- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 10
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 127
- 1/48двое суток
- 145
- 1/72трое суток
- 156
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
📅 ዛሬ ነሐሴ 8 ቀን 2018 📖 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል ዘሌ 23:33-44
🎧 የእሁድ ስብከተ ወንጌል ━━━━━━━━━━━━━━━ "ጌታ ሆይ ጸሎት አስተምረን!" ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያቱ ባስተማረው ጸሎት ላይ ተመሥርቶ በጀመርነው «ጸሎት» የተሰኘ ተከታታይ ትምህርት ውስጥ ባለፉት ሁለት ተከታታይ ሳምንታት የተላለፉት ትምህርቶች የድምጽ ቅጂ ከላይ ተያይዟል👆👆 በማስተዋል እንድታደምጡ ቤተ-ክርስቲያን ዐደራ ትላለች። እንዲሁም በተማርነው መሠረት የፊታችን እሁድ በሚኖረን ትምህርት አገልጋዩ ቃሉን በሚገባ ይናገር ዘንድ አጥብቀን እንጸልይለት!
без подписи
без подписи
📅 ዛሬ ነሐሴ 7 ቀን 2018 📖 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል ዘሌ 23:15-32
🎤🎤 የሀዘን ማስታወቂያ የእህታችን ደስታ ቀነኒ ልጅ በረከት መርጊያ በደረሰበት ድንገተኛ አደጋ አርፏል። የቀብር ስርዓቱ ዛሬ ነሐሴ 6/2018 ዓ.ም. ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን ስለሚደረግ ሁላችንም ተገኝተን ቤተሰቡን እንድናፅናና ቤተክርስቲያን አደራ እንላለን። ቤታቸው ማሞ ሰፈር ፓሊስ ጣቢያው አካባቢ ነው።
የጾምና ጸሎት ፕሮግራም ማስታወቂያ ለቤተክርስቲያናችን አባላትና ምዕመናን በሙሉ! የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና ፍቅር ከሁላችሁ ጋር ይሁን። ቤተክርስቲያናችን በየዓመቱ የምታዘጋጀው ዓመታዊየጾምና ጸሎት ፕሮግራም በቅርቡ ይካሄዳል። ከዚህ ቀደም በነበረው ማስታወቂያ ላይ የቀን ስህተት የነበረ በመሆኑ፣ የመጨረሻውና የተወሰነው ትክክለኛው የፕሮግራማችን ቀን ከነሐሴ 30 ቅዳሜ እስከ ጳጉሜ 4 ረቡዕ መሆኑን እንገልጻለን። ይህ የጾምና ጸሎት ጊዜ እጅግ ልዩና ጠንካራ የመንፈስ ቅዱስ ባርኮት የሚገለጥበት እንደሚሆን እናምናለን። በእነዚህ ቀናት፦ 👉 ስለ ቤተክርስቲያናችን፣ 👉 ስለ ወንጌል ሚሽን፣ 👉 ስለ ውድ ሀገራችን፣ 👉 ስለ ግለሰቦች ሕይወት፣ ጤና፣ ሥራና የኑሮ ሁኔታ አጥብቀን ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን። ስለሆነም፡- እቅድዎን ያስተካክሉ፡ ማንኛውም የቤተክርስቲያናችን አባልና ምዕመናን ከወዲሁ ፕሮግራማችሁን በመመልከትና የሥራ ፈቃድ በማውጣት ራሳችሁን እንድታዘጋጁ። ለወጣቶች፡ በተለይም ወጣቶች ከዚህ ቀደም ከነበረው በተሻለና በላቀ ተነሳሽነት ራሳችሁን መንፈሳዊና አካላዊ ዝግጅት እንድታደርጉ። እንዳይቀሩ፡ ማንም አባል ከዚህ በረከት እንዳይጎድልና እንዳይቀር ቤተክርስቲያን አጥብቃ አደራ ትላችኋለች። በጸሎት ተነቃቅተንና ተዘጋጅተን የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ ለመለማመድ በአንድነት እንገናኝ! እግዚአብሔርን ይባርካችሁ!
