Konso Zone Communication / ኮንሶ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
СтатистикаCommunication is the bridge between people and Government ! www.konsozone.org https://t.me/KonsoZone
- Последний пост
- 18:00
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 9
- Всего постов
- 27
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 148
- 1/48двое суток
- 169
- 1/72трое суток
- 182
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ወላጅ አጥ ተማሪ፤ የኮንሶ ልማት ማህበር የ2018 ጳጉሜ የበጎነት ንቅናቄን በይፋ አስጀምሯል ካራት፣ ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) የሰፊው ህዝብ ተቋም የሆነው የኮንሶ ልማት ማህበር (KDA) በትምህርትና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያለውን የበጎ ተግባር በማስቀጠል፣ “የ2018 ጳጉሜ ለላቀ በጎነት፣ አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ወላጅ አጥ ተማሪ” በሚል መሪ ቃል የድጋፍ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ ጀመረ። ንቅናቄው ከነሐሴ 10 እስከ 30/2018 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን፣ ዓላማውም በኢኮኖሚ አቅም ምክንያት የ2019 የትምህርት ዘመን የትምህርት መሳሪያ መግዛት ለማይችሉ ወላጅ አጥ ተማሪዎች ድጋፍ በማድረግ፣ ትምህርታቸውን በተስፋና በእኩል ዕድል እንዲቀጥሉ ማገዝ ነው። የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሽብሮ ሲካ እንደገለጹት፣ ተግባሩ የአጭር ጊዜ ድጋፍ ብቻ ሳይሆን በትምህርት ዕድል የተሻለ ነገን ለመገንባት የትውልድ ላይ የሚያተኩር በጎ ተግባር ነው። በመሆኑም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በንቅናቄው እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል። በዚህ መሠረት ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ በጎ ፈቃደኞች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ የሂሳብ ስም፦ KDA ESAP2 የሂሳብ ቁጥር፦ 1000056457872 በመጠቀም ድጋፋቸውን ማበርከት ይችላሉ። https://www.facebook.com/share/p/1Gk3hDwnp2/
📢 Telegram :- https://t.me/konsocommunication ▶️ YouTube :- https://youtube.com/@konsozonegovtcommunication?si=B6SNAh71M6ctoCxh 🌐 Website :- https://www.konsozone.org 🐦 X (Twitter) :- https://x.com/konso_zone 💬 WhatsApp Channel :- https://whatsapp.com/channel/0029VajH5rZHbFVAGLGuDG2C 🔗 All-In-One Links :- https://heylink.me/konsozonecomms 📷 Photo Request (ፎቶ ለመጠየቅ) :- https://www.konsozone.org/infoseekers/ ከተቋሞ ፎካል ፐርሰን ለመላክ፣ https://www.konsozone.org/focal-person/ #Communication_One_to_Man
