የኛ- ሥርዓተ ቅዳሴ ተሰጥዎ መማርያ
Статистикаይህ ቻናል በዋነኝነት ሰለ ቅዳሴ እንዲሁም በቅዳሴ ጊዜ ይበል ህዝብ የሚለውን ክፍል በዜማ እና በትርጉም እናጠና ዘንድ የተከፈተ ነው። ለምታውቋቸው ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ እንድታጋሯቸው በትህትና እንጠይቃለን። @temesegen24 ሀሳብ ካላችሁ በዚህ ልትልኩልን ትችላላችሁ። በራሱ ማንነት ውስጥ የሚኖር እውነተኛ "ኦርቶዶክሳዊ ኢትዮጵያዊ" ለመሆን ዕለት ዕለት እንትጋ💕
- Последний пост
- 12 июн.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የኛ- ሥርዓተ ቅዳሴ ተሰጥዎ መማርያ pinned «ሰላም ቤተሰቦቼ እንዴት ናችሁ? የኦርቶዶክሳዊ ኤቨንት ዝግጅት ቢዝነስ ጀምሬያለሁ። ከላይ ያለው ሊንክ በቤተክርስቲያን ለሚያገቡ ሙሽሮች መዝሙር ማጥናት ይችሉ ዘንድ የተከፈተ ነው እና በቅርብ የምታገቡ ሙሽሮች ሚዜዎች ቤተሰብ ተቀላቀሉን። ማንኛውንም አይነት ኦርቶዶክሳዊ ሰርግ ሽምግልና ምርቃት ክርስትና እንድናዘጋጅላችሁ ከፈለጋችሁ @sebencreationevent ያናግሩን። ሰለምታበረታቱኝ አመሰግናለሁ ❤»
ሰላም ቤተሰቦቼ እንዴት ናችሁ? የኦርቶዶክሳዊ ኤቨንት ዝግጅት ቢዝነስ ጀምሬያለሁ። ከላይ ያለው ሊንክ በቤተክርስቲያን ለሚያገቡ ሙሽሮች መዝሙር ማጥናት ይችሉ ዘንድ የተከፈተ ነው እና በቅርብ የምታገቡ ሙሽሮች ሚዜዎች ቤተሰብ ተቀላቀሉን። ማንኛውንም አይነት ኦርቶዶክሳዊ ሰርግ ሽምግልና ምርቃት ክርስትና እንድናዘጋጅላችሁ ከፈለጋችሁ @sebencreationevent ያናግሩን። ሰለምታበረታቱኝ አመሰግናለሁ ❤
https://t.me/sebencreationevents
"ሰንበትን አክብሩ እውነትንም አድርጉ ብል የማያበላሸው የማያገኘው ሌባም የማያገኘው በስማያት ያለ መዝገብን ለእናንተ ሰብስቡ" ልዕልት ሰንበትን በቅዳሴ❤
⭐️የዋናው ትንሣኤ ሳምንት እሑድ ዳግም ትንሣኤ⭐️ በዚች ሰንበት የትንሣኤው ዕለት ጌታችን ለቅዱሳን ሐዋርያት በዝግ በር ገብቶ በመካከላቸው ተገኝቶ ሰላም ለሁላችሁ ይሁን ብሎም ትንሣኤውን ሲገልጽላቸው ሐዋርያው ቶማስ አልተገኘም ነበር፡፡ በኋላ ከሔደበት ሲመጣ የጌታችን መነሣትና እንደተገለጸላቸውም በደስታ ሲነግሩት በኋላ እናንተ አየን ብላችሁ ልትመሰክሩ፣ ልታስተምሩ፣ እኔ ግን ሰምቼአለሁ ብዬ ልመሰክር፣ ላስተምር? አይሆንም እኔም ካላየሁ አላምንም በማለቱ የሰውን ሁሉ፤ ይልቁንም የመረጣቸው ወዳጆቹን የልብ ሐሳብ ምክንያቱን ለይቶ የሚያውቀው፣ ቸርነቱ ወሰን የሌለው የባሕርይ አምላክ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ልክ እንደ መጀመሪያው ትንሣኤ ዕለት አበው ሐዋርያት በአንድነት በተዘጋ ቤት እንዳሉ በሩን ሳይከፍት ገብቶ ሰላም ለሁላችሁ ይሁን በማለት በመካከላቸው