tgindex
ህይወትን በጥበብ

ህይወትን በጥበብ

Статистика

CONTACT ADMIN👦➖ @Eftah12 GROUP :- https://t.me/big_dreamerss

Последний пост
19 сент. 2025 г.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
15 авг.
Подписчики
1 189
0 за сутки
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
2 149
19 постов
Вовлечённость
180,7%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • #በመሬት_ልብ_ውስጥ_ያለው_ወርቅ በአንተ አእምሮ ውስጥም አለ! ሀሳብ የመፍጠር ኃይል ነው ወይም የፈጠራ ኃይል እንዲንቀሳቀስ ማድረግ የሚችል ተጽዕኖ ፈጣሪ ኃይል ነው፡፡ በተወሰነ መንገድ ማሰብ ሀብትን ወደ እናንተ ያመጣል፡፡ ነገር ግን ለተግባራችሁ ትኩረት ሳትሰጡ በሀሳባችሁ ላይ ብቻ መተማመን የለባችሁም፡፡ ብዙ ሳይንሳዊ ሜታፊዚክስ አሳቢዎች የሚሰናከሉበት አለት ይህ ነው፡፡ ሀሳብን ከግለሰባዊ ተግባር ጋር ማገናኘት አለመቻል፡፡ ካለ ተፈጥሯዊ ሂደቶች ወይም ካለ ሰው ልጅ ጣልቃ ገብነት ነገሮችን ከቅርጽ አልባው ንጥረ ነገር መፍጠር ይቻላል ብለን ብንል እንኳን የሰው ልጅ እንደዚህ አይነቱ የእድገት ደረጃ ላይ አልደረሰም፡፡ #ሰው_ማሰብ_ብቻ_ሳይሆን_ያለበት፣ የግል ተግባሩም ሀሳቡን የሚያሟላ መሆን አለበት፡፡ በመሬት ልብ ውስጥ ያለውን ወርቅ በሀሳባችሁ ኃይል ወደ እናንተ እንዲመጣ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን ወርቁ እራሱን ከመሬት አውጥቶ፣ አጣርቶ፣ ቅርጽ ያለው ሳንቲም አድርጎ በጎዳናዎች ላይ እየተሽከረከረ ወደ ኪሳችሁ አይገባም፡፡ @lifeandwisdom

  • Invest in yourself ⏰⏰⏰ " ለሰው ልጅ ሁሉ እኩልና ያለስስት የተሰጠ ሀብት ቢኖር ጊዜ ነው ። ጊዜህን መጠቀም ስትችል እራስህን ትለውጥበታለህ...ራሥህን መለወጥ ሥትችል ሌሎችንም ትለውጣለህ ። ራስህን ለመለወጥ ጊዜን ካልወሰድህ ሌላን መለወጥ አትችልም ። ( Invest in your self )ራስህ ላይ ፈሰስ አድርግ መጀመርያ ራስህን ለውጥ ። አስተሳሰብህን ሞርድ ፣ እይታህን አጥራ ፣ ንግግርና እርምጃህን ገምግም ነገ የሚኖርህ ዛሬን ስትጠቀምበት ነው ። ከዛሬም ያለህ ጊዜ አሁን ነው...አሁን ደግሞ እያለፈ ነው! ጥያቄው እንዴት እያለፈ ነው የሚለው ነው ። ለዚህ ጥያቄ የምትመልሰው መልስ #ነገ በምትለው ምናባዊው ቀን ላይ ያለህን አንተነት ይወስነዋል ። " ዛሬህን ተጠቀምበት... @lifeandwisdom

