tgindex
ቅንጭብጭብ

ቅንጭብጭብ

Статистика

ካየሁት 👀 አስገራሚ ከሠማሁት 👂 መሣጭ ካነበብኩት 📖 አስተማሪ ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ እነሆ #ቅንጫቢ ፅሁፎቻችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን። ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @bcrAzykid ይጠቀሙ።

Последний пост
14 нояб.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
am
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
5 959
−7 за 4 дн.
Сутки
−2
−0,03%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
2 705
20 постов
Вовлечённость
45,4%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 14 нояб.2 2538из Medinamagazine

    ውድ የመዲና ዲጂታል መጽሔት አንባብያን እነሆ የጥቅምት ወር እትም! በቤት ለእንግዳ ዐምዳችን ባለፈው ከሠዓሊ ለይኩን ጋር የጀመርነውን ዘለግ ያለ ቆይታ ቀጥለናል። ልቦለዱ፣ ግጥሙ፣ አጤሬራው፣ ሽርሽሩ፣ ፌርማታው፣ እንቆቅልሹ፣ እፍታው፣ ግብዣው ሁሉም ሙሉ ነው። ሐሳብ አስተያየታችሁን በሚከተሉት የማኅበራዊ ሚዲያ አድራሻዎቻችን ላኩልን። መልካም ንባብ! https://t.me/Medinamagazine medinadigitalmagazine@gmail.com ወይም @medinamagazinebot ከዚህ በፊት የወጡትን ቅጾች Medina DM Bot👆 በተሻለ ጥራት ያገኟቸዋል። በተጨማሪም በፌስቡክ፣ በዋትሳፕ እና ኢንስታግራም ቤተሰብ ይሁኑን! https://www.facebook.com/profile.php?id=61556884335163&mibextid=ZbWKwL https://www.instagram.com/medinadigitalmegazine?igsh=ejZqbjN3OXF0dHJj https://chat.whatsapp.com/GTCtybsFRDGKTtzu8c1Sgc?mode=ac_t @medinadigitalmagazine

  • 8 сент. 2025 г.2 94921из Medinamagazine

    ውድ የመዲና ዲጂታል መጽሔት አንባብያን እንኳን ለ2018 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ያሳለፍነውን ዓመት አብራችሁን ስለቆያችሁ እናመሰግናለን። የሚመጣው ዓመት የልባችሁ የሚሳካበት ዐዳዲስ ከፍታ የምታዩበት እንዲሆን ምኞታችን ነው። መጽሔታችንም በዚህም ወር ዐዲሱን ዓመት የምንቀበልበትን ገጸ በረከት ይዛ ቀርባለች። ከወትሮው የተጓደለ የለም። አንብባችሁ አስተያየቶቻችሁን በማኅበራዊ ሚድያ አድራሻዎቻችን ብትልኩልን ይደርሰናል። ጽሑፎችም ካላችሁ በኢ ሜይል አድራሻችን ይላኩልን። መልካም ንባብ! https://t.me/Medinamagazine medinadigitalmagazine@gmail.com ወይም @medinamagazinebot ከዚህ በፊት የወጡትን ቅጾች Medina DM Bot👆 በተሻለ ጥራት ያገኟቸዋል። በተጨማሪም በፌስቡክ፣ በዋትሳፕ እና ኢንስታግራም ቤተሰብ ይሁኑን! https://www.facebook.com/profile.php?id=61556884335163&mibextid=ZbWKwL https://www.instagram.com/medinadigitalmegazine?igsh=ejZqbjN3OXF0dHJj https://chat.whatsapp.com/GTCtybsFRDGKTtzu8c1Sgc?mode=ac_t

  • 29 апр. 2025 г.3 4092из Medinamagazine

    "እልፍ እምነቶች አሉን። አንዲት አበባም አለች። በእልፍ ፈጣሪዎች የተፈጠረች፥ አንዲት ተፈጣሪ፡፡" መዲና ቅጽ ቅጽ1 ቁጥር ምርቃት ገጽ 10

  • 23 апр. 2025 г.3 09131из Medinamagazine

    እንኳን ለዓለም የመጻሕፍት ቀን አደረሳችኹ! የምትወዱትን መጽሐፍ በcomment አጋሩን። የኛንም ቆየት ብለን እናጋራችኋለን።

  • ዓድዋ . . .