ኮንሶ ዞን በሳምንቱ : የልማት፣ የአገልግሎት፣ የተቋማዊ አፈጻጸምና የማህበረሰብ ተሳትፎ ተግባራት በትኩረት የተከናወኑበት ሳምንት ካራት፣ ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን ) በኮንሶ ዞን ባሳለፍነው ሳምንት በጤና፣ በመንገድና ውሃ ልማት፣ በኃይል መሠረተ ልማት፣ በትምህርት፣ በሲቭል ሰርቪስ፣ በተቋማዊ አፈጻጸም፣ በስፖርትና በማህበራዊ ግንኙነት ዘርፎች በርካታ አበይት ተግባራት ተከናውነዋል። የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽንም እነዚህን ዋና ዋና ክንውኖች በመከታተል፣ በማጠናቀርና በተደራሽ የመረጃ አቀራረብ ለማህበረሰቡና ለተለያዩ የመረጃ ተቀባዮች አድርሷል ፣ በአብነትም :- | በጤና ዘርፍ የተጠናከረ አፈጻጸም የኮንሶ ዞን ጤና መምሪያ ከሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ከ1.2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ዕድሳት የተደረገለት አዳራሽ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል። በተጨማሪም የ2018 በጀት ዓመት የጤና ልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ አፈጻጸም በጥልቀት ተገምግሞ፣ የ2019 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ ዙሪያ ምክክር ተካሂዷል። ለተሻለ አፈጻጸም ላበረከቱ አካላትና ተቋማትም የምስክር ወረቀትና ሽልማት ተሰጥቷል። | ግብርናው ዘርፍ በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ዘርፍ ዞናችን የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፣በቀጣይ በይበልጥ ለመፈጸም የሚመለከተው ሁሉ በቅንጅት መረባረብ ይጠበቅበታል፣ | በተመሳሳይ በ2018 የገቢ አሰባሰብ ስራ ዞናችን በክልል ደረጃ የእውቅና ሽልማት አግኝቷል፣በቀጣይ ዓመት የበለጠ መረባረብ ከሁሉም የሚጠበቅ ይሆናል፣ | የዞኑ ምክር ቤት የአፈጻጸምና የበጀት ሂደቱን አጠናቋል የኮንሶ ዞን ምክር ቤት በዞኑ አስፈጻሚ ተቋማት የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ዕቅድ አፈጻጸምና የ2019 ዕቅድ ላይ ያካሄደውን ግምገማ በስኬት አጠናቋል። በተጨማሪም 13ኛ መደበኛ ጉባኤውን በልማት ሥራዎች የመስክ ምልከታ በማስጀመር፣ ከ2.3 ቢሊዮን ብር በላይ የሆነውን የዞኑን በጀት በማጽደቅ አጠናቋል። | የመንገድና የውሃ ልማት ሥራዎች በመስክ ተገምግመዋል በዓይዴ ገጠር ቀበሌ ከጮሮ አስፋልት መንገድ እስከ ኮላይቴ የሚዘልቀው የጠጠር መንገድ ሥራና በአካባቢው እየተከናወነ ያለው የውሃ ማስፋፊያ የመስመር ዝርጋታ በመስክ ተጎብኝቶ የአፈጻጸም ደረጃው ተገምግሟል። በተመሳሳይ ከፓሳቃ አስፋልት መገንጠያ ጀምሮ የከና ወረዳ መንገድ ጥገና ሥራ በይፋ ተጀምሮ፣ ሥራው በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትና ፍላጎት አስነስቷል። | የኮንሶ ኤሌክትሪክ ማስፋፊያ ሥራ ወደ ቀጣይ የቴክኒክ ሂደት ተሸጋግሯል ከEthiopian Electric Power የኢንጂነሪንግ ክፍል የተውጣጣ የኃላፊዎችና ባለሙያዎች ቡድን በኮንሶ ዞን ለሚገነባው የሳብስቴሽን ፕሮጀክት የግንባታ ቦታ ምልከታ፣ የዲዛይንና የሳይት መረጃ ማረጋገጥ እንዲሁም ቀሪ የሰርቬይንግ ሥራዎችን ለማከናወን ወደ ዞኑ ገብቷል። ቡድኑ ከዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ጋር ውይይት ካደረገ በኋላ የጋሞሌ አምባ መንደርን ጎብኝቷል። የቴክኒክ ሥራውን ከማከናወን ባሻገር የኮንሶን ታሪክና ባህል ለማወቅ ዕድል በመፍጠሩም ቡድኑ አድናቆቱን ገልጿል። | የተቋማዊ አፈጻጸምና የአመራር ግምገማ የኮንሶ ዞን ብልፅግና ኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን የ2018 ዓ.