  • ፍላጎትን ለፍርሃት የማስበለጥ ስኬት “እንዲሳካልህ ከፈለክ፣ ካለብህ የመውደቅ ፍርሃት ይልቅ ለስኬት ያለህ ፍላጎት ሊልቅ ይገባዋል” – Bill Cosby ከልባችን ያልተጸየፍነውን ነገር አንሸሸውም፤ በጽኑ ያልፈለግነውንና ያልተከታተልነውን ነገር ደግሞ በፍጹም ልንደርስበት አንችልም፡፡ የአንድ አንድ ሰው ሕልም በትምህርት አንድ ደረጃ መድረስ ነው፡፡ የሌሎች ሕልም ደግሞ ቤተሰባቸው አሁን ካለበት ችግር ማላቀቅ ነው፡፡ ከዚህም ባለፈ ሁኔታ፣ በስራ፣ በግል ጤንነት፣ እና በሌሎች ሁኔታዎች አንጻር ሰዎች ግብን አውጥተው እዚያ ለመድረስ ይጣጣራሉ፡፡ የእነዚህ ሁኔታዎች መሳካት የአጠቃላይ ሕይወት መሳካት ባይሆንም የስእሉ አካል ስለሆኑ አስፈላጊ ጉዳዮች ናቸው፡፡ በዚህ ሰው ሁሉ በሚጋራው አንድ ደረጃ የመድረስ ጉዞ ውስጥ ማንንም የማይምር አንድ ችግር አለ፤ እርሱም የፍርሃት ችግር ነው፡፡ ሁላችንም ቢሆን በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የምንፈራቸው ነገሮች አሉን፡ የመውደቅ ፍርሃት፣ ስኬት የማጣት ፍርሃት፣ ተቀባይነት የማጣት ፍርሃት፣ ጀምሮ የማቋረጥ ፍርሃት …፡፡ በአጭሩ፣ ከፍርሃት ነጻ የሆነ ሰው የለም፡፡ ይህንን ሰው ሁሉ የሚጋራውን ፍርሃት የተሰኘውን ተራራ አልፎ ወደ አላማ ለመዝለቅና ወደግባችን ለመድረስ ያለን የውስጥ ፍላጎት ካለብን ስጋትና ፍርሃት በብዙ እጥፍ ሊጠነክር ይገባዋል፡፡ ለመራመድ ያሰብከውን እርምጃ አስበውና ያንን ነገር ለማድረግ ያለህን ፍላጎትና በውስጥ የምትፈራውን ነገር በሚዛን ላይ አስቀምጣቸው፡፡ የትኛው ያመዝናል? ፍርሃቱ ካየለ ወደኋላ ያስቀርሃል፣ ፍላጎቱ ካየለ ግን ፍርሃትህን አሸንፈህ እንድትዘልቅ ብርታት ይሆንሃል፡፡ ፍላጎትህን ከፍርሃትህ ለማስበለጥ ከፈለክ ደግሞ ክምትወስደው እርምጃ የተነሳ የምታገኛቸውን ወሳኝ ለውጦችና ጥቅሞች ማሰብ፣ ማወቅና ማሰላሰል ያስፈልጋል፡፡ @lifeandwisdom

  • #ሕይወትን_በዛሬ_ልክ_ኑር! ኢትዮጵያዊው የበረሃ መልእክተኛ አባ ሙሴ እንዲህ ተብለው ተጠየቁ ‘ለነገ አትጨነቁ፤ (ማቴ ፮፥፴፬) ተብሎ የተጻፈው ለማን ነው?’ ሽማግሌውም መለሱ፣ “ስቃዬ ምነው በዛ መቼስ ነው የሚያበቃልኝ፣ ብሎ ለሚጨነቅ ሰው ነው የተጻፈው። ከዚህ ይልቅ ለራሱ “ዛሬ” ማለት አለበት” ብዙውን ጊዜ አዲስ አመት በመጣ ቁጥር፣ ከቀደመው ጠባያችን ሳንላቀቅ፣ የኃጢአት ኮተቶቻችንን እንደያዝን፣ “ይሄኛው አመት የተለየ ይሆናል፣ የተሻለም እሆናለሁ!” እንላለን፣ ሆኖም አባ ጴሜን እንዳሉን... ህይወትን በዛሬ ልክ መኖር አለብን። ከውድቀት ራሳችንን ማስቀረት ባንችል እንኳ፣ ብንወድቅም የሚያነሳን አባት አለንና አስቀድመን መጨነቅ አያስፈልገንም፤ ጭንቀታችን ሁሉ ለአምላካችን ሰጥተን ዛሬ ላይ ብቻ የምንችለውን ማድረግ ይኖርብናል፤ ነጋችንን እሱ ብቻ ያውቃልና። ማለዳችንን እግዚአብሔርን በማመስገን ከጀመርን፣ ስቃያችን በአዲስ ህይወት የሚቀየርበት ቀን ይሆንልናል። @lifeandwisdom

  • #ይሄኔ_የት_በደረስኩኝ_ነበር?! • ሰዎች በእኔ ላይ ምን እንደሚያስቡ ለማወቅ የታገልኩትን ያህል ራሴን ለማወቅ ብሰራ ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • በፍጹም የማይፈልጉኝን ሰዎች ስለማመጥና ስከታተል ያሳለፍኩትን ጊዜ ለእኔ ዋጋ ላላቸው ሰዎች ሰጥቸው ቢሆን ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • በማያገባኝ የሰዎች ስራና ሃሳብ ላይ በማውራትና በመቃወም ያባከንኩትን ጊዜ የሚደገፍ ሰው ፍልጌ ደግፌ ቢሆን ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • በየጊዜው ካለእቅድ የማወጣቸውን የገንዘብ መጠኖች በጥንቃቄ ብቆጥባቸው ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • ምንም ያህል ብጨነቅ መለወጥ በማልችላቸው ነገሮች ላይ መጨነቄን ትቼ ለመለወጥ አቅም ያለኝ ነገሮች ላይ አተኩሬ ቢሆን ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • የሚወዱኝ ቤተሰቦቼና ጓደኞቼ ሲመክሩኝ የመስማትና ጥሩውን ምክር የመቀበል ልማድ ኖሮኝ ቢሆን ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • ለመጀመር ያሰብኳቸውን እነዛን ወሳኝ ነገሮች ጀምሬያቸው ቢሆን ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • የማይሆኑ የማሕበራዊ ጎጾች ሳስስ ያመሸሁባቸውን ምሽቶች የቀኑን ውሎየን ለመገምገምና ለነገ በማቀድ ባሳልፋቸው ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • ለየእለት ገጠመኞች ምላሽ እየሰጡ ከመሯሯጥ ይልቅ በራእይና በዓላማ ኖሬ ቢሆን ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! ያም ሆነ ይህ ያለፈው አልፏል! ከጥቂት አመታት በኋላ እንደገና “ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?!” የሚል የግምገማ ስሜት እንደሚመለስብኝ ስለማውቅ አሁኑኑ ለውጥን አመጣለሁ። @lifeandwisdom

