✍ዮ_ሚን
Статистикаፈጠራዎችን እንደመምባቸዋለን ስለሀሳብ እንሰማለን፡፡ እናሰላስላለን፡፡ ሰክረን ሳይሆን ሰክነን፡፡ሀሳብን እናስበዋለን፡፡ ዘላለም የሚቆየው ሀሳብ ነው፡፡ @Yob_minn
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 7
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Книги (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 358
- 1/48двое суток
- 410
- 1/72трое суток
- 442
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ፈጣሪ እኮ የእንደገና አምላክ ነው !! @yomin1_2
የኔ እናት... ስለአንቺ ሳወራ ልክ ነው እያለኝ ለምነው ሀገሩ ከፊቱ ዞር ስል ''ጅላጅል' የሚለኝ? አላምንም ማንንም... ከአንቺ ሀሳብ ሌላ አቅፈሻል ቢሉኝም የሌላ ሰው ገላ እከራከራለው ብቻዋን ነበረች ውሸት ነው እላለው "ሄዳለች" አትበለኝ "ሌላ ወንድ" አትበለኝ እከራከራለው ብቻዋን ነበረች... እርግጥ ወንድ አቅፏታል ብቻዋን ነበረች... እርግጥ ሰው ስሟታል ብቻዋን ነበረች... እርግጥ ባክኗል ነብሷ ብቻዋን ነበረች... እርግጥ መሬት ወድቋል ስጦታ ቀሚሷ ቢሆንም ብቻዋን ነበረች... ያዩዋት ለኔ ቢያሟት... መጠላት አይደለም ተጠላህ መባል ነው ያፍቃሪ አሟሟት አላምንም... አላምንም አላምንም ማንንም ልቤን ሆነ ምኔን ተይዘሽ ቢያይሽም አላምነውም አይኔን። የሚገርምሽ ነገር... ድሮም ይዋሸኛል... አካል ሰውነቴ ያኔም ስንጣላ ''አትወድህም" ብሎ ዋሽቶኝ ያውቃል ስንቴ። ግን አልጠላሺኝም ምንም ጎኔ ቢያጣሽ ትተሺኝ ሄድሽ እንጂ "ጠላሁክ" የሚል ቃል አንቺ መቼ ወጣሽ? Elias shitahun @yomin1_2
‹‹ስለ እንትን አትጻፍ›› --- ወዳጄ ሰለሞን ሳህሌ ትላንት ልብ ሰባሪ የፌስቡክ መልእክት ለጥፎ ነበር፡፡ "ፍቅር እኮ ነው" የተሰኘውን መጽሐፉን ለአንባቢዎች ለማቅረብ ዝግጅቱን ጨርሶ ዛሬ ሊያስመርቅ ደፋ ቀና ሲል «ቁጥጥር ከሚያደርጉ» አካላት "መጽሐፉ አይመረቅም" የሚል የእገዳ መርዶ እንደደረሰው ነገረን። ውጥኑ፣ ገንዘቡ እና ህልሙ በአንዲት ውሳኔ እጁ ላይ ሟሙ። ይህ ምን ማለት እንደሆነ አውቃለሁና ማምሻውን በሶል ጉዳይ ተነስቼ ልል ስለምፈልገው ተለቅ ያለ ነገር እየተብሰለሰልኩ ሰሞኑን ሁለንተናዬን ወደተቆጣጠረው ድንቅ መጽሐፍ ንባቤ ተመለስኩ፡፡ በረጅም ታሪኩ ውስጥ ካሉት መአት ሰዎች አንዱ ደራሲ በመሆን ዋዜማ ላይ ያለ ወጣት ገጸባህርይ ነው፡፡ የእሱን አንደኛ መደብ ትረካ ተመስጩ እያነበብኩ ነበር፡፡ የታሪኩ ‹‹መቼ›› በ1967 ዓ.