- Последний пост
- 11 янв. 2025 г.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
#ሰበር_መረጃ ሞያሌን ጨምሮ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ዛሬ ጠዋት አመፅ ተቀስቅሷል። ሞያሌ ከተማ አሁን በዚህ ሰአት ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ ተቃዉሞ እየተካሄደ ነው። #ትግላችን_አይሸጥ
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ወራሪው ሰራዊት በወሎ ተራሮች ስር ሰጥሞ እየቀረ ነው። የዛሬው ተረኛ ዞብል ተራራ ነው። "ዞብል ተራራ ላይ ጥይት ቅበሩበት አደራ ሚያወጡ ደፋሮች አሉበት" ተብሎ የተገጠመላቸው የምስራቅ አማራ ነብሮች የ48ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ሌ/ኮሎኔል ተካ መከቦ መሐመድ እና የክፍለ ጦሩ አንድ ሬጅመንት አዛዥ ምክትል መቶ አለቃ ተሬሳ ገዙ ቢቄላን ከነጭፍሮቻቸው ዋጋቸውን ሰጥተዋቸዋል። ህዝብ ለመጨፍጨፍ የጫኑት ቁሳቁስም በወገን ቁጥጥር ስር ገብቷል::
ማይ ወሎ አማራ ታሪክ ሰራ! ሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ውስጥ ሌተናል ኮሎኔሉ ተሸኝቷል። የአማራ ፋኖ በወሎ ምስራቅ አማራ ኮር ፩ ዞብል አምባ ክፍለ ጦር ሌተናል ኮሎኔል ተካ መከቦ መሃመድን ጨምሮ ከሁለት መቶ በላይ ወታደሮችን ሸኝቷል። የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 48ተኛ ክፍለ ጦር ቀፎዋ ቀረ። ዋርካው ይችላል💪
ሰበር ዜና! በዘመቻ ፊታውራሪ ደሳለው ስጦት እና ግራ አዝማች አረቡ ታደሰ ሸህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ቃኝ የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ላይ ከባድ እርምጃ በመዉሰድ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ:: የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር መቅደላ ክፍለጦር አካል የሆነው ሸህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ መቅደላ ወረዳ ልዩ ስሙ ድስም የሚባል ቦታ ላይ ከባድ የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም ሶስት ባስ አንድ ፓትሮል የጠላት ሃይል ሙሉ ለሙሉ ደምስሰዋል:: በተጋድሎው የብልፅግና ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት አብዘሃኛው የጥይት ራት ሲሆን ቀሪው ገደል ገብቶ አልቋል::አንድ ፓትሮልም ከነ 12 ሰራዊቱ ሙሉ ለሙሉ ተቃጥሏል:: ሌላኛው የአማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር አካል የሆነው ታቦር ተራራ ብርጌድ ዘመቻ ፊታውራሪ ደሳለው ስጦትና ግራ አዝማች አረቡ ታደሰ በማስቀጠል አማራ ሳይንት ወረዳ ከባድ ትንቅንቅ ሲያደርግ የዋለ ሲሆን ጠላትን በርካታ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል ተጎናፅፏል:: በተጨማሪም ተንታ ወረዳ ላይ የአገዛዙ ዙፋን ጠባቂ የነበሩ አስራ አንድ ሚሊሾች ፋኖ ጋር አንዋጋም በማለት ትጥቅ ያስረከቡ ሲሆን አገዛዙ ሁሉንም አስሯቸዋል:: በቀጣይም ራሳቸዉን ከአገዛዙ ጥቃት ለመጠበቅም ሲባል ሚሊሾች ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ፋኖን እንዲቀላቀሉ የፋኖ አመራሮችመልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል:: በቀጣይም መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ድል ለፋኖ ድል ለአማራ ህዝብ የአማራ ፋኖ በወሎ ወሎ ቤተ-አምሐራ ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም
DNE-AFRICA የተሰኘ የአፍሪካ ሚዲያ “አስፈሪው የምስራቅ አፍሪካ አማፂ ኃይል” በሚል ርዕስ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተለያዩ የአማራ አካባቢዎች ተውጣጥተው ሰልጥነው የተመረቁ የፋኖ ኮማንዶዎችን በቦታው ተገኝቶ ቀርፆ አለምአቀፉ ማህበረሰብ እንዲያየው አሰራጭቶታል።
🔥#ጎንደር አዘዞ💪 #ያዝ እንግዲህ! አዞዞ ከሚገኘው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ካምፕ ከ40 በላይ መከላከያ ከአንድ ሻምበል መሪ ጋር ከድተው መጥፋታቸውን ታውቋል::
ወደ ስራ ተመልሰናል!!
