tgindex

ትዝታሽን ለኔ ...ትዝታዬን ላንቺ

Статистика
@miliyonaddisuанглийский

For any comment👉 @milasmith01

Последний пост
29 июл.
Последнее чтение
ещё не заходили
Постов за неделю
0
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 618
0 за 4 дн.
Сутки
+2
+0,12%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
616
22 постов
Вовлечённость
38,1%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
322
1/48двое суток
369
1/72трое суток
397

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • የዝምታው ዋጋ ​አንድ ባልና ሚስት ነበሩ። ሁለቱም እጅግ ይዋደዱ ነበር፣ ነገር ግን ሁለቱም እጅግ ኩሩዎች ነበሩ። በትዳራቸው ውስጥ ችግር ሲፈጠር፣ ችግሩን በውይይት ከመፍታት ይልቅ፣ አንዱ ሌላውን በዝምታ በመቅጣት የመጨረሻው ተጠቃሚ ለመሆን ይጥሩ ነበር። ​አንድ ቀን፣ ባልየው ከስራ ሲመጣ ሚስቱ ያዘጋጀችለትን ምግብ በትንሽ ጨው ምክንያት "ምግብሽ አልጣፈጠኝም" ብሎ ተቸ። ሚስትየዋም ተቀየመች፤ ነገር ግን ምንም ሳትል ዝም አለች። ባልየውም ኩራቱ አልፈቀደለትምና ይቅርታ አልጠየቀም። ይህ ዝምታ ለተከታታይ ቀናት ቀጠለ። በቤት ውስጥ መግባባት ሙሉ በሙሉ ቆመ። ​ቀናት ወደ ሳምንታት፣ ሳምንታት ወደ ወራት ተለወጡ። ሁለቱም በተመሳሳይ ጣሪያ ስር ይኖራሉ፤ ነገር ግን እንደ ሁለት እንግዳ ሰው እርስ በርስ አይተያዩም። በልባቸው ውስጥ ይቅርታ ለመጠየቅ ቢፈልጉም፣ ኩራታቸው ግን አንዱ የሌላውን ጉልበት እንዲፈትኑ አደረጋቸው። ​አንድ ቀን፣ ሚስትየዋ ባልየው አብሮት ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ በውስጧ ትልቅ ምኞት ነበራት። ነገር ግን ባልየው በስራው ተጠምዶ ቤት ውስጥ በዝምታ መቆየቱን መረጠ። ሚስትየዋ በውስጧ የነበረውን ጥልቅ ብቸኝነት እና የትዳር ብስጭት መቋቋም አቃታት። በድንገት የልብ ህመም አጠቃት። ባልየው በሳሎን ውስጥ ስራውን እየሰራ ስለነበር የሷን የህመም ስሜት አላስተዋለም። ​በመጨረሻም፣ ሚስትየዋ በአልጋዋ ላይ እያለፈች ነበር። በድንገት ባልየው ወደ ክፍሏ ሲገባ፣ ሚስቱ በደካማ ድምፅ እጁን ለመያዝ ሞከረች። ባልየው በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ እጇን ያዘ። ሚስትየዋ የመጨረሻ ቃሏን በሹክሹክታ ተናገረች፡ ​"ውድ ባለቤቴ፣ ባለፉት ወራት ያንተን ዝምታ እንደ ድምፅ እየሰማሁ ነበር። ስህተቱ የኔም፣ የአንተም ነበር። እኔ ይቅርታ ልጠይቅህ ፈልጌ ነበር፣ አንተ ግን ኩራትህን አስቀደምክ።  እባክህ፣ የምትወዳቸውን ሰዎች በኩራት አትቅጣ..." ​ሚስትየዋ አሸለበች። ባልየው በክፍሉ ውስጥ ተንበርክኮ አለቀሰ። ነገር ግን ዝምታዋን ለመስበር እና ይቅርታ ለመጠየቅ ከሚስቱ ትንፋሽ መቋረጥ በኋላ የነበረው ጊዜ፣ ምንም ዋጋ አልነበረውም። ​ 👉ኩራት በትዳር ውስጥ መርዝ ነው፡ ትክክል መሆን ወይም አሸናፊ መሆን በትዳር ውስጥ ምንም ትርፍ የለውም። ተሸናፊው ሁሌም ፍቅር ነው። 👉ዝምታ የትዳር መቃብር ነው፡ በትዳር ውስጥ መነጋገር፣ መተቸት፣ መከራከር እንኳን ይሻላል፤ ነገር ግን ዝም ብሎ መራራቅ እጅግ አደገኛ ነው። 👉አንድን ሰው ማጣት ምን ያህል እንደሚያሳዝን፣ ሰውየው ሲጠፋ ብቻ ነው የሚታወቀው። ያንን ጊዜ ከመምጣቱ በፊት፣ ይቅርታ መጠየቅ እና መተሳሰብ የሰው ልጅ ታላቅነት ነው። 👉ነገ የሚባል ቀን የለንም፡ የምንወዳቸውን ሰዎች ዛሬ እንውደዳቸው፤ ነገ የሚባል ቀን ለማንም ዋስትና የለውም።

  • የ3 አመት ፍቅረኛዋ ነው። ስለሱ ስታወራ እንባ ይተናነቃታል። "ጠልቸዋለሁ። ባላየው ሁላ ደስተኛ ነኝ" "...እሱ ያደረገኝን ነገር መቼም አልረሳውም። በጣም ብዙ ጊዜ ታግሼው ነበር። ከእንግዲህ ወዲያ ህይወቴ ውስጥ እንዲመለስ እድል አልሰጠውም።" አለችኝ። . . እንደዛ ስትለኝ ለምን እንደሆነ አላውቅም ደስ አለኝ። ጉዳቷን በፍቅር ልክስ ውስጤን አዘጋጀው። አነጋገሯን ሳስተውለው እውነትም እሱን ከልቧ መዝገብ ላይ ፍቃዋለች ብዬ አመንኳት። . . ሰፈሯ ሸኝቻት ወደቤት ስመለስ ከእሷ ጋር እንዴት አብረን መቀጠል እንዳለብንና ምን አይነት ሰው እንደምሆንላት እያሰብኩ ነበር። ጠዋት እስካገኛት ድረስ ለሊቱ እንደ ምፅአት ቀን ራቀብኝ። . . በማግስቱ አብረው እንዳደሩ ሰማው። ራቆቱም የሚተዋወቅ ሰው መቼስ ባለጋቢ አያስታርቀው አይደል