ም መሆኑን ልብ በሉ፡፡ ስለሶል ማሰቤን ሳላቆም እያነበብኩ እጩው ደራሲ የፓለቲካው መጋጋል ካሳሰባቸው እናቱ ጋር ያደረጋት ቁራጭ የስልክ ውይይት ፊት ለፊቴ መጣች፡፡ ‹‹ትጽፋለህ አሁን ድርሰት ምናምን?›› ይላሉ እናቱ፡፡ ‹‹አንዳንዴ›› ይመልሳል፡፡ እናቱ ያኔ ምን አሉ…? ‹‹በል ተጠንቀቅ፡፡ መንግሥት የሚነካ ነገር እንዳታደርግ፡፡ ወሽካታው በዝቷል፡፡ በጥርስህ ንጣት የቀና ያሳስርሃል መጥፎ ጻፈ ብሎ፡፡ ስለፍቅር ብቻ ጻፍ፡፡ ስለ ሌላ ሌላ ጻፍ፡፡ ስለወፎች ጻፍ፡፡ በቃ ብልጥ ሁን፡…..›› ግጥምጥሞሹ በጣም ገረመኝ፡፡ ቀድሞም በ2018 ዓ. ም ‹‹ይዘቱ ተገምግሞ›› የመጽሐፍ ምርቃት መከልከሉንም እንደሌላው ነገር ‹‹ወይ ጉድ›› ብሎ ማለፍ ያለፈለገው አንጎሌ ይህችን የድርሰት ብጣሽ ሲያይ ሃገሬ ዛሬም የኋሊት ጉዞ ላይ እንደሆነች አስታወሰኝ፡፡ የሳንሱር ሸምቀቆ ዛሬም ፈጠራን አንቄ ልግደል፣ ፈጣሪን አስቦክቼ ብእሩን ላንጥፍ ይላል፡፡ መርጠህ ጻፍ ብሎ ይዝታል፡፡ አስኳሉ ይሄ ነው ወዳጆቼ፡፡ ሌላውን ትተን ሃምሳውን አመት ብንቆጥር እንኳን ከመራመድ ይልቅ ባለንበት ተቸንክረናል፤ ሲብስም ወደኋላ ተንሸራተናል፡፡ በዚህ ላይ በዚህ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ መጽሐፍ ጽፎ ለህትመት ማብቃት፣ ብሎም ለአንባቢ ማድረስ በራሱ ተራራ መግፋት ነው፡፡ እልህ አስጨራሽ፣ ተስፋ አስቆራጭ እና እጅግ ፈታኝ ነው! መሰናክሉ መዓት፣ አሳሩ ብዙ ነው። የህትመት ዋጋ የምታውቁት ነው፡፡ አይቀመስም። እድል ሰምሮ አሳታሚ ቢገኝ እንኳን ከመጽሐፍ ሽያጭ ተቆራርጦ ደራሲው ኪስ በሚገባው ሳንቲም እንኳን ክብር ያለው ሕይወት ሊኖር የዕለት ጉርስን እንኳን መሸፈን አይቻልም። የምናደንቃቸው የኪነጥበብ ሰዎች አደባባይ ወጥተው ‹‹ራበኝ›› እስከማለት የደረሱት ለዚህ ነው፡፡ ከገንዘብ ነክ ፈተናው ባሻገር ደግሞ ሌሎች ያፈጠጡ ችግሮች አሉ፤ ደራሲው ለሰው ከማይታዩ ጠላቶች ጋር በየጓዳው ይታገላል። "ማን ምን ይለኝ ይሆን?" በሚል ፍርሃት ተሸብቦ የራሱን ብዕር ይቆጣል፤ ወቀሳና ውንጀላን ለመሸሽ ራሱ ላይ ማዕቀብ (Self-censorship) ያደርጋል። ይህ ሁሉ ፈተና እንዳለ ሆኖ፣ ይባስ ብሎ ዛሬ በሶል እንዳየነው ያሉ መንግስታዊ እቀባዎች እና ግልጽ ጫናዎች ብቅ እያሉ የፈጠራ ነፃነትን ማነቅ ከጀመሩ ሰንብተዋል። የመንግሥት ተቋማት ዜጎች ምን ማንበብ፣ ምን ላይ መወያየት ወይም የትኛውን መጽሐፍ መመረቅ እንዳለባቸው ለመወሰን ጣልቃ ሲገቡ፣ የግለሰቦችን መጽሐፍትና ዝግጅቶች ብቻ ሳይሆን ነፃ አስተሳሰብን እያፈኑ መሆኑ ግልጽ ነው። ጉዳዩ ከአንድ ደራሲና ከአንድ መጽሐፍ የሰፋ ነው፡፡ መዘዙም ብዙ ነው፡፡ ይሄ አካሄድ ጨቋኝና አፋኝ ነው። የሚያስተላልፈው መልእክትም አደገኛ ነው፡፡ «ስለ እንትን ሳይሆን ስለ እንትን ጻፍ» የሚል አሰራር ጎታችና በዚህ ዘመን መኖሩ የሚያሳፍር አካሄድ ነው!