💚💛❤ 9 አውደ ውጊያ በአንድ ቀን የአማራ ፋኖ በጎጃም‼️ ================================= ህዳር 9/2017 ዓ.ም የአማራ ፋኖ በጎጃም ረቡዕ ገበያ፣ምርክታ፣ደንበጫ ከተማ፣ዳባ፣ቀኝ አቦ፣እነጋትራ፣አጋምና፣የሺሚት፣የሰንበት ላይ ከባድ ውጊያ ሲያደርግ ውሏል። √#ረቡዕ ገበያና #ምርከታ ላይ የ3ኛ( ጎጃም አገው ምድር)ክፍለ ጦር ለ2 ቀን ያክል ጠላትን ሲቀጠቅጠው ውሏል። የክፍለ ጦሩ ጥምር ጦር #ቀኝ አዝማች ስሜነህ ደስታ ብርጌድ(እንጅባራና አካባቢው) #ዘንገና ብርጌድ (ቲሊሊና አካባቢው) #ጊዮን ብርጌድ (ሰከላና አካባቢው) #፲ አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ (ፋግታ ለኮማና አካባቢው) በጥምረት ባደረጉት አውደ ውጊያ ቁጥሩ ያልታወቀ የብርሃኑ ጁላ ጦር ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል። √ #ደንበጫ ከተማ ላይ የ6ኛ(የቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴ) ክ/ጦር #ኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ 2 ሻለቃ ጦር በማስገባት ጠላትን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ደንበጫ ከተማን ለረጅም ሰዓት መቆጣጠር ችሏል። √#ዳባ ላይ የ6ኛ(የቀኝ ጌታየ ዮፍታሄ ንጉሴ) ክፍለ ጦር #ኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ #በላይ ዘለቀ ብርጌድ እንዲሁም #ከ2ኛ(ተፈራ ዳምጤ) ክፍለ ጦር #መዝገቡ ዋለልኝ ብርጌድ በጥምረት ባደረጉት ውጊያ በርካታ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል።ከሞት የተረፈው የጠላት ኃይል እስከምሽት ድረስ ሙትና ቁለኛውን እያነሳ ይገኛል። √#ቀኝ አቦ(ቢሮ) ከሚባል ቦታ ላይ የ6ኛ(ቀኝ ጌታየ ዮፍታሄ ንጉሴ) ክፍለ ጦር #ንጉስ ተ/ሃይማኖት ብርጌድ ና ከ7ኛ(ሐዲስ አለማየሁ) ክፍለ ጦር #የየቦቅላ አባይ ብርጌድ በጥምረት የአብይን ገዳይ ቡድን ከደብረ ዘይት ተነስቶ ወደ የቦቅላ ለመግባት ሙከራ እያደረገ እያለ በከበባ ሲቀጠቀጥ ውሏል።በርካታ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል። በዛሬው እለት ከአምስት አቅጣጫ (ከደ/ማርቆስ፣ከሉማሜ፣ከአምበር፣ከደብረ ዘይት) ብዙ ቁጥር ያለው የአብይ ጭፍራ ወደ የቦቅላ ለመግባት ሙከራ ያደረገው የጠላት ኃይል በጀግኖቹ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ተቀጥቅጦ ያሰበውን ሳያሳካ ሙትና ቁስለኛውን ጭኖ ተመልሷል። √#እነጋትራ ላይ የ7ኛ(ሀዲስ አለማየሁ) ክፍለ ጦር #መብረቁ ብርጌድ 2ኛና 3ኛ ሻለቆች ጠላትን በደፈጣ በመያዝ እያባረሩ ሲረፈርፉት ውለዋል። √#የሻሚትና #አጋምና ላይ የ7ኛ(ሀዲስ አለማየሁ) ክፍለ ጦር #ደባይ ጮቄ ብርጌድ ወደ ቀኝ አቦ በመሄድ ላይ የነበረን ጠላት ከበባ ውስጥ በማስገባት ሲለበልበው ውሏል። √#የሰንበት ላይ የ7ኛ(ሀዲስ አለማየሁ) ክፍለ ጦር #የቦቅላ አባይ ብርጌድና #መብረቁ ብርጌድ በጥምረት የብርሃኑ ጁላን ጨፍጫፊ ቡድን እያባረሩ ሲደመስሱት ውለዋል። ሲጠቃለል እጅግ በርካታ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ተደርጓል።