tgindex
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን

Статистика

"በተማርከው እና በተረዳኸው ነገር ፀንተ ኑር"

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
5
Всего постов
164
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 958
−7 за 5 дн.
Сутки
−1
−0,05%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
27
40 постов
Вовлечённость
1,4%
к подписчикам
Постов в день
0,7
всего 164
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
15
1/48двое суток
17
1/72трое суток
18

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • 05/12/2018            ሉቃስ 15:1-11 ቀራጮችና ኀጢኣተኞችም ሊሰሙት ወደ እርሱ ይቀርቡ ነበር። ጻፎችና ፈሪሳውያንም፥ “ይህስ ኀጢኣተኞችን ይቀበላል፤ አብሮአቸውም ይበላል” ብለው አንጐራጐሩ። 'እንዲህም ብሎ መሰለላቸው። “ከእናንተ መካከል መቶ በጎች ያሉት ሰው ቢኖር፥ ከእነርሱ አንዲቱ ብትጠፋው ዘጠና ዘጠኙን በምድረ በዳ ትቶ እስኪ ያገኛት ድረስ ይፈልጋት ዘንድ ወደ ጠፋችው ይሄድ የለምን? በአገኛትም ጊዜ ደስ ብሎት በትከሻው ላይ ይሸከማታል። ወደ ቤቱም በገባ ጊዜ፥ ወዳጆቹንና ጎረቤቶቹን ጠርቶ፦ የጠፋችኝን በጌን አግኝቼአታለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ይላቸዋል። እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሓ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኙ ጻድቃን ይልቅ ንስሓ ስለሚገባ ስለ አንድ ኀጢኣተኛ በሰማያት ፍጹም ደስታ ይሆናል። "ዐሥር ድሪም ያላት ሴት ብትኖር፥ አንዲቱ ብትጠፋባት መብራት አብርታ በቤቷ ያለውን ሁሉ እየፈነቀለች እስክታገኛት ድረስ ተግታ ትፈልግ የለምን? 'ያገኘቻት እንደሆነ ወዳጆችዋንና ጎረቤቶችዋን ጠርታ የጠፋችብኝን ድሪሜን አግኝቼአታለሁና፥ ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ትላቸዋለች። እላችኋለሁ፣ እንዲሁ ንስሓ ስለሚገባ ስለ አንድ ኀጢኣተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት በሰማያት፥ ደስታ ይሆናል........ 2 ቆሮንጦስ 12:10-17 1 ዮሐንስ 5:14-ፍጻሜ ሐዋ.ሥራ 15:1-13 👉ቅዳሴ ዘእግዝእትነ አው ግሩም ምስባክ          መዝሙር ፲፯ :፵፫ – ፵፬ ወትሠይመኒ ውስተ ርእሰ ሕዝብ ሕዝብ ዘኢየአምር ተቀንየ ሊተ ውስተ ምስማዐ ዕዝን ተሠጥዉኒ ትርጉም የአሕዛብም ራስ አድርገህ ትሾመኛለህ የማላቀው ሕዝብም ይገዛልኛል በጆሮ ሰምተው ተገዙልኝ https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780

  • #ኢየሱስ #ክርስቶስ " ... የጥበብ ነገር የምክርም ቃል የረድኤት መዝገብ የደስታ መኖሪያ ። የጥቅም መገኛ የጥበብ ምንጭ  ደገኛ ፈሳሽ ። በሐዋርያት የተመሰገንህ የክብር ጉድጓድ የመንግስት ጌጥ። የካህናት ንጹሕ ዘውድ  ዘውዱ የተመሰገነ ንጉሥ የሚሰግዱለት የምስጋና መገኛ የክብር ብርሃን ። ያልተሰራ ልብስ ያልተፈተለ ቀሚስ ወደ አባቱ ለመድረስ ጎዳና ወደ ወለደው ለመግባት የሚሆን በር ። የተገለፀ ወርቅና የተገኘ እንቁ ነው ። የበዛ ምናን ። እጽፍ ድርብ የሆነ መክሊት ። ዱቄትን የቻለው እርሾ አልጫ የሆነውን ያጣፈጠ ጨው ። ጨለማን ያሳደደው ብርሃን ዓለምን ሁሉ ያበራው ፋና የማይነዋወጥ መሠረትና የማይፈርስ ግንብ ። የማይሰበር መርከብና የማይሰረቅ ማህደር  ። ያማረ ቀንበርና የቀለለ ሸክም እርሱ ለአባቱ ኃይሉ ጥበቡም የሚሆን #ኢየሱስ #ክርስቶስ  ነው ። " ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ፵፩ - ፵፭ https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780

  • • ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሰንበተ ክርስቲያን "…ሰንበተ ክርስቲያን አለ ሰንበተ አይሁድ አለችና ኪዚያ ሲለይ ነው። ያውስ ቢሆን እንዲያው በከንቱ ነውን? ሁለቱን በዓላት ቅዳሜና እሑድን የሚያከብር አንድ ክርስቲያን በሌላ ኃጢአት ተይዞ ወደ ሲኦል የገባ እንደሆነ አርብ በሠርክ ወደ ገነት ይወጣል፤ ሰኞ በነግህ ወደ ሲኦል ይወርዳል። አንዱን በዓል ዕለተ እሑድን የሚያከብር የሆነ እንደሆነ ግን ቅዳሜ በሠርክ ይወጣል ሰኞ በነግህ ይወርዳል። እንዲህ እያለ እስከ ዕለተ ምጽአት ይኖራል። እግዚአብሔርም ሰማይና ምድርን ለማሳለፍ የሚመጣው በዕለተ እሑድ ነውና በዚያው እንደወጣ ይቀራል። እስመ በዛቲ ዕለት ተፈጸመ ፍሥሓሃ ለቤተክርስቲያን በአማን ተፈጸመ እንዲል። • • • "…ክርክር በሰኞ ተፈጽሟልና "ባርክኒ" ይላታል እርሷም በረከተ ወልድየ ወአቡሁ መንፈስ ቅዱስ ይኅድር ትለዋለች። እርሱም ተባርኮ ምስጋናዋን ይጀምራል። ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በአፍኣ ባሉ ንዋያት እየመሰለ ሲያመሰግናት ሰንብቶ ነበር። በዕለተ እሑድ ግን በቤተ መቅደሱ ውስጥ ባሉት ንዋያተ ቅድሳት በመሶበ ወርቅ፣ በተቅዋመ ወርቅ፣ በማዕጠንተ ወርቅ እና በበትረ አሮን እየመሰለ ያመሰግናታል። "…ውዳሴ ዘሰንበተ ክርስቲያን፤ ውዳሴ በሰንበተ ክርስቲያን "ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሰንበተ ክርስቲያን ቅድስት" ቢል አንድ ነው፣ ቃለ ጸሓፊ ነው። እርሱ ግን ነገሩን "ተሰመይኪ ፍቅርተ ብሎ ያመጣዋል። ቅድስት አለ ከሰባቱ ዕለታት ለይቶ አክብሯታልና። https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780

  • ❤ ውድ የቴሌግራሜ ቻናል ተከታታዮች ተወዳጅ ቤተቦቼ እንዴት ሰነበታችሁ ቸር አላችሁ ኔትወርክ ወደ ማይሠራቦት ቦታ ወጣ ስላልኩ # ያለው ቀድሜ Post አድጌዋለሁ ወደኋላ እያላችሁ የየቀኑን ተመልከቱ  አምላከ ቅዱሳን ልዑል እግዚአብሔር ጾሙን በሰላም አስጀምሮ በሰላም አስጨርሶ ለእናታችን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለብርሃነ ትንሣኤዋና ዕረገቷ ያድርሰን። ለሁላችንም የበረከት ጾምና መልካም ሱባኤ ይሁንልን።                  https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780

  • ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች እንኳን ለዚህ የተባረከ የጾምና የጸሎት ወቅት በሰላም አደረሳችሁ። ይህ ጾም ነፍሳችንን የምናጸዳበት፣ ከፈጣሪያችን የምንቀርብበት፣ ፍቅርንና ምሕረትን የምንለምንበት የተባረከ ጊዜ ይሁንልን። እግዚአብሔር ጾማችንን ይቀበል፣ ጸሎታችንን ይስማ፣ ቤተሰቦቻችንን በሰላም ይጠብቅልን። እኔንም በጸሎታችሁ አስቡኝ። 🤲❤️ መልካም ጾም https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780

  • ተከታታይ ትምህርት   የትምህርቱ ርዕስ  #ምሥጢራተ_ቤተክርስቲያን ክፍል አንድ ምሥጢር :- ማለት በስጋ ዓይን የማይታይ ፣ በስጋ ጆሮ የማይሰማ ፣ በስጋ እጆች የማይዳሰስ በአጠቃላይ በስጋዊ አካላችን የማናያቸው ነገር ግን በልበ ዓይን አይተን በልበ ጆሮ ሰምተን ወደ ልብ እጅ የምንዳስሰው ምሥጢር ይባላል ። " እንግዲህ ሁል ጊዜ ታምነን በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና በሥጋ ስናድር ከጌታ ተለይተን በስደት እንዳለን የምናውቀው ከሆንን... " በ2ኛ ቆሮ 2÷7 እንዲል። @eotc_spritual_books ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን:- ማለት ቤተክርስቲያን ከማህጸነ ዮርዳኖስ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ምእመናንን ወልዳ በማሳደግ ለክብር የምታበቃበት መንገዶች ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን በመባል ይታወቃል ። ምሥጢራተ ቤተክር በቁጥር ፯(7) ናቸው ። ምሳ 9÷1-6 " ጥበብ ለራሷ ቤቷን ሰራች ሰባቱ ምሥጢራቷን(አእማድን) አቆመች " እንዲል። እነርሱም :- 1. ምሥጢረ ጥምቀት 2. ምሥጢረ ሜሮን 3. ምሥጢረ ቁርባን 4. ምሥጢረ ክህነት 5. ምሥጢረ ንስኀ 6. ምሥጢረ ተክሊል 7. ምሥጢረ ቀንዲል  ይባላሉ። ከእነዚህ ምሥጢራት ውስጥ የሚደገሙና የማይደገሙ ምሥጢራት አሉ ። የሚደገሙት :- ምሥጢረ ቁርባን ፣ ምሥጢረ ንስኀ እና ምሥጢረ ቀንዲል ናቸው። የማይደገሙት :- ምሥጢረ ጥምቀት ፣ ምሥጢረ ሜሮን፣ ምሥጢረ ተክሊል እና ምሥጢረ ክህነት ናቸው ። 1.ምሥጢረ ጥምቀት ይቀጥላል ... https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780