  • #እስቲ_ለአላማ_ኑር! ህይወትህን ለአላማ ኑር! ትኩረትህን ያለህ ነገር ላይ መባረክህ ላይ አድርግ። በሌለህ ነገር ከምትማረር ከምትሰላች ተስፋ ከምትቆርጥ ስላለህ ነገር አመስግን። ባለህበት ቦታ ጥቅምህን አስቀጥል። ማግኘትህን አካብት። የሌለህ ያ- ፍላጎትህ ራሱ ዳዴ ብሎ፣ ድክ ድክ እያለ፣ እየተረመደ ከዛም በፍጥነት እየሮጠ ወዳለህበት እንዲመጣ ያለህን ነገር ተጠቀምበት። እድለቢስ ስለመሆንህ አትብሰልሰል። ጥንካሬ እና ብርታት አሻግሮ፣ አርቆ፣ አልሞ ማሰብ ከተቻለህ እድል ከፈጣሪ ዝቅ ሲል አንተ ለራስህ የምታመቸው ስራ ማለት ይሆናል። ከድክመትህ ይልቅ ለጥንካሬህ ቦታ ስጥ። ከሚያልፈሰፈስህ ስንፍና የሚያበረታህን ጉብዝና ምን እንደሆነ ለይ። ራስህን ሁን- ማንነትህን፣ አስተሳሰብህን ለሌሎች ለማረጋገጥ አትድከም፤ ከዛ ተሻልና ስለራስህ- ለራስህ ሃላፊነት ይሰማህ። ከሁሉም በይበልጥ ደግሞ አዎንታዊ አመለካከት እና የተረጋጋ አእምሮ ይኑርህ። ያለህበት አሁናዊ ሁኔታ ምንም ይሁን ምን፣ የሌለህን ሳይሆን ያለህን በረከትህን ቁጠር፤ ያንን ኮትኩት፣ አሳድግ፣ አበልጽግ የሌለህ ዳዴ፣ ድክድክ፣ ረመድመድ፣ እሎጥ እሮጥ እያለ ይቀርብሃል። ☑️ ህይወትህ ምን ያህል ውብ እንደሆነ እወቅ። አንተ ያለህ ሌሎች የሌላቸው ምን እንደሆነ ለይ- ተረዳ። @lifeandwisdom

  • ህይወትን በጥበብ pinned a video

  • #ከዜሮ_መጀመር_አልፈራም ሰው ሁኔታን መቀበል ስለማይችል ነው በሁኔታ የሚጎዳው፤ ዛሬ ካጣህ፣ የለመድከው ነገር ከቀረ፣ ከነገሮች ጋር ራስን ማዋሃድ ነው ያለብህ በቃ! የሚቀሩብህ ነገሮች ይኖራሉ፤ ለዛሬ ይቅሩ፤ ነገ ይደርሳሉ። እኔ አሁን ማጣትን አልፈራም፤ ከዜሮ መጀመር አልፈራም፤ ዜሮ ደግሞ ብሩ እይደለም። እኛ ብር አይደለም የሚከብደን- ሰው ነው የሚከብደን፤ አሁን እኔን «በየ ፖድካስቱ ለፍልፎ ይሀው ዜሮ ገብቶ. . . መክሮን ይኸው ዛሬ ዜሮ ገባ. . . .» ቢሉ አልፈራውም! እወጣዋለሁ! እንዲያውም ታሪኬን ያሳምርልኛል። አንተ ውስጥህ ሰላም ከሆነ፣ ጤና ካለህ ምን ያስፈልጋል? ሁሉም ነገር ያለው አእምሮ ውስጥ ነው፤ ሁሉም ነገር ጨዋታው ያለው አእምሮ ውስጥ ነው! @lifeandwisdom

  • መሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ብር ተዋውለው ወዲያውኑ ቤትዎን ይረከቡ። በመሀል ልደታ ላይ የሚገኝ ባለ 9 ወለል ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርትመንት 100% የተጠናቀቀ እና fully furnished ሁለት ቤት ብቻ ቀርተውታል! 3ኛ ወለል ላይ 173 ካሬ ባለ 3 መኝታ 8ኛ ወለል ላይ 151 ካሬ ባለ 3 መኝታ አፓርትመንቱ የተማሉለት -ሊፍት -መጠባበቂያ ጀነሬተር -ውሀ -ፓርኪንግ -ሰገነት በካሬ ከ 95ሺ ብር ጀምሮ እውነተኛ ገዢ ከሆኑ ቅናሽ ይደረግሎታል ለበለጠ መረጃ ይደውሉ: 📞09 36 04 06 30