በጠላት ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል። የአብይ ገዳይ ቡድን እንደተለመደው የንጹኃን ግድያ፣የንብረት ውድመት፣የአርሶሩን ሰብል በከባድ መሳሪያ ሲያቃጥል ውሏል።የየሰንበት 2ኛ ደረጃ ት/ቤትን ንብረት በሙሉ ጭኖ ወስዶታል። #አዲስ ትውልድ፣ #አዲስ አስተሳሰብ፣ #አዲስ ተስፋ!
ሰበር ዜና❗️ የአማራ ፋኖ በወሎ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ የአብይ አህመዱን ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በደፈጣ ጥቃት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ማሳቀቅ ማዋከቡና ረፍት መንሳቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል:: በፋኖ ካሳ አበበ የሚመራው ሃውጃኖ ክፍለጦር ራያ ቆቦ ጮቢ በር የመሸገዉ የጠላት ሃይል ላይ ዛሬ ህዳር ዘጠኝ ከሰዓት ቡሃላ የክፍለጦሩን ቃኝ ደፈጣ ጥቃት እንዲፈፅም በማድረግ ትልቅ ድል ተቀዳጅተዋል:: በጥቃቱ ዙፋን ጠባቂው የጠላት ሃይል ሙትና ቁስለኛ ሆኗል ሲል የሃውጃኖ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ጌታየ ተስፋየ ገልፇል:: በቀጣይም ጠላትን ሲያሻን በደፈጣ ሲያሻን በመደበኛ ዉጊያ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ እንዲሁም በመማረክ ረፍት መንሳቱና መፈናፈኛ ማሳጣቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የሃውጃኖ ክፍለጦር ዋና አዛዥ ፋኖ ካሳ አበበ ገልፇል:: በዚህ ሰዐትም የየጁዋ እመቤት ወልዲያ ከተማ ውስጥ ከባድ ጦርነት ተቀስቅሷል:: ከሼሁ ስታዲየም ሜካናይዝዱ ሰራዊት የሚተኩሰው ከባድ መሳሪያ ያልበገረዉ የአማራ ፋኖ በወሎ ሰርጂካል ኦፕሬሽን እየሰራ ነው። የህልዉና ተጋድሎው እስከ ድልና ነፃነት ተጠናክሮ ይጥላል ሲል የአማራ ፋኖ በወሎ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ ፋኖ አበበ ፈንታው ገልጿል። =
🔥#ደምበጫ‼️ የአሸባሪው የአብይ አህመድ ቡድን ከደምበጫ ማዘዣ ጣቢያው ሀይሉን አሰባስቦ #ገሊላ ቀጠና የሚገኜውን #የደምበጫ_ፋኖ (የአማራ ፋኖ በጎጃም ቀኝ ጌታ ዬፍታሄ ንጉሴ ክ/ጦር እንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ) አፍናለሁ አድመስሳለሁ ብሎ በማሰብ ከለሊቱ 6:00 ሰዓት ጀምሮ ወደ #ገሊላ ቀጠና ተንቀሳቅሷል‼️ ይሁን እንጅ አናብስቶች #ዳባ ሲደርስ ጠብቀው