  • ዓድዋ . . .

  • 14 янв. 2025 г.3 07941из Medinamagazine

    ውድ የመዲና ዲጂታል መጽሔት አንባቢያን መጽሔታችን እንዲህ እንዲህ እያለች ቅጽ አንድን ወደማገባደዱ ደርሳለች። ይህ የቅጽ አንድ የመጨረሻ እትም ነው። እስከዛሬ ለቃለ መጠይቅ በመተባበር፣ ጽሑፍ በመላክ፣ ሃሳብ አስተያየቶቻችሁን በመለገስ፣መጽሔታችንን በማንበብና በማስተዋወቅም ጭምር ለተራዳችሁን ወዳጆች መኮንን ደፍሮ፣ ሄኖክ አባይነህ፣ መንበረ ማርያም ኃይሉ፣ ፀደይ ወንድሙ (ዶ/ር)፣ አንተነህ አክሊሉ፣ ጉቺ ሽመልስ፣ ሱራፌል አየለ፣ ምግባር ሲራጅ፣ ዮርዳኖስ አልማዝ ሰይፉ፣ ሲራክ ወንድሙ፣ ሳራ አህመድ፣ ትሬዛ ዮሴፍ፣ ዕፀ ገነት መልካሙ፣ ሳሚያ ጡሃ፣ ጽዮን ልሳኑ፣ በረከት ጌታነህ፣ ተኩ ዣን፣ ይርዳው ግፎ (መምህር)፣ ሰሎሜ መብራቱ፣ ትዕግስት ደሣለኝ፣ ውብ አረገ አድምጥ፣ ናትናኤል ማናዬ፣ ጃፈር መጻሕፍት፣ ኤዞፕ መጻሕፍት እና ሌሎችም በስም ላልጠቀስናችሁ ወዳጆች በሙሉ ምስጋናችን ከልብ ነው። አንባቢያንም እንዲሁ ጊዜያችሁን ሰጥታችሁ ስለምታነቡን ደስ ይለናል። እናመሰግናለን። ለቅፅ ሁለት ቢስተካከል የሚሉትን በኢሜይል አድራሻችን ይላኩልን። እስከምንመለስ ቸር ሰንብቱልን። መልካም ንባብ! https://t.me/Medinamagazine በተጨማሪም በፌስቡክ እና ኢንስታግራም ቤተሰብ ይሁኑን! https://www.facebook.com/profile.php?id=61556884335163&mibextid=ZbWKwL https://www.instagram.com/medinadigitalmegazine?igsh=ejZqbjN3OXF0dHJj ለአስተያየትዎ medinadigitalmagazine@gmail.com ጥር 2017 ዓ.ም

  • 17 дек. 2024 г.3 10113из Medinamagazine

    ውድ የመዲና ዲጂታል መጽሔት አንባብያን፥ መዲና ቅጽ 1 ቁጥር 9 እትሟን ይዛ ተመልሳለች። ሀሳብ አስተያየታችሁን በሶሻል ሚዲያ አካውንቶቻችን ብታጋሩን ደስ ይለናል። ስለምታነቡን እናመሰግናለን። https://t.me/Medinamagazine በተጨማሪም በፌስቡክ እና ኢንስታግራም ቤተሰብ ይሁኑን! https://www.facebook.com/profile.php?id=61556884335163&mibextid=ZbWKwL https://www.instagram.com/medinadigitalmegazine?igsh=ejZqbjN3OXF0dHJj ለአስተያየትዎ medinadigitalmagazine@gmail.com ኅዳር 2017 ዓ.ም

  • 16 нояб. 2024 г.3 20011из Medinamagazine

    "ዋቢ ሳቢ ሕይወትን ከነጉድለቱ እንድንቀበል የሚያስተምር ውብ የአኗኗር ዘይቤ ነው። አንድ ገጸ-ድር ላይ ያገኘኹት ጽሑፍ አንድ ሰው አብርሆት ላይ የሚደርሰው ጉድለቱን መቀበል ሲችል እንደሆነ ይናገራል።" መዲና ቅጽ 1 ቁጥር 6 ሚሊየን

