tgindex
አንድ እርምጃ

አንድ እርምጃ

Статистика

Media Company

Последний пост
25 июн. 2025 г.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
15 авг.
Подписчики
331
мало замеров
Замеров пока мало
Сутки
 
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
256
20 постов
Вовлечённость
77,3%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • https://youtu.be/7RKeRFsGEco

  • https://youtu.be/M2BD5CG1gNg

  • https://youtu.be/XKeq23zgioo

  • https://youtu.be/LpJDW9SwlmI

  • ሰበር ዜና! ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የውስጥ አካውንት 7.7 ቢልዮን ብር በላይ መዘረፉን ተገለጸ። EMS በዘገባ ይሄን ዝርፊያ ማን እንደፈፀመው ያለው ነገር የለም።

  • የኤርትራው የተቃዋሚ እንቅስቃሴ ብርጌድ ንሓመዱ፣ ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ አባላቶቹ ወታደራዊ ስልጠና መስጠት መጀመሩ ተሰምቷል። እንቅስቃሴውን የሚመሩት ግለሰቦች በአዲስአበባ ፅህፈት ቤት መክፈታቸው የተሰማው ከጥቂት በፊት ወራት ነበር። በዐቢይ አህመድ መንግሥት እንደሚደገፍ የሚነገርለት ይህ ቡድን፣ በየካቲት፣ 2017 ዓ.ም በአዲስአበባ የከፈተውን ቢሮ “ለወታደራዊ ማዕከላዊ ፅህፈት ቤትነት የመጠቀም ዕቅድ እንዳለው” ባሳለፍነው ሚያዚያ ወር ለቢቢሲ አማርኛ ገልፆ ነበር። ብርጌድ ንሓመዱ በቅርቡ በኢትዮጵያ በሁለት ቦታዎች ወታደራዊ ስልጠና መጀመሩን ዞብል ፖስት ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ወገኖች ሰምቷል። ቡድኑ ወታደራዊ ስልጠና የጀመረበት አንደኛው ቦታ፣ በአፋር ክልል የሚገኘው ልዩ ስሙ “መጋሊ” የተባለ ስፍራ ሲሆን፣ ሌላኛው ወታደራዊ ማሰልጠኛ ቦታ ግን ሚስጥራዊ እንዲሆን መደረጉ ተሰምቷል።

  • ይህስ ምን ይባላል! የሚሊሻና የፖሊስ አባላት የመብራት ትራንስፎርመሩን በጥይት ደብድበው እንዳፈነዱት ተሰማ! አሁን ከመሸ የደረሰን መረጃ! አፋብኃ በወሎ ላስታ አሳምነው ኮር ስር የሚገኘው ኃይሉ ከበደ ክ/ጦር ዛሬ ግንቦት 18/2017 ዓ/ም በዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን ሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ በሁለት አቅጣጫ ጥቃት ከፍቶ ከባድ ጉዳት ማድረሱን መዘገባችን ይታወቃል። ከአምደወርቅ ከተማ በቅርብ ርቀት በምትገኘው ልዩ ስሟ ጭላ ተብላ በምትጠራው ከተማ እና ከሰቆጣ 35km ርቀት ላይ በምትገኘው ሀሙሲት ተብላ በምትጠራው ከተማ በነበሩ የአገዛዙ ወታደሮች ላይ ነው የፋኖ አባላቱ ጥቃቱን የፈፀሙት። በዚህ ጥቃት ከባድ ኪሳራን ያስተናገዱት የአገዛዙ ወታደሮች፡ የፋኖ አባላቱ ኦፕሬሽኑን ፈፅመው አከባቢውን ለቀው ሲወጡ የከተማውን የመብራት ትራንስፎርመር በጥይት ደብድበው እንዲፈነዳ አድርገውታል ሲሉ የአከባቢው ነዋሪዎች በአይናቸው ያዩትን  መረጃ አድርሰውናል። "የሚሊሻና የፖሊስ አባላቱ የከተማዋን መብራት ትራንስፎርመር በጥይት ደጋግመው በመምታት እንዲፈነዳ አድርገውታል" ሲሉ የገለፁት የአከባቢው ነዋሪዎች፡ በአሁን ሰዓት በከተማዋ የመብራት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል ብለዋል። የፖሊስና የሚሊሻ አባላቱ ድርጊቱን ፋኖ ነው የፈፀመው በሚል ለከተማዋ ማሕበረሰብ የተናገሩ ሲሆን፡ ትራንስፎርመሩ ከሚሊሻ አባላት በተተኮሰ ጥይት ከጥቅም ውጭ ሲደረግ በቦታው የነበሩ ሰዎች ፋኖ ነው ያፈነዳው በሚል ብቻ እንዲናገሩ ከባድ ማስጠንቀቂያ ተሰቷቸዋል ነው የተባለው። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ወሎ (ቤተ-አምሓራ) ላስታ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን አሳውቋል።      ድላችን በተባበረ ክንዳችን!      የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ)      ግንቦት 18/ 2017 ዓ.ም