📅 ዛሬ ነሐሴ 6 ቀን 2018 📖 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል ዘሌ 23:1-14
📅 ዛሬ ነሐሴ 5 ቀን 2018 📖 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል ዘሌ 22:17-31
ነገር ግን መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና። ዕብ 13÷16 ውድ የጌታ ቤተሰቦችና የቤተክርስቲያናችን አባላት፤ በቤተክርስቲያናችን ስር በሚካሄደው የወላጅ አጥ ሕፃናት ድጋፍና አገልግሎት ውስጥ እስከዛሬ ድረስ በፍቅርና በቅንነት እየተሳተፋችሁ፣ በቋሚነት ገንዘባችሁን በመለገስ በርካታ ሕጻናትን እና ቤተሰቦችን ለደገፋችሁ ሁሉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን። ይህንን መልካም ሥራ እያደረጋችሁ ስላላችሁ እግዚአብሔር አምላክ አገልግሎታችሁንና ሕይወታችሁን አብዝቶ ይባርክ! ነገር ግን አሁንም ቢሆን የብዙዎች ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው፣ የኛን እርዳታ የሚጠብቁ በርካታ ሕፃናትና ቤተሰቦች አሉ። የእናንተ ትንሽ አስተዋጽኦ ለነሱ ትልቅ ተስፋና ሕይወት ነውና ይህንን መልካም ሥራ ሳታቋርጡ አብራችሁን እንድትቀጥሉ በፍቅር እናሳስባችኋለን። የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ፦ የባንክ ስም፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) የሂሳብ ስም፦ የኢትዮጵያ ብርሃነ ወንጌል መጥምቃውያን ቤተክርስቲያን ጎፋ ማዞሪያ (Beethi Bireha Wongel Bapti CH Go Mz) የሂሳብ ቁጥር፦1000601999513 በጥሬ ገንዘብ ገቢ ለማድረግ፦ ለእህታችን ይርገድ ተመስገን ( 0911860393) መስጠት ትችላላችሁ። እጃችንን ዘርግተን የነዚህን ወገኖቻችንን ሕይወት በጋራ እንለውጥ! ጌታ አብዝቶ ይባርካችሁ!
📅 ዛሬ ነሐሴ 4 ቀን 2018 📖 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል ዘሌ 22:1-16
📅 ዛሬ ነሐሴ 3 ቀን 2018 📖 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል ዘሌ 21:1-24
📜 የስልጠና ማስታወቂያ ጥሪ "እግዚአብሔር ይባርከናል፥ የምድርም ዳርቻ ሁሉ ይፈሩታል።"— መዝሙረ ዳዊት 67:7 📢 ለታላቁ የሚሽን ጉዞ (Mission Trip) የሁለተኛው ዙር የማነቃቂያ እና የሥልጠና ፕሮግራም ጥሪ! ሰላም ለእናንተ ይሁን የተወደዳችሁ የቤተክርስቲያናችን አባላት በሙሉ! ከነሐሴ 18 እስከ 23 የሚደረገውን ታላቅ የሚሽን ጉዞ (Mission Trip) አስመልክቶ በሐምሌ 18 የተጀመረው የወንጌል ማነቃቂያ እና የዝግጅት ትምህርታችን ዛሬ ነሐሴ 2 ቀን ከቀኑ 8:30 ጀምሮ ይቀጥላል! ወንጌልን ለዓለም ማብሰር የሁላችንም አደራ በመሆኑ፣ ለዚህ ታላቅ ጉዞ ራሳችንን በጸሎት፣ በትምህርት እና በእውቀት ማዘጋጀታችንን እንቀጥላለን። የቀጠሮ ቦታ እና ሰዓት፦ 📅 ቀን፦ ዛሬ ነሐሴ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ⏰ ሰዓት፦ ከቀኑ 8:30 ጀምሮ የቤተክርስቲያናችን አባላት፣ የየአገልግሎት ክፍላት ተሳታፊዎች እና የመጽሐፍ ቅዱስ ህብረት አባላት በሙሉ ለታላቁ ጉዞ በበለጠ ብቃት ለመታጠቅ በሰዓቱ እንድትገኙ በፍቅር ጥሪያችንን እናቀርባለን! እግዚአብሔር ይባርካችሁ!
📅 ዛሬ ነሐሴ 2 ቀን 2018 📖 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል ዘሌ 20:1-27
“አገልጋዩ ንጉሥ" - አርብ ምሽት የማርቆስ ወንጌል ተከታታይ ትምህርት ሰላም! ሳምንታዊው የማርቆስ ወንጌል ጥናታችን ዛሬ ማታ ከ11:30 - 01:15 በጎፋ ማዞሪያ ብርሃነ ወንጌል መጥምቃውያን ቤተ ክርስቲያን ይቀጥላል። 📖 ሳምንት ካቆምንበት እንቀጥላለን!! ክፍሉን አንብበው በሰዓቱ እንዲገኙ በአክብሮት እንጋብዛለን!
📅 ዛሬ ነሐሴ 1 ቀን 2018 📖 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል ዘሌ 19:20-37
📅 ዛሬ ሐምሌ 30 ቀን 2018 📖 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል ዘሌ 19:1-19
🎤🎤 የሀዘን ማስታወቂያ ልጃችን አሚ ዳምሽ (የዳምሽ ልጅ) በደረሰበት ድንገተኛ አደጋ አርፏል። የቀብር ስርዓቱ ነገ ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም. ከቀኑ 7:00 ላይ በለቡ ገብርኤል ምስራቀ ፀሐይ ቤተክርስቲያን ሲሆን ከዚያ አስቀድሞ የሽኝት ስርዓት 5:30 ላይ በመኖሪያ ቤታቸው ስለሚደረግ ሁላችንም ተገኝተን ፕሮግራሙን በመካፈል እና ቤተሰቡንም እንድናፅናና እንደ ቤተክርስቲያን አደራ እንላለን። ቤታቸው ቤቴል ሆስፒታል ገባ ብሎ አምሮኝ ምግብ ቤት አጠገብ ነው።
📅 ዛሬ ሐምሌ 29 ቀን 2018 📖 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ክፍል ዘሌ 18:1-30