  • 10 нояб. 2024 г.3 12041из Medinamagazine

    ውድ የመዲና ዲጂታል መጽሔት አንባብያን፥ መዲና ቅጽ 1 ቁጥር 8 እትሟን ይዛ ተመልሳለች። ሀሳብ አስተያየታችሁን በሶሻል ሚዲያ አካውንቶቻችን ብታጋሩን ደስ ይለናል። ስለምታነቡን እናመሰግናለን። https://t.me/Medinamagazine በተጨማሪም በፌስቡክ እና ኢንስታግራም ቤተሰብ ይሁኑን! https://www.facebook.com/profile.php?id=61556884335163&mibextid=ZbWKwL https://www.instagram.com/medinadigitalmegazine?igsh=ejZqbjN3OXF0dHJj ለአስተያየትዎ medinadigitalmagazine@gmail.com ጥቅምት 2017 ዓ.ም

  • መልክአ ሕይወት ቧልትን ከፈገግታ ሣቅን ከፌዝ ጋራ ባንድ ላይ ቀይጠን አቅልመን በጥብጠን በሐዘን ባሕር ላይ ብናንቆረቁርም ባሕሩ ሰፊ ነው መልኩን አይቀይርም ከበዕውቀቱ ስዩም (ስብስብ ግጥሞች) Art work by Edvard Munch - Melancholy (1894-96) https://t.me/dailythoughtsdailythoughts

  • #amazing_facts 1. የአለም ትንሹ መፅሃፍ፡ ትንሹ የታተመ መጽሐፍ "Teeny Ted from Turnip Town" ነው የሚለካው 0.07 ሚሜ x 0.10 ሚሜ ብቻ ነው።  focused ion beam በመጠቀም የተፈጠረ ሲሆን በኤሌክትሮን ማይክሮስኮፕ ብቻ ነው የሚነበበው። 2. በጽሕፈት መሳርያ ላይ የተጻፈ የመጀመሪያው ልቦለድ፡ ማርክ ትዌይን የቶም ሳውየር አድቬንቸርስ (1876) በጽሕፈት መሳርያ ላይ የተጻፈ የመጀመሪያው ልቦለድ እንደሆነ ይታመናል፣ ይህም በሥነ ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው ጊዜ ነው። 3. ረጅሙ የመፅሃፍ ርዕስ፡ በጊነስ ወርልድ ሪከርድስ የረዥሙ መጽሐፍ ርዕስ 3,777 ቃላትን ይዟል!  እ.ኤ.አ. በ2019 የታተመው የህዝብ ፖሊሲ ​​ላይ የጣልያን መጽሐፍ ነው። 4. የመጀመሪያው ኢ-መጽሐፍ፡ የመጀመሪያው ኢ-መጽሐፍ በ1971 ሚካኤል ኤስ ሃርት የዩኤስ የነጻነት መግለጫን ዲጂታል ሲያደርግ ተፈጠረ ነው ።  ይህ ፕሮጀክት በመጨረሻ የዓለማችን ትልቁ ዲጂታል ቤተ መፃህፍት ፕሮጀክት ጉተንበርግ እንዲፈጠር አድርጓል። 5. የመጀመሪያው የህዝብ ቤተ መፃህፍት፡ በአለም የመጀመሪያው የህዝብ ቤተ መፃህፍት የተቋቋመው በ1833 በፒተርቦሮ ፣ ኒው ሃምፕሻየር ፣ አሜሪካ ነበር።  መጽሐፍትን በነጻ ለሕዝብ ተደራሽ በማድረግ በታክስ ዶላር የተደገፈ የመጀመሪያው ቤተ መጻሕፍት via jafer books