የሰርክ ፀሎት 🙏 የማያረጅ ፣ የማይቀጭ ፣ ወረት አልባ ፍቅር ስጠኝ ፤ ማግኘቴ ውስጥ የምሰጠው ፣ የማግዘው ፣ የሚደሰት ይኖረኝ ዘንድ ቸር ልብ ስጠኝ ፦ የምችለውን ችግር ስጠኝ ፣ መኖሬ በሰው ቸርነት ይቀጥል ዘንድ የምለምን አልሁን ፦ ሳጠፋ ይቅርታ የሚጠይቅ ልቦና ስበደል ይቅርታ አድራጊ ልብ ስጠኝ፦ ገመና የምሸሸግ ፣ ብልግናን የማላጎላ ፣ ዘመዴ የሆነውን የሰው ልጅ የምወድ እና የምረዳ አድርገኝ ፦ እንግዳ እንደሆንኩ ስኖር በዚች አለም ይገባኝ ዘንድ ልቦናዬን አብራልኝ ስለሆነልኝ ፣ ስለምታረግልኝ ነገር እኔ ባሪያህ አመሰግንሃለሁ አሜን 🙏🙏 @yomin1_2
መታለሌ አይደለም እንዲ ያቆሰለኝ። ማታለል በሙሉ ቀን ምግባሬ የሆንኩ ሰው መታለል አያሳምመኝም ፤ ባታላይ ተከብቤ የምውል ሰው ነኝ እንቅስቃሴዬ ላለመታለል በጥንቃቄ ነው። ያቆሰለኝ በእሷ በእማምናት ፊት ስቆም ሃጥያቴን የምታጎላብኝ ናት በምላት ስታለል ነው የቆሰልኩት ። ጥንቃቄዬን አውልቄ በጣልኩባት ልጅ ስለሷ ንፅህና ስደሰኩር የምውልላት ልጅ እንዳታለለቺኝ ስደርስበት ነው የታመምኩት ። አንድ የማምናት ትወደኛለች የኔ ናት ያልኳት ስታታልለኝ ፤ ማመኛዬን ስታቃጥለው ነው መታመሜ ። እስከዛሬ ስለሷ የሰጠውት ምስክርነት ለካ ውሸት ነበር ። አንድ እሷን ባምናት አንድ ከጀርባዬ አታሴርም የምላት ልጅ የማልወደውን የማልፈልገውን ነገር ስትከውን መሆኑን ስደርስበት ነው መታመሜ ። መካድን የመሰለ ፈውስ አልባ ህመም የለም !! ከበደሉ በላይ የበዳያችን ማንነት ነው ገዳያችን። © Adhanom Mitiku @yomin1_2
በወላጅ ዓይን ውስጥ ከሚታይ ኩራት በላይ ለልጅ ምን ስጦታ ይኖራል? @yomin1_2
ተመለሰልኝ ደስታ ሰላሜ 🙏 @yomin1_2
ተሰብስበን ኤክሳችን የተወችንን ምክንያት እያወራን ነበር ...፦ ፍሬንድ ጀመረ "እድሜ ትበልጠኝ ነበር ። ወሬዬ ሙግቴ ውስጥ ሁላ ልጅነቴ ይታይ ነበር መሰል... ቀስ ብላ ላሽ አለቺኝ " አንደኛው ጀለስ " እኔ እበልጣት ነበር በእድሜ.... ወሬዬ ሁሉ ፣ትዳር ፣ኑሮ ፣ልጆች ወልደን ፣ ስራ ሰርተን ጥረን ግረን ምናምን ሲሆን ቸካት ...በዚህ እድሜ' ዬማ ችስታ ሹገር ዳዲ አልጠብስም ብላ ይመስለኛል ተወቺኝ ...ከኔ ቀጥሎ የሆነ ኮሚክ ቁምነገር ውል የማይልበት እኩያዋን ጠበሰች ፦ ሌላ ፍሬንድ ቀጠለ " የኔ ዋ ጋ እንኳን እኩያሞች ነበርን ። ማኔጅ መደራረግ ከበደን መሰለኝ ። በሰል የሚል ፈልጋ ይመስለኛል ገሸሽ አደረገቺኝ" ። እኩያ ብትሆን፣ ብትበልጥ፣ ብታንስ ልትተው ትችላለህ ለመተው እና ለመወደድ አለም አቀፍ ቀመር የለም! @yomin1_2
ሰው ይመኛል! አንዱን ሲሰለች ሌላ ፥ አንዱን ሲጥል አንዱን እያነሳ። በጊዜ ምኞት ሁሉ እንደማያፈራ ፥ አብዝቶ የጓጓለትን እንደሚያጣ ያያል — ግን አይማርም። ስኬት - ማግኘት ብቻ አይደለም።እዉነትን መጋፈጥ ፥ ማጣትንም ማመን ይጨምራል። ከአለት ትግል የሞኝ ነዉ። ሲሆን - መጨከንም ድል ነዉ። @yomin1_2