  • без подписи

  • ኢሳያስ በላይ ለምን ተገደለ? የአማራ ክልልን የሬዲዮ መገናኛ አውታር አቀናጅቶ ከተመለሰ ከሁለት ወር በኋላ አንድ ቀን ጧት 4:00 ሰዓት ላይ ቢሮ ከመግባቱ የኢንሳ የውስጥ ደኅንነት እና ጥበቃ ኃላፊ የኢሳያስን መታወቂያ ቀማው። በኢንሳ ተቋም ውስጥ የውስጥ ደኅንነት እና የጥበቃ አባል የሰራተኞችን መታወቂያ ቀምቶ ከወሰደ ቢሮ መግባት የተከለከለ ነው። ኢሳያስም ለምን መታወቂያው እንደተወሰደበት ቢሮ ገብቶ ኃላፊውን መጠየቅ አልቻለም። ከስራ እንዳሰናበቱት ቆጥሮ ሌላ ስራ ማፈላለግ ያዘ። ከወራት በኋላ አማራ ባንክ ተቀጥሮ ለሁለት አመታት ያህል በሙያው እየሰራ ባለበት ወቅት ሚያዝያ 23 ቀን 2016 ዓ/ም ከምሽቱ 2:30 የፌደራል ፖሊሶች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ትፈለጋለህ በሚል ይዘውት ወጡ። በማግስቱ ባለቤቱ እና የቅርብ ቤተሰቦቹ አዲስ አበባን ሲያካልሉ ውለው ማታ አዲስ አበባ ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ አገኙት። በምን ጠርጥረው እንዳሰሩትም እርሱም አላወቀም። ከሁለት ቀን በኋላ ከ14 ተጠርጣሪዎች ጋር ወደ አፋር ክልል ሰመራ ጉዞ ተጀመረ። ሰመራ ከተማ መግቢያው አካባቢ አንድ የግለሰብ ግቢ ውስጥ እንዲገቡ ተደርገው በዕለቱ ከምሽቱ 4:00 ሰዓት እስረኞቹ በየተራ እየተጠሩ በመርማሪዎች ይጠየቃሉ። "የኢሳያስ ተራ ደረሰ" ይላል ከኢሳያስ ጋር አብሮ የነበረ ስሙን እንዳይገለፅ የጠየቀን አንድ ወጣት። እኔ ይላል ይሄው ወጣት "አራት መርማሪዎች በየተራ እየተነሱ እውነቱን ተናገር እያሉ በጥፊ እና በእርግጫ እየደበደቡ አድክመውኛል፣ በዛ ላይ እጅግ ይሞቃል። መቆም አቅቶኝ ተዝለፍልፌ ወድቂያለሁ። እጅ እና እግሬን ይዘው በሩ ላይ ጣሉኝ። ኢሳያስን ይዘውት ሲመጡ ይታየኛል። ሊቢያ ውስጥ በአሸባሪዎች እንደ ታረዱት ወጣቶች ጀርባውን ጨምድደው ወደ ታች ደፍቀው ይዘውት ገቡ። እጁን ወደ ኋላ አዙረው በካቴና አስረውታል። ወደ ግርግዳው ፊትህን አዙር ሲሉት ይሰማኛል" በማለት የሚያስታውሰውን ምልልስ እንዲህ ያስረዳል። "ማነው ስምህ?" "ኢሳያስ በላይ" "የት ነው የተወለድከው?" "ጎንደር" "ለምን እንደ ታሰርክ ታውቃለህ?" "አላውቅም" "ምን አባህ ሆነህ ነው የማታውቀው?" ሌሎቹ እየደበደቡት አንዱ ይጠይቃል: "ለምንድን ነው የማታውቀው?" "አላውቅም! ከቤቴ ነው ይዘውኝ የመጡት" "ከፋኖዎች ጋር ምን ነበር ስታወራ የነበረው?" "ከማንም ጋር አውርቼ አላውቅም?" "ስልካችሁ እንዳይጠለፍ ምን አድርጉ ነው ስትላቸው የነበረው?" አሁንም የእርግጫ እና የጥፊ ድምፅ ይሰማኛል። "ይናገራል ቆይ" ሲል አንዱ ገልጋይ ሆኖ ተከሰተ። "በሕይወት መኖር ከፈለግህ ተናገር ካልሆነ አስከሬንህን እዚህ ነው በእሳት የምናቃጥለው" የእሱ ድምፅ አይሰማኝም "ልጆች አሉህ አይደል?" "ተናገር እንጂ!" እንዲናገር ተንጫጩበት፣ የእሱ ድምፅ አሁንም አይሰማም። አንዱ በምን እንደ መታው ባላውቅም ኢሳያስ "አአአአአአአአ ..... ብሎ ሲወድቅ ተሰማኝ። ከወደቀበት በእግራቸው ሲደበድቡት አንደኛው "አሁን ይናገራል ተውት" ብሎ አስቆማቸው። ኢሳያስ መሬት ላይ እንደ ተኛ ያቃስት ነበር። "ለፋኖ ስልካችሁ እንዳይጠለፍ ምን አድርጉ ብለህ እንደ ተናገርህ ካላወጣህ አስከሬንህን ለጅብ ነው የምንሰጠው፣ ልጆችህን ድጋሜ አታያቸውም" ሁለቱ መርማሪዎች የክፍሉን ሙቀት መቋቋም ያቃታቸው ይመስላል። ሲወጡ እኔ መኖሬንም ረስተው "ይሄን ነው በደንብ ጠይቁት ያለው ኮማንደር" ሲል ሰማሁት። "ማን ነበር ስሙ?" አንደኛው ጠየቀ "ኢሳያስ" አለው ሌላኛው