ንቁ | Waken
СтатистикаIn this Channel We Share Information,Ideas,Creativity,Books and many others.Join us for Cognizance and make the world better with us. በዚህ ቻናል መረጃን ፣ሀሳቦችን ፣ፈጠራን ፣መፅሃፎችን እና ሌሎችንም እናካፍላችኋለን።ለማወቅ ይቀላቀሉ እና አለምን ከኛ ጋር የተሻለ እናድርግ። https://t.me/waken_joe
- Последний пост
- 12 июн.
- Последнее чтение
- ещё не заходили
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
💀 See everything, say nothing. Observe the world with wisdom and patience. Not every thought needs to be spoken, and not every situation requires a reaction. True strength often lies in understanding more than you reveal. Silence can be more powerful than words.
🧠 ዲዮጋነስ ማን ነው? ባጭሩ ዲዮጋነስ የጥንታዊ ግሪክ ፈላስፋ ነበር። እሱ የ“Cynic” ፍልስፍና ተከታይ ነበር — ማለትም ቀላል እና ነፃ ኑሮ የሚያምን። 🏺 ታሪኩ እንዴት ነበር? 😔 መጀመሪያ ላይ ከአገሩ ተሰዶ ነበር (ስህተት ወይም ችግር ምክንያት)። ከዚያ በኋላ በአቴንስ ውስጥ ቀላል ኑሮ ጀመረ። 🏠 ቤት አልነበረውም… 🛢️ በትልቅ በርሜል (barrel) ውስጥ ይኖር ነበር። 💰 ገንዘብ፣ ክብር እና ሀብት አይወድም ነበር። “ሰው ደስታ በቀላል ነገር ይመጣል” ይላል። 🔦 ታላቁ ታሪኩ (ከንጉሥ ጋር) 👑 አንድ ቀን የዓለም ታላቁ ንጉሥ Alexander the Great መጣ። “ምን እፈልጋለሁ እንድረዳህ?” አለው። 😎 ዲዮጋነስ ግን በቀላሉ መለሰ፦ “ከፀሐይ ብርሃን አትከልክለኝ ትንሽ ወደ ጎን ሂድ…” 🔥 ንጉሡ ተደነቀና አለ፦ “እኔ አሌክሳንደር ነኝ!” 🧠 ዲዮጋነስ ግን በትልቅ ትምክህት ሳይደነቅ መለሰ፦ “እኔ ዲዮጋነስ ነኝ… ምንም አልፈልግም።”
2. አምላክ God = Nothing - Something ይህ ቀመር የአምላክን ረቂቅነት እና ሁሉንም ነገር አቃፊነት የሚያሳይ ነው። አምላክ "ምንም" (Nothing) እና "አንድ ነገር" (Something) መካከል ያለውን ክፍተት የሚሞላ ህልውና ነው፡፡ "Nothing" የሚለው ቃል ባዶነትን ሳይሆን፣ ገደብ የሌለውንና ቅርጽ ያልያዘውን (Infinite/Formless) አቅም ያሳያል። "Something" ደግሞ እኛ የምናየውን፣ የምንዳስሰውንና በስም የምንጠራውን ቁሳዊ ዓለም ይወክላል። አምላክ ከቁሳዊው ዓለም ("Something") በላይ የሆነ፣ ነገር ግን ቁሳዊውን ዓለም ያስገኘ የሁሉ ነገር መገኛ ነው፡፡ ምሳሌ .....፦ አንድን የሸክላ ዕቃ ብንወስድ፣ ዕቃው "Something" ነው። ያ ዕቃ ከመሰራቱ በፊት በሸክላ ሰሪው አእምሮ ውስጥ የነበረው ሃሳብ ግን "Nothing" (ገና ያልታየ) ነው፡፡ አምላክ ያንን ያልታየውን ወደ ታየው የመለወጥ ሚስጥር ነው፡፡ እንዲሁም በጠፈር(Space) ውስጥ ያሉ ከዋክብት "Something" ሲሆኑ፣ እነርሱን የያዘው ሰፊው ባዶነት ደግሞ "Nothing" ነው፡፡ አምላክ በሁለቱም ውስጥና ባሻገር ያለ ህልውና ነው። Join us 👉 @waken_joe
