ነፃ ዓለም✨✨✨
Статистика✨አጫጭር ወጎች ✨ልቦለዶች ✨መፃህፍት ✨profile picture ✨የተለያዩ ሰዎች ድንቅ አባባል ✨ግጥሞችን ያገኛሉ። ለሀሳብ ለአስተያየት @netsi2_9
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 6
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 490
- 1/48двое суток
- 561
- 1/72трое суток
- 605
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን 😊😍🙏🙏
ሁሌም የሴቶች ዶርም ድረስ መጥቶ ሸኝቶኝ ሲመለስ ባለማመን ያዩታል። «ሔለን ግን ሙድ እየያዝሽብን ነዋ! ያን ሁሉ ወንድ ያባረርሽው ይሔ ፉንጋ ጋር ለመሆን ነው?» ትላለች አንደኛዋ። «እስኪ ተያት ምን ታውቂያለሽ? ራቁቱን ያዬችው እሷ!» ብላ ሌላኛዋ ታሽካካለች። እኔም አስከፋናት ብለው እንዳይደብራቸው እስቅላቸዋለሁ። ዋና ምክኒያቴን ከሚያውቁብኝ የጠረጠሩት እውነት እንደሆነ እንዲሰማቸው ባደርግ ይሻለኛል።…
https://t.me/NEKU_TEWLD10
"እንግሊዝኛ እሰማለሁ፣ እረዳለሁ... ግን መናገር ስጀምር ቃላት ይጠፉብኛል!" የሚል የሁልጊዜ ስጋት አለባችሁ? 🤦♂️🤦♀️ የቃላት እጥረትና የሰዋስው ስህተት ፍርሃት ወደ ኋላ እንዳያስቀራችሁ! እንግሊዝኛን ልክ እንደ አማርኛ ያለ ምንም መቆራረጥ አቀልጥፈው የሚናገሩበትን ብቸኛ አማራጭ አቅርበንላችኋል። 🌟 @ENGLISH_LANGAUGE_CLUB 🌟 ከእኛ ጋር ሲማሩ፡ የአነጋገር ስልትዎን (Accent & Pronunciation) ያሻሽላሉ። በየቀኑ የሚጠፉብዎትን ቃላት (Vocabulary) በቀላሉ ይለምዳሉ። ከስህተት ፍርሃት ነፃ ሆነው መናገር ይለማመዳሉ። አሁኑኑ ይቀላቀሉና የቋንቋ ብቃትዎን ወደ ላቀ ደረጃ ያሳድጉ! 👇👇 ሊንኩን ይጫኑ 👇👇 👉 @ENGLISH_LANGAUGE_CLUB 👈 የለውጥዎ መጀመሪያ!
📚 የ9–12ኛ ክፍል እና 𝗨𝗔𝗧 (𝗔𝗨,𝗔𝗦𝗧𝗨,𝗦𝗜𝗧.. ተማሪዎች — ይህ ለእናንተ ነው! ውጤታችሁን ማሻሻል እና ለፈተና በተሻለ ሁኔታ መዘጋጀት ትፈልጋላችሁ? በቻናሉ: 📌 ✅የ9–12ኛ ክፍል የአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ኖቶች 📝 ✅𝗘𝗨𝗘𝗘 & 𝗨𝗔𝗧 ጥያቄዎች ከማብራሪያ ጋር 🗣️ ✅የዕለት ተዕለት English 𝗩𝗢𝗖𝗔𝗕𝗨𝗟𝗔𝗥𝗬👌 📖 😍ጠቃሚ የትምህርት ማቴሪያሎች እና የፈተና ምክሮች 🔒 ቻናሉ በቅርቡ 𝗣𝗥𝗜𝗩𝗔𝗧𝗘😱 ይሆናል። አሁኑኑ በነፃ ይቀላቀሉ! 👇 እዚህ ይቀላቀሉ: https://t.me/highschoolnote