አንደኛው መርማሪ የእስረኞቹን ክፍል ከፍቶ ሁለት እስረኞችን ይዞ መጣና "ይዛችሁት ግቡ" ብሎ አንጠልጥለው ክፍሌ ውስጥ አስገቡኝ። ኢሳያስ በላይ ምርመራ ክፍል ውስጥ አድሮ ጧት እንደ ጨርቅ ሰውነቱ ልሞ በእስረኞች ተደግፎ መጣ። ሙቀቱ እሳት ነው። የሚሰጠን ውሃ በቀን ግማሽ ሊትር ከአንድ ዳቦ ጋር ነው። ሁላችንም ተዳከምን። ወደ መጨረሻው ቀን ኢሳያስን እና እኔን በመኪና ራቅ ያለ ቦታ ይዘውን ሄዱ። እልም ያለ በረሀ ነው። ከመኪና አስወርደው ሁለት እጅ እና እግራችንን በካቴና አስረው "እዚህ በረሀ ላይ ጅብ ነው የሚበላችሁ። ማንም አይደርስላችሁም። እውነቱን ብትነግሩን ይሻላል" ሲል አንዱ መርማሪ ጠየቀን። እኔ ከማንም ጋር ተገናኝቼ እንደማላውቅ ነገርኩት። ኢሳያስ ደካክሞ ስለነበር የሚለው አይሰማም። እኔን መልሰው መኪናው ላይ አንስተው ጫኑኝ። ኢሳያስን ትተነው ሄድን። የተወሰነ ርቀት ከተጓዝን በኋላ እኔንም አውርደው ጥለውኝ ሄዱ። ሁለት እግሮቼ እና ሁለት እጆቼ በካቴና የታሰሩ በመሆናቸው በፍፁም መንቀሳቀስ አልችልም። ለመገላበጥ አያመችም እንጂ ከምርመራ ግቢው የተሻለ አየር አገኘሁ። ነፃነትም ተሰማኝ። ነገር ግን አውሬ ቢተናኮለኝ መከላከል እንደማልችል ሳስብ ደግሞ ስጋት ገባኝ። በግምት ከሌሊቱ 11:00 ሰዓት አካባቢ ሲሆን የመኪና ድምፅ ቀሰቀሰኝ። አንድ በማስክ እስከ አፍንጫው ድረስ የተሸፈነ መርማሪ ጋቢና ውስጥ ብቅ ብሎ በተኛሁበት ቁልቁል እየተመለከተ፣ "ጅብ አልበላህም?" ሲል አብሮት ያለው ሹፌር ሳቀ። ሁለት ፈርጠም ፈርጠም ያሉ ፖሊሶች አንስተው ማታ ከጣለችን ሽፍን ወታደራዊ ተሽከርካሪ ውስጥ ጣሉኝ። ትንሽ ከተጓዝን በኋላ ኢሳያስን አገኘነው። "ይሄም ሰውዬ አለ። የዚህ አገር ጅብ ምን ነካው? በአፉ እንድናጎርሰው ፈልጎ ነው?" ሲል ሰማሁት ለቃቅመው ወደ ምርመራ ካምፕ መለሱን። ከቀኑ 10:00 ሰዓት ሲሆን መርማሪዎቹ ኢሳያስን ጠርተውታል። እስረኛው ስለተዳከመ እና አቅም ስላነሰው እንደ በፊቱ አንዱ አንዱን ደግፎ መሄድ አልቻለም። ራሳቸው ፖሊሶች ሰቅስቀው አንስተው ይወስዱናል። ኢሳያስንም እንደዚሁ አድርገው ወደ ምርመራ ክፍል አስገቡት። ምርመራ ክፍል አስር ሰዓት ገብቶ 12:00 ላይ ይዘውት ወጡ። እሱ ከምርመራ ክፍል ሲወጣ እኛ ለሽንት ወጥተን ተገናኘን። ሆዱ አካባቢ ደም በደም ሆኗል። ከላዩ ላይ ውሃ የተደፋበትም ይመስለኛል። ልብሱ ሁሉ በስብሷል። እስከ ሱሪው ድረስ በደም ተነክሯል። ደም እና ውሃ ከሰውነቱ ይወርዳል። ፖሊሶቹ በር ላይ ስለጣሉት ዝልፍልፍ ብሎ ተኛ። ጠጋ ብዬ ሳየው ሆዱ ተቀዶ የውስጥ ክፍሉ ይታያል። ጠጋ ብዬ በእሱ በኩል አለፍኩ። መራመድ አቃተኝ። ኢሳያስ አልኩት። አልመለሰልኝም። የሚደበድቡን በተቆረጠ የፌሮ ብረት ነው። ብረቱ ጫፉ ላይ ሲቆረጥ ትንሽ ሰየፍ ያለ በመሆኑ እሱ ሁላችንንም ብዙ ቦታ እየቆረጠን ደም ፈሶናል። ብዙ ደም ስለፈሰሰን ሰውነታችን ገርጥቷል። ኢሳያስንም ያገኘው ይሄው ብረት ነው። ብረቱ ጫፉ ላይ ስለት እንዳለው ስለሚያውቁ የሚመቱን በስለቱ በኩል ነው። በኋላ መርመሪዎቹ ከምርመራ ክፍል ወጥተው ወደ ህክምና ልንወስደው ነው ገንዘብ አዋጡ አሉን። ከቤታችን ስንያዝ ኪሳችን ውስጥ የነበረችውን በሙሉ አሰባስበን ሰጠን። ይዘውት ወጡ። በማግስቱ እኛንም ወደ አዲስ አበባ ይዘውን ተመለሱ" ሲል የደረሰባቸውን ግፍ ለመሠረት ሚዲያ ተናግሯል። መርማሪዎቹ የኢሳያስን አስከሬን ለቤተሰቦቹ ሲያስረክቡ "ለማንም ቢሆን ታስሮ እንደነበር እንዳትናገሩ" ብለው የዛሬ ዓመት ግንቦት 7 ቀን አስከሬኑን አስረከቧቸው። ኢሳያስ በላይ የሁለት ልጆች አባትና ባለ ትዳር ነበር። መረጃውን ያጠናቀረው መሠረት ሚዲያ ነው።