  • Invest in yourself ⏰⏰⏰ " ለሰው ልጅ ሁሉ እኩልና ያለስስት የተሰጠ ሀብት ቢኖር ጊዜ ነው ። ጊዜህን መጠቀም ስትችል እራስህን ትለውጥበታለህ...ራሥህን መለወጥ ሥትችል ሌሎችንም ትለውጣለህ ። ራስህን ለመለወጥ ጊዜን ካልወሰድህ ሌላን መለወጥ አትችልም ። ( Invest in your self )ራስህ ላይ ፈሰስ አድርግ መጀመርያ ራስህን ለውጥ ። አስተሳሰብህን ሞርድ ፣ እይታህን አጥራ ፣ ንግግርና እርምጃህን ገምግም ነገ የሚኖርህ ዛሬን ስትጠቀምበት ነው ። ከዛሬም ያለህ ጊዜ አሁን ነው...አሁን ደግሞ እያለፈ ነው! ጥያቄው እንዴት እያለፈ ነው የሚለው ነው ። ለዚህ ጥያቄ የምትመልሰው መልስ #ነገ በምትለው ምናባዊው ቀን ላይ ያለህን አንተነት ይወስነዋል ። " ዛሬህን ተጠቀምበት... @lifeandwisdom

  • እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ በዓሉ የደስታ፣ የፍቅር እና የጤና እንዲሆንልላችሁ እመኛለሁ 🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄🎄

  • #አታስመስል_የሆንከውን_ሁን! በትክክል የሆንከውን ሆነህ መታየት ስትጀምር ሕይወትህን በከፍተኛ ደረጃ መለወጥ ትጀምራለህ። የሆንከውን ሆነህ መታየት ስትጀምር፣ አላስፈላጊ መረጃዎችን እንዲቆሙ ታደርጋለህ። በዚህም ራስህን እንደምትወድ ብቻ ሳይሆን፣ ዋጋ ያለህ መሆንህንም ለዓለም ታውጃለህ። ከዚያ እሴቶች ብቻ ሳይሆን ሊያስፈልግህ የሚችል ሁሉም ነገር ይኖርሃል። የምትፈልገው ቦታ ስትደርስም ባለመርህ ብቻ አትሆንም። የሆነ ሰው ሲያፈቅርህም ደስተኛ ብቻ አትሆንም። እንደሆንከው ሆነህ ስትመጣ ይህንን አካሄድ ታፋልሳለህ። ከዚህ በኋላ የሕይወት መልካምነት ምናልባት ላትሆን ለምትችለው ለተሻለው አንተነትህ የተያዘ አይደለም። እንዴት መታየትና ስሜትህን ማሳየት መፍቀድ መጀመር እንዳለብህ ከማወቅህ በፊት፣ በተፈጥሮ ጥሩ ስሜት የማይሰማህ ለምን እንደሆነ ለራስህ ማብራራት ለአንተ ሁልጊዜ ጨዋታ ነበር። አሁንም በጨለማ ውስጥ የምትኖር ከሆነ፣ ያንን ማፈንና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ማሳየት ነበረብህ። ዛሬ የሆንከውን ሆነህ እየታየህ፣ ለምናባዊው አንተነትህ የሚገባውን ሳይሆን፣ የአንተ የሆነውን ትወስዳለህ። ዓለም የሚሰጥህ ያስብልኛል ብለህ የምታስበውን ሳይሆን፣ አንተ፣ እዚህ፣ አሁን የምታስበውን ነው። #እውነተኛ_ፈውስ_ያ_ነው። ልክ ልክህን እየነገረ ምርጥ ጓደኛ የሚሆንህን #ተራራው_አንተ_ነህ_መጽሐፍ ደግሞ እንድታነበው ትጋበዛለህ @lifeandwisdom

  • #5ቱ_የእርጋታ_በረከቶች ብዙ ሰዎች ይህን ለማወቅ አመታት ፈጅቶባቸዋል። አንተ ግን እኒህ እውነታዎች በማንበብ ብቻ፤ አሁን ልታውቃቸው እና ልትተገብራቸው ይቻላል። #አንደኛ እስኪ… ቀስ ብለህ ተራመድ። እስኪ...ቀስ ብለህ ተናገር። ምክንያቱም ብዙ ሰዎች ቸኩሎ የመሄድና ፈጥኖ የመናገርን ስሜት ሊቆጣጠሩት አይችሉም። አንተ ልዩ ለመሆን እድሉ አለሁ። ወዳጄ '' የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል።'' #ሁለተኛ ሰዎችን ስታገለግል የበለጠ ሃይል እንደሚኖርህ ተረዳ። መኮፈስ የሚባለውን አላዋቂነት በጊዜ ብትተወው ሰው ለመሆን ትበቃለህ። #ሶስተኛ የበዛ ራስ ወዳድነትህን ዜሮ እስኪደርስ ገሸሽ አድርገው። #አራተኛ ሁሌም በየቀኑ ለሰዎች አንድ ነገር ማድረግን ልመድ። ምንም አጸፋ፤ ምትክ ባለመጠበቅ በለጋስነት የመቆም ብቃት ይኑርህ። #አምስተኛ። ሰዎች ንቀት ባሳዩህ ጊዜ ዝምታህ ይብለጥ። ክብርህ አንተው ጋር እንደሆነ እስኪገባቸው ድረስ፤ አይኖቻቸውን አትኩረህ ተመልከት። ☑️ እስኪ ባንተው አቅም ለሰዎች ምን ማድረግ ትችል ይሆን? ሀሳብህን አካፍለን፡፡ @lifeandwisdom

