Fuad Mohammed
Статистикаقناة لفوائد متنوعة (Barnootaafii muhaadaraa oromiffaa garaagaraa) Yaadaaf @FuadMohammed
- Последний пост
- 11 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- om
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 317
- 1/48двое суток
- 363
- 1/72трое суток
- 391
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ስለተናገርክ፣ስላስተማርክ ብቻ አንተ የተሻልክ ነህ ማለት አይቻልም !! በዚህ ዘመን መለኪያ እየሆነ ያለው ዝና፣ የ"ተከታይ" ብዛት እና የመሳሰለው ከንቱ ነገር ነው.... አፈር ይብላ ዝና ! ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ ሙ/ኑር https://t.me/MerkezulimamiAhmed
ምዝገባ ላይ ነን ! ከቃዒዳ ጀምሮ ነዘር ማስተካከል ድረስ ! አዲስ ሂፍዝን ጨምሮ ሙራጀዐ መመለስ ድረስ ! በ6ት ፈኖች ላይ ኪታቦች ይቀራሉ ! 0913291117 0969688568 የመርከዙ ቻናል t.me/MERKEZ_ABU_UBEYDAH
🎉 አስደሳች ዜና!! ♥️የኪታቡ ስም፡ اِنْتَبِهْ أَنْتَ مُرَاقَبْ!! (ኢንተቢህ አንተ ሙራቀብ) ✍️ የኪታቡ ፀሐፊ፡ አቡ ዐብዱረሕማን አኒስ ብኑ ሷሊሕ 🎙አቅራቢ ፡በኡስታዝ ዐብዱረዛቅ አል ባጂ 🗓 መቼ ይጀምራል? ነሐሴ 4 ፣ ሰኞ ⏰ የዘወትር ፕሮግራማችን ቀናት እና ሰዓት፡ ☑️ ቀናት፡ በየሳምንቱ ቅዳሜ እና ሰኞ ☑️ሰዓት፡ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ⚠️ሐቂቃ ይህ ኪታብ በተለይም በዚህ ዘመን በድብቅ ወንጀል ለተፈተነ፣ ስማርት ስልኮችና ኢንተርኔት ላመጡት የብቸኝነት ፈተና መፍትሔ የሚሰጥ፣ እንዲሁም ጌታችን አላህ ሁሌም እየተመለከተን መሆኑን በማስታወስ ልብን የሚያነቃቃ ድንቅ ኪታብ ነው! 🔴ትምህርቱ ቀጥታ ስርጭት የሚሰጥበት ቻናል፦🔗 ✈️⬜️ስለ ቀልባችን☑️ ➡️ Share: t.me/Sle_qelbachn1 😬የኪታቡን PDF ለማገኘት:t.me/Sle_qelbachn1/1963
ወደ ፊት ብቻ! ~ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሁሉም አይነት ሰው አለ። ሞቅ ያለ ተሳትፎ ካለን በተለያዩ አካላት እንገመታለን። እንገመገማለን። እንተመናለን። በአቋም የሚመስለን እንዳለ ሁሉ የሚቃረነንም ብዙ ነውና ዋጋችንና ቦታችን ከሰው ሰው ይለያያል። * ከፊሉ የምትፅፈው/ የምትናገረው ነገር አይጥመውም። ከፊሎቹ ጋር ደግሞ እውነታው ይለያል። * ከፊሉ ቀድሞ በጥላቻ ስለተሞላ የኔ የሚለው ሰው ቢናገረው የሚደግፈውን