tgindex
S

Success with Natnael (ስኬት ከናቲ ጋር)

Статистика
@successJorneyанглийский

🚀 እንኳን ወደ ስኬት ጉዞ በሰላም መጡ! በዚህ ቻናል፦ 💡 የአስተሳሰብ ለውጥ 💰 የፋይናንስ ነፃነት 📱 ስልክን ለገቢ ምንጭነት መጠቀም የምንማርበትና አብረን የምናድግበት መድረክ ነው። "ስኬት ምርጫ ነው፤ ዛሬውኑ ይምረጡ!" 🦁💎 ለበለጠ መረጃና ምዝገባ፦ 👇 👇 📩 @Natisucces 📞 09-55-70-06-58

Последний пост
26 июл.
Последнее чтение
ещё не заходили
Постов за неделю
0
Всего постов
19
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
188
−1 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
115
19 постов
Вовлечённость
61,2%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 19
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
37
1/48двое суток
42
1/72трое суток
45

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • እድልን መጠበቅ ወይስ እድልን መፍጠር?" 🤔🔥 ብዙዎቻችን አዲስ ነገር ለመጀመር "ትክክለኛው ጊዜ" እስኪመጣ እንጠብቃለን። ነገር ግን ስኬታማ ሰዎች ጊዜውን አይጠብቁም—ያላቸውን ይዘው አሁኑኑ ይጀምራሉ። እንኳን ወደ Success with Natnael በሰላም መጣችሁ! 🚀 በዚህ ቻናል ላይ፦ 🔹 የፋይናንስና የቢዝነስ አስተሳሰብ (Mindset) 🔹 ከትምህርትና ከስራ ጎን ለጎን ተጨማሪ ገቢ የመፍጠሪያ መንገዶች 🔹 የልማድና የግል እድገት (Personal Development) ምስጢሮችን አብረን እንማራለን። 💡 ዛሬ የምትወስናት አንዲት ትንሽ ውሳኔ የነገ ህይወትህን ልትቀይር ትችላለች! 👇 ወዳጆቻችሁ እንዲማሩበት ቻናሉን ሼር አድርጉ፦ 🔗 @successJorney

  • без подписи

  • #የለውጥ_አስፈላጊነት 📌 #ካልተቀየርክ_ትጠፋለህ! ✈️ ዓለማችን በከፍተኛ ፍጥነት እየተቀየረች ነው። የድሮው አሰራርና የድሮው እውቀት ዛሬ ባለው የዲጂታል ዘመን ዋጋ እያጣ ነው። ከዘመኑ ጋር እራስህን ካላደስክና አዳዲስ የቴክኖሎጂና የቢዝነስ ክህሎቶችን ካልለመድክ የትም ልትደርስ አትችልም። ለመማር ፍቃደኛ ሁን። ⚠️ ለውጥን አለመቀበል (ለመቀየር መፍራት) የሚያስከትለው አደገኛ ጉዳት፡ 1. ቀስ በቀስ መሞትና መሰረዝ (Obsolescence)፦ የኖኪያ (Nokia) ወይም የኮዳክ (Kodak) ኩባንያዎችን ታሪክ አስታውስ። ከዘመኑ ጋር አብረው ለመቀየር ባለመፈለጋቸው ብቻ ከገበያ ጠፉ። አንተም ካልተቀየርክ፣ የዛሬው እውቀትህ ነገ ሙሉ በሙሉ ዋጋ ቢስ ይሆናል። 2. በትንሹ መርካትና መቅረት፦ አለም ወደፊት እየገሰገሰች ስትሄድ አንተ ባለህበት ከቆምክ፣ ወደኋላ እየቀረህ ነው። ለውጥን መቃወም ማለት ካለህበት የኑሮ ደረጃ፣ የገቢ መጠንና የዕድገት ጣሪያ መቼም እንዳትሻገር እራስህን መቆለፍ ማለት ነው። 3. በቴክኖሎጂና በስርአት መበለጥ፦ ዛሬ ላይ ነገሮችን በዲጂታል መንገድና በሲስተም መምራት ያልቻለ ቢዝነስም ሆነ ግለሰብ፣ በዘመናዊ እውቀት በታጠቁ አዳዲስ መሪዎች መበለጡና መተካቱ የማይቀር ሀቅ ነው። 🚀 ለውጥን በደስታ መቀበል የሚሰጠው ታላቅ ስጦታ፡ አዳዲስ ዕድሎችና የገቢ በሮች መከፈት፦ ለውጥን ስትቀበልና አዳዲስ ክህሎቶችን ስትማር፣ ከዚህ በፊት አይተሃቸው የማታውቃቸው የዕድገትና የስኬት በሮች ይከፈቱልሃል። የማይበገር ስብዕና (Adaptability) መገንባት፦ ማንኛውም ማዕበልና የኢኮኖሚ መዋዠቅ የማይጥለው፣ ከሁኔታዎች ጋር በፍጥነት የሚለዋወጥ "የውስጥ ምህንድስና" እና ጠንካራ ማንነት ይኖርሃል። የመሪነትና የመባዛት አቅም፦ እራስህን ስትቀይርና ስታሳድግ፣ በዙሪያህ ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የመለወጥ፣ የመምራትና ታሪክ የማስቀመጥ ተፅዕኖህ ይጨምራል። "ለውጥ ሁልጊዜም ህመም አለው፤ ነገር ግን በማይመችህ ቦታ ተጣብቆ ከመቅረት የሚመጣውን ያህል ህመም የለውም!" 🎯 የእውነት ለመቀየር፣ ለማደግና የዘመኑን የቢዝነስና የቴክኖሎጂ ጥበብ ለመቆጣጠር ዝግጁ ነህ? 👇 አሁኑኑ በኮሜንት መስጫው ላይ "#ለውጥ" ብለህ ጻፍ! እራስህን ለመቀየር የመጀመሪያውን እርምጃ የወሰድክ ሰዎችን ብቻ የምናገኝበትን ልዩ መንገድ እናሳይሃለን። #Change #Innovation #Adaptability #Mindset #Growth #Leadership@successJorney