ም የ2ኛ መንፈቀ ዓመት የአመራር ግምገማና ምዘና አካሂዷል። በመድረኩ የተከናወኑ ተግባራት ተገምግመው ጠንካራ ውጤቶች እንዲጠናከሩና ጉድለቶች እንዲታረሙ የቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል። በተጨማሪም በ2018 በጀት ዓመት በፓርቲና በመንግስት ዘርፎች የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት በጥልቀት ተገምግመው ለቀጣይ ሥራ አቅጣጫ ተቀምጧል። | የካራት ከተማ ልማትና የግል ዘርፍ ተሳትፎ በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ገለቦ ጎልቶሞ የተመራ የከፍተኛ ሥራ ኃላፊዎች ልዑክ በካራት ከተማ የተለያዩ ልማታዊ ሥራዎችን በመስክ ጎብኝቷል። በግል ዘርፍ በመሰማራት የራሳቸውን ሕይወት ከመለወጥ ባሻገር በአካባቢው የሥራ ዕድል የፈጠሩ ተቋማትና ባለሀብቶችም ተበረታተዋል። | ለለውጥ የተጠራ የሲቭል ሰርቪስ ውይይት “በትጋት የተለወጠ የህዝብ አገልጋይ ነኝ!” በሚል መሪ ቃል ከዞን ማዕከል ሲቭል ሰርቫንቶች ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል። በመድረኩ ተገልጋይን ማንገላታት፣ አድሎአዊነት፣ አገልግሎትን በእጅ መንሻ መስጠትና ለቅሬታዎች ተገቢ ምላሽ አለመስጠት በአገልግሎት አሰጣጥ የሚስተዋሉ ችግሮች መሆናቸው ተነስቷል። የዞኑ አመራሮችም ሲቭል ሰርቫንቱ ከራሱ ጥቅም በላይ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም፣ በተመደበበት የሥራ መስክ በተጠያቂነት፣ በታማኝነትና በትጋት መሥራት እንዳለበት አሳስበዋል። | የኮንሶ ኒውዮርክ እግር ኳስ ክለብ የደጋፊዎች ማህበር የኮንሶ ኒውዮርክ እግር ኳስ ክለብ የደጋፊዎች ማህበር ተመስርቶ የአባላት የወር፣ የስድስት ወርና የዓመት መዋጮ ተመን ወጥቷል። ይህም የክለቡን ደጋፊዎች በተደራጀ መልኩ በማሰባሰብ ለክለቡ ዘላቂ ድጋፍ የሚፈጥር አደረጃጀት ሆኗል። | የጤና መረጃና ወረርሽኝ ቅድመ-ጥንቃቄ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ከሚዲያና የጤና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ጋር በመሆን የኢቦላ ቫይረስ በሽታን ጨምሮ ወረርሽኞችን በቅድመ-ጥንቃቄ ለመከላከል ሥልጠና ሰጥቷል። የበሽታው ምልክቶች፣ የመተላለፊያ መንገዶችና የሚዲያ ሚና በሥልጠናው ተነስተዋል። ትክክለኛና ተደራሽ የጤና መረጃን በተለይም በአካባቢ ቋንቋዎች በተከታታይ ማድረስ ወረርሽኝን በቅድሚያ ለመከላከል ወሳኝ መሆኑም ተጠቁሟል። | የ2019 የትምህርት ዘመን ምዝገባ ማስታወቂያ የኮንሶ ዞን ትምህርት መምሪያ የ2019 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 11 እስከ 20/2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ ለማህበረሰቡ አሳውቋል። | የፖሊስ አማካሪ ምክር ቤት የ2019 ዕቅድ የኮንሶ ዞን ፖሊስ ገለልተኛ አማካሪ ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በተዘጋጀው ዕቅድ ላይ ለምክር ቤቱ አባላትና ለምድብተኛ አመራር የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጥቷል። በሳምንቱ የተከናወኑ ተግባራት፤ ከመረጃ ማድረስ ባሻገር የለውጥ ታሪክን መመዝገብ ተችሏል :: በዚህ ሳምንት የተከናወኑት ተግባራት በቁጥር የሚገለጹ የልማት ክንውኖች ብቻ ሳይሆኑ፣ የተቋማት አፈጻጸምን ለማሻሻል፣ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ፣ መሠረተ ልማትን ለማስፋፋትና የማህበረሰቡን ተሳትፎ ለማጠናከር የተደረጉ ጥረቶች ናቸው። በተለይም የኮንሶ ህዝብ በግብርና ጥበብ፣ በባህልና በልማት ያበረከተው ድንቅ ሥራ በማህበራዊ ሚዲያ ትኩረት እንዲያገኝ በማድረግ፣ የአካባቢውን እውነተኛ ገጽታ ለሰፊው ህዝብና ለዓለም ማስተዋወቅ ተችሏል። የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በዞኑ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን፣ የመንግስት አገልግሎቶችን፣ ወቅታዊ መረጃዎችንና ማስታወቂያዎችን በተከታታይ ለማህበረሰቡ ማድረሱን ይቀጥላል። የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮቹን Like Follow Subscribe Share በማድረግ ወቅታዊና ተዓማኒ መረጃዎችን ይከታተሉ። 