  • "መጀመሪያ ታስቃለች... መጨረሻ ግን ልብህን ትነካለች።" ታክሲ ውስጥ ስለገጠመኝ ሰውዬ እያዋራኋት ነው። በጣም ስላሳቀኝ መስማት እንዳልፈለገች እያወቅኩ ነው የማወራት። ለንቦጯን ብትጥልም በጨዋታው ላይ ስለተማመንኩ ወሬዬን ቀጠልኩ። ረዳቱ "ለህፃኑም ትከፍላለህ!" ሲለው ሰውዬው "አልከፍልም" ይላል! ትከፍላለህ አልከፍልም ካልከፈልክ ወንበር አይዝም ይይዛል ከያዘ ክፈል አልከፍልም ካልከፈልክ እቀፈው ይከብደኛል! እኔ 😂 እሷ 😑 <በቦታው ብትኖሪ በጣም ነበር የሚያስቅሽ> አልኩ ሀፍረቴን እያፋፈስኩ። <ብታይ ረዳቱ ራሱ ሰውዬው እንደዛ ሲል ዙሮ ሁላችንም አዬን...የታክሲው ሰው እንዳለ አፍሮ ዝም አለ...እኔ ነኝ ያቃተኝ...'ቡፍፍፍ' ብዬ መሳቅ ስጀምር ሁሉም ያፈነውን ሳቅ ለቀቀው። ታክሲዋ በሳቅ ተሞላች! ሰውዬው ስንስቅበት የተናገረው እሱም ገባው መሰለኝ እንዴት ሽምቅቅ እንዳለ!> የሆነ ሰው ዝም ብሏችሁ ምን እንደምታወሩ ግራ ገብቷችሁ ያውቃል? <ላገባ ነው!!>ያስገርመዋል ብላ ያሰበችውን ያህል አልተገረምኩም። ያዘዘኩትን ውሀ ጎንጨት ብዬ ወሬዬን ቀጠልኩ! መጠዬቅ ፈርቼ ነውጂ I know something was off ሰሞኑን! <ብር አለው?> <አዎ> <እድሜውስ?> <ምራቁን የዋጠ> ሳይታወቀኝ ምራቄን ዋጥኩ። ምራቁን የዋጠ ስንት አመት ማለት ነው? <ስታይው ተመቸሽ?> <መጥፎ አይመስለኝም> የመጀመሪያ ቀን አብረን ያደርን ለታ "መጥፎ አይደለህም" ያለችኝ ትዝ አለኝ። <ሽማግሌ ተላከ> <አዎ> <ደስ ይላል!> <እእእ> ከአንድ አመት ፍቅረኛህ ጋር እንደዚህ ማውራት ህልም ይመስላል። ነገር ግን ሁለታችንም በውስጣችን መቼም እንደማንጋባ እናውቅ ነበር መሰለኝ አልከበደንም። ተነስታ ስትሔድ ልቤ ውስጥ የሆነ ሸርተት የሚል ሀዘን ተሰማኝ። አለ አይደል የሆነ የበረዶ ግግር ግምስ ብሎ ወደታች ሲወርድ? ልክ እንደዛ! ምን እንደሆነ አልገባኝም! እንድንጋባ ስንቴ ለመነችኝ! እኔም ለመጀመሪያ ጊዜ "ይቺ ልጅ አንድ አራት አመት ከታገሰችኝ አገባታለሁ" የሚል ሀሳብ በልቤ ሽው እንዲል ያደረገችው እሷ ናትና እንድትቆይ ፈልጌ ነበር። አልሆነም እንጂ! <እኔ እና አንተ ብንጋባ ነበር ትክክለኛ የአብረሀም እና የሳራ የሚሆነው> <እኔ ከሰራተኛችን ስለምወልድ?> <ስነስርዓት ይኑርህ እሺ! ባለጌ! እሱ እኮ ተገዶ ነው ያን ያደረገው> <ታዲያ ምናለበት ትዳራችሁ የአብርሀም እና የሳራ ይሁን መባሉ ቢቀር?> <ቆይ አንተ ግን ራስህን ፈልገህ ሳታገኝ ጌታውን ፈልጎ ያገኘውን አብርሀምን ልትተች ስትነሳ ትንሽ አይከብድህም?> እንዲሁ ልክ ልኬን ስትነግረኝ ነበር ድስቴ እንደሆነች ግጣሟ እንደሆንኩ የሚገባኝ። አልሆነም እንጂ። ገና እግሯን ሳዬው ነበር ያፈቀርኳት። እግሯ የምታምር ሴት ለትዳር የምትሆን ይመስለኛል። ለኔ ውስጣዊ ውበት ማለት የእግር ውበት ነው። እግሯ የሚያምር ሴት መርዛማ መሆን የምትችል አይመስለኝም። ቆንጆ እግር ክንፍ ነው...መለአክ ያደርጋቸዋል። እኛ ስንራመድ እነሱ ይበራሉ። ታዲያ አንድ ቀን በዚህ ክንፍ እንዳትበርብኝ እሰጋ ነበር። <ምን እንደሚያስለቅሰኝ ታውቃለህ?> አልኩት ግሮሰሪ ያገኘሁትን ስትሬንጀር! <ምን> አለኝ ብቻዬን ተወኝ በሚመስል ቅላፄ <እሷን ማጣቴ ምንም አልመሰለኝም። የሚያስለቅሰኝ የኔ እንዲህ ሁኖ መቅረት ነው። አይኔ እያዬ ሶስት ሴቶቼ ጥለውኝ ወደ ትዳር ገቡ። ሶስት!> ያወጣኋቸው ጣቶች ሶስት መሆናቸውን ለማረጋገጥ ደግሜ አየሁት። ሁለት ናቸው። አንዱን ጨመርኩት። <እ> አለኝ! "እ" አባባሉ እሽ ቀጥል ሳይሆን "እ"ን የተደገፋት ነው የሚመስለው እእእእ አይነት! ገብቶኛል በቃ ተወኝ መሰለኝ የሚለው። ተናደድኩና ዝምብዬ መጠጣት ጀመርኩ። ዝም ስል እንዳኮረፍኩ ገባው መሰለኝ በጥፋተኝነት ስሜት ሊያዋራኝ ሞከረ። <ታፈቅራታለህ> <እእእእ> <ይሔን ያህል ከፈለካት ለምን አታገባትም> <አላገባም> <ግዴለህም አግባት> <አላገባም> <ስለዚህ ሌላ እንድታገባ ትፈልጋለህ ማለት ነው?> <አልፈልግም> <እንደዛ ካልሆነ አግባታ> <አልችልም> የጧቱ ሰውዬ አባባል አሁን ገና ነው የገባኝ። ክፈል...አልከፍልም...ካልከፈልክ እቀፈው...ይከብደኛል። ለካስ ከውጭ ሲታይ የሚያዝናናው ሁሉ ከውስጥ ህመም ነው። ሌላ ታግባ...አልፈልግም...እንደዛ ከሆነ አግባታ....አልችልም። አብሮኝ የሚጣጠው በውዝግቤ ተገርሞ ይስቅብኛል። የሚሰማኝ ግን ያንን አባት ስስቅበት የነበረው የራሴ ድምፅ ነው። ከህይወት ክብ ወዴት ይመለጣል