  • #ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ . . #ለጊዜ_ጌታ_የተፃፈ_ደብዳቤ! . . ፈጣሪዬ ሆይ በሰማያት የምትኖር.. ብዙ መንገድ መተናል፣ ብዙ ትዝታዎችን ቋጥረናል፣ ብዙ ተስፋዎችን ሰንቀናል፣ ብዙ ሰዎችን አቅርበናል፣ ልብ ለልብ ተሳስረናል፣ መኖር አስከፊ ገፅ ቢኖረውም! ለመሰንበት ጓጉተናል፣ ገና መኖርን ናፍቀናል፣ አዲስ ትዝታዎችን መመስረት አስበናል፣ በጥልቅ ፍቅር ወድቀናል፣ አብሮ ማርጀትን ተመኝተናል፣ ሞትን አርቀህ ትንሽ ጊዜ ስጠን ብለናል፣ እባክህ ጌታ ሆይ.. ቅጣት ያልካት ምድር አቅፋ አኑራኛለች፣ ስረግጣት ቢመራት ልትውጠኝ 'ጠብቃለች..! እማይቻልህ የለ ሁሉ በጅህ አይደለ! በቃ ጊዜን አቁመው ቀናተም ይዘግዩ፣ የሰው እድሜ ይርዘም የወጣትነቱ፤ ኧረ ባክህ ጌታ ያላየነው አለ.. አታሳልፍብን ትንፋሽህን አትንሳን ከመምጣታችን በፊት መቆየት እንሻለን.. ወይ ደግሞ ሁሉም ይቅር! ሁሉም ባንዴ ይጥፋ፣ የቀደመው ሞቶ! ቀሪው ከሚከፋ! ወይ ሁሉም ባንድ ይሁን..!! . . . ✍️Aman😑 YTZ

  • #Arichitecture

  • ሰውዬው መጠጥ ቤት ሲገባ ሁልጊዜ በአንዴ 3 ጠርሙስ ቢራ ያዛል። ሶስቱን ሲጨርስ ደግሞ ሌላ 3 ያዝዝና ይጠጣል። በቃ ልማዱ ይኸው ነው። የመጠጥ ቤቱ ባለቤት በዚህ ልማዱ ተገርሞ ሰውዬውን ጠየቀው፣ "ሁልጊዜ በአንዴ ሶስት ጠርሙስ እያዘዝክ ስትጠጣ አይሃለሁ፣ ቢራው እንዳይሞቅብህ ለምን ተራ በተራ አንድ አንድ አታዝም?" "ጥሩ ጥያቄ ነው የጠየከኝ። ይኸውልህ ሁለት ጓደኞች አሉኝ። እነሱ አሁን ለሥራ ወደ ሌላ አገር ሄደዋል። ታዲያ ስንለያይ ማንም ሰው ብቻውን ሆኖ መጠጥ ሲያዝዝ ለማስታወሻ አብረን እንዳለን እንዲመስለን አንዱ 3 አዝዞ ይጠጣል። እሱን ሲጨርስ ደግሞ መድገም ከፈለገ አሁንም 3 አዝዞ እንዲጠጣ ቃል ተግባብተናል" ሲል መለሰለት። አንድ ቀን ግን ሰውዬው መጣና 2 ብቻ አዘዘ። የመጠጥ ቤቱ ባለቤት በሁኔታው አዝኖ ሰውዬውን አነጋገረው፣ "በጣም አዝናለሁ! አንዱ ጓደኛህ ሞቶብህ ነው?" "አይደለም?" "ምነው ታዲያ ሁለት ብቻ አዘዝክ?" "እኔ መጠጥ አቁሜ ነው" ባሻዬ! እንዲህ ዓይነት ጓደኛ የት ይገኛል? እንዲህ ዓይነት ሰው ቢኖር አገራችን የት ትደርስ ነበር!!! Via Tesfaye Hailemariam