  • እውነት...? (በፍልስፍና...!) ፨፨፨ ሱፊስቶች ስለ እውነት ይህንን እይታ ያስቀምጣሉ << እውነት የሚመጣው ከስሜት ነው። ስለዚህም የእውነት ጥያቄ ምላሹ ስሜትህ ነው።...ስለዚህም እውነት ማለት የምትቀምሰው፣ የምታሸተው፣ የምትነካው፣ የምትሰማውና የምታየው ነገር ነው። >> ይላሉ ይህንን እይታ ካልተቀበሉት ፈላስፎች ግንባር ቀደሙ ፕሌቶ ነበር እሱም እንዲህ አለ... << እውነት ማለት ሱፊስቶች እንደሚሉት ስሜትህ ከሆነ እውነት የለም ማለት ነው። ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰው አንድን ነገር የሚያሸተው፣ የሚነካው፣ የሚቀምሰው፣ ወዘተ...በተለያየ መንገድ ነውና። >> ፨ አንድን ነገር ሁለት ሰዎች በሁለት መንገድ ከሰማው ወይም ካየው ነገሩ አንድ መሆኑ አብቅቷል፤ ስለዚህ ነገሩ በራሱ እውነት አይደለም! እያለን ነው እንግዲህ ፕሎቶ...! << ስለሆነም የእውነት ጥያቄ የሚመለሰው በምክንያታዊ ማሰብ(Reasoning) እንጂ በስሜት አይደለም።...አንድን ነገር ለማየት ማሰብ ያስፈልጋል። አስቀድመህ የምታስበው ነገር ወደ አይንህ መልእክት አስተላልፎ የምታየውን ማየት ቻልክ፤ በሌላ አባባል የምታየው እውነት መሆኑን በማሰብህ ነው፤ ስለዚህ እውነት ማለት 'ማሰብ' ነው ። >> ይላል ፕሉቶ ፧ የጠርጣሪነት ፍልስፍና መስራች የሆነው #ፊሮ ደግሞ የሱፊንም ሆነ የፕሌቶን አስተሳሰብ አይቀበልም ያንንም አስመልክቶ ይህንን ይለናል... ስለ ሱፊዎች እምነት... << የምታየውን እንዴት ማመን ትችላለህ?...ፀሐይ ከመሬት እጅግ ብዙ እጥፍ ግዙፍ እንደሆነች እናውቃለን። ነገር ግን መሬት ላይ ቆመን ፀሐይን ስናያት ትንሽዬ ነች። ስለዚህ የምናየው ነገር ሁሉ እውነት አይደለም ማለት ነው። >> ስለ ፕሎቶ እና አርስቶትል እይታ... << እንግዲህ አንድን ነገር እውነት የሚያደርገው ማሰብ ስለቻልን ከሆነ፦ ሰው የሚያስብ ፍጡር ነው፤ ሶቅራጥስ ደግሞ ሰው ነው፤ ስለዚህም ሶቅራጥስ ሰው ስለሆነ ማሰብ ይችላል ማለት ነው። ይኽ ደግሞ ሁልጊዜ አይሠራም ምክንያቱም ሰው ሁሉ ማሰብ ይችላል ማለት ሞኝነት ነውና። >> ይለናል ፊሮ ፧ ከሁሉም በተለየ መልኩ የሱፊ እምነት ተከታይ የነበረው ጎርጂያስ ደግሞ እውነትን በተናጋሪው የንግግር እና የማሳመን ችሎታ ይመነዋል ያንንም አስመልክቶ ይህንን ይለናል... << እውነት የሚባል ነገር የለም፤ ቢኖር እንኳን ነገሩን ነገሩን እውነት የሚያደርገው የአንተ ተናግሮ የማሳመን ችሎታ እንጂ የነገሩ እውነትነት አይደለም >> ይላል ሲያብራራው ደግሞ ይህንን ያክልበታል... << ምንም ነገር የለም፤ አንድ ነገር ቢኖር እንኳን መኖሩን ማወቅ አንችልም፤ ማወቅ ብንችል እንኳን ስለዚያ ነገር ማስረዳት አንችልም፤ ምክንያቱም አለ ብለን የምናስበው ነገር የለምና፤ ስለዚህም አለ ብለን ነገሩን ስላሰብን ብቻ እንዴት በድፍረት አለ ብለን እንፈርዳለን>> ይለናል... በምሳሌ ሲያብራራው ደግሞ ይህንን ያክላል... << ለምሳሌ አንድን ነገር ሁለት ሰዎች እንዴት እንደሚያዩት ብትጠይቅ በጣም የተለያየ መልስ ታገኛለህ፤ ስለነገሩ አስረዱኝ ብትላቸው ደግሞ ከሁለቱ ሰዎች የአንዱ ንግግር ስለነገሩ የበለጠ ሊያሳምንህ ይችላል። ለዚህም ነው ነገሮች እውነት ናቸው ብለን እንድናምን የተሻለ ተናጋሪ ሰው መፍጠር አለብን የምንለው...>> ፧ ምንጭ ፦ ጥበብ ከጲላጦስ ቅጽ ፩ ( 4 በ 1) ፨ መቼም በፍልስፍናው ዓለም እውነትን በተመለከተ ዛሬም ድረስ የሚያስማማ እይታ ማግኘት አልተቻለም...በርግጥም የፍልስፍና አላማው መስማማት አይደለምና...ዛሬ ላይ #እውነትን በተመለከተ ያሉት እይታዎችም በዚህ ዙርያ የሚሽከረከሩ ይመስለኛል... ፩, እውነት አለ #ፍጹማዊም ነው ፪, እውነት አለ ግን #አንፃራዊ ነው ፫, እውነት ብሎ ነገር #የለም...!! ፧ @lifeandwisdom

