tgindex

ጓደኛዬ | Guadegnaye™

Статистика

ለሰዉ መድኃኒቱ Man ነዉ?! ጓደኛ እየፈለጉ ነዉ? ይህ ትክክለኛዉ platform ነዉና ያናግሩን።

Последний пост
17 июн.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 239
−8 за 4 дн.
Сутки
−3
−0,24%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
633
21 постов
Вовлечённость
51,1%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • “በአንድ ሰው ሕይወት ውስጥ በጣም የብቸኝነት ስሜት የሚሰማው ቅጽበት፣ መላው ዓለሙ ሲፈራርስ እያየ ምንም ማድረግ ሳይችል በባዶ እይታ መመልከት ብቻ የሚችልበት ጊዜ ነው።” ​ፍ. ስኮት ፊትዝጄራልድ ሼር እንዳይረሳ ለበለጠ ቻናሉን ይቀላቀሉ https://t.me/+zlTDnNbnyZ42MDg0

  • 📌 በኢንተርኔት ዓለም ውስጥ "ኩኪዎች" (Cookies) ምንድን ናቸው? ለምንስ የግላዊነት ጥያቄ ያስነሳሉ? ብዙዎቻችን የተለያዩ ድረ-ገጾችን ስንከፍት "ይህ ድረ-ገጽ ኩኪዎችን ይጠቀማል፣ ትቀበላለህ?" የሚል ጥያቄ በተደጋጋሚ ይገጥመናል። አብዛኛው ሰው ዝርዝሩን ሳያነብ "Accept" የሚለውን ይጫናል፤ ነገር ግን እነዚህ ትናንሽ ፋይሎች በዲጂታል ሕይወታችን ውስጥ ትልቅ ሚና አላቸው። ኩኪ (HTTP Cookie) ማለት አንድን ድረ-ገጽ ስንጎበኝ ያ ድረ-ገጽ ወደ ስልካችን ወይም ኮምፒውተራችን የሚልከው በጣም ትንሽ የሆነ የጽሁፍ ፋይል (Data) ነው። ይህ ፋይል ድረ-ገጹ እኛን ለይቶ እንዲያውቀንና ቀጣይ ስንመለስ ምርጫዎቻችንን እንዲያስታውስ የሚያገለግል እንደ "ዲጂታል መታወቂያ" ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። የኩኪዎች ዋነኛ ጥቅም ለተጠቃሚዎች ድረ-ገጾችን ምቹና ፈጣን ማድረግ ነው። ለምሳሌ፣ በአንድ ድረ-ገጽ ላይ አካውንታችንን ከፍተን ከገባን በኋላ (Login)፣ በየደቂቃው ድጋሚ የይለፍ ቃል እንዳይጠይቀን የሚያደርጉት እነዚህ ኩኪዎች ናቸው። እንዲሁም በቋንቋ፣ በገጽ ቀለም ወይም በሌሎች የግል ምርጫዎች ደረጃ የሰጠናቸውን ትዕዛዞች በቃላቸው ይዘው በመቆየት፣ በቀጣይ ጉብኝታችን ድረ-ገጹ በትክክል እኛ በፈለግነው መልኩ ተስተካክሎ እንዲጠብቀን ያደርጋሉ። ያለ ኩኪዎች አጠቃቀም፣ የኢንተርኔት ቆይታችን አሰልቺና በእያንዳንዱ እርምጃ መረጃን ደጋግመን የምናስገባበት ይሆን ነበር። ይሁን እንጂ ኩኪዎች ከጥቅማቸው ጎን ለጎን "ለምን ህግና ጥበቃ አስፈለጋቸው?" የሚለው ጥያቄ በስፋት ይነሳል። ምክንያቱም አንዳንድ ኩኪዎች የእኛን የኢንተርኔት እንቅስቃሴ (Browsing History) በዝርዝር የመከታተል አቅም አላቸው። በተለይ "Third-party cookies" የሚባሉት፣ ከአንድ ድረ-ገጽ አልፈው በሌሎች ገጾች ላይ የምናደርገውን እንቅስቃሴ በመከታተል ምን አይነት ምርቶችን እንደምንፈልግ መረጃ ይሰበስባሉ። ይህ መረጃ ደግሞ ለትልቅ የማስታወቂያ ኩባንያዎች ተላልፎ ስለሚሰጥ፣ በፌስቡክ ወይም በዩቲዩብ ላይ የግል ፍላጎታችንን የሚመስሉ ማስታወቂያዎች ተከታትለው እንዲመጡብን ያደርጋል። ይህ ሁኔታ የሰዎችን የግል ሚስጥርና ነፃነት ይጋፋል ተብሎ ስለሚታመን፣ እንደ አውሮፓ ህብረት (GDPR) ያሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ድረ-ገጾች ማንኛውንም መረጃ ከመሰብሰባቸው በፊት የተጠቃሚውን ፈቃድ እንዲጠይቁ በህግ አስገዳጅ አድርገዋል። ለማጠቃለል ያህል፣ በድረ-ገጾች ላይ የሚመጡ የኩኪ ምርጫዎችን ስናይ በዘፈቀደ ከመጫን ይልቅ አማራጮቹን ማየት ተገቢ ነው። ድረ-ገጹ በትክክል እንዲሰራ የሚያስፈልጉ (Essential) ኩኪዎችን መፍቀድ የግድ ቢሆንም፣ የእኛን የግል መረጃ ለንግድና ለማስታወቂያ የሚጠቀሙ ኩኪዎችን ግን የመከልከል መብት አለን። በዲጂታል ዘመን ስለ ቴክኖሎጂው አሠራር በቂ ግንዛቤ መያዝ፣ የግላዊነት መብታችንን ለማስከበር የመጀመሪያውና ዋናው እርምጃ ነው። #ShareThisPost ጠቃሚ ሆኖ ካገኛችሁት ሼር አድርጉት! Mohammed Seid #Technology #Cookies #DigitalPrivacy #CyberSecurity ሼር እንዳይረሳ ለበለጠ ቻናሉን ይቀላቀሉ https://t.me/+zlTDnNbnyZ42MDg0

