tgindex
በኩር ጋዜጣ Bekur Newspaper

በኩር ጋዜጣ Bekur Newspaper

Статистика

የሰኞ ጋዜጣዎ

Последний пост
12 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
12
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
4 880
0 за 4 дн.
Сутки
−1
−0,02%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
340
20 постов
Вовлечённость
7,0%
к подписчикам
Постов в день
1,7
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
272
1/48двое суток
311
1/72трое суток
336

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • без подписи

  • “የደን ስራ ተስፋን መትከል ነው”   የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ በስፋት እየተተገበረ የሚገኝ ብሔራዊ ንቅናቄ ነው። ይህ መርሃ ግብር በአማራ ክልል በምን መልኩ እየተመራ እንደሚገኝ፣ የችግኝ መጽደቅ ምጣኔው ምን ደረጃ ላይ እንዳለ፣ ዘርፉ ስለሚፈጥረው የስራ እድል እና ስለሚያጋጥሙት ተግዳሮቶች ከአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  ከአቶ እስመለዓለም ምህረት ጋር ቆይታ አድርገናል።   አቶ እስመለዓለም ምህረት በደን ሳይንስ ሁለተኛ ዲግሪ አላቸው።  ሙሉ የስራ ዘመናቸውን በተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ ያሳለፉ እና እያሳከፌ የሚገኙ  ባለሙያ ናቸው። ከወረዳ እስከ ክልል ድረስ ያገለገሉ አንጋፋ ባለሙያ እና መሪ ናቸው። የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ቅድመ ዝግጅት ምን እንደሚመስል በማብራራት ቢጀምሩልን? የአረንጓዴ አሻራ ስራ የአንድ ወቅት ሳይሆን የዓመቱን ሙሉ ስራ የሚጠይቅ ነው። ለምሳሌ እንደ ጽድ፣ ወይራ እና ዝግባ ያሉትን ለቀጣይ ዓመት የሚተከሉ ችግኞችን ገና ከሐምሌ ጀምረን ማዘጋጀት እንጀምራለን።   የእኛ ትልቁ መርህ “እቅድ ከታች ከማህበረሰቡ መነሳት አለበት” የሚል ነው። ህብረተሰቡ ተወያይቶበት የሚተከለውን የችግኝ አይነትና ቦታ ስለሚለይ፣ እቅድ ለማውጣት ብቻ እስከ ሶስት ወር ተኩል ይወስድብናል። ቦታን ስንለይ የቦታውን ባለቤት (ግለሰብ፣ ቡድን ወይም ቀበሌ) አብረን እንለያለን። በመቀጠል እንደ አየር ንብረቱ (ደጋ፣ ወይና ደጋ፣ ቆላ) ተስማሚ የሆኑ ችግኞችን በማፍላት እና ጉድጓድ በማዘጋጀት ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ስራ ስንሰራ ከርመናል።   (መሰረት ቸኮል) በኲር የነሐሴ 4  ቀን 2018  ዓ.ም ዕትም ሙሉን በዚህ ሊንክ ገብተው ያንብቡ! https://ameco.et/bekur/19427/

  • без подписи

  • አባ ሻንቆ   የወሎው ንጉሥ ሚካኤል (በፈረስ ስማቸው አባ ሻንቆ) በኢትዮጵያ የታሪክ ማኅደር ውስጥ በሃይማኖታዊ ማንነታቸው፣ በታዋቂው የዘር ሐረጋቸው እና በታላቅ የጦር መሪነታቸው ጉልህ አሻራ ያሳረፉ ታላቅ መሪ ናቸው። የሕይወት ታሪካቸው እና የታሪክ አሻራቸው ከእስልምናው ዓለም መነሻ እስከ ሰሎሞናዊው ሥርወ-መንግሥት መገናኛ ድረስ ሰፊ ታሪካዊ ይዘት አለው።   ንጉሥ ሚካኤል ጥር 27 ቀን 1842 ዓ.ም ነበር የተወለዱት፡፡ በኢትዮጵያ በተለይም በወሎ ባላባቶች ባህላዊ የታሪክ አተራረክ ውስጥ ንጉሥ ሚካኤል የነብዩ መሐመድ 38ኛ የዘር ሐረግ እንደሆኑ በስፋት ይነገራል። በወሎ እስላማዊ ሥርወ-መንግሥት ማለትም በመሐመዶ ሥርወ-መንግሥት ማኅደር መሠረት የንጉሡ የትውልድ ሐረግ በቀጥታ ከነብዩ መሐመድ ልጅ ከፋጢማ እና ከባለቤቷ ከዐሊ ኢብን አቢ ጧሊብ ይነሳል።    ይህ የዘር መስመር በባህል ደረጃ ትልቅ ክብር እና ቅቡልነትን ያሰጣቸው ነበር። ዘመናዊ የታሪክ ምሁራን በሰባተኛው ክፍለ ዘመን በኖሩት በነብዩ መሐመድ እና በ19ኛውክፍለ ዘመን በኖሩት በንጉሥ ሚካኤል መካከል ያለውን የአንድ ሺህ ሶስት መቶ ዓመታት ልዩነት በማስላት 38ኛ ትውልድ የሚለው ቁጥር ጥቂት የትውልድ ክፍተቶች ሊኖሩት እንደሚችል ቢናገሩም ይህ ትረካ በወቅቱ የወሎን መሪዎች ታላቅነት እና ክብር ለማሳየት ትልቅ የታሪክ ሰነድ ሆኖ ያገለግላል።   እዚህ ላይ ማስታወስ የሚገባው በሰባተኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያዎቹን ሙስሊም ስደተኞች በመቀበል ከነብዩ መሐመድ ጋር በቀጥታ የተገናኙት የአክሱሙ ንጉሥ ነጃሺ ሲሆኑ ንጉሥ ሚካኤል ግን በዘር ሐረግ የሚገናኙት የወሎው መሪ መሆናቸውን ነው።   (ቢኒያም መስፍን) በኲር የነሐሴ 4  ቀን 2018  ዓ.ም ዕትም ሙሉን በዚህ ሊንክ ገብተው ያንብቡ! https://ameco.et/bekur/19403/

