ከስነ-ፅሁፍ ዓለም
Статистика✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል! የቻናላችን https://t.me/Ethiobooks ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ። ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ @firaolbm እና @tekletsadikK ተጠቀሙ።
- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 11
- Всего постов
- 27
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 333
- 1/48двое суток
- 381
- 1/72трое суток
- 411
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ሹመት ═✦═ ✍ ሙሉጌታ ተስፋዬ (አያ ሙሌ) ' ሹመቴ ... ሺ ሞቴ ... እሱም እንደ ልቡ ... እኔም እንደ አሞቴ ባይልም ዳሞቴ እንደ ክራሞቴ ቢፈቅደኝ ... ሊያሞኘኝ ... ቢያቅደኝ ... ቢመኘኝ ... እኔ ምን ተዳዬ ... ሁሉም ያሻው ቢሆን ... ስንቄንና ትጥቄን ሳይሰጠኝ ... ላይሸኘኝ ... አሜን ብዬ ካደርኩ ... ምን አለ እሚሳነኝ አሀዱ ለፍቅር ... ለሰላም ሽልማት ምን አለ ልዕልና ... ከጣር ከህማማት ዕድሜ እየነገረ ... ልብ እየሰገረ ... እጅ እየጋገረ ... ቀን እየማገረ ... ቢሾሙም ... ጥንስስ ነው ቢመጡም ... እንጥስ ነው ቢሄዱም ... ብጥስ ነው ቢኖሩም ... ቅንጥስ ነው እሁ ..... ተነፈስኩ ፈሰስኩ ..... እንደ ደም ባልረጋም ... ካልተሾምኩ አልሰጋም። ═════════ 📔 የባለ ቅኔ ምህላ 🗓 2003 ዓ.ም. 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks
видео или голосовое, без подписи
ወ ታ ደ ር 👨🎨 👨🎨 👨🎨 ወታደር፣ ዋቶ አደር። 👨🎨 ወታደር ባለቃው፣ ባላገር በጭቃው። 👨🎨 ለወታደር በቅሎ፣ ለተማሪ ቆሎ። 👨🎨 ወታደር አወራውረኝ፣ ገበሬ አቆጣጥረኝ። 👨🎨 ወታደር ሲደኸይ፣ ጃኖ ያዘወትራል። 👨🎨 ዘንጋዳና ወታደር፣ በመኸር ጊዜ ይታይ ነበር። 👨🎨 ወታደር ቢበደር፣ ባላገር ይካስ። 👨🎨 ጦርነትን ከወታደር፣ ወሬን ከባላገር። 👨🎨 ለወታደር ሰፊ መንደር፣ ለወንዲላ መልካም ዱላ። 👨🎨 ሞኝ ወታደር፣ ሚስቱን ጥሎ መንደር። 👨🎨 ወታደር ሲያረጅ፣ አቃቤ ይሆናል። 👨🎨 ባጠፋ ወታደር፣ ይክሳል ባላገር። 👨🎨 በቅሎ ማዋስ ለወታደር፣ ሸማ ማዋስ ለባላገር። 👨🎨 የወታደር ፈዛዛ፣ የእናት ነዝናዛ፣ የሴት ቀበዝባዛ። 👨🎨 👨🎨 ነገር በምሳሌ @ethiobooks
видео или голосовое, без подписи