  • የሆነ ቀን አሞኝ አልጋ ላይ ብዙ ጌዜ ከረምኩ ምኔም እምድን አይመስልም ነበር እሚያስቡልኝ አምላክ ሞቴን ቢያፋጥንልኝ ጥሩ እንደሆነ በልባቸው የተመኙልኝ ይመስለኛል ... እኔ ግን ዳንኩ የሆነ ግዜ ሱስ ጀመርኩ ጫት ሲጋራ መጠጥ ፊቴን እስኪቀይረው ተከተብኩ አዬ መና ቀረ ተባልኩ እኔ ግን ሱስ አቆምኩኝ ። የሆነ ቀን ጓደኞቼ ሁሉ አልፈው እኔ አስረኛ ክፍል ወደኩ ሁሉም በጋራ አዘኑልኝ ብለን ነበረ አሉኝ ሰፈር ቀረ አሉኝ እኔ ግን ተመልሼ private ተፈትኜ አልፌ እስከሁለተኛ ድግሪ ድረስ ተማርኩ የሆነ ግዜ እናቴ ለቆሶ ልቴድ ፈልጋ ነጠላ ስትበደር አይቻት እኔ ሳድግ አምስት ቅያሪ ነጠላ እገዛልሻለሁ አልኩኝ የሰሙ ሰዎች ሳቁብኝ ለምን እንደሳቁ አላቅም እኔ ግን ስራ ስይዝ አረ አምስት ነጠላ ምን ይሰራል እያሉኝ ጥለቱን እየቀያየርኩ ገዛው .... ትላንት ብዙ አይሆንምን አልፌያለሁ ። ብዙ አበቃለትን ተሻግርያለሁ ፣ ነገ የተሻለ እንደሚሆን ትላንት ምስክሬ ነው ። መሞከር ፣መማር፣ ለመሻሻል መጣር ፣መታገስ አናቆምም ሁሉም ይስተካከላል ❤ ©Adhanom Mitiku

  • 6 окт. 2024 г.1 93032из Medinamagazine

    ውድ የመዲና ዲጂታል መጽሔት አንባብያን መጽሔታችን በአዲስ ዓመት ቅጽ 1 ቁጥር 7 እትሟን ይዛ ተመልሳለች። ሀሳብ አስተያየታችሁን በሶሻል ሚዲያ አካውንቶቻችን ብታጋሩን ደስ ይለናል። ስለምታነቡን እናመሰግናለን። https://t.me/Medinamagazine በተጨማሪም በፌስቡክ እና ኢንስታግራም ቤተሰብ ይሁኑን! https://www.facebook.com/profile.php?id=61556884335163&mibextid=ZbWKwL https://www.instagram.com/medinadigitalmegazine?igsh=ejZqbjN3OXF0dHJj ለአስተያየትዎ medinadigitalmagazine@gmail.com መስከረም 2017 ዓ.ም

  • ገላጣ (በእውቀቱ ስዩም) ዛሬ የተከበረውን የዓለም አቀፍ ራሰ በራዎች ቀን ሳልዘክር ወደ ምኝታየ ብሄድ የሶቅራጥስ አጽም ይወጋኛል፤ ሊቁ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ “በራሕ”የሚለውን ቃል ሲተረጉሙት-“ በራ፥ መላጣ፥ ራሰ ገላጣ፥ ከቦታው የታጣ፥ የራሱ ቁርበት፥ ሳንባና ጉበት የሚመስል “ ይላሉ (መጽሀፈ ስዋሰው ወግስ ፥ ገጽ 287፤ በትርጉሙ ውስጥ ያሉትን አሉታዊ ቃላት ብዛት ለተመለከተ አለቃ ባለ ሙሉ ጠጉር እንደሆኑ መገመት አያቅተውም፤ አለቃ “ራሰ ገላጣ “ ቢሆኑ ኖሮ “ራሰ በራ ” የሚለውን ሲተረጉሙ “ራሱ የበራለት፤ ታጥቦ የተወለወለ የንጉስ ብርሌ የመሰለ፥ መላጣ፥ ከፎረፎርና ከቅማል ስጋት ነጻ የወጣ “ብለው ሊተረጉሙት ይችሉ ነበር፤ በታሪካችን ትልልቅ ራሰ በራ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ነበሩ፤ ከጌቶች መካከል ብንጠቅስ፥ ራስ ስኡል ሚካኤል፥ አጤ ምኒልክ፥ ራስ ዳርጌ፥ መለስ ዜናዊ፥ ከደራሲ ፥ሀዲስ አለማየሁ፥ ጃርሶ ኪሩቤል ሞትባይኖር፥ መንግስቱ ለማ፥ ሊጠቀሱ ይችላሉ፤ ( ሎሬት ጸጋየ ገብረመድህን ራሰ በራ ነው ወይስ የተሸጋሸገ ጎፈሬ ነው የሚለው በታሪክ ሲያከራክር ይኖራል ) “ለኔ እየሰጠችኝ ደረቁን እንጀራ እስዋ በነካካው በራሰው ልትበላ" የሚለውን ጥንታዊ ውስጠ ወይራ ዘፈን መናሻ አድርገን ብንናገር ፥ ሴቶች ከሚያበጥር ይልቅ የሚወለውል ወንድ የበለጠ እንደሚማርካቸው መረዳት አያቅትም፤ ስለ ጸጉር ጨዋታ በተነሳ ቁጥር ፈገግ የምታሰኝኝ ድምጻዊ አብነት አጎናፍር የተናገራት ናት፤ አብነት እንዲህ አለ፤ “ ከጥቂት ጊዜ በፊት ጸጉር ላስተክል ቱርክ ሄጄ ፤ ጸጉር የሚተከለው ሰውየ መላጣ መሆኑን ሳይ ትቸው ተመለስኩ"🙂 በዚህ አጀንዳ ላይ ሌሎች የከተማው ነዋሪዎች ያላቸውን አስተያየት ለመስማት ከፈለጉ ከታች የጫንኩትን ትረካ ያድምጡ።