🔵 Facebook :- https://www.facebook.com/konsozone.org 📸 Instagram :- https://www.instagram.com/konsozonecommunication?igsh=MW1ncTJrenFzaWVsNA== 🎵 TikTok :- https://www.tiktok.com/@konsozonegovernmentcomms?_r=1&_t=ZS-97rRPAWRaSK
без подписи
ኮንሶ- የአካባቢ ጥበቃ ባህልና የግብርና ጥበብ የተዋሃዱባት ምድር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንሶ አካባቢ የሚገኙት ተራራማ ቦታዎች የተፈጥሮንና የሰው ልጅ ጥበብን አዋህደው የያዙ አስደናቂ ውብ መልክአምድር መሆናቸውን የግብርና ሚኒስትር አቶ አዲሱ አረጋ ገለጹ። አቶ አዲሱ አረጋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ የኮንሶ ህዝብ ለአያሌ ዘመናት ተራራማውን፣ አስቸጋሪውንና ቁልቁለታማውን መሬት በድንጋይና አፈር በመከለልና በመገደብ አሳምሮ በመደርደር ወደ ተዋቡ ምርታማ ቦታዎች ቀይረውታል ብለዋል። ይህ በእጅ የሚከወን የጥበብ ስራ መሬት እንዳይጎዳ፣ አፈር በዝናብ እንዳይሸረሸር በማድረግ አካባቢውን ለጥምር ግብርና ስራ ተስማሚ ማድረጉን ሚኒስትሩ አብራርተዋል። የኮንሶ እርከን ሥራ አስደናቂ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ጥበብ በውስጡ በርካታ ልዩ ባህሪያትን የያዘ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ የኮንሶ የእርከን ሥራ ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ የመኖር ሚስጥርን የያዘ የትጋትና የፅናት ትልቅ ማሳያ መሆኑን የጠቀሱት አቶ አዲሱ አረጋ፤ ኮንሶዎች ዛሬም ይህንን ትልቅ ድንቅና ውብ ቅርስ ጠብቀውና ተንክብክበው በመያዝ ለትውልድ እያስተላለፉ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ይህ አስደናቂ የአካባቢ ጥበቃ ስራ እ.ኤ.አ በ2011 በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የዓለም ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ ይታወቃል። #ሀገራዊመግባባት #ኢትዮጵያ_ትመካከራለች #konso #ዩኔስኮ #UNESCO
https://www.konsozone.org/የኮንሶ-ዞን-ብልፅግና-ኢንስፔክሽንና-የሥ/
https://www.facebook.com/share/17cZzdgEpn/
без подписи
የኮንሶ ኒውዮርክ እግር ኳስ ክለብ የደጋፊዎች ማህበር ተመሠረተ ካራት፡ ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) የኮንሶ ኒውዮርክ እግር ኳስ ክለብ የደጋፊዎች ማህበር ምስረታና የመጀመሪያ ዙር ጠቅላላ ጉባዔ ተካሂዷል። በመድረኩ የዞኑ ምክትል ዋና አስተዳዳሪና የክለቡ ፕሬዚዳንት አቶ ጉራሾ ጎስኬ እንደገለጹት፣ ኮንሶ ኒውዮርክ እግር ኳስ ክለብ የኮንሶ ሕዝብን የሚወክል አምባሳደር በመሆን በተለያዩ ውድድሮች ውጤታማ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል። ክለቡ በ2017 ዓ.