  • ‹‹ባለ ተራ›› ----------- መጀመሪያ የማረካት ቀናነቱ ነበር፡፡ አዲስ ገቢ በሆነችበት ቢሮ በሁሉ ነገር አገዛት፡፡ የሻይ እና የቡና ስኒዎቹ የት እንደሚቀመጡ አሳያት፡፡ በጊዜ ብዛት የፈዘዘ የድርጅቱ ሎጎ ያለበትን ኩባያ እንዳትጠቀም ነገራት፡፡ እጁ ሰባራ ነው አላት፡፡ ቁርስ ሳትበላ ከመጣች አሪፍ ፓስቲ የት እንደሚሸጥ ጠቆማት፡፡ በቅርብ ያለ ጁስ ቤት ስልክ ቁጥር ሰጣት፡፡ ቀና ነበር፡፡ በዚያ ላይ አስቂኝ፡፡ በእሷም ቀልዶች ይስቅ ነበር፡፡ በማያስቁት እንኳን፡፡ አንድ ቀን ጠዋት ፣ ‹‹አንተ ይሄ ፕሪንተር አጋንንት አለበት መሰለኝ፡፡ ገና ሳልነካው ይጮሃል›› አለችው፡፡ ‹‹ጠበል እናስረጨዋ ታዲያ!›› አላት ስቆ፡፡ በዚያው ቀን ከሰአት ፕሪንተሩ ጋር ስትደርስ ላዩ ላይ በቢጫ ‹ስቲኪት ኖት›› እንዲህ ተብሎ የተለጠፈ ነገር አየች፡፡ ‹‹ ጠበል መሄድ ስላለበት እንዳትነኩት›› የእሱ የእጅ ፅሁፍ ነበር፡፡ ብቻዋን እንደ ጉድ ሳቀች፡፡ የሚሰጣት ጥቃቅን ትኩረት ቀኗን ያበራላት፣ ደስ ያሰኛት ነበር፡፡ ዴስኳ አጠገብ መጥቶ ያንዣብባል፡፡ ሰበብ እየፈጠረ በቀን አስር ጊዜ መጥቶ ያዋራታል፡፡ ለሚረባውም ለማይረባውም ወዳለችበት ይሄዳል፡፡ ስላነበበው መጽሃፍ ያጫውታታል፡፡ ስላየው ፊልም ይተርክላታል፡፡ ‹‹ይሄን ሳየው ትዝ አልሽኝ›› ብሎ ኢንተርኔት ሲያስስ ያገኘውን የቲክቶክ ቪዲዮ፣ ዜና፣ ወሬ ሊንክ ይልክላታል፡፡ አንዱን ቀን ከደሞዝ ቀን ውጪ ከማትደፍረው ኢሊ ካፌ (ዋጋቸው ስል ቢላ ነው) የምትወደውን ማኪያቶ፣ ልክ እንደምትወደው አሰርቶ አመጣና ጠረጴዛዋ ላይ አስቀመጠ፡፡ ከፍታ ስታየው ወይ ያልነጣ፣ ወይ ያልጠቆረ የእሷ ማኪያቶ ነው፡፡ ከአንዲት ቀን በስተቀር የማኪያቶ ምርጫዋን ነግራው ስለማታውቅ በማስታወሱ ልቧ ዳንኪራ መታች፡፡ ብዙ ሳይቆይ፤ ሰውየው… ሻይ ቤቷ ከምታፈላላት ወፍራም ቡና በላይ፣ ከኢሊ ማኪያቶ በላይ፣ ከሙልሙል የጾም ኩኪስ በላይ፣ከኢማና ክትፎ በላይ፣ከወርቃ ቅቅል በላይ፣ ከሁሉ ነገር በላይ ቀንደኛ ሱስ ሆነባት፡፡ በወራት ውስጥ መነፋፈቃቸው፣ በሰበብ አስባብ መገናኘትና ሌላ ሰው ጣልቃ የማያስገባ የማያልቅ ወሬያቸው መጀመሪያ ላይ ጉዳት የሌለው ወደሚመስል መሞላፈጥ፣ ከዚያ ደግሞ ከጓደኝነት ባሻገር በሚፈላለጉ ወንድና ሴት መሃከል ወደ ሚካሄድ የቃላት ጨዋታና ማሽኮርመም፣ ብሎ ብሎ ደግሞ ወደ ለስላሳ መጀናጀን እና ፈጣጣነት አደገ፡፡ ‹‹አንቺ ጉደኛ›› ይላታል ባገኛት ቁጥር፡፡ እፈልግሻለሁ በሚል ድምጹ፡፡ ከጅዬሻለሁ በሚል አኳኋኑ፡፡ የቡድን ምሳ ላይ፡፡ ስብሰባ ላይ፡፡ ኮሪደር ላይ፡፡ እንዲህ እያላት ፈገግ ሲል ሆዷ ይገላበጣል፡፡ ከዚያ ሁለቱ ብቻ ለምሳ መውጣት ጀመሩ፡፡ ባንኩ አጠገብ ያለው ቤት፡፡ ራቅ ብሎ ትልቁ ህንጻ ስር ያለው ሬስቶራንት፡፡ ከዚያ ፈቀቅ ብሎ ያለው ሆቴል፡፡ አንዱን የጾም ቀን የአትክልት ድብልቅ ሲበሉ አበባ ጎመኑን አንድ ባንድ እያነሳች ስታነክት አየና፣ ‹‹ሚስቴ አበባ ጎመን ስትጠላ! በዚያ ላይ ሲቀቅሉት ይገማል ትላለች›› አላት፡፡ ‹‹እኔ ደግሞ ነፍሴ ነው›› አለችው ሳቅ ብላ፡፡ እሱም ሳቀ፡፡ ባለትዳር መሆኑን በፊትም ታውቃለች፡፡ ሚስት ካለው ሰው ጋር ፍቅር እንዲይዛት አልፈለገችም፡፡ ግን ያዛት፡፡ ውሎ አድሮ እስካሁን ለራሷም ያላመነችው ጠንካራ ስሜቷ ሲያስፈራት ግን ሰበብ እየፈጠረች አራቀችው፡፡ ምሳ አልችልም ማለት፣ ቴክስት አለመመለስ፣ ሰላምታ አለማርዘም ጀመረች፡፡ በቀደደችለት ቦይ ፈሰሰና ራቃት፡፡ ያኔ ግን ለጉድ ተከፋች፡፡ ወንበሯን ተደግፎ የሚያወራት፣ ቡና ልታመጣ ስትሄድ የሚከተላት፣ ፕሪነተሩ ጋር የሚጠብቃት፣ ስድስት ሰአት ከመሆኑ በአይኑ እንውጣ የሚላት ናፈቃት፡፡ ስሟን አጠራሩ፡፡ አወራሩ፡፡ ሳያስጠጣ ክንዷን በክንዱ አጨባበጡ፡፡ አጎነባበሱ፡፡ አተነፋፈሱ፡፡ አለም የማያየው ነገሩ ሁሉ ናፍቋት ተንገበገበች፡፡ ከአይኖቿ ሳይርቅ በእጦቱ ተንገረገበች፡፡ አቃታት፡፡ በጭራሽ አቃታት፡፡ አንዱን ቀን ከቢሮ ሲወጡ አስቆመችውና፣ ‹‹እንደዚህማ አትራቀኝ…አመረርክ እኮ! ሰው ጓደኛ አይሆንም እንዴ!›› አለችው፡፡ በራቃት ፍጥነት መልሶ ቀረባት፡፡ ነውር የሚባል አካላዊ ግንኙነት ሳይፈጥሩ፣ መስመር ጥሰው ሳይነካኩ በህልሟ ግን ስንት ጊዜ ከእሱ ጋር አልጋ ተጋራች…? ስንት ጊዜ መልሶ ራሷን ያሳፈራትና ጉድ ያስባላት ፍቅር ሰራች…? ስንቴስ በእቅፉ ውስጥ ሆና በእርካታ አቃሰተች…? አንዱን ጊዜ (በህልሟ) የኢሊን ቺዝ ኬክ ሲያጎርሳት አየች፡፡ በነጋታው መጥታ ‹‹ምን ማለት ይሆን?›› ስትለው ፣ ‹‹ቺዝ ኬኩ እኔ፣ ሹካው አንቺ መሰልሽኝ›› ሲላት ያፈቀረችው ልቧ አብራት ተሽኮረመመች፡፡ ------ የሆነ ሰኞ ሚስቱን ቢሮ ይዟት መጣ፡፡ የባንክ ብድር ጉዳይ ልትፈርም ነበር አመጣጧ፡፡ ፊቷ ከመከፋትና ከምሬት የተሰራ የምትመስል ረጅምና ሰላላ ሴት ናት፡፡ ጸጉሯ አያማትም አንዴ በሚያስብል መጠን ተሰብስቦ ተጠፍንጎ፡፡ ስስ ከንፈሯ ውሃ እንዳጣ መሬት ደርቆ፡፡ አስቀያሚና ዘልዛላ ኮት ለብሳ፡፡ ጥፍር ቀለም ያልተቀቡና ጫፋቸው ላይ ቆሻሻ ያጨቁ አጫጭር ጥፍሮቿ፡፡ ናቀቻት፡፡ በሃይል ናቀቻት፡፡ እንዳየቻት ወደ ምስጢረኛ ጓደኛዋና ሪሴፕሽኒስቷ ፍቅርተ ዞር አለችና፣ ‹‹ምን ትመስላለች በናትሽ…? ምንም አትመጥነው…! እኔ የእሱ ሚስት ብሆን ራሴን እንደ ጉድ እንከባከብለት….በሄደበት ሁሉ እየቀደምኩ አበባ እጎዘጉዝለት ነበር…››አለቻት፡፡ ፍቅርተ ትከሻዋን በግዴለሽት ንስት-ጣል አደረገችና፤ ‹ባክሽ መስሎሽ ነው፡፡ አንቺ ትኩስ፣ በዚ ላይ የሩቅ ፍቅር ውስጥ ነው ያለሽው..እሷ ግን የስንት አመት ትዳሩ ናት፡፡ አንቺ ጋር ሲመጣ ታጥቦ፣ ዘንጦ፣ ፈገግ ብሎ ነው፡፡ እሷ ጋር ሲሄድ እንዲህ ይመስልሻል….? ያላበው፣ ያረጀ ቱታ የለበሰው፣ ነጭናጫው ትንሳኤ ነው ለእሷ የሚደርሳት…፡፡ ካንቺ ጋር ስለትናንትናው የበስንቱ ኤፒሶድ እየሳቀ ያወራል…እሷን ግን ‹‹ፓንቴና ካልሲዎቼን አጠብሽልኝ?›› ነው የሚላት›› ብላ መለሰችላት፡፡ አብረው ሳቁ፡፡ ---- ከጊዜ በኋላ፣ ከስሩ የተቦረቦረው ትዳሩ ባንድ ጊዜ ተደረመሰ፡፡ ሚስቴ ጥላኝ ሄደች አላት፡፡ ሳትዘገይ ሚስቱ ዘግታ የወጣችውን በር ከፍታ ገባች፡፡ የእውነት ፍቅር፣ የከረመ ግንኙነት፣ ትዳር መሰል ነገር ተጀመረ፡፡ ያለ ሰቀቀን መገናኘቱ፣ ቤት ቤት ማለቱ፣ መጣገብን አመጣ፡፡ ብዙ ሳትዘገይ፣ በብዛት ከሚዳምነው ፊቱ ጋር መፋጠጥ፣ በንጭንጩ መበሳጨት፣ ቆሻሻ ካልሲና አዳፋ ፓንቶቹን ማጠብ ጀመረች፡፡ ---- አንዱን ቀን ታጥበው የደረቁ ካልሲዎቹን በፕላስቲክ መዘፍዘፊያ ይዛ መታጠቢያ ቤት ውስጥ ካለው ፊቷ ጋር ስትተያይ ሁለ ነገርዋ የትንሳኤን የቀድሞ ሚስት መስሏት ክው አለች፡፡ ‹‹ መቼ ነው ያቺን ጣእረ ሞት የመሰልኩት?›› አለች ለራሷ፡፡ ከድንጋጤዋ ሳታገግም፣ መዘፍዘፊያውን እንደያዘች ወደ ሳሎን ስትሄድ ሶፋው ላይ እንደተቀመጠ፣ ስልኩን እየጎረጎረ ለእሷ ከለገሳት የቆየውን ከአንጀት የሚመነጭ ሳቁን ሲስቅ አገኘችው፡፡ ቀናም ብሎ ሳያያት በቆመችበት፤ ‹‹ይሄን..እኔን ጠልፎ የጣለኝ ሳቁን ያገኘችው ባለ ተራ … ሰሞኑን ስላነበበው መጽሐፍ፣ ስላየው ፊልም፣ ስለሰማው ወሬ የሚያጫወታት አዲሷ እኔ ማን ትሆን›› ብላ ራሷን ስትጠይቅ፣ መዘፍዘፊያው ከእጆቿ አፈትልኮ ወደቀ፡፡

  • የያዕቆብ_ሌሊት ያድርግልን ማለት ምን ማለት ነው?                  መጀመሪያ ያዕቆብ ማነው!? ቅዱስ ያዕቆብ የይስሐቅ ልጅ ማለትም የአባትችን የአብርሃም የልጅ ልጅ ነው። የአብርሃም ልጅ ይስሐቅ ርብቃን አገባ ርብቃም መካን ስለነበረች  ልጅ አልነበራትምና አባታችን ይስሐቅ ስለ ሚስቱ እግዚአብሔርን ለመነ እግዚአብሔርም ተለመነው፥ርብቃ ሚስቱም ፀነሰች። ልጆቹም በሆዷ ውስጥ ይገፋፉ ነበር ርሷም፦እንዲህ ከሆነ ይህ ለእኔ ምኔ ነው አለች። ከእግዚአብሔርም ትጠይቅ ዘንድ ሄደች። እግዚአብሔርም እንዲህ አላት፦ሁለት ወገኖች በማህፀንሽ ናቸው፥ሁለቱም ሕዝብ ከሆድሽ ይከፈላሉ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል ታላቁም ለታናሹ ይገዛል። ትወልድ ዘንድ ዘመኗ በተፈፀመ ጊዜም፦እነሆ በማህፀኗ #መንታ ነበሩ።   በፊትም የወጣው ቀይ ነበረ፥ሁለንተናውም ጠጉር ለብሶ ነበር ስሙም #ዔሳው ተባለ።   ከዚያም በኋላ ወንድሙ ወጣ፥በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር ስሙም #ያዕቆብ ተባለ። አባታቸው ይስሐቅም ዔሳውን ይወድ ነበር እናታቸው ርብቃ ግን ያዕቆብን አብልጣ ትወደው ነበር   ስለዚህም አባታቸው ይስሐቅ በሸመገለ ጊዜ በጣም አርጅቶ ነበርና ለሚወደው ልጁ ሊባርከው (ሊመርቀው) አሰበ። ነገር ግን እናታቸው ርብቃ የዔሳውን ምርቃን ለያዕቆብ በመምከር የዔሳውን በረከት አስወሰደችበት። ዔሳውም በጣም ተናዶ ወንድሙ ያዕቆብን ለመግደል ወሰነ (በረከቱ) ወስዶበታልና፦ እናቱ ርብቃም ይህ የታላቁ ልጇ የዔሳውን ቃል ደረሰላት ታናሹንም ልጇን ያዕቆብንም አስጠርታ እነሆ ወንድምህ ዔሳው ሊገድልህ ይፈቅዳል። ልጄ ሆይ ቃሌን ስማ ተነስና ወደ ካራን ምድር ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሂድ የወንድምህ ቁጣ እስኪበርድለት ጥቂት ቀናት በዚያው ተቀመጥ ብላ አሳመነችው። ያዕቆብም እሺ ብሎ መንገዱን ጀመረ። ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ወደ ካራን ሄደ። ወደ አንድ ስፍራም ደረሰ፦ፀሐይም ጠልቃ ነበርና፥ከዚያ አደረ በዚያም ስፍራ ድንጋይ አነሳ፥ከእርሱም በታች ተንተርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ። ሕልምም አለመ እነሆም መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ፥ራሱም ወደ ሰማይ ደረሰ፥እነሆም የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበርና። እነሆም፥እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር፥እንዲህም አለ፦የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ይህችን አንተ የተኘህባትን ምድር ለአንተም ለዘርህም እሰጥሃለሁ ዘርህም እንደ ምድር አሸዋ ይሆናል እስከ ምዕራብና እስከ ምስራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ የምድርም አህዛብ ሁሉ ባንተ በዘርህም ይባረካሉ። እነሆም እኔ ከአንተ ጋራ ነኝ፥በምትሄድበትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፥ወደዚችም ምድር እመልስልሃለሁ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና። ያዕቆብም ከእንቅልፉ ተነስቶ፦ በእውነት እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ ነው እኔ አላወቅሁም ነበር አለ። ፈራ፥እንዲህም አለ፦ይህ ስፍራ እንዴት ያስፈራ ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም ይህም የሰማይ ደጅ ነው። ያዕቆብም ማልዶ ተነሳ፥ተንተርሶት የነበረውንም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አድርጎ አቆመው፥በበላዩም ዘይትን አፈሰሰበት። ያዕቆብም ያንን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው አስቀድሞ ግን የዚያንች ስም ሎዛ ነበረ። ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ። እግዚአብሔር ከእኔ ጋራ ቢሆን፥በምሄድበትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ፥የምበላውንም እንጀራ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ፥ ወደ አባቴ ቤትም በጤና ብመለስ፥እግዚአብሔር አምላኬ ይሆንልኛል። ለሐውልት የተከልሁት ይህም ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከአስር እጅ አነዱን እሰጥሃለሁ። ብሎ ቃል ገባ።   ➕ ስለዚህም እኛም የያዕቆብ ሌሊት ያድርግልን የምንባባለው እግዚአብሔር አምላክ ከቅዱሳን መላእክቱ ከኛጋር እንዲያድርና ጥሩ የሰላም እንቅልፍ እንዲያስተኛን ቅዱሳን በህልማችን መላእክትን እንዲያሳየን ከመጥፎ ህልም እንዲጠብቀን እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንዲሆን ከመጥፎ አጋንንት እንዲጠብቀን #የያዕቆብ_ሌሊት ይሁንልን እንላለን።               ወስብሐት ለእግዚአብሔር ይቆየን!!!          ለበለጠ ኦሪት ዘፍጥረት (26_30) አንብቡት