  • без подписи

  • የዝዋይ ሐይቅ   በኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ መካከል ከአዲስ አበባ በስተደቡብ 162 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው የሚገኘው -የዝዋይ ሐይቅ፡፡ ሐይቁ ቀደም ብሎ የዝዋይ ሐይቅ ይባል ነበር - በቅርበት የምትገኘው ዝዋይ ከተማን መነሻ አድርጐ፤ አሁን ላይ ከተማዋ ባቱ ሐይቁም የደምበል ሐይቅ የሚል ስያሜ መያዛቸውን ድረገፆች አስነብበዋል፡፡   የኃይቁ ስፋት 434 ኪሎ ሜትር ስኩዌር ተለክቷል፡፡ ሐይቁን በደቡብ ምስራቅ  የካታር ወንዝ፣ በሰሜን ምእራብ አቅጣጫ የመቂ ወንዝ ይመግቡታል፡፡  ከሐይቁ የሚወጣው ብቸኛ ወንዝ ደግሞ የቡልቡላ ወንዝ ነው፡፡ በሐይቁ መካከል ቱሉ ጉዶ፣ ፀዳቻ፣ ገሊላ፣ ፉንዱሮ እና ደብረ ሲና  የተሰኙ  ደሴቶች  ይገኛሉ፡፡ ደሴቶቹም የዛዬ ጐሳ መኖሪያ ናቸው፡፡ የዝዋይ ሐይቅ ለባቱ እና መቂ ከተማ ኗሪዎች የገቢምንጭ ነው፡፡ አርሶ አደሮች አትክልት በማምረት  ይተዳደራሉ -ከሐይቁ ውኃ በመሳብ፡፡   ሐይቁ አእዋፍ መመልከት ለሚሹ ጎብኚዎች ተመራጭ ነው፡፡ “ስቶርክ”ወይም አባኮዳ የተሰኘው ግዙፍ የወፍ ዝርያ ዓሳ ለመያዝ ሲሽቀዳደም ማየት ለጐብኚዎች ትልቅ ሀሴት ይፈጥራል፡፡ የሐይቁን ዙሪያ ዓሳ አስጋሪዎች እና ዓሳ ጥብስ ሻጮች ያደምቁታል፡፡ ከአባኮዳ በተጨማሪ “ዳርትስ፣ ሄሮይንስ ፣ ፔሊካን” የመሳሰሉት ዓእዋፍት የሐይቁ ጌጦች ናቸው፡፡   የዝዋይ ሐይቅ በ2018 እ.አ.አ በዩኔስኮ ተመዝግቧል፡፡ በሐይቁ ዙሪያ ለአበባ ልማት 700 ሄክታር መሬት በመሰጠቱ በውኃ መሳቢያ ሞተር በቀን ከ115517 ሊትር መውጣቱ ተፅእኖ አድራሽ ሆኗል፡፡ በቅርበት የሚገኘው የመጠጥ ውኃ ማሸጊያ ኢንድስትሪም ሌላው  የሐይቁን ውኃ በመሳብ ተጠቃሚ ነው፡፡ እነዚህ እና መሰሎች የሚያደርሱት ተፅእኖ በ70 ዓመታት ውስጥ ሐይቁን ሊያደርቁ ይችላሉ ተብሎም በስጋትነት ተቀምጧል፡፡   በመጨረሻም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በባለቤትነት እና በተቆርቋሪነት ስሜት መገልገል ፣ መጠበቅ እንደሚገባቸው ነው በማጠቃለያነት የሰፈረው- በድረ ገፆች፡፡ ለዘገባችን በመረጃ ምንጭነት ብሪሊያንት ኢትዮጵያ፣ ሀስቲኪንግ እና ስኘሪንግስ-አርሲሲ ዶት ኦርግ ድረ ገፆችን ተጠቅመናል፡፡   (ታምራት ሲሳይ) በኲር  የነሐሴ  4  ቀን 2018 ዓ.ም  ዕትም

  • без подписи

  • ስሜትን መግለፅ የቻለው የሮቦት የፊት ገፅ   በቻይና “ኤሄድ ፎርም” የተሰኘ ኩባንያ በሰው እና ሮቦት መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ጥቃቅን እንቅስቃሴዎችን እና የፊት አገላለፆችን በሞተር በሚሰራ የሮቦት ጭንቅላት ሲከውን ለእይታ ማብቃቱ በርካቶችን ማስደመሙን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ አስነብቧል፡፡ በ2024 በኒውዮርክ በሚገኘው የኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ በፈጠራ ምህንድስና ትምህርት የተካነው ዩሀንግሁ “ብሬክዳውን ዘቤሪዬር” እንቅፋትን መሻገር በሚል በቅርቡ የሰራውን የሮቦት ምስል ለእይታ አብቅቷል፡፡   “ኤም 1” በሚል የተነደፈው የሮቦት ከአንገት በላይ ምስል የሰውን እንቅስቃሴ እና የሰሜት ለውጥ ማመላከት የቻለ ነው ተብሎለታል፡፡ይህም በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት በመታየቱ ብዙዎችን አስደምሟል፡፡የአንገት በላይ ምስሉ በውስጡ በጥቃቅን የኤሌክትሪክ ክሮች ረቂቅ ስሜት እና እንቅስቃሴን ማሳየትም ችሏል፡፡   የሮቦት ጭንቅላቱን ለመስራት ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ግድ በማለቱ ዋጋው እስከ 150 ሺህ ዶላር እንደሚደርስ ነው ድረ ገጹ ያሰፈረው፡፡ “ኤሄድ ፎርም” ኩባንያ በቅርቡ “ኤም 1”ን ለማሻሻል እና ከከንፈር እንቅስቃሴ እና ድምፅ ጋር የተቀናጀ እምርታ ለማሳየት  መዘጋጀቱ  ነው  በማጠቃለያነት ለንባብ የበቃው፡፡    (ታምራት ሲሳይ) በኲር  የነሐሴ  4  ቀን 2018 ዓ.ም  ዕትም