ቆመ፤ ቶማስንም ያመንክ እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን እነሆ የተቸነከሩ እጆቼንና እግሮቼን፣ የተወጋ ጐኔንም ናና እይ ብሎ አሳየው፡፡ እርሱም ምልክቱን በማየቱ፤ በመዳሰሱ ትንሣኤውንና አምላክነቱን እንደፍላጎቱ በመረዳቱ ጌታዬ አምላኬ ብሎ መስክሮ አመነ፡፡ እንግዲህ ይህ የትንሣኤው ምስጢር ለሁለተኛ ጊዜ ለሐዋርያት የተገለጠበት ዕለት ስለሆነ ዳግም ትንሣኤ ተብሎ ሰንበቱ ይጠራበታል፤ ይከበርበታል፡ ልዕልት ሰንበትን በቅዳሴ❤
ዛሬ በክርስቲያን ሰንበት ደስታ ኾነ፤ ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቷልና፤ ከቀናቶች ኹሉ ቀደሳት፣ አከበራት፣ ከፍ ከፍም አደረጋት፤ በእውነት ከሙታን ተነሥቷል። እንኳን አደረሳችሁ ፤ ክብርት ሰንበትን በቅዳሴ❤
https://telegra.ph/ሥርዓተ-ማኅሌት-ዘሆሣዕና-በግእዝና-በአማርኛ-04-12
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
አስቀድማችሁ በዜማ ለማድመጥ ደግሞ ይኸው (የዜማዎቹ ምንጭ- መዝሙረ ማህሌት https://t.me/zemariian)
ይኼን ውብ ሥርዓት እናይ ዘንድ የምንችል ሁላችንም ቤተክርስቲያን እንደር ካልሆነ ቅዳሴ እንሂድ። ከአቅም በላይ ሆኖ ሁለቱንም ማድረግ ካልቻልን ግን ጠዋት አደራ እንዳንቀር። በሰሞነ ህማማት ፍትሐት ስለማይደረግ ጸሎተ ፍትሐት ነገ ለሁላችንም ይደረጋል በዛውም ጌታችንን በአንድነት "እባክህ አሁን አድን " እንለዋለን። (ለቤተሰቦቻችሁ ሼር አድርጉላቸው ) መልካም በዓል 🤍
ሥርዓተ ዑደት ዘሆሣዕና (በአራቱ አቅጣጫ እየተዞረ የሚባለው የዑደት ሥርዓት በግእዝና በአማርኛ ነው) 🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁 🌿አቡን በ፪ ሀሌታ- አርእዩነ ፍኖቶ ወንሑር ቤቶ እምጽዮን ይወጽህ ህግ ወቃለ እግዚአብሔር እም ኢየሩሳሌም ንሳለማ ለመድኃኒትነ በትፍሥሕት ተቀበልዋ ለታቦት እስመ ዋካ ይዕቲ ወብርሐን ቤቱ እንሔድ ዘንድ መንገዱን አሳዩን ከጽዮን ሕግ ይወጣል የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም መድኃኒታችንን እንሳለማት በደስታ ታቦቷን ተቀበሏት ዋካ እና ብርሃን ናትና። ምልጣን፦ ንሳለማ ለመድኃኒትነ በትፍሥሕት ተቀበልዋ ለታቦት እስመ ዋካ ይዕቲ ወብርሐን መድኃኒታችንን እንሳለማት በደስታ ታቦቷን ተቀበሏት ዋካ እና ብርሃን ናትና። ይ.ሕ. እየወጡ እንዲህ ይበሉ ዋካ ይእቲ ወብርሃን ዋካ ይእቲ ወብርሃን ዋካ እና ብርሃን ናትና ዋካና ብርሃን ናትና። ይ.ዲ. ምስባክ፦ ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘየኀድር ውስተ ጽዮን። ወንግርዎሙ ለአሕዛብ ምግባሮ። እስመ ተዘከረ ዘይትኀሠሥ ደሞሙ። በጽዮን ለሚኖር ለእግዚአብሔር ዘምሩ። በአሕዛብም መካከል አደራረጉን ንገሩ። ደማቸውን የሚመራመር እርሱ አስቧልና። ... ይ.