  • የቱ ጋር መሰለህ… (ሚካኤል አ) መባቻ ጅምርህ የነፍስህ ድባቴ ውድቀት እንግልትህ ያኔ … ባሽትሪ መያዣ ፣ በሲጋራ ብናኝ በርጋፊ ቅጠል ፣ ድባቧ የሚቃኝ በዛች ጠባብ ክፍል ምጥን መሰብሰቢያ ዙሪያህን ሰው ሞልቶህ ቀንህን ማጣፊያ ለአፕላይ ግብዣ የተዘረጋች ጣት በሚግተለተል ጢስ ፣ ሰንቃልህ እሳት እሷን ለመቀበል ስትፈግግ ባ’ክብሮት የሰበብ አስባብ ጢስ ቀረ ቤትህን ወርሶት። የቱ ጋር መሰለህ? በቀይ መብራት ፍካት በቅልቅል ሽቶ አዲስ አይነት ክርፋት በጭላጭ ብርጭቆ ተላኮበት ድራፍት ከስፒከር ማህፀን ሙዚቃ ተለቆ ጭፈራ እና ዳንሱ አንድ ላይ ተዛንቆ የቀይ ሴት ታፋ ዓይንህ በስስ ሰርቆ በምራቅህ ድርቀት ጉሮሮህ ተጨንቆ ጠቅሰህ ስትጠራት ያቺን የሞት ብልቃጥ ከባቷ ፈልቅቀህ ዕፅዋን ስትቀምሳት በገላህ ፍሰሀ መቅደስህን ናድካት ። የቱ ጋር መሰለህ? የልጅነት ልምድህ ከሰንበት ቤት ገዳም ምልልስ ብርታትህ በሀይኪንግ ሲቀየር የያሬዱ ወረብ በእስክስታ ሲዛወር ሳትቆም ለፀሎት ሳይንስ ከእምነት ልቆት ኒቼ ቦታ ሲወርስ የየኔታን መንበር የነፍስህ ቁዘማ መንደርደሪያ ነበር። ትዝ አለህ? ዘር መራጭ ስትሆን የደም ሴል መንጣሪ ጆሮህ ዳባ ሲለብስ ለፍጥረት እንግልት ለህፃናት ጥሪ… መንገድህ ሲሳለጥ በ V 8 መኪና ዝርግ አስፓልት ሲመስልህ ጉርብጥብጥ ጎዳና ፤ ስቆልኛል ስትል ጥርሱን የነከሰ እንባው አንሸራሽሮህ ጌታ ዘንድ ደረሰ። ምላሹስ የከፋው መቼ ላይ ሆነና? ጥሬ እየቆረጥክ ሆድህ ሲመረመር እስቲም ሳውና ገብተህ ፊትህ ሲጭበረበር በድሎትህ መኃል ገላን የሚያኮስስ የእሾህ ስንጥር ነበር። ትዝ አለህ? መኝታህ በምቾት ተሞልቶ በአጀብ እንቅልፍህ ሲናጠብ? ትዝ አለህ? በውድ ቀለም ቤቶች ልጆችህ ሲማሩ ከግብረገብ ታዛ ተናንሰው ሲቀሩ? ትዝ አለህ? የጉያህ መልካም ሴት የአጥንትህ ፍላጭ አሁን ከምን ጊዜው ሆነችብኝ ምላጭ? ብለህ ስትቆዝም … እንዲያ ነው አይዋ ግፍ ፅዋው ሲሞላ በትሩን አይመርጥም። ትዝ አለህ? ታወሰህ? የቱ ጋር መሰለህ? የተፈታው ውሉ የጎደልክ ከሙሉ ኧረ ስከን ሲሉ ከዕድሜ የተማሩ የጋሽ ውቤን ምክር የእመት ጉሌን ዝክር ረግጠህ ስትበር… ስትሻገር ፣ ስጥስ የምስኪናን ድንበር የዛሬ ውድቀትህ ፣ በግጥም ሊነገር ክንፍህ የተመታው ይሄን ጊዜ ነበር። ትዝ አለህ? ፡ አዎን እሱ ጋር ነው!