  • ፍርሃትህን መጋፈጥ!!! ውድቀቶቻችን ከሚያስከትሉብን ኋላ ቀርነት ይልቅ ፍርሃታችን የሚያስከትልብን ይብሳል፡፡ ስለዚህ፣ ፍርሃትን አስቡበት፣ መንገድ ፈልጉለትና አሸንፉት እንጂ ውድቀትን አትፍሩት፡፡ ፍርሃት ከውድቀት በበለጠ ሁኔታ  ለስኬት ትልቅ እንቅፋት ነው። ውድቀት ስኬትን ለጊዜው ሊያዘገይ ቢችልም፣ ፍርሃት ግን አንድ ሰው ከመጀመሩ በፊት እንዲቆም ያደርገዋል። በዚህም ምክንያት፣ ብዙ ህልሞች እውን ሳይሆኑ ይቀራሉ፤ ይህ የሆነው ሰዎች ስላልቻሉ ሳይሆን፣ የመጀመሪያውን እርምጃ እንኳን ለመውሰድ ስለፈሩ ነው። ውድቀት የእድገት መደበኛ አካል ነው። ውድቀት ጠቃሚ ትምህርቶችን ያስተምራል፣ ጥንካሬን ይገነባል፣ እና ብዙውን ጊዜ ወደ ተሻለ ስኬት ያመራል። ፍርሃት ግን ሰዎችን ማመንታት፣ ጥርጣሬ እና እንቅስቃሴ አልባ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እንዲታሰሩ ያደርጋል። ፍርሃት ለምን አደገኛ ነው? ፍርሃት ብዙ ጊዜ እንደነዚህ ያሉ ሀሳቦችን በውስጣችን ያሰርጻል፦ ❓ "ብወድቅስ?" ❓"በቂ ችሎታ ባይኖረኝስ?" ❓ "ሰዎች ቢስቁብኝስ?" ❓ "በቂ ልምድ ባይኖረኝስ?" ❓"አደጋ ቢደርስብኝስ?" ❓ "ሌላ ሰው የተሻለ ሰው ቢኖርስ?" ሰዎች እነዚህን የፍርሃት ሀሳቦች ሲያምኑ፦ 🚫 የሚፈልጉት ስራ እያለ ፈጽሞ አያመለክልቱም። 🚫 ያሰቡትን የንግድ ስራ ፈጽሞ አይጀምሩም። 🚫 ሃሳባቸውን ፈጽሞ አያጋሩም። 🚫 ስጦታቸውንና ችሎታቸውን ፈጽሞ አያዳብሩም። በተጠቀሱት ሁኔታዎች ሁሉ ህልማቸው እንዲሞት ያደረገው ውድቀቱ ሳይሆን፣ የፈጠረባቸው ፍርሃት ነው። ፍርሃታችሁን በጥንቃቄ፣ በጥበብና በድፍረት ተጋፈጡት! LIKE & SHARE ! https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

