tgindex
ርትዕት ኃልዮ/Thinking Orthodox

ርትዕት ኃልዮ/Thinking Orthodox

Статистика

ኑ ! የአማናዊት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን አስተሳሰብ እና ትውፊታዊ ትምህርትን እንረዳ። https://www.youtube.com/@retiethaliyot1

Последний пост
12 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Видео
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 448
−4 за 5 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
617
21 постов
Вовлечённость
25,2%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
98
1/48двое суток
112
1/72трое суток
121

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ✥✥✥ ፅንሰታ ለእግዝእትነ ✥✥✥ 👉 ነሐሴ 7 እመቤታችን የተፀነሰችበት ነው። ቤተክርስቲያናችንም ከምታከብራቸው ዓበይት በዓላት መካከልም ነው። 👉  አባ ሕርያቆስ ስለ እመቤታችን የመፀነስዋን ነገር ሲናገር ድንግል ሆይ በልተው ጠጥተው ጾር ሲጸናባቸው በሚያደርጉት ግንኙነት የተፀነሽ ኣይደለሽም ጋብቻ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ነው ብዙ ተባዙ ባለው ፈቃድ በሩካቤ ዘበሕግ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ በማለት ያደንቃል! 👉  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም " የእግዚኣብሔር ልጆች የቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ማኅበር እንግዲህ ይህችን ንጽሕት ሙሽራ የወለዱልንን ኢያቄምንና ሐናን እናድንቃቸው የማትነቀፍ የእስራኤል ድንግል የተባረከችይቱም ፍሬ የተፈራችባት የሩካቢያቸው ንጽሕት ቀን እንደምን ያለች ናት፡፡ ከይሁዳ ወገን የምትሆነውን ንጽሕት ርግብ ለመፀነስሽ ለእግዚኣብሔር ፈቃድ የሆነው የመገናኘታቸው ቀን እንደምን ቅድስት ናት፡፡ የንጉሥ አዳራሽ የምትሆን የርሷ መሠረት የተመሠረተባት ዕለት እንደምን ደስ ያለች ናት፡፡ ➛   ነቢዩ ኢሳይያስም እንዲህ አለ " ከዕሤይ ሥር በትር ትወጣለች፡፡ ከግንዱም አበባ ይወጣል በላዩም የእግዚኣብሔር መንፈስ ያርፍበታል፡፡ " (ኢሳ ፲፩፣ ፩፣ ፪) -    ይኸውም ትንቢት በጽዮን የተነገረው በኢየሩሳሌም የተሰበከው በነቢያት አንደበት የተሰማው በሌዋውያን እጅ በዕብራይስጥ ልሳን የተጻፈው ሊፈጸም የክህነት በትር በቀለችልን፡፡ የመንግሥትና የኃይል የሕይወትና የመድኃኒት የሃይማኖት የንጽሕና የቅድስና በትር የኃይል የመዊዕ በትር በቀለችልን፡፡ ➛  "ከዕሴይ ዘር በትር ትወጣለች፤ ከግንዱም አበባ ይወጣል የሚለው እንደተጻፈ፤ ያሰበውን ለማድረግ የሚከለክለው የለም፤ ከኢያቄም ኣብራክ ተከፍላ በሐና ማህፀን ከተፀነሰች ከቅድስት ድንግል የትውልድ ዘር በቀር የበትር ከሥሩ መውጣት ምንድነው? የእመቤታችን የማርያም ኣባቷ ኢያቄም ከዕሴይ ዘር ነውና፤ ዳግመኛም ከኢያቄም ሴት ልጁ የመለኮት ሰው መሆን በቀር የአበባ የግንድ መውጣት ምንድነው?" 👉   የልደትዋን ነገር አያይዞ ሲናገርም ፦  በኢያቄም በኣባትሽ ወገን የንጉሥ ልጅ ሆይ አመሰግንሻለሁ፡፡ የዳዊት ልጅ ነሽና የሊቀ ካህናት ልጅ ሆይ ውዳሴሽን አቀርባለሁ፡፡ ከእናትሽ ወገን የኣሮን ልጅ ነሽና፡፡ ገናንነትሽንም አደንቃለሁ፡፡ የነገድሽን ወገን አመሰግናለሁ ከቤተ መንግሥትና ከቤተ ክህነት ተገኝተሻልና፡፡ ➛  ስለዚሀም የነጎድጓድ ልጅ ነሽ እልሻለሁ ያዕቆብና ዮሓንስን ኣኔሬጌስ ብሎ እንደጠራቸው ይኸው የነጎድጓድ ልጆች ማለት ነው፡፡ ከቤተ መንግሥትና ከቤተ ክህነት ናቸውና፡፡ ስለዚህም የነጎድጓድ ልጆች ተባሉ፡፡ ➛  እኔም የነጎድጓድ ልጅ ነሽ ኣልሁሽ፡፡ የመወለድሽ ድምፅ (ወሬ) እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ይሰማልና፡፡  ከሁለቱ ከተቀቡት ነገድ በነቢያት አለቃ በሙሴ እጅ ለክህነት ከተቀባው ከኣሮን ቤት፡፡ በሳሙኤል እጅ ለመንግስት ከተቀባው ከዳዊት ዘር፡፡ (፩ ሳሙ ፲፮፣ ፲፫) (ዘሌዋ ፰፣ ፲፪)   👉  ደግሞም ያንበሶች ልጅ ነሽ እልሻለሁ እንደ አንበሳ ግልገል ጩኸት እንደ ሴትም አንበሳ ድምፅ የልደትሽ ወሬ ይሰማልና፡፡ አባቱ ያዕቆብ ይሁዳን ያንበሳ ግልገል ብሎታልና፡፡ (ዘፍጥ ፵፣ ፱፣ ፱) ➛ ስለዚህም ያንበሶች ልጅ እልሻለሁ፡፡ ሰሎሞን እንደተናገረ እንዲህ ሲል ኣንቺ ሙሽራ ከሊባኖስ ጋራ ነይ ከሊባኖስ ጋራ ነይ፡፡ ከአንበሶችም ጉድጓድ ወጥተሽ ነይ፡፡ (መኃ ፬፣ ፰) ከተመረጠ ነገዱ የተነሣ ከሚመካ ወገን የመወለድሽ ወሬ እጅግ ግሩም ነው፡፡ በማለት ያደንቃል።  ይቆየን ➕ ፍቅርዋን ከልቡናችን ጣዕመ ምስጋናዋንም ከአንደበታችን ታሳድርልን አትለይብን።