  • እጅግ የሚዘገንን ለማንበብም አቅምን የሚጠይቅ የምርመራ ዘገባ እነሆ ልክ የዛሬ ዓመት በዚህ ወር በምርመራ ክፍል ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ስለተገደለው ኢሳይያስ በላይ የተሠራ የምርመራ ዘገባ ኢሳያስ በላይ ማነው ? ለስድስት አመታት ያህል በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ውስጥ ከፍተኛ የሳይበር ደኅንነት ባለሙያ ሆኖ አገልግሏል። በ2014 ዓ/ም የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እና የክልሉ ሰላምና ደኅንነት የሚጠቀምበት ወታደራዊ ሬዲዮ የመለያ ኮዱ በቀላሉ ተጋላጭ ሆኖ ተገኘ። ይህንን የሬዲዮ ትስስር እንደ አዲስ ማስተሳሰር ግድም ሆነ። የወታደራዊ ሬዲዮ ትስስሮች እንዲሁ በቀላሉ የሚከወኑ አይደለም። በዘርፉ ልምድ ያላቸው አለም አቀፍ ተቋማት ተወዳድረው በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር የሚጠይቁበት ስራ ነው። አገርን ለከፍተኛ ወጪ የዳረገ የሬዲዮ ግንኙነት መረብ እንዲሁ በቀላሉ የይለፍ ቃሉ ተሰብሮ ሚስጥሮች የሚባክኑ ከሆነ ደግሞ ሌላ የአገራዊ ደኅንነት ስጋት ነው። ይህ ስጋት በ2014 ዓ/ም በአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እና የሰላም እና ደኅንነት የሬዲዮ መገናኛ ላይ በግልፅ ታየ። ችግሩ እንዴት ይቀረፍ? በሚል ኢንሳ መፍትሄ ሲያፈላልግ ኢሳያስ በላይ በተቋሙ ውስጥ ያገኘውን አለም አቀፍ ልምድ በመውሰድ የክልሉን የሬዲዮ አውታር እንደ አዲስ ለማቀናጀት ሀሳቡን አቀረበ። ኢንሳ ሰባት አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን አዋቅሮ ኢሳያስን የቡድኑ መሪ አድርጎ ወደ አማራ ክልል ሸኘው። ቡድኑን በማስተባበር የአማራ ክልልን ከወረዳ ጀምሮ እስከ ዋናው ቢሮ ድረስ ያለውን የሬዲዮ ትስስር በዘመናዊ መልኩ አቀናጅቶ ለክልሉ መንግስት በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ አስረክቧል። ኢሳያስ ዛሬ በሕይወት ባይኖርም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እና የሰላምና ደኅንነት ቢሮ እስከ ወረዳ ድረስ የሚጠቀሙበት የሬዲዮ መገናኛ መረብ በዚህ ድንቅ ወጣት የተሳሰረ ነው።