  • без подписи

  • በመኖሪያ ቤት ውስጥ የተገኘው ድብ   በአሜሪካ ኮሎራዶ የላቭላንድ ቀጣና ኗሪዋ ድመታቸው ከቤት  ውጪ እንድትንቀሣቀስ ከፍተው በተዉላት በር ድብ ገብቶ ፊት ለፊት መፋጠጣቸውን  ናይን ኒውስ ድረ ገጽ ባለፈው ሳምንት ለንባብ አብቅቶታል፡፡   ሊን ፊልድማን የተሰኙት ሴት ከቀናት በፊት የኮሎራዶ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣናት በቀጣናው በተከሰተው ድርቅ የዱር እንስሳት በተፈጥሯዊ መኖሪያቸው የሚበሉት በማጣታቸው ወደ ሰዎች መኖሪያ ሊገቡ እንደሚችሉ እና ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ማሳሰቡን አስታውሰዋል፡፡   ሊን ፊልድማን ቀደም ባሉት ጊዜያት መኖሪያ ቤታቸው በኩሬ አቅራቢያ በመሆኑ አልፎ አልፎ የዱር እንስሳት በግቢያቸው ይመለከቱ ነበር፡፡ በእለቱ ወደ ቤታቸው ዘልቀው መተላለፊያውን ሲመለከቱ  ግን ከድቡ ጋር ይፋጠጣሉ፡፡ ድብ ሲያዩ የመጀመሪያ ጊዜያቸው በመሆኑም መደናገጣቸውን አልሸሸጉም፡፡   ድቡን እንደተመለከቱት የተራበ አለመሆኑን ተገንዝበዋል፤ ጀነን ብሎ ወደ ሚቀጥለው ክፍል ሲገባም በቀጥታ ወደ ስልካቸው አምርተው ለፖሊስ 911 የድረሱልኝ ጥሪ ያሰማሉ፡፡ ኗሪዋ ድቡ በቤታቸው ውስጥ እንዳለ ፎቶ ግራፍ ማንሳት አልቻሉም ነበር፡፡ ጐረቤቶቻቸው ግን ውጪ ድቡን ባዩበት ወቅት በቪዲዮ መቅረጻቸውን ኋላ ላይ ተረድተዋል፡፡   የርዳታ ጥሪ የተደረገለት የፖሊስ ጣቢያም አባላቱን ልኮ በቦታው እንደደረሱ           ድቡ ከአካባቢው መራቁን ለሊን ፊልድማን አስረድተዋቸዋል፡፡ ጥቂት ቆይተው ሊንድ ማን ዙሪያቸውን ሲያማትሩ ለድመቷ የቀረበላት ምግብ ሙሉ በሙሉ ተበልቷል፡፡ የኮሎራዶ የፓርክ እና የዱር እንስሳት ጥበቃ ቃል አቀባይ ካራቫን ሁስ ድቦች ለኃይል ምንጭ የሚያስፈልጋቸው የምግብ መጠን በርካታ በመሆኑ ትርፍራፊ፣ የሚጣል ተረፈ ምግብ ፍለጋ በሰዎች መኖሪያ ቀጣና እንደሚዘልቁ  ነው ያስታወቁት፡፡   (ታምራት ሲሳይ) በኲር  የነሐሴ  4  ቀን 2018 ዓ.ም  ዕትም