  • https://vt.tiktok.com/ZS43r9GHT/

  • እንኳን አደረሳቹሁ !                                                      ጾመ ፍልሰታ #ጾም_በሐዲስ_ኪዳን፡- የሐዲስ ኪዳን ጾም ከብሉይ ኪዳን ጾም የተለየ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን የነበረው ጾም ሥጋዊ ችግርን የሚመለከት ሲኾን፤ በሐዲስ ኪዳን ግን የምንጾመው ለጽድቅ ነው፡፡ ጌታችን  መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ  የመጀመሪያ ሥራ ያደረገው ጾምን ነው፤ እንደዚሁም ያስተማራቸው ደቀ መዛሙርት  ከሥራቸው በፊት ጾምን እንደ ጌታቸው አስቀደሙ፡፡ የሚከተሉት ጥቅሶች በሐዲስ ኪዳን ጾም እንደታዘዘ የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ ማር.፱፣፳፱፣ ማር.፪፣፳፣ ማቴ.፮፣፮፣ ሉቃ.፮፣፳፩፣ የሐ.ሥራ.፲፫፣፫፡፡ ስለዚህ ቤተክርስቲያናችን እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል አብነት በማድረግ ጾምን በአዋጅ እንድንጾም በቀኖናዋ (በሥርዐቷ) ደንግጋለች፡፡    በቤተክርስቲያናችን የአዋጅ ጾም የሚባሉት ሰባት ናቸው፡፡ እነርሱም፡- 1. ✣ ዐቢይ ጾም (ጾመ ኩዳዴ)     5. ✣ ጾመ ነነዌ 2. ✣ ጾመ ድኅነት (የረቡዕና ዐርብ)    6. ✣ጾመ ጋድ 3. ✣ ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም)    7. ✣ #ጾመ #ፍልሰታ 4. ✣ ጾመ ነቢያት (የገና ጾም)         #ጾመ_ፍልሰታ ፍልሰታ የግእዝ ቃል ነው፤ #ፈለሰ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም ተለየ፣ ሄደ፣ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ መሄድን ያመለክታል፡፡ ጾመ ፍልሰታ ሐዋርያትን አብነት አድርገን፤ ሐዋርያት የተቀበሉትን በረከት ለማግኘት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን የምንጾመው ታላቅ ጾም ነው። እመቤታችን እንደ ሰው ልማድ ሞትን ትቀምስ ዘንድ ግድ ስለኾነ፤ ጻዕርና ሕማም በሌለበት አሟሟት፤ ዕዝራ በመሰንቆ፥ ዳዊት በበገና እያጫወቷት፤ በተወለደች በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን #በ48 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ አርፋለች። ሐዋርያትም እንደምታርፍ በመንፈስ ቅዱስ ስለተገለጸላቸው ከያሉበት (ከየሀገረ ስብከታቸው) ወደ መኖሪያ ቤቷ (የሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ቤት) ተሰባስበው ነበር። ነፍሷ ከሥጋዋ እንደተለየች ሥጋዋን ገንዘውና ሸፍነው ወስደው ለመቅበር ወደ #ጌቴሴማኒ ሲሄዱ አይሁድ ሰምተው መጡና ሐዋርያትን ከበቧቸው። የአይሁድ ተንኮል አስከሬኗን ከሐዋርያት እጅ ቀምተው በእሳት ለማቃጠል ነበር፤  ይህንንም ማድረግ የፈለጉበት ምክንያት፤ የሐዋርያት ትምህርት (የጌታችን ከሞት መነሳትና ለፍርድ ተመልሶ መምጣት)ከአይሁድ አልፎ ዓለም ሁሉ እያመነበት ስለመጣ እመቤታችንም ተነሥታ ዐርጋለች እያሉ ሐዋርያት ያስተምራሉ በሚል ስጋት ነበር። ‹‹የፈሩት ይነግሣል፥ የጠሉት ይወርሳል›› እንዲሉ አበው፤ የእመቤታችን ትንሣኤም ሆነ ዕርገት አይቀሬ ሁኗል። አይሁድ የእመቤታችንን ሥጋ ለመንጠቅ በሞከሩበት ጊዜም ታውፋኒያ የተባለ ጎልማሳ ሰው በጉልበቱና በድፍረቱ በአይሁድ ዘንድ ተመርጦ የእመቤታችንን ሥጋዋ ያረፈበትን ቃሬዛ ከሐዋርያት ነጥቆ መሬት ላይ ለመጣል ሲሞክር፤ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ ሁሉቱንም እጆቹን ቀንጥሶ (ቆርጦ) ጥሏቸዋል። ነገር ግን ጥፋቱን አውቆ ወዲያው ስለተፀፀተና ይቅርታ ስለጠየቀ በአምላክ ፈቃድ በእመቤታችን አማላጅነት በቅዱስ ጴጥሮስ አማካኝነት እጆቹ እንደገና ተመልሰውለት የእመቤታችንን እመ አምላክነት (የአምላክ እናት መሆኗ)ና ክብርን ለመመስከር በቅቷል። የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ በመላእክት ተነጥቆ ከተወሰደ በኋላ በገነት ውስጥ #በዕፀ ሕይወት ሥር መቀመጡ ከዮሐንስ በስተቀር ለሌሎች ሐዋርያት ለጊዜው ምሥጢር ሆኖባቸው ቆይቶ ነበር። ቆየት ብሎ ግን ሐዋርያው ዮሐንስ ስለ እመቤታችን ሥጋ ነገራቸው። ቅዱሳን ሐዋርያትም ለእመቤታችን ካላቸው ክብርና ፍቅር የተነሳ ለምን አልቀበርናትም? ለምንስ የሥጋዋ ምሥጢር ለዮሐንስ ተገልጾ ለኛ ይደበቅብናል? በማለት እያዘኑና እየለመኑ ከጥር 21 አንስተው ለስድስት ወራት ከዐሥር ቀናት ቆይተዋል። ከዚህም በኋላ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ሱባዔ ይዘው ለ14 ቀናት እግዚአብሔርን በጾምና በጸሎት ጠየቁት። በመጨረሻም የነገሩትን የማይረሳ፥ የለመኑትን የማይነሳ ልጇ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነሐሴ 14 ቀን ሥጋዋን አምጥቶ ስለሰጣቸው፤ ሳይውሉ ሳያድሩ በዕለቱ በጌቴሴማኒ በታላቅ ክብርና ዝማሬ ቀበሯት። በተቀበረችም በ3ኛው ቀን በነሐሴ 16 ከተቀበረችበት መቃብር ተነሥታ ወዲያውኑ በታላቅ ክብር በመላእክት አጃቢነት ወደ ሰማይ ዐርጋለች። ጥበበኛው ሰሎሞንም “ውዴ  እንዲህ ይለኛል ሙሽራዬ ውዴ ሆይ! ተነሺ የእኔ ውብ ሆይ ነዪ አብረን እንሂድ” በማለት አመሣጥሮ የተናገረው በጥበበ እግዚአብሔር ተመርቶ እንደ ክርስቶስ ሆኖ ውዴ ያላት እመቤታችን መሆኗንና ልጇ ተነሥቶ እንደ ዐረገ እሷም መነሣቷንና ማረጓን እንረዳለን። /መሓ.፪፥፲/። እመቤታችን ባረገችበት ጊዜ ሐዋርያው #ቶማስ በመንፈስ ቅዱስ ጥበብ በደመና ተጭኖ  ከሀገረ ስብከቱ  (ሕንድ) ወደ   ኢየሩሳሌም ሲመለስ እመቤታችን በመላእክት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ ተገናኙ። በዚህ ጊዜ ቶማስ ቀድሞ የልጇን ትንሣኤ ሳላይ አሁንም ደግሞ እርሷን ሳልቀብራት ከትንሣኤዋም ሳልደርስ ቀረሁ ብሎ አዘነ ከደመናው ላይ ሊወድቅም ፈለገ፤ ሆኖም እመቤታችን ዕርገቷን ከእርሱ በቀር ሌሎች አለማየታቸውን ገልጻ አረጋጋችው፤ ዕርገቷንም ለሐዋርያት እንዲነግርና ምልክትና ማስረጃ እንዲሆነው ተገንዛበት የነበረውን ሰበኗን/የከፈን ጨርቅ/ ሰጥታ አሰናበተችው።     ቶማስም መሬት ለይ ወርዶ መቀበሯን፣ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያላወቀ መስሎ ሐዋርያትን ስለ እመቤታችን ሥጋ ጉዳይ ጠየቃቸው፤ እነርሱም ሱባዔ ገብተው እግዚአብሔርን በጸሎት መጠየቃቸውን፣ ከሱባዔያቸው በኋላ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ሥጋዋን መላእክት አምጥተው እንደሰጧቸውና እንደቀበሯት አስረዱት። እርሱ ግን ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር›› እንዴት ሊሆን ይችላል? ሲል ተከራከራቸው። ሐዋርያትም ቶማስን ለማሳመንና ለማሳየት ወደ መቃብሯ ወሰዱት፤ ሆኖም መቃብሯ ባዶ ሆኖ አገኙትና ተደናገጡ፤ በዚህ ጊዜ ቶማስ የሆነውን ሁሉ ገልጾ ለምልክትና ለማረጋገጫ የሰጠችውን ሰበኗን /ተገንዛበት የነበረውን ጨርቅ/ አሳያቸው፤ የራሱን ድርሻም አስቀርቶ አከፋፍሎ ሰጣቸው፤ #ዛሬም_ካህናት ከእጅ መስቀላቸው ጋር የሚይዙት እራፊ ጨርቅ የሚይዙበት ምክንያት ሐዋርያት የተከፋፈሉት የእመቤታችን ሰበን ምሳሌ ነው።        ሐዋርያትም የዕርገቷን ምሥጢር ካመኑ በኋላ ዕርገቷን ለማየት በዓመቱ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደገና ከነሐሴ 1 ቀን ጀምረው ለ፪ኛ ጊዜ ሁለት ሱባዔ ገቡ፣ እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ በነሐሴ ወር በ16ኛው ቀን ጌታችን ሐዋርያትን ወደ ሰማይ አውጥቷቸው እመቤታችንን አግኝተዋት ከሷ ተባርከው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረዘይት ተመልሰዋል። በአጠቃላይ #የእመቤታችን ለሐዋርያት በተለያዩ ጊዜያት መታየት፣ የሥጋዋና የነፍሷ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ፍልሰት ሲባል ከዚህ የተነሣ #የነሐሴ ጾም በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዐት መሠረት ሐዋርያት ያገኙትን በረከት ለማግኘት ጾመ ፍልሰታን እንጾማለን

  • ✝️ ጌታችን ለምን ዐረገ ? 1- ሰው በመሆኑ ተለወጠ ፍጡር ሆኖ ቀረ የሚሉ አሉና ወረደ በተባለው ሰው መሆኑን እንደተገለጸው ፤ ዐረገ በመባሉ ደግሞ ሰው አምላክ ሆነ የሚለውን ለመግለጽ ጌታችን ዐረገ:: 2 - ቅዱሳን ጻድቃን ኋላ ርስት መንግሥተ ሰማያትን እንደሚያገኙ ለማስረዳት 0ረገ። " ዐርገ ከመ ያለቡ ዕርገተ ጻድቃን ንጹሓን / የጻድቃንን ዕርገታቸውን ( የሚወርስዋትን መንግሥተ ሰማያት ) እንዳለች ለማሳወቅ ዐረገ" እንዲል (መቅድመ ወንጌል ) ✝️ ጌታችን ለምን በ40 ኛው ቀን ዐረገ ? -> ጌታችን ያረገው ሞትን በሥልጣኑ  ድል አድርጎ በተነሳ በ40 ኛው ቀን ነው (የሐዋ 1፥ 3 ) ።  ለምን 40 ቀን እስኪሞላ ጠበቀ ከ 40 በታች ወይም በላይ ለምን አልቆየም ? 1- አዳም የ30 0መት ጎልማሳ ሆኖ ተፈጥሮ በ40ኛው ቀኑ አግኝቶ ያጣትን ገነትን እንደመለሰለት ለማጠየቅ 40 ቀን ሲሆነው ዐረገ :: 2 - ሰው (ወንድም ሆነ ሴትም ) ተስእሎተ መልክዕ የሚሳልለት ከተጸነሰ በ40ኛው ቀኑ ነውና ተስዕሎተ መልክዕ ለተሣለለት የሰውል ልጅ ሁሉ ካሳን ፈጸምኩ ለማለት ዕርገቱን ከተነሳ በ40 ቀኑ አደረገው:: 3- ሰጎን ጫጩቶቿን የምትፈለፍለው እንደ ሌሎቹ አዕዋፍ በመታቀፍ አይደለም፡፡ ለ40 ዕለት ያህል ተባዕቱም ሆነ እንስቲቱ ሰጎን እንቁላሉን ትክ ብለው ይመለከቱታል ፤ዕንቁላሉም ነፍስ ዘርቶ ይፈለፈላል ፤ለጥቂት ፊታቸውን ቢመልሱ ግን ዕንቁላሉ ይበላሻል ፡፡ ጌታችንም ከትንሳኤው በኋላ 40 ቀን እስኪሆን መቆየቱ ዘውትር እንደሚጠብቀን ፥ ከእኛም ዐይኑን እንደማያነሳ ምሳሌም ነው ። ✝️ ጌታችን ትንሣኤ ባደረገበት ዕለት ለምን አላገረም ? 40 ቀን በምድር ምን ሲያደርግ ቆየ ? 1- ከትንሣኤው በፊት ወንጌልን ለሐዋርያት እንዳስተማራቸው ከትንሣኤው በኋላ ቤተክርስቲያን የምትተዳደርበትን ሥርዓትን (ኪዳንን ) ሊያስተምራቸው ቆይቷል ። 2 - ለቅዱሳን ሐዋርያት ከሞት በኋላ ስላለው ሕይወት ስለ ገነት ስለ መንግሥተ ሰማያት ኑሮ ምን እንደሚመስል ስለ ሚጠብቃቸው ታላቅ ስጦታ እየነገራቸው ቆይቷል። (የሐዋ 1፥ 3 ) 3 - በዕለተ ዓርብ በሲኦል ለነበሩ ለነፍሳት የተደረገላቸው ነገር ለሐዋርያት እየነገራቸው ቆይቷል ። ቅዱስ ጴጥሮስ " ሄዶ በወህኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው " በማለት ጌታችን በዕለተ ዐርብ ለነፍሳት የተደረገውን የነገራቸውን ለእኛ ጽፎልናል። (1ኛ ጴጥ3:19 ) 4 - ጌታችን በሕማሙ በሞቱ አዝነው የነበሩ ቅዱሳን ሐዋርያትን ሊያጽናናቸው ከትንሣኤው በኋላ አብሯቸው ቆይቷል 5 - ለሰቀልያኑ አይሁድ የንስሓ ጊዜ ለመስጠት እና ትንሣኤው እውነተኛ መሆኑን ለማስረዳት ነው ። ሞትን በሥልጣኑ ድል አድርጎ መነሳቱን 0ይተው እንዲያምኑ ነው፡፡ ጌታችን " ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም ። ዮናስ በዓሣ ዐንበሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል " ( ማቴ 12፥39-40 ) እንዳለው አይሁድን ወደ እምነት ለማቅረብ የተሰጠው ትልቁ ምልክት ሞትን ድል አድርጎ መነሳቱ ነው፡፡ ለዚህም ቅዱስ ሉቃስ በሐዋርያት ሥራ እንደጻፈልን " በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው ። " በማለት ለአይሁድም ሆነ ለሰው ልጅ ሁሉ አምላክቱን የሚያስረዳ ትንሣኤውን እውነተኛ መሆኑን ለማሳወቅ እንደተነሳ ሳያርግ ከተነሳ በኋላ  ያለመነው ለማሳመን ያመነውንም ለማጽናት 40 ቀን እየታያቸው ቆይቷል ። (የሐዋ1፥3 ) 6 - ድርገተ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን እያሳወቃቸው ቆይቷል ። ቅዱስ ሉቃስ በሐዋርያት ሥራ  " ከነርሱም ጋራ ዐብሮ ሳለ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ አዘዛቸው ፥ ነገር ግን ፦ ከእኔ የሰማችሁትን አብ የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠብቁ " የሐዋ 1፥4  በማለት እንደገለጸው ከትንሣኤው በ50 ኛው ዕለት ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ሲወርድ ሐዋርያት በምን መልኩ መቀበል እንዳለባቸ እራሳቸው እንዲያዘጋጁ እያስተማራቸው ቆይቷል።

