tgindex
JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY

Статистика

Grade 1- 8

Последний пост
8 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 251
0 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
623
21 постов
Вовлечённость
49,8%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
494
1/48двое суток
566
1/72трое суток
610

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ምዝገባ ሙሉበሙሉ የጨረስን መሆኑ እናሳውቃለን።              ት/ቤቱ

  • ጎበዝ ተማሪ የመሆን ዋና ዋና አበይት ነጥቦች ጎበዝ እና ውጤታማ ተማሪ መሆን ድንገት የሚመጣ አጋጣሚ ሳይሆን፣ የትክክለኛ ልማዶች፣ የጽናት እና የጥሩ ስልት ውጤት ነው። ​በጥናት እና በተግባር የተረጋገጡ ጎበዝ ተማሪ የመሆን ዋና ዋና ሚስጥሮች የሚከተሉት ናቸው። ​1. የማጠናት ስልትን ማሻሻል (Smart Study) ​በሰንጠረዥ ማናት (Time Blocking): ዋና ዋና የሚባሉትን አበይት ነጥቦች እጥር ምጥን ባለ መልኩ ለይቶ ማውጣት በየቀኑ ለጥናት የሚሆን የተወሰነ ሰዓት መመደብ፤ በጥናት መካከልም አጭር የዕረፍት ጊዜ መውሰድ(ለምሳሌ፦ 25 ደቂቃ አጥንቶ ለ5 ደቂቃ) ማረፍ። ​ንቁ ተሳትፎ (Active Recall): ማንበብ ብቻ በቂ አይደለም። ያነበብነውን መጽሐፍ ዘግተን "ምን ተረዳሁ?" ብለን ራሳችንን መጠየቅ፣ ወይም ማስታወሻ ሳናይ ራስን መፈትን። ​ለሌላ ሰው ማስረዳት (Feynman Technique): ያጠናነውን ርዕስ ለጓደኛችን ወይም ለራሳችን በቀላል ቋንቋ ለማስረዳትም ሆነ ለመረዳት መሞክር። ጽንሰ-ሐሳቡን ምን ያህል ጠልቀን መረዳታችንን ለማወቅ የተሻለው መንገድ ይህ ነው። ​2. ክፍል ውስጥ ንቁ መሆን ​ከፊት መቀመጥና ማስታወሻ መያዝ: ባብዛኛው የምንረዳው ክፍል ውስጥ እንደመሆኑ መጠን አስተማሪው የሚናገረውን/የሚያስረዳውን  በአጭር በአጭሩ መያዝ። ​ጥያቄ መጠየቅ: ያልገባንን ነገር ወዲያውኑ አስተማሪያችንን ወይም ጓደኞቻችንን ጠይቀን መረዳትና የሚጠየቁ ጥያቄዎችን አለማከማቸት። ​3. ጊዜን በአግባቡ መያዝ (Time Management) ​ዛሬ የሚሰራውን ለነገ አለማስተላለፍ: የቤት ሥራዎችን፣አሳይመንቶችንና እና ፕሮጀክቶችን በተሰጠው ቀን መጀመርና ሰርቶ ማጠናቀቅ ከፈተና በፊት የሚፈጠርን ጭንቀት ይቀርፋል። ​ቅደም ተከተል ማውጣት: አስቸጋሪ ወይም ትኩረት የሚሹ ትምህርቶችን አእምሯችን ሳይደክም ጠዋት ወይም በጥናታችን መጀመሪያ ላይ ማጠናቀቅ። ቤተ መፅሀፍ ገብተን የምናነብበትን ጊዜ፣ የተለያዩ ትምህርቶችን መለማመጃ/መዘጋጃ ጥያቄዎችን የምንሰራበትን ጊዜ መመጠን ይኖርብናል። ​4. የአኗኗር ዘይቤ እና የአእምሮ ዝግጅት ​በቂ እንቅልፍ ማግኘት: አእምሮ ያጠናውን ነገር መዝግቦ የሚይዘው እና የሚያድሰው በእንቅልፍ ወቅት ነው (በቀን ከ7–8 ሰዓት እንቅልፍ አስፈላጊ ነው)። ​ጤናማ ምግብ እና እንቅስቃሴ: የተመጣጠነ ምግብ መመገብና አካላዊ ጤንነት ለንቁ አእምሮ መሰረት ናቸው። ​አዎንታዊ አስተሳሰብ (Growth Mindset): "አልችልም" ከማለት ይልቅ "በደንብካጠናሁና ከተለማመድኩ እችላለሁ" የሚል እምነት ሊኖረን ይገባል። በአጠቃላይ ጎበዝ ተማሪ ማለት በቀን 24 ሰዓት የሚያጠና ሳይሆን፣የሚያጠናበትን ሰዓት በአግባቡና በትኩረት የሚጠቀም ነው።