  • без подписи

  • በረራ አራዛሚው አዲስ ርምጃ   ተመራማሪዎች በድሮን ላይ ጨረር ተቀባይ ክፍል በመግጠም በዓየር ላይ ባትሪውን ኤሌክትሪክ ኃይል በመሙላት የበረራ ጊዜውን ማራዘም እንደሚቻል  መገንዘባቸውን ዘናሽናል ኒውስ ድረ ገጽ ሰሞኑን አስነብቧል፡፡ እስከ አሁን በገመድ አልባ ስልክ፣ ሰዓት… ኃይል  መሙላት ቢቻልም ድሮንን ለመሙላት መሬት ማረፍ ግድ ሆኖ ቆይቷል፡፡   አሁን ግን በቻይና የሲቪል አቪዬሽን ዩኒቨርስቲ ተመራማሪው ጂያን ሁዋ ሀን ረዘም ላለ ጊዜ ለደን ቁጥጥር፣ ለአደጋ ክትትል እና ቁሳቁስ አቅርቦት… ለሚሰሩ ድሮኖች ችግር ለነበረው የኃይል አቅርቦት መፍትሄ ማግኘታቸውን ነው ያበሰሩት፡፡ በአዲሱ ግኝታቸው “ፔሮብስኪት” ንብብር፣ የካልሺየም ማእድንን በመገልገል የጨረር ኃይሉን ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል መቀየር ይቻላል ነው ያሉት - ተመራማሪው፡፡ ኃይል መሙያው የሚገኝበት የድሮኑ ክፍል በጨረሩ ሙቀት እንዳይጐዳም ማቀዝቀዣ ንብብር መግጠም እንደሚቻል ነው ያሰመሩበት፡፡ በጨረር ከተቋተው የብርሃን ኃይል 38 ነጥብ 49 በመቶውን ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል መቀየር መቻሉንም አረጋግጠዋል፤ የተቀየረው ኃይልም ድሮኑን የማንቀሳቀስ አቅም መፍጠሩን ተመራማሪዎቹ አስታውቀዋል፡፡   ኃይል በመሙላቱ የሙከራ ሂደት በጨረር ኃይል መቀበያው በኩል ያለው የድሮኑ ክፍል ከ80 እስከ 90 ዲግሪ ሴልሺየስ መሞቁን ነው የተገነዘቡት፡፡ ይህንን ለመቆጣጠርም የሙቀት መከላከያ ጥቃቅን “ክሪስታሎች” አስገብተው በማቀዝቀዝ አፈፃፀሙን ማስተካከል ችለዋል− ተመራማሪው ጂያን ሁዋ ሀን እንዳብራሩት፡፡ በመጨረሻም ከቤተ ሙከራ ወጥቶ በአስተማማኝ መልኩ መስራት እንደሚችል ለማረጋገጥ ኃይል የመሙላቱ ተግባር ቀለል ባሉ ድሮኖች እንደሚሞከር ነው ያደማደሙት -ተመራማሪው፡፡   (ታምራት ሲሳይ) በኲር የነሐሴ  4  ቀን 2018 ዓ.ም  ዕትም

  • без подписи

  • የነፍስ ጩኸት   “ብሉዝ” የሚለው ስም የመጣው “In the Blue Devils” (በከባድ ትካዜ እና ጭንቀት ውስጥ መሆን) ከሚለው ዘይቤያዊ አባባል እንደሆነ ይነገራል። ባሪያዎቹ መከራቸውን እና ሰብአዊ ክብራቸውን ማስጠበቂያ መንገድ አድርገው ጊታር፣ ባንጆ እና ሃርሞኒካ  በመጠቀም የነፍሳቸውን ጩኸት በዜማ ቀረፁት።   ብሉዝ ሙዚቃ የጥሪ እና መልስ ስልት ይከተላል።  ድምፃዊው አንድ ስንኝ ሲናገር፣ ጊታሩ ወይም ሃርሞኒካው መልስ  ይሰጣል። ጊታሩ እንደ ሁለተኛ ዘፋኝ ሆኖ ያሰማል፤ ይቃሰታል፤ ይጮሃል። አንዳንድ ጊዜ ከዘፋኙ በላይ ጊታሩ ልብን ሰርስሮ የመግባት አቅም አለው።   (አቢብ አለሜ) በኲር የነሐሴ 4  ቀን 2018  ዓ.ም ዕትም ሙሉን በዚህ ሊንክ ገብተው ያንብቡ! https://ameco.et/bekur/19381/