  • የሰዎች 'Selfish' (ራስ ወዳድ) መሆን ሁልጊዜ ከመጥፎ ማንነት አይመጣም፤ አብዛኛውን ጊዜ ከተሰበረ ደግነት የሚወለድ መከላከያ (Defence mechanism) ነው!🙌 ​በሕይወታችሁ ውስጥ ለሁሉም ሰው ድልድይ ለመሆን አትሯሯጡ። ደግነታችሁንና ቅንነታችሁን አላግባብ የሚጠቀሙ ሰዎች፣ መጨረሻ ላይ እናንተን ሰብረው ያላችሁን መልካምነት ይገድሉታል፦ ​ለሁሉም ሰው ሲባል ራስን መስዋዕት ማድረግ... ደግነት ሳይሆን የራስን ማንነት ማጣት ነው። ​እናንተ ለረዳችኋቸው ሰዎች ሁሉ... በችግራችሁ ሰዓት ከጎናችሁ እንዲቆሙ አትጠብቁ፤ አብዛኞቹ ሰዎች ዋጋችሁን የሚያውቁት ስታጡላቸው ብቻ ነው። ሰዎችን ለመርዳት ስትሉ የራሳችሁን Mental health እና ሰላም አሳልፋችሁ አትስጡ። ለራሳችሁ ወሰን (Boundary) ማበጀታችሁና NO ማለታችሁ ራስ ወዳድነት ሳይሆን ራሳችሁን የመጠበቅ ብልህነት ነው። አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች 'ራስ ወዳድ' የሚሏቸው ግለሰቦች፣ ትላንት ለሁሉም ሰው ሲሉ ራሳቸውን የሰጡና ደግነታቸው በአስመሳይነት የተመለሰላቸው ናቸው። ​ደግ መሆን ውብ ስብዕና ነው፤ ነገር ግን ደግነታችሁ ወሰን (Boundary) ከሌለው ሰዎችን ሳይሆን እናንተን ያፈርሳል። ለራሳችሁ ሰላምና አእምሮአችሁ ቅድሚያ መስጠት 'Selfish' መሆን አይደለም። ለሚገባው ሰው ብቻ መስጠትንና ለሰላማችሁ ሲባል 'NO' ማለትን ልመዱ። 🤍✨ Being kind is a virtue, but setting boundaries is a necessity. Don't let ungrateful people drain your light until you become cold. Help when you can, but protect your peace first. በርቱ! አመሰግናለሁ! Your Healing Corner - Gentle words for tired souls. 🤌🥰

  • https://www.howlow.et?grsf=3TOWVX

  • ለማን ትኖራለህ ? ብዙውን ጊዜ የምንሸወድበት ጥያቄ ነው። ለማነው የምትኖረው ስትባል የምትኖርለት የሚመስልህ ነገር ግ የማትኖርለትን ሰው ትጠቅሳለህ። በህይወትህ ለማነው የምትኖረው ? ለምንድነውስ ለዛ ለጠቀስከው ሰው የምትኖርለት ? 👉እሱ ለራሱ መኖር ስለማይችል ወይስ ለመኖር አቅም ስለሌለው ነው ወይስ አንተ ለራስህ የምትኖርበትን ምክንያት ስላጣህ ቢያንስ ለአንድ ሰው ልኑር ብለህ አስበህ ነው ? 👉 ብዙውን ጊዜ ለሌሎች ሰዎች የሚኖሩ የሚመስላቸው ሰዎች ከራሳቸው ጋር የተጣሉ ናቸው። እውነት ለምትወደው እና እኖርለታለው ብለህ ላሰብከው ለዛ ሰው ኑርለት ነገር ግን እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ አንተ ለራስህ እየኖርክ ነው ? ያ እኖርለታለው ያልከው አካል እሚኖረው ባንተ መኖር ውስጥ እንደሆነስ ታውቀዋለህ። 👉እናቴ እንደዚህ ትላለች ገና ቂጥህን ሳትጠርግ አትንቀልቀል ትለኝ ነበር። ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ ለራስህ ሳትሆን ለሌላው ለመሆን አትሩጥ ለማለት ነው። የውላችሁ የምትኖሩለት አካል ካለ በጣም ደስ የሚል ህይወት ነው የምትኖሩት። ነገር ግን አንድ ነገር አስቡ እናንተ ለራሳችሁ እየኖራችሁ ካልሆን እኖርለታለው ለምትሉት ሰው የምትኖሩለት ይመስላችሁዋል እንጂ አይደለም። 👉መኖር ማለት ለአላማህ መገኘት ማለት ነው ። ማንም ሰው አላማ ያለውን ሰው ይወዳል። ስለዚህ የምር የምትኖሩለት አካል ካለ መጀመሪያ እራሳችሁን እንደዚህ ጠይቁት እኔ ለራሴ እየኖርኩ ነው ወይ ? አዎ ከሆነ መልሳችሁ አላማችሁን አስቀምጡት። አይ ከሆነ ደግሞ የተፈጠራችሁበትን አላማ ፈልጉ። መተንፈስ መኖርን አያመለክትም ህይወት ያለው መሆንን ያሳያል እንጂ። መኖር ማለት ለአላማህ በአላማ መገኘት ነው። @abufkr1621

  • ለማን ትኖራለህ ? ብዙውን ጊዜ የምንሸወድበት ጥያቄ ነው። ለማነው የምትኖረው ስትባል የምትኖርለት የሚመስልህ ነገር ግ የማትኖርለትን ሰው ትጠቅሳለህ። በህይወትህ ለማነው የምትኖረው ? ለምንድነውስ ለዛ ለጠቀስከው ሰው የምትኖርለት ? 👉እሱ ለራሱ መኖር ስለማይችል ወይስ ለመኖር አቅም ስለሌለው ነው ወይስ አንተ ለራስህ የምትኖርበትን ምክንያት ስላጣህ ቢያንስ ለአንድ ሰው ልኑር ብለህ አስበህ ነው ? 👉 ብዙውን ጊዜ ለሌሎች ሰዎች የሚኖሩ የሚመስላቸው ሰዎች ከራሳቸው ጋር የተጣሉ ናቸው። እውነት ለምትወደው እና እኖርለታለው ብለህ ላሰብከው ለዛ ሰው ኑርለት ነገር ግን እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ አንተ ለራስህ እየኖርክ ነው ? ያ እኖርለታለው ያልከው አካል እሚኖረው ባንተ መኖር ውስጥ እንደሆነስ ታውቀዋለህ። 👉እናቴ እንደዚህ ትላለች ገና ቂጥህን ሳትጠርግ አትንቀልቀል ትለኝ ነበር። ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ ለራስህ ሳትሆን ለሌላው ለመሆን አትሩጥ ለማለት ነው። የውላችሁ የምትኖሩለት አካል ካለ በጣም ደስ የሚል ህይወት ነው የምትኖሩት። ነገር ግን አንድ ነገር አስቡ እናንተ ለራሳችሁ እየኖራችሁ ካልሆን እኖርለታለው ለምትሉት ሰው የምትኖሩለት ይመስላችሁዋል እንጂ አይደለም። 👉መኖር ማለት ለአላማህ መገኘት ማለት ነው ። ማንም ሰው አላማ ያለውን ሰው ይወዳል። ስለዚህ የምር የምትኖሩለት አካል ካለ መጀመሪያ እራሳችሁን እንደዚህ ጠይቁት እኔ ለራሴ እየኖርኩ ነው ወይ ? አዎ ከሆነ መልሳችሁ አላማችሁን አስቀምጡት። አይ ከሆነ ደግሞ የተፈጠራችሁበትን አላማ ፈልጉ። መተንፈስ መኖርን አያመለክትም ህይወት ያለው መሆንን ያሳያል እንጂ። መኖር ማለት ለአላማህ በአላማ መገኘት ነው። @abufkr1621