  • 🕯አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ🕯 🕯"እዌድሰኪ ኦ ድንግል ምልእተ ውዳሴ መጠነ ይክል አፉየ አስተበፅዕ ዕበየኪ ማርያም ልሳነ ኪሩቤል ኢይክል አብጽሖ ውዳሴኪ ወአፈ ሱራፌል ኢይፌጽም ነጊረ ዕበየኪ ማርያም ጽበተ ከርሥኪ ሰፍሐ እምርሕበ ሰማይ ወጸዳልኪ አብርሀ እምብርሃነ ፀሓይ አስከሬነ ወርቅ ጽሩይ መዝገበ ባሕርይ ቡርክት አንቲ ማርያም ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት ወስብሕት በሐዋርያት አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ ወትምክሕተ ቤቱ ለእስራኤል ሠርጸ መንግሥት ዘእምሥርወ እሴይ ወጽጌ ንጽሕት ዘእምጒንደ ዳዊት ወብኪ ይትሜዐዙ ኵሎሙ ቅዱሳን"🕯 ትርጉም:- 🕯ምስጋናን የተመላሽ ድንግል ሆይ አመሰግንሻለሁ፤ማርያም አንደበቴ እንደሚችል ገናንነትሽን አከብራለሁ። የኪሩቤል አንደበትም ምስጋናሽን መፈጸም ማድረስ አይችልም ማርያም የሱራፌል አንደበትም ገናንነትሽን ተናግሮ አይፈጽምም። ከሰማይ ስፋት ይልቅ የማሕፀንሽ ጽበት ሰፋ፤ወጋገንሽም(የፊትሽም ጸዳል) ከፀሓይ ብርሃን ይልቅ በራ፤የጥሩ ወርቅ ሣጥን የዕንቁ መዝገብ ማርያም አንቺ የተባረክሽ ነሽ። የእስራኤል የቤቱ መመኪያ የያዕቆብ የበረከቱ አክሊል የሆንሽ ድንግል ማርያም በነቢያት አንደበት የተመሰገንሽ ነሽ በሐዋርያት ዘንድም የከበርሽ ነሽ። ከእሴይ ሥር የተገኘሽ የመንግሥት ቡቃያ ነሽ ከዳዊት ግንድ የተገኘሽ ንጽሕት አበባ ነሽ፤ቅዱሳን ሁሉ በአንቺ ይሻተቱብሻል። 🕯 🕯መጽሐፈ ሰዓታት🕯 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780

  • "ኃጢአት ለመሥራት ቀጠሮ ትይዛለህ፤ ጽድቅ ለመሥራት ግን ጊዜ የለኝም ትላለህ፡፡ ጓደኛህን ለማግኘት ጊዜ አለህ፤ ንስሐ አባትህን ለማግኘት ግን ጊዜ የለህም፡፡ በሥጋ ስትራብ ከየትም አምጥተህ (ለምነህም ቢኾን) ትበላለህ፤ ነፍስህ የክርስቶስ ሥጋ ከራባት ግን ዘመናት ተቆጠሩ፡፡ ወዳጄ ሆይ! እባብ አሳተኝ ያለችውንና፥ ከፍርድ ያላመለጠችውን ሔዋን ታስታውሳለህን? እንግዲያውስ፥ አንተም እንደ እርሷ ምክንያት በመደርደር ራስህን ለማጽደቅ አትሞክር፡፡ ይህ ሲነገርህም በተግባር እንጂ በከንፈርህ መልስ ለመስጠት አትጣር፡፡" https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780

  • • ሰዓሊ ለነ ቅድስት "…ሰዓሊ ለነ ቅድስትን ቅዱስ ኤፍሬም አልተናገረውም። ይኸውም ሊታወቅ በሀገራቸው ከመጽሐፍ ቢፈልጉ በቃል ቢጠይቁ አይገኝም፡፡ ቅዱስ ያሬድ የዜማ መክፈያ አድርጎ ተናግሮታል፡፡ እርሱም ከአፍኣ አምጥቶ ከልቡ አንቅቶ የተናገረው አይደለም። ከዚያው ከውስጥ ሰአሊ ካለው ሰአሊን ቅድስት ካለው ደግሞ ቅድስትን አምጥቶ ተናግሮታል፡፡ "…ንጽሕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ሆይ ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመናት በግብርናተ ዲያብሎስ ተይዞ የነበረ አዳምን ነጻ ያወጣው ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን አእምሮውን ለብዎውን ሰላሙን ፍቅሩን በልቡናችን በአእምሯችን ሳይብን አሳድሪብን። https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780