ብትናገር እንኳ ሰበብ ፈልጎ ያብጠለጥልሃል። * ከፊሉ ዘንድ ሚዛናዊ ነህ። ሌላው ዘንድ ደግሞ ፅንፈኛ፣ ፍርደ ገምድል ነህ። * ከፊሉ ዘንድ አስተዋይና በሳል ነህ። ሌላው ዘንድ የሃገርና የወቅት ተጨባጭ ያልገባህ ጥሬ ነህ። * ከፊሉ ዘንድ አዛኝ ነህ። ከፊሉ ዘንድ ጨካኝ ነህ። * ከፊሉ ዘንድ እየበሰልክ ነው። ሌላው ዘንድ እየባሰብህ ነው። * ከፊሉ ዘንድ ቡድንተኛ ነህ። ሌላው ዘንድ ውግንናህ ለሐቅ ብቻ ነው። የሚርቅህ ብቻ ሳይሆን የተሻለ የሚቀርብህ ራሱ የበለጠ ሊጠላህ እና ንግግርህንም ዝምታህንም ያላሰብከውን ትርጉም እየሰጠ ሊያጣጥልህ ይችላል። ቢሆንም ታገስ። ሞራልህ ሳይጎዳ ወደፊት ገስግስ። የተራራቁ አመልካከቶች በበዙበት፣ ከዒልምና ተርቢያ የራቀ ትውልድ እንደ አሸን በፈላበት፣ በሺርክና መልከ ብዙ ቢድዐዎች ላይ የተዘፈቀው ወገን በበዛበት፣ ይሄ ሁሉ ወፈ ሰማይ በነፃነት የሚናገርበት መድረክ አግኝቶ ከየትኛውም አካል ጉንተላ ሳያገኘኝ ሰላም እጓዛለሁ ማለት ዘበት ነው፣ አጉል ምኞት። ስለዚህ ደዕዋ ላይ ያለኸው ወገኔ ሆይ! በደዕዋህ ላይ ትችትና ዘለፋ አያስደንብርህ። ቲፎዞና ጭብጨባም አያቅልጥህ። ሰዎች የሚሰጡህ ደረጃም አይድነቅህ። ሁሉም አላፊ ነው። ይልቅ አላህን ብቻ አስብ። በኢኽላስ ተጓዝ። በኢኽላስ ለካ! በኢኽላስ ቁረጥ። ጫጫታ ሳይበግርህ ወደፊት ብቻ። እልህ እንዳይሾፍርህም ሚዛንህን ጠብቅ። ዝቅ ብለህ ጀምር። ወርደህ ስራ። ተግተህ ጣር። መስመር ይዘህ፣ አላህን እያሰብክ እስከተጓዝክ ድረስ መንናቅ አያሳምምህ። ዝናም አያንጠባርህ። በየትኛውም ሁኔታ ከደዕዋ እንዳትርቅ። እንዳትርረታ። * ያያያዝኩት ግጥም የኔ አይደለም። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
видео или голосовое, без подписи
ደርስ ~ * መንሀጁ ሳሊኪን * ክፍል:- 5️⃣3⃣ * የሚሰጥበት ቦታ፦ የሺ ደበሌ ከፍ ብሎ ሑዘይፋህ መስጂድ * የሚሰጥበት ጊዜ፦ ዘወትር እሁድ ረፋድ ላይ * የእለቱ ደርስ መነሻ፦ باب الخلع = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
ሳምንታዊ ደርስ በሑዘይፋ መስጂድ ~ ዘወትር እሁድ ከረፋዱ 4፡00 ጀምሮ። የሚሰጡት ደርሶች * من أصول عقيدة أهل السنة والجماعة * كن سلفيا على الجادة * منهج السالكين
⬇️#⃣የዛሬው ኹጥባ#⃣ ٣ صفر ١٤٤٨ July 17/2026 ርዕስ : أنفاس لا تعود ( الوقت ) የማይመለሱ ትንፋሾች(ጊዜ) መስጂድ : በዘይድ ኢብኑ ሳቢት መስጂድ አድራሻ : ሮም ሰፈር ቤተል ቪሌጅ ሪልስቴት ጊቢ አቅራቢ: أبو العباس https://t.me/Abulabas