ገጥመው እንደ ቅጠል እያረገፉት ይገኛሉ። በአሁኑ ሰዓት ጠላት አስከሬኑን እየለቀመ ከባድ መሳሪያውን ነቅሎ ወደ #ኋላ እያፈገፈገ ሲሆን አናብስቶች ተከትለው በሚገባው ቋንቋ እያናገሩህ ነው💪 በተያያዘ መረጃ ጀብድ የማይሰለቼው የደምበጫ ፋኖ ከቆላ ቀጠና ያለውን ሀይል በማንቀሳቀስ ከተማው ገብተው የቀረውን ሀይል በተገቢው ቋንቋ እያናገሩት ሲሆን ሙሉአለም ችግኝ ከሚገኜው የኮንክሬት ምሽጉ እንደ አይጥ ተደብቆ የተለያዩ ከባድ መሳሪያዎችን #ሞርታር ጨምሮ እየተኮሰ ይገኛል ።
💚💛❤ምንጃር ሸዋ ‼️ 08/03/2017 በምንጃ ሸንኮራ በአሁኑ ሰአት በከባድ መሣሪያ የታገዘ በአይነቱ ከበድ ያለ ውጊያ እየተደረገ ነው አገዛዙን የከሰም ክፍለ ጦር አናብስት በምንጃር ከገበሬው ጋር ግንባር በመፍጠር እየወቃው ነው ። ወጥር ጀግናው አማራ እኛ ምንጃሮች ነን። https://t.me/goldmediaet
በምስራቅ ጎጃም ዞን ቢቡኝ ወረዳ ወይን ውሃ ቀበሌ ላይ ፋሲለደስ ቤተ ክርስቲያን የመሸገውን ሰዎ በላ የአራዊት ስብስብ በጥዋቱ ጀምረው ከተማው ላይ ዘልቀው በመግባት አይበገሬው ተፈራ ዳምጤ ክፍለ ጦር የተወጣጡ 3 ጥምር ብርጌዶች መሄጃውን እያስጠፉት ከጠላት ጋር አፍላ ውጊያ እያደረጉ ነው ! እና በአካባቢው ያሉ ፋኖዎች ተጨማሪ ሀይል ከሞጣ እና በድጎ ፅዮን እንዳይጨምር ደፈጣ በመጣል አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ የክ/ጦሩ ቃል አቀባይ አሳስቧል አማራ ላያሸንፍ አይጀምርም ፋኖነት አሸናፊነት 💪💪
ባህር ዳር አሁን ‼️ ባህርዳር ከደቂቃዎች በፊት ታንክና ዙ23 የያዘ እግረኛ ከመኮድ ወደ ኤየር ፖርት በመሄድ ላይ ነው‼️
ሕዳር 07 ቀን 2017 ዓ.ም ባሕር ዳር ብርሃኑ ጁላ ከብአዴን የተሸለመው ካባ ከትከሻው ሳይወልቅ ተዓምር ተሰርቷል! ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት አካባቢ ሁለት ወታደራዊ አውሮፕላኖች ከባህርዳር ኤርፖርት ተነስተው የተለመደውን የንፁሃን ጭፍጨፋ ሲያደርጉ ከዋሉ በኋላ ያልገመቱት ነገር ገጥሟቸዋል። ከወጡበት ስምሪት ሲመለሱ ባህርዳር ኤርፖርት ለማረፍ ዝቅ ብለው በሚበሩበት ወቅት የአማራ ፋኖ በጎጃም 1ኛ ክፍለ ጦር በረጅም ርቀት መሳሪያ ለመምታት ባደረገው ርብርብ አንደኛዋ ላይ ከባድ ጉዳት ማድረስ ችሏል:: በዚሁ ምክንያት የተመታችዉ ተዋጊ አውሮፕላን የሲቪል አውሮፕላን ማኮብከኮቢያው ላይ ተከስክሳለች። በስፍራው የነበረው የመከላከያ ምዕራብ ዕዝ እስታፍ ሙሉ ኤርፖርቱን በቁጥጥሩ ስር በማዋሉ ምክንያት የእሳት አደጋ መኪኖች እና አምቡላንሶችም ወደ ስፍራው እንዳይገቡ ተከልክለዋል:: አብራሪውን ጨምሮ በረራው ላይ የነበሩት በሙሉ መሞታቸው ተረጋግጧል። መደበኛ በረራም ተቋርጧል:: የአብይ አህመድ ወራሪ ጦር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርፖርቶችን እና የሲቪል አውሮፕላኖችን ለሰራዊቱ መጠቀም ካላቆመ ፋኖ የበረራ ክልከላ (No Fly Zone) ወደ ማወጁ ይሸጋገራል። ይኸኛው ትዉልድ አሸናፊ ነው! አዲስ ትዉልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! ©አስረስ ማረ ዳምጤ