1. ደስታ | Happiness 😊 Happiness = Life - Expectations 👉ደስታ በቁሳቁስ ክምችት ወይም በስኬት ብዛት የሚለካ ሳይሆን፣ በምንኖረው እውነታ (Life) እና በምንመኘው/በምንጠብቀው (Expectations) መካከል ያለው ልዩነት ውጤት ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የሰው ልጅ "ደስተኛ የምሆነው ይህ ሲሟላልኝ ነው'' የሚል ቅድመ-ሁኔታ ያስቀምጣል። ይህ "የሚጠበቅ ነገር" (Expectation) በጨመረ ቁጥር ካለን የህይወት እውነታ ጋር ሰፊ ክፍተት ይፈጥራል። ቀመሩ እንደሚያሳየው፣ ከህይወታችን ላይ የምንጠብቀውን ነገር ስንቀንስ (ወይም ወደ ዜሮ ስናስጠጋ) ውጤቱ እውነተኛ ደስታ ይሆናል። ምሳሌ .....፦ ሁለት ሰዎችን ብንወስድ፤ አንደኛው ሰው በልደቱ ቀን ውድ መኪና በስጦታ እንደሚሰጠው ጠብቆ ነበር (Expectation = 100)። ነገር ግን የተሰጠው ስልክ ነው (Life = 20):: ውጤቱ 20-100= -80 (ሀዘን)😞ይሆናል። ......ሁለተኛው ሰው ግን ምንም ዓይነት ስጦታ አልጠበቀም (Expectation = 0)። ስልክ ሲሰጠው ግን ውጤቱ 20-0=20 (ደስታ) ይሆናል። ደስታ የሚመነጨው ካለህ ነገር ሳይሆን፣ ከጠበቅኸው ነገር አንጻር ባለው ስሌት ነው:: Join us 👉 @waken_joe
አራቱ የንቃተ-ሕሊና ቀመሮች 1. እውነተኛ ደስታ | Happiness 2. አምላክን ማወቅ | Know the Creator GOD 3. እውነተኛ እምነት | Faith 4. እኔ"ነትን መካድ | Kill the Ego በቀጣይ እያንዳንዱን ክፍል ተንትነን እናያለን stay tuned 😎 Join us 👉 @waken_joe
#ውጤታማ #የቤትህን_ድመት ጠይቅ።🐾 ውጤታማ ለመሆን የግድ የሰው ምክር ብቻ አያስፈልግህም፤ የቤትህን ድመት ተመልከት! ከእሷ የምንማራቸው 5 ቁልፍ ትምህርቶች፡- :-ትኩረት (Focus):ድመት አድባ ስትይዝ አይኗ ሌላ ቦታ አያይም። አንተም በአንድ ጊዜ አስር ስራ አትጀምር፤ በአንዱ ላይ አተኩር። * መላመድ (Resilience): ድመት ከየትም ብትወድቅ በእግሯ ነው የምታርፈው። ውድቀት ሲያጋጥምህ እንዴት ተመልሰህ እንደምትቆም እንጂ ስለመውደቅህ አትጨነቅ። * እረፍት (Rest): ድመት ስትተኛ በደንብ ነው፤ ስትሰራም በንቃት ነው። ውጤታማ ለመሆን በቂ እረፍት አድርግ፤ ማሽን አይደለህም። * ድንበር (Boundaries): ድመት ካልፈለገች አትጠጋትም። ጉልበትህን ለሚበዘብዙ ሰዎች "አይ" ማለትን ተለማመድ። *ንጽህና (Self-Care): ራስህን ጠብቅ። ድመት ራሷን ለመንከባከብ ጊዜ አታጣም፤ አንተስ ለራስህ ምን ያህል ጊዜ ሰጥተሃል?
Brain of IT Support specialist.......