እውን ሂንድ የሐምዛን ጉበት አኝካለችን? ~ ሂንድ ቢንቱ ዑትባህ የአቡ ሱፍያን ባለቤት፣ የሙዓዊየህ እናት ነች። ከመስለሟ በፊት የሐምዛን ጉበት አውጥታ አኝካለኝ በሚል ክስ ዛሬም ድረስ ትብጠለጠላለች። በሺዐዎች በተዘጋጀው አር-ሪሳላህ ፊልም ውስጥ ሂንድን እጅግ ጋጠ ወጥ አድርጎ የሚያሳይ በርከት ያለ ክፍል አለ። በርግጥ ይሄ ከሺዐ የማይጠበቅ አይደለም። ለአቡበክርና ለዑመር ያልተመለሱ ጠማሞች ለሂንድ ይመለሳሉ ተብሎ አይጠበቅም። የነብዩ ﷺ አጎት የሆኑት የአላህ አንበሳ ሐምዛ ብኑ ዐብዲል ሙጦሊብ ረዲየላሁ ዐንሁ የኡሑድ ጦርነት ጊዜ በሐበሻዊው ወሕሺይ መገ - ደላቸው የሚታወቅ ነው። ከዚያም ሆዳቸው ተቀዶ አካላቸው ተቆራርጦ ነውረኛ ተግባር ተፈፅሞባቸዋል። ታሪኩ እዚህ ድረስ ትክክለኛ መረጃ የመጣበት ነው። ከዚህ ውጭ ግን እንዲህ የሚል ዘገባ አለ። "ሂንድ ሆዱን ቀዳ ጉበቱን በማውጣት አኘከችው። ልትውጠው ግን አልቻለችም። የአላህ መልክተኛ ﷺ ሲያዩት 'ከእሱ በልታለት ይሆን?' ብለው ጠየቁ። 'አልበላችም' ሲሏቸው 'አላህ የሐምዛን አንድም ክፍል ወደ ጀሃነም እሳት እንዲገባ አይፈቅድም' አሉ።" [ሙስነድ አሕመድ፡ 4414] ይህንን ዘገባ መነሻ በማድረግ ሂንድን ዛሬም ድረስ ክፉኛ የሚያንቋሽሹ ሰዎች አሉ። ሺዐዎች እንኳ ከዚህም የከፋ ብዙ ነገር ስላላቸው ምንም ቢሉ አይደንቅም። የሚገርመው በነሱ ቅጥፈት ተመርዘው ዛሬም ሂንድን የሚኮንኑ ሰዎች ሁኔታ ነው። ይሄ አካሄድ ስሜትን በሸሪዐ ልጓም አለመቆጣጠር ነው። ሐምዛ ላይ የተፈፀመው ድርጊት እጅግ በጣም የሚያም መሆኑ ግልፅ ነው። ነገር ግን ለሐምዛ ያለን ቁጭትና መቆርቆር መነሻው ኢስላም ከሆነ ኢስላማዊ ህግጋትን ሰው እየመረጥን ልንጥስ አይገባም። በዚህ ክስ ሂንድን የሚያወግዝ አካል ቢያንስ ሁለት መሰረታዊ ነጥቦችን ጥሷል። #አንደኛው፦ ባልተጨበጠ ዘገባ ላይ ተመርኩዞ ነው ውግዘት ውስጥ የገባው። ታሪኩ የተላለፈበት ሰነድ ከ0ፋን፣ ከሐማድ፣ ከዐጧእ ብኑ ሳኢብ፣ ከሸዕቢይ፣ ከኢብኑ መስዑድ የሚል ነው። ደረጃው ለማስረጃ የሚበቃ ጥንካሬ የሌለው ደካማ ዘገባ ነው። እንዴት እንደሆነ እንመልከት፦ 1. ሸዕቢይ ከኢብኑ መስዑድ አልሰማም። አቡ ሓቲም፣ ዳረቁጥኒይ፣ ሓኪም እና ኢብኑ ሐጀር ይህንን አስረግጠው ተናግረዋል። [አልመራሲል፣ ኢብኑ አቢ ሓቲም ፡ ቁ. 591] [ጃሚዑ ተሕሲል ሊአሕካሚል መራሲል፣ አልዐላኢይ፡ 204] [መዕሪፈቱ ዑሉሚል ሐዲሥ፡ 111] [ተህዚቡ ተህዚብ: 7/419] 2. ዐጧእ ብኑ ሳኢብ ኢኽቲላጥ (የሒፍዝ መደባለቅ) የገጠመው ሰው ነው። ይህንን ኢብኑ መዒን፣ ቡኻሪ፣ ዒጅሊ፣ ኢብኑ ዐዲይ፣ ኢብኑ ቀጧን፣ ኢብኑ ከሢር፣ ኢብኑ ሐጀር ገልፀውታል። [አት-ታሪኹል ከቢር፡ 6/465] [አሥ-ሢቃት፣ ዒጅሊ፡ 332] [አልካሚል፡ 7/72] [ተቅሪቡ ተህዚብ፣ ኢብኑ ሐጀር፡ 1/391] [አድ-ዱዐፋኡል ከቢር፡ 3/398] [አልቢዳያ ወንኒሃያ፡ 5/430] [ተህዚቡ ተህዚብ: 7/207] ይሄም የዘገባውን ዋጋ ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ሌላ ድክመት ነው። የሚከተሉት ሙሐዲሦች ደግሞ ታሪኩ ደካማ እንደሆነ በቀጥታ የገለፁ ናቸው፦ 1ኛ፦ ኢብኑ ከሢር [አልቢዳያ ወንኒሃያ፡ 5/430] 2ኛ፦ አልሐይሠሚ 3ኛ፦ አልአልባኒይ [ፊቅሁ ሲራ፡ 279-280] ታሪኩን ሶሒሕ ወይም ሐሰን በማለት ዋጋ ለመስጠት በሞከሩት አሕመድ ሻኪርና አርነኡጥ ላይ ዘለግ ያለ አጥጋቢ ምላሽ የተሰጠበትን ትንታኔ መመልከት የፈለገ إزاحة الغمة في بيان ضعف قصة أكل هند من كبد حمزة የተሰኘውን ጥናት መመልከት ይችላል። #ሁለተኛው መሰረታዊ የዘገባው ችግር፦ ከሰነድ ባለፈ መልእክቱ ራሱ ፍፁም የተሳሳተ መሆኑ ነው። ዘገባው ላይ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል የሚል አለበት:- “አላህ የሐምዛን አንድም ክፍል ወደ ጀሃነም እሳት እንዲገባ አይፈቅድም።” ይሄ ማለት ሂንድ የእሳት ነች ማለት ነው። ይሄ የተሳሳተ ነው። ሶሒሕ አይደለም እንጂ ሂንድ ድርጊቱን መፈፀሟ ቢረጋገጥ እንኳ ይሄ ተግባር ከመስለሟ በፊት የተፈፀመ ነው። መስለሟ በአስተማማኝ ሰነድ ተረጋግጧል። [ቡኻሪ፡ 3825] [ሙስሊም፡ 1714] በተለያዩ ሐዲሦች እንደተረጋገጠው ኢስላም የቀደመን ወንጀል ሁሉ ያብሳል። ይህ ከሆነ ድርጊቱን ለመፈጸሟ በቂ መረጃ የለም እንጂ ቢኖርስ ከመስለሟ በፊት በነበረ ጉዳይ እንዴት የእሳት ትሆናለች? ይሄ ከመሰረታዊ የኢስላም አስተምህሮት ጋር የሚቃረን ነው። በርካታ የምንወዳቸው ሶሐቦችኮ ከመስለማቸው በፊት ሺርክን ጨምሮ ብዙ ከባባድ ወንጀሎችን ፈፅመዋል። ልክ እነዚያ ከመስለማቸው በፊት በተፈፀመ ወንጀል እንደማይወቀሱት ሂንድም ከመስለሟ በፊት በተፈፀመ ድርጊት አትወቀስም። ልክ የሐምዛ ገዳይ የሆነውን ወሕሺይን ከመስለሙ በፊት በፈፀመው ድርጊት ከሰለመ በኋላ እንደማንወቅሰው ማለት ነው። ጌታችን እንዲህ ማለቱ ይታወስ፦ {قُلۡ یَـٰعِبَادِیَ ٱلَّذِینَ أَسۡرَفُوا۟ عَلَىٰۤ أَنفُسِهِمۡ لَا تَقۡنَطُوا۟ مِن رَّحۡمَةِ ٱللَّهِۚ إِنَّ ٱللَّهَ یَغۡفِرُ ٱلذُّنُوبَ جَمِیعًاۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلۡغَفُورُ ٱلرَّحِیمُ} "በላቸው 'እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡" [አዝ-ዙመር: 53] ይህንን ከመሰሉ ሰፋፊ የአላህ የእዝነት አዋጆች ውስጥ ሂንድን ለይተን ልናወጣ ነውን? ለራሳችን ልንፈራ ይገባል። በሌላም ቦታ ጌታችን አላህ ሺርክ የሚፈፅሙ፣ ነፍስ የሚያጠፉ፣ ዝሙት የሚፈፅሙ ሰዎች