድረግ፣ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እንዲደረግ መመሪያ አስተላለፈ። አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ «የሙያና ቴክኖሎጂ ትምህርት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ ከእድሜ ጋር በተመጣጠነ መልኩ ይሰጣል» በሚለው አቅጣጫ መሠረት፣ በ7ኛ እና 8ኛ ክፍል ራሱን ችሎ ተማሪዎች በቀጣይ የሚፈልጉትን ሙያ እንዲመርጡ እየተደረገ ይገኛል። በተጨማሪም በ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ከቀለም ትምህርት ጎን ለጎን ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በ12 የሙያ ዓይነቶች ትምህርት እየተሰጠ እንደሆነ ተገልጿል። ሚኒስቴሩ ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ለሚተገበሩት 11 ተጨማሪ የሙያ ዓይነቶች የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል መርሐ-ትምህርቶችን፣ እንዲሁም የ11ኛ ክፍል የተማሪ ሞጁሎችንና የመምህራን መመሪያዎችን አዘጋጅቶ ማጠናቀቁን አስታውቋል። ለዚሁ ትግበራ የክልልና የከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች፦ 👉ዝርዝር ዕቅድና በጀት በመያዝ የሙያ ዓይነቶችን በትምህርት ቤትና በተማሪዎች ደረጃ እንዲያስመርጡ፣ 👉የሙያ መምህራንን እንዲቀጥሩና እንዲያሰለጥኑ፣ 👉የመማሪያና ማስተማሪያ ግብዓቶችን እንዲያሟሉ፣ የትምህርት አመራሮችን በማሰልጠንና የሕዝብ ንቅናቄ በመፍጠር ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል። የአዲሶቹ 11 የሙያ ዓይነቶች ዝርዝር፦ 👉ብረታ ብረት ሥራ ቴክኖሎጂ 👉አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ 👉አልባሳት ቴክኖሎጂ 👉ሕንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ቧንቧ ሥራ 👉ሶፍትዌር ማበልጸግ 👉ሰብል አመራረት 👉ጤና ክብካቤ አገልግሎት 👉ሆቴል አገልግሎት 👉ፀጉር ሥራና ውበት አገልግሎት 👉ምግብ ዝግጅት ለተጨማሪ መረጃ ✅Share Share🇪🇹 🛜JOIN👉ETHIO UNIVERSITIES DIGITAL NETWORK
ምዝገባ ተጀምሯል; የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ0 አመት የሰልጣኝ ክፍት የሥራ ቦታዎች ማስታወቂያ REGISTRATION PLACES/ LOCATIONS: - ADAMA SCIENCE AND TECHNOLOGY UNIVERSITY, ADAMA ADDIS ABABA, ONLINE (APPLICATION LINK WILL BE ACTIVATED DURING APPLICATION PERIOD) AMBO UNIVERSITY, AMBO ARBAMINCH UNIVERSITY, ARBAMICH ASSOSA UNIVERSITY, ASSOSA BAHIR DAR UNIVERSITY, BAHIR DAR WOLLO UNIVERSITY, DESSIE DIRE DAWA UNIVERSITY, DIRE DAWA UNIVERSITY OF GONDAR, GONDAR HARAMAYA UNIVERSITY; HARAR CAMPUS, HARAR HAWASSA AIRPORT, HAWASSA JIGJIGA UNIVERSITY, JIGJIGA JIMMA UNIVERSITY, JIMMA MADDA WALABU UNIVERSITY, ROBE WOLLEGA UNIVERSITY, NEKEMETE SEMERA UNIVERSITY, SEMERA WOLKITE UNIVERSITY, WOLKITE BORENA UNIVERSITY, YABELLO NEGELLE BORENA HEALTH SCIENCE COLLEGE, NEGELLE Registration Date : AUGUST 10, 2026 – AUGUST 14, 2026 Closing Date : AUGUST 14, 2026 How to Apply https://elelanjobs.com/job/ethiopian-airlines-local-job-openings/ ለተጨማሪ መረጃ ✅Share Share🇪🇹 🛜JOIN👉ETHIO UNIVERSITIES DIGITAL NETWORK Website Link https://elelanjobs.com