ካ. ወንጌለ ማቴዎስ ፳፩፤ ፩ 🌿አቡን በ፮ ሀሌታ- ሰመያ አብርሃም ወይቤላ ዛቲ ዕለት በዓለ እግዚአብሔር ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሠርቅ በእምርት ዕለት በዓልነ ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን አብርሃም ዕለቷን የእግዚአብሔር በዓል ናት ብሎ ጠራት በመባቻ ዕለትም መለከትን ንፉ በዚች ዕለትም ጽዮንን አስበናታልና በዓላችን ነው። 🌱ምልጣን፦ ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሠርቅ በእምርት ዕለት በዓልነ ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን በመባቻ ዕለትም መለከትን ንፉ በዚች ዕለትም ጽዮንን አስበናታልና በዓላችን ነው። ይ.ሕ. ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ ይ.ዲ. እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ። በእንተ ጸላዒ። ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ። ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን። አዘግጀህ ስለ ጠላትህ። ጠላትንና ቂመኛን ለማጥፋት።... ይ.ካ. ወንጌለ ማርቆስ ፲፩፥፩ 🌿አቡን በ፮ ሀሌታ- ወትቤ ጽዮን አርኅዉ ሊተ አናቅጸ ይባኡ ሕዝብ ብዙሃን ወያእትቱ እብነ እምፍኖት ለንጉሥ ለወልደ ዳዊት ንጉሦሙ ለእስራኤል ውእቱ ይብሉ ሆሳዕና በአርያም ጽዮን ሕዝቡ ኹሉ ገብተው ለዳዊት ልጅ ለንጉሡ ከመንገድ ድንጋይን ያነሡ ዘንድ ደጆች ይከፈቱ ትላለች ለእስራኤል ንጉሣቸው ነውና ሆሣዕና በአርያም ይላሉ። 🌱ምልጣን፦ እብነ እምፍኖት ለንጉሥ ለወልደ ዳዊት ንጉሦሙ ለእስራኤል ውእቱ ይብሉ ሆሳዕና በአርያም ለዳዊት ልጅ ለንጉሡ ከመንገድ ድንጋይን ያነሡ ዘንድ ደጆች ይከፈቱ ትላለች ለእስራኤል ንጉሣቸው ነውና ሆሣዕና በአርያም ይላሉ። ይ.ሕ. ይብሉ ሆሳዕና በአርያም ይብሉ ሆሳዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ይላሉ ፣ ሆሳዕና በአርያም ይላሉ ይ.ዲ. ምስባክ፦ እምሥራቀ ፀሐይ እስከነ ዐረብ። ወእምጽዮን ሥነ ስብሐቲሁ። እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ። ከፀሐይም መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ... ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል። ይ.