  • ቀን፡ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም አስቸኳይ መልዕክት ለ ወላጆች፡- 🔕🔔🔔🔔🔔🔕📣📣📣📣 ከዓርብ፣ ነሐሴ 01/2018 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ ተማሪዎች ስለምንቀበል ዘግይተው የሚመጡ ነባር ተማሪዎች የክፍል ምጣኔ ቢሞላ ት/ቤቱ ሐላፍነት የማይወስድ ሲሆን፤ እስከ ቅበላ አቅም ድረስ የነባር ተማሪዎች ምዝገባ በአንድ ተማሪ በቀን 30 ብር ቅጣት የሚያስቀጣ በመሆኑ፣ እስከ አሁን ልጆቻችሁን ያላስመዘገባችሁ ወላጆች ቀድማችሁ እንድታስመዘግቡ ከወዲሁ እናሳስባለን።                                                  ት/ቤቱ Date: August 3, 2026 Urgent Message to Parents: We will start accepting new students on Friday, August 07, 2026. Therefore, the school will not take responsibility for returning students who arrive late if the class capacity is full. Furthermore, until the enrollment capacity is reached, registration for returning students will incur a late penalty of 30 Birr per day per student. We strongly advise parents who have not yet registered their children to do so in advance.                                      The School

  • 1 авг.633из joint_vision

    ለወላጅ ወይም አሳዳጊዎች በሙሉ የ2019 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባ የዘጠነኛ ክፍል የጨረስን ሲሆን:ሌሎች ክፍል ላይ ውስን ቦታዎች ብቻ የቀሩን መሆኑን እንገልፃለን።ሁለተኛ ደረጃ

  • The four pillars of education (አራቱ የትምህርት አምዶች) 📚📚📚📚 ✍️ 1. ለማወቅ መማር ✍️  2. ለመሥራት መማር ✍️ 3. አብሮ ለመኖር መማር ✍️ 4. ለመሆን መማር 📚 የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) በጃክ ዴለርስ በሚመራው ኮሚሽን አማካኝነት የዘረጋቸው  አራቱ የትምህርት አምዶች (Four Pillars of Education) ለ21ኛው ክፍለ ዘመን ትምህርት መሠረት ናቸው። 👉  እነዚህ አምዶች ትምህርት ዕውቀትን ብቻ ሳይሆን፣ ክህሎትንና ስብዕናን ማዳበር እንዳለበት ያመለክታሉ።(Skill plus Attitude) ✍️ 1. ለማወቅ መማር (Learning to Know) ይህ አምድ ትኩረት የሚያደርገው መሠረታዊ ዕውቀትን ከማግኘት ባለፈ፣ እንዴት መማር እንዳለብን መማር (Learning how to learn) ላይ ነው። 🎯 ዋና ዓላማ 🕯 ተማሪዎች ዓለምን እንዲረዱ፣ የማወቅ ጉጉታቸውን እንዲያሳድጉ እና የማስታወስ፣ የማሰብ እንዲሁም የማተኮር ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ ማስቻል።   🔑 ቁልፍ ነጥብ 👉 ዕውቀት በየጊዜው ስለሚለወጥ፣ አንድ ተማሪ በራሱ አዳዲስ መረጃዎችን የመፈለግና የመረዳት ፍላጎት እንዲኖረው ማድረግ ነው። ✍️  2. ለመሥራት መማር (Learning to Do) ዕውቀትን ወደ ተግባር መለወጥ ላይ ያተኩራል። ይህም ተማሪዎች የተማሩትን ነገር በተግባራዊ ሕይወታቸውና በሥራ ዓለም ላይ እንዲጠቀሙበት ያዘጋጃቸዋል። 🎯ዋና ዓላማ 🕯የሙያ ክህሎትን ማዳበር ብቻ ሳይሆን፣ እንደ ችግር ፈቺነት፣ ከሰዎች ጋር በቡድን የመሥራት ብቃት እና በሥራ ላይ የሚገጥሙ ተግዳሮቶችን የመቋቋም ችሎታን ማዳበር ነው።   🔑 ቁልፍ ነጥብ 👉 በአሁኑ ዘመን "ለመሥራት መማር" ሲባል በእጅ ከሚሠራ ሥራ (Manual Labor) ባለፈ፣ መረጃን የመተንተንና የፈጠራ ሥራዎችን የመሥራት ብቃትን ይጨምራል። ✍️ 3. አብሮ ለመኖር መማር (Learning to Live Together) ይህ አምድ በዘመናዊው ዓለም ውስጥ እጅግ አስፈላጊው እንደሆነ ይታመናል። ትኩረቱም በሰዎች መካከል ሰላምን፣ መቻቻልንና መግባባትን መፍጠር ነው። 🎯ዋና ዓላማ 🕯 የሌሎችን ታሪክ፣ ባህልና እሴት ማክበር፣ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት እና የጋራ ግቦችን ለማሳካት በጋራ መሥራትን መልመድ ነው።   🔑 ቁልፍ ነጥብ 👉 በትምህርት ቤት ውስጥ የሚከናወኑ የቡድን ሥራዎችና ውይይቶች ለዚህ አምድ ተግባራዊነት ትልቅ ድርሻ አላቸው። ✍️ 4. ለመሆን መማር (Learning to Be) ይህ አምድ የሰውን ልጅ ሁለንተናዊ ዕድገት (Physical, Intellectual, Emotional, and Spiritual) የሚመለከት ነው። 🎯ዋና ዓላማ 🕯 እያንዳንዱ ግለሰብ የራሱ የሆነ ነፃነት፣ የማመዛዘን ችሎታ፣ የሥነ-ምግባር ጥንካሬ እና ኃላፊነት እንዲኖረው ማድረግ ነው። 🔑 ቁልፍ ነጥብ 👉  ትምህርት የአንድን ሰው የተደበቀ ተሰጥኦ (Potential) አውጥቶ ለራሱና ለማኅበረሰቡ የሚጠቅም ሙሉ ሰው እንዲሆን መርዳት አለበት። ባጭሩ፦ ✍️✍️✍️✍️ እነዚህ አራቱ አምዶች እርስ በርሳቸው የተሳሰሩ ናቸው። ለማወቅ መማር  መሣሪያ ሲሆን፣ ለመሥራት መማር  ተግባር ነው፣ አብሮ ለመኖር መማር ማኅበራዊ መሠረት ሲሆን፣ ለመሆን መማር ደግሞ የሦስቱም የመጨረሻ ውጤት ወይም ድምር ነው። @Lifelong learner 🎯📌👇 Bloom's taxonomies of education 1.Cognitive domain (Knowledge/HEAD) 2.Affective domain (Attitude /HEART) 3.Psychomotor domain (Skill/HAND)