ሁሌም የሴቶች ዶርም ድረስ መጥቶ ሸኝቶኝ ሲመለስ ባለማመን ያዩታል። «ሔለን ግን ሙድ እየያዝሽብን ነዋ! ያን ሁሉ ወንድ ያባረርሽው ይሔ ፉንጋ ጋር ለመሆን ነው?» ትላለች አንደኛዋ። «እስኪ ተያት ምን ታውቂያለሽ? ራቁቱን ያዬችው እሷ!» ብላ ሌላኛዋ ታሽካካለች። እኔም አስከፋናት ብለው እንዳይደብራቸው እስቅላቸዋለሁ። ዋና ምክኒያቴን ከሚያውቁብኝ የጠረጠሩት እውነት እንደሆነ እንዲሰማቸው ባደርግ ይሻለኛል። ለሰው ባይመስልም ፉንጋው የፀሎቴ መልስ ብቻ ሳይሆን ጨለማ ክፍል ውስጥ ያገኘሁት ሻማዬ ነው። «ሔሉዬ ሌላ ቅፅል ስም ጠፍቶ ነው 'ሻማዬ' የምትይኝ?» ይለኛል። «ሻማዬ ካላልኩህ ችቦዬ ነው የምልህ...የቱ ይሻልሀል?» «አይ ሻማው ይሁን በቃ!» ይላል እየተቅለሰለሰ። አንዲት ፀበል ለፀበል የምትመላለስ ታላቅ እህት አለችኝ። ሰዎች መንፈስ ይዟት ነው እያሉ ያወራሉ። እኔ ግን ባሏን ፈትታ ከመጣች ቡኃላ የዘመድ አዝማዱን ወሬ አትችለው ብላ እንዳበደች አውቃለሁ። ከዛ ጊዜ ጀምሮ ፀሎቴ አንድና አንድ ብቻ ነው። «ጌታ ሆይ የምወደውን ሳይሆን የሚወደኝን ስጠኝ!» ለዛ ነው ሻማዬ የፀሎቴ መልስ ነው የምለው። የመጀመሪያ ቀን ሰውነቱ በላብ ተጠምቆ፣ እጁ እየተንቀጠቀጠ፣ መተንፈስ አቅቶት እየቃተተ ሲጠይቀኝ እንደማገባው ወስኜ ነበር። የግቢውን ወንዶች ሁሉ መልሼ እሱን የጠበስኩት እነሱ እንደሚሉት የተለዬ ነገር አግኝቼበት አይደለም። ሪስክ መውሰድ ስለማልችል ነው። የፈሪ ሰው ጥቅም?...ቀድሞ አያጠቃም! ግቢ ውስጥ በኔ ምክኒያት ያልደረሰበት ግፍ የለም። ለሁሉም ታዋቂ ካፕሎች ቅፅል ስም ሲሰጡ እኛን ማን ቢሉን ጥሩ ነው? "Beauty And The Beast" ሆሆ! ተረባውን ችሎ አለፍ ሲል ደግሞ መምህራኖች ግሬድ ያበላሹበታል። ጉልበተኞች ዱላ የቀላቀለበት ማስፈራሪያ ያዘንቡበታል። ዘበኞች እንኳን ባቅማቸው ያዋክቡታል። ሁሉም እንደየስልጣኑ ይበድለዋል። «ሻማዬ ከዚህ በላይ እንድትጎዳ አልፈልግም» ስለው «ቀላል ነው ብዬ አልዋሸሽም። ሽልማቴ አንቺ እንደሆንሽ ሳስበው ግን 'ኧረ ያንሰኛል ጨምራችሁ ምቱኝ' ልላቸው ሁላ ያምረኛል!» እያሳዘነ ያስቀኛል። ገፍተው ገፍተው ለራሱ ያለውን አመለካከት እንዳወረዱበት የገባኝ የአመቱ መጨረሻ ላይ ነው። እሱ ተመራቂ ስለነበር ቀጣይ አመት እንደማንገናኝ ገብቶት እያለቀሰ መጣ። «አንተም ስራ ልታገኝ የምትችለው እዚሁ አዲሳባ ነው። እኔም እዚሁ ነው የምማረው! ምን የተለዬ ነገር ተፈጠረና ነው የምታለቅሰው?» «አንድ ነገር ብቻ ቃል ግቢልኝ!» አለ አሁንም እያለቀሰ! «እሺ ምንድን ነው?» «እስክትመረቂ ድረስ የፈለግሽው ወንድ ጋር ሁኚ! ከዛ ቡኃላ ግን ተመልሰሽ ወደኔ ልትመጭ ቃል ግቢልኝ!» ምንም አላልኩትም። በቆመበት ጥዬው ሔድኩ። ምን ባደርገው ነው ሊተማመንብኝ የሚችለው? እኔስ በዚህ ደረጃ ከሚወደኝ ወንድ ውጭ ሌላ ምን እፈልጋለሁ? ከሶስት ቀን ቡኃላ የሻማዬን ልብ ያረጋል ብዬ ያሰብኩትን ትልቅ ውሳኔ ወሰንኩ። ሲያዬው አዲስ እንደተወለደ ህፃን ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ ጀመረ። ለነገሩ እኔም ከዛ ያነሰ ግብረመልስ አልጠበኩም። ይሔንን ፊት ለዘላለም እንዳይጠፋ አድርጌ ጀርባዬ ላይ ተነቅሼለት ለቅሶ ሊበዛብኝ ነው? የሚያስቀው እንራራቃለን ብዬ ፊቱን ተነቅሼለት ሌክቸረር ሁኖ እዛው ግቢ ቀረ። የሚያሳዝነው ደግሞ ተማሪዎች በገቡ በመጀመሪያው ሳምንት ሁሉም ስለታቱዬ አወቁ። የፈሪ ትልቁ ችግር?....ምርኮኛ አያያዝ አይችልም! «ለማን ተናግረህ ነው?» ብዬ ሳፈጥበት...አብሮት ሌክቸረር ለሆነ ሰቃይ ጓደኛው ብቻ መናገሩን ነግሮ ይቅርታ ጠየቀኝ። እኔም ከተያዙ ቡኃላ መንፈራገጥ ጥቅም የለውም ብዬ ተውኩት። የግቢው አየር ባንድ ጊዜ ተገለበጠ። ሻማዬ የግቢው ቁጥር አንድ ተፈላጊ ወንድ ሆኖ ቁጭ አለ። እኔ ደግሞ ስወጣ ስገባ የተረባ መለማመጃ ሆንኩ። አንዴ ወጣቶች ተወራርደው አስገድደው ልብሴን ገልጠው፣ ታቱዬን ካዩብኝ ቡኃላ ከሀዘን የወጣሁበት ቀን ትዝ አይለኝም። ሻማዬ ሊጠብቀኝ ቀርቶ ቶሎ ቶሎ ሊያገኘኝ ራሱ ጥረት አያደርግም። እኔ ነኝ የምደውልለት። እንዲያውም አልናገርም ብዬ እንጂ አልፎ አልፎ የግቢው ታዋቂ ሴቶች ከቢሮው ሲወጡ አያለሁ። በአንድ ወቅት ሊነካኝ ከብዶት ሲንቀጠቀጥ የነበረ ሰው፤ ዛሬ መዳፉ ላይ ሲያገኘኝ ጨብጦ ሊያፈርጠኝ ሲዳዳ ባዬው...ለመረዳት ከበደኝ። የሆነ ቀን ጉዳዩን ጨራርሰን እንደተቀመጥን «ሰሞኑን መድሀኒት ስትጠቀሚ አላይሽም! ሌክቸረር ሆነ ብለሽ ልታረግዥብኝ ነውዴ?» አለኝ። በዚች ንግግሩ ታሪኬን ቀዬረው። ትምህርቴን አቋርጨ አዲስ ህይወት ጀመርኩ። ስሜንም ቀየርኩ። ታቱዬን ሙሉ ጥቁር አድርጌ "ብላክ ሆል" ነው እያልኩ መንገር ጀመርኩ። ሰላም ያለው ህይወት ለመኖር የነበረኝ አንድ አማራጭ ነበር። ሁሉንም ሰው ከህይወቴ አስወጥቼ ልጄን ማሳደግ። የዚያኔ እንደዛ ባለኝ ሰዓት ፀባዩ ሲስተካከል እነግረዋለሁ እያልኩ ያረፈድኩባት ፅንስ ነበረችኝ። አሁን አሁን ሳስበው ታሪኬ ረጅም ይመስላል እንጂ አጭር ነው። ይቺው ናት ውጣ ውረዴ! ልጄን እስካሳድግ ድረስ ሁለት ጊዜ ብቻ ነው ከቤተሰቦቼ ጋር የተገናኘሁት። እነሱም እምብዛም ሊያዩኝ አይፈልጉም። መላቀቅ ነው! ይቅሩብኝ ከነምላሳቸው! ምላስ ሽሽት ነው ነው ኑሮዬ! አልፎ አልፎ ስር እንዳይሰድ አድርጌ የወሲብ ግኑኝነት እጀምራለሁ። እነሱም ስለኔ ትንሽ ማወቅ ሲጀምሩ ጥያቸው ዲዲዲዲዲዲ! በዚህ ርዕስ ላይ ከማወራ ይሻለኛል። ልጄ በኔ መልክ ባባቷ ጭንቅላት በመውጣቷ ያገኛት ሁሉ ይወዳታል። እኔም በሷ እየተፅናናሁ እኖራለሁ። በቃ። ይሔን ሁሉ ቁጭ ብዬ የማስበው ዛሬ «አባቴ ማነው?» ብላ ጠይቃኝ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ሩጨ የማላመልጣት ሰው ገጠመችኝ። የመመለስ ግዴታ እንዳለብኝ አውቃለሁ። ግን እንዴት ነው የአ'ምሮ በሽተኛ ሳላደርጋት ስለአባቷ ልነግራት የምችለው? ተረት ላድርገው ይሆን? እምብዛም የማይንቁት...እምብዛም የማያደንቁት የ'ንደኔ አይነቷ ኖርማል ሰው ህይወት እንዴት ነው የሚተረተው? «ተረት ተረት!» «የመሰረት!» «በድድሮሮሮሮ ጊዜ አንዲት ሔለን የምትባል፤ ከብርጭቆዋ ጋር ጨለማ ክፍል ውስጥ የምትኖር ልዕልት ነበረች።» «እእእሽ» «ሁሌም ሌቦች ብርጭቆዬን ይሰርቁብኛል ብላ ስለምትሰጋ ጨለማው ያስፈራት ነበር። ከዛ አንድ ቀን ምን ብታገኝ ጥሩ ነው?» «ምን?» «ሻማ!...በጣም ደስ አላት። ሻማዋን አብርታ እያዬች ደስ አላት። 'ይቺ ሻማ እስካለች አልሰጋም' ስትል አሰበች። ሻማዋ ግን 'እጠፋለሁ' ብላ ትሰጋ ነበር። ንፋስ በመጣ ቁጥር ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ ይላል። ልዕልቷም ሻማዋን ከንፋስ ለማስጣል ብላ አንድ የሞኝ ውሳኔ ወሰነች!» «ምን አደረገች?» «በብርጭቆዋ ሸፈነቻት።» «ከዛስ?» «ከዛማ ሌባ ይገባል ብላ በር በሩን እያዬች ከኋላዋ ቃቃቃቃቃቃ የሚል ድምፅ ተሰማት። ደንግጣ ስትዞር የምትሳሳላት ብርጭቋዋ ናት። ንፋስ መቋቋም አቅቷት ልትጠፋ የነበረችው ሻማ በሙቀቷ ብርጭቆዋን ሰንጥቃባታለች። ልዕልቲቱ አዘነች። ውሀ አጣጯ ቢመጣም ውሀ መጠጫ እንደሌላት እያሰበች አለቀሰች! አለቀሰች!..» እያለ የሚቀጥል ተረት! ፨፨፨ By Michel azmeraw @wegoch @wegoch @paappii
አብረን እንድናድር ብዙ ለምኛታለሁ...እምቢ ብላኝም አታውቅም...እሺ ትለኝና የሷ ነገር ሚጀምረው ቀኑ ሲደርስ ነው።ለመቅረት ምክንያት አታጣም ..ታጥቤ ታጥኜ ስጠብቃት አልቅሳ ያሳመነቺኝ ቀናቶች ብዛታቸው።ወዳታለሁኮ ግን ታናድደኝ ነበር ስለ ትውውቃችን ትንሽ ልንገራችሁ... ምግባር ትባላለች...ታምራለች ቢሉ ተማሪ ሁሉ ሚስማማባት ጠይም ቆንጆ ነች።ስትስቅ ብቻ ፍንጭቷ ይታያል...ሌላው ይኼ ቀረሽ የማትባል ውብ ናት...