Semera customs branch office - የሠመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
Статистика- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 21
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 222
- 1/48двое суток
- 254
- 1/72трое суток
- 274
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል ችግኞችን ተከሉ ሰመራ (ነሐሴ 7 ቀን 2018 ዓ.ም) የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አመራሮችና ሠራተኞች የሀገሪቱን የአካባቢ ጥበቃ እና የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ በመደገፍ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ከ1,000 በላይ ችግኞችን ተክለዋል ። በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በተካሄደው በዚህ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ላይ የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና በርካታ ሠራተኞች የተሳተፉ ሲሆን፤ በዋናነት በሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ እና በኢባትሎአድ (ደረቅ ወደብ) ግቢ ውስጥ አረንጓዴ ዐሻራቸውን አሳርፈዋል። መርሃ-ግብሩ የአካባቢውን የስነ-ምህዳር ሚዛን ለመጠበቅ፣ በረሃማነትን ለመከላከል እና ለነገዋ ኢትዮጵያ ዘላቂ ተስፋን ለመገንባት ያለመ መሆኑ ተገልጿል ። በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ገዳና ፀጋዬ እንደገለጹት፤ መርሃ-ግብሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ የቀረበውን አረንጓዴ ጥሪ መነሻ በማድረግ የተዘጋጀ ነው ። “እንደ ሀገር የቀረበውን የጥሪ ጥያቄ በመቀበል፣ እኛም እንደ ሰመራ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሀገራዊ ኃላፊነታችንን ለመወጣትና ዘላቂ አሻራችንን ማስቀመጥ ስላለብን በዛሬው ዕለት በሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክና በደረቅ ወደብ ግቢ ተገኝተን ችግኞችን ተክለናል”አቶ ገዳና ፀጋዬ (የሰመራ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ) ዋና ሥራ አስኪያጁ አክለውም የዛሬው የችግኝ ተከላ የመስክ እንቅስቃሴ ሁለተኛው ምዕራፍ መሆኑን ጠቁመው፣ በቀጣይም በቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ሥር በሚገኙ ሌሎች ቁልፍ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ ተከላው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል ። በዚህም መሠረት በሰርዶ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ እና በሚሌ መቆጣጠሪያ ተመሳሳይ መርሃ-ግብር በመተግበር፣ በአጠቃላይ በሁሉም ጣቢያዎች 1,100 ( አንድ ሺህ አንድ መቶ ችግኞችን ለመተከልና ለመንከባከብ እቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል ። በዕለቱ የተሳተፉት የጽሕፈት ቤቱ ሠራተኞች በበኩላቸው፤ ተክለው ከማሳደግ ባለፈ ለተተከሉት ችግኞች አስፈላጊውን እንክብካቤ በማድረግ የነገዋ ኢትዮጵያን ለምለምና አረንጓዴ የማድረግ ሒደት ውስጥ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣታቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል ። የሠመራ ጉምሩክን የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- በፌስቡክ https://tinyurl.com/semcustoms በቴሌግራም https://t.me/semeracustomsoffice "ተቋምን በልህቀት ፣ ገቢን በስኬት"! በደንበኞች ትምህርት ቡድን የተዘጋጀ ፎቶግራፈር ፦ ሳሙኤል ነሃሴ 07/ 2018 ዓ/ም
без подписи
без подписи
без подписи