  • #በመሬት_ልብ_ውስጥ_ያለው_ወርቅ በአንተ አእምሮ ውስጥም አለ! ሀሳብ የመፍጠር ኃይል ነው ወይም የፈጠራ ኃይል እንዲንቀሳቀስ ማድረግ የሚችል ተጽዕኖ ፈጣሪ ኃይል ነው፡፡ በተወሰነ መንገድ ማሰብ ሀብትን ወደ እናንተ ያመጣል፡፡ ነገር ግን ለተግባራችሁ ትኩረት ሳትሰጡ በሀሳባችሁ ላይ ብቻ መተማመን የለባችሁም፡፡ ብዙ ሳይንሳዊ ሜታፊዚክስ አሳቢዎች የሚሰናከሉበት አለት ይህ ነው፡፡ ሀሳብን ከግለሰባዊ ተግባር ጋር ማገናኘት አለመቻል፡፡ ካለ ተፈጥሯዊ ሂደቶች ወይም ካለ ሰው ልጅ ጣልቃ ገብነት ነገሮችን ከቅርጽ አልባው ንጥረ ነገር መፍጠር ይቻላል ብለን ብንል እንኳን የሰው ልጅ እንደዚህ አይነቱ የእድገት ደረጃ ላይ አልደረሰም፡፡ #ሰው_ማሰብ_ብቻ_ሳይሆን_ያለበት፣ የግል ተግባሩም ሀሳቡን የሚያሟላ መሆን አለበት፡፡ በመሬት ልብ ውስጥ ያለውን ወርቅ በሀሳባችሁ ኃይል ወደ እናንተ እንዲመጣ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን ወርቁ እራሱን ከመሬት አውጥቶ፣ አጣርቶ፣ ቅርጽ ያለው ሳንቲም አድርጎ በጎዳናዎች ላይ እየተሽከረከረ ወደ ኪሳችሁ አይገባም፡፡ @lifeandwisdom

  • #በምንም_ሁኔታ_የማይበገር_ሁን! #1_አይበገሬነትህን_ተቀበለው! ውስጥህ የተደበቀ አይበገሬነት አለ፤ ሁሉም ሰው ይህ ተፈጥሮ አለው። ይህ አይበገሬ ማንነት የማይፈራ፣ የሚተማመንና የትኛውንም ነገር ማሳካት የሚችል ነው። በዚህ መጽሐፍ የምትማረውም ድጋሚ ይህን ተፈጥሯዊ ማንነት ስለመቀበልና ስለማግኘት ነው። #2_ከምቾት_ቀጠናህ_ውጣ እድገትህ ያለው ከምቾት ቀጠናህ ማዶ ነው። ከግቦችህ እና ይገባኛል ከምትለው የተሟላ ሕይወት የሚያደርስህን ቁልፍ የምታገኘውም ምቾት ማጣትንና አደጋን መቀበል ስትጀምር ነው። #3_ራስህን_ማነጻጸር_አቁም ስለራስህ ያለህን ዋጋ ለማሳነስ ፈጣኑ መንገድ ራስን ከሌሎች ማነጻጸር ነው። የራስህ መንገድና ጉዞ ላይ ብቻ አተኩር፤ ያንተ በሆኑ ጥንካሬዎችህና ስኬቶችህ ተደሰት። #4_በራስህ_እመን መድረስ ከሚገባህ ታላቅነት እንዳትደርስ ገድቦ የያዘህ ብቸኛው ነገር የራስህ ጥርጣሬ ነው። ራስህ ላይ ያለህን መተማመን በማጎልበት እውነተኛ አቅምህን የማውጣት እና እስከ ጥግ የመጠቀም አቅም አለህ። #5_ገዳቢ_እምነቶችህን_ጣል እነዚህ ገዳቢ እምነቶች ለራስህ ይህን እችላለሁ፣ ይህን ደግሞ አልችልም እያልክ የምትነግረው የተሳሳቱ አመለካከቶች ናቸው። እነዚህን አመለካከቶች ለይ እና ሞግታቸው፣ አስወግዳቸው። በቦታቸው የሚያበረቱ፣ የሚያነቃቁ ግቦችን ተካ። #6_ሐብት_ይገባሃል! የምትፈልጋቸውን ነገሮች ለማሟላት ገንዘብ ያስፈልግሃል። ገንዘብ መስራት፣ ሐብት ማካበት እንደምትችልና እንደሚገባህ እመን። አቅሙ አለህ። ዋናው ነገር ጥበቡን ማወቅ ነው! #7_ገንዘብ_ኃይል_ነው! ገንዘብ ያንተን እምነትና ድርጊት መሰረት አድርጎ ከአንተ የሚወጣ እና ወደ አንተ የሚመጣ ኃይል ነው። ስለዚህ ስለ ገንዘብ የሚኖርህ አመለካከትና ድርጊት ገንዘብን ወደ አንተ እንዲፈስ እንጂ ከአንተ እንዲወጣ የሚያደርግ እንዳይሆን ተጠንቀቅ! @lifeandwisdom