ለመጀመርያ ጊዜ ያየኋት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አካውንቲንግ ዲፓርትመንት ጋ ነው ፍሬሽ እንደሆነች ወድያው ነበር ያወቅኩት ወረቀት ይዛ ግራ ቀኝ እያማተረች ሀይለአብ እባላለሁ...ምረዳሽ ነገር አለ ??አልኳት እስከዛ ሰአት ድረስ ሴት አውርቼ አላውቅም ነበር... ጤና ተመድቤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከገባሁ 3ተኛ አመቴ ነው አንድም ቀን ለሴት ደንግጬ አላውቅም ያን ቀን ግን ለሷ ልቤ ደነገጠ ምግባር አለቺኝ አይኔን ላለማየት ሩቅ እያማተረች....ግን ደሞ እርዳታዬን ፈልጋም ስለነበር ግቢውን እየመራኋት ጉዳይዋን እስክትጨርስ ተግባባኋት።በወሬዋ መሀል ሊያስመዘግባት የመጣ ወላጅ ቅርብ የሆነ ዘመድ እንደሌለ ገብቶኛል ስልኳን ወስጄ ከተለየኋት ማግስት ግንኙነታችን ቀጠለ የካፌ ሻይ እያጋትኳት ረጅም ወሬ አወራን ምስኪን ናት እናት እና አባቷ የሞቱት በልጅነቷ ነው ቶሎ ሆድ የሚብሳት ነገር ናት.... ከወራት በኋላ መግባባታችን ቀጥሎ ጥንዶች ሆነን አረፈፍነው።ፍቅር ያልነካካው ልቤን ሰብራ የፍቅር አጥሯን አጠረችበት ህይወቴ ላይ ሌላ ህይወት ዘራችበት ከንፈሬ ላይ ለመጀመርያ ቀን አሻራዋን አሳረፈችበት ትንፋሽ እስኪያጥረኝ ሳመቺኝ...ከየት አመጣሽው??እንዴት ለመድሽ?? አላልኳትም።በየቀኑ እያገኘኋት አለሜን መቅጨት ጀመርኩ....አንቀን አብረን እንደር አልኳት ማታ ወደ ዶርሟ እየሸኘኋት...እጇን ይዤው ስለነበር በቅፅበት ሲረጥበኝ ተሰማኝ መልስ አልሰጠቺኝም ምነው አልኳት ደግሜ.... አቅፋኝ ብቻ ወደ ዶርሟ ገባች።ከዛ ወዲህ መለወጧ እየጨመረ እየሸሸቺኝ መጣች እኔም አንዳንዴ ለምን አብረን አናድርም የሚል ጭቅጭቄ እየባሰ ኩርፊያችንን በየቀኑ ሆነ እየተኳረፍን አመት ገፋ..እኔ 6ተኛ አመቴ ሲመጣ እሷ ሶስት አመቷን ጨርሳ ተመርቃ ወጣች....ትንሽ ክፍተት ትልቁን ኩርፊያችንን አባሰችው እየወደድኳት እየፈለገቺኝ ድምፃችን ተራራቀ...አካላችንን ሀሳባችን እዚህ እና እዚያ ሆነ ፍቅር እያሳሳቀ አለያየን።ብቻዬን ሲኦል የገባሁ እስኪመስለኝ መኖር እስኪከብደኝ ተሰቃየሁ የሷን ነገር ግን ሳላውቅ ተመርቄ ወጣሁና ዶክተር ሆኜ ስራ ገባሁ "ተረኛ ምግባር ሲሳይ"የሚል ድምፅ ነርሷ በር ላይ ቆማ ስትጣራ ደነገጥኩኝ ስሟ አዲስ አልሆነብኝም ጭራ ልቤ ይረግጠኝ ጀምሮ ነበር....ወዲያው ግን በሩ ተከፍቶ አንዲት ከሲታ ምስኪን ሴት ገባች ያቺ የድሮዋ ምግባር መሆኗን ለማወቅ ሰኮንድ አልፈጀብኝም ምግባር???አልኳት ከተቀመጥኩበት እንደመነሳት እያልኩ ሀይለአብ አለች አልረሳቺኝም የት ጠፍተሽ ነው??