  • без подписи

  • ''ብዙ ሰው ትላንቱን ይሄ ነበርኩ ብሎ ለማካፈል ይፈራል ፡፡ እውነት ነው ከትላንት ማንነትህ ዛሬ ከፍ ማለት ካልቻልክ "ትላንትእና ዛሬ " ምትለው  ህይወት ስለማይኖር እውነት ነው ያስፈራል'' ፡፡....ናትናኤል መሰረት

  • Please subscribe my YouTube channel👇 https://www.youtube.com/@AsharazeOrthodox

  • ርዕስ፦ "ከወር ደመወዝ ተከፋይነት ወደ የራስ ስራ ባለቤትነት - የለውጥ ጉዞ!" "በአሁኑ ሰዓት አለማችን ላይ ያለው ትልቁ ፈተና የኑሮ ውድነት ሳይሆን የገቢ ምንጭ ማነስ ነው። ብዙዎቻችን አንድ የገቢ ምንጭ (ደመወዝ) ላይ ብቻ ተንጠልጥለን እንኖራለን። ግን ደመወዝ ማለት ህልምህን ረስተህ የሌሎችን ህልም እንድታሳካ የሚከፈልህ 'ማስታገሻ' መሆኑን ተረድተሃል? የስራ ክብር፦ ዛሬ በትንሽ ነገር ላይ ታማኝ የሆኑ ነገ በትልቅ ነገር ላይ ይሾማሉ። የምትሰራውን ስራ ውደደው፣ ግን በዛ ብቻ አትወሰን። ሁልጊዜ 'እንዴት ተጨማሪ ገቢ ማግኘት እችላለሁ?' ብለህ ራስህን ጠይቅ። ገንዘብ ላንተ እንዲሰራ አድርግ፦ ድሃ ለገንዘብ ይለፋል፤ ሀብታም ግን ገንዘብ እንዲሰራለት ያደርጋል። በትርፍ ሰዓትህ የምትገነባው ትንሽ ቢዝነስ፣ ነገ ሙሉ ነፃነትህን ሊሰጥህ ይችላል። ዲጂታል እድሎችን ተጠቀም፦ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ስልክ ይዞ ድሃ መሆን ምርጫ ነው። ኢንተርኔት የአለምን ገበያ እቤትህ ድረስ አምጥቶታል። ስልክህን ጌጥ ብቻ ሳይሆን የገቢ ምንጭ አድርገው። ያስታውሱ፡- ድህነት ማለት ገንዘብ ማጣት ሳይሆን፣ አማራጭ እና እይታ ማጣት ነው። ዛሬ የምትዘራው ዘር (የምትሰራው ስራ) ነገ የምታጭደውን ፍሬ ይወስነዋል።" https://t.me/successJorney https://www.youtube.com/@AsharazeOrthodox