ም በጂንካ ከተማ በተካሄደው የኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር አንደኛ በመውጣት የውድድሩ አሸናፊ መሆኑን ያስታወሱት አቶ ጉራሾ፣ ይህም የኮንሶን ሕዝብ ስም ከፍ እንዲል ያደረገ ስኬት መሆኑን ገልጸዋል። ክለቡ በ2018 የውድድር ዘመንም በአዳማ ከተማ በተካሄደው ሀገር አቀፍ ውድድር ንቁ ተሳትፎ ማድረጉን ጠቁመው፣ በዚህ ሂደት የዞኑ መንግሥት ለክለቡ የፋይናንስ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱንም አስረድተዋል። የደጋፊዎች ማህበሩ መቋቋም ዋና ዓላማም የክለቡን የገቢ አቅም በሕዝባዊ መሠረት ማስፋትና ከመንግሥት ለክለቡ የሚወጣውን ወጪ በመቀነስ ሀብቱ ለሌሎች የልማት ሥራዎች እንዲውል ማስቻል መሆኑን አቶ ጉራሾ ገልጸዋል። ከደጋፊዎች ማህበሩ በተጨማሪ ሁሉም የክለቡ ደጋፊዎችና የኮንሶ ሕዝብ ክለቡን በሞራል፣ በገንዘብና በእውቀት በመደገፍ የክለቡን ሁለንተናዊ ስኬት ለማጎልበት መረባረብ እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል። #SeeMore https://www.facebook.com/share/p/18782jV64v/
የተጠናከረ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራምና ብቁ ባለሙያዎች ጤናማና ፅዱ ህብረተሰብን ይገነባሉ፤ አቶ አራርሶ ጋሮ ካራት፣ ነሐሴ 01/2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) የኮንሶ ዞን ጤና መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የጤና ልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ አፈጻጸምን በመገምገም እንዲሁም የ2019 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድን ለማስቀመጥ ያተኮረ የምክክር ጉባኤ እያካሄደ ይገኛል። በጉባኤው ላይ የ2018 በጀት ዓመት የጤና ዘርፍ አጠቃላይ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በዞኑ ጤና መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ አራርሶ ጋሮ ቀርቧል። በሪፖርታቸውም መሠረታዊ የጤና አገልግሎቶችን ለማሳደግ ዋናው SeeMore, https://www.facebook.com/100069055695172/posts/1358793009765876/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v
ከ1.2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ዕድሳት የተደረገለት አዳራሽ ምረቃ ስነ ስርዓት ተካሄደ፣ ካራት:ነሐሴ 01/2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) የኮንሶ ዞን ጤና መምሪያ በክልሉ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያሳደሰውን አዳራሽ የዞኑ የፊት አሰተባባሪዎች በተገኙበት ተመርቋል፣ የአዳራሽ ምረቃ ስነ ስርዓት በአባቶች ቡራኬ የተጀመረ ሲሆን በግቢው የተከናወነው ልማታዊ ስራ እንደ ሀገር ከተጀመሩ የጤና ልማት ሪፎርም ስራዎች መካከል አንዱ ነው ሲሉ ገልጸዋል። https://www.facebook.com/100069055695172/posts/1358582653120245/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v
የኮንሶ ዞን ጤና መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የጤና ልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ ዙሪያ የምክክር ጉባኤ ማካሄድ ጀመረ፣ ካራት:ነሐሴ 01/2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) የኮንሶ ዞን ጤና መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የጤና ልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ ዙሪያ የምክክር ጉባኤ በመካሄድ ላይ ይገኛል :: https://www.facebook.com/100069055695172/posts/1358611739784003/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v
በኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ የተካሄደው እርቀ ሰላም ኮንፈረንስ ሙሉ ዝግጅት #KONSO #ETHIOPIA #SEGEN https://youtu.be/8urMld2Gpo0?si=DSAOnpNxbUuqDVTy
የኮንሶ ዞን ገቢዎች መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ባስመዘገበው አመርቂ የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከሚገኙ ዞኖች መካከል 3ኛ ደረጃን በመያዝ ተሸልሟል። see more https://www.konsozone.org/go/news/60
የካራት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ5ኛ ዙር በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን ሠልጣኞች አስመርቋል፣ ካራት:ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጁ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ70 በላይ ሠልጣኞችን አስመርቋል። በምረቃ ስነ ስርዓቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የካራት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ አማኑኤል ሲዳሞ በፖሊ ቴክኒክ ኮሌጃችን እየተሰጠ ያለው ስልጠና በዘንድሮው ዓመት 5ኛ ዙር ሲሆን ከዚህ በበለጠ ክልሉ የሚፈቅደው አዳዲስ የሙያ ዘርፎችን ለመጨመር ያለው ዕውቀትና ሙያዊ ክህሎት ከነበረበት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ኮሌጁ የያዘውን ራዕይ እውን ለማድረግ ሁሉም ሊረባረብ ይገባል ብለዋል። የካራት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ይህን ዕውቅና ካገኘ በኋላ ወዲያውኑ በክላስተር ደረጃ አጎራባች ኮሌጆችን እንዲያስተባብር በክልል ደረጃ ዕውቅና ማግኘቱን ገልጸዋል። አቶ አማኑኤል ጨምረው በዘንድሮ ዓመት ኮሌጃችን በቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድር በክልል ደረጃ ከተወዳደሩ ኮሌጆች መካከል 3ኛ ደረጃ አግኝቶ በቀጣይ 1ኛ ደረጃ ለማግኘት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፣ለዚህም ስኬት የሁሉም አካላት ርብርብ ይጠይቃል፡፡ በዘንድሮ ዓመት የአይሲቲ፣ የአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ የጋርመንትና የሰርቬይ ሙያ ዘርፎችን ሥልጠና አጠናቃችሁ ለዛሬ ምረቃ ቀን የበቃችሁ በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን! ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የዞኑ ስራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ስምኦን ገልገሎ በበኩላቸው የአንድ አገር ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚመሰረተው ብቁ፣ ሥራ ፈጣሪና ምርታማ የሆነ የሰው ሀብትን በመገንባት መሆኑን ገልጸዋል። የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ይህንን ግብ በማሳካት ረገድ ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ በመሆናቸው የዛሬው ተመራቂዎች በካራት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቆይታችሁ የወቅቱን የሥራ ገበያ የሚመጥን ክህሎት፣ ተግባራዊ ዕዉቀትና የሙያ ሥነ-ምግባርን እንዳገኛችሁ እናምናለንና በድጋሚ እንኳን ለዚህ ክብር አበቃችሁ ሲሉ ምኞታቸውን ገልጸዋል አቶ ስምኦን። የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ገለቦ ጎልቶሞ እንደገለጹት የዘንድሮው 5ኛ ዙር የሠልጣኞች ምረቃከባለፉት የምረቃ ስነ ስርዓት ልዩ የሚያደርገው ሀገራችን "ለሀገር