  • የአብዛኛው ፍልስፍና መፅሐፍ ቶቻችን የቃላት ውስንነት ይታይባቸዋል ከደራሲው የሚመነጩ አንዳንዱም ከዘርፉ ባህሪ አንባቢም ግር ላለማሰኘት ፀሐፊዎች በቅንፍ የእንግሊዘኛውን ቢያስቀምጡ መልከም ይመስለኛል ይሄንን ከዘረያቆብ ገፅ ነው ያገኘሁት ተከተሏቸው አሪፎች ናቸው የፍልስፍና መዝገበ ቃላት ============= 1. Pragmatic - ገቢራዊ 2. Statuesque - ነቢር 3. Hierarchy - የላዕላይነት ተዋረድ 4. Normative - የልኬት-ሚዛን 5. Theory - ህልዮት 6. Ideal - ተምኔታዊ-ስዕል 7. Moral sense - ግበረ-ገባዊ ህዋስ 8. Collective - ጋርዮሻዊ 9. Soul-Body dichotomy - የነፍስና ስጋ ኩፋሌ 10. Compromiser - አመቻማች 11. Ethos - የአኗኗር-ዘይቤ-መንፈስ 12. Aristocratic - ባላባታዊ/ጌትነታዊ 13. Moderation - ታጋሽነት 14. Courageous - ደፋርነት 15. Indulgence - ልልነትን 16. Passivity - ቀሰስተኛነት 17. Chaotic - ውጥንቅጥ 18. Master Morality - የጌትነት ምግባር 19. Slave Morality - የደካሞች ምግባር 20. Life-negating - ህይወትን የሚያማርር 21. Life-affirming - ህይወትን የሚያፈቅር 22. moral supremacy - ግብረገባዊ ልእልና 23. Contextual background - አውዳዊ ዳራ 24. Intuition - ውስጠተ-ስሜት 25. Oedipus Complex - የወንድ ህቡዕ ፆታዊ ምኞት 26. Electra Complex - የሴት ህቡዕ ፆታዊ ምኞት 27. Classics - ብሉያት 28. Humanists - ሥነ ሰብዓውያን 29. Renaissance - ዘመነ ትንሳኤ 30. Critical Thinking - ነቂሳዊ እሳቤ 31. Artificial Intelligence - ሰው ሰራሽ አስተውሎት 32. Sculpture - ኪነ ቅርፅ 33 Painting - ኪነ ቅብ 34. Premises - መነሻ ሐሳቦች 35. Argument - ነገረ ሐሳብ 36. Critical Social Theory - የማህበራዊ ነቀሳ ህልዮት 37. Thesis, Anti-thesis, Synthesis - አንብሮ፣ ተቃርኖ፣ አስተፃምሮ 38. Virtue - ምግባረ እሴት [ሰናይነት] 39. Altruism - ለሌላው ቅድሚያነት 40. Contemporary - ዘመነኛ 41. Existentialism - የአኗኗር ፍልስፍና 42. Authority - መሪ ሊቅ 43. Absurd - ወለፈንድ 44. Prejudice - ፅልማዊነት 45. The Problem of Evil - ነገረ እኩይ 46. Moral Evil - ክፋት 47. Scholastic - መጽሐፋዊ 48. Fallacy - ተፋልሶ 49. Historical Background - ታሪካዊ ዳራ 50. Being/Existence - ኑባሬ 51. Term - አኃዝ 52. Dialectic - ሕገ-ተቃርኖ