  • ✥ ትጒህ በጸሎት ✥ -> አቡነ ተክለሃይማኖት እየረዱ (ረድ ሆነው ) ሰባት ሰባት ጊዜ ዳዊትን ያደርሱ ነበር (ማር ይስሐቅ ገፅ 77 / ገድለ ተክለሃይማኖት ) አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቡልጋ ደብረ ጽላልሽ ወይም ዞረሬ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የሰበካ ክልል ከአባታቸው ከካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ቅድስት እግዚእ ኃረያ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው፤ በ1197 ዓ.ም ታኅሣሥ 24 ቀን ተወለዱ፡፡ በተወለዱ በሦስት ቀናቸው ከእናታቸው እቅፍ ወርደው «አሐዱ አብ ቅዱስ፣አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ» ብለው ሥላሴን አመስግነዋል፡፡ ወላጆቻቸውም ፍስሐ ጽዮን አሏቸው፡፡ ትርጓሜውም የጽዮን ተድላዋ ደስታዋ ማለት ነው፡፡ በወላጅ አባታቸው በካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብ ግብረ ዲቁናን ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ሲያጠኑ ቆይተው በአሥራ አምስት ዓመታቸው ከእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቄርሎስ /ጌርሎስ/ ዲቁናን ተቀብለዋል፡፡ -> አባታችን ከመነኮሱም በኋላ በዳዊት ጸሎት ከነቢያት ምስጋና ሌሊቱን ሙሉ ይተጉ ነበር በያንዳንዱ መዝሙርም አሥር አሥር ስግደትን ይሰግዱ ነበር፡፡  ለ22 ዓመት ቆመው በመጸለይ የአንድ እግራቸው አገዳ ተሠበረ ደቀ መዝሙሮቻቸው በጨርቅ ጠቅልለው ቀበሩት፡፡ በአንድ እግራቸው ለ7 ዓመት በጸሎት ቆሙ በጠቅላላው ለ29 ዓመት በጸሎት ከቆሙ በኋላ በ99 ዓመት ከ10 ወር ከ10 ቀን ነሐሴ 24 ቀን 1296 ዓ.ም አረፉ አባታችን ባረፉ 57 ዓመት  በ1353 ዓ.ም ለአባታችን ለአቡነ ሕዝቅያስ ተገልጸው አጽማቸው ከደብረ አስቦ ወደ ደብረ ሊባኖስ ግንቦት 12 ቀን እንዲፈልስ አድርገዋል፡፡ በረከታቸው በእኛ አድራ ትኑር

  • ​​👉ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ👈 ⚡⚡⚡ሰኞ⚡⚡⚡ 👉ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡ ⚡⚡⚡ማክሰኞ⚡⚡⚡ 👉ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29 ⚡⚡⚡ረቡዕ⚡⚡⚡ 👉አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡ ⚡⚡⚡ሐሙስ⚡⚡⚡ 👉አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡ ⚡⚡⚡ዓርብ⚡⚡⚡ 👉ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡ ⚡⚡⚡ቅዳሜ⚡⚡⚡ 👉ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡ ⚡⚡⚡እሁድ⚡⚡⚡ 👉ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡

  • #በግብረ_ሕማማት_ውስጥ_የሚገኙ_እንግዳ_ ቃላት_እና_ትርጉማቸው በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡ #ኪርያላይሶን፦ ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን»ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙ «አቤቱ ማረን»ማለት ነው፡፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ«ኤ» በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡ #ናይናን፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡ #እብኖዲ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው #ታኦስ፦ የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡ #ማስያስ፦ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው #ትስቡጣ፦ «ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው #አምነስቲቲ_ሙኪርያቱ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡ #አምንስቲቲ_ሙዓግያ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ -ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡ #አምንስቲቲ_ሙዳሱጣ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡ ✍"ጸልዩ ከመ እግዚእ አምላክነ ይምሐረነ ወይሣሃለነ ወይትወከፍ ስእለተነ ወያፈጽመነ ዛተ ሰሙነ በደኅና ወበሰላም ወያርእየነ ብርሃነ ትንሣኤሁ በፍስሐ ወበሐሴት ወይስረይ ለነ ኃጣዉኢነ" ጌታችን አምላካችን ራርቶ ይቅር ይለን ዘንድ ልመናችንንም ተቀብሎ ይችን ሳምንት በደኅናና በሰላም ያስፈጽመን ዘንድ የትንሣኤውንም ብርሃን በፍጹም ደስታ ያሳየን ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሰርይልን ዘንድ ጸልዩ" ✞በእንተ ጽንዐ ዛቲ(ግብረ ሕማማት ገፅ ፻፳፪) ----------------------------------- ኪርያላይሶን እብኖዲ ናይን ኪርያላይሶን ታኦስ ናይን ኪርያላይሶን ማስያስ ናይን ኪርያላይሶን ኢየሱስ ናይን ኪርያላይሶን ክርስቶስ ናይን ኪርያላይሶን አማኑኤል ናይን ኪርያላይሶን ትስቡጣ ናይን [በቀኝና በግራ በመቀባበል በል፡፡] "እንበለ ደዌ ወሕማም፣ እንበለ ጻማ ወድካም፣ አመ ከመ ዮም ያብጽሐነ፤ያብጻሕክሙ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም፡፡"አሜን ርትዕት ኃልዮ

  • 9 апр.473412

    የዕለተ አርብ(ስቅለት) የምንሰግድበት ፅሁፍ። ማንኛውንም ሃሳብ አስተያየት ካሎት በ @fenote_Abew_bot ያስቀምጡልን። ቤተሰብ ይሁኑ 👉TELEGRAM https://t.me/fenote_abew 👉FACEBOOK https://www.facebook.com/profile.php?id=100040602775882 👉 YOUTUBE https://www.youtube.com/@finoteabew 👉TIK TOK https://www.tiktok.com/@fenoteabew_zetewahido?_t=8mB9Wj5mAPV&_r=1

  • 5 ድረገጾች ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች በአሁኑ ሰዓት በየቤታችሁ ለተቀመጣችሁ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናን በሙሉ፥ ይህ ወቅት ከጾም እና ከጸሎት ባለፈ ጥልቅ የተመስጦ ጊዜ መሆን አለበት። ተመስጦው የእግዚአብሔርን ቃል እንደ መስታወት ተጠቅሞ ራስን ለመመልከት፥ ሕይወታችን በመገምገም አካሄዳችንን የምናቃናበት ሊሆንም ይገባዋል። ይህንን በማድረግ ሒደት ውስጥ መንፈሳዊ ትምህርትን መከታተል ሊካተት ይገባዋልና፥ የተወሰኑ የኢንተርኔት ምንጮችን ላቀብላችሁ ወደድኹ። 1. ደበሎ - ይህ ደበሎ የተሰኘ በኢንተርኔት የተዘረጋ የአብነት ትምህርት ቤት ነው። የድረ-ገጹ ባለቤቶች በሚገባ የሠሩት ገጽ ነው። ዲቁና መቀበል ለሚፈልጉ የግብረ ዲቁና ትምህርቶች በድምጽ ተጭነዋል። ከዚያ ባለፈ፥ የተለያዩ የቤተክርስቲያን መጻሕፍትን በንባብ ለመስማት ያስችላል። አንድምታም ቢሆን የየመጽሐፉ ተዘጋጅቷል። የዜማ ትምህርት ለሚፈልግም ቅዳሴ፥ ኪዳን፥ ውዳሴ ማርያም እና የተለያዩ ምስባኮች አሉ። ከመጀመሪያ አንስቶ ለመማር የምትፈልጉ በድምጽ በድምጽ በሚገባ ተዘጋጅተዋልና ብትጎበኙት ታተርፋላችሁ። አድራሻው ከታች ተቀምጧል። ድረገጽ - www.debelo.org 2. ይህንን መጽሐፍ ብላ - ይህ ድረገጽ በሚገባ ከመዘጋጀት አንጻር በጥቂቱ ከደበሎ የተሻለ ነው። ድረገጽን ስትከፍቱ ንባብ ቤት፥ ዜማ ቤት እና መፅሐፍ ቤት ተብለው ተከፍለው ታገኛላችሁ። ጀማሪ የሆነ ከንባብ ቤት ይጀምራል። በዚህም መልእክተ ዮሐንስ እና ወንጌለ ዮሐንስ በሦስቱም የንባብ አይነቶች (ግዕዝ ንባብ፥ ውርድ ንባብ፥ ቁም ንባብ) ቀርበዋል። ከዚህ ቀጥሎ የዘውትር ጸሎት፥ የሰባቱም እለት ውዳሴ ማርያም፥ መልክዐ መልክ እና የመዝሙረ ዳዊት ውርድ ንባብ ይገኛል። የብሉያትና የሐዲሳት መጻሕፍትም ንባብ በየመልኩ ቀርበዋል፤ እንደ መጽሐፈ ሲራክ፥ መጽሐፈ ሶስና፥ መጽሐፈ ባሮክ፥ ተረፈ ዳንኤል እና መጽሐፈ ሄኖክ ሳይቀሩ ንባባቸው ተካትቷል። በመቀጠል የዜማ ቤት አለ። በዚህም ማንኛውም ዓይነት ዜማ ከመጀመር በፊት የዜማ ስረይ ምልክቶች ተዘጋጅተዋል። እነዚህ ዜማውንና ምልክቶቹን በሚገባ ለማወቅ ያስችላል። በዜማ ቤቱ ውስጥም ሥርዓተ ቅዳሴ፥ ኪዳንና ሰዓታት፥ የተመረጡ የጾመ ድጓ ዜማዎች እና የዐቢይ ጾም ዜማዎች ተካትተዋል። ሦስተኛውና የመጨረሻው የመጽሐፍ ቤት ነው። በዚህም የብሉይ ኪዳን አንድምታ፥ የሐዲስ ኪዳን አንድምታ፥ የመጽሐፈ ሊቃውንት አንድምታ (ጰላዲዎስ ቄርሎስ፥ ተረፈ ቄርሎስ፥ ድርሳን ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ... ወዘተረፈ) እና የመጽሐፈ መነኮሳት አንድምታ ሁሉ በድምጽ ተዘጋጅተው ቀርበዋል። በእውነቱ አዘጋጆቹ በእጅጉ የሚያስመሰግን ሥራ ሠርተዋል፥ እግዚአብሔር አምላክ ዋጋቸውን ይክፈል። የድረገጹ አድራሻ ከታች አለ። ድረገጽ - www.eathebook.org 3. የኢኦተቤ እምነትና ሥርዓት - ይህ ድረገጽ ደግሞ ከድምጽ ይልቅ በPDF የተዘጋጁ አነስተኛ ጽሑፎችን የያዘ ነው። ጽሑፎችም የቤተክርስቲያን ታሪክ፥ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን፥ ቅዱሳት መጻሕፍት፥ ተደጋጋሚ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው፥ የዜማ መጽሐፍትና ታሪካቸው በሚል ተከፍለዋል። ዲቁና ለመቀበል ለሚፈልጉም የተዘጋጁ ትምህርቶች በድምጽ አሉ። በቁጥር ብዙ የሆኑ የቤተክርስቲያኒቷን መጻሕፍትም በPDF ማግኘት ትችላላችሁ። የድረገጹ አድራሻ ከታች አለ። ድረገጽ - www.ethiopianorthodox.org 4. ማኅበረ ቅዱሳን ሐመር ክምችት - የማኅበረ ቅዱሳን ድረገጽ በራሱ እጅግ ብዙ እውቀትን የሚያስጨብጡ ጽሑፎችን አካትቷል። የማኅበረ ቅዱሳን የሐመር መጽሔት ክምችት ግን "ራሱን የቻለ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ነው" ብዬ ብናገር ማካበድ አይሆንም። እጅግ በምናከብራቸው መምህራን በብዙ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ጽሑፎች ታገኛላችሁ። ከቻላችሁ ሁሉንም በማውረድ - ከ1985 ጀምሮ ያሉ እትሞች ይገኛሉ - ጊዜ ሰጥታችሁ አንብቡት። በእጅጉ ትጠቀማላችሁ። ድረገጹ ከሥር ይገኛል። ድረገጽ- www.hamer.eotcmk.org/no 5. Orthodox Ebooks - ይህቺን ደግሞ ለእንግሊዝኛ አንባቢዎች ልመርቅ። በውስጡ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተጻፉ እና እጅግ ብዙ ጉዳዮችን የሚዳስሱ መጽሐፍትን በሦስት አይነት(PDF, EPUB, MOBI) ታገኛላችሁ። በተለይ የብጹእ አቡነ ሺኖዳ መጻሕፍት በስፋት ይገኛሉ። ድረገጹ ከታች ይገኛል። ድረገጽ - www.orthodoxebooks.org/allbooks እንግዲህ፥ ቤት ዘግቶ መቀመጥ ካልቀረ፥ እነዚህን በመጠቀም ጊዜውን በአግባብ መጠቀም ይቻላል። |ርትዕት ኃልዮ