ትምህርት መስከረም 5 ይጀመራል‼ የትምህርት ሚኒስቴር የ2019 ዓ.ም አጠቃላይ የትምህርት ዘመን ዓመታዊ ካላንደር እንደሚያሳየው መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ ትምህርት ይጀምራል። ለተጨማሪ መረጃ ✅Share Share🇪🇹 🛜JOIN👉ETHIO UNIVERSITIES DIGITAL NETWORK
🚨 ከስር #Mute የሚል ከሆነ ትክክል ላይ ናቹ ካልሆነ ግን ነክታቸ ቀይሩት ።
#AAU ለ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የተለያዩ የአካዳሚክ መረጃ የሚያገኙበት ፕሮግራም ከ ከነሐሴ 8 -16 2018 ይካሄዳል በመረጃ ሳምንት ውስጥ፣ የሚከተሉትን መረጃ ያገኛሉ • የመግቢያ መስፈርቶች • የማመልከቻ ሂደቶች • የመጀመሪያ ዲግሪ የመግቢያ ፈተና (UAT) • የስኮላርሺፕ አማራጮች (መንግስት፣ በግልና፣ ፕሬዝዳንታዊ) • ስለ ምደባ መረጃ ቦታ፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ ዋናው ጊቢ፤ ፎረም ሕንፃ ለተጨማሪ መረጃ ✅Share Share🇪🇹 🛜JOIN👉ETHIO UNIVERSITIES DIGITAL NETWORK
🎓 በቀጣይ ዓመት ዩኒቨርሲቲ ለመግባት እያሰባችሁ ነው? ዩኒቨርሲቲ ከመምረጣችሁ በፊት የ2026 የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎችን ደረጃ ይመልከቱ! 👇 1.Addis Ababa University 2.University of Gondar 3.Jimma University 4.Bahir Dar University 5.Mekelle University 6.Hawassa University 7.Haramaya University 8.ASTU 9.AASTU 10.Arba Minch University 11.Dire Dawa University 12.Jigjiga University 13.Debre Birhan University 14.Wolaita Sodo University 15.Debark University 16.Dilla University 17.Unity University 18.Wollo University 19.Debre Markos University 20.Ethiopian Civil Service University 21.Kotebe Education University 22.Mattu University 23.Arsi University 24.Madda Walabu University 25.Ambo University 26.Wachemo University 27.Aksum University 28.Wolkite University 29.Adigrat University 30.Woldia University 31.Assosa University 32.Wollega University 33.Samara University 34.Mizan-Tepi University 35.Bule Hora University 36.Debre Tabor University 37.Werabe University 38.Bonga University 39.Injibara University 40.Kebri Dehar University 41.Oda Bultum University 42.Oromia State University 43.Gambella University 44.Raya University 45.Rift Valley University 46.Selale University 47.Mekdela Amba University 48.Jinka University 49.Dembi Dolo University 50.Borena University ለተጨማሪ መረጃ ✅Share Share🇪🇹 🛜JOIN👉ETHIO UNIVERSITIES DIGITAL NETWORK
#AAU በ2019 የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል ማኅበረሰብ ትምህርት ቤት (AAU-MCS) ልጆቻችሁን ለማስተማር ያስመዘገባችሁ የተቋሙ ሠራተኞች #ያልሆናችሁ በሙሉ፦ 📆 የተማሪዎች የመግቢያ መለያ ፈተና ረቡዕ ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም 4:00 ሰዓት ይሰጣል። በመሆኑም ልጆቻችሁን በመያዝ ምዝገባ በተካሄደበት ቦታ (አምስት ኪሎ) 3:30 ሰዓት እንድትገኙ የተባለ ሲሆን፤ የመግቢያ ፈተና ያልወሰደ ተማሪን የማይቀበል መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። ለተጨማሪ መረጃ ✅Share Share🇪🇹 🛜JOIN👉ETHIO UNIVERSITIES DIGITAL NETWORK\