ምነው እንዲ ከሳሽ...ምነውውው ችግር አለ???አልኳት በስስት እያየኋት ችግርማ የቅርብ ወዳጄ አደለ??ገና ከመጀመሯ እንባዋ ይፈስ ጀመረ.... ሀይሌ ላንተ ብዬ ነው የሸሸሁት አንተን ለማዳን ብዬ አለችና ሲቃዋ ቀደማት እኔን ከምን ለማዳን ምግባሬ?? ከበሽታ ....ሲያልፍም ከሞት....እናት አባቴ ሲወልዱኝ አውርሰውኝ የሞቱት በሽታ አለብኝ ከኔጋ ሆነህ የደበቅኩህ እንዳላጣህ ነበር...አሁን ግን ጊዜ አገናኘን ልቤ ውስጥ ባለ ፍቅር ተቀራርበን ደሜ ውስጥ ያለው ቫይረስ አለያየን ..በዚህ ብንቀጥል አንተንም አጣሀለው እኔ ደሞ ምፈልገው እንድትኖርልኝ ነው።ትንሽ አመም ያረገኛል..አሁን ማረፍ እፈልጋለሁ አንተ ግን አምሮብሀል አለቺኝ እንባዋ እየወረደ ፈገግ ለማለት እየታገለች ምግባሬ አግብቻለሁ ሁለት ቆንጆ ልጆችም ወልጃለሁ አልኳት አንገቴን እንደሰበርኩ አውቃለሁ ስትመረቅ ሩቅ ሆኜ አስመርቄሀለው ..ስታገባም ሰርግህን ከሩቅ ታድሜያለሁ..አጨብጭቤልሀለው...ስትወልድ ለሚስትህ ውብ አበባ በሰው ልኬያለሁ ደሞ ሁሌም እኮራብሀለው እሺ የተናነቀኝ እንባ ሽፋሽፍቴን ጥሶ ጉንጬ ላይ ሲንከባለል ተሰማኝ ወድያው መርመሬያት እንድንለያይ ፈለኩ ደሟን ወስጄ ሚሰማትን ጠይቄ ውጤቷን በኋላ እንደሚደርስ ነግሬያት ተለየኋት.....አንዳች መጥፎ ነገር እንዳለ ግን ስመረምራት ታውቆኝ ነበር ምግባር ውጤቷ የካንሰር ተጠቂ መሆኗንና ከቀናት በላይ እንደማትቋይ ያሳያል..... ለምን???ለምን???ለምንንንን እያልኩ አምርሬ ጮኽኩ ምግባርን ልጅ ለምን አትወልጂም እስከመቼ ያልኳት ጥያቄ መልስ ጆሮዬ ላይ መጣ "እስከመጨረሻው.."ብላኝ ነበር ምናልባትምኮ መጨረሻችን ነገ ወይ ከነገወድያ ወይ አሁን ነው አደለ.....?? "አንዳንዱ ከመጀመርያው ይታደላል ሌላው እስከመጨረሻው ይፈተናል" @highlight #source_facebook @NetsaAleme
አልጠረጠረም
አልጠረጠረም
በክፍል ውስጥ ተማሪዎች በዘር፣ በቡድን እየተከፋፈሉ መምህሩን አስቸገሩት። መምህሩም ለተማሪዎቹ አንድ ተግባራዊ ትምህርት ለመስጠት "ይቅር የማትሉትን እያንዳንዱን ሰው እያሰባችሁ በየስሙ አንድ አንድ ቲማቲም በከረጢት ውስጥ ክተቱ" አላቸው። ተማሪዎቹም እንደተባሉት አደረጉ። ... መምህሩ በመቀጠል "ይህንን ከረጢት ለሰባት ቀናት በሄዳችሁበት ሁሉ ሳትለዩ ተሸከማችሁ ዙሩ።" አላቸው። ተማሪዎች የተባሉትን ሲያደርጉ ቀናት እያለፉ ሲሄዱ ተማቲሙ መበስበስ በመጀመሩ ሽታው ሰላም ነሳቸው፤ ይባስ ብለው ግማሾች መቋቋም ተስኗቸው ለመጣል ተገደዱ። ሳምንቱ ሲያልቅ ተማሪዎቹ እየተማረሩ ከረጢቱን