  • ✥ገብር ኄር✥   "መንግሥተ ሰማያት ነጋዴ ናት " -> መንግሥት ሰማያት ነጋዴ ናት ትርፍን ትፈልጋለች ስለዚህ በመጽሐፍ መንግሥት ሰማያት ብላቴኖቹን ጠርቶ ወጥተው ወርደው ያተርፉበት ዘገድ ገንዘቡን የሰጣቸውን ነጋዴ ትመስላለችና ይላል። (ማቴ ፳፭፥፲፭) -> ሹመትም ውርደቱም ፣ መጽደቅ መኮነንም በዋጋ (በጸጋ) ሳይሆን በትርፍ ነው። 5 እና 2 መክሊት የተሰጣቸው አገልጋዮች የተሾሙት በትርፋቸው እንጂ ቀድሞ የተሰጣቸውን መክሊት በማቆየታቸው አይደለም ፥ 1 መክሊት የተሰጠውም ባሪያ የተኮነነው የተሰጠውን መክሊት በማጥፋቱ አይደለም ባለማትረፉ እንጂ መክሊቱንስ አስቀምጦ ጌታው በመጣ ጊዜ መልሶለት ነበር በተሰጠው ባለማትረፉ ግን ቀድሞ የተሰጠውን መክሊት ሳያጠፋ ጠብቆ በመገኘቱ ብቻ ከመኮነን አላዳነውም። ስለዚህ ጽድቅና ኵነኔ በትርፍ መሆኑን ተረዳን። በማቴ 25 ላይም በምሳሌው የተገለጸው ይህንን የሚያስረዳ ነው ➕ ባዕል ነጋዴ ብሎ ጌታን (መንግሥተ ሰማያት) ፣ አግብርት ብሎ መምሕራንን ካህናትን ማምጣት ነው። -> ባለ ፭. ፪ትም የተባሉት ፍጹም ትምህርት ተምረው መክረው አስተምረው ራሳቸውን አስመስለው ያወጡ መምህራን ናቸው:: ጴጥሮስ ቀሌምንጦስን፣ ጳውሎስ ጢሞቴዎስን እንዳወጡ፡፡ - እነዚህ መምህራን በትምህት የሚወልዱ በመሆናቸው ብዙ ተባዙ ያለውን ቃል የፈጸሙ ናቸው -> ባለ ፩ የተባለ ተምሮ ሳያስተምር የቀረ ነው:: ዐላውያን እሳት ስለት አሳይተው ቢያስክዱኝ፣ መናፍቃን ተከራክረው ምላሽ ቢያሳጡኝ ብሎ፤ ሃይማኖቱን በልቡ የያዘ ነው::  - ይህን ባሪያ የመሰሉ በትምህርት የማይወልዱ የጋን መብራቶች ሜልኮላውን ናቸው።  ይህም በአባ መልክአ ክርስቶስ ታውቋል ። ፍጹም ትምርት ተምረው ሳለ ሳያስተምሩ ቀርተዋል በተባሕትዎ መላ ዘመናቸውን ፈጽመውታል ። በሚሞቱበት ጊዜ መልአክ ገሠጻቸው ። ቀለሙ አካል እየገዛ ሲወጣ ታይቷል ። -> ጸጋ ስጦታ ነው መመስገኛም መወቀሻም የሚሆነው ግን በተሰጠ ጸጋ በሚሠሩት ሥራ እና ባለ መሥራት ነው። የነጋዴ ጥቅሙ በትርፍ እንደሆነ ሰው መሾም መሻሩ ፥ መጽደቅ መኮነኑ በተሰጠው ጸጋ ሌላው ምዕመናን ትርፉ በማድረጉ ነው። - በምሳሌውም " ላለው ይጨመርለታል " ያለው ጸጋ ላለው ጸጋ ይጨመርለታል ማለቱ ሳይሆን በተሰጠው ጸጋ ትርፍ ያለው ሰው ሌላ ያተርፍ ዘንድ ጸጋ ይጨመርለታል ማለት ነው " ለሌለው ግን ያለውን ይወሰድባታል " ማለቱም ትርፍ ለሌለው ግን እንኳንስ ሌላ ጸጋ ሊሰጠው ቀርቶ ቀድሞ የተሰጠው ጸጋ ይወስድበታል ማለቱ ነው። - ስለዚህ መንግሥተ ሰማያት ነጋዴ ናት ያተረፉ የሚገቡበት የትሩፋን ሀገር ናት። -> መዝሙር ዘገብርኄር ፦ መኑ ውእቱ ገብርኄር ወምዕመን -> ምንባብ ዘቅዳሴ - 2ጢሞ 2÷1-16 - 1ጴጥ 5-1-12 - ግ.ሐዋ 1፥6-9 -> ምስባክ ፦ " ከመ እንግር ፈቃደከ መከርኩ አምላኪየ ወሕግከኒ በማዕከለ ከርሥየ ዜኖኩ ጽድቀከ በማኅበር 0ቢይ "  መዝ 39፥8 -> ወንጌል :- ማቴ 25÷14-31 -> ቅዳሴ :-  ዘባስልዮስ