  • በጠበኩሽ ቁጥር አንቺን ለመርሳት አቅም አጣለሁኝ ልቤ አንቺን በመጠበቅ አዙሪት ውስጥ ታስሮ ነፃነቱን አጥቷል።የኔ ዓለም ግን አሁንም ትተሽኝ በሄድሽበት ቅፅበት ላይ ቆሟል። የቅርብ ሰዎች "እርሳት ህይወትህን ቀጥል" ይሉኛል። ለእነሱ ቃሉ ቀላል ነው ለኔ ግን ህያው የሆነውን የነፍሴን ክፋይ ቆርጦ የመጣል ያህል ይከብደኛል። እውነታው ይህ ነው።በጠበኩሽ ቁጥር አንቺን ለመርሳት አቅም አጣለሁኝ። የሄድሽበት መንገድ ባዶ መሆኑን እያወቅኩ አሁንም አይኖቼ ያንቺን መምጣት ተስፋ ከማድረግ አልቦዘኑም።   ምናልባት ዛሬ ትመጣለች የሚለው የዘወትር ምኞቴ አንቺን ልረሳሽ ስሞክር በየቀኑ አዲስ ቁስል ይፈጥርብኛል። አንቺን መርሳት ማለት ራሴን እንደመርሳት ማለት ነው። ለካስ የፍቅር ትልቁ ህመም መራቅ ሳይሆን የራቀን ሰው በናፍቆት እየጠበቁ በከንቱ መኖር ነው። ለመሸሽ የምሞክረው ሙከራ ሁሉ መልሶ ወደ ትዝታሽ እቅፍ ያመጣኛል። እስከመቼ እንደምጠብቅሽ አላውቅም ግን አንድ ነገር ብቻ አውቃለሁ..... በጠበኩሽ ቁጥር አንቺን ለመርሳት ያለኝ አቅም ከዕለት ወደ ዕለት እየተሟጠጠ ነው። MAN✍️

  • በጠበኩሽ ቁጥር አንቺን ለመርሳት አቅም አጣለሁኝ ልቤ አንቺን በመጠበቅ አዙሪት ውስጥ ታስሮ ነፃነቱን አጥቷል።የኔ ዓለም ግን አሁንም ትተሽኝ በሄድሽበት ቅፅበት ላይ ቆሟል። የቅርብ ሰዎች "እርሳት ህይወትህን ቀጥል" ይሉኛል። ለእነሱ ቃሉ ቀላል ነው ለኔ ግን ህያው የሆነውን የነፍሴን ክፋይ ቆርጦ የመጣል ያህል ይከብደኛል። እውነታው ይህ ነው።በጠበኩሽ ቁጥር አንቺን ለመርሳት አቅም አጣለሁኝ። የሄድሽበት መንገድ ባዶ መሆኑን እያወቅኩ አሁንም አይኖቼ ያንቺን መምጣት ተስፋ ከማድረግ አልቦዘኑም።   ምናልባት ዛሬ ትመጣለች የሚለው የዘወትር ምኞቴ አንቺን ልረሳሽ ስሞክር በየቀኑ አዲስ ቁስል ይፈጥርብኛል። አንቺን መርሳት ማለት ራሴን እንደመርሳት ማለት ነው። ለካስ የፍቅር ትልቁ ህመም መራቅ ሳይሆን የራቀን ሰው በናፍቆት እየጠበቁ በከንቱ መኖር ነው። ለመሸሽ የምሞክረው ሙከራ ሁሉ መልሶ ወደ ትዝታሽ እቅፍ ያመጣኛል። እስከመቼ እንደምጠብቅሽ አላውቅም ግን አንድ ነገር ብቻ አውቃለሁ..... በጠበኩሽ ቁጥር አንቺን ለመርሳት ያለኝ አቅም ከዕለት ወደ ዕለት እየተሟጠጠ ነው። MAN✍️

  • 15 июл.424из 21 Ěñąťě

    https://youtu.be/MdSJsC1_GxE?si=NjQN2Qe2kJnBLwzm

  • 15 июл.460из 21 Ěñąťě

    Selam wendme endet aderk and neger laschegrh neber be 6 12 seat lay betguh zmare yetelekeke adiss zmare neberegn bzu eyetayelgn aydelem bemlklh link hebte endyaylgn ena menfesawi tbbr endtaderglgn neber kechalk share adrglgn beslase sm eteykalehu

  • 12 июн.1 12013

    "እኔን እንደሳመችኝ እሱንም ከንፈሩን ትስመዋለች?"ብዬ አሰብኩ። "አይ አይሆንም....ግን ደግሞ አዲሱ ፍቅረኛዋ አይደል በደንብ ትስመዋለች"አልኩ ለራሴ። ይህንን ሀሳብ ግን ማመን ከበደኝ። . . "ለነገሩ ከእኔ በፊት የነበረውን ፍቅረኛዋን እስኪበቃት ከንፈሩን ስማው የለ።"ብዬ እራሴን ለማረጋጋት ስሞክር ያሰብኩት ሀሳብ በራሱ ዘገነነኝ። . . ለራሴ ደነገጥኩ። "እኔን የሳመችኝ እሱን በሳመችው ከንፈሯ ነው???? "ብዬ ተበሳጨው። "ቱ" ብዬ ከንፈሬን በሸሚዜ ጫፍ ጠራረኩት። . . ማሰቤን አላቆምኩም። "ቆይ ያ ሁሉ የፍቅር ቃላቶቿስ?" "ከእኔ በፊት ለነበሩ ፍቅረኞቿ ተጠቅማቸዋለች ማለት ነው?.." መልስ የሌለው ጥያቄ ራሴን እጠይቃለሁ። . . ፍቅር... ማሬ...የኔ ባል...መሰል ቁልምጫዎችን ሁሉ ለሌላ ወንድ ማለቷን አምኖ መቀበል አቃተኝ። . . ራሴን አመመኝ። ከዚህ በላይ ካሰብኩ ጥሩ አይመጣም ብዬ ለመተኛት አልጋዬ ላይ ጋደም እንዳልኩ ጭራሽ ያሰብኩትን ሀሳብ በምስል አድርጎ በህልሜ ሲያሳየኝ ጊዜ ባንኜ ተነሳሁ። . . ወይ ፈተና አስመሳይን ሰው እንዴት ነው መርሳት የሚቻለው ቆይ?

  • የማይሽር ቁስል የማይድን ጠባሳ የለም! ይሄ የራሴው እውነተኛ ታሪክ ነው። ከሁለት አመታት ከስድስት ወራት በፊት እጅግ በጣም የማፈቅራት የልጅነት ጓደኛዬ..ፍቅሬ..ሚስቴና የልጄ እናት የሆነችው ውድ ሚስቴ ከዚህ አለም በህይወት ስትለየኝ የተሰማኝ ስሜት እጅግ በጣም ለገለፃ የማይመች ከባድ ነበር። የያዛት ህመም እንደማያድናት ባውቅም ሞት እውን ሆኖ ሲከሰት በህመሟ ጊዜ ጥርሴን ነክሼ ያሳከምኳትን ያህል ጥንካሬ ሊኖረኝ አልቻለም...ለአመታት የገነባሁት ጥንካሬ በአንዴ ብንን ብሎ ጠፋ..ለአምስት አመቱ ልጄ ጥንካሬን ለመስጠት እሱ ፊት በጣም ደስተኛ ለመምሰል እጥራለሁ...ዘወትር ምሽት እሱን ካስተኛሁ በኋላ የእኔ የስቃይ ጊዜ ይጀምራል...የቤቴ እያንዳንዱ ነገር እሷን ያስታውሰኛል...ከስራ ውዬ ስገባ ይጠብቀኝ የነበረው ፈገግታ...ድባብ ሁሉም ይናፍቀኛል..ሌሊቱን በትዝታና በትካዜ እገፋውና ጧት ለስራ እነሳለሁ..ወንድ ህመሙን ዋጥ አድርጎ እንደሚኖረው እንደዛ ያዝዝ አድርጌው ስራ ቦታ ለመሳቅና ለመጫወት እሞክራለሁ...ምሽቱን የምር እፈራዋለሁ...ባይመጣ እላለሁ...ጨለማው ይዞት የማይመጣው ትዝታ የለም...የማያስታውሰኝ ነገር የለም...ወላ "መብራት አንተ አጥፋ አንች አጥፊ" የምንባባለው ሁላ ሳይቀር ይታወሰኝና ፈገግታና እንባ ፊቴን ሁለት መልኩ ይሰጡታል...ብዙ የትካዜና የጭንቀት ቀናት አለፉ...በልጅ የካሰኝ መድሃኒያለም ልቤን አደነደነው...እሷን ሳስብ ይወርድ የነበረው እንባዬን በፈገግታ ቀየረው...ዛሬ ትዝታዋ ጥንካሬ ሆኖኝ ፡ ትካዜን አንገት ለአንገት ተናንቄ አሸንፌ የአብራኬ ክፋይ የሆነውን ..የእሷን አይን ማያዬን የአደራም የስጋም ልጄን በደስታ እያሳደግኩ እገኛለሁ... እናም ይሄንን ማለት እፈልጋለሁ..."ዛሬ የጨለመ የመሰላችሁ እህት ወንድሞቼ ሁሉ...የማያልፍ ቀን የማይሽር ቁስል የለም! የፈተና...የወጀቡን ጊዜ ማለፊያ ጥበቡን ከፈጣሪ እየለመናችሁ ይሄንን ቀን በዝግታ እለፉት...ተስፋ መቁረጥ ራስ ተስፋ እስኪቆርጥባችሁ ድረስ በርቱ!" ይሄ የተኖረ. ..የሚኖርም ህይወት ነው! @sura ብዕረኛው @santa

