- Последний пост
- 8 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 144
- 1/48двое суток
- 165
- 1/72трое суток
- 177
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
መውደድን ይዞ በሩቁ ለሄደ ምንስ ማፅናኛ አለው በአይኑ ለወደደ ሀሳቡን ሳያቀርብ መልሱንም ሳይሠማ ምንስ ማፅናኛ አለው ልቡን ለተቀማ ስሜቱ ገዝፎ ስሌት ላቃተው ምንስ ማፅናኛ አለው ለዚህ ምስኪን ሠው ፈራጅ ለበዛበት መውደድን ባመነ ምንስ ነው ፍርዱ ፍቅርን ለለመነ ምን...?እንጃ ብቻ ይጠብቃል ቀኑን የዘመናት ጎርፍ እስኪነጥቀው ህልሙን #eyu_ze_mariam https://t.me/teseo12
የአዳም ብቸኝነት እግዜር ቢይስጨንቀው ሄዋንን ሊፈጥራት እንዲተኛ አዘዘው😴 ሰው ሁሉ ቢመስለው ለአዳም የተሰጠች ሄዋን ናት ባለእድል አዳምን ያገኘች እኔም የሄዋን ዘር 🙍♀አዳሜን የሰጠኝ ከሴቶች መርጦ የሱ ያደረገኝ ቃላት ባልጠቀም ባልችልም ልገልፀው እስቲ በዚ ግጥም ትንሽ ልጀንጅነው🤭 የፍቅር ቃላት ደርድሬ ብነግረው የኔ ውድ የኔ አባት ብዬ ባማልለው💋 ቆይ ምን ብለው ነው ባሌን ማስደስተው?🤔 ከመልክም ባለ መልክ የሆነ ጀንታላ🤌 በአይኖቹ ብቻ ሺዎችን ሚያጣላ💪 ኧረ እኔስ ፈራሁኝ ከኔ እንዳትለየኝ ከሺዎቹ መሀል አንዷ እንዳትወሰድብኝ እኔ ግን የምልህ አላሳዝንህም 🤔በፍቅርህ ምክንያት እንቅልፍ ስታሳጣኝ በል ትንሽ ልንተራስ ትከሻህን ስጠኝ ልክ እንዳስለመድከኝ😁😉 @teseo12
መገንባት እንደ ማፍረስ ቀላል ቢሆን ጥሩ ነበር.... @teseo12
✍️አትፍረድ ቀናት ከሌሊት ጋር ደቂቃን ከሰአት አፈራርቆ የያዘው የህይወቴ ምልአት በ 2 የህይወት ክፍል በብዙ ምዕራፎች በአንድ ሰሞን ደስታ በሌላው ሃዘኖች ደራርበው እየመጡ ህይወቴን ቢያከብዷት ጥርሴን ነጭ በነጭ ደስታን ሞልቼበት መከራዬን ይዜ በውስጤ አምቂያት ምንም እንዳላየ ሰው ስፍለቀለቅ ቢያዩኝ አንቺ ምን አለብሽ ብለው ለምን ተናገሩኝ ጉዳዩን የት አውቀው በምንስ ተረድተው መስካሪው ማን ሆኖ ማስረጃስ ምንድን ነው እነሱ በኔ ላይ ፈራጅ ያረጋቸው ደሞስ ማን ፈቅዶ ነው #nayo @teseo12
.........እኔ ምለው ....... የሄደ ተወቃሽ የጠበቀ ታጋሽ❤️ የሄደማ አጥፊ በዳይ ፍቅርን ገፊ😒 ያስኬደስ ምንድነው?..... ትግስት የሚያሳጣው መቆየት እንዳይችል እንዲሄድ ያደረገው😏 እሱስ ግን ምንድነው?... እእ ምንድነው??? @teseo12
@teseo12