  • ✥✥✥ በዐለ ደብረዘይት ✥✥✥ ትርጉሙ፦ ደበረ ዘይት ትርጉሙ የወይራ መብቀያ፣ በወይራ ደን የተሸፈነ ተራራ ማለት ነው። ወይም «ደብር» ማለት «ተራራ» ማለት ሲሆን «ዘይት» ማለት ደግሞ «ወይራ» ማለት ነው። በተገናኝ «ደብረ ዘይት» ማለት የወይራ ዛፍ የሞላበት፣ የበዛበት፣ የወይራ ተራራ ማለት ይሆናል። -  ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ የሚገኝ ቦታ የሚገኝ ተራራ ሲሆን በመካከል የቄድሮን ሸለቆ ብቻ ነው ያለው። ከግርጌው ጌቴ ሴማኒ የተባለው የአትክልት ስፍራ ይገኛል። የጸሎተ ሐሙስ ማታ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተያዘበትና በኋላም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ሥጋዋ ያረፈበት ወይም የድንግል መካነ መቃብር በዚህ ተራራ ግርጌ ይገኛል። ቤተ ፋጌ እና ቢታንያ በኮረብታው ጫፍ እና በምስራቅ ዳገታ ላይ ይገኛሉ። -      ይህ ተራራ በመፅሐፍ ቅዱስ የሚገኙ ብዙ ድርጊቶች የተደረጉበት ቦታ ነው። ጌታችን ስለ ቤተ መቅደሱ መፍረስ፣ ስለ ዓለም ፍጻሜና ስለ ዳግም ምጽአት በዚህ ተራራ ላይ በትንቢት መልክ ተናገረ (ማቴ.24፥3)። በዚሁ ተራራ ላይ ወደ ሰማይ ዐረገ (ሉቃ.24፥50)። በዚሁ ተራራ ላይ ቀን በከታማና በገጠር ሲያስተምር ውሎ ሌሊት የሚያድርበት የኤሌዎን ዋሻ ይገኛል። በኋለኛው ምጽአቱ በዚሁ ቦታ እንደሚገለጥ ትንቢትተነግሯል።(ዘካ. 14፥3-5)። -   ስያሜው፦ የ0ቢይ ጾም እኩሌታ ላይ ያለው ሰንበት በዚህ ተራራ ተጠርቷል። ይህንን ዕለት የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ያሬድ የዳግም ምጽአት አድርጎ መዝሙሩን ጽፏል። በዚህ ተራራ ላይ «እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው። ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት» (ማቴ.24፥3)። ተብሎ እንደተጻፈው ለደቀ መዛሙርቱ የደግም ምጻቱን፣ የዓለምን ፈጻሜ፣ የትንሣኤ ሙታንን፣ ትምህርት በሰፊው ስላስተማረ በዓሉ በተራራው ስም ተሰይሟል። ➕  አመጣጡስ እንዴት ነው? -  ጌታ ይህንን ዓለም ለማሳለፍ ለሁሉም እንደ ሥራው ለመክፈል በግርማ መለኮቱ በክበበ ትስብዕቱ ይመጣል፡፡ ጊዜው ዘመነ ዮሐንስ ወርኃ መጋቢት ዕለተ እሑድ መንፈቀ ሌሊት እንደሆነ ሊቃውንት ተናግረዋል፡፡ ምነው ‹‹ የሚያውቀው የለም ይል የለምን ቢሉ እውነት ነው የሚያውቀው የለም ብዙ የዮሓንስ ዘመን ብዙ የመጋቢት ወር ብዙ የእሑድ ዕለት የበዙ ሌሊቶች አሉና ለይቶ የሚያውቅ የለም ለማለት ነው፡፡ ->  ሞት ለማንም ኣይቀርምና ሁሉም ይሞታል፡፡ ዘፍ 3፡19 በዕለተ ምጽኣትም ቅዱስ ገብርኤል ስምንቱን ነፋሳተ መዓት ከየመዛግብታቸው ያወጣቸዋል፡፡ ዛፍን ነቅለው ድንጊያውን ፈንቅለው ምድርን እንደብራና ይዳምጧታል፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ነጋሪቱን ይመታል ፩ኛመቃብ ፱፥፰ ነጋሪት የተባለው በቁሙ ነጋሪት የሚመታ ሆኖ ሳይሆን አዋጁን የምትክ ንቃ የሚል አዋጅ የሚናገር ይታወጃልና ነጋሪት ይመታል አለ . ስለዚህ ቅዱስ እግዚኣብሔር ቅዱስ ዘያነቅሖሙ ለሙታን ሲል በዱር በገደል በባህር በየብስ በመቃብር ውስጥ ያሉት በአውሬ ሆድ ውስጥ ያሉ ሁሉ ይሰበሰባሉ፡፡ .  በሁለተኛው ነጋሪት ሲመታ አጥንትና ሥጋ አንድ ሆነው ፍጹም እንደ ዕለት በድን ይሆናሉ፡፡ .  ሦስተኛው ነጋሪቱን መትቶ /ቅዱስ እግዚኣብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ህያው ዘኢይመውት / ንቃሕ መዋቲ ዘትነውም ባለ ጊዜ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ደጉ ደግነቱን ክፉውም ክፋቱን ይዞ ይነሳል፡፡ -  ወንዱ የ30 ዓመት ሴቲቱ የ15 ዓመት ሆነው ጻድቃን ብርሃን ለብሰው ብርሃን ተጎናጽፈው ከፀሐይ 7 እጅ አብርተው ማቴ 13፡43 ኃጥአን ጨለማ ለብሰው ፍጹም ዲያብሎስን መስለው ይነሳሉ፡፡  ጻድቃን ስለሠሩት መልካም ሥራ ኑ የኣባቴ ብሩካን ብሎ መንግሥተ ሰማያትን ያወርሳቸዋል፡፡ ኃጥኣንን ስለክፋ ሥራቸው /ከኔ ሂዱ/ ብሎ ገሃነም ይሰዳቸዋል፡፡ ጻድቃን ደስ ይላቸዋል ኃጥአን ግን ያዝናሉ ዋይ ዋይ እያሉ ደረት ይደቃሉ እንባቸውን ያፈሳሉ፡፡ የማይጠቅም ልቅሶ የማይረባ ኃዘን ነው ሰቅለው የገደሉትም አይሁድ ክብሩን 0ይተው ላይጠቀሙ ይጸጸታሉ፡፡ - በዳግም ምጽአቱ ጊዜ ከቅዱሳኑና ከሰማዕታቱ ጋር ለመቆም ያብቃን፡፡🤲 -> መዝሙር ዘደብረ ዘይት እንዘ ይነብር እግዚእነ ወስተ ደብረ ዘይት ይባላል -> ምንባብ ዘቅዳሴ - 1ተሰሎ 4÷13-ፍም:: - 2ጴጥ 3÷7-15:: - ግሐዋ 24÷1-22 -> ምስባክ " እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመፅእ፣ ወአምላክነሂ ኢያረምም እሳት ይነድድ ቅድሜህ" መዝ 49÷2 -> ወንጌል፦ ማቴ፡ 24÷1-36 -> ቅዳሴ አትናቴዎስ

  • #መጻጒዕ -> የ0ቢይ ጾም አራተኛ ሣምንት መጻጕዕ ይባላል። -> ፀግ0 ፤መጸጕዕ ፦ በቁሙ ጎባጣ በጀርባው ላይ እንደ ሻኛ ያለው ደረቱ ከጉልበቱ የተጠጋ ሕመምተኛ በሽተኛ ማለት ነው። -> በዚህ ሣምንተ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያንን መፈወሱን ዕውራንን ማብራቱን የሚያነሳ መዝሙር ይዘመርበታል፡: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለጌትነቱ ምልክት በሕዝቡ ያሉ ድውያንን ሁሉ ይፈውስ ነበር፡። የተአምራቱም ዜና በሶርያ በአራቱ ማዕዘን ደረሰ ተብሎ በተነገረው መሠረት ቅዱስ ማቴዎስ 4፥23-25 አንደጻፈው ቀጥለን እናያለን በማቴ 8 ፥1-4 ከተራራ በወረደ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት ለምጻም ቀርቦ ጌታ ብትወድስ ልታነፃኝ ትችላለህ እያለ ሰገደለት እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና ንፃ አለው ወዲያውም ለምፁ ነፃ - በምዕ 8፥5-13 የመቶ አለቃውን ልጅ በቃሉ ፈወሰ፣ የጴጥሮስ አማት ከንዳድ ፈወሳት - በምዕ 8 ፥14 አጋንንት አወጣ በምዕ 8፥16ና በ8፥28 በዚህ ተአምራት የምንረዳው ቁም ነገር ሰስዎች ያደሩ አጋንንት ክርስቶስን የእግዚአብሔር ልጅ ብለው ማመናቸውን ነው:: የሐዋ 19÷15:: ያዕ 2÷19:: ->    ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የፈወሳቸው ህሙማን ብዙ ሲሆኑ ለምሳሌ ያህል ከላይ በጠቀስነው በማቴዎስ ምዕራፍ 8 ያሉትን እንዳዳነ ሁሉ በሌሎች ወንጌላውያን ምዕራፍና ቁጥርም በርካታ በሽተኞችን እንደፈወሰ ተገልጿል ከተፈወሱት ሰዎች መካከል የኻያ ሦስቱ ታሪክ ተገልጦአል ከእነርሱ ሌላ ኢየሱስ ሦስት ሙታንን አስነስቶአል አንደኛ የኢያኢሮስን ሴት ልጅ (ማቴ 9፥18-26) ሁለተኛ የመበለቲቱን ልጅ ፈወሳት (ሉቃ 7÷11-17) ሦስተኛውም ደግሞ አልዓዛር (ዮሐ 11፥43-44)፡፡ -> ክርስቶስ በአምስት አይነት መንገድ ህሙማን ፈወሰ 1- በቃሉ (ማቴ8፥16፡፡ ዮሐ 4÷50) 2- በመዳሰስ (ማቴ 8፥} ፣ ሉቃ 5÷13) 3- እጅ በመጫን(ማር 6፥5፣ 8፦22) 4- ጭቃን በመቀባት (ዮሐ 9÷6-7) 5- በልብሱ ጫፍ (ማቴ9፥20፡፡ 14፥36) -> እግዚአብሔር ፈዋሽ ነው (ዘጸ 15፥26) ፈዋሽነቱ ለሁሉ ቢሆንም በሰፊው የሚነገረው ግን በዮሐ 5÷5-15 ያለ በሽተኛ ነው:: ይኸውም ኋላ ጌታችን ኢየሱስን በጥፊ የመታው ነው ብለው ሊቃውንት ይተረጉማሉ (ዮሐ 18፥22):: ➕ መዝሙር ዘመፃጉዕ አምላኩስ ለአዳም ➕ ምንባብ ዘቅዳሴ - ገላ 5፥1-ፍም:: - ያዕ 5፥14-ፍም:: - ግሐዋ 3÷1-12 ➕ "ምስባክ እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ አራተ ሕማሙ ወያመይጥ ሎቱ ኩሎ ምስካቤሁ እምደዌሁ አንዕ እቤ እግዚኦ ተስሐለኒ " (መዝ 40፥3) ➕ ወንጌል ዮሐ 5÷1-25 ➕ ቅዳሴ ዘእግዚእነ (ነአኩተከ)

  • +++አበው ስለ ጾም እንዲህ አስተማሩ!+++ + ‹‹አንድ ንጉሥ የጠላቶቹን ከተማ በቀላሉ መያዝ ከፈለገ ፤ “የከተማይቱን ውኃ እና ምግብ አቅርቦት ያቋርጠዋል” ፤ ጠላቶቹ በረኃብ እየሞቱ ራሳቸውን ለእርሱ አሳልፈው ይሠጡታልና፡፡ የሥጋም ፈተና እንዲሁ ነው ፤ አንድ ሰው የሚጾም ከሆነ የነፍሱ ጠላቶች ተርበው ይደክማሉ፡፡›› (ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር) [1] + ‹‹ጾም የሥራ መጀመሪያ ናት ፤ የጽሙዳን ክብራቸው ናት ፤ የድንግልና የንጽሕና ጌጣቸው ናት ፤ የንጽሕና መገለጫ ናት ፤ የወንጌል ሥራ መጀመሪያ ናት ፤ የጸሎት ምክንያት ናት ፤ የዕንባ መገኛ ናት ፤ አርምሞን የምታስተምር ናት ፤ ለበጎ ሥራ ሁሉ ታነቃቃለች፡፡›› (ማር ይስሐቅ) [2] + የድኆች ወዳጅ የተሰኘው አባ አብርሃም( 1829-1914) ዋናው ምግቡ ባቄላ እና ሽንብራ ነው፡፡ በአንድ ወቅት ዶሮ መብላት አማረውና ፤ ደቀ መዛሙርቱን ዶሮ ሠርተው እንዲያመጡለት አዘዛቸው፡፡ ምግቡን ሠርተው ሲያቀርቡለት ጸሎት አደረገበትና ፤ ደቀ መዛሙርቱን እንዲያነሡትና ነገ መልሰው እንዲያቀርቡለት አዘዛቸው፡፡ በሁለተኛው ቀን በሦስተኛውም ይህንኑ ትእዛዝ አዘዛቸው፡፡ በአራተኛው ቀን የተሠራው ምግብ ተበላሽቶ ነበር ፤ አባ አብርሃም ምግቡን እየተመለከተ ፤ “ሰውነቴ ሆይ አሁን የፈለግኽውን ብላ” አለ፡፡ [3] + ቅዱስ እንጦንስ እንዲህ አለ፡- በአንድ ወቅት እየጾምሁ ሳለሁ ፤ ሰይጣን እንደ መነኩሴ ለብሶ ፤ ብዙ ዳቦ ይዞ ወደ እኔ ቀረበ ፤ “ብላ ብዙ መድከምን ተው ፤ ብዙ ድካምን የሚያበዛ ሰው ይታመማል” አለኝ ፡፡ እኔም የተንኮል አሠራሩን ተረድቼ ተነሥቼ ጸሎቴን ጀመርኹኝ ፤ ጸሎቱን መቋቋም ሲከብደው እንደ ጢስ በንኖ በበሩ ሲወጣ ታየኝ፡፡ [4] + ‹‹የሚመስለው የሌለ አስደናቂውን የብርሃን ጸዳል እናይ ዘንድ ዐይኖቻችንን ወደ ላይ እናንሣ ፤ ይኽ የእኛ አካል ያለበትን እንመለከት ዘንድ እንደ ንሥር ክንፎቻችንን እናንሣ ፤ ለንጉሡ እጅ መንሻ ይሆን ዘንድ የተወደዱ ፍሬዎች ጾምና ጸሎትን እናዘጋጅ፡፡›› (ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ) [5] + ኃይለኛ መድኃኒት መርዘኛ ፍጥረታትን ነቅሎ እንደሚያወጣ ፤ ከጾም ጋር የተባበረ ጸሎትም ክፉ ሀሳቦችን ነቅሎ ይጥላል፡፡ (እማሆይ ሲንቅለጢቃ) [6] +++