  • "በህይወት ስትኖር ምንም ነገር ሊገጥም ይችላል። ሰው ነህ በቃ አለም ላይ ያሉ ሰዎች የገጠማቸው ነገር በጠቅላላ አንተ ህይወት ውስጥ ሲደገም ልታይ ትችላለህ።እንደ አደገኛ እኔ ምናምን አትበል" ይለኛል እየተቆጣ ሊያረጋጋኝ እየሞከረ። . . "ለምሳሌ አሁን እኔን ተመልከተኝ..."ይላል የሁልጊዜው ምሳሌ እራሱ ነው። "... በህይወት ዘመኔ ደደብ የሆነች ሴት ልቤን ትሰብረዋለች ብዬ በጭራሽ ገምቼ አላውቅም። በጭራሽ.. ግን ደግሞ ፍቅር መምጫው አይታወቅም አይደለ ያቺ ልቤን ትሰብረዋለች ብዬ አስቤያት የማላቃት ሴት እጅ ላይ ጣለኝ። ለስሙ ፊደል ቆጥራለችኮ ግን ከእሷ ጋር በቴክስት አውርቶ ለመግባባት በራሱ በጣም ብዙ ጊዜ ነው የፈጀብኝ። በዛ ላይ እንደዛም ሆኖ ትንሽ እንግሊዘኛ ጣል እንደምታደርግ ሳስበው ያስቀኛል። ባይነበብም ከነጉድለቱም ቢሆን አስተካክዬ አነበው ነበር። ለምን ብትለኝ ፍቅር ለሚሉት ነገር ብዬ..." እያለ ስለበፊት ፍቅረኛው ይነግረኛል። ስለየትኛዋ እንደሆነች አላውቅም። ብቻ ዝም ብዬ እሰማዋለው። . . "እና እንዳልኩህ ነው በህይወቴ ውዴ(Wde) ብሎ ለመፃፍ Wda የምትል አንተ(Ante) ለማለት Anta እያለች የምትፅፍ ሴት ልቤን ትሰብረዋለች ብዬ በስህተት አስቤ አላውቅም። በዛ የተወላገደ አፃፃፏ እንለያይ ብላ ልቤን ሰበረችው" ብሎ ከት ብሎ ሳቀ። አነጋገሩና አሳሳቁ ሳልፈልግ አሳቀኝ። . . ቀጠለና "እሷን ሳስታውስ ትዝ የሚለኝ ዘፈን አለ" አለኝ። "ምን የሚለው ነው?"አልኩት ከብዙዎቹ የፍቅር ዘፈኖች አንዱ እንሚሆን እየገመትኩ። "የአለማየው እሸቴ ተማር ልጄ ተማር ልጄ..."ብሎኝ ሳቀ። "አንተ እውነትም ለይቶልሀል"ብዬው እየሳኩኝ ተነስቼ ልሄድ ስል"ስማ ነገም ፊትህን ዘፍዝፈህ እንዳትመጣብኝ በቃ ተዋት አለም ከእሷ በበለጡ በብዙ እንስቶች ተባርካለች። አታስብ" አለኝ። . .

  • አገባኮ አልኳት እንዴት እንደምነግራት ሳወጣ ሳወርድ ወር ሞላ..... እናቴ እናቴ ብቻ አይደለችም ሚስጥረኛዬም ናት ሰሞኑን ግን ደህና ነሽ .... በግዜ በር ዘግተሽ መተኛት ጀመርሽ ምነው አይነት ጥያቄዎቿን ከጀመረቺኝ ሳምንታት ተቆጥረዋል እማ ልታለቀልቅ አሽታ በእጇ የያዘችውን ብርጭቆ ሳታስቀምጥ ቀጥዬ የምላትን ለመስማት አይን አይኔን ማየት ጀመረች ከወሬዬ እንባዬ ቀደመኝ እናቴ ... ምንድነው የሚያነፋርቅሽ የሆንሽውን አትናገሪም እንዴ ለመጨረሻ ግዜ መች እንደሳቅኩ እንጃ እንጂ ይኸው ለተከታታይ ቀናት በሬን ዘግቼ መነፋረቅ ከጀመርኩ ሰነባበትኩ አገባኮ አልኳት እ ...አለቺኝ በማመንና ባለማመን መሀል ምን እንዳለ እንጃ ብቻ የነገርኳት ነገር ግራ እየሆነባት ጓደኞቻችን ፎቶውን አሳዩኝ እንባ ያቀረሩ አይኖቿን እያሸሸች የእኔ ልጅ ቀረሽበታ ምን አባቱ አለቺኝ በርግጥ ከዚህ የተሻለ ሌላ የምትለኝ ነገር መኖሩን እንጃ የእውነት ግን ቀርቼበታለሁ? አልኩ ለራሴ ቀረብኝ ወይስ ቀረሁበት? አንዳንድ ነገር ሚዛን አይደፋም አይደል ቀረብኝ የእድሜዬ ክፋይ ቀረብኝ ....ሰባት አመታቴ ቀሩብኝ ጥበቃዬ መና ቀረብኝ እንጂ .... እኔ መች ቀረሁበት ይኸው ሌላ ለመደ አይደል መወደድ ብርቅ እንዳልሆነ አየው አይደል እኔ ሞኟ ቀረብኝ እንጂ እንዲያ ተሞሽሬ አምሮብኝ ተውቤ አማረብሽ ሲሉኝ መላው ቤተሰቤ..... ፊት ለፊቴ የተቀመጠው ሬዲዮ ላይ የያዝኩትን ጥላ አሽቀነጠርኩት አቃጣሪ ሬዲዮ ድግስ ከእሱ ቤት ዘፈኑ እኔ ቤት ምን ይሰራል ተነስቼ እግሬ ወዳመራኝ ሄድኩ ...መድረሻዬን እንጃ ከኋላ የእናቴ ቃል ተከተለኝ የሴት ልጅ ትልቁ ፈተናዋ ምርጫ ነው.... ምርጫሽ ይመር writed by @Koki✨

  • በጣም ከታወቁት የቱርክ የጎዳና ላይ ግድግዳ ጥቅሶች አንዱ እንዲህ ይላል፦ ‘Oysa herkes öldürür sevdiğini…’ ትርጉሙም… ‘ሆኖም ግን፥ ሰው ሁሉ የወደደውን ይገድላል።’ ሁልጊዜ በኃይል ወይም በጉልበት አይደለም… አንዳንድ ጊዜ በውሸት፣ በመራራቅ፣ በዝምታ፣ ወይም ደግሞ ለነሱ የሚገባውን ያህል ዋጋ ባለመስጠት። ይህ ጥቅስ በበዙ የቱርክ ጎዳናዎች ግድግዳዎች ላይ ሊጻፍ የቻለው ለዚህ ነው… ምክንያቱም ብዙ ሰዎች ጥቅሱ በውስጣቸው ያለውን ህመም እና እውነታ እንደገለጸላቸው ስለተሰማቸው ነው።” በተለይ “Yet everyone kills the thing they love” የሚለው የአየርላንዳዊው ጸሐፊ የኦስካር ዋይልድ (Oscar Wilde) ታዋቂ ስንኝ ሲሆን፥ በቱርክኛ ደግሞ በታዋቂው ገጣሚ ቱንጄል ኩርቲዝ (Tuncel Kurtiz) ድምፅ በ‹ኢዘል› (Ezel) ድራማ ላይ በመቅረቡ በሰፊው የተወደደና የብዙዎችን ልብ የነካ ጥቅስ ነው።

