tgindex
Tribune sport ትሪቡን ስፓርት የኮከቦች ገፅ

Tribune sport ትሪቡን ስፓርት የኮከቦች ገፅ

Статистика

ትሪቡን ስፖርት ስፖርትን ለመከታተል ትክክለኛው ቦታ በ ኤፍሬም የማነ እና ፍቅር ይልቃል

Последний пост
4 нояб.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
15 авг.
Подписчики
1 890
0 за 3 дн.
Сутки
−2
−0,11%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
3 160
20 постов
Вовлечённость
167,2%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • “ በቅርቡ ጫማ እሰቅላለሁ “ ሮናልዶ ⏩ “ አለም ዋንጫ ህልሜ አይደለም " ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቅርቡ ጫማ ለመስቀል ዝግጅት መጀመሩን በሰጠው አስተያየት ገልጿል። “ ጨማ የመስቀያ ጊዜዬ በቅርቡ ነው “ ያለው ሮናልዶ “ ከባድ ይሆናል ያንን ሳስብ አለቅሳለሁ ነገርግን ዝግጅት ጀምሬያለሁ ብሏል። ሮናልዶ ስለ አለም ዋንጫ ምን አሉ ? - የአለም ዋንጫ ህልሜ አይደለም እኔን እንደ ተጨዋች ሊገልፀኝ አይችልም። - አንድ ውድድር 6 ወይም 7 ጨዋታዎች ተጫውቼ የምንግዜም ምርጡ ተጨዋች አያደርገኝም እንደዛ ከታሰበ ፍትሀዊ አይደለም። ሮናልዶ ስለ ዲያጎ ጆታ ምን አለ ? የዲያጎ ጆታን መሞት ስሰማ ማመን አልቻልኩም ነበር ለብዙ ሰዓት አልቅሻለሁ። - ለሀገሬ ፣ ለቤተሰቤ ፣ ለቡድን አጋሮቼ ለሁሉም ሰው በጣም አስቸጋሪ ወቅት ነበር። ሮናልዶ ለግል ህይወቱ ምን አለ ? - ገንዘብ እቃዎችን ለመግዛት አስፈላጊ ነው ነገርግን በህይወት ውስጥ በጣም አስፈላጊው ነገር አይደለም። - ስንት መኪና እንዳለኝ በግልጽ አላውቀውም 41 ይመስለኛል ነገርግን እርግጠኛ አይደለሁም። - በህይወቴ ከገዛኋቸው ነገሮች ሁሉ አሁንም ከፍተኛ ገንዘብ ያወጣሁበት ውዱ የግል ጄቴ ነው። ሮናልዶ ስለ ዶናልድ ትራምፕ ምን አለ ? ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይሄንን አለም ወደ ተሻለ መለወጥ ከሚችሉ ሰዎች አንዱ ነው።

  • без подписи

  • без подписи

  • ከአለቃ ዶናልድ ትራምፕ ፊት ሚስተር ቼልሲ ምርጡ ፔዤን አፈዘዘ ። ሽንፈት ረስተው የከረሙት ፓሬዚያኑ በዓለም ክለቦች ዋንጫ ፍፃሜ 3ለ0 ተረቱ ። የማሬስካ ታታሪ ሰሚያዊ ቼልሲ ከice co ማጂክ ጋር የፔዤ የኳስ ቀመርን አፈራረሰ ። የተሻለው ቡድንም ድል ነስቷል ። ቼልሲ ከቶድ ቦኸሊ ቢሊዮን ፓውንዶች ከፈሰሰበት ስብስቡ ጋር በጣሊያናዊ አሰልጣኙ ኤንዞ ማሬስካ ተደናቂ የቡድን ግንባታ ጉዞ ወደ ኋያልነቱ ለመመለስ ዕውነተኛው ተስፋውን ያየበት የፍፃሜው ጨዋታ ከአሜሪካ ኒዮርክ ... ቀለሙ ሰሚያዊ ነው ! መቀመጫው ምዕራብ ለንደን ! ስቴዲየሙ ብሪጅ ! ክለቡ ቼልሲ ! አዲሱ የዓለም ክለቦች ዋንጫ ሻምፒዮን ! የኮንፈረንስ ሊጉ ሻምፒዮን የቻምፒየንስ ሊጉ ዋንጫ ባለቤትን ሙሉ ለሙሉ በልጦ ረቷል ። ሰሚያዎቹ ለዳግም የታላቅነት ጉዞ ህልማቸው የመጀመሪያውን ከባዱን ፈተናም በብቃት ተወጥተዋል ። Blue Is the Colour ...

  • без подписи

  • без подписи

  • ምርጡ ፔዤ ከቼልሲ ምሽት 4:00 የዓለም ክለቦች ዋንጫ ፍፃሜ ? ሰውየው በፍፃሜው ጨዋታ ይገኛሉ ። የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋኒቶ የልዕለ ሀያሏ ሀገር አሜሪካ ፕሬዝዳንት እግር ኳስ በጣም እንደሚወዱ መስክረዋል ። ዳግም ወደ ስልጣን መንበሩ ከመጡ በኋላ ዓለምን እንደፈለግኩ ካላደረኩ እያሉ ያሉት አወዛጋቢው ዶናልድ ትራምፕ በፔዤ Classic የኳስ ዘዋሪ ቀመረኛ ኮኮቦች እና ሚስተር ቼልሲ መሃከል የሚካሄደውን የፍፃሜ ጨዋታ 90 ደቂቃ በዕርጋታ ይጨርሳሉ ? ወይስ ታይተው ይጠፋሉ ? መልሱን ምሽት እንገኛለን ። ምርጡ ፔዤ ወይስ ቼልሲ ለዓለም ክለቦች ዋንጫ ? ማን የበላይነቱን ይወስዳል ?