ይዘው ተመለሱ። ... መምህሩም "በውስጣችሁ ቂምና ጥላቻን ስታቆዩ በልባችሁ ላይ የሚፈጠረው ነገር ልክ እንደዚሁ ነው። ሰዎችን ይቅር አንልም ስንል፣ የጥላቻውን ሸክምና ግማት የምንሸከመው እኛው ራሳችን ነን።" አላቸው። ... ይቅርታ ማድረግ ሌላውን ሰው መጥቀም ብቻ ሳይሆን፣ ራስን ካልተፈለገ የቂምና የጥላቻ ከባድ ሸክም ነፃ ማውጣት ነው። ልባችን የፍቅር እንጂ የበሰበሰ ድንች ማከማቻ መሆን የለበትም። #source_ማዕደ_ጥበብ @NetsaAleme
እኔ ብሆን አደርገዋለሁ ወይ ብዬ ራሴን እንድጠይቅ የሚያደርጉኝ ለሰው ብዙ የሆኑ ሰዎች አሉ። የሚያስገርሙኝ የሚያስደንቁኝ ብቻቸውን ለብዙሀን የሚሆኑ ምን ሰው አለ በዚ ዘመን እንዳልል ለዘመኑ ደግ ልባቸው ከለላ የሆነላቸው። የዋህነት የተዋሀዳቸው....በየትኛውም መስፈርት ሚዛን የሚደፉ አመስጋኝ ልበቀና ሰዎች አሉ። የልባቸው መንጣት ለቆሻሻው አለም የማይመጥን....የደገፉት እንዳይጥላቸው የምፈራላቸው....ነጭ ልባቸው በአለም ጥቀርሻ እንዳይመነችክ የሚያስፈራኝ ሰዎች አሉ። ሁለት ልብ በኖራቸው ብዬ አስባለሁ....በነጭ ልብስ ስራ አይሰራም ይመነችካል እንደሚባለው....እዚህ ቦታ ነጭ ልብ ይመነችካል ነጩን አውልቁ ለማለት የሚዳዳኝ....ሰዎች አሉ። የመነቸከ ሁሉ አይለቅም ማለት እንዳልሆነ ቢገባኝም....የመነቸከው ለማስለቀቅ ያለውን ትግል ሳይ....ያለቦታቸው ተገኝተው ልባቸው ቆሽሾ እንዳይቀር ያሰጋኛል። ያም ሆኖ ግን በእንደነዛ አይነት ሰዎች እቀናለሁ..... ነገሮችን አቅንተው በሚመለከቱ....ሁሉን በበጎ የሚተረጉሙ....ሰዎችን ለመረዳት ለሚቸኩሉ....ሰው ማመን እንደ መታመን ለቀለላቸው......ለመንቀፍ በዘገዩ ደጋግ ሰዎች ..በልበ ቀናዎች እቀናለሁ.....!!!! ✍ነፂ_ነኝ #ነፃሁኑልኝ ✨✨✨ @NetsaAleme
ለካ ሁሉም ናፍቆት እንባ ብቻ አይደሉም ሳቅም አለባቸው። ንፍቅ ስትለኝ አይኔ እንባ አቅሮ ፊቴ ፈገግ አለ። እንባዬ መለያየታችንን አዛዝኖት ነው። ፈገግታዬ ደግሞ ባጣህም ደስታዬ ስለሆንክ ነው። እኔ ባንተ ደስ ብሎኝ እንጂ አዝኜ አላውቅም። ወደ ፊትም አላዝንም። ልባችንን እና ፍቅራችን ግን ያሳዝነኛል። እኔ ያንተ ምስኪን አንተ የኔ ምስኪን ሁለታችን ምስኪኖች ነን ፍቅር ሳይቸግረን ጊዜ ያለያየን ምስኪን.... አብሶ እንዲ ስትናፍቀኝ አይይይ አለመታደል ያስብለኛል። ✍ነፂ_ነኝ #ነፃሁኑልኝ ✨✨✨ @NetsaAleme
ገንዘብ ማግኘት አፈርን በሚስማር እንደመቆፈር.....ገንዘብ ማጥፋት ደግሞ አሸዋ ላይ ውሀ እንደማፍሰስ ነው...!!! ያለው ማን ነበር። ድንቅ አባባል አይደል..?!