#AAU_Postgraduate_Application የGAT ውጤታችሁን ያያችሁ ተፈታኞች አሁን ላይ AAU ለድህረ ምረቃ ትምህርታችሁ በOnline ማመልከት ትችላላችሁ። ለማመልከት👇 https://admission.aau.edu.et/announcementforapply/graduate የማመልከቻ ጊዜው ከሀምሌ 23- ነሀሴ 12 ዓ.ም ብቻ ስለሆነ የሚጠየቁትን መረጃ በትክክል በማስገባት ማመልከት ትችላላችሁ። ለOnline ማመልከቻ የተጠቀማችሁትን መረጃ በHard Copy የGAT ውጤትን ጨምሮ ለሬጅስትራል ማስገባት ይጠበቅባችኋል ካልሆነ Approve አያደርጉላችሁም። ለተጨማሪ መረጃ ✅Share Share🇪🇹 🛜JOIN👉ETHIO UNIVERSITIES DIGITAL NETWORK
#NGAT_Updates የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ እስከ ረቡዕ ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም የተራዘመ ሲሆን፣ ተከታዮቹን መረጃዎች ያስተውሉ፦ ➻ የፈተና ጣቢያ ምርጫችሁን አሁን ላይ Update ማድረግ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል። ➻ መስማት ወይም ማየት የማትችሉ አመልካቾች ፕሮፋይል ገፃችሁን Refresh በማድረግ የተደራሽነት ሁኔታችሁን (Accessibility Status) Update ማድረግ ትችላላችሁ። ➻ ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ አመልካቾች አሁን ላይ የNGAT ምዝገባቸውን ማድረግ ይችላሉ። Non-Ethiopian applicants can now register for NGAT. 🔔 ለተመዝጋቢዎች Username፣ Password እና Entrance Ticket የምዝገባ ጊዜው ከተጠናቀቀ በኋላ እንደሚላክ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ✅Share Share🇪🇹 🛜JOIN👉ETHIO UNIVERSITIES DIGITAL NETWORK
በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች እና የሚያስተምሩ መምህራን ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ እንዲዘዋወሩ ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰማ። በትግራይ በሚገኙ አራት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ የተወሰኑ ተማሪዎች እና መምህራን በክልሉ ባለው የጸጥታ ስጋት ምክንያት ወደ ሌሎች የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲዛወሩ ጥያቄ እያቀረቡ እንደሚገኝ ተሰምቷል። በመቐለ፣ አክሱም፣ ዓዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች እና የሚያስተምሩ መምህራን ጥያቄያቸውን ለመንግሥት እያቀረቡ ነው። ተማሪዎች እና መምህራን በክልሉ በሚታየው የጸጥታ ስጋት ምክንያት የቅሬታ ጥያቄ እያስገቡ ሲሆን፤ እስካሁን ከትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠ የዝውውር ውሳኔም ሆነ የተገባ ቃል አለመኖሩን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ኅብረት ፕሬዝዳንት ሓየሎም ስዩም ገልፀዋል። ለተጨማሪ መረጃ ✅Share Share🇪🇹 🛜JOIN👉ETHIO UNIVERSITIES DIGITAL NETWORK
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አመልካቾችን በስፖንሰር አድራጊነት አወዳድሮ በሰልጣኝ የበረራ አስተናጋጅነት (Trainee Cabin Crew) የሥራ መደብ ላይ መቅጠር ይፈልጋል። ተፈላጊ መስፈርቶች ✅የትምህርት ደረጃ ፡ ቢያንስ የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና (EUEEC) ወስዶ/ዳ 200 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያለው/ላት። ➡️ዕድሜ ፡ ከ21 እስከ 30 ዓመት (ሁለቱንም ዕድሜዎች ያካተተ)። ➡️ቁመት ፡ ለሴቶች ፡ ቢያንስ 1.58 ሜትር እና የእጅ መድረሻ (Arm Reach) 212 ሳንቲሜትር። - ለወንዶች ፡ ቢያንስ 1.70 ሜትር። ➡️ክብደት ፡ ከቁመት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ። ➡️ የቋንቋ ችሎታ ፡ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታ ደረጃ III (Level III)፤ ከእንግሊዝኛ ውጪ ተጨማሪ የውጭ ወይም የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች እውቀት ማቅረብ ተጨማሪ አወንታዊ ነጥብ ያስገኛል። ✅የምዝገባ ቦታዎች / ማዕከላት ➡️አዳማ ፡ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ➡️አዲስ አበባ ፡ በኦንላይን (የማመልከቻ ሊንኩ በምዝገባው ወቅት የሚከፈት ይሆናል) ➡️አምቦ ፡ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ➡️አርባ ምንጭ ፡ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ➡️አሶሳ ፡ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ➡️ባሕር ዳር ፡ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ➡️ደሴ ፡ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ➡️ድሬዳዋ ፡ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ➡️ጎንደር ፡ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ➡️ሀረር ፡ ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ (ሀረር ካምፓስ) ➡️ሀዋሳ ፡ ሀዋሳ ኤርፖርት ➡️ጅግጅጋ ፡ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ➡️ ጅማ ፡ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ➡️ሮቤ ፡ መድወላቡ ዩኒቨርሲቲ ➡️ነቀምቴ ፡ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ➡️ሰመራ ፡ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ➡️ወልቂጤ ፡ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ➡️ያቤሎ ፡ ቦረና ዩኒቨርሲቲ ➡️ነገሌ ፡ ነገሌ ቦረና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ማሳሰቢያ 🟢ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ሙሉ በሙሉ ማሟላታችሁን አረጋግጡ። 🟡በምዝገባ ወቅት ዋናውን የትምህርት እና የሥራ ማስረጃዎችን ይዛችሁ መቅረብ ይኖርባቹሃል ፤ ይህም የሚከተሉትን ያካትታል፡ 🟠የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ካርድ እና የልደት ሰርተፊኬት 🔴የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት 🟤የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ (ፊት እና ጀርባ) 🔵ሀሰተኛ መረጃ አቅርቦ የተገኘ ማንኛውም አመልካች በማንኛውም የቅጥር ወይም የሥልጠና ሂደት ውስጥ ቢሆን ወዲያውኑ ከሂደቱ ወይም ከሥራው የሚሰናበት ይሆናል። ለተጨማሪ መረጃ ✅Share Share🇪🇹 🛜JOIN👉ETHIO UNIVERSITIES DIGITAL NETWORK
🚩Big Opportunity 🎴ETHIOPIAN AIRLINES GROUP🎴 POSITION _ ET SPONSORED TRAINEE CABIN CREW REQUIRED EDUCATIONAL QUALIFICATION: A MINIMUM OF ETHIOPIAN UNIVERSITY ENTRANCE EXAM CERTIFICATE (EUEEC) WITH A MINIMUM 200 RESULT. AGE LIMIT: 21-30 YEARS’ OLD INCLUSIVE. HEIGHT: A MINIMUM OF 1.58 METER AND AN ARM RICH OF 212 CM FOR FEMALE AND A MINIMUM OF 1.70 METER FOR MALE. WEIGHT: PROPORTIONAL TO HEIGHT ENGLISH LANGUAGE PROFICIENCY: LEVEL III AND KNOWLEDGE OF OTHER LANGUAGE OTHER THAN ENGLISH IS ADVANTAGEOUS. ▪️Find More Details here 💧💧💧💧💧 https://elelanajobs.com/job/ethiopian-airlines-july-29-26/?utm_source=telegram&utm_medium=mobile_app ▪️Deadline : August 10-14 , 2026