#astawesegne @teseo12
Follow yaregegnal unfollow yaregegnal atarguta channelun ere join asdergu😂 @teseo12
እሷን እየጠበኩ አንቺን እንዳገኘው በፍጽም አትርሺ ያልከኝን ቃል ሰምተው ወዳጅ ዘመዶቼ ይቅርብሽ ቢሉኝም ያፈቀረ እውር ነው በሚል መፈከር ካንተ ጋር ብቆይም ዛሬ ግን አስተዋልኩ ጉዳዩን ተረዳው ጠላሁህ መሰለኝ ጉድፍህን አየው ታድያ ጥያቄዬ ስንት አመት ጠበካት ዘመናት አመታት ወራት ነው ሳምንታትት የገዛሀው አበባ እሷን ለማስደሰት በቀይ ሽፋን ጠቅልለህ የያዝካት ጊዜው ሄዶበት ጠውልጎ አላበቃም መቅራቷን ሳታቀው ቀርታለች ምትለው ትግስት ባይኖርህ ነው ሌላ ምታየው አዎ ባትወዳት ነው እንጂ አመታት አይደለም ትጠብቃት ነበር ዘመናት ቢያልፋትም እንጂ አትመጣም በሚል ውሸት ነበር ባልተካሃት በሌላኛዋ ሴት @teseo12
ደሀ አልወድም ስትይ ስትገፊው ማጣቴን ቁራሌው ቁራሌው አሮጌ ጫማ ያለው ለሚለው ለዛ ሰው ሸጥኩት ቀለበቴን ዋናው ነገር ገንዘብ ብለሺኛልና ይሄው አተረፍኩኝ ቃልሽን ገዛሁት ቃሌን ሸጥኩኝና በችግር የፀናች በእምነት ያለፈች የመውደድ ኪዳኔን ማቆየት ካልቻለች አንድ አንቺን ለጎኔ አይጠቅመኝምና እንደውም እንደውም የሚፈልግ ካለ ሸጠዋለው ልቤን ዛሬ ሰው ሚወደው ወረቀት ገንዘቤን ፍቅር ፍቅር አትበል ኪስህን ሳትሞላ ብለሺኛል አይደል እውነትሽ ገብቶኛል ከዛሬ በኃላ እንደ ዘይት ሽንኩርት ፍቅር እና መዋደድ በኪስ ነው ሚገዛ ልብ ዋጋ ቀንሷል አይበልጥም ካስቤዛ ቆራሌው ቆራሌው አሮጌ ጫማ ያለው አሮጌ ልብ አለኝ ሶሉ ያልተነካ ፍቅሩ ያልተነካ እሱን ውሰድና አሲዘኝ ረብጣ የምወዳትን ልጅ አጥቼ እንዳላጣ እኔማኮ ሳላውቅ እንደ ድሮ መስሎኝ ልቆ ገዝፎ ሚታይ ኪሴን ችላ ብዬ ሰርቼ ነበረ በንፁህ ልቤ ላይ ፀባይ ስነምግባር አስተዋይ ህሊና አይበጅም ከንግዲ አይሸጥምና ተወኝ ህሊናዬ ተወኝ ሰውነቴ ኪሴ ላይ ነው ሀብቴ ባልነት መደብር ሚስትነት መደብር ሱቅ ላይ ተሰቀለ ትዳር ከላይ ቀርቶ በእጅ ተሸቀለ ወይኔ እናቱን ኑሮ ወይኔ እኔ ዘመኔ ሰውነቴ አልረባም ብረት ብለቃቅም ይሻለኛል እኔ ቆራሌው ቆራሌው አሮጌ ጫማ የሌው አሮጌ ልብ አለኝ ፍቅሩ ያልተነካ እሱን ውሰድና አሲዘኝ ረብጣ የምወዳትን ልጅ አጥቼ እንዳላጣ @teseo12
..ዳግም ተመልሼ እስከምበድልህ በል ቁጥር ንገረኝ ስንት ልስገድልህ? ትላንት ሀሙስ ለታ ልቤን የቀደደ መገለጥ ተሰማኝ፣ አስገደፈችልህ /በጧሚ አፏ ስማኝ/ አወይ ባትጀምረኝ ወይ መሳሟን ባትተው ፣ ከርቤ ከርቤ አለችኝ ከንፈሯን ብትከፍተው! መብረቅ ዳብሳለች ወይ እስከማርያም ጣቷ? አንዘረዘረችኝ አቤት ሀጢያቴ_አቤት ሃጢያቷ! /ሳመችኝ ነው ምልህ/ ምላሷን አውጥታ ጥርሴን አነጣችው ባፍንጫዬ ዘልቃ ጀሮዬን ሳመችው እስቲ ምናለበት ጉሮሮዬን አልፋ ውስጤ ብትቀበር፤ ድምፄን ያመኝ ነበር? ልቤን ያመኝ ነበር? ይመመኝ ይመመኝ ተስፋ ቆርጦ ይሂድ አስታማሚ ደክሞት /ፍታት አይቀርብኝ/ እንኳን በሷ ምላስ_ወባ ነድፋኝ ብሞት። በል ቁጥር ንገረኝ ስንት ልስገድልህ ዳግም ተመልሼ እስከምበድልህ ከተናደድኽብኝ መሰንዘር ከወድድኽ እጅህን ለበቀል ሀዘንህ ጎርፍ ይሁን ቁጣህ ሁሉን ይንቀል እንባችን ወንዝ ይሙላ ባይነት በግፍ በግፍ በልምጭ ካቃትንህ ከሰማይ ቀስት አርግፍ ሰው ምርጫው ካረገ ስሜትና ሆዱን ክፍትፍቱን ክደን የመዳን መንገዱን አጥፋው ሁሉን ፍጡር ጨለማን አታንጋው፤ ዋ ብቻ አደራህን /ከንፈሯን/ አትዝጋው:: ዳግም ተመልሼ እስከምበድልህ ...........ስንት ልስገድልህ! @teseo12
አዎን እቀናለው ያልቀኑበት ነገር ሲነጠቅ ስላየው ይኸውልሽ ጉዴ ከከንፈርሽ በታች ባለው ጥቁር ነጥብ ስቀና ያየሺኝ እንደማላቅ ነገር ማርያም ስማኝ አልሺኝ ለምን…? ለምን አንቺን መረጣ? ለምን ከንፈርሽ ጋር? ለምን ለምን ለምን… ለምን እያልኩኝ ስል ብዬ ደፋ ቀና አትፍረጂ ፍቅሬ… አፍቃሪ አይመርጥም በፍቅሩ ሲቀና እኔ ምን አውቃለው ብቻ እወድሻለው ብቻ አፈቅርሻለው !! @teseo12
በአለም 🌎መዛግብት ስሙ ያላኖረ አንዱ ጀግና ነበር አለምን ያኖረ ቆይ እኔ ምለው እንዴት እረሳችው?🤔 እንዴት ዘነጋችው? እንዴትስ ተወችው? በአለም መዛግብት ቢኖሩም ሺ ጀግኖች ቆይ ለሱ የሚሆን ትንሽ🤏 ቦታ አጣች? ጎራዴ ባይጨብጥ ሰይፍን ⚔ ባያወጣ ሀገርን ለማልማት ከሀገር ባይወጣ ለልጆቹ ሲባል ሆኗል መላጣ 👴 አለም ነይ ስትለኝ ፈጣሪም ሲፈጥረኝ አልደላኝም ነበር አባቴን እስካገኝ አዎ ምድሪቱ ባታቀው አባቴ ነው ጀግና አለሜን ያዳነው ከአባትም ምርጥ አባት ከስንት አንዴ ሚገኝ ከስጣታዎች🎁 መሀል ለኔ የተሰጠኝ አባቴ ጀግና ነው በሀገር ያልታወቀ ለልጃቹ ሲል ሺ ችግር ያወቀ ቢከፍውም እንካን ህይወት ብትከብደው እኛን አስደስቶ በኛ ደስታ ነበር ከቶ ሚደሰተው🥹 እና ጌታዬ ሆይ ለዚህ ለብርቱ ሰው 👨🦰 አንዱ ፀሎት🧎 አለኝ ላንተ የማደርሰው እንዳይቀድመኝ ሄዶ ጊዜው ይሄ ሁሉ ለፍቶ ገደል እንዳከተው የልፋቱን ፍሬ ለአባቴ ላሳየው😇 @teseo12
መተው የነበረብንን ነገሮች በጊዜው ባለመተዋችን ነው አሁን ላይ ዋጋ የምንከፍለው !!