https://vt.tiktok.com/ZS4GuACYX/
Check out Hiwot Emishaw's video! #TikTok https://vm.tiktok.com/ZS41WS5Bg/ This post is shared via TikTok Lite. Download TikTok Lite to enjoy more posts: https://www.tiktok.com/tiktoklite
Check out Hiwot Emishaw's video! #TikTok https://vm.tiktok.com/ZS41WS5Bg/ This post is shared via TikTok Lite. Download TikTok Lite to enjoy more posts: https://www.tiktok.com/tiktoklite
ስበደል የምሸሸግብሽ ፤ ተዝረክርኬ ዝንጥ እንዳልኩ የምታሰሚኝ ፤ህመሜ የሚረብሽሽ ፤ ስኬቴ የሚያስፈነድቅሽ ነገሬ ሁሉ ጉዳዬ ነው የምትይ ፤ ጠይቄሽ የማትከለክይኝ ። አንቺ ለኔ ረቂቄ ነሽ!! @yomin1_2
በህይወት ጉዞ በኑሮ ዳገት ልብሽ ቢሰበር ቢከፋሽ ድንገት ፤ በምትቆሚበት አብረው እየቆሙ ባለደረግሽው… ሰዎች ወዳንቺ ቢጠቋቆሙ ፤ በምታምኝው ሰው ቀልብሽ ቢሰበር ዳግም ላትከፍቺው… ብትጠረቅሚው የእምነትሽን በር ፤ ፍቆ ሊያጠፋሽ ከህይወት ቀለም ቢሰለፍ ምድር ቢሰለፍ አለም ብቻ… እንደባለገች ከሌላ ሰው ባል ፍርዷን ትቀበል ትወገር ቢባል ይህን አስታውሺ… ሚወድሽ አለ ኢዮብ የሚባል። (እዮብ ዘ ማርያም) @yomin1_2
ማነሽ አንቺ ከአለም ከተኳረፍኩ በኋላ የመጣሽው ፤ እምነት የማያልቅ ከነፍስ የተዋሀደ መሆን የምታበስሪኝ ማነሽ ? ታውቆሻል ? መወደድ የሚገባ ነህ እያልሺኝ ነው? እንደምናፈቅ እያሳየሺኝ ነው? መወደድን የሚያክል ምን በረከት አለ? ገብቶሻል አይደል? እንቅስቃሴሽ ይመለከተኛል እያልኩ ነው? የሚቆረቁርልኝ ፣ ያገባኛል የሚለኝ ሰው ሊኖረኝ ነው ? እየደረኩ ነበር እንደናፈቅሺኝ አይኖችሽ ሲያቃጥሩ ነው የለመለምኩት ። ስቀና ፣ ስብከነከን ፣ ስትናፍቂኝ ጊዜ ነው እስከዛሬ የተዜሙት ዜማዎች ትርጉም የሰጡኝ ። እወድሻለሁ ❤ @yomin1_2
ከረፈደም ቢሆን መልካም ልደት 🖤 @yomin1_2
ጠዋት በጨረፍታ የሰማሁት ፀሎት "አምላኬ ሆይ የሰጠኽኝ ይበቃኛል እሱን ባርክልኝ ልቦናዬንም አብራልኝ" 🙏🙏❤ @yomin1_2
ያለኝ የነበረኝ ገና ሚኖረኝን ሳይቀር እያጣሁት፤ ይኸን ያህል ስክነት ከየት አመጣሁት። Elias shitahun @yomin1_2
ናልኝ ቢሉህ :ትመጣለህ ስጠኝ ቢሉህ :ትሰጣለህ ቸር አይደለህ! እኔ ግን ምን ብዬ ልጠይቅ? ሂወቴን ምን ላርገው እወቅልኝ እስቲ ምንድነው ጌታዬ እኔ ምፈልገው?? Unknown poet @yomin1_2
ተሳካላት አሉኝ እየተሳቀቁ እማዝን መስሏቸው .. ስስቅ ገረማቸው ተያቸው !! ስኬትሽ ..... አብረን የወጠነው ፣አብረን ያወጣነው፣ አብረን ያወረድነው ፤ ፀሎቴም መሆኑ ስላልገባቸው ነው !!! @yomin1_2