God doesn't give hard roles to weak souls he choose you for a reason. ❄️ ችግሮች እና መከራዎች ቢፈራረቁብን ለምክንያት ነው it's because GOD Believes in us and to make us Stronger For Hard days. 🙏 Join us 👉 @joe_imagination
ስሜቶችህን ካልተቆጣጠርክ.... በቅጽበት የስሜት ግንፈላ የገነባኸዉን ማንኛዉንም ነገር ልታጣ ትችላለህ።የለፋህበትን ልታፈርስ ትችላለህ።በአፍታ ንዴትም ሰዉ ገድለህ ለእድሜ ልክ እስርና ለዘላለም ጸጸት ልትዳረግ ትችላለህ....ስሜትን መቆጣጠር አለመቻል ዋጋዉ ከባድ ነዉ። «ስሜትን መቆጣጠር» ትርጉም፦ሀኒም ኤልያስ Join us 👉 @joe_imagination
ካስመሰልክ ከሰው ጋር በሰላም ትኖራለኽ እምቢኝ ካልክ ደግሞ ትገለላለህ፤ በቤትህ፣ በጎረቤትህ፣ በመስሪያ ቤትህ፣ በሃገርህ ባዕድ ትሆናለህ" ይህ ማለት ግን በማስመሰልህ በሰላም ትኖራለህ ማለት አይደለም።በማስመሰልህ ከሌሎች ጋር ብትኖርም ለራስህ ግን ባዕድ ነህ፡፡ ከሰው መሃል ሆነህ ከራስህ ግን ተገልለሃል፡፡ እያንዳንዱ ድርጊትህ ከራስህ ወይ ከሌላው ይለይሃል፤ ትልቁ የመኖር አጣብቂኝም ይሄ ነው። 📓አለመኖር Join us 👉 @Informative_Joe
"በህይወት ውስጥ አኩሪ ነገር በጭራሽ አለመውደቅ ሳይሆን ወድቆ መነሳት ነው!" – Nelson Mandela
ከመካሪዎች ሁሉ ብልሁ ጊዜ ነው! “Time is the wisest counselor of all.” – Pericles @Informative_Joe
ሁላችንም የምንፈልገው አንድ ነገር ነው፤ ሙሉ በሙሉ የሚያምነን አንድ ሰው። ችግሩ ግን፣ ያንን ሰው ስታገኘው፣ ትልቁን ድክመትህን አግኝተሃል ማለት ነው። ምክንያቱም ያንን ሰው ሊጠቀሙብህ ይችላሉ፤ ያንን ሰው ሊጎዱብህ ይችላሉ። ፍቅር በዚህ አለም ውስጥ እጅግ አደገኛው መሳሪያ ነው። Join us @Informative_Joe
🗣ሰይጣን የምናወራውን እንጂ የምናስበውን አያውቅም።ስለዚህ በዝምታ ስሩ፤ያለጥርጥር ይሳካላችኋል።
ወደ ገነት የገባው የመጀመሪያው ሰው ወንበዴ ነበር ።ወደ ሲኦል የገባው የመጀመሪያው ሰው የጌታ ሐዋርያ ነበር ስለዚህ ልትጨነቁ የሚገባው እናንተ በሰው አይን ማን እንደሆናችሁ ሳይሆን በፈጣሪ አይን እኔ ማነኝ ብላችሁ መሆን አለበት። "ኦሾ" #ፍልስፍና #ኦሾ Join us 👉 https://t.me/Informative_Joe
ቆንጆ ማለት ለዓይን የሚማርክ፣ ለጆሮ የሚጥም፣ የሚያምር፣ የሚያስደስት፣ የሚያማልል፣ ሰው፣ እንስሳ፣ ሳር፣ ቅጠል፣ አየር፣ ውሃ፣ ቃል፣ ሁኔታ፣ ድርጊት ሌላም መዓት ትርጉም ይኖረዋል፡፡ አሻሚ ነው ቃሉ፡፡ 'ውብ' የሚለው ቃል ግን አያሻማም አያደናግርም፣ “ውብ” ማለት “እናቴ” ማለት ናት ! የእኔ እማማ ብቻ !! አዎ እናቴ ውብ ናት !! በችግር የማይፈታ ውበት፡፡ ማንም በአድናቆት ቃል በእንቶፈንቶ ድለላ ውሉን እጁ አስገብቶ የማይተረትረው ነጭ ቱባ ናት እማማ ፤ ፈገግ ስትል ከጥርሶቿ ድል ማድረግ በአካባቢው ይነዛል፡፡ እንደ እናቴ ፈገግታ ልብ የሚሰነጥቅ ሳቅ አላየሁም፤ የእናቴ ፈገግታ ብርታቴ ነው፡፡ ሰውነቴ በፈገግታዋ ይታደሳል፡፡ የተፈጥሮ ፍልውሃ ነው ፈገግታዋ !! 📓ዶክተር አሸብር እና ሌሎች Join us 👉 https://t.me/Informative_Joe