  • #ስሜትህን_ቀይር! አንድ ማወቅ ያለብህ ነገር ስሜትህን መቀየር እንደምትችል ነው። ነገር ግን እንዴት የገባህበትን ከባድ ስሜት ወደተሻለ ስሜት መቀየር ትችላለህ? ከባድ ጥያቄ ይመስላል። በትክክል ቀላል አይደለም። ልምምድ ያስፈልገዋል። ህምምም... እንበልና የሆነ ሰው አበሳጨህ፣ ዝቅ አድርጎሃል! ጉዳት ተሰምቶሃል እና? በመጀመሪያ ስሜቱን አትካደው ነገር ግን ለምን እንደዛ ሊሰማህ እንደቻለ ራስህን ጠይቅ... ምናልባት ያ ሰው እንደዛ እንዲሰማህ አልፈለገም... ምናልባት ያ የራስህ የአረዳድ ችግር ይሆናል... ምናልባት ያለብህ የበታችነት ስሜት... ምናልባትም ለዛ ሰው ያለህ ድብቅ ጥላቻ... ወይም በትክክል ያበሳጨህ ሰው ሆን ብሎም ሊሆን ይችላል። የፈለገ ይሁን የሚረብሽ ስሜት ለምን ውስጥህ ቀረ? ይሄን ጥያቄ ምትመልሰው አንተ ሁነህ ሳለ እኔም የምጠቁምህ ነገር ይኖራል። እዚህ ጋር- ህይወት ሁሌም ደስታ፣ መፈለግ፣ ማግኘት፣ እኩል መሆን፣ ስኬት እንዳልሆነች ተገንዘብ። ብስጭት ወይም የስሜት መረበሽ ሲያጋጥምህ ዝም ያለ ቦታ ሂድ፤ ከራስህ ጋር በፍቅር ተነጋገር። የመጥፎ ገጠመኞችን ጥሩ ጎን ለማየት ራስህን በአዎንታዊነት እንዲመራ አስገድድ። የበደለህን ይቅር በለው ጤና ይሰጥሃል። የተበላሸብህ ነገር ደግመህ ሞክረው- ጥንካሬን ስለምታገኝ። ደስተኛ ለመሆን ቻል መከፋት ሲረዝም በብዙ ስለሚያሳጣ። ፈጣሪህን አመስግን- የተሻለ ስለምታገኝ። ካንተ የባሰበትን ተመልከት መጽጽናናት ስለሚሆንልህ። ካንተ የተሻለውን አስተውል- ተስፋ ስለሚጎበኝህ። ስለገጠመኝህ ሰዎችን አማክር- መፍትሄ ስለሚሰጡህ። ጸልይ፣ ለብቻህ ተደብቀህ አልቅስ- ለእፎይታህ። @lifeandwisdom

  • መሳጭ ከሆኑ የፈላስፋው #ኮንፊሽየስ ንግግሮች በጥቂቱ... << የታላቅ ሰው ታላቅነት የሚገለጸው #በተግባሩ እንጂ #በንግግሩ አይደለም። የተግባር መሰረቱ ደግሞ #ጽኑ_ፍላጎት ነው።....የአንድን ተራ ሰው ጽኑ ፍላ ፍላጎት ከውስጡ ከመውሰድ፣ የአንድን ታላቅ ሃገርን የጦር አዛዥ መማረክ ይቀላል። >> ፧ << ሰዎች እያወሳሰቧት እንጂ ሕይወት ቀላል ናት...ሰዎች በጨለማው ላይ ከሚያፈጡና ከሚያለቅሱ ይልቅ አንዲት ሻማ ቢለኩሱ ለጨለማው ችግራቸው በቀላሉ መፍትሄ ያገኛሉ። >> ፧ << ታላቅ ሰው ችሎታውን ለማሳየት አይሽቀዳደምም...የአላዋቂን ሰው ስንፍና ልኩን የሚያውቅ አዋቂ ሰው ብቻ ነው። እናም በሌሎች ዘንድ ለመታወቅ ከመድከም ይልቅ ልታወቅ የሚገባኝ ነኝ በሚለው እምነት ውስጥ ሞልተህ ተቀመጥ። የእውቀቱ አንዱ ጥቅሙ በራስ መተማመንን ማምጣቱ ነውና።...ታላቅ ሆኖ ሳለ ነገር ግን ታላቅነቱ ባለመታወቁ የማይናደድ ሰው እሱ በእርግጥ ታላቅ ነው። >> ፧ << አንድን ነገር መቼም ላውቀው አልችልም በሚል ስሜት ተማረው፤ ስታውቀው ደግሞ ላጣው እችላለሁ በሚል ስሜት አጥብቀህ ያዘው። >> @lifeandwisdom