━ ስልታዊ ማፈግፈግ ━ (Strategic Retreat) ━━━━✦━━━━ ✍ ዶ/ር ኢዮብ ማሞ ' ስልታዊ ማፈግፈግ (Strategic Retreat) ማለት አንድን የጀመርነውን ነገር ርግፍ አድርጎ መተው ማለት አይደለም። ለወደፊት በብቃት ለመንቀሳቀስ ሲባል ለተወሰነ ጊዜ በብልሃት ወደ ኋላ ማፈግፈግ ማለት ነው። በሕይወት ውስጥ አንዳንዴ ለማሸነፍ ምርጡ መንገድ ወደ ፊት መግፋቱን መቀጠል ሳይሆን፤ ቆም ብሎ ማሰብ፣ ሁኔታዎችን መገምገም፣ ከተጎዳንበት ነገር ማገገም እና እራስን እንደገና ማዘጋጀት ነው። ስልታዊ ማፈግፈግ ማለት ጥንካሬን ለመጠበቅ፣ ግልጽነት ለማግኘት እና ለወደፊት ለተሻለ ውጤታማነት ለመዘጋጀት ሆን ተብሎ የሚወሰን ጊዜያዊ ዝምታ፣ ከነገሮች ዘወር የማለት፣ የመውጣት፣ የመቆም ወይም አቅጣጫን የመቀየር ውሳኔ ነው። ይህ ማለት፦ ✔️ ማቋረጥ ሳይሆን፣ መስተካከል (recalibrating) ነው። ✔️ ፍርሃት ሳይሆን፣ ጥበብ ነው። ✔️ መሸነፍ ሳይሆን፣ ለተሻለ የላቀ ግስጋሴ መዘጋጀት ነው። "አንዳንዴ ትልቁን ስእል ለማየት ወደ ኋላ ማፈግፈግ ያስፈልጋል" እንደሚባለው ማለት ነው። መቼ ነው ስልታዊ ማፈግፈግን ማሰብ ያለብን? 1. ወደ ፊት መቀጠል አላስፈላጊ ጉዳት ሲያስከትል፦ አንዳንድ ጊዜ ሁኔታው ውስጥ መቆየት የስሜትን ወይም የአካልን ጥንካሬ ሲያሟጥጥ መለስ ማለት ጥሩ ነው። 2. ግልጽነት እና አቅጣጫ ስንፈልግ፦ አንዳንድ ጊዜ ሕይወት ግራ ሲያጋባን፣ “ትክክለኛ አቅጣጫ ላይ ነኝ?" ብሎ ለመጠየቅ ማፈግፈግ አስፈላጊ ነው። 3. ዝለት (Burnout) ሲሰማን፦ አንዳንድ ጊዜ ብዙ ለፍተን ጥቂት ስናገኝ፣ ከመሯሯጣችን የተነሳ ውስጣችን ሲደክም መረጋጋት ያስፈልጋል። 4. መርዛማ (Toxic) ሰዎች ሲበዙብን፦ አንዳንድ ጊዜ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ከጥቅማቸው ጉዳታቸው ሲበዛና ጤና-ቢስ የሆነ ሃሳብና ተግባራቸው ሲበዛ ዘወር ማለት የግድ ነው። 5. ለታላቅ እድል ለመዘጋጀት፦ አንዳንድ ጊዜ እስካሁን በሠራነው ሥራ፣ በሄድንበት መንገድና በድግግሞሹ የሕይወት ለውጥና እድገት ካላገኘን ራሳችንን ለማሻሻል የትኩረት ለውጥ ማድረግ ወሳኝ ነው። በስልታዊ ማፈግፈግ ወቅት ምን ማድረግ አለብን? ስልታዊ ማፈግፈግ ስናደርግ ከከባድ ሁኔታዎች በማምለጥ ዝም ብለን ገለል ማለት ሳይሆን የሚከተሉትን ልምምዶች ማዳበር ማለት ነው። ➢ ማሰላሰል (Reflect)፡ ምን ትምህርት ተምሬያለሁ? ➢ ማገገም (Recover)፡ አካላዊ፣ ስሜታዊ እና መንፈሳዊ ጥንካሬን መመለስ። ➢ እንደገና መገምገም (Re-evaluate)፡ ምን መቀጠል አለበት? ምን ማቆም አለበት? ➢ ቦታ መቀየር (Reposition)፡ ቀጣዩ ሥራዬ ወይም እድሌ የት ነው? ➢ እንደገና መገንባት (Rebuild)፡ አዳዲስ ልማዶችን፣ ሥርዓቶችን እና አመለካከቶችን ማዳበር። አንዳንዴ ጥንካሬ የሚገኘው ዝም ብሎ ወደ ፊት በመገስገስ ሳይሆን መቼ ወደ ኋላ ማፈግፈግ እንዳለብን በማወቅ፣ በመረጋጋት፣ ጸሎት በማድረግ፣ አመለካከትን በማስተካከል እና ለቀጣዩ የሕይወት ምዕራፍ በመዘጋጀት ነው። ━━━━━━━━ 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks
видео или голосовое, без подписи
ዲፔንድራ - 2 የመጨረሻው!