  • "የአስተሳሰብ እስረኛ መሆን ይብቃህ - ወደ ስኬት የሚወስዱ 5ቱ ወርቃማ መንገዶች!" "ብዙዎቻችን ስኬትን የምናየው ከሩቅ እንደሚታይ ተራራ ነው፤ ግን ስኬት የሚጀምረው ከውስጣችን ነው። ህይወትህን መቀየር ከፈለግክ መጀመሪያ አስተሳሰብህን (Mindset) መቀየር አለብህ። ለዚህ ደግሞ እነዚህን ነጥቦች በጥልቀት አስተውላቸው፦ የምቾት ቀጠናን (Comfort Zone) መስበር፦ ህይወት የምትጀምረው ምቾት ከሚሰጥህ ቦታ ወጣ ስትል ነው። አሁን ባለህበት ሁኔታ ብቻ ረክተህ የምትቀመጥ ከሆነ፣ ከዚህ በፊት ያልደረስክበት ቦታ ለመድረስ አትችልም። አዳዲስ ነገሮችን ለመሞከር አትፍራ፤ ውድቀት ትምህርት እንጂ ፍጻሜ አይደለም። ተከታታይነት እንጂ ፍጥነት አይደለም ዋናው፦ አንድን ዛፍ ለመቁረጥ ሺህ ጊዜ መምታት ሊጠበቅብህ ይችላል። 999ኛው ምት ላይ ብታቆም ዛፉ አይወድቅም። ስኬትም እንዲሁ ነው። በየቀኑ የምታደርጋቸው ትናንሽ ጥረቶች ድምር ውጤት እንጂ የአንድ ቀን ተአምር አይደለም። ከአሉታዊ ሰዎች ራቅ፦ አእምሮህ ልክ እንደ የአትክልት ስፍራ ነው። አረም (አሉታዊ ሃሳብ) ከፈቀድክለት አበባዎችን (ህልሞችህን) ይውጣቸዋል። 'አይቻልም'፣ 'አይሆንም'፣ 'ከባድ ነው' ከሚሉህ ሰዎች ይልቅ 'ለምን አይሆንም?' ብለው ከሚያበረታቱህ ጋር ዋል። የእውቀት ጥም፦ አለም በየሰከንዱ እየተቀየረች ነው። የዛሬ 10 አመት የነበረው እውቀት ዛሬ ላይሰራ ይችላል። አንብብ፣ ጠይቅ፣ ተማር። እውቀት በጨመረ ቁጥር የምታያቸው እድሎች ይበዛሉ። የራስህ ባለቤት መሆን፦ ህይወትህን በሰው እጅ ላይ አታስቀምጥ። መንግስት፣ ቤተሰብ ወይም አሰሪህ ህይወትህን እንዲቀይሩልህ አትጠብቅ። የህይወትህ መሪ (Captain) አንተ ራስህ መሆን አለብህ።" https://t.me/successJorney

  • ይገርመኛል ስልጠና ሠው ይሰራል ስል ይህ ነው ማስረጃዬ!!!! @Natisucces

  • ዛሬ አዲስ ታሪክ ለመጀመር ዝግጁ ናችሁ? "ስኬት በአንድ ጀምበር የሚገኝ ድንገተኛ ዕድል ሳይሆን፣ በየቀኑ በምናደርጋቸው ትናንሽ ጥረቶች የሚገነባ ውጤት ነው። ብዙዎቻችን ትልቅ ቦታ ለመድረስ እናልማለን፤ ነገር ግን ያ ህልም እውን የሚሆነው ዛሬ በምንወስደው እርምጃ ነው። በስልክህ ብቻ፣ ባለህ ትርፍ ሰዓት እና በቁርጠኝነት ለውጥ ማምጣት ትችላለህ። የአለምን ሁኔታ መቀየር ባንችልም፣ የራሳችንን የፋይናንስ ሁኔታ የመቀየር አቅሙ ግን በእጃችን ላይ ነው። መልካም እና ስኬታማ ቀን ይሁንላችሁ! 🚀" ለእናንተ ሰሰኬት ማለት ምን ማለት ነው? ሀሳባችሁን በኮሜንት አጋሩኝ #SuccessWithNatnael #Motivation #DigitalMarketing #FinancialFreedom #Ethiopia