  • 25 мар.1 53717

    ዛሬም እንደ ትላንቱ ቤቱ ውስጥ የነገሰው ጭርታ ጆሮዬ ላይ ይጮኻል። የክፍሉ ቅዝቃዜ ከአጥንቴ አልፎ ነፍሴን ይበረብራታል። ሶፋው ላይ ተቀምጬ አይኖቼን ስልኬ ላይ ተክያለሁ። "መጣሁ እኮ!" የሚል ድምፅ ሰምቼ በደስታ የምዘልበት፣ ወይም የስልኬ ስክሪን በርቶ "ሂሩ" የሚል ስም የሚታይበት ይመስለኛል። ግን ሁሉም የናፈቅኩት ቅዠት ነው። እውነታው ግን የመቃብር ያህል ዝምተኛ ነው። ታሪኩ የሚጀምረው ለሦስት ዓመታት አብረን በኖርንበት የትዳር ዘመን ውስጥ፣ እኔ ግን "ፍቅር" የሚባለውን ታላቅ ሀብት እንደ ተራ ቁሳቁስ ቆጥሬ ችላ ባልኩበት ቅጽበት ነበር። ሂሩ ለኔ የልቤ ትርታ፣ የኑሮዬ ትርጉም እና የመከራዬ መጠጊያ ነበረች። እኔ ግን በስኬት ስም፣ በገንዘብ አምልኮ እና በሥራ ጫና ተሸፍኜ ያንን ሁሉ ንቄ ነበር። ያን እለተ ሐሙስ በጭራሽ አልረሳውም። ከቢሮ የወጣሁት በከፍተኛ ጭንቀት እና ብስጭት ነበር። ወደ ቤት ስገባ ሂሩ እንደ ሁልጊዜው ቤቱን በሻማ እና በምርጥ ምግብ አውዳው እየጠበቀችኝ ነበር። ፈገግታዋ ከደጃፍ ይቀበላል። "ውዴ፣ ዛሬ አምሽተህ መጣህ? ና እራት ብላ" አለችኝ፣ ድምጿ ውስጥ ካለው ፍቅር ጋር። እኔ ግን በውስጤ የነበረውን የቢሮ ጭንቀት በእሷ ላይ አፈሰስኩት። "አልፈልግም! ሰርቼ ደክሞኛል፣ ዝም ብለሽ ተኚ!" አልኳት በደረቁ። በዛች ቅጽበት በፊቷ ላይ የነበረው ብርሃን ሲጠፋ፣ አይኖቿ ውስጥ የነበረው ተስፋ ሲረግፍ አየሁት። ምንም ሳትናገር፣ አንገቷን ደፍታ ወደ መኝታ ቤት ሄደች። ያኔ ግን "ይቅርታ" ማለት አልፈለግኩም። ኩራት ነፍሴን ሞልቶት ነበር። በማግስቱ ጠዋት ሂሩ ለኔ ያላት ፍቅር ከራሷ በላይ ነበር። ቁርሴ ተዘጋጅቷል፣ ልብሴ ተተኩሷል። ስወጣ ግን ግንባሯን እንኳን አልሳምኳትም። ከሰዓት በኋላ ቢሮ ውስጥ ስልኬ ጠራ። "ሂሩ" ይላል ። በንዴት አነሳሁት። "ምን ፈልገሽ ነው?" አልኳት። "አይ... ዝም ብዬ ነው... ድምፅህን ልስማ ብዬ ነው። ዛሬ የሆነ ስሜት እየተሰማኝ ነው... ቶሎ ትመጣለህ?" ድምጿ ይንቀጠቀጥ ነበር። እኔ ግን ለዛ ለሚማጸን ድምፅ መልሴ ጩኸት ነበር። "ሂሩ፣ ስራ ላይ ነኝ! ለእንዲህ አይነት ወሬ ጊዜ የለኝም!" አልኩና ስልኩን ጆሮዋ ላይ ዘጋሁት። ያ የሰማሁት የመጨረሻው ድምጿ እንደሚሆን፣ ያ ጥሪ የመጨረሻው የስንብት ጥሪ እንደሆነ እንዴት አውቃለሁ? ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ ወደ ቤት ስመለስ ግን ነገሮች ተለውጠዋል። የግቢው በር ክፍት ነው፤ አምቡላንስ ቆሟል። ጎረቤቶቼ በረንዳው ላይ ቆመው ሲያለቅሱ አየሁ። ልቤ በከፍተኛ ሁኔታ መምታት ጀመረ። እየሮጥኩ ወደ መኝታ ቤት ስገባ ያየሁት ትዕይንት ዓለሜን አፈረሰው። ሂሩ መሬት ላይ ወድቃለች። ዶክተሮች በነጭ ጨርቅ ሊሸፍኗት ሲሉ "አትንኳት!" ብዬ ጮህኩ። አጠገቧ ስልኳ ወድቋል። አነሳሁት። ስምንት ጊዜ ደውላ ስልኩን አልመለስኩላትም ነበር። ዶክተሩ ትከሻዬን ነካ አድርጎ በሀዘኔታ "ልቧ በድንገት ነው የቆመው... ስትሞት በእጇ የያዘችው ይሄንን ነበር" ብሎ አንድ ወረቀት ሰጠኝ። ወረቀቱ በእንባዬ ረጠበ። እንዲህ ይላል፦ "ውዴ፣ ዛሬ ቀኑን ሙሉ የልቤ ምት ሲለዋወጥ ታወቀኝ። ብቻዬን መሆን ስለፈራሁ ደወልኩልህ። ስልኩን ስትዘጋብኝ በጣም አዘንኩ። ግን አሁንም እወድሃለሁ። ቻው የኔ አለም..." ያኔ ነው መላ አካሌ የሰለለው። በድንጋይ ጭንቅላቴን ብመታው፣ ጩኸቴ ሰማይ ቢነካ... የሚሰማኝ የለም። እሷ በጠራችኝ ሰዓት እኔ ለገንዘብ እና ለሥራ ዋጋ ሰጥቼ ነበር። ያቺ ሰከንድ፣ ያቺ የስልክ ጥሪ ህይወቴን ሙሉ የሚከተለኝ እሳት ሆነ። ዛሬም ድረስ በየቀኑ ወደ ስልኳ እደውላለሁ። ኦፕሬተሯ "ደንበኛው ጥሪ አይቀበሉም" ስትለኝ ሂሩ "አልሰማህም" እያለችኝ ይመስለኛል። አልጋው ላይ ስተኛ የእሷ ጠረን አሁንም አለ። ፎቶዋ ላይ አፈጠጣለሁ። አንድ ጊዜ እንኳን "ይቅርታ" ሳልላት፣ አንድ ጊዜ እንኳን "እወድሻለሁ" ሳልላት ተለየችኝ። እኔ ዛሬ የቁም ሙት ነኝ። ትልቅ ቤት አለኝ፣ ጥሩ መኪና አለኝ፣ ባንክ ቤት ውስጥ ገንዘብ አለኝ። ግን እነዚህ ሁሉ ሂሩን ሊመልሱልኝ አልቻሉም። የቤቱ ጭርታ ዛሬም ጆሮዬ ላይ ይጮኻል። የእኔ መልክት ለእናንተ አንድ ብቻ ነው። የምትወዱትን ሰው ሳታጡት ዋጋ ስጡት። The End . ✍️ፀሀፊ:-April

  • 25 мар.1 1501

    без подписи