በቀል ችግሮች ሀገር በቀል መፍትሄዎች" በሚል መሪህ የሀገራችን የቀጣይ ዕጣ ፈንታ ለመወሰን ሀገራዊ ምክክር እየተደረገ ባለበት መካሄዱ እናም ኮሌጁ ከቴክኒክና ሙያ ወደ ፖሊ ቴክኒክ ኮለጅ ያደገበት ወቅት ላይ መሆኑን ገልጸዋል። የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና የሀገራችን ኢኮኖሚ ዕድገት እና ኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን መሠረት ነው ያሉት ክቡር አቶ ገለቦ፤ዛሬ ከዚህ ኮሌጅ የሚትመረቁ ምሩቃን በዕውቀት፣በክህሎት እና በስራ ወዳድነት ታንጻችሁ ስራ ፈላጊ ሳትሆኑ ስራ ፈጣሪ ሆናችሁ ለዞናችን፣ለክልላችን ብሎም ለሀገራችን በሠለጠናችሁት ሙያ ለሁለንተናዊ ብልጽግና የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ፕረዝዳንት ኢ/ር ከማል አብደላ (ዶ/ር) እንደተናገሩት ዛሬ በፍጥነት በሚቀየር ዓለም ውስጥ የአንድ ሀገር እድገት የሚለካው በተፈጥሮ ሀብቷ ብቻ ሳይሆን፣ በሰው ኃይሏ፣ በእውቀቷ እና በሙያ ብቃቷ ነው። ስለዚህ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት የሥራ እድልን የሚፈጥር፣ የሥራ ፈጠራን የሚያበረታታ፣ የኢኮኖሚ እድገትን የሚያፋጥን ወሳኝ መሠረት ነው ብለዋል። የካራት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅም ይህንን ታላቅ ተልዕኮ በመሸከም ብቁ ባለሙያዎችን በማፍራት፣ ወጣቶችን በክህሎት በማብቃት እና ለማኅበረሰቡ ተጨባጭ አስተዋጽኦ በማድረግ የሚያኮራ ተቋም ነው፣ ይህንን ስኬት ያመጣችሁት የአመራሩ ቁርጠኝነት፣ የመምህራን ትጋትዠ፣ የተማሪዎች ጥረት እና የማኅበረሰቡ ድጋፍ በመተባበር መሆኑን አስገንዝበዋል። የቀድሞ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ዘርፍ ኃላፊና የአሁኑ የባስከቶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር በዛብህ ገበየሁ በበኩላቸው የዛሬው ቀን ሠልጣኞች የትጋታቸውንና የልፋታቸውን ፍሬ ያገኙበት ልዩ ቀን ነው ብለው የካራት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሰው ሀይል በማፍራትና በቴክኖሎጂ ሽግግር እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ የሚነደቅ ነው ብለዋል። ኮሌጁ ለ5ኛ ዙር ያስመረቃቸው ሠልጣኞች በአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ 8፣በአይ ሲ ቲ 60፣በጋርመንት ቴክኖሎጂ 5 እና በሳርቬይንግ 4 አጠቃላይ ድምሩ 77 ሠልጣኞች መስመረቁን የኮሌጁ ምክትል ዲና የሰው ሀይል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገልሲሞ ገመይዳ ገልጸዋል። በምረቃ ስነ ስርዓት ላይ የቀድሞው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ዘርፍ ኃላፊና የአሁኑ የባስከቶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር በዛብህ ገበየሁ፣የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ፕረዝዳንት፣የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ገለቦ ጎልቶሞ፣የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ጉራሾ ለሚታ፣የክልል ከፍተኛ ስራ ኃላፊዎች፣የዞኑ የፊት አስተባባሪዎች፣የካራት ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣የወረዳዎች አስተዳዳሪዎች ተሳትፈዋል። በኩሲቶ ካንቢሮ SeeMorePhotos, https://www.facebook.com/share/p/18CPfgo4qd/
без подписи
https://t.me/AbiyAhmedAliofficial?livestream
без подписи
без подписи
без подписи