  • 🌹ውዳሴ 🌹ማርያም 🌹አንድምታ                        💐መቅድም ውዳሴ ማርያምን ኤፍሬም ሶርያዊ ደርሶታል። ይህም በኒቅያ ተሰብስበው አርዮስን ከረቱት ከ318ቱ ሊቃውንት አንዱ ለሆነው ለያዕቆብ ዘንጽቢን ደቀመዝሙር የነበረ ነው። ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ ስለክብረ ወንጌል የወርቅ ልብስ ይለብስ ነበር። በውስጥ ግን ማቅ ይለብስ ነበር። ቅዱሳን የራሳቸው ክብር ከሚገለጥ የወንድማቸው ክብር ቢገለጥ ይወዳሉ። ድንግል ማርያም በሰባቱ ዕለታት ትመሰላለች። በዕለተ እሑድ አሥራወ ፍጥረታት የሚሆኑ አራቱ ባሕርያት ተገኝተዋል። ከድንግል ማርያምም አሥራወ ፍጥረታት ጌታ ተወልዷል። በዕለተ ሰኑይ ጠፈር ተፈጥሯል። ድንግል ማርያም የዕለተ ሰኑይ ምሳሌ ጠፈር ክርስቶስ ከእርሷ የነሣው ሥጋ ምሳሌ ብርሃን የጌታ ምሳሌ ነው። በዕለተ ሠሉስ ምግብ የሚሆኑን ዕፀዋት ተገኝተዋል። ከድንግል ማርያምም መንፈሳዊ ምግብ ክርስቶስ ተገኝቷል። በዕለተ ረቡዕ ፀሐይ ጨረቃ ከዋክብት ተገኝተዋል። ከድንግል ማርያምም ብርሃን ጌታ ተወልዷል። በዕለተ ኀሙስ ደማውያን ፍጥረታት ከውሃ ተፈጥረዋል። ዕለቲቱ የድንግል ማርያም ባሕር የጥምቀት ምሳሌ ነው። በዕለተ ዐርብ በኵረ ፍጥረታት አዳም ተገኝቷል። ከድንግል ማርያምም ዳግማዊ አዳም ኢየሱስ ክርስቶስ ተወልዷል። በዕለተ ቀዳሚት ዕረፍት ተገኝቷል። ከድንግል ማርያምም የመንፈሳውያን ዕረፍት ክርስቶስ ተወልዷል።                          💐ዘሰኑይ አምላክ ሰው ሆኖ አዳምን ወደቀደመ ክብሩ (ልጅነቱ) ወደቀደመ ቦታው (ገነት) መልሶታል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ጽንዕት በድንግልና (በድንግልና የጸናች)፣ ሥርጉት በቅድስና (በቅድስና ያሸበረቀች ያጌጠች) እንላታለን። ድንግል ማርያም ክርስቶስን በሥጋ ወለደችው። ቤዛ ይስሐቅ በግዕ ከኅቱም ጕንድ ተገኝቷል። ቤዛ ዓለም ክርስቶስም በኅቱም ማኅፀን ለመወለዱ ምሳሌ ነው። ጽምዐ እስራኤልን ያበረደ ውሃ ከኅቱም ኮኵሕ ተገኝቷል። ጽምዐ ነፍሳትን ያበረደ ማየ ሕይወት ክርስቶስም በኅቱም ማኅፀን ለመወለዱ ምሳሌ ነው። ጽምዐ ሶምሶንን ያበረደ ውሃ ከኅቱም መንሰከ አድግ ተገኝቷል። ጽምዐ ኃጥአንን ያበረደ ማየ ሕይወት ጌታም በኅቱም ማኅፀን ለመወለዱ ምሳሌ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለው ስም የመለኮት ብቻ ወይም የትስብእት ብቻ ስም አይደለም። ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ቢሆን የወጣለት ስም ነው እንጂ። ቃለ እግዚአብሔር የእኛን ሥጋ ተዋሐደ። አማኑኤል ማለት ሰው የሆነ አምላክ ማለት ነው። አብ ወልድን ላከው ማለት ወልድ ሰው እንዲሆን፣ ሥጋን እንዲለብስ፣ በሥጋዊ አካል እንዲገለጥ የአብ ፈቃድ ሆነ ማለት ነው። በወልድ ሰው መሆን ዓለሙ ሁሉ ይድን ዘንድ የሦስቱ የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ነው። በፈቃድ አንድ ናቸውና። ክንድ ከአካል ሳይለይ የወደቀውን ዕቃ አንሥቶ ይመለሳል። ወልድም ከአብ አንድነት ሳይለይ አዳምን አድኗልና የአብ ክንድ እየተባለ ይጠራል። አዳም ከኅቱም ምድር እንደተገኘ ክርስቶስም ከኅቱም ማኅፀን ተገኝቷልና ዳግማይ አዳም ይባላል። ጌታ ሰው መሆኑ በጥንተ አብሶ ምክንያት ብቻ ሳይሆን በምልዐተ ኃጢአትም ምክንያት ነው። አምላክ ሰው ሲሆን ሰው አምላክ ሆነ። ዲያብሎስ በሥጋ ከይሲ ተሠውሮ ቢያስትበት ክርስቶስ ደግሞ በሥጋ ብእሲት ተሠውሮ አድኖበታል። ክርስቶስ ፍዳን አጠፋ። ዕለት ዕለት የምንሠራውን ኃጢአታችንን እየጻፈ የሚያዘክር ሰይጣን አለ። ቄሱ እግዚአብሔር ይፍታሕ ሲለን ይፋቅልናል። አምላክ ሰው በመሆኑ ፍጥረት ሁሉ ደስ አለው። ክርስቶስ መንፈሳዊ ልደትን (ልጅነትን) ሰጠን። ድንግል ማርያም ከኀልዮ፣ ከነቢብ፣ ከገቢር ኃጢአት ንጽሕት ናት። እናትነትን ከድንግልና አስተባብራ የያዘች እርሷ ብቻ ናት።                          💐ዘሠሉስ ማርያም ማለት ፍጽምት ማለት ነው። መልክ ከደም ግባት አስተባብራ የያዘች፣ ንጽሐ ሥጋ ንጽሐ ነፍስ ንጽሐ ልቡናን ድንጋሌ ሥጋ ድንጋሌ ነፍስ ድንጋሌ ልቡናን አስተባብራ የያዘች ናትና ፍጽምት ትባላለች። አንድም ማርያም ማለት ጸጋ ወሀብት ማለት ነው። ለጊዜው ለእናት ለአባቷ ፍጻሜው ለሰው ልጅ ሁሉ ጸጋ ተሰጥታለችና። አንድም ምእመናንን ወደገነት መንግሥተ ሰማያት መርታ የምታስገባ በመሆኗ መርሕ ለመንግሥተ ሰማያት ትባላለች። አንድም ልዕልት ማለት ነው። መትሕተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን ናትና። አንድም እግዝእተ ብዙኃን ማለት ነው። ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በራእይ ያያት የወርቅ መሰላል የእመቤታችን ምሳሌ ናት። የወርቁ መሰላል የተተከለበት ድንጋዩ የትንቢተ ነቢያት ምሳሌ። በዚያ ላይ ጸንታ ማየቱ በትንቢተ ነቢያት ጸንታ ለመገኘቷ ምሳሌ ነው። ዙፋን የማኅፀኗ ንጉሥ የጌታ ምሳሌ ነው። ሙሴ ያያት ዕፀ ጳጦስ የድንግል ማርያም ምሳሌ ናት። ነበልባል የጌታችን ሐመልማል የእመቤታችን ምሳሌ ናት። አንድም ሐመልማል የትስብእት ነበልባል የመለኮት ምሳሌ ነው። ነበልባሉ ሐመልማሉን ሳያቃጥለው ሐመልማሉ ነበልባሉን ሳያጠፋው በተዋሕዶ በተዓቅቦ አይቶታል። ሙሴ ወደ ደብረ ሲና ሲቀርብ ጫማውን እንዳወለቀ እኛም ነገረ እግዚአብሔር ወደሚነገርበት ቤት ስንገባ ጫማ አውልቀን እንገባለን። ፍሬ ሕይወት ጌታ ከድንግል ማርያም ተወለደ። ድንግል ማርያም የመላእክት ደስታቸው የሚሆን ጌታን በሥጋ ወለደችልን። ኻያ ሁለቱን ሥነ ፍጥረት የፈጠረ የእግዚአብሔርን ጌትነቱን ጠንቅቀን ፈጽመን መናገር አይቻለንም። አንድም የሥጋዌውን ነገር ጠንቅቀን ፈጽመን መናገር አይቻለንም። ድንግል ማርያም እንድትመረጥ ሆና ብትገኝ ጌታ እናቱ ትሆን ዘንድ መረጣት። ከአብ አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ የተወለደ አካላዊ ቃል ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰው ሆኖ አዳነን። ድንግል ማርያም የአካላዊ ቃል እናቱ ሆነች። ኪሩቤል የእግዚአብሔርን ዙፋን ይሸከማሉ መባሉ በዘፈቀደ የሚገለጥበትን ዙፋን ይሸከማሉ ማለት ነው እንጂ እነርሱንም በመሐል እጁ ይዞ የሚያኖራቸው እግዚአብሔር ነው።                           💐ዘረቡዕ በሠርግ ቤት አዝማደ መርዓዊና አዝማደ መርዓት አንድ ይሆኑበታል። በድንግል ማርያምም መለኮትና ትስብእት ተዋሕደውባታልና ከብካብ ንጹሕ ትባላለች። እመቤታችን ሀገረ እግዚአብሔርም ትባላለች። ንጉሥ በከተማው እንዲኖር በድንግል ማርያም ማኅፀንም ጌታ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ማኅፀኗን ዓለም አድርጎ ኖሮባታልና። ድንግል ማርያም በደመና ኤልያስ ትመሰላለች። በተጨማሪም በንጹሕ የሽቱ ዕቃ (ሙዳየ ዕፍረት) ትምሰላለች። አምላክ ለሆነ ለሥጋ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በአንድነት ምስጋና ይገባዋል። የሥላሴ ባሕርይ ጽድቅ እንጂ ኃጢአት አይስማማውም። ድካምም አይስማማውም። በሕማም በሞት አይለወጥም። ሥላሴ በአካል በግብር (አካላዊ) በስም ሦስት ሲሆኑ በባሕርይ በህልውና አንድ ናቸው። ጥንት የሌለው መለኮት በሥጋ ዘመን ተቆጠረለት። ቅድምና የሌለው ሥጋም በመለኮት ቀዳማዊ አምላክ ተባለ። ድንግል ማርያም ሕዝቅኤል በራእይ ባያት ቤት ትመሰላለች። ቤት የእመቤታችን፣ መቆለፊያ የማኅተመ ድንግልናዋ፣ በር ሳይከፍት የገባ ቀይ ጎልማሳ የጌታ፣ እንደተቆለፈች ገብቶ እንደተቆለፈች መውጣቱ በድንግልና ተፀንሶ በድንግልና ለመወለዱ ምሳሌ ነው። https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780

  • ❣ጾመ ፍልሰታ/ጾመ ማርያም/        🌺ፍልሰታ ማለት ፈለሰ፤ ተሰደደ፤ ተጓዘ፤ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሄደ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ «ፈለሰት ማርያም እምዘይበሊ ኀበኢይበሊ፤ ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም፣ ከምድር ሕይወት ወደ ሰማያዊ ሕይወት፣ ተሻገረች» በማለት ፍልሰታ የሚለውን ቃል ትርጓሜ አመሥጥሮ ገልጾታል፡፡   🌺ጾመ ፍልሰታ ከእመቤታችን ድንግል ማርያም የዕረፍት ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ እመቤታችን በዚህ ዓለም ፷፬ ዓመታትን በሕይወተ ሥጋ ከቆየች በኋላ ጌታችን የእናቱን ተድላ ነፍሷን እንጂ ተድላ ሥጋዋን አይወድምና ጥር ፳፩ ቀን ፵፱ ዓመተ ምሕርት አረፈች፡፡ ዕረፍቷም እንደሌላው ሰው በሕማምና በድካም አይደለም፡፡ በገነት ዕፀዋት መዓዛ ተመስጣ ቅድስት ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይታለች፡፡   🌺ታሪኩ በነገረ ማርያም እንደተጻፈው ሐዋርያት እመቤታችንን በአጎበር አድርገው አክብረው ወደጌቴሴማኒ መካነ መቃብር ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉም ነበርና ቀድሞ ልጇን ተነሣ ዐረገ እያሉ ሲያውኩ ኖረዋል፤  እርሷን ደግሞ ተነሣች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን ነውና «ኑ የማርያምን ሥጋ በእሳት እናቃጥለው» ብለው በምቀኝነት ተነሱ፡፡ ከመካከላቸው አንድ ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ከሐዋርያት እጅ ለመንጠቅ ዘሎ ሄዶ የአልጋውን ሸንኮር ሲይዝ የታዘዘ መልአክ በረቂቅ ሰይፉ እጆቹን ቆረጠው፡፡ እጆቹም በአልጋው ሸንኮር ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ፡፡ የምሕረት እናት የሆነችው ድንግል ማርያም ቅዱስ ጴጥሮስ ጸልዮ እጆቹን እንዲመልስለት ነግራው እንደነበረ አድርጎለታል፡፡   🌺የእመቤታችን ሥጋዋን መላእክት ከዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር ወስደው አስቀምጠውታል፡፡ ሥጋዋ ያለበትን ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ እነርሱ ባለማየታቸው እመቤታችን ባረፈች በ፮ኛው ወር ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ፲፬ ቀን ድረስ ከጾሙ በኋላ በ፲፬ኛው ቀን ሥጋዋን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በጌቴሴማኒ ባለው መቃብር ቀብረውታል፡፡   🌺ከዚህ በኋላ እንደ ልጇ በ፫ኛው ቀን ተነሥታ መላእክት እየዘመሩላት ወደሰማያት ስታርግ፤ ሐዋርያው ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሰ ዕርገቷን በማየቱ መላእክት «እመቤትህ እርሷ ናት፤ስገድላት» አሉት፤ እርሱም «ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ ይላል፤ከደመናው ሊወድቅ ወደደ» ምክንያቱም ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ፤ ዛሬ ደግሞ የእርሷን ትንሣኤ ለማየት ብሎ ነው፡፡ እመቤታችንም «ትንሣኤየን ያየህ አንተ ነህ ሌሎቹ አላዩም» ብላ ሐዋርያት ገንዘው የቀበሩበትን የሐር ግምጃ ሰጥታ አጽናንታ ሰደደችው፡፡   🌺ቅዱስ ቶማስ ኢየሩሳሌም ሲደርስ የእመቤታችን ነገር እንዴት ሆነ ብሎ ጠየቃቸው፤እነርሱም አግኝተው እንደቀበሯት ነገሩት፤ እርሱም ያየውን ምሥጢር በልቡ ይዞ «ሞት በጥር፤ በነሐሴ መቃብር፤ ለሰሚውም አያምር፤ይህ እንዴት ይሆናል?»፤ ቢላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ «ድሮም አንተ ተጠራጣሪ ነህ፤ማን ያርዳ የቀበረ፤ ማን ይናገር የነበረ እንዲሉ፤ ገንዘን የቀበረን እኛ እያለን እንዴት ትጠራጠራለህ» ብለው ወደ መቃብሯ ሄደው መቃብሯን ቢከፍቱት ባዶ ሆኖ አገኙት፡፡ በዚህ ተደናግጠው ተያዩ፤ በዚህ ጊዜ ቅዱስ ቶማስ «አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችን ተነሣች፤ዐረገች፤ ይኸው ምልክቱ» ብሎ ገንዘው የቀበሩበትን ሰበን አሳያቸው፤ እነርሱም አምነው ሰበኗን ለበረከት ተካፈሉት፡፡   🌺በዓመቱ ነሐሴ ፩ ቀን ሐዋርያት በመንፈሰዊ ቅናት ተነሳስተው «ቶማስ ትንሣኤዋን አይቶ እኛ ሳናይ እንዴት ይቀርብናል» በማለት ነሐሴ ፩ ቀን ሱባኤ ጀምረው በ፲፮ኛው ቀን የሐዋርያትን ሱባኤ ተቀብሎ እመቤታችንን መንበር ጴጥሮስን ተራዳኢ፣ ካህን እስጢፋኖስን ሠራዔ ዲያቆን አድርጉ ቀድሶ አቁርቧቸዋል፡፡ ከዚያ ጊዜ በኋላም ከነሐሴ ፩ እስከ ፲፭ ቀን  ጾመ ፍልሰታ ተብሎ ሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ ይጾመዋል፡፡ 💛የጾሙ እና የትንሣኤዋ በረከት ተካፋይ ያድረገን፤ አሜን💛 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780