አሳማሚ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው በዛተበት ላይ ተውበት የሚያደርጉትን ግን እንዲህ ሲል እንደሚምራቸው ገልጿል:- {إِلَّا مَن تَابَ وَءَامَنَ وَعَمِلَ عَمَلࣰا صَـٰلِحࣰا فَأُو۟لَـٰۤىِٕكَ یُبَدِّلُ ٱللَّهُ سَیِّـَٔاتِهِمۡ حَسَنَـٰتࣲۗ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورࣰا رَّحِیمࣰا} "ተፀፅቶ የተመለሰና ያመነ መልካምንም ሥራ የሠራ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡ እነዚያም አላህ መጥፎ ሥራዎቻቸውን በመልካም ሥራዎች ይለውጣል፡፡ አላህም እጅግ መሓሪ አዛኝ ነው።" [አል-ፉርቃን፡ 70] ታዲያ ሂንድን ከሰለመችም በኋላ ከነዚህ የአላህ የተስፋ ቃል ውጭ ልናደርጋት ይቻላል ወይ? አደብ ሊኖረን ይገባል። ሁሉንም ሶሐቦች አላህ መልካም ስራዎቻቸውን ይውደድላቸው። ከመስለሟ በፊት በተፈጠረ ክስተት ማብጠልጠል ለምን አስፈለገ? ምክንያቱ ወዲህ ነው። እነዚህ ባ -ለጌዎች የአቡ ሱፍያንንም፣ የሂንድንም መስለም አይቀበሉም። ሺዐዎች እና እነሱን በጥመት የተከተሉ እንደ ሰይድ ቁጥብ ያሉ የኢኽዋን አፈንጋጮች ዘንድ የበኑ ኡመያ ቤተሰቦች ኢስላምንና የነብዩን ﷺ ቤተሰቦች ለመበቀል ነው የሰለሙ የመሰሉት እንጂ ኢማን ወደ ልባቸው አልገባም። በዚህ ደረጃ የነብዩን ﷺ ሶሐቦች ከእስልምና እያስወጡ እያከ^ ፈሩ ለዘብተኛና ሚዛናዊ መስለው ሲተውኑ ስቅም አይላቸውም።
видео или голосовое, без подписи
የዛሬው ኹጥባ ٢٥ محرم-١٤٤٨ / July 10/2026 ርዕስ : (غض البصر عن محارم الله) ( ዓይንን መስበር ) መስጂድ : በዘይድ ኢብኑ ሳቢት መስጂድ አድራሻ : ሮም ሰፈር ቤተል ቪሌጅ ሪልስቴት ጊቢ አቅራቢ: أبو العباس https://t.me/Abulabas
اَلسَـــــــــــــــلاّمُ عَلَيـَـــــــــــكُم وَرَحَمَتُــــــــــــــهِ اللَّٰه وَبَرَكَــــٰـــــــــــــــــاتَه 🛍🛍🛍🛍🛍🛍🛍🛍🛍🛍🛍🛍 ℛℰᏇⅅᎯ- 𝑙𝑠𝑙𝑎𝑚𝑖𝑐-ℎ𝑖𝑗𝑎𝑏_(UAE🇦🇪) 🛍🛍🛍🛍🛍🛍🛍🛍🛍🛍🛍🛍 ➲ዱባይ_ኢሜሪት_ሁሉም_ቦታ 🇦🇪 ➺ውብ እና ጥራታቸውን የጠበቁ ሸሪዓዊ ልብሶች ጥራት መለያችን ነው ከእናንተ ሚጠበቀው ትዕዛዛችሁን ማቀበል ብቻ ነው እኛም በአሏህ ሱበሓነሁ-ወተዓላ ፈቃድና እገዛ ትዕዛዛችሁን ሰርተን ያላችሁበት እናደርሳለን ➴ባሉበት ሆነው ቢያዙን ትዛዛቹሁንና ፈላጉታቹሁን አሟልተን እቤትው ድረስ እናቀረባለኝ ➲የተለያዩትን ኢስላማዊ አልባሳትን በፈለጉት ከለርና ዲዛይን ቢያዙ ፈላጎቶን አሞላትን ከጥራትጋር እናቀረባለን ➺ ጅልባብ ፣አባያ ራስ እና ኒቃብ ፣ገሽዋ፣ሂማር