  • без подписи

  • ፋኖ የአባቶቹን አደራ እንዳይበላ ሊጠነቀቅ እንደሚገባው አንድ የታሪክ ምሁር ገለፁ የፋኖን የትግል እንቅስቃሴ በቅርበት የሚከታተሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የታሪክ ምሁር እንዳሉት አባት አርበኞች እንደዛሬው የመገናኛ ቴክኖሎጅው ሳይዘምን፣ በቀላሉ ለመገናኘት ምቹ መንገድ ሳኖር፣ ዘመናዊ ትጥቅ እና ስንቅ ሳይዙ በአንድ ልብ ለአንድ አላማ ብቻ በቁርጠኝነት በመታገላቸው ውድ ህይወታቸውን ገብረው ለትውልዱ ነፃ ሀገር አስረክበዋል፣ የዛሬው ትውልድ ደግሞ የአባቶችን አደራ በመጠበቅና ፈለጋቸውን በመከተል በአንድነት ለነፃነቱ መታገል ታሪካዊ ግዴታው ነው ብለዋል። ከፋሽስት ጣሊያን ጋር የተፋለሙት ፋኖዎች ቤት ንብተታቸውን ትተው ዱር ቤቴ ያሉት ቅኝ ግዛትን በመፀየፍ ለነጭ አልገዛም፣ ባህል፣ ማንነታችንና እምነታችን አይበረዝም ብለው  በአንድነት መንፈስ  በመነሳታቸው ነው ያሉት የታሪክ ምሁሩ የዛሬዎቹ አማራንም ኢትዮጵያንም ከዘረኛ እና አንባገነን ስርአት ለማላቀቅ የሚታገሉት ፋኖዎችም የተነሱበትን አላማ ከግብ ለማድረስ እኔነትን አስወግደው ለእኛነት በአንድነትና በህብረት ለአንድ አላማ በፅናት መቆም እንደሚገባቸው ተናግረዋል። ነፍጥ አንስቶ ጫካ የገባ ሀይል ሊያሳስበው የሚገባው ነፍጥ ለማንሳት ምክንያት የሆነው ጉዳይ መልስ ማግኘቱና አለማግኘቱ እንጅ ስለሚይዘው ስልጣን አይነትና እርከን መሆን እንደሌለበት አፅንኦት ሰጥተው የተናገሩት ምሁሩ የአባት አርበኞችን ቀን ስናስብ የፋኖ ሀይሎች ቅድሚያ አንድነታቸው ላይ መስራት እንዳለባቸው ደግመው ደጋግመው እንዲያስቡበት የአባቶቻችንን የትግል አላማ ፅናት በማስታወስ እና ለሀቀኛ እና ወንድማማችነታዊ ህብረት እንዲተጉ ግፊት በማድረግና በማበረታታት ነው ሲሉ አብራርተዋል። በአጭር ጊዜ የአሁኑ ትውልድ ፋኖ ልዩነቱን አጥብቦ አንድ ጠንካራ ሀይል ሆኖ እንደሚመጣ ሙሉ እምነት እንዳላቸውም የታሪክ ምሁሩ ተናግረዋል።