  • ✥ ዘወረደ ✥ -> የ0ቢይ ጾም የመጀመሪያው እሁድ (ሳምንት ) ዘወረደ ይባላል። ->ጌታችን እኛን ለማዳን ከሰማይ መውረዱን የሚነገርበት ሳምንት በመሆኑ ዘወረደ ተብሏል። -> ከሰማይ ወረደ ማለት እርሱ የሌለበት ኖሮ ካለበት ወደዚህ መጣ ማለት አይደለም እርሱስ ጽርሐ አርያም ምጥቀቱ በርባኖስ ጥልቀቱ ፥ አድማስ ናጌብ ስፋቱ ተብሎ የማይነገርበት በዓለም ሙሉዕ ነውና ዓለማትን ቢወስን እንጂ ዓለማት እርሱን አይወስኑትም ።   -> የፀሐይ ብርሃን ከክበቡ ሳይለይ ከ0ይናችን ብሌን ጋር እንደሚዋሓድ ወልደም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ሳይለይ በምልዓቱ መወሰን ሳይኖርበት በሥጋ ማርያም መገለጹን ሰው መሆኑን ያስረዳል :: -> ከሰማይ ወረደ ሲባል ስንሰማ መረዳት የሚገባን 1- "ሰማይ" ያለው ዕበዩን፣ ክብሩን ፣ ልዕልናውን ፣ ጌትነቱን፣ መንግሥቱን ፣ ርቀቱን .... ነው :: ስለዚህ ከሰማይ ወረደ ማለት የባሪያውን መልክ ይዞ ሰው መሆኑን ለመግለጽ ነው። (ፊል 2፥6-8) ->   ሰው ሆኖ መፈጠር ታላቅ ክብር ነው ለአምላክ ግን ሰው መሆኑ ተዋርዶ ነውና ይልቁንም እኛን ለማዳን በለበሰው ሥጋ መራብ መጠማቱ ፣ መገረፍ መታመሙ ... እንኳን ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ይቅርና ከመላእክት እንኳን ያነሰበት ነው መላእክት በባህሪያቸው መራብ መጠማት፣ መታመም የለባቸውምና " ከመላእክት እንኳን አሳነስከው " ያለውም ስለዚህ ነው ። (መዝ 8፥5 / ዕብ 2፥7) ->  ይህ ማለት ግን ወልድ ሰው መሆኑ አምላክነቱን አጥቶ በዚህም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ አነሰ ማለት አይደለም ጌታችንም "አብ ይበልጠኛል" ያለው በለበሰው ሥጋ ባገኘው መራብ መጠማት አነሰ ለማለት ነው አብ እና መንፈስ ቅዱስ ሰው ሆነው መራብ መጠማት ... ያላገኛቸው መሆኑን ለመግለጽ ነው። (ዮሐ.14፥28) 2- መጣ ወረደ መባሉ የሰው ልጅ በበደሉ ምክንያት ከአምላክ ምን ያህል ርቆ ኮብልሎ እንደነበር ተረዳ ስለዚህ የጠፋን እኛን ለመፈለግ የራቅነውን ወደርሱ ለማቅረብ መጥቷልና ዘወረደ ተባለ። (ሉቃ 15 ) 3- የፍጥረት ጥንቱ መጸነሱ ነው ፥ የጌታችን ጥንቱ ግን ከማርያም ከተጸነሰ ወዲህ አይደለምና ዘወረደ የሚለው የጌታንን ቅድምናውን ያስረዳል። -> ፎጢኖስ የተባለ መናፍቅ የወልድ ሕልውና ከማርያም ከተወለደ ወዲህ ነው (ለፌ እም ማርያም ) የሚል ነበር በቅዱስ መጽሐፍ ግን ስለ ወልድ ሕልውና ከማርያም በፊት ጥንት በማይነገርበት መጀመሪያ መሆኑን ያስረዱናል እነዚህ ማስረጃ ያድርጉ👇 - ዮሐ 1፥1 " በመጀመሪያ ቃል ነበረ.. " - ዮሐ 8 " እውነት እውነት እላችዃለኹ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለኹ " - ዮሐ 17 " አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር ባንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ። " -> ቅዱስ ያሬድ ጾመ ድጓውን ሲጀምር  " ሃሌ ሃሌ ሉያ ዘወረደ እም ላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ ወሚመ ኢያእመሩ እግዚአ ኩሉ ዘየሃዩ በቃሉ / ከሰማየ ሰማያት የወረደ አይሁድ የሰቀሉት ሁሉን በቃሉ እንደሚያድን አይሁድ ያላወቁት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው " በማለት ሰው ሆኖ በአይሁድ ተዋርዶ ያገኘው መሆኑን የዚህን ሳምንት ጠቅላላ ሀሣብ ይገልጻል። ➕ የዘወረደ የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ) ሃሌ ሉያ ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት በፍርሃት ወተኃሠዩ ሎቱ በረዓድ፤ /መዝ.፪፥፲፩/ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ፤ ባኡ ቅድሜሁ በተጋንዮ ወውስተ አዕጻዲሁ በስብሐት እመንዎ፤ /መዝ.፺፫፥፫-፭/ እስመ … ንጹም ጾመ ወናፈቅር ቢጸነ ፥ ወንትፋቀር በበይናቲነ፤ እስመ … አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ እስመ ሰንበትሰ በእንተ ሰብእ ተፈጥረት፤/ማቴ.፲፪፥፰/ እስመ … ምሕረተ ወፍትሐ አሀሊ ለከ እዜምር ወእሌቡ ፍኖተ ንጹሐ፤ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ አባግዓ መርዔቱ፨ ትርጕም፤ እግዚአብሔርን በመፍራት ተገዙለት፤ ለእርሱ መገዛትም ደስ ያሰኛችሁ፡፡ እግዚአብሔር ቸር ምሕረቱም ለዘለዓለም፣ እውነቱም ለልጅ ልጅ ነው፡፡ እኛስ ሕዝቡ የመሰማርያው በጎች ነን፡፡ ወደ ደጁ በመገዛት፤ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፤ ጾምን እንጹም፤ ጓደኞቻችንን እናፍቅር፤ እርስ በርሳችንም እንፋቀር፡፡ ሰንበት ስለሰው ተሠርታለችና፤ ሰንበትን እናክብር፡፡ እውነትንም እንሥራ፤ አቤቱ ምሕረትንና ፍርድን እቀኝልሃለሁ፤ እዘምራለሁ፤ ንጹሕ መንገድንም አስተውላለሁ፡፡ ➕ የዘወረደ ምስባክ (መዝ. 2፥11 ) " ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ። አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዐፅ እግዚአብሔር። ትርጉም፦ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፥ በረዓድም ደስ ይበላችሁ። ጥበብን አጽኑአት ፤ እግዚአብሔር እንዳይቆጣ። "

  • #ቀጸላ_መንግሥቱ_ለጊዮርጊስ በማኅሌተ ጽጌ ቁመት በየሳምንቱ አዲስ ቃለ እግዚአብሔር የሚደርስ ሲሆን ነገር ግን በሁሉም ሳምንታት ዘወትር እንዘ ተሐቅፊዮ እና ክበበ ጌራ ወርቅ ይባላል። -> አባ ጽጌ ድንግል እመቤታችንን ከሰማዕቱ ጊዮርጊስ ጋር በምሥጢር አገናኝቷቸዋል :- " ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እም ዕንቊ ባሕርይ ዘየሐቱ ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ ወለክኒ ይሰግድ ውእቱ ፤ የስሙና የሞቱ መታሰቢያ በአንቺ የተጻፈብሽ የሚያበራ ከሆነ ዕንቍ ባሕርይ ይልቅ የጠራ ወርቅ ክበብ ያለው የራስ ቍር የተባለ የጊዮርጊስ የመንግሥቱ የራስ ልብስ ጌጥ ሽልማት የአበባ አክሊል ማሪያም ሆይ አንቺ ለርሱ ሁሉን ታንበረክኪለታለሽ እርሱ ግን ለአንቺ ይሰግዳል " (አባ ጽጌ ድንግል) -> አባ ጽጌ ድንግል ይህንን ቃል የወሰደው ከሰማዕቱ ከዜና ገድሉ ነው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሰባ ነገሥታት ጋር ለሰባት 0መት ተጋድሎ ሲያበቃ ሰማዕትነት በተቀበለ ጊዜ ከአንገቱ ደም ውሃ ወተት ፈሰሰ ጌታችንም ለሰማዕቱ " ወአልበሶ ልብሰ ብርሃን ... ወአስተቀፀሎ በጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘልቡጥ በአዕናቊ ባሕርይ ፤ በዕንቊ ባሕርይ ያጌጡ ከጽሩይ ወርቅ የተሠሩ መከራ በተቀበለባቸው ሰባት ዐመታት ልክ ከዕፀ ሕይወት አበቦች የተሠሩ አክሊሎች ያሉበት ዘውድን አቀናጀው" ያለውን ነው ሊቁ ጽጌ ድንግል የወሰደው። 1- ፍልስተ ሥጋው ከፍልስተ ሥጋው ጋር የተገናኘለት በመሆኑ ፦ -> በዚችም ዕለት ዳግመኛ የሰማዕታት አለቃ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥጋው ከፋርስ አገር ወደ አገሩ ልዳ በክብር የፈለሰበት ነው። የሥጋውም ፍልሰት ከእመቤታችን ድንግል ማርያም የሥጋ ፍልሰት ጋር አንድ ሁኗልና ስለዚህም እርሷን መውደዱ የሚያውቁ ሥዕሉን ከሥዕሏ አጠገብ ይሥላሉ በስሙ ለሚማፀኑ የድኅነት ወደብ ይሆን ዘንድ። በፍልሰትኪ ድንግል ዘተቶስሐ ፍልሰተ ዐፅሙ። እንዘ ይብል ሶበ ጸለየ ኀቤሃ ቀዲሙ። ምስለ ፍልሰትኪ ደምርኒ እሙ።" እንዲል።  (አርኬ ፦ መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ ፲፮)። 2 - ትምእርተ ስሙ ማር ጊዮርጊስ ማር ማለት በሶሪያ ቋንቋ ቅዱስ ማለት ነው ለሴት ማርት ሲሆን ቅድስት ማለት ነው። ስለዚህ ማር ጊዮርጊስ ሲል ቅዱስ ጊዮርጊስ ማለት ሲሆን ማር የሚለው ስሙ ከእርስዋ ማርያም ከሚለው ስም በሁለቱ ፊደል ተሳትፏልና ትምእርተ ስሙ ስለሆነችለት "ሰላም ለጊዮርጊስ ተውላጠ ፃማሁ ወሕማሙ። እንተ ተለዓለ ሞገሰ ስሙ። " አለ 3- ዜና ገድሉ እንደሚነግረን ሰማዕቱ ሦስት ጊዜ ሞቶ ተነስቶ በአራተኛው ሞቱ ሕይወተ ሥጋው ተፈጽሞ አክሊል ተቀናጅቷል፤ በዚህም አራት ፊደል ካለው "ማርያም" ከተባለው ስሟ ጋር ተገናኝቶለታልና የስሙ እና የሞቱ መታሰቢያ ከእርሷ ተሰማምቶለታልና ሊቁ "የስሙና የሞቱ መታሰቢያ በአንቺ የተጻፈብሽ " አለ። -> እመቤታች በደብረ ምጥማቅ በምትገለጽ ጊዜ ከሁሉ ሰማዕታት ቀድሞ መጥቶ ከፈረሱ ወርዶ የሚሰግድላት ሰማዕቱ ነው እርሱ ሰግዶ በተነሳ ጊዜ ሌሎች ደግሞ ለእርሱ ይሰግዱለታልና ሊቁ  " አንቺ ለርሱ ሁሉን ታንበረክኪለታለሽ እርሱ ግን ለአንቺ ይሰግዳል " አለ ። -> ዳግመኛም ቅዱስ ጊዮርጊስን ያንገላታ የነበረው ንጉሥ ዱድያኖስ ንግሥት እለስክንድርያ የምትባል ሚስት ነበረችው። መሳፍንቱና መኳንንቱ ኹሉ ለእርሷ ይሰግዱ ነበር። በሰማዕቱ ትምህርት አምና ለቅዱስ ጊዮርጊስ የፀጋ ስግደትን ሰገደችለት። በዚህም ምክንያት በሚያዝያ 15 አንገቷን በሰይፍ እንድትቆረጥ ተደርጋለች። ያቺ ሣር ቅጠሉ ኹሉ ይሰግድላት የነበረች ንግሥት ለቅዱስ ጊዮርጊስ መስገዷን ያስተዋለው ሊቁ ግን በማኅሌተ ጽጌው "አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ - አንቺ ለእርሱ ኹሉን ታሰግጂለታለሽ" ሲል በእመቤታችንና በሰማዕቱ ምስጋና ላይ ዘከራት። ይቆየን ማንኛውንም ሃሳብ አስተያየት ካሎት በ @fenote_Abew_bot ያስቀምጡልን። ቤተሰብ ይሁኑ 👉TELEGRAM https://t.me/fenote_abew 👉FACEBOOK https://www.facebook.com/profile.php?id=100040602775882 👉 YOUTUBE https://www.youtube.com/@finoteabew 👉TIK TOK https://www.tiktok.com/@fenoteabew_zetewahido?_t=8mB9Wj5mAPV&_r=1