  • без подписи

  • «ይህ ትውልድ በ"ጊዜ"ው ላይ ተሸንፏል። ቢያኮርፍ እንኳ የሚያባብለው የለም። ታላላቆቹ ጥይት በማንጣጣት ተጠምደዋል። ለረሀቡ ዳቦ ለእንባው ደሞ መሀረብ የሚያቀብለው ታላቅ የለውም። የኑሮ ትርምስና ውጣ ውረድ ታላላቆቹን ሽባ አድርጓቸዋል።» - «አንዳንዴ መፍትሄ ከሚሰነዝሩልን አፎች በላይ የሚያዳምጡን ጆሮዎች ያስፈልጉናል። በጥልቀት በመፍትሔ ሳይሆን በመደመጥ ብቻ የሚድኑ ህመሞች ብዙ ናቸው። ማቀፍ ደረጃ ያልደረሱ በመዳበስ ላይ የሚገኙ መነካካቶች ብቻ የብቸኝነትን ቆፈን ይገፋሉ።» (📖 ''ጥሪ ወደ ሞት'' ~ አህመድ ሀስ (ሻድ)) ፨፨፨፨ ሼር እንዳይረሳ ለበለጠ ቻናሉን ይቀላቀሉ https://t.me/+zlTDnNbnyZ42MDg0

  • ትንቢት አይደለም! በዚህ ሳምንት ሁለት ቲክቶከሮች ራሳቸውን ማጥ*ታቸውን አነበብኩ። ሁለቱም ወጣቶች። ይህ የተለየ የነብይነት ጸጋ የሚጠይቅም ነገር አይደለም። ነገር ግን በተለይ ቲክቶክ ላይ የምናያቸው ልጆች፣ የብዙዎቹ መጨረሻ አያምርም። ራስን ማ*ጥፋት፣ የአእምሮ መታወክና የመሳሰሉት ችግሮች ከፊታቸው ይጠብቋቸዋል። ለምን? ​የመጀመሪያው ጉዳይ፦ ዓለም አቀፍ የቢዝነስና የማርኬቲንግ ኤክስፐርቶች ባወሳሰቡት ዘግናኝ ሲስተም ውስጥ፣ ድክም ያለ ኢትዮጵያዊ ስነ-ልቦናና ዕውቀት ይዘው ነው የሚገቡት። ሳንቲሙ ብቻ ነው የሚታያቸው። ላይኩ ትንንሽ እውቅናው ያጓጓል። ሲስተሙ ልክ እንደ አምልኮ ሙሉ ለሙሉ መሰጠትና የራስን ማንነት መጣል ይጠይቃል። የማሰቢያ ይቅርና የመተንፈሻ ጊዜ አይሰጥም። ከራስ ጋር፣ ካደጉበት ባህልና እምነት ጋር በየቀኑ ግጭት ውስጥ ይገባሉ። ሕዝቡ ደግሞ ራሱን ጨዋ አድርጎ እየሳለ፣ ብልግናውን እንደ ሱቅ አሻንጉሊት አልብሶ የሚያቆማቸው ሚስኪን ወጣቶች በጭብጨባ በጊፍት ይፈጥራል። በፈለገው ልክ ይሰድባቸዋል፤ ያንቋሽሻቸዋል። ለሚያገኟት ሳንቲም ሲሉ ይህን ሁሉ ይሸከማሉ። ይህ ደግሞ መጨረሻው ባዶነት ነው። ​ሁለተኛው፦ የማይሞላው የሲስተሙ የብልግና ፍላጎት ነው። ዛሬ አንዲት ሴት ጫማዋን ብታወልቅና ሰዎች እግሯን ቢያደንቁ፣ ነገ ቀሚሷን እንድታወልቅ ይገፋፋታል። ከነገ ወዲያ... ራቁቷን ካስቀራት በኋላ እንደ ቆሻሻ ይጥላታል። ከዚያ በኋላ "እዩኝ እዩኝ" ለማለት የማይደረግ ነገር የለም። ለምናችሁ ፊቷን ያያችኋት ልጅ ለምናችሁ ርቃኗን ትቆማለች። መቸ ባገኘናቸው ብለን የጓጓንላቸው ታዋቂ ሰዎች ሳይቀሩ ዘግናኝ ውድቀት ሲወድቁና እንደውሻ ሂዱ ወደዚያ እየተባሉ ሲንቋሸሹ ተመልክተናል። ዛሬ ብሩም ክብሩም እጃቸው ላይ የለም፤ እንደአእምሮ ህመምተኛ ድሪቶ ሐሳብ እየጎተቱ በየድጅታል ሙዚቃ ቤቱ በር እየደነሱ ነው። ልክ እንደ ቁማር ነው ሲስተሙ፣ ትንሽ ተስፋ ይሰጠሀል ያለህን ይቀመሃል። ​ሶስተኛው፦ ለትምህርትና ለሌላ ሥራ ያለውን ፍላጎት መግደሉ ነው። ዛሬ ላይ ቀላል የማይባል ሕዝብ በዩቲዩብና በቲክቶክ ምክንያት ለሥራም፣ ለትምህርትም ሆነ ለማህበራዊ ኑሮ ያለው ፍላጎት እየሞተ ነው። ነገ ከነገ ወዲያ፣ በተለይ ድሃ አገራት የነፃ ኢንተርኔት እንዲያገኙ መደረጉ አይቀርም። ያኔ አሁን ከምናየው በብዙ ሺህ እጥፍ የሚበልጥ "ጉድ" አደባባይ ይወጣል። እንደ ኢትዮጵያ አይነት ከባድ ድህነትና የደከመ ዓለም አቀፍ ዕውቀት ያለባቸው አገራት፣ ውስብስቡን የስነ-ልቦና ወጥመድ ቀርቶ የዕለት ተዕለት ድርጊቱንም መረዳት ዳገት ይሆንባቸዋል። ሌላውን ተውት ብዙወች የተሟላ እንቅልፍ እንኳን አይተኙም። የብዙወቻችን ሲስተም ተዛብቷል። ​አራተኛ፦ የውሸት ሀብትና ሀብታሞች ይፈጠራሉ። አይሰሩም፣ አያሰሩም፣ አዲስ ነገርም አይፈጥሩም፤ ግን ብር እጃቸው ላይ ስለሚገባ የበለጠ ገንዘብ ለመስራት ሲስተሙን ይረብሹታል። ሴተኛ አዳሪነት፣ ሱስ፣ አደገኛ መጤ ባህሎች ፣ ብልጭልጭ ነገር በተለያየ ሽፋን ባህል ይሆናል። የሶሻል ሚዲያው ስብከት የቆምንበትን ማንነት ያፈራርሰዋል። በመጨረሻም ማንም ምንም አይኖረውም። እርሻ አታዮ ፋብሪካ ግን ሐብታም እዛና እዚህ ታያላችሁ። አምስተኛና አሳዛኙ ነገር የሚሰበከው ከሶሻል ሚዲያ ይገኛል የሚባለው ገንዘብ አለመኖሩ ነው። ጥቂቶች ጥቂት ይከፈላቸዋል፣ ሌላው ሕዝብ ግን ራሱን ጭምር ይከፍላል። ጊዜውን፣ ተስፋውን ሕይወቱን ቤተሰቡን! በዚህ ተስፋ አስቆራጭ ሂደት ብዙ ወጣቶች ራሳቸውም ላይ ሆነ በሌሎች ላይ ዘግናኝ ነገር ማድረጋቸው አይቀሬ ነው! የተሞከረ የታየ እውነት ነው። ​ምን እናድርግ??? ​እጃችን ላይ ያለውን ሥልጣን እንጠቀም፦ ልጆችን ቢያንስ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት (High School) በፊት ከሶሻል ሚዲያ እናርቃቸው። እንደ አገር ሥጋት፣ እንደ ሰውም ክብረ-ቢስነት ውስጥ የሚከቱ ይዘቶችን (Contents) ሪፖርት በማድረግ እናስወግድ። ጥሩ ኮንቴንቶችን እናበረታታ። የግለሰቦችን ነፃነት የሚጋፉ ስርጭቶች በሙሉ እንደ ሕዝብ ጠላት ሊታዩ ይገባል። ​የሃይማኖት ሰዎች ከዚህ ግፊያና ፍትጊያ ይራቁ፦ ወንጌል ለመስበክ በሚል ሰበብ፣ መተማመንንና አንድነትን ከማስፋፋት ይልቅ ባዶነትን ለትውልድ እያወረሱ ነው። እንደ ተቋም በሥርዓት ከሚሰራጩ አስተምህሮቶች ውጭ፣ በእምነት ስም፣ ባልሰለጠኑና ሞራል በሌላቸው ግለሰቦች የሚሰራጩ ፀያፍ ነገሮች ሁሉ ሊታገዱ ይገባል። ​ውይይትና ሕግ፦ በሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ላይ ምሁራንና ሕዝብን ያሳተፈ ውይይት በማድረግ አስፈላጊ ሕጎች ይውጡ። ይህ ማለት መንግሥት ለራሱ ሥልጣን ማራዘሚያ አፋኝ ሕግ ያውጣ ማለት አይደለም። ​እንጸልይ ጓዶች፦ የአሁኑን ድህነትና መመሳቀል የሚያስናፍቅ "የቆሸሸ ጊዜ" ከፊታችን እየመጣ ነው። ጨለምተኝነት አይደለም የእጃችሁን ሰዓት አይታችሁ ምሽቱ ምን ያህል ጊዜ እንደቀረው የመናገር ያህል ቀላልና ግልፅ ነው። #ሼር ያድርጉ (አሌክስ አብርሃም) ሼር እንዳይረሳ ለበለጠ ቻናሉን ይቀላቀሉ https://t.me/+zlTDnNbnyZ42MDg0

  • без подписи

  • የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሠርተፊኬት (12ኛ ክፍል ፈተና) ከሰኔ 24 እስከ ሃምሌ 17 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። በሌላ በኩል ፦ - የሬሜዲያል ፕሮግራም ሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 17 እስከ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ/ም - የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ/ም - የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና (NGAT) ከሃምሌ 29 እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2018 ዓ/ም - የመሰረታዊ የንባብና የስሌት ክህሎት ምዘና ጥናትና ምርምር መረጃ መሰብሰብ ከሚያዚያ 26 እስከ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ/ም ይሰጣል። ሼር እንዳይረሳ ለበለጠ ቻናሉን ይቀላቀሉ https://t.me/+zlTDnNbnyZ42MDg0

  • በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ለ7ኛው ምርጫ የመራጭነት ምዝገባ ከሚያዝያ 17-24/2018 ዓ.ም እንደሚከናወን ተሰምቷል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ፖርታል (https://uni.mirchaye.nebe.org.et) አዘጋጅቷል፡፡ ምዝገባውን ለማከናወን ምን ያስፈልጋል? ➫ በሚገኙበት ዩኒቨርሲቲ ኔትዎርክ ላይ መሆን፣ ➫ ስልክ፣ ኮምፒውተር ወይም ላፕቶፕ፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ፣ ➫ ብሔራዊ መታወቂያ ሲያወጡ የወጣበት የስልክ ቁጥር፡፡ ሼር እንዳይረሳ ለበለጠ ቻናሉን ይቀላቀሉ https://t.me/+zlTDnNbnyZ42MDg0

  • በረቂቅ መመሪያዎች ላይ አስተያየት ይስጡ! በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በተዘጋጁ ሦስት ረቂቅ ደንብና መመሪያዎች ላይ የትምህርት ማኅበረሰቡ እና ባለድርሻ አካላት አስተያየት እንዲሰጡ ጠይቋል፡፡ 🟠 በትምህርት ሚኒስቴር የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የራስ-ገዝነት የሽግግር መመሪያ፦ https://forms.gle/KiRAQn6kjsZ6yymt6 🟠 የራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ የመንግሥት ጥቅል የበጀት ድጋፍ ለመደንገግ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ፦ https://forms.gle/YEsQJwjE3wYUypJz6 🟠 በትምህርት ሚኒስቴር ለመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራር አሰያየምን ለመደንገግ የወጣ መመሪያ፦ https://forms.gle/HLqZm83W2ANMWMLt5 ሼር እንዳይረሳ ለበለጠ ቻናሉን ይቀላቀሉ https://t.me/+zlTDnNbnyZ42MDg0

  • የፌስቡክ እና ኢንስታግራም ባለቤት ሜታ ያለ ዲግሪ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ ስራ ሊቀጥር ነው ሜታ በቴክኖሎጂ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዘርፎች ለሚወጡ የስራ መደቦች የዩኒቨርሲቲ ዲግሪን እንደ ግዴታ መጠቀም ማቆሙን አስታወቋል። ኩባንያው ከአካዳሚክ ማስረጃ ይልቅ ለተግባራዊ ልምድ፣ ለግል ፕሮጀክቶች እና ለፈጠራ ችሎታ ቅድሚያ እንደሚሰጥ ገልጿል። እንደ ማርክ ዙከርበርግ ገለጻ፣ ወቅታዊው የትምህርት ስርአት ከቴክኖሎጂ ገበያው ፍጥነት ጋር የማይጣጣም በመሆኑ ይህ ውሳኔ ተላልፏል። አመልካቾች በኢንጂነሪንግ እና በማሽን ለርኒንግ ዘርፎች ያላቸውን ብቃት በተግባር ማሳየት እስከቻሉ ድረስ ያለ ዲግሪ መቀጠር ይችላሉ። እንዴት ማመልከት ይቻላል? በ metacareers.com በመግባት "AI" ወይም "Software Engineering" ብሎ መፈለግ። በስራ ዝርዝሩ ውስጥ "Equivalent practical experience" የሚል አማራጭ መኖሩን ማረጋገጥ። የሰራችኋቸውን የAI ፕሮጀክቶች ወይም የኮዲንግ ስራዎች (GitHub) ማስረጃ አድርጎ ማያያዝ። የግል መረጃንና ሲቪን (Resume) በመሙላት ማመልከቻውን ማጠናቀቅ። ይህ አሰራር በራስ ጥረት የሚገኝ እውቀትን የሚያበረታታ ሲሆን፣ በተለይ ዲግሪ ለሌላቸው ባለሙያዎች ትልቅ እድል ይከፍታል ተብሏል። ሼር እንዳይረሳ ለበለጠ ቻናሉን ይቀላቀሉ https://t.me/+zlTDnNbnyZ42MDg0

  • без подписи

  • без подписи

  • #SubmitYourComplaint በመውጫ ፈተና ውጤትዎ ላይ ቅሬታ ካለዎት በኦንላይን ቅሬታዎን ያስገቡ፡፡ ማንኛውም አይነት ቅሬታ ካለዎ ማለትም ➫ ውጤትዎ ያልተገኘ ከሆነ ➫ Disqualified የተባሉ ከሆነ ➫ ፊርማ ቢፈርሙም NG የተባሉ ከሆነ ➫ የተሳሳተ ጾታ ከመረጡ ➫ ሌላ ቅሬታ ካለዎ ማቅረብ ይችላሉ፡፡ የመውጫ ፈተና ውጤት ባዩበት ሊንክ (https://result.ethernet.edu.et) ላይ Submit Complaint የሚለውን ይጫኑ፣ Complaint Category ከሚለው ይምረጡ፣ Description የሚለው ባዶ ቦታ ላይ ቅሬታውን አጠር አድርገው ይግለፁ፣ ስልክ ቁጥርዎን ያስገቡና Submit Complaint የሚለውን በመጫን ያጠናቅቁ፡፡ ሼር እንዳይረሳ ለበለጠ ቻናሉን ይቀላቀሉ https://t.me/+zlTDnNbnyZ42MDg0

  • በየዓመቱ በመንግሥት ከሚመድቡላቸው ተማሪዎች በተጨማሪ የአካባቢያቸውን ሰዎች የሚያስተምሩ ዩኒቨርሲቲዎች መኖራቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት ቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሔደ ነው፡፡ በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እንዳሉት፣ ትምህርት ሚኒስቴር በየዓመቱ ለዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች የሚመድብ ሲሆን፤ ዩኒቨርሲቲዎቹ ግን በአካባቢያቸው የሚገኙ ሰዎችን ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ እንደሚያስተምሩ ገልፀዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች የፌዴራል ተቋማት በመሆናቸው ከተለያዩ ክልሎች የሚመጡ ተማሪዎች የሚመደቡባቸው ቢሆኑም፣ ተማሪዎቻቸው በአብዛኛው ከአካባቢያቸው የተገኙ ናቸው ብለዋል፡፡ ለማሳያ በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ 17ዐ ተማሪዎች ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ይዘው ሲማሩ መገኘታቸውን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ በትምህርት ዕድል ስም በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ከደቡብ ሱዳን መጥተው የሚማሩ መኖራቸውን ገልፀዋል። በዚህ ዓመት ስድስት ወራት የሚያስተምሯቸውን ተማሪዎች መረጃ ሳይልኩ የቀሩ ዩኒቨርሲቲዎች መኖራቸውን የገለፀፀፁት ሚኒስትሩ፤ በዚህም ሚኒስቴሩ በየዓመቱ የሚመድባቸው ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎቹ ውስጥ እየተማሩ መሆናቸውን ለማረጋገጥ መረጃ ወደ ማሰባሰብ መገባቱንም አንስተዋል። በቅርቡ በተሰጠው የመውጫ ፈተና ስርቆት መከሰቱን፣ የዩኒቨርሲቲዎች የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች በፈተና ስርቆት እንዳሉበትና የዩኒቨርሲቲ መምህራንም ለተፈታኞች ሲፈተ መያዛቸውን ሚኒስትሩ ተናግረዋል። የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ይህ ችግር ሲፈጠር እንዳላየ ያሳልፋል ሲሉም ችግሩ የከፍተኛ አመራሩ ጭምር መሆኑንም ገልፀዋል። #ሪፖርተር ሼር ይቀላቀሉ https://t.me/+zlTDnNbnyZ42MDg0

  • በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ለ2018 ዓ.ም በድኅረ-ምረቃ ዲፕሎማ በአማራጭ የመምህርነት ትምህርት ስልጠና ፕሮግራም የተመለመላችሁ የኬሚስት፣ ፊዚክስ፣ ሒሳብ፣ እርሻ፣ ባዮሎጂ እና እንግሊዝኛ ትምህርት መስክ አመልካቾች ሪፓርት ማድረጊያ ቀን ቅዳሜ መጋቢት 05/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ሪፖርት ማድረጊያ ቦታ፦ በዩኒቨርሲቲው አይናለም (MIT) ግቢ ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የመጀመሪያ ዲግሪ ሰርቲፊኬት ዋናውና ስካንድ ኮፒ፣ ➫ ትራንስክሪፕት ዋናውና ስካንድ ኮፒ ➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብሰ እና የትራስ ልብስ ሼር እንዳይረሳ ለበለጠ ቻናሉን ይቀላቀሉ https://t.me/+zlTDnNbnyZ42MDg0

  • без подписи

  • #NGATResult የካቲት 04/2018 ዓ.ም የተሰጠው 2ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት ተለቋል። ውጤትዎን ለማየት 👇 https://result.ethernet.edu.et ሊንኩን ከተጫኑ በኋላ 'NGAT Results' ላይ 'View Results' የሚለውን በመጫንና Username በማስገባት ውጤትዎን ይመልከቱ። ሼር እንዳይረሳ ለበለጠ ቻናሉን ይቀላቀሉ https://t.me/+zlTDnNbnyZ42MDg0

  • የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ሥራ ላይ እንዲውል መንግሥት ወሰነ። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ የካቲት 23/2018 ዓ.ም ባካሔደው መደበኛ ስብሰባ ውሳኔ ካሳለፈባቸው ጉዳዮች መካከል፣ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ይገኝበታል። "መደመር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ" በአዋጅ ቁጥር 1294/2015 መሠረት ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ እንዲቋቋም ረቂቁ ይገልጻል። ረቂቅ ደንቡ የዩኒቨርሲቲውን ተግባርና ኃላፊነት በመደንገግ ተቋሙ ለሀገር ዕድገት የበኩሉን ሚና እንዲወጣ የህግ ማዕቀፍ ሆኖ እንዲያገለግል ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ መወሰኑ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡ ሼር እንዳይረሳ ለበለጠ ቻናሉን ይቀላቀሉ https://t.me/+zlTDnNbnyZ42MDg0

  • без подписи

  • без подписи