“ ትላንት ላይ ሆነን ዛሬ ጸሎታችን ነበር። ዛሬ ላይ ሆነን ስለ ነገ እንፀልያለን እንጨነቃለን ነገር ግን ሁሌም አንድ ነገር አለ ትላንት ያለፈው ዛሬ ያለው ነገ የሚኖረው የሚሆነው ሁሉ በእርሱ ነውና አንድ ጊዜ አብረን 👉 ተመስገን 👈 እንበለው🙏 “ @teseo12
የአለምን ፍቅር ፈጣሪ ሲለካው ለእናት ልብ የሚሆን ስንት ሜትር በቃው? ለልጆቿ ፍቅር ሰስታ አታውቅም ልክ እንደ ሴቶቹ መኳኳል ቢያምራትም ልጆቻን ሳቷሱብ ከቶ አዘንጥም አትዩት ማድያቷን አትዩት መክሳቷን አትዩት መውዳቋን አትዩት ማልቀሷን ብርታቷን እዩላት ለልጆቿ ስትል አለምን መያዟን የእሷን ህይወት ትታ ለልጆቿ የኖረች ሌላ ሴት የለችም እናት ብቻ እኮ ናች 9 ወር መያዟን እንዴት ዘነጋነው? ውበቷ መርገፉን እንደ ቀልድ አለፍነው? ታዲያ ለዚች እናት አምላክ ለፈጥራት ለደስታዋ እንዲሆን ምን ነገር ሰጠናት? ደስታዋ ድብቅ ነው ፍጽም ውስብስብ አንዴ ፈገግ ስትል ልብን የሚስብ በል ጎበዝ ተነሳ ጊዜው ሳይፈርድ ገና እናትን ለማስደሰት ጊዜ አለ እና መልካም የእናቶች ቀን!!! @teseo12
በአለም 🌎መዛግብት ስሙ ያላኖረ አንዱ ጀግና ነበር አለምን ያኖረ ቆይ እኔ ምለው እንዴት እረሳችው?🤔 እንዴት ዘነጋችው? እንዴትስ ተወችው? በአለም መዛግብት ቢኖሩም ሺ ጀግኖች ቆይ ለሱ የሚሆን ትንሽ🤏 ቦታ አጣች? ጎራዴ ባይጨብጥ ሰይፍን ⚔ ባያወጣ ሀገርን ለማልማት ከሀገር ባይወጣ ለልጆቹ ሲባል ሆኗል መላጣ 👴 አለም ነይ ስትለኝ ፈጣሪም ሲፈጥረኝ አልደላኝም ነበር አባቴን እስካገኝ አዎ ምድሪቱ ባታቀው አባቴ ነው ጀግና አለሜን ያዳነው ከአባትም ምርጥ አባት ከስንት አንዴ ሚገኝ ከስጣታዎች🎁 መሀል ለኔ የተሰጠኝ አባቴ ጀግና ነው በሀገር ያልታወቀ ለልጃቹ ሲል ሺ ችግር ያወቀ ቢከፍውም እንካን ህይወት ብትከብደው እኛን አስደስቶ በኛ ደስታ ነበር ከቶ ሚደሰተው🥹 እና ጌታዬ ሆይ ለዚህ ለብርቱ ሰው 👨🦰 አንዱ ፀሎት🧎 አለኝ ላንተ የማደርሰው እንዳይቀድመኝ ሄዶ ጊዜው ይሄ ሁሉ ለፍቶ ገደል እንዳከተው የልፋቱን ፍሬ ለአባቴ ላሳየው😇 @teseo12
🌟 Exciting Tutoring Opportunity! 🌟 Are you passionate about education and looking for a part-time job? Join us in shaping the future of Ethiopia! We are seeking enthusiastic individuals who want to make a difference through tutoring. Whether you're a student, a professional, or someone with a passion for teaching, we welcome you to be part of our team! 📚 Why Join Us? • Flexible hours to fit your schedule • Opportunity to inspire and empower students • Contribute to the educational development of Ethiopia If you're interested in making a positive impact and building a brighter future, we want to hear from you! 👉 Contact us at @emahus_32 to learn more and apply! Let’s work together to create a better tomorrow! 🌍✨
እንኳን ደስ አላችሁ፣ ከ Emahus Tutor ጋር ልጆቻችሁንወደስኬት እናምጣ እያልን ከ KG እስከ Grade 12 ድረስ አስጠኚ ለምፈልጉ? በትምህርት ላይ ልጆቻችሁን ስኬታማ ለማድረግ የሚችሉ እና ሙያ ያላችው አስጠኚዎች ዝግጁ ናቸው። 📞 ለመገናኘት በፍጥነት ይደውሉ፦ 0957329588 0981555648 እኛ በተቻለን ፍጥነት እናገናኛችሁ። በልጆቻችሁ ትምህርት ጉዞ ላይ የሚያግዝ እና የሚያበረታታ አስጠኚ ማግኘት ከዚህ በላይ ቀላል አይሆንም። ልጆቻችሁ በትምህርት ዘርፍ እንዲያድጉ እና ስኬታማ እንዲሆኑ ከእኛ ጋር ተቀላቀሉ።
🚀 Join the emahus Tutor Network We are building the most reliable tutoring marketplace in Ethiopia, and we want YOU to be part of it. We bridge the gap between talented educators and parents seeking quality education. 📋 Requirements: Current University Student or Graduate. Strong communication skills. Deep knowledge in your specific subject area. Punctuality and professional conduct. 📍 Locations: All areas of Addis Ababa (Bole, CMC, Old Airport, Sarbet, Lebu, etc.) 🔗 Registration Link: https://forms.gle/7A88xzNG2ESWd9Vm7 Help us shape the future of Ethiopian students. Register today! @emahus_32