  • "ከንስሐ አባትህ ጋር ስትሆን ጥያቄህን እንጂ ውሳኔህን አታቅርብላቸው፤ በልብህ ካሰብከው ጋር እንዲስማሙ ሳይሆን በሐሳብህ ላይ ሐሳባቸውንና ምክራቸውን እንዲሰጡህ አድርግ።" ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሣዊ https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780

  • ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች፤ ሙሽሪትን በሰርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል፤ ይሸልሙታል፡፡ ወደ ሰርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሰርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ፣ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል፡፡ እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ልቡናችንን በማንጻት፣ ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ፣ የክፋት እርሾን በማስወገድ፣ ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት የምግባር እናት፣ የማስተዋል እንዲኹሉም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን፤ ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች፡፡ በሌላ አገላለጽ ብነግራችኹ ሐኪሞች በአንድ ታማሚ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፣ መርዘኛ ፈሳሽን ማስወገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ታማሚው ምግብ ከመውሰድ እንዲቈጠብ ነው፡፡ ታማሚው ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከለ ሓኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት እንደተፈለገው ውጤት አይሰጥም፡፡ እኛም ቁስለ ነፍስ ቁስለ ሥጋ የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚኽ በላይ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስን የምንሻ ከኾነ ልቡናችንን ንጹሕና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል፡፡ እንዲኽ ካልኾነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780

  • https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780 https://t.me/tewahdo2780