እዳ ያልከፈሉ እየተከሰሱ ነው‼️ በቴሌብር ዲጂታል ብድር ውዝፍ ዕዳ ላይ ህጋዊ እርምጃ እና ክስ መጀመሩ ተገለጸ‼️ ዳሸን ባንክ እና ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌብር መተግበሪያ አማካኝነት የወሰዱትን የዲጂታል ፋይናንሲንግ ብድር በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ያልከፈሉ ተበዳሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውን እና በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ክስ እየመሰረቱ እንደሚገኙ አስታወቁ። ባንኩ ባወጣው መግለጫ እንደገለጸው፣ ተበዳሪዎች ያለባቸውን ውዝፍ ዕዳ እንዲከፍሉ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም የተደረገውን የቅጣት ክፍያ ምሕረት ተጠቅመው ዕዳቸውን ያልከፈሉ ወገኖች ላይ የህግ አካሄድ መጀመሩን ገልጿል። በመግለጫው መሠረት፣ አስቀድሞ ለቀረበላቸው ጥሪ ምላሽ ያልሰጡ ተበዳሪዎች ላይ በፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶ ከዋናው ዕዳ በተጨማሪ ባንኩ ለክስ ያወጣቸውን ልዩ ልዩ ወጪዎች እንዲሸፍኑ ውሳኔ እየተሰጠ እንደሚገኝ ተጠቁሟል። ዳሸን ባንክ አክሲዮን ማህበር የህዝብ ገንዘብ ለማስመለስ የጀመረውን ህጋዊ እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመጠቆም፣ እስካሁን የክስ መጥሪያ ያልደረሳቸው ተበዳሪዎች ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ከመሄዱ በፊት እና ተጨማሪ አላስፈላጊ እንግልት እንዲሁም ወጪ ሳይደርስባቸው ያለባቸውን ዕዳ በአስቸኳይ እንዲከፍሉ ጥብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፏል። ለተጨማሪ መረጃ ✅Share Share🇪🇹 🛜JOIN👉ETHIO UNIVERSITIES DIGITAL NETWORK
ትምህርት ሚኒስቴር በማስተማር ሥራ ላይ ያሉ መምህራንን ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና ለመጀመር በርካታ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ገልጿል። በቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ጋር የተናበበ የሥልጠና ማዕቀፍ፣ ፕሮግራሙን ለመምራት የሚያስችሉ የትግበራ ሰነዶችን እና የሰልጣኝ መምህራንን ምልመላ፣ መረጣ እና ምደባ መከናወኑን አመልክቷል። ባለፉት አመታት በስልጠናው አሰጣጥ ጥራት ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የመምህራን የክረምት የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና በዚህ ክረምት ለማስጀመር 8 ዩኒቨርሲቲዎች ተለይተዋል። እነዚህም፦ - ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ - ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ - መቐለ ዩኒቨርሲቲ - ጅማ ዩኒቨርሲቲ - ሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ - ጎንደር ዩኒቨርሲቲ - አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሲሆኑ፣ በ2018 ዓ.ም. ክረምት 8,273 መምህራንን ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ወደ ስልጠና ለማስገባት ዝግጅት መጠናቀቁን ይፋ አድርጓል። የመግቢያ ምዘና ወስደው ያለፉና በየዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ ሰልጣኝ መምህራን፣ ምዝገባው ሐምሌ 24 እና 25/2018 ዓ.ም. የሚካሄድ መሆን ትምህርት ሚኒስቴር አመልክቷል። ሰልጣኞች በተጠቀሱት ቀናት በየተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች በመገኘት እንዲመዘገቡ አሳስቧል። ሰልጠኞች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ ለማወቅ ይህን ሊንክ https://shorturl.at/ZjN9e መጠቀም ይችላሉ ተብሏል። ለተጨማሪ መረጃ ✅Share Share🇪🇹 🛜JOIN👉ETHIO UNIVERSITIES DIGITAL NETWORK