አሳዛኝ መረጃ! የአገዛዙ ሰራዊት አማራን የማጥፋት ተልዕኮውን ተሸክሞ የሚዞረው ስብስብ ዛሬ ማለትም 07/ 2017 ዓ.ም ሁለት ሲቪል ግለሰቦችን ከቤት አውጥቶ ረሽኗል። ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ላይ ከፍ/ሰላም ወደ ሐሙሲት(አውንት መንዝ) ለመሔድ የተነሳው የአገዛዙ ሰራዊት መንገድ ላይ(ገራይ ትምህርት ቤት አካባቢ) ባልጠበቀው ሁኔታ በራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ክፍለ ጦር በአረንዛው ዳሞት ብርጌድ ሲመታ ወደ ኋላ በማፈግፈግ ከ ከተማው ዙሪያ ካሉት ገጠራማ መንደሮች መካከል ገራይ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ቤት ለቤት እየዞረ ንጹሀንን ሲረሽን አርፍዷል። ከአንድ ቤት ሁለት ግለሰቦችን እረሽኗል። በዚህም አንዲት ሴት ወንድሟንና ባሏን በአንድ ቅጽበት አጥታለች።ባለቤቷን ከቤት አውጥተው ከቤቱ በራፍ ፊትለፊት ሲገድሉት ወንድሟን ደግሞ እዛው እቤት ውስጥ ገድለውት ሒደዋል። አገዛዙ ለማንም የማይራራ የክፉዎችናስብስብ ስለሆነ ሁሉም ሰው በአገኘው አጋጣሚ አምርሮ ሊታገለው ይገባል።
"የውጭ ባንኮች እንዲገቡ ቢፈቀድም እንዲቆጣጠሩን አልተፈቀደም" ብሔራዊ ባንክ‼️ የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ገብተው እንዲቀሳቀሱ እንጂ የቁጥጥር ስራን እንዲሰሩ ፍቃድ እንዳልተሰጠ ተነግሯል፡፡ ይህ የተሰማው የህዝብ እንደራሴ ምክር ቤት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የፕላን በጀት እና ፍይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ከተለያዩ የባንክ ባለ ድርሻ አካላት ይፋዊ የሆነ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው። በዚህ ወቅት የብሔራዊ ባንክ ገዢው ማሞ ምህረቱ የውጭ ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸው በሚያመጣው እድል እና ስጋት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ክፍት ማድረግ ማለት ተጨማሪ ተዋናዮችን መጋበዝ ሲሆን ይቆጣጠሩናል ማለት ከቁጥጥር ነፃ ማድረግ ነው። እኛ ከቁጥጥር ነፃ እናድርጋቸው እያልን ሳይሆን እየተቆጣጠርን ዘርፉን ክፍት እናደርጋለን ነው ያልነው ሲሉም መልሰዋል። አክለውም የውጭ ባንኮች በመግባታቸው ለዘርፉ የተሻለ ተጠቃሚነትን የፍይናንስ ጤናማነት በተጠበቀ መልኩ ሲሆን ነው ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ ስለ ባንኮች ውህደት ለቀረበላቸው ጥያቄ እንደ መመሪያ ህግ ስርዓት ታስቦ የተቀመጠ እንጂ የፖሊሲ ውሳኔ አይደለም ሲሉም ነው ያብራሩት። https://t.me/goldmediaet
በምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻክል ወረዳ አማኑኤል ከተማ በርካታ ነዋሪዎች መታሰራቸው ታወቀ! በምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻክል ወረዳ አማኑኤል ከተማ በርካታ ነዋሪዎች "የፋኖ አባላት ቤተሰቦች ናችሁ" እየተባሉ እየታሰሩ እንደሆነ ታወቀ። መሠረት ሚድያ ከሰሞኑ ባደረገው ምርመራ በስፍራው በርከት ያሉ የመንግስት ሀይሎች በፋኖ ታጣቂዎች መወሰዳቸውን ተከትሎ በአማኑኤል ከተማ እና በገጠር ቀበሌው "የፋኖ ቤተሰብ ናችሁ" በሚል በርካታ ሰው እየታሰረ እንደሆነ ታውቋል። ሕፃናት እና እናቶች ጭምር "እህትሽ እና ባልሽ የፋኖ አባል ነው፣ አባላችንን ካልመለሱልን አንለቃችሁም" እየተባሉ በብዛት እየታሰሩ እንደሆነ ታውቋል። ከ6 አመት እና ከ10 አመት ልጇ ጋር የታሰረች ግለሰብ ጭምር ታስራ እንደምትገኝ የታወቀ ሲሆን የአካባቢው ነዋሪ "ከዛሬ ነገ ምን ይፈጠር ይሆን?" እያለ በስጋት ላይ እንደሚገኝ ታውቋል። በምስራቅ ጎጃም ዞን የአማኑኤል ከተማ አስተዳደር የነጭ ቀበሌ ነዋሪዎች ከትናንት በስቲያ ህዝባዊ ውይይት ማካሄዳቸውን የመንግስት ሚድያዎች የዘገቡ ሲሆን የዚህ የሰላማዊ ዜጎች እገታ ድርጊትም በህዝቡ መነሳቱ ታውቋል። በስፍራው የመንግስት ስራ ከተስተጓጎለ በርካታ ወራት እንደተቆጠረ የሚታወቅ ሲሆን የመንግስት ሰራተኞች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ስራ አቁመው ደሞዝም እንደተቋረጠባቸው ይገኛል።
🔥#የደፈጣ_እርምጃ‼️ የቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ብርግድ ዛሬ ከመሸ ጠላትን በደፈጣ ሲያራግፈው አምሽቷል💪 የአማራ ፋኖ በጎጃም የ3ተኛጎጃም አገው ምድር ክ/ጦር ቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድ 05/03/2017ዓ.ም ከምሽቱ 12:30 ላይ ከዳንግላ ወደ ዱርቤቴ በሚወስደው መንገድ ላይ ከጭሮ ከፍ ብሎ ቴሌው አካባቢ በተወሰደ የደፈጣ ጥቃት ሰባት የሚደርሱ የአገዛዙ የስልጣን አስጠባቂ ሰራዊት አባላት ሲደመሰሱ አምስቱ ክፉኛ ቆስለዋል የተረፈው ተበታትኖ ወደ ዱርቤቴ ፈርጥጧል ። ጠላት በተደጋጋሚ በሚደርስበት የደፈጣ ጥቃት በመማረር እየከዳ እና እየተበታተነ ይገኛል ከፊሉም ወደ ወገን ጦር እጁን እየሰጠ ወደ ሰላማዊ ሒይወቱ እየተመለሰ ይገኛል ። ስቦ መምታቱ እና ስቦ ማስከዳቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል ። ክፋት ለማንም -በጎነት ለሁሉም አዲስ ትውዉ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ ©#ቢትወደድ_መንገሻ_ጀምበሬ_ብርጌድ ዳንግላ #ላንጨርስ_አልጀመርነውም💪 #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 5/3/17 ዓ.ም