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 1 авг.515из jointvisionsuccess18

    በዛሬው ዕለት ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም በጆይንት ቪዥን ሰክሰስ አካዳሚ የ2018 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም ግምገማ ሪፖርት ቀርቦ የወተመህ ስራ አስፈፃሚ አባላት እና የት/ቤቱ ባለቤቶች በተገኙበት  ሰፊ ውይይት እና ግምገማ ተደረገ።

  • видео или голосовое, без подписи

  • በወላጅ ጥያቄ መሰረት የተማሪዎች ምዝገባ እስከ ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም ድረሰ ብቻ ተራዝመዋል።

  • 25 июл.1 0452

    видео или голосовое, без подписи

  • ቀን:- ሐምሌ  17/2018 ዓ.ም ለነባር ተማሪ ወላጆች በሙሉ:- 🔔🔔🔔🔔🔔🔔 የነባር ተማሪዎች የ 2019 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባ የሚጠናቀቅበት ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም እንደሆነ ይታወቃል። በዚህም መሰረት የምዝገባ ስዓት ነገ ቅዳሜ ፣  ሐምሌ 18/2018 ዓ.ም እስከ 6:00 እና ሰኞ፣ ሐምሌ20/2018 ዓ.ም እስከ 10:00 ብቻ ማስመዝገብ የምትችሉ መሆኑን በድጋሜ እናሳስባለን።  ከዚህ ቀን በኋላ ለሚፈጠር የቦታ ማጣት ችግር ት/ቤቱ ኋላፍነት የማይወስድ መሆኑን በጥብቅ ለማሳሰብ እንወዳለን።                                  ት/ቤቱ

  • ቀን:- ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም ለነባር ተማሪ ወላጆች በሙሉ:- 🔔🔔🔔🔔🔔🔔 በመጀመሪያ ሰላምና ጤና በያላችሁበት እንመኛለን። የነባር ተማሪዎች የ 2019 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባ ከጀመርን ሁለት ሳምንት ሆነናል። ስለዚህ እስከ አሁን ልጆቻችሁ ያላስመዘገባችሁ ወላጆች እስከ ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም ብቻ እንድታስመዘግቡ እያሳሰብን ከሐምሌ 21/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባልተመዘገቡ ነባር ተማሪዎች ምትክ በጊዜየዊ መዝገብ ላይ የመዘገብናቸውን አዳዲስ ተማሪዎች ለመመዝገብ ቃል የገባን ስለሆነ የምዝገባ ቀናቱን ባለመጠበቅ ምክንያት ለሚፈጠር የቦታ ማጣት ችግር ት/ቤቱ ኋላፍነት የማይወስድ መሆኑን በጥብቅ ማሳሰብ እንወዳለን።                                  ት/ቤቱ

JOINT VISION SUCCESS ACADEMY — tgindex