  • (ከፕሮቴስታንትነት ወደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሕማማትን መጽሐፍ  አንብቦ የተመለሰው ወንድም ) መጽሐፈ #ሕማማት እና የእኔ ገጠመኝ #የሕማማት መጽሐፍ ከአንባብያን ከቀረበች ሶሰተኛም የዓብይ ጾምን ይዛለች። መጽሐፉ ጸሐፊ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እኔ የምኖርበት አካባቢ የሕማማት መጽሐፍት እንዳሉና የታተመውን መጽሐፍ እኔ ከምኖርበት ከሻሸመኔ ወደ አዲስ አበባ እንዳደርስ ነግሮኝ ስለነበር ከዛሬ ሰባት ቀን በፊት በነግህ ተነስቼ በግዮን ባስ መጽሐፍቱን ይዤ ወደ አዲስ አበባ አቀናሁ። ዲያቆን ሄኖክ መጽሐፍቱን እንዳስረክበው በስልክ ካገናኘን ሰው ጋር ተገናኝተን መጽሐፍቱን አስረክቤ ዕለቱን ወደ ሻሸመኔ መመለስ ስለነበረብኝ ከዚህ ቀደም ባነበውም ለመንገድ እንዲሆነኝ ብዬ አንድ ፍሬ የሕማማት መጽሐፍ ወስጄ ከስቴዲየም ከሰዓት በሚነሳው ባስ ውስጥ ለመመለስ ተሳፈርኩኝ። ሰዓታችን ሲደርስ ጉዞ ተጀመረ። ባለኝ ልማድ ማንኛውም መጽሐፍ እጄ ሲገባ የመጽሐፉ የመጨረሻ ገጽ ላይ ስሜንና የእጅ ስልክ ቁጥሬን ጽፌ ከውስጥ ካሉት አንዱን ርዕስ መርጬ ንባቤን ጀመርኩ። ዝዋይ አካባቢ ስደርስ ግን ድካሜ በርትቶ ፊት ለፊት ባለው ማስቀመጫ መጽሐፉን አስቀምጬ ራሴን አመቻችቼ ተኛሁ። ከእንቅልፌ የነቃሁት ግን ሻሸመኔ ወራጅ ካለ መጨረሻው እዚህ ነው የሚል ድምጽ ስሰማ ነው። ተደነባብሬ ወረድኩኝ። መጽሐፉን ረስቼ መውረዴን ያስታወስኩት ቤት ከገባሁ በኋላ ነው። ከአንድ ሳምንት በኋላ ግን የእጅ ስልኬ ላይ አንድ መልዕክት ደረሰኝ አስደናቂው የእግዚአብሔር ተዓምር ደግሞ ይህ ነው። በስልኬ የደረሰኝን መልዕክት ሳልጨምር ሳልቀንስ ላላካፍላችሁማ። እንዲህ ይላል:- ጤና ይስጥልኝ ዲ/ን ሚክያስ። ዘውዱ እባላለሁ ከዲላ። ስምህንና ስልክህን ባለፈው ሳምንት ከአዲስ አበባ ወደ ሀዋሳ ስትመጣ በባስ ውስጥ ረስተህ በወረድከው ሕማማት የተባለው መጽሐፍ ላይ ነው ያገኘሁት በወቅቱ አጠገብህ ነበርኩ ረስተክ እንደወረድክ መጽሐፉን ስወርድ ይዤው ወርጄ ነበር። ሰሞኑን ቤት እየዋልኩ ስለነበር ለድብርት ያህል አነበብኩት። እኔ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ነኝ። ኦርቶዶክሶች ግን ስለ ኢየሱስ እንደዚህ አይነት ትምህርት እንዳላት ፈጽሞ አላውቅም በህይወቴ ብዙ ጥያቄ የሆኑብኝ ነገሮች መልስ አግኝቼበታለሁ። የመጽሐፉ ጸሐፊ ጋ ይህን መልዕክት መላክ ይኑርብኝ አይኑርብኝ አላወኩም የመጽሐፉ የመጨረሻ ገጽ ላይ ይህን ስልክና ስም ሳገኝ ላኩልህ። እናም ወንድ አንድ የኦርቶዶክስ ጓደኛዬን አናግሬው ከቄስ ጋር አገናኘኝ አንዳንድ ነገሮች እያስተማሩኝ ነው ጌታ ቢፈቅድ ደሞ ለትንሳኤ ክርስትና ትነሳለህ እናጠምቅሃለን ብለውኛል በጣም ደስተኛ ነኝ። እንኳንም መጽሐፉን ረስተህ ወረድህ እንዳትቆጭ አንድ ህይወት አድነሃል አመሰግናለሁ። ታዲያ ከዚህ በላይ ምን ተዓምር አለ ትላለህ? በሐዋ 2 ላይ ቅዱስ ጴጥሮስ በአንድ ስብከት 3000 ሰው እንደመለሰ ተጽፏል። አሁን ግን በ3000 ስብከት አንድ ሰው መመለስ ባልተቻለበት ጊዜ መጽሐፍትን በማንበብ ብቻ እንዲህ አይነት ዜና መስማት በጸሐፊውና በመጽሐፉ ያለውን የእግዚአብሔርን ጸጋ ያሳየናል። ነፍሴ ፍፁም ሀሴት አድርጋለች። ለነገሩ እኔ ብቻ አይደለሁም የተደሰትኩት የሰማይ መላእክት ጭምር እንጂ። ንስሃ በሚገባ በአንድ ኃጥእ በሰማይ ደስታ እንደሚሆን ተነግሮን የለ? ወንድሜ ተክለ ማርያም ሆይ ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ... በቀረውስ በጌታ በኃይሉ ችሎታ የበረታችሁ ሁኑ እንዳለ የበለጠ ትጉህ እንድትሆን ይህ ላንተ የመንፈስ ብርታትህ ነው። #ጥቂት_መግቢያ_ሕማማትን_ላናነበባችሁ መጽሐፉ በክርስቶስ ሕማም ዙሪያ ከሐሙስ ማታ ጀምሮ እስከ ዓርብ ዓሥራ አንድ ሰዓት ያለውን የጌታችንን የሃያ ሰዓታት ለሰው ልጆች መዳን ሲል የተቀበለውን መከራ የሚዳስስ አስደናቂ መጽሐፍ ነው። የሃያ ሰዓታትን የመከራ ጉዞ ይናገር እንጂ መጽሐፉ ባለ ሃያ ገጽ እንዳይመስልህ። የሰማይ ያህል የሚከብዱ ጠንካራ ጉዳዮችን የያዙ ባለስድስት ምዕራፍ ÷ በሁለት እጅ የማይነሳ ባለ አምስት መቶ ሃያ አምስት ገጽ እንጂ። ሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ነገረ ሕማማቱን የክርስቶስን የማዳን ሥራ ስታነብ ስታስነብብ የኖረች ሀገር ነች። ጸሐፊው እንዳስቀመጠልን በመልዕክተኛዋ ጃንደረባው አማካኝነት ገና መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ሳይጠናቀቅ ማንበብ የጀመረችና መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቁጭ ብላ መጽሐፍ ቅዱስን ስታነብ የተገኘች ሀገር ነች። የዚህ መጽሐፍ ዋነኛ ዓላማም ከጃንደረባው ጉዞ ጀምሮ ቤተክርስቲያናችን ስታነበው የኖረችውን የመድኃኔዓለም ክርስቶስን የሕማማቱን ነገር በወንጌል መሰረትነት በአበው ትምህርት ብርሃንነትንና በሊቃውንት ምርኩዝነት ከእኛ ዘመን ነባራዊ ሁኔታ ጋር አገናዝቦ የሚያሳይ መጽሐፍ ነው። ምንአልባት ለአፍታ እንኳን የጌታን ሕማም አስበን መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነፍሱን እስከ መስጠት ድረስ ያደረገልንን እንድናስታውስና ካለንበት የኃጢአት ባህር ወጥተን ወደ ቀራንዮ ኮረብታ በሕሊናችን እንድንመለስና እንድንጸጸት የሚያደርግ መጽሐፍ ነው። የሥነ ጹሑፉ መምህር እንዳሉት መጽሐፉ በወረቀት ላይ በመልክና በፊደል ስለቀረበ መጽሐፍ እንበለው እንጂ በሥነ ጹሑፋዊ አቀራረቡ ግን ፊልም ነው ሊባል የሚያስደፍር ምስል ከሳች ነው። በዚህ የሃያ ሰዓታትን የሕማም ጉዞ ላይ ከጌታ ጋር የራስህን ሕይወት እየተመለከትክ አብረህ በእንባ ትጓዛለህ። ለጌታችን መያዝ ምክንያት የሆነው ይሁዳ ራሱ ጌታችን ስለሰው ልጆች ከታገሳቸው መከራዎች አንዱ ነውና ከአስቆሮቱ ይሁዳ ንባብህን ትጀምራለህ። ወዳጅ መስሎ ከማቁቁሰል የከፋ መሳምን እየሳመው የሚሸጠው የይሁዳን ነገር ስታነብ ህሊናህ ይቃጠላል። ይሁዳም በዚህ ምክንያት የደረሰውን ዕጣ ፋንታ አይተህ ስታበቃ ወደ ሌላኛው የጌታ ሕማም ትሻገራለህ። ጌታ ተይዞ እስከ ጠዋት ድረስ ሲንገላታ ፣ ወደ ጲላጦስ አደባባይ ወስደውት መከራን ሲቀበልና ስለምን ትመታኛለህ ሲል ትሰማዋለህ። ጌታ ይሰቀል ሲሉ እንሰማለን ፣ ሲገርፉት ቆመን እናያለን። ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ መስቀሉን ይዞ ሲሄድ በእግረ ሕሊናችን አብረን እንከተለዋለን። ከስምዖን ጋር አብረን እናግዘዋለን ከገሊላ ሴቶች ጋር አብረን እናለቅሳለን ከመስቀሉ ሥር ከእናቱ እና ከዮሐንስ አጠገብ ቆመን ከመስቀሉ በታች ሆነን ጌታ ሚናገራቸውን እንሰማለን። በመጨረሻም ነፍሱ ከሥጋው መለየቱን አይተን ከለንጊኖስ ጋር ከጎኑ ውኃ ተጠምቀን ፣ ከኒቆዲሞስና ከዮሴፍ ጋር አልቅሰን እንቀብረዋለን ትንሣኤውን ተስፋ አድርገንም ሕማማት የተሰኘውን መጽሐፍ ንባባችንን እናበቃለን። በዚህ መጽሐፍ የጌታ ሥቃይ ከማንኛውም ፍጡር በላይ ዘልቆ የተሰማት ከመስቀሉ ሥር ቆማ እያየች ልብዋ በኃዘን እሳት የተቃጠለ ፣ የእንባ ጎርፍ በዓይኖቿ የፈሰሰ ፣ ደሙ እንደ ውኃ ሲጎርፍ ቆማ እያየች ነፍስዋ በኀዘን ሰይፍ የተወጋ ድንግል ማርያምን የእናትነት መከራዋን በዚህ መጽሐፍ እናያለን። በዚህ ድንቅ መጽሐፍ ነው አምላክ ድንቅ ሥራውን ያደረገው። ሕማማትን ያላነበባችሁ ሁሉ ብታነቧት በሕይወታችሁ እንደምታተርፉባት ልነግራችሁ እወዳለሁ። መምህራችን ዲያቆን ሄኖክ ሊቀ ጉባኤ እንዳሉት ክብር ካለኝ ከክብሬ ዕድሜ ካለኝ ከዕድሜዬ ተቀንሶ ቢሰጥህ ብዬ ተመኘሁ። አምላክ ከዚህ የበለጠውን የእውቀትን ሽታ ያድልህ። ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም የሚወድሽ ልጅሽ ዲያቆን ሄኖክ /ተክለ ማርያምን በተሰጠሽ ቃል ኪዳን ልጅሽን አስቢው ሞገስና ክብርን አጎናጽፊው። አሜን።