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • ያሲን ቦኖ The spider Man ያሲን ቦኖ ግድግዳው የጋርዲዮላ ሲቲን ጥሏል ። 10 ጣጣቸውን የጨረሱ የሲቲ ኳሷችንም ግራ ቀኝ እንደ spider Man እየተሳበ አድኗል ። ክለቡ አልሂላልን ይዞ ወደ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል ። ሞሮካዊ ግብ ጠባቂ ከጓደኞቹ ጋር ኮኮብ ሆኖ አምሽቶ ለሳውዲው ከለብ አዲስ ታሪክ አስፅፈዋል ። የአለም ክለቦች ዋንጫም ከወደ አሜሪካ ከነ ሰፊ ክፍተቱ ቀልብ ገዢ ፍክክር በተወሰኑ የLast -16 ጥሎ ማለፎች ማሳየት ጀምሯል ። ትልልቆቹም ባልተጠበቁት እየወደቁ ነው ። የቲያጎ ሲልቫ ፍሌሜኔሴ ኢንተር ሚላንን ገንድሶ ብዙዎችን አስገርሟል ። የብራዚል ተወካዮች ጠንካራ ሊግ እንዳላቸው ከአውሮፓዊያኑ ተናንቀው እያስመሠከሩ ነው ። የሜሲ ሚያሚ ጡረተኞች በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው ፔዤ 4 ለ0 ተረምርመዋል ። ቼልሲ በአሜሪካ መጥፎ ንፋስ የቀላቀለ አየር ንብረት ምክንያት ለሁለት ሰዐት በተቋረጠ ጨዋታ ቤኔፊካን ረቶ ሩብ ፍፃሜ ደርሷል ። ባቫሪያኑ ፍላሚንጎን 4ለ2 አሸንፈው በሩብ ፍፃሜው ከፔዤ ይፋለማሉ ። ዛሬ ሪያል ማድሪድ ከጁቬ ይጫወታል ። የአሮጊቷ እና ሎስብላንኮስ ፍጥጫ ይጠበቃል ። ነገ ዶርቱሙንድ ከሞንቴሪ የመጨረሻውን Last -16 መርሃ ግብር ያከናውናሉ ። ከዓለም ክለቦች ዋንጫ የዝውውር ወሬዎች የተመልካችን ቀልብ ይስባሉ ተብሎ የታማው ! እንደ ጥንቸል ኳስ የሚያፈናጥሩ ሜዳዎች ላይ እንዴት ኳሱን አንሸራሽረን እንጫወት የሚል ወቀሳ በፔዤው አለቃ ኤኔሪኬ የቀረበበት ! ተመልካች አልባው ... በሀገራቸው ኳስ ጨዋታ የዓለም ክለቦች ዋንጫ እየተካሄደ መኖሩን ዛሬም በማያውቁ አሜሪካዊያን የታጀበው ! በመጥፎ አየር ንብረቱ የተጀመረ ጨዋታን ለሁለት ሰዐት የሚያቋርጠው በሆሊውድ የአላዲን ኮሜዲ Movie ማስታወሻ ስታይል ከi Love America ምድር እየተከናወነ የሚገኘው የዓለም ክለቦች ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች የበለጠ በማራኪ የፍክክር ዳንኪራዎች ባልተጠበቁ ፉክክሮች እንደሚደምቁ የሳውዲው አልሂላል እና የብራዚሉ ፍሌሜኔሴ ሲቲ እና ኢንተርን ገንድሰው ፍንጭ ሰጥተዋል ። በሩብ ፍፃሜው ፍሌሜኔሴ ከአልሂላል ባየርን ከፔዤ በLast -16 የሀገሩ ክለብ ቦቶፋጎን 1ለ0 የረታው ፓልሜሪያስ ከቼልሲ የዛሬ የማድሪድ እና ጁቬ አሸናፊ ከነገ የዶርቱሙንድ እና ሞንቴሪ አሸናፊ በLast -8 ሩብ ፍፃሜ ይፋለማሉ ። የዓለም ክለቦች ዋንጫም ከዶናልድ ትራምፕ ሀገረ አሜሪካ በተወሰነ ደረጃ ቀልብ መግዛትም ጀምሯል ።

  • #EthiopianPL 🇪🇹 በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ መርሐግብር የወራጅ ስጋት ያለባቸው ክለቦች ያደረጓቸው ሶስት ጨዋታዎች በተመሳሳይ ሰዓት ተደርገዋል። አዳማ ከተማ ከፋሲል ከነማ ጋር ያደረጉትን ተጠባቂ ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል። የአዳማ ከተማን ግቦች ነቢል ኑሪ እና አድናን ረሻድ ሲያስቆጥሩ ለፋሲል ከነማ ጌታነህ ከበደ እና አንዋር ሙራድ ከመረብ አሳርፈዋል። መቐለ 70 እንደርታ በበኩሉ ከወልዋሎ ