- Последний пост
- 8 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 759
- 1/48двое суток
- 869
- 1/72трое суток
- 938
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የሁለተኛ ደረጃ የተማሪዎች ምዝገባ ሙሉ በሙሉ የጨረስን መሆኑ እናሳውቃለን። ት/ቤቱ
ጎበዝ ተማሪ የመሆን ዋና ዋና አበይት ነጥቦች ጎበዝ እና ውጤታማ ተማሪ መሆን ድንገት የሚመጣ አጋጣሚ ሳይሆን፣ የትክክለኛ ልማዶች፣ የጽናት እና የጥሩ ስልት ውጤት ነው። በጥናት እና በተግባር የተረጋገጡ ጎበዝ ተማሪ የመሆን ዋና ዋና ሚስጥሮች የሚከተሉት ናቸው። 1. የማጠናት ስልትን ማሻሻል (Smart Study) በሰንጠረዥ ማናት (Time Blocking): ዋና ዋና የሚባሉትን አበይት ነጥቦች እጥር ምጥን ባለ መልኩ ለይቶ ማውጣት በየቀኑ ለጥናት የሚሆን የተወሰነ ሰዓት መመደብ፤ በጥናት መካከልም አጭር የዕረፍት ጊዜ መውሰድ(ለምሳሌ፦ 25 ደቂቃ አጥንቶ ለ5 ደቂቃ) ማረፍ። ንቁ ተሳትፎ (Active Recall): ማንበብ ብቻ በቂ አይደለም። ያነበብነውን መጽሐፍ ዘግተን "ምን ተረዳሁ?" ብለን ራሳችንን መጠየቅ፣ ወይም ማስታወሻ ሳናይ ራስን መፈትን። ለሌላ ሰው ማስረዳት (Feynman Technique): ያጠናነውን ርዕስ ለጓደኛችን ወይም ለራሳችን በቀላል ቋንቋ ለማስረዳትም ሆነ ለመረዳት መሞክር። ጽንሰ-ሐሳቡን ምን ያህል ጠልቀን መረዳታችንን ለማወቅ የተሻለው መንገድ ይህ ነው። 2. ክፍል ውስጥ ንቁ መሆን ከፊት መቀመጥና ማስታወሻ መያዝ: ባብዛኛው የምንረዳው ክፍል ውስጥ እንደመሆኑ መጠን አስተማሪው የሚናገረውን/የሚያስረዳውን በአጭር በአጭሩ መያዝ። ጥያቄ መጠየቅ: ያልገባንን ነገር ወዲያውኑ አስተማሪያችንን ወይም ጓደኞቻችንን ጠይቀን መረዳትና የሚጠየቁ ጥያቄዎችን አለማከማቸት። 3. ጊዜን በአግባቡ መያዝ (Time Management) ዛሬ የሚሰራውን ለነገ አለማስተላለፍ: የቤት ሥራዎችን፣አሳይመንቶችንና እና ፕሮጀክቶችን በተሰጠው ቀን መጀመርና ሰርቶ ማጠናቀቅ ከፈተና በፊት የሚፈጠርን ጭንቀት ይቀርፋል። ቅደም ተከተል ማውጣት: አስቸጋሪ ወይም ትኩረት የሚሹ ትምህርቶችን አእምሯችን ሳይደክም ጠዋት ወይም በጥናታችን መጀመሪያ ላይ ማጠናቀቅ። ቤተ መፅሀፍ ገብተን የምናነብበትን ጊዜ፣ የተለያዩ ትምህርቶችን መለማመጃ/መዘጋጃ ጥያቄዎችን የምንሰራበትን ጊዜ መመጠን ይኖርብናል። 4. የአኗኗር ዘይቤ እና የአእምሮ ዝግጅት በቂ እንቅልፍ ማግኘት: አእምሮ ያጠናውን ነገር መዝግቦ የሚይዘው እና የሚያድሰው በእንቅልፍ ወቅት ነው (በቀን ከ7–8 ሰዓት እንቅልፍ አስፈላጊ ነው)። ጤናማ ምግብ እና እንቅስቃሴ: የተመጣጠነ ምግብ መመገብና አካላዊ ጤንነት ለንቁ አእምሮ መሰረት ናቸው። አዎንታዊ አስተሳሰብ (Growth Mindset): "አልችልም" ከማለት ይልቅ "በደንብካጠናሁና ከተለማመድኩ እችላለሁ" የሚል እምነት ሊኖረን ይገባል። በአጠቃላይ ጎበዝ ተማሪ ማለት በቀን 24 ሰዓት የሚያጠና ሳይሆን፣የሚያጠናበትን ሰዓት በአግባቡና በትኩረት የሚጠቀም ነው።
ቀን፡ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም አስቸኳይ መልዕክት ለ ወላጆች፡- 🔕🔔🔔🔔🔔🔕📣📣📣📣 ከዓርብ፣ ነሐሴ 01/2018 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ ተማሪዎች ስለምንቀበል ዘግይተው የሚመጡ ነባር ተማሪዎች የክፍል ምጣኔ ቢሞላ ት/ቤቱ ሐላፍነት የማይወስድ ሲሆን፤ እስከ ቅበላ አቅም ድረስ የነባር ተማሪዎች ምዝገባ በአንድ ተማሪ በቀን 30 ብር ቅጣት የሚያስቀጣ በመሆኑ፣ እስከ አሁን ልጆቻችሁን ያላስመዘገባችሁ ወላጆች ቀድማችሁ እንድታስመዘግቡ ከወዲሁ እናሳስባለን። ት/ቤቱ Date: August 3, 2026 Urgent Message to Parents: We will start accepting new students on Friday, August 07, 2026. Therefore, the school will not take responsibility for returning students who arrive late if the class capacity is full. Furthermore, until the enrollment capacity is reached, registration for returning students will incur a late penalty of 30 Birr per day per student. We strongly advise parents who have not yet registered their children to do so in advance. The School
The four pillars of education (አራቱ የትምህርት አምዶች) 📚📚📚📚 ✍️ 1. ለማወቅ መማር ✍️ 2. ለመሥራት መማር ✍️ 3. አብሮ ለመኖር መማር ✍️ 4. ለመሆን መማር 📚 የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) በጃክ ዴለርስ በሚመራው ኮሚሽን አማካኝነት የዘረጋቸው አራቱ የትምህርት አምዶች (Four Pillars of Education) ለ21ኛው ክፍለ ዘመን ትምህርት መሠረት ናቸው። 👉 እነዚህ አምዶች ትምህርት ዕውቀትን ብቻ ሳይሆን፣ ክህሎትንና ስብዕናን ማዳበር እንዳለበት ያመለክታሉ።(Skill plus Attitude) ✍️ 1. ለማወቅ መማር (Learning to Know) ይህ አምድ ትኩረት የሚያደርገው መሠረታዊ ዕውቀትን ከማግኘት ባለፈ፣ እንዴት መማር እንዳለብን መማር (Learning how to learn) ላይ ነው። 🎯 ዋና ዓላማ 🕯 ተማሪዎች ዓለምን እንዲረዱ፣ የማወቅ ጉጉታቸውን እንዲያሳድጉ እና የማስታወስ፣ የማሰብ እንዲሁም የማተኮር ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ ማስቻል። 🔑 ቁልፍ ነጥብ 👉 ዕውቀት በየጊዜው ስለሚለወጥ፣ አንድ ተማሪ በራሱ አዳዲስ መረጃዎችን የመፈለግና የመረዳት ፍላጎት እንዲኖረው ማድረግ ነው። ✍️ 2. ለመሥራት መማር (Learning to Do) ዕውቀትን ወደ ተግባር መለወጥ ላይ ያተኩራል። ይህም ተማሪዎች የተማሩትን ነገር በተግባራዊ ሕይወታቸውና በሥራ ዓለም ላይ እንዲጠቀሙበት ያዘጋጃቸዋል። 🎯ዋና ዓላማ 🕯የሙያ ክህሎትን ማዳበር ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ችግር ፈቺነት፣ ከሰዎች ጋር በቡድን የመሥራት ብቃት እና በሥራ ላይ የሚገጥሙ ተግዳሮቶችን የመቋቋም ችሎታን ማዳበር ነው። 🔑 ቁልፍ ነጥብ 👉 በአሁኑ ዘመን "ለመሥራት መማር" ሲባል በእጅ ከሚሠራ ሥራ (Manual Labor) ባለፈ፣ መረጃን የመተንተንና የፈጠራ ሥራዎችን የመሥራት ብቃትን ይጨምራል። ✍️ 3. አብሮ ለመኖር መማር (Learning to Live Together) ይህ አምድ በዘመናዊው ዓለም ውስጥ እጅግ አስፈላጊው እንደሆነ ይታመናል። ትኩረቱም በሰዎች መካከል ሰላምን፣ መቻቻልንና መግባባትን መፍጠር ነው። 🎯ዋና ዓላማ 🕯 የሌሎችን ታሪክ፣ ባህልና እሴት ማክበር፣ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት እና የጋራ ግቦችን ለማሳካት በጋራ መሥራትን መልመድ ነው። 🔑 ቁልፍ ነጥብ 👉 በትምህርት ቤት ውስጥ የሚከናወኑ የቡድን ሥራዎችና ውይይቶች ለዚህ አምድ ተግባራዊነት ትልቅ ድርሻ አላቸው። ✍️ 4. ለመሆን መማር (Learning to Be) ይህ አምድ የሰውን ልጅ ሁለንተናዊ ዕድገት (Physical, Intellectual, Emotional, and Spiritual) የሚመለከት ነው። 🎯ዋና ዓላማ 🕯 እያንዳንዱ ግለሰብ የራሱ የሆነ ነፃነት፣ የማመዛዘን ችሎታ፣ የሥነ-ምግባር ጥንካሬ እና ኃላፊነት እንዲኖረው ማድረግ ነው። 🔑 ቁልፍ ነጥብ 👉 ትምህርት የአንድን ሰው የተደበቀ ተሰጥኦ (Potential) አውጥቶ ለራሱና ለማኅበረሰቡ የሚጠቅም ሙሉ ሰው እንዲሆን መርዳት አለበት። ባጭሩ፦ ✍️✍️✍️✍️ እነዚህ አራቱ አምዶች እርስ በርሳቸው የተሳሰሩ ናቸው። ለማወቅ መማር መሣሪያ ሲሆን፣ ለመሥራት መማር ተግባር ነው፣ አብሮ ለመኖር መማር ማኅበራዊ መሠረት ሲሆን፣ ለመሆን መማር ደግሞ የሦስቱም የመጨረሻ ውጤት ወይም ድምር ነው። @Lifelong learner 🎯📌👇 Bloom's taxonomies of education 1.Cognitive domain (Knowledge/HEAD) 2.Affective domain (Attitude /HEART) 3.Psychomotor domain (Skill/HAND)
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
በዛሬው ዕለት ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም በጆይንት ቪዥን ሰክሰስ አካዳሚ የ2018 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም ግምገማ ሪፖርት ቀርቦ የወተመህ ስራ አስፈፃሚ አባላት እና የት/ቤቱ ባለቤቶች በተገኙበት ሰፊ ውይይት እና ግምገማ ተደረገ።
በወላጅ ጥያቄ መሰረት የተማሪዎች ምዝገባ እስከ ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም ድረሰ ብቻ ተራዝመዋል።
видео или голосовое, без подписи
ቀን:- ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም ለነባር ተማሪ ወላጆች በሙሉ:- 🔔🔔🔔🔔🔔🔔 የነባር ተማሪዎች የ 2019 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባ የሚጠናቀቅበት ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም እንደሆነ ይታወቃል። በዚህም መሰረት የምዝገባ ስዓት ነገ ቅዳሜ ፣ ሐምሌ 18/2018 ዓ.ም እስከ 6:00 እና ሰኞ፣ ሐምሌ20/2018 ዓ.ም እስከ 10:00 ብቻ ማስመዝገብ የምትችሉ መሆኑን በድጋሜ እናሳስባለን። ከዚህ ቀን በኋላ ለሚፈጠር የቦታ ማጣት ችግር ት/ቤቱ ኋላፍነት የማይወስድ መሆኑን በጥብቅ ለማሳሰብ እንወዳለን። ት/ቤቱ
ቀን:- ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም ለነባር ተማሪ ወላጆች በሙሉ:- 🔔🔔🔔🔔🔔🔔 በመጀመሪያ ሰላምና ጤና በያላችሁበት እንመኛለን። የነባር ተማሪዎች የ 2019 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባ ከጀመርን ሁለት ሳምንት ሆነናል። ስለዚህ እስከ አሁን ልጆቻችሁ ያላስመዘገባችሁ ወላጆች እስከ ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም ብቻ እንድታስመዘግቡ እያሳሰብን ከሐምሌ 21/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባልተመዘገቡ ነባር ተማሪዎች ምትክ በጊዜየዊ መዝገብ ላይ የመዘገብናቸውን አዳዲስ ተማሪዎች ለመመዝገብ ቃል የገባን ስለሆነ የምዝገባ ቀናቱን ባለመጠበቅ ምክንያት ለሚፈጠር የቦታ ማጣት ችግር ት/ቤቱ ኋላፍነት የማይወስድ መሆኑን በጥብቅ ማሳሰብ እንወዳለን። ት/ቤቱ
видео или голосовое, без подписи
ቀን፡ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም አስደሳች ዜና ለተማሪ ወላጆች !!! ሰላም ውድ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪ ወላጆች / ህጋዊ አሳዳጊዎች በሙሉ፡፡ 🙏🙏🙏🙏👏👏👏👏🎉🎉🎉🎉🎉 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ምዝገባ በተለያዩ ምክንያቶች የ 2019 ዓ.ም የተማሪ ምዝገባ ሳይጀመር እንደቆየ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ በዛሬው ዕለት ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጉዳዩ መፍትሄ ስላገኘ ልጆቻችሁ ከነገ ቅዳሜ ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምራችሁ ማስመዝገብ የምትችሉ መሆኑን በታላቅ ደስታ እናበስራለን፡፡ 👌👌👌👌👌 ✅ ማስታወሻ፡ 👉 የጀማሪ ተማሪዎች እና ለአዲስ ተማሪዎች 1ክላሰር ፤ 2 ጉርድ ፎቶ ግራፍ የተማሪ ፤ 1 ጉርድ ፎቶግራፍ የወላጅ እና የልደት ሰርተፍኬት ያስፈልጋል ፡፡ 👉 ነባር ተማሪ ( ኬጂ 2 እና ኬጂ 3) ከሆኑ የተማሪው/ዋ ካርድ፤ 2 ጉርድ ፎቶ የተማሪ እና 1 የወላጅ ፎቶ ግራፍ 👉 የመስከረም ወር እና የመመዝገቢያ ክፍያ በሚመለከት ነባር ተማሪዎች በ2018 ዓ.ም መክፊያ ኮድ ፤ አዲስ ተማሪዎች ደግሞ ከት/ቤቱ መክፊያ ኮድ በመውሰድ በ አዋሽ ባንክ መክፈል ይጠበቅቦታል፡፡ በትዕግስት ስለጠበቃቹን ከልብ እናመሰግናለን፡፡ ክብረት ይስጥልን!!! ት/ቤቱ Exciting News for Parents! 🎉🎉🎉🎉👍👍🎉🎉🎉🎉🎉 Hello, dear pre-primary school parents / legal guardians, As you may know, the registration of pre-primary school students for the 2019 E.C. academic year has been temporarily delayed due to various reasons. However, we are thrilled to announce that the issue has been resolved today, Hamle 10, 2018 E.C. (July 17, 2026). You can start registering your children starting tomorrow, Saturday, Hamle 11, 2018 E.C. (July 18, 2026). 💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫 📋 Registration Requirements ✅ For New / Beginner Students: 1 student file folder 2 passport-sized photos of the student 1 passport-sized photo of the parent/guardian Student's birth certificate ✅ For Returning Students (KG 2 & KG 3): The student's report card/ID card 2 passport-sized photos of the student 1 passport-sized photo of the parent/guardian 💳 Payment Information Regarding the registration fee and September (Meskerem) monthly tuition fee: ✍ Returning Students: Please make your payment at Awash Bank using your payment code from last year. ✍ New Students: Please obtain a new payment code from the school office first, and then make the payment at Awash Bank. Thank you very much for your patience. Respectfully, 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 The School Administration