  • የግፍ እስረኞቹ ጥቃት ተፈጸመባቸው አቶ ክርስቲያን ታደለ እና አቶ ዮሐንስ ቧያሌው በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ጥቃት ተፈፀመባቸው። ሚያዚያ 22 ቀን 2017 ዓ/ም የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እስረኞች ወደ ማደሪያቸው ከገቡ በኋላ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ላይ ቀይ ቦኔት የጫኑ የፌደራል ፖሊሶች ቁልፍ ሰብረው ገብተው አቶ ክርስቲያን ታደለን እና አቶ ዮሐንስ ቧያሌውን ከእስር ቤታቸው እንዳስወጧቸው እና እስከ ሌሊቱ 7:00 ሰዓት ድረስ ሜዳ ላይ አስተኝተው እንዳሳደሯቸው ተገልጿል። በተመሳሳይ ዶ/ር ወንደሰን አሰፋ፣ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፣ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ ፕሮፌሰር መዓረጉ ቢያበይን እና ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው ይሄው ድርጊት የተፈፀመባቸው መሆኑን አርብ ሚያዚያ 24 ቀን 2017 ዓ/ም ለፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርበዋል።  "ቀይ ቦኔት የጫኑ የፌደራል ፖሊሶች ምሽት 12:00 ሰዓት  በሩን በኃይል ከፍተው ከገቡ በኋላ ሁላችንንም እጃችንን ወደ ላይ እንድናደርግ አዘው ሜዳ ላይ በሰልፍ አቁመውን በመሳሪያ ሲያስፈራሩን ነው ያደሩት" ሲሉ ነው ለፍርድ ቤቱ የገለፁት። "ቀደም ሲል በምርመራ ወቅት ድብደባ የፈፀሙብን የመንግስት ሹማምንት ከሁለት ዓመት በኋላ የቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን አጥር ጥሰው፣ የተኛንበትን ቤት በር በኃይል ሰብረው እስከ ሌሊት 7:00 ሰዓት ድረስ  ሜዳ ላይ አሰልፈው አሳድረውናል። ሕይዎታችን አደጋ ላይ መሆኑን  ሕዝባችን እንዲያውቅልን" ሲሉ አሳስበዋል። አቶ ዮሐንስ ቧያሌው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ ከአንድ አመት በፊት በአዋሽ አርባ ወታደራዊ እስር ቤት በነበሩበት ወቅት የከፋ የጤና መታወክ ገጥሟቸው እንደ ነበር ይታወቃል። በመሆኑም ጤናቸው ገና ሳያገግም በድጋሜ ሜዳ ላይ ተሰልፈው እንዲያድሩ መደረጉ ለባሰ የጤና እክል ተጋልጠዋል ተብለዋል። የፌደራል ፖሊሶች የማረሚያ ቤቱን አጥር ሰብረው ለምን እንደገቡ እና በሽብር የተጠረጠሩ እስረኞችን ለምን ከክፍላቸው አስወጥተው ሜዳ ላይ እንዳሳደሯቸው የታወቀ ነገር የለም ሲል መሰረት ሚዲያ ዘግቧል።