  • без подписи

  • без подписи

  • 💰 ድህነት ምርጫ ነው ወይስ አጋጣሚ? ብዙዎቻችን "ሀብታም ለመሆን እድለኛ መሆን አለብኝ" ብለን እናምናለን። ነገር ግን እውነታው ከዚህ ይለያል። ሀብት የሚጀምረው ከኪስ ሳይሆን ከአእምሮ ነው! ለአንድ ሰው 100,000 ብር ብትሰጠው፡ ያልተገነባ አእምሮ ያለው ሰው 👉 ወዲያውኑ ልብስና ጌጥ ገዝቶ ይጨርሰዋል። የቢዝነስ አእምሮ ያለው ሰው 👉 ያንን ገንዘብ እንዴት አባዝቶ 1 ሚሊዮን እንደሚያደርገው ያስባል። የዘመኑ ትልቁ ሀብት ምንድነው? በአሁኑ ሰዓት ትልቁ ሀብት "መረጃ" ነው። በአለም ላይ ያሉ ቢሊየነሮች በሙሉ የሚጠቀሙበት ሚስጥር አንድ ነው፦ ሲስተም (System) መገንባት! እርስዎ የትኛው ጋር ነዎት? . ለገንዘብ የሚሮጡ? . ወይስ ገንዘብ ለእርስዎ እንዲሮጥ የሚያደርግ ሲስተም የገነቡ? እኔና የቢዝነስ አጋሮቼ አሁን ላይ ወጣቶች፣ እናቶችና ተማሪዎች በትርፍ ሰዓታቸው በስልካቸው ብቻ በመጠቀም እንዴት የራሳቸውን የገቢ ምንጭ መፍጠር እንደሚችሉ የሚያስተምር ትልቅ ፕሮጀክት ላይ እየሰራን ነው። ይህ ስራ በስልጠና የሚመራና ማንኛውም ሰው ሊሰራው የሚችል ቢዝነስ ነው። ስሙንና ዝርዝር አሰራሩን ግን የምንገልጸው በቁምነገር ስኬትን ለሚሹና ለመለወጥ ለወሰኑ ሰዎች ብቻ ነው። ምን ማድረግ አለብዎት? ለውጥ የሚጀምረው ከመረጃ ነው። አዲስ ነገር ለመማርና ካሉበት የገቢ ደረጃ ከፍ ለማለት ዝግጁ ከሆኑ፡ @Natisucces 📩 በውስጥ መስመር "ለውጥ" ብለው ይላኩልኝ። በዝርዝር እናወራለን። "አለም እየተቀየረች ነው፣ እርስዎስ?" 🦁💎 https://t.me/successJorney

  • ክርስቶስ ተንስአ እሙታን በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን አሠሮ ለሠይጣን አግአዞ ለአዳም ሰላም ሰላም እም ይእዜሰ ፍስሐ ወሰላም "ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ ምድርም ፋሲካን ታደርጋለች በከርስቶስ ደም ስለታጠበች " እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሠላም አደረሳችሁ በዓሉ የፍስሐ የሐሴት የተቸጠሩ ወገኖቻችን የምንረዳበት።፣የታሰሩ እና በሕመም ላይ ያሉ ወገኖች እንዲፈቱ እንዲምራቸው የምንጠይቅበት ከትንሽ ከትልቁ ጋር በደስታ የምናከብርበት በዓል ያድርግልን ። መልካም በዓል ይሁንሎ ከመላ ቤተሰቦ ጋር ናትናኤል ስዩም (ናቡቴ) 2018

  • እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ። እርሱ ስለ እኛ በደል ቆሰለ፤ ስለ እኛም መከራን ተቀበለ። መልካም በዓል ይሁንሎ

  • без подписи

  • ሰኞ - መርገመ በለስ መ/ር ጌታቸው በቀለ ሁለተኛይቱ ዕለት በግእዝ ሰኑይ(ሠኑይ) ስትባል በአማርኛ ደግሞ ሰኞ ትባላለች፡፡ ሰኑይ ሁለተኛ ዕለት ማለት ነው፡፡ “ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሁለት ቀናትም በኋላ ከዚያ ወጥቶ ወደ ገሊላ ሔደ” እንዲል /ዮሐ.፬፥፵፫/፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሠኑይ ሰነየ-አማረ ከሚለው ግሥ የወጣ ሲኾን፤ ሠኑይ ማለት ያማረ ማለት ነው፡፡ ይኽም “እግዚአብሔር የሠራውን ፍጥረት ሁሉ ያማረ እንደ ኾነ አየ” እንዲል፤ ዕለቲቱ ለፍጥረታት ሁለተኛ ቀን ስለኾነች ዕለተ ሰኑይ ስትባል የተፈጠረባትን ፍጥረት መልካምነት ለመግለጥ ደግሞ ዕለተ ሠኑይ ተብላለች /ዘፍ.፩፥፳፩/፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቢታንያ ወደ ኢየሩሳሌም የገባው በዕለተ ሆሣዕና ነው፡፡ ከዚያም ወደ ቤተመቅደስ ሲሔድ፤ ቤተ መቅደሱ የንግድ ቤት ኾኖ አገኘው፡፡ “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት” ብሎ የሚሸጡትን ሁሉ ገለበጠባቸው ገርፎም አስወጣቸው፡፡ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበረው የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታ ችንን ሁሉ እንደ አራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ በማለዳ ከቢታንያ ሲወጡ ተራበ /ማቴ.፳፩፥፲፪-፲፯፤ ማር.፲፩፥፲፩-፲፪፤ ሉቃ.፲፱፥፬-፭/፡፡ ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፡፡ በለስ የተክል እንጨት፤ ከወይን ጋር የሚተከል ቅጠሉ ሰፋፊ ፍሬው የሚበላ አጭር ዛፍ ወይም ቁጥቋጦ ነው፡፡ /ኪዳነ ወልድ ክፍሌ(1948)፡፡ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፡፡ አዲስ አበባ፤ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፡፡ ገጽ 274፡፡/ ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘበትም ከአሁን ጀምሮ ከአንቺ ፍሬ አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፡፡ በለስ በሦስት ነገር ትመሰላለች፡፡ በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፡፡ ከእስራኤል ፍቅርን ሃይማኖትን ፈለገ አላገኘም፡፡ እስራኤል ደጐች ባለመኾናቸው፤ ፍሬ አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፡፡ በለስ ኦሪት ናት፡፡ ኦሪትንም በዚህ ዓለም ስንፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም፣ ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፡፡ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በርሷ ድኅነት አይደረግላትም ፍሬ ባንቺ አይሁን አላት፡፡ በለስ ኃጢአት ናት፡፡ በለስ ቢበሉት ይጣፍጣል፣ ቆይቶ ግን ይመራል፡፡ ኃጢአት ሲሠሩት ለጊዜው ደስ ያሰኛል ኋላ ግን ቆይቶ ይመራል፣ ያሳዝናል፡፡ ወደ እርሷም ሔዶ ማለትም ባንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውን በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፡፡ ፈጥና መድረቋም በአዳም ምክንያት ዕዳ በደል በእርሱ እንዳጠፋልን ለመግለጽ ነው /ትርጓሜ ወንጌል፤ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፩/፡፡ የጌታችን ረኀብ የአንዲት የበለስ ዘለላ ፍሬ ሳይኾን የበለስ ውክልና ከተሰጣቸው ቤተ እስራኤል የሃይማኖትና የመልካም ሥነ ምግባርን ፍሬ የፈለገ መኾኑን ለማጠየቅ ነው፡፡ ጌታችን የፈለገውን ባለማግኘቱ በአይሁድ ጉባኤ የነገሠውን ኃጢአት፣ በበለስ አንጻር መርገሙን ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “በበለስ አንጻር ኃጢአትን ረገማት” ብሏል፡፡ እስራኤልም በአንድ ወገን የተጠበቀባቸውን ፍሬ ባለማፍራታቸው ተረግመዋል፡፡ እንደ ማጠቃለያ ዛሬም ጌታችን ወደ መቅደስ ሕይወታችን ቢመጣ ምን ያገኝ ይሆን? ፍሬ ወይስ ቅጠል? የእግዚአብሔር ቃል ግን ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ ይለናል /ማቴ.፫÷፰/፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ከእኛ የሚፈልገውን የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ እናፍራ /ገላ.፭÷፳፪/፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ የእምነት ፍሬ አፍርተን ከእግዚአብሔር ዘንድ ዘላለማዊ ፍቅሩን ለማትረፍ እንትጋ፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ዋቤ መጻሕፍት ✍️ መጽሐፍ ቅዱስ ✍️ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ ✍️ ጾም፣ጸሎት ምጽዋት ✍️ ከስቅለት እስከ ትንሣኤ

  • без подписи