  • #ይሄኔ_የት_በደረስኩኝ_ነበር?! • ሰዎች በእኔ ላይ ምን እንደሚያስቡ ለማወቅ የታገልኩትን ያህል ራሴን ለማወቅ ብሰራ ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • በፍጹም የማይፈልጉኝን ሰዎች ስለማመጥና ስከታተል ያሳለፍኩትን ጊዜ ለእኔ ዋጋ ላላቸው ሰዎች ሰጥቸው ቢሆን ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • በማያገባኝ የሰዎች ስራና ሃሳብ ላይ በማውራትና በመቃወም ያባከንኩትን ጊዜ የሚደገፍ ሰው ፍልጌ ደግፌ ቢሆን ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • በየጊዜው ካለእቅድ የማወጣቸውን የገንዘብ መጠኖች በጥንቃቄ ብቆጥባቸው ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • ምንም ያህል ብጨነቅ መለወጥ በማልችላቸው ነገሮች ላይ መጨነቄን ትቼ ለመለወጥ አቅም ያለኝ ነገሮች ላይ አተኩሬ ቢሆን ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • የሚወዱኝ ቤተሰቦቼና ጓደኞቼ ሲመክሩኝ የመስማትና ጥሩውን ምክር የመቀበል ልማድ ኖሮኝ ቢሆን ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • ለመጀመር ያሰብኳቸውን እነዛን ወሳኝ ነገሮች ጀምሬያቸው ቢሆን ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • የማይሆኑ የማሕበራዊ ጎጾች ሳስስ ያመሸሁባቸውን ምሽቶች የቀኑን ውሎየን ለመገምገምና ለነገ በማቀድ ባሳልፋቸው ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! • ለየእለት ገጠመኞች ምላሽ እየሰጡ ከመሯሯጥ ይልቅ በራእይና በዓላማ ኖሬ ቢሆን ኖሮ . . . ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?! ያም ሆነ ይህ ያለፈው አልፏል! ከጥቂት አመታት በኋላ እንደገና “ይሄኔ የት በደረስኩኝ ነበር?!” የሚል የግምገማ ስሜት እንደሚመለስብኝ ስለማውቅ አሁኑኑ ለውጥን አመጣለሁ። @lifeandwisdom

  • #4ቱ_ሰዎች_የሚለወጡባቸው_ጊዜያት #1_በከባድ_ህመም_ውስጥ_ሲሆኑ በህይወት ውስጥ የሰው ልጅ ከባድ ጊዜያቶችን ሲያሳልፍ ህይወቱን ለመቀየር ግድ ይሆንበታል። የመለወጥ ፍላጎት ባይኖረው እንኳን ህመሙን ላለመሸከም ነገሮችን ሳይፈልግ እንዲቀይር ይገደዳል። #2_ሰዎችን_አይተው_ሲነሳሱ አድርገው የሚያሳዩ መልካም ምሳሌዎችን መመልከት እኔም እችላለሁ የሚል ስሜት በውስጣቸው ያጭራል። የእነሱንም ፈለግ በመከተል ብዙዎች ራሳቸውን ይቀይራሉ። #3_በቂ_ሲያውቁ እውቀት ብርሀን ነው። በብርሀን አይናችን ዙሪያውን እንዲያይ እንደሚረዳው እውቀትም አእምሯችን ችሎታውን እንዲያይ ይረዳዋል። የመለወጥ አቅሙ እንዳላቸው ሲያውቁ "ለምን አልለወጥም?" የሚል የመለወጥ ፍላጎት ይፈጠርባቸዋል። #4_ውጫዊ_ለውጦች በህይወት የሚከሰቱ ለውጦች ሰውዬውንም የመለወጥ አቅም አላቸው። የጊዜ መለወጥ፣ የአካባቢ ለውጥ፣ የኑሮ ደረጃ መሻሻል፣ ታዋቂነት፣ በህይወት የሚመጡ መልካም እድሎች ሰውን ይቀይራሉ። እስቲ በህይወታችሁ የለወጣችሁን አጋጣሚ ኮሜንት ላይ አጋሩን! መልካም የለውጥ ጊዜ!!! @lifeandwisdom

ህይወትን በጥበብ — tgindex