  • ዛሬ ባህርዳር ብርጌድን ለማፈን በ5 አቅጣጫ የመጣው የጠላት ሀይል አልሳካለት ብሎ ሲመለስ የጨፈጨፋቸው ንፁሀን ስም ዝርዝር፦ ባህርዳር ዙሪያ ወረዳ፦ 1. ሸጋው ንግሩ - ወጅር ወልደመንታ ቀበሌ - እድሜ 2. ⁠ታዴ ሞኘ -  ወጅር ወልደመንታ ቀበሌ - እድሜ 3. ⁠⁠አወቀ ጣሰው - ወጅር ወልደ መንታ ቀበሌ - እድሜ55 4. ⁠መንጌ ይርዳው - ወጅር ወልደ መንታ ቀበሌ - እድሜ54 5. ⁠ጋሻ እውነቱ - የግንድ ዘሞቻ ቀበሌ - እድሜ42 6. ⁠ጌጡ ጥላሁን - የግንድ ዘሞቻ ቀበሌ - እድሜ42 7. ⁠ፋሲካው አወቀ - ወጅር ወልደመንታ ቀበሌ-እድሜ25 8. ⁠ይሁን መንጌ - ወጅር ወልደመንታ ቀበሌ - እድሜ20 ይልማና ዴንሳ ወረዳ፦ 1. ምህረቱ ቻሌ - አንጋር ቀበሌ - እድሜ30 2. ⁠አትርሴ ጉዳይ - አንጋር ቀበሌ- እድሜ33 3. ⁠⁠ውበት አለባቸው - አንጋር ቀበሌ- እድሜ28 4. ⁠አለምነው አለኸኝ - አንጋር ቀበሌ - እድሜ35 5. ⁠⁠ ብርሀኑ ነጋ - አግታ ቀበሌ - እድሜ33 6. ⁠አለልኝ ታፈረ - አግታ ቀበሌ - እድሜ51 7. ⁠አግታ ኢየሱስ ቤተክርስትያን - 03የአብነት ተማሪዎች ደራ ወረዳ 1. ቸሬ ጌጡ - ሜጮ ቀበሌ - እድሜ14 2. ⁠ተሸራሽ ዘሬ (ከባድ ቁስለኛ) - ሜጮ ቀበሌ - እድሜ12 3. ⁠ንግሬ ሙጨ በላቸው (ከባድ ቁስለኛ) - ደስኳ ቀበሌ - እድሜ16

  • ኢትዮጵያ በአህዮች ብዛት ዓለምን ትመራለች! በዓለም ላይ 50 ሚሊዮን አህዮች እንዳሉ የ2025 ሪፖርት ያመለክታል። በኢትዮጵያ 10 ሚሊዮን አህዮች እንደሚገኙ ተገልጿል። ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር ብዛቱ ጨምሯል። በዓለማችን ትንሽ አህዮች ያሉባት ሀገር ሱሪናሜ ስትሆን ሰባት አህዮች ብቻ ይገኛሉ። በአሜሪካረ 52ሺህ አህዮች ይገኛሉ። 1ኛ ኢትዮጵያ 10.6 ሚሊዮን 2ኛ ሰሜን ሱዳን 7.6 ሚሊዮን 3ኛ ፓኪስታን 5.8 ሚሊዮን 4ኛ ቻድ 4.6 ሚሊዮን 5ኛ ሜክሲኮ 3.3 ሚሊዮን

  • без подписи

  • без подписи

  • ሰበር ዜና‼️ 5ኛ ክ/ር ቡሬ ዳሞት ብርጌድ ዘመነ ካሴ ሻለቃ ዛሬ በጧቱ ቀንደኛ የአገዛዙ አገልጋይ  የአድማ መከላከል አዛዡን ጨምሮ ከ10በላይ ሚኒሻ አስወግዳለች ሲሉ ምንጮች ለቢዛሞ ሚዲያ ገልጸዋል። መጋቢት 03/2017ዓ.ም