ቁልምጫ ነው መልሱላት እስቲ😁
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
Hypopituitarism የሚባለው በሽታ ሰወች ፍቅር የሚባል ነገር እንዳይሰማቸው ያደርጋል. በዚህ በሽታ የተጠቃ ሰው ፍቅር ብሎ ነገር እርሱ ጋር አይሰራም @PyschologyFact @PyschologyFact
видео или голосовое, без подписи
ሀሳቧን ሳትቀይር ሁለት አመታት ተቆጠሪሩ.......የኔ ሁና ያልገባኝ እሷነቷ ትዝታዋ እንደተራራ እየገዘፈ እንደ ደመና እየተንሳፈፈ ፀፀት ውስጥ ውስጤን ሲበላኝ ድፍን ሁለት አመት ሞላኝ። እንዲ አልነበረችም ትወደኝ ነበር መውደዷ በልቧ የኖረ ብቻ ሳይሆን ነፍስ ዘርቶ እንደሚራመድ ፍጡር የሚዳሰስ የሚታይ የሚኖር አይነት ነበር። በሶስት አመት የፍቅር ግንኙነታችን ውስጥ ስለኔ ይደክማታል ብዬ አስቤ አላውቅም። የኔ ነህ ከማለት በላይ እኔነህ የሚያስብል ፍቅር ለኔ ነበራት። እኔ ግን የእሷ ብቻ መሆን ከበደኝ ይሄንን ስታውቅ የኔ ብቻ ካልሆንክ አካሌም አይደለህም አይነት ፊት አሳየችኝ። ከልቧ አልፎ እንደ ህፃን ልጅ የሚፍለቀለቀው የፍቅሯ መልክ ቀስ በቀስ ደበዘዘ .... ልጃችን ፍቅራችን ነበር....የሳመምኩትም እኔ ነኝ። መድሀኒት ፍለጋ ተሯሩጣም ነበር....የእሷን ቃል ባልሰማ በማከብራቸውና በምታከብራቸው ሰዎች አስጠየቀችኝ.....ምክር ያልሰማን መከራ እንደሚመክረው ስላላወኩ ስመከር አልሰማም አልኩ። ደከማት....ፊቷ ላይ የሀዘን ድባብ ያንዣብባል....አይዞሽ አላልኳትም .....የት ዋል የት አደርክ ማለት አቆመች። ልትጠላኝ እንደሆነ አላወኩም ነበር። ልጃችን ፍቅራችን ነው....!!! ሳቁ ጠፍቷል ምግብ ከበላ ሰነባብቷል....ታሞ አተነፋፈሱ አንጀት ይበላል....የአቅሜን ለፍቼልሀለሁ ከእንግዲ ምን ላድርግ ይመስላል አኳኋኗ መድሀኒት ፍለጋውን ትታዋለች። ያኔ ከእንቅልፉ እኔደሚባንን ሰው ባነንኩ....መድሀኒት ፍለጋ ሮጥኩ ስለበደሌ ብዛት በእንባ ተማፀንኳት....ፍቅራችንን ያረገዘው ልቧ ፍቅሬን መልሶ አያዝገባም በሀዘን ተኮማትሯል። ያስለቀስኮቸው አይኖቿን ለእንባዬ መራራት አልሆን አላቸው። ፍቅራችን ልጃችን ነው። ፍቅራችን ሞተ....ብዙ ስለሆነችለት በመሞቱ ብታዝንም አልተጎዳችም የአልጋ ቁራኛ ሁኖ ብዙ ተሰቃየ እንኳን እንደሚሉት አይነት ነው ስሜቷ....ፍቅራችንን አስታማ ቀብራዋለች። እኔ ግን አላስታመምኩት መታመሙንም አላየሁትም የመታመሙ ምክንያት መሆኔ ፀፀቴን አከፋው። ያን ሁሉ ቀን ሳልደርስለት መሞቱ ድንገተኛ መርዶ ሆነብኝ። ልቤ ውስጥ ያልሞተው ፍቅር ስትቀብረው ሳይ ውስጤ ከመጨስ በላይ አረረ ጠቆረ ከሰለ....ግን ረፍዷል። መውጫ መግቢያዋን ሰለልኳት ከድታኝ ነው ሌላ ፍቅረኛ አላት እኔ ብቻ አይደለሁም ከዳተኛ ልለው ለራሴ.....ግን አሁንም ብቻዋን ናት። የኔ ታማኝ የኔ ንፁህ....ታማኝነቷ ከሀዲነቴን ከሰሰው....ንፁህነቷ መቆሸሼን ፊቴ አሰጣው። ከእኔ ጋር ከመሆን ብቸኝነት ተሻላት ባዶ ቤት ሰላም ሰጣት....ከወናነት ማነሴ አንገት አስደፋኝ። ይቅርታ አልላት ነገር ይቅር ብዬሀለሁ ብላኛለች። ግን አብራኝ አደለችም። እሷ ብቻዋን ናት እኔ ....ከፀፀት ጋር....!!! ✍ነፂ_ነኝ #ነፃሁኑልኝ ✨✨✨ ስጨርሱ❤Like አትርሱ😉 @NetsaAleme
видео или голосовое, без подписи