በፈለጋቹት ከለርና ዲዛይን እናሰራለን ➻ኢስላሚክ ጅልባብ ➻ሰለፊያ አባያ፣ጓንት፣ካልሲ ➺ሺቲ ፣ድርያ ➻የልጆች አልባሳት ጫማዎች ➺ኪታቦች አማርኛ መፃፎች ➺መጋረጃ፣አልጋ ልብስ ➺ቀሚሶች፣ሽፎን፣ጫማዎች ➺ባህላዊ አልባሳቶች ➺ ➺ሽቶ የሴቶች ውበት መጠበቂያዎች ➲ ዱባይ_ኢሜሪት_ሁሉም_ቦታ ባሉበት ሆነው ቢያዙን ትዛዛቹሁንና ፈላጉታቹሁን አሟልተን እቤትው ድረስ እናቀረባለን! ለማዘዝ ለፈጣን መስተንግዶ🛍 WhatsApp .. አናግሩኝ Call ➺➺ +971589201725 ➺➺+971505893702 🛍🛍🛍🛍ጥራት ያለው ኢስላማዊ አለባበሶችን ለሚፈልጉ እህቶቼ ተደራሽነት እንዲኖረው ሼር አድርጉ ባረከላህ ፊኩም። እንዲሁም ቴሌ ግራም ጉሩፕ ላይ በመግባት ጓደኞቻቹን አድ አድ አድ አድርጉ የልብስ ምርጫዎችን ለማግኘት ጉሩፑን ተቀላቀሉ ASALAAMU ALAYIKUM WARAHAMATULLAAHI WABARAKAATUH ➴ Kabajamtoota maamiltootaa keenyaa waan barbaaddan ajajaan isin biraan geenya Marree meshaalee isiin biraan genyuu kanneen akka 👇👇👇👇👇👇👇 ➲Jilbaabaa fi niqaabaa ➲ Kitaab📚 fi Qur'aana ➲ Uffata adda addaa 👇👇👇👇👇👇👇 ➲ Gara UAE 🇦🇪 🚙tti kaan dhiheessinu kanneen akkaa👇👇 👉 Kitaaba fi Qur'aana 👉 Jilbaabaa fi niqaabaa 👉 Abayaa 👉 Uffata adda addaa👗🥿👝👛 ➠Magaalota Itti geessinu ➧Ajmaan ➧Abu Daabii ➧ Raasil Khaayimaa ➧Dubaayi fi magaalota biroottillee nii dhiheessina ➠ Ajajuuf,liinkii 👇👇 fayyadamaa kana irratti nii haasofsiisanaa (@Rewda_umu_nuh) ➺+971589201725 ➺+971505893702 ➲Gree keenyatti makamuudhaan wantoota barbaaddan ilaaluu fi filachuu fi ajajuu ni dandeessu ➴➴➴➴🌷🛍🌷 https://t.me/Rewda_online_Shopping
የዛሬው ኹጥባ ١٨ محرم / July 3/2026 ርዕስ : إتباع منهج السلف الصالح ( የ መልካም ቀደምቶችን ጎዳና መከተል ) መስጂድ : በዘይድ ኢብኑ ሳቢት መስጂድ አድራሻ : ሮም ሰፈር ቤተል ቪሌጅ ሪልስቴት ጊቢ አቅራቢ: أبو العباس https://t.me/Abulabas
https://youtu.be/PI0OY5xf-i8?si=bpg7rG_tbNh-fzqY
ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 20/2018 የ አል አርበዑን ፊ ሂቁቂ ረቢል ዓለሚን ደርስ ይኖራል፣ ኢንሻአላህ። * ቦታ፦ ዘይድ ኢብኑ ሳቢት መስጂድ ( ሮም ሰፈር ቤተል ቪሌጅ ሪልስቴት ጊቢ ውስጥ ) * ጊዜ፦ ዘወትር ረቡዕና ቅዳሜ ከመግሪብ እስከ ዒሻ * ኪታቡን በዚህ ሊንክ pdf ፋይል ታገኛላችሁ:- https://t.me/merkezabumussa1
የደዕዋ ማስታወቂያ ~ የፊታችን እሁድ ሰኔ 21/2018 በሑዘይፋ መስጂድ የደዕዋ ፕሮግራም ስለሚኖር ሁላችሁም ተጋብዛችኋል። ጊዜ፦ ከረፋዱ 3፡30 ጀምሮ * ኢብኑ ሙነወር፣ * አቡል 0ባስ፣ * ሙሐመድ ሱልጧን እና * ሳዳት ከማል ቦታው ከየሺ ደበሌ ከፍ ብሎ
📢 አስደሳች ዜና ለጠቅላላው የሙስሊሙ ማህበረሰብ! ኢኽላስ የቁርአን እና የተርቢያ ማእከል የዘንድሮውን የክረምት ወቅት አስመልክቶ ለልጆች፣ ለወጣቶች እና ለወላጆች በሙሉ የሚሆን "ልዩ የክረምት ኮርስ" ማዘጋጀቱን በታላቅ ደስታ ይገልጻል። የቁርአን ትምህርት እና ተርቢያን በአዲስ መልክ! በኡስታዝ አብዱረዛቅ (አል-ባጂ) ልዩ ክትትል እና አስተምህሮ፣ ልጆቻችሁን በቁርአን እና በስነ-ምግባር ለማነጽ ዝግጅታችንን አጠናቀን መዝገባ ላይ እንገኛለን። የምንሰጣቸው ትምህርቶች፦ ↪️ቁርአን 1⃣ሂፍዝ (አዲስ እና ሙራጃዕ) 2⃣ቁርአን ነዟር (በተጅዊድ) 3⃣ቃዒደቱ ኑራኒያ (ለጀማሪዎች) ↪️የኪታብ ትምህርቶች 1⃣ ዓቂዳ (የእምነት መሰረቶች) 2⃣አዳብ (ኢስላማዊ ስነ-ምግባር) 3⃣ፊቅህ (የኢባዳ ህግጋት) 4⃣ሲራ (የነብዩ ﷺ የህይወት ታሪክ) 5⃣ተጅዊድ (የቁርአን አነባበብ ህግጋት) የሚተሀፈዙ መትኖች ይኖራሉ የመርከዙ ፕሮግራሞች: ለትልልቆች (ሁለቱም ጾታ) 1⃣ ሙሉ ቀን በተመላላሽ 2⃣ከፈጅር በኃላ እስከ ጠዋት ሁለት ሰዐት 3⃣.ከ 2 ሰዐት ጠዋት እስከ ዙሁር 4⃣ ከዐሶር - መግሪብ ለልጆች 1⃣ ቀኑን ሙሉ በተመላላሽ የሚኖረን ቦታ የተገደበ ስለሆነ ቦታው ሳይሞላቦት ፈጥነው በመምጣት ተመዝግበው ቦታዎን ያስይዙ። 📍አድራሻ:[ ቦሌ ሚካኤል ከ እግረኛ ድልድይ ወደ ውስጥ 50 ሜትር ትንሽ ገባ ብሎ ። 📞 ስልክ፡ [ 0911119260 ] [ 0973849898 ] [ 0919829850 ] ሌላው ልዩ ጥሪ ለሀይስኩል እና ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የዘንድሮውን የክረምት ወቅት አስመልክተን፣ ለኤለመንታሪ፣ ለሀይስኩል እና ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአይነቱ ልዩ የሆነ "የክረምት ኮርስ" አዘጋጅተንላችኋል መድረሳችን በመምጣት ይታደሙ
видео или голосовое, без подписи
ኸጥባ 02 ርዕሰ = ኢስላም ምድርን ይቀድሳል አቅራቢ = አብዱልናስር መኑር አል-ጃቢሪይ https://t.me/twhidsunabegegnea
🎙 [ كلمة الشيخ عبدالعزيز بن يحيى البرعي ] = የቴሌግራም ቻናል t.me/AbulbukhariSeid