ካ. ወንጌለ ሉቃስ ፲፱፥፳፰ 🌿አቡን በ፮ ሀሌታ- ባረኮ ያዕቆብ ለይሁዳ ወልዱ ወይቤሎ ሀሎ ንጉሥ ዘይወጽሕ እምኔከ ዘየሐፅብ በወይን ልብሶ ወበደመ አስካል ሰንዱኖ ንጉሦም ለእስራኤል ውእቱ ይብሉ ሆሳዕና በአርያም ያዕቆብ ልጁ ይሁዳን እንዲህ እያለ ባረከው ልብሱን በወይን ጨርቁንም በደም የሚያጥብንጉሥ ከአንተ ይወጣል የእስራኤል ንጉሣቸው ነውና ሆሣዕና በአርያም ይላሉ 🌱ምልጣን፦ ዘየሐፅብ በወይን ልብሶ ወበደመ አስካል ሰንዱኖ ንጉሦም ለእስራኤል ውእቱ ይብሉ ሆሳዕና በአርያም ልብሱን በወይን በፍታውንም በዘለላ ደም የሚያጥብ ንጉሥ ከአንተ ይወጣል የእስራኤል ንጉሣቸው ነውና ሆሣዕና በአርያም ይላሉ ይ.ሕ. ይብሉ ሆሳዕና በአርያም ይብሉ ሆሳዕና በአርያም ሆሣዕና በአርያም ፣ ሆሣዕና በአርያም ይላሉ። ይ.ዲ. ምስባክ፦ ንፍሑ ቀርነ በዕለተ ሠርቅ። በዕምርት ዕለት በዓልነ። እስመ ሥርዓቱ ለእሥራኤል ውእቱ። በመባቻ ቀን በከርተኛው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ ፤ ለእሥራኤል ሥርዓቱ ነውና።... ይ.ካ. ወንጌለ ዮሐንስ ፲፪፥፲፪ 🌿አቡን በ፪ ሀሌታ- ባኡ ውስተ ሀገር ወበዊአክሙ ትረክቡ ዕዋለ አደግ እቡረ ፍትሕዎ ወአምጽእዎ ሊተ ወደ ከተማ ግቡ አህያ ከውርንጭላም ጋር ታገኛላችሁ ፈታችሁም አምጡልኝ ምልጣን፦ ፍትሕዎ ወአምጽእዎ ሊተ ፍትሕዎ ወአምጽእዎ ሊተ ፈታችሁም አምጡልኝ ፣ ፈታችሁ አምጡልኝ 🌿ሰላም፦ ሃሌ ሉያ አልጺቆ ኢየሱስ ኢየሩሳሌም ርእያ ለሀገር ወይቤላ ሶበ ተአምሪ ጽዮን ነዋ ንጉሥኪ በጽሐ ብርሃንኪ ዮም ሰላምኪ ሃሌሉያ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ቀርቦ አያትና እንዲህ አላት ጽዮን ሆይ ታውቂ ዘንድ ንጉሥሽ ይኸውና ፣ ብርሃንሽ ደርሷል ፣ ሰላምሽ ዛሬ ነው። 🌱ምልጣን፦ ወይቤላ ሶበ ተአምሪ ጽዮን ነዋ ንጉሥኪ በጽሐ ብርሃንኪ ዮም ሰላምኪ እንዲህ አላት ጽዮን ሆይ ታውቂ ዘንድ ንጉሥሽ ይኸውና ፣ ብርሃንሽ ደርሷል ፣ ሰላምሽ ዛሬ ነው። (ምንጭ- ኪዳን ዘኢየሱስ https://t.me/KidanZeIyesus)
"ሰንበትን አክብሩ እውነትንም አድርጉ ብል የማያበላሸው የማያገኘው ሌባም የማያገኘው በስማያት ያለ መዝገብን ለእናንተ ሰብስቡ" ልዕልት ሰንበትን በቅዳሴ❤
እንግዲህ ሰንበት በእግዚአብሔር ቸርነት ከስጋ ድካማችን እናርፍባት ዘንድ የተሰጠችን ጸጋ መሆኗን አውቆ በሚገባ ማክበር ይገባናል። ~ልዕልት ሰንበትን በቅዳሴ~
ወደ እግዚአብሔር አምልኮ የገባ መጻተኛ ከሕዝቡ ይለየኝ ይሆን? አይበል ፤ በጎ ያደረገ ሰንበትን የሚያከብር ሁሉ ጻድቅ ነው። በጎ ሽልማት የምታስገኝ ሰንበትን በቅዳሴ እናክብራት🤍
"ሰንበትን አክብሩ እውነትንም አድርጉ ብል የማያበላሸው የማያገኘው ሌባም የማያገኘው በስማያት ያለ መዝገብን ለእናንተ ሰብስቡ" ልዕልት ሰንበትን በቅዳሴ❤
https://youtu.be/nqgDU0UT1FY?si=W4YvYLugOar6FeM0 ክርስቶስን የምናስብበት የተባረከ ምሽት ይሁንልን❤