  • без подписи

  • без подписи

  • የማይበጠሰዉ ፍቅር ከነሐሴ 1 እስከ 7 የሚከበረው የዓለም የጡት ማጥባት ሳምንት በ2026 ለ35ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ28ኛ ጊዜ እየተከበረ ነው። ዓለም ጤና ድርጅት (WHO) እና ዩኒሴፍ (UNICEF) ጡት ማጥባት ለሕፃናት የተሟላ ምግብ፣ ለእናትና ለልጅ ደግሞ የጠነከረ የፍቅር ትስስር መሆኑን አስገንዝበዋል።   በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ምግብና አመጋገብ ባለሙያ ወ/ሮ ገነት እንዳልክ እንደገለጹት፣ ሕፃናት በመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት የእናት ጡት ብቻ ሊጠቡ እንደሚገባ ያሳወቁ ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ ተጨማሪ ምግብ እየተሰጣቸው ጡት ማጥባቱ እስከ ሁለት ዓመት ወይም ከዚያ በላይ እንዲቀጥል መክረዋል። የእናት ጡት ወተት ሕፃናትን ከበሽታ በመጠበቅ፣ ለአዕምሮ ዕድገት በማገዝና የተሟላ ንጥረ ምግብ በማቅረብ የማይተካ ጠቀሜታ እንዳለውም  ገልጸዋል።      እንዲሁም ጡት ማጥባት ለእናቶች ከወሊድ በኋላ የጤና መሻሻልን እና ከአንዳንድ ሕመሞች የመከላከል ጥቅም እንዳለው ተጠቁሟል። እንደ ወ/ሮ ገነት ማብራሪያ  እናቶች ጤናማ አመጋገብ በመከተል፣ በቂ ፈሳሽ በመውሰድና ልጆቻቸውን በፍቅርና በደስታ በማጥባት ለሕፃናት ጤናማ እድገት መሠረት እንዲጥሉ ጥሪ አቅርበዋል። "ከቤት ውጭ የሚሠሩ እናቶችም ቢሆኑ ወተታቸውን በጽዳት አልበው አየር በማይገባበት ዕቃ በማስቀመጥ መጠቀም ይችላሉ፤ የታለበ ወተት በክፍል ሙቀት (Room Temperature) ውስጥ እስከ አራት ሰዓት፣ በማቀዝቀዣ (ፍሪጅ) ውስጥ ደግሞ እስከ አራት ቀን እና ከዚያም በላይ በማቆየት መጠቀም እንደሚችሉ" ነው የተናገሩት።   (ሰናይት በየነ) በኲር የነሐሴ 4  ቀን 2018  ዓ.ም ዕትም ሙሉን በዚህ ሊንክ ገብተው ያንብቡ! https://ameco.et/bekur/19368/

  • የታፈኑ ስፖርተኞች በዓለም ላይ ተወዳጅ በሆነው የእግር ኳስ ስፖርት በ90 ደቂቃ ውስጥ የአንድ ጊዜ ወይም የ15 ደቂቃ እረፍት ብቻውን በቂ ወደማይሆንበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡ በቅርቡ በሸኘነው 23ኛው የዓለም ዋንጫ ላይ ሳይቀር ተጨዋቾች ከእረፍት በፊትና ከእረፍት በኋላ የውሃ እረፍት ወይም የማቀዝቀዣ ጊዜ በሚል እረፍት ሲሰጣቸውም አስተውለናል፡፡ በአትሌቲክስ ስፖርት በተለይም የረጅም ርቀት ሯጮች ውሃ ሳይጠጡ ወይም በራሳቸው ላይ ሳይደፉ ብዙ ርቀቶችን መሮጥ እየተሳናቸው ሄዷል፡፡ በሁሉም የስፖርት ዓይነቶች ለስፖርተኞች መታፈን ወይም ትንፋሽ ማጣት ቀዳሚው ምክንያት የዓለም ሙቀት መጨመርና የዓየር ንብረት መዛባት መሆኑን ዓለም በተጨባጭ አረጋግጣለች፡፡ (እሱባለው ይርጋ) በኲር የነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም ሙሉን በዚህ ሊንክ ገብተው ያንብቡ! https://ameco.et/bekur/19362/

  • без подписи