ፅኑ ስብዕና (resilient personality) የወርቅ ንፅህና በእሳት ተፈትኖ እንደሚለየው የሰው ልጅ ፅናትም በመከራ ውስጥ ነው ፍንትው ብሎ የሚወጣው። ለምሳሌ ሁለት ነጋዴዎች በተመሳሳይ ጊዜ ሊከስሩ ይችላሉ። ማንነታቸው ግን የሚወሰነው በደረሰባቸው ኪሳራ ሳይሆን ለኪሳራው በሰጡት ምላሽ ይሆናል። አንዱ ተስፋ ቆርጦ ድባቴ ውስጥ ሊዘፈቅ ይችላል፣ ሌላው ደግሞ የተሻለ ለመስራት ሊነሳሳ ይችላል። ፅኑ ስብዕና ምንድን ነው? ፅኑ ስብዕና ማለት በተለያዩ የሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ተፈትኖ ማለፍ፣ ወድቆ የመነሳትና ችግሮችን ወደ ዕድል የመለወጥ ማንነት ነው። ለመሆኑ፣ የሰብዕናችን የፅናት ደረጃ ከፍ ያለ ወይ ዝቅ ያለ መሆኑን እንዴት እንለያያለን? ሀ) ቀና አመለካከት (Optimism) ለነገሮች ያላቸው አመለካከት ቀና ነው። ሁሌም ችግሮች ጊዜአዊ እንደሆኑና "ሁሉ ነገር ለበጎ ነው" የሚል አስተሳሰብ አላቸው። ለ) ተጣጣፊነት (flexibility) በታላቅ አውሎነፋስ ውስጥ ብዙ ዛፎች ተገንድሰው ሲወድቁ የዘንባባ ዛፍ 🌴ግን ያንን አውሎ ነፋስ ዝቅ ብሎ ያሳልፍና መልሶ ቀና ይላል። ፅኑ ስብዕና ያላቸው ሰዎችም ልክ እንደ ዘንባባ ለተለያዩ ችግሮች የተለያዩ ምላሾች በመስጠት ያልፉታል፤ መናገር ሲገባቸው ይናገራሉ፣ ዝም ማለት ሲኖርባቸው አያወሩም፣ አንድን ችግር ችክ ብለው በተመሳሳይ መንገድ ለመፍታት አይዳክሩም። ሐ) አለማስመሰል (Genuine) ፅኑ ሰዎች ያልሆኑትን መስለው መታየት አይፈልጉም፤ ደካማ ጎናቸውን ለመሸፋፈን አይሯሯጡም። የሌላቸውን "አለኝ" ለማለት ለታይታ ሲሉ የተለያዩ ጭምብሎችን በማጥለቅ በማጥለቅና በማውለቅ አሳራቸውን አይበሉም። Join us 👉 https://t.me/Informative_Joe
ወደ ቤተመንግስት የመግቢያው መንገድ ምንጩ ያልታወቀ የጥንት አባባል እንዲህ ይላል፣ “ወደ ቤተ መንግስት የመግቢያው መንገድ ሁለት ነው፡፡ አንደኛው ንጉስ መሆን ነው፡፡ ሁለተኛ ግን የንጉሱ ታማኝ አገልጋይ በመሆን ነው”፡፡ ከላይ የተጠቀሰውን አባባል ከፖለቲካና መሰል ሁኔታዎች አንጻር ብቻ ለመመልከት ጊዜህን ሳታባክን በቀጥታ በየእለት ሕይወትህ አድገህ ልታገኘውና ልትደርስበት ከምትፈልግበት የስራ፣ የእውቀትና የመሳሰሉት ደረጃዎች አንጻር ተመልከተው፡፡ ጥሩና አትራፊ ንግድ ውስጥ ለመግባት ከፈለክ እዚያ ውስጥ የገባን የንግድ “ንጉስ” በማገልገል ጀምር፤ መግባትህ አይቀርም፡፡ የላቀ የእውቀት ዘርፍ ውስጥ ለመግባት ከፈለክ በእውቀቱ አለም የላቀውን የእውቀት “ንጉስ” አገልግል፤ መግባትህ አይቀርም፡፡ በአንድ ስኬታማ መስሪያ ቤት ውስጥ የላቀው ደረጃ መድረስ ከፈለክ በዚያ መስሪያ ቤት ውስጥ ያለውን የአመራር “ንጉስ” በማገልገል ጀምር፤ መግባትህ አይቀርም . . . እያለ ተግባራዊነቱ ይቀጥላል . . . በፉክክር፣ በጥላቻ፣ አንዱን ጥሎ ለመነሳት በመሞከር፣ ስም አጥፍቶ የራስን ስምና ዝና ለመትከል በመሞከር አንድ ደረጃ ለመድረስ ከመታገል ይልቅ የላቀው መንገድ ራስን ቀለል አድርጎና ከእኛ የቀደሙትን እንስቶ፣ አክብሮና አገልግሎ ከእነሱ ጋር አብሮ የመነሳት መንገድ ነው፡፡ Join us https://t.me/Informative_Joe
Who are you When Nobody's Watching?
Know the Difference Mr. '' Mister'' :- used for all adult men Mrs. '' Missus'' :- used for married women Ms. '' Mizz'' :- used for all adult women Miss :- used for girls or Single women Join us https://t.me/Informative_Joe