  • ✥✥✥ ቅድስት አርሴማ ✥✥✥ 👉    ጥር 6 ልደቷ፣ መስከረም 29 እረፍቷ፣ ታህሳስ 6 ፍልሰተ አጽሟ ይታሰባል። ✥     እናታችን ከአባቷ ከቅዱስ ቴዎድሮስና ከእናቷ ቅድስት አትናሲያ በስዕለት ተወለደች ። ቤተሰቦቿ እግዚኣብሔርን በቅንነት ያገለግሉ ከነበሩ ከከበሩ ካህናት ወገን እንደነበሩ የገድሏ መጽሓፍ ይነግረናል ። ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ቅዱሳት መጻሕፍትን ከቤተሰቦቿ በሚገባ የተማረች፤ የተማረችውንም በተግባር የተረጎመች፤ በጸሎት ሕይወት የምትተጋ ከቅዱሳት አንስት አንዷ ናት ። ✥     ቅድስት ኣርሴማ ፣ ሂርፕሲም (አርሜኒያዊት) እንዲሁም ሪሂፕሲም ፣ ሪፕሲም ፣ አርብሲማ ወይም ኣርሴማ ተብላ ትጠራለች። የትውልድ ሃገሯ ሮም ። እርሷ እና ባልደረቦችዋ የሰማዕትነት አክሊል በተቀዳጁበት አርሜንያ የመጀመሪያዎቹ የአርሜንያ ሰማዕታት እንደሆኑ ተደርገው ይታያሉ ። 👉     የሕይወት ታሪኳን ሊቃውንት በቅዳሴ አንድምታ ላይ የመዘገቡትን እነሆ፦ ዲዮቅልጥያኖስ መልከ መልካም ብላቴና ፈልጋችሁ ሥዕሏን ሥላችሁ አምጡልኝ ከዚያ በኋላ እሷን ታመጡልኝአላችሁ ብሎ ሠራዊቱን በያገሩ ሰደደ፤ ይህች አርሴማ ፸፪ (72) ያህል ደናግል ይዛ ከተራራ ላይ ወጥታ ተቀምጣለች፤ ኸያ ዓራቱ ደናግል፤ የቀሩት መዓስባን(ያገቡ) ናቸው፡፡ ✥      እመ ምኔቲቱ አጋታ (Agatha(Ghana)) ትባላለች፡፡ እየፈለጉ ካለችበት ደረሱ፡፡ ሥዕሏን ሥለው ወስደው ሰጡት፡፡ መልካም ብላቴና አግኝታችሁልኛል፤ እስዋን አምጡልኝ አላቸው፡፡ እስዋም እንዳስፈለጋት አውቃ አርማንያ ወረደች፡፡ ✥      እሱም ከዚያ እንደ ወረደች አውቆ የአርማንያ ንጉሥ ድርጣድስ ይባላል፤ እንዲህ ያለች ብላቴና ወዳገርህ መጥታለችና አስፈልገህ ስደድልኝ ብሎ ላከበት፡፡ ቢያስፈልግ አገኛት፤ ቢያያት እንደ ፀሐይ ስታበራ ዓያት፤ ይህችንማ ለራሴ ምን ይዤ ለሱ እሰድለታለሁ ብሎ እመ ምኔቲቱን/አጋታን/፦ ይህችን ብላቴና ለምኝልኝ ኣላት፡፡ አይሆንም ያልሁ እንደሆነ ነገር አጸናለሁ ብላ ይሁን አለችው፡፡ ኋላ ግን ለሰማያዊ መርዓዊ ለክርስቶስ አጭቸሻለሁና ይህ ርኩስ እዳያረክስሽ እወቂ አለቻት። ✥     ብላቴኖች ሰዶ አስወስዶ መልኳን አይቶ ብታምረው ተራምዶ ያዛት፤ ኃይል መንፈሳዊ ተሰጥቷታልና ጎትታ ከመሬት ወቃችው፡፡ ንጉሥ ነውና ቢያፍር በሰይፍ አስመታት፡፡ ከዚያ አያይዞ መላውን አስፈጅቷቸዋል፡፡ ሰይጣን አስቀድሞ ያልሆነ ስራ ማሰራት ኋላ ማጸጸት ልማዱ ነውና መልኳ ትዝ እያለው እህል ውሃ የማይቀምስ ሆነ፡፡ ✥      ብላቴኖቹ ሲሞት እናያለን? ኣደን እንጂ ኃዘን ያስረሳል፤ ኣደን ይዘነው እንሂድ ብለው ይዘውት ሄዱ፡፡ በዚያ ባለበት ዕሪያ ሁኖ ቀርቷል፡፡ ማን ባዳነልን እያሉ ሲጨነቁ መልኣክ ለእኅቱ ከጎርጎርዮስ በቀር የሚያድንላችሁ የለም አላት፡፡ በሃይማኖት ምክንያት ተጻልቶት ከአዘቅተ ኲስሕ አስጥሎት ነበርና የሞተ መስሏቸው ደነገጡ፡፡ ✥    /ለቅዱስ ጎርጎርዮስ ግን/   መልኣክ ላንዲት መበለት ነግሮለት አንድ ፥ አንድ እንኩርኩሪት እየጣለችለት ፲፭ (15) ዓመት ያህል ኑሯል፡፡ የኒህ ክርስቲያን አምላክ ጽኑ እንጂ ነው እንዳለ ብለው ገመድ ቢጥሉ መኖሩን ለማስታወቅ ገመዱን ወዘወዘው ሐብሉን ቢስቡት ከሰል መስሎ ወጥቷል፡፡ ✥   ወንድሜን አድንልኝ ኣለችው፡፡ ያለበትን ታውቂውአለሽን አላት፡፡ አዎን አለችው፡፡ አስቀድሞ አጽመ ሰማዕታት ያለበትን ኣሳይኝ ብሏት አሳየችው፡፡ አጽመ ሰማዕታትን አስቀብሮ በዪ ውሰጂኝ አላት፡፡ ይዛው ሄደች፡፡ አንተ ባድንህ በፈጣሪዬ ታምናለህን አለው፡፡ ወኣድነነ ርእሶ ወኣንገሥገሠ ርእሶ ከመ ኦሆ ዘይብል ይላል፡፡ ግዕዛኑን(አዕምሮውን) አልነሣውም ነበርና ይሁን አለው፡፡ እንዳይታበይ ከእጁ ከእግሩ የእርያ ምልክት ትቶለት ጸልዮ አድኖታል፡፡ አስተማረው ኦሳመነው አጥምቀኝ አለው፡፡ ማጥመቅስ ሥልጣን ካላቸው ሂደህ ተጠመቅ፤ ለኔ ስልጣን የለኝም ኦለው፡፡ የአንጾኪያውን ሊቀ ጳጳስ አስመጥቶ ተጠምቋል፡፡ [መጽሐፈ ቅዳሴ ከቀድሞ አባቶች ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ንባብና ትርጓሜው፤ ሥርዓተ ቅዳሴ፤ ምዕራፍ ፪፤ ገጽ. 20 -21]:: ✥     “  ድንግል እናታችን ቅድስት አርሴማን በምን እንመስላታለን? እርሷ በኣድማስ ላይ ተቀምጦ እንደሚያበራ እንቁ ናትና ክብሯ ብዙ ነው ። መድኃኒታችን ክርስቶስ በወንጌል እንዳለው "በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትምና ።" የሰማዕቷ ሕይወት በፊታችን እንደ ብርሃን ተገልጦ ይታያል ። ቅድስት አርሴማ እንደ ልጅ ወላጆቿን በመታዘዝ ደስ ያሰኘች ቡርክት ናት ። ቅድስት አርሴማ ይሕ ቀረሽ የማይሏት ውብ ናት ። ቅድስት አርሴማ ድንግል ናት ። ቅድስት አርሴማ ባሕታዊት ጻድቅ ናት ። ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት ። ” ( ገድለ ቅድስት አርሴማ ) ✥   “ሰላም ለአርሴማ ቅድስት ከመ በቀልት ዘይመስል ቆማ ወዘከለላ ዘመንፈስ ግርማ ዘፈጸመት ገድላ በጻማ ወበመንግሥተ ሰማይ ዐቢይ ስማ”፡፡ (ገድሏን በሥቃይ የፈጸመች፤ የመንፈስ ግርማ የጋረዳትና ቊመቷ እንደ ዘንባባ የሚመስል ለምትኾን ለቅድስት ኣርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ በመንግሥተ ሰማይም ስሟ ታላቅ ነው)  /ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን/ ✥    “   እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፥ ጽድቅን አደረጉ፥ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ፥ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፥ የእሳትን ኃይል አጠፉ፥ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፥ ከድካማቸው በረቱ፥ በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ፤ ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤ ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፥ ተፈተኑ፥ በመጋዝ ተሰነጠቁ፥ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፥ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ። ”  (ዕብ፲፩÷፴፫-፴፰) ✥     የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ አማላጅነት፤ ቃል ኪዳን ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡

  • без подписи

  • ✥✥✥ ተቀጸለ ማኅሌተ ጽጌ ✥✥✥ ✥   በቤተክርስቲያናችን ዘመነ ጽጌ ከመስከረም 26 - ህዳር 5 ቀን በማኅሌት በየሳምንቱ እሑድ እሑድ (በተለምዶው ቅዳሜ ሌሊት በሚባለው)  በስብሓተ ነግሕ /መኀልየ ሰሎሞን በመቆም/ በማኅሌተ ጽጌ በዘወትርም ጸሎትና ስብሐተ እግዚአብሔር ታከብራለች፡፡ ✥      አባ ጽጌ ድንግል ማኅሌተ ጽጌ/ የተባለውን ድርሰት ደርሰዋል፡፡ የተወለዱትም በሰሜን ሸዋ በይፋት አውራጃ ውስጥ ሲሆን መጀመሪያ ኢ አማኒ /ያለመነና ያልተጠመቀ/ ነበር፡፡ ከዕለታት ኣንድ ቀን ይህ ሰው በወጣትነት እድሜው ኣውሬ ለማደን ወደ ጫካ ሄደ በጫካ ውስጥም ፊቷ በጽጌረዳ አበባ የተከበበና ያጌጠ እጅግም ደስ የምታሰኝ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ዓይቶ በሥዕሏ ውበት እየተደነቀ ሳለ ጓደኛው መጥቶ ምን እየፈለክ ነው? ይህ እኮ የክርስቲያኖች ሥዕል ነው በማለት በያዘው በትር ሥዕሏን ሲመታት ወዲያው ተቀስፎ ሞተ፡፡ ከዚህ በኋላ ክንፎቹ በጽጌረዳ አበባ ያጌጡ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል በነጭ ወፍ ተመስሎ ወደ እርሱ መጥቶ ኣንድ ቀይ መነኩሴ እስከሚመጣ ድረስ ይህችን ሥዕል ጠብቃት ብሎ ተሰወረ፡፡ ✥      ኢትዮጵያዊው ጻድቅ መነኩሴ አቡነ ዜና ማርቆስ በይፋት ኣውራጃ በነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት ምዕ፲፩÷፩ “ትውፅእ በትር እምሥርወ እሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ ”  የሚለውን በግእዝ ቋንቋ ሲያነብ በሰማ ጊዜ ኣባቶቼ አይሁድ የነቢያት ትንቢት ንባቡን ኣስተምረውኛል አውቀዋለሁ ትርጉሙ ግን አላውቀውምና ተርጉምልኝ አለው፡፡ ✥     አቡነ ዜና ማርቆስም ሲተረጉምለት እንዲህ አለ ትወፅእ በትር እምሥርወ እሴይ የሚለው ንባብ ከእሴይ ነገድ የሕይወት በትር የሆነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትወለዳለች ማለት ነው፡፡ ወይወርድ ጽጌ እምኔሃ የሚለው ንባብ ደግሞ እመቤታችን ተወልዳ ከእርሷም ጌታ በድንግልና ይወለዳል፡፡ ከጌታም ክብር ይገኛል ማለት ነው፡፡ ይህም ጌታ ተወልዶ ትንቢቱ በእውነት ተፈጽሟል ብሎ ተረጎመለት፡፡ ( ት ኢሳ፯÷፲፬ ማቴ፲፰፡፳፬ ) ✥     ይህ ሰው በዚህ ትርጉም ደስ ተሰኝቶ ኣባት የኢሳይያስን ትንቢት በመልካም ሁኔታ ተረጎምከው መልካም ነገር ተናገርክ አለውና ሥዕሏ ወዳለችበት ቦታ ወስዶ ታሪኩ ላይ እንደተገለጸው በጫካ ውስጥ ያያትን ሥዕል ጓደኛው በያዘው በትር ሲመታት ወዲያው እንደተቀሰፈና ክንፎቹ በጽጌረዳ አበባ ያጌጡ አንድ ነጭ ወፍ የሆኑ (ቅዱስ ሩፋኤል) ወደ እርሱ መጥቶ ቀይ መነኩሴ እስከሚመጣ ድረስ ይህችን ሥዕል ጠብቃት ብሎ በሰው አነጋገር ያነጋገረውን ሁሉ ነገረው፡፡ ✥      አቡነ ዜና ማርቆስ የተደረገውን ሰምቶ እጅግ ደስ አለውና በል በመጀመሪያ እመቤታችን በድንግልና በወለደችው በአብ የባሕርይ ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን ይህችን ሥዕል ያስገኘው ሰማይና ምድር በውስጣቸው ያለውን ሁሉ የፈጠረ እርሱ እንደሆነ እወቅ አለውና በኣብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቆ ጽጌ ብርሃን /ጽጌ ድንግል/ ብሎ ሰየመው፡፡ ✥     ማኅሌተ ጽጌ ማለት ማኅሌት የሚለው ቃል የግእዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ምስጋና ማለት ነው፡፡ ጽጌ ማለት እንደሱ የግእዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙ አበባ የፍሬ ምልክት ማለት ነው፡፡ ማኅሌት ጽጌ ተብሎ በአንድነት ሲነገር ሲተረጎም ደግሞ የኣበባ ምስጋና ማለት ነው፡፡ ይህም ድንግል ማርያም የማኅጸኗ ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ መዓዛ ባላቸው አበባዎችና ፍሬዎች እየተመሰሉ የሚመሰገኑበት ምስጋና ማለት ነው፡፡ ✥      ማኅሌተ ጽጌን በግጥም /ቅኔ/ ስንኝ በ5 በ5 የተደረሰ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ድርሰት ነው፡፡ ይህ ድርሰት በቤተክርስቲያን ኣገልግሎት የሚውለው በዘመነ ጽጌ እሑድ እሑድ (በተለምዶ ቅዳሜ ሌሊት በሚባለው)  በሚቆመው ማኅሌት ነው፡፡ በዚህ ዕለት ሙሉ ድርሰቱ በዜማ በጽናጽልና ከበሮ የሚዘመር ሲሆን በዘወትርና በዓመት በዓላትም በሚቆም ማኅሌት በዓሉን የሚመለከተው ክፍል እያንዳንዱ እየወጣ በዜማና በጽናጽል ይዘምራል፡፡ ✥     በሃገራችን የመስከረምና የጥቅምት ወራት የኣበባ ወራት /ዘመነ ጽጌ/ ይባላል፡፡ ይህም ወቅት ተራሮችና ሜዳዎች በኣበባ የሚያጌጡበትና ለዓይን ማራኪ የሚሆኑበት ጊዜ ነው፡፡ -    በዚህ ዘመን ጌታችን ፈጣሪአችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለልብስ ለምን ትጨነቃላችሁ የሜዳ አበቦች እንዴት እንደሚያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፡፡ አይደክሙም ኣይፈትሉም ነገር ግን እላችኋለሁ ሰሎሞን እንኳ በክብሩ ሁሉ ከእነዚህ እንደ ኣንዱ አልለበሰም ብሎ በአበባ ምሳሌነት የሰው ልጆች ስለ ልብስ እንዳይጨነቁ አስተምሯል፡፡ ( ማቴ፭÷፳፰-፴፫ ) -    ንጉሥ ዳዊትም ተዘከር እግዚኦ ከመ መሬት ንሕነ ወሰብእሰአ ከመ ሣዕር ወዋዕሊሁ ወከመጽጌ ገዳም ከማሁ ይፈሪ ኣቤቱ እኛ ኣፈር እንደሆነ ኣስብ ሰውስ ዘመኑ እንደ ሣር ነው እንደ ዱር አበባም እንዲሁም ያብባል ነፋስ በነፈሰበት ጊዜ ያልፋል (መዝ ፻፪፥፲፬-፲፮/) በማለት እንደተናገረው ሣር በቅሎ አድጎ አብቦ ፀሓይ በወጣ ጊዜ ይደርቅና በሞት ነፋስ ይወሰዳል፡፡ ✥     አባ ጽጌ ድንግል የደረሰው ማኅሌተ ጽጌም ምሥጢሩ ከእነዚሁ የቅዱሳት መጻሕፍት መልእክታት ጋር ተቀራራቢ ነው፡፡ የማኅሌተ ጽጌ ብዛቱ 150 ነው፡፡ ጽጌ አስተርአየ ሠረጸ አምአጽአሙ አበባ ከአጥንቱ ወጥቶ ታየ ብሎ ይጀምራል፡፡ አጥንት ያለው እንጨቱን ነው፡፡ ዕፅ እመቤታችን አበባው ልጅዋ ኢየሱስ ነው በማኅሌተ ጽጌ ኣበባ ጌታ ሲሆን እመቤታችን ዕፅ ትባላለች ፍሬ ጌታ ሲሆን እመቤታችን አበባ ትባላለች፡፡ ✥    ማኅሌተ ጽጌ በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን አሜን ::

  • без подписи

  • ✥✥✥ የድኅነት ድልድይ ✥✥✥ “ በአንድ እንጨት ምክንያት ሰው ሁሉ ወደ ሲኦል እንደወረደ  እንዲሁ በአንድ እንጨት ምክንያት የሰው ልጅ ሁሉ ወደ ሕይወት ማደሪያ ተሸጋገረ ። በእንጨት መራራ ሞትን ተጎነጨን ፣ በእንጨት ደግሞ ጣፋጭ ሕይወትን አጠጣን።”  (ቅዱስ ኤፍሬም) -> በትረ ሙሴ ባህረ ኤርትራን ከፈለ ወደ ምድረ ርስት ለመግቢያ መንገድን ተገኘ ክርስቶስም በመስቀሉ የኃጢአትን ባሕር ሲኦልን ከፈለ ወደገነት መግቢያ አደረገው፡፡ -> በበትረ ሙሴ ጽምዓ እስራኤል ያበረደ ውኃን ከዓለት መነጨ ፤ በዕፀ መስቀልም ጽምዓ ነፍሳትን የሚያረካ መጠጥ ተገኘ :: ዮሐ.19 ✝️ ለብርሃነ መስቀሉ ያደረሰል አምላክ ይክበር ይመስገን የበረከት በዐል ያድርግልን ✝️