  • የፖለቲካ እስረኛ መንበር አለሙ ዛሬ በአገዛዙ ፍርድ ቤት የተናገረው ያለ ፍትህ በአገዛዙ ከታገትን 2 ዓመት አልፎናል። የተከሰስነው ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድ ተንቀሳቅሳችኋል ተብለን ነው። በሚገርም ሁኔታ ግን የዜጎችን የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት ህገ-መንግስታዊ መብት በግላጭ እየጣሰ ያለው የአገዛዙ ምልምል ካድሬ(ዐ.ህግ) ያለ ከልከይ ፍትህን ነፍጎን ለ2 ዓመት ዐግቶን አልረካ ብሎ እየቀጠለ ነው። *** የአገዛዙ ካድሬ ዐ.ህጎች ምስክሮችን ማምጣት ያልቻልነው በሰላም መደፍረስና መንገድ ስለሚዘጋ ነው የሚል ይደሰኩራሉ። ለመሆኑ አገዛዙ ሰሞኑን አማራ ክልል ከሁሉም አካባቢ የተውጣጡ የብልፅግና ታማኝ አባላት፣ ወጣትና ሴት ሊግ የድርጅት አባሎቹን በማደናገሪያ መሳሪያው የምክክር ኮሚሽን ባህርዳር እያወያየሁ ነው በማለት አገዛዙ ልሳኔ በሚላቸው የቴሌቪዥን መስኮቶቹ ነግሮናል። አረ ለመሆኑ አገዛዙ በመቶወች የሚቆጠሩ ታማኝ አባላቱን ለድንግርግር ኮሚሽን ወደ ባህርዳር አጓጉዞ ሰብስቦ ማወያየት ከቻለ በኛ ላይ ይመሰክራሉ ብሎ ያሰለጠናቸውን ቀሪ  50 የከሚሴ ሸኔ አባላት ለምስክርነት ማቅረብ ለምን ተሳነው? ዐቃቢ ህግ ይሄን ቀልድ የሚቀለደው፣ ፍትህን እየቀበረ ያለው፣ ችሎቱን ጭምር እየመራ ያለው፣ በዳኞች ይሁንታ ነው፣ ስለሆነም ችሎቱ ዐ.ህግን ሀይ ሊለው ይገባል? ገለልተኛ ሁኖ ይዳኘን እሱ የማይሆን ከሆነ ግን ''ዳኛውም ዝንጀሮ መፋረጃው ገደል ከምን ላይ ተቀምጦ ይነገራል በደል፡" የሚለውን የፋሲል ደመወዝ ዘፈን ጋብዘናችሁ ከነ አካቴው ፍርድ-ቤት የምንቀር መሆናችን ልንገልፅላችሁ እንገደዳለን!

  • ፋኖን ትደግፋለህ ተብሎ ቂሊንጦ ማጎሪያ ታስሮ የነበረው ግለሰብ በፍርድ ቤት 300 ሺህ መቶ ብር ዋስትና ከፍሎ እንደወጣ መልሶ በብልጽግና ቡድን ታፈነ  በሽብር ወንጀል ተጠርጥሮ  በቂሊንጦ ለአስር ወራት ያህል በእስር ላይ የቆየው ሚካኤል መላክ የተባለው ግለሰብ  አሻንጉሊት የከፍተኛው ፍርድ ቤት በ300 ሺህ ብር እንዲፈታ ወስኖ ነበር ይላሉ ቤተሰቦቹ።  ይሁን እንጂ ተከሳሹ የተጠየቀውን የዋስትና ገንዘብ አስይዞ ዛሬ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሲፈታ በር ያልታወቁ ሰዎች  አፍነው ውሰደውታል ብለዋል። "በር ላይ ጠብቀው በኃይል ወደ መኪናቸው ውስጥ አስገቡት" ሲሉ የነገሩን  አንድ  የቅርብ ቤተሰብ ነን ያሉ  የዐይን እማኝ አፍነው ከወሰዱት ሰዎች መሀል የተከሳሹን ክስ የያዘው ናትናኤል ስንታየሁ የተባለው ዓቃቢ ሕግ አብሮ ነበር ሲሉም  ገልፀዋል። በተለያዩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያዎች እና በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ማረፊያ ቤቶች ብንጠይቅም አድራሻውን ልናገኝ  አልቻልንም ሲሉ አክለው ተናግረዋል። አቶ ሚካኤል መላክ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰውን ፋኖን  በሚዲያ ታግዛለህ በሚል ከ2016 ዓ/ም ሰኔ ወር ጀምሮ ለአስር ወራት ያህል በቂሊንጦ ማጎሪያ በእስር ላይ ቆይቷል። ቀደም ሲል በ2011 ዓ/ም አዲስ አበባን ከአዲስ አበቤ ውጭ ያለ ሰው ሊመራት አይገባም በማለት  ወጣቶችን አደራጅተሀል ቀስቅሰሀል እና ስልጠና ሰጥተሀል በሚል  ለወራት ያህል በእስር አሳልፎ ነበር። ዘገባው የመሠረት ሚዲያ ነው።