ዲፔንድራ - 1
видео или голосовое, без подписи
▶ ዲፔንድራ ቢር ቢክራም ━━━━━━━━ «በደም የጨቀየው ቤተ መንግሥት» @ethiobooks
видео или голосовое, без подписи
💿 ሰ ው 💿 ══❁══ 🎤 ይርዳው ጤናው 🎧 @ethiobooks 🎼🎵🎶🎵🎶🎵 [ለፍቅር ቢደከም ቢለፋ የሚታመን ወዳጅም ቢጠፋ 2× አልሰለችም እጠብቃለሁ እኔ አልቆርጥም ተስፋ] 2× 🎶🎵🎶 ብዙ መቅረብ ቢጎዳኝም ደግነቴ ባይጠቅመኝም አልታክትም እጠብቃለሁ ለ'ኔ እስኪለው ቀኑ ሰው እስኪሰጠኝ 🎶🎶 [ሰው... ሰው... አሁንም ሰው 2× ይገኝ አይገኝ ባላውቅም ሰው ነው 'ምፈልገው አ... ዎ... ] 2× 🎵🎶🎵🎶🎵 [ለፍቅር ቢደከም ቢለፋ የሚታመን ወዳጅም ቢጠፋ 2× አልሰለችም እጠብቃለሁ እኔ አልቆርጥም ተስፋ] 2× 🎶🎵🎶 ለፍቶ መቅረት ባልመኝም ሰው መፈለግ አይደክመኝም መበደሌ ከዚ' እምነቴ መቼም አይለውጠኝ ሰው እስኪሰጠኝ 🎶🎶 [ሰው... ሰው... አሁንም ሰው 2× ይገኝ አይገኝ ባላውቅም ሰው ነው 'ምፈልገው አ...ዎ...] 4×|| 🎶🎵🎶 @ethiobooks
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የገደል መንገድ ━━✦━━ ያ ደግ ሰው በመንደሩ ውስጥ እየተዘዋወረ ሳለ፣ ወጣት ወንድና ሴት ከዛፍ ሥር ቁጭ ብለው ሲጫወቱ ተመለከታቸው። የሚያወሩት ነገር ከስሜት የተሠራ ስለኾነ የሰሚን ጆሮ ከሩቁ ጠልፎ ያመጣል። እንደ ሰንደል ሽታ በአየር ላይ የቃጫ ገመድ መስሎ ይጥመለመላል፣ ይፈታል፣ ይዘረዘራል። ሰሚ ጆሮ ቃል እያሸተተ ርምጃውን ያሳድጋል፤ ሩቅ ከነበረበት "ምንድር ነው? ምንድር ነው?" እያለ ይጠጋል። ያ ደግ ሰው ተጠጋ። በስሜት የታጀለ ንግግር ከወንዱ ወደ ሴቷ ይፈሳል። «አንቺና እኔ ጥቁር ምንጣፍ በመሰለ ጨለማ ላይ ብንንከባለል ጨለማው ርኩሰት የሌለበት ነጭ ሻሽ ነው የሚኾነው። ፍቅር የነገሠበት ቦታ ላይ ኹሉ ጽድቅ እንጂ ኩነኔ አይበቅልም» ይላታል። ሌላም ሌላም እያከለ ... ያ ደግ ሰው "ሰው አለ" ብሎ ለማሳወቅ ጒረሮውን ሲጠርግ፣ ኹለቱም ብርግግ ብለው ቆሙ። ሴቷም ቸኮል ብላ ተሰናብታ ኼደች። ያ ደግ ሰው፡ «እስኪ ና የኔ ልጅ! ትንሽ እንጫወት» አለው። ያ ልዝብ ቃል ይጥል የነበረው ወጣት እንደ ማፈር ብሎ ተጠጋው። «ካለየኸኝ ቦታ ኾኜ ስታወራ የነበረውን ነገር ሰምቻለኹ። እንኳን ኹለት እግር ያለውን ሰው አራት እግር ያለውን ፍጡር ያንሸራትታል። እውነት ይህች ልጅ ላንተ በትልቁ መዝገብ የተጻፈችልህ ከኾነ መደበቅም፣ መንሾካሾክም አያስፈልግህም። በሰው ፊት ጮክ ብለህ ትጠራታለህ። ያለ ጊዜው ነገርን ቢቆርጡት ግን ዘር ኾኖ አይነሣም።» «በምላስ ያልተወደደ ፍሬ አረም እንደሚባል፣ ከሰው ምላስ አትዋሉ። ተንጋዶ ያደገ ስሜት ፍሬው ዝሙት ይኾናል» አለው። ያ ወጣት እጁን እያሻሸ መሬት መሬት እያየ ነበር። ያ ደግ ሰው፡ «ቃልህ ግን ያምር ነበር - እንደ ፈሪ ወታደር ያለቦታህ እያፈሰስኸው ትጨርሰዋለህ እንጂ! ደሞ ትክክለኛዋ ሚስትህ ስትመጣ ምን ትላታለህ? ቀድመህ ቃልህን በትነኸው ተመልሰህ ልትሰበስበው ነውን?» አለው። ━━━━━━━━━ 📔 ግርባብ - ያ ደግ ሰው ✍ ፍቃዱ አየልኝ 📄 41 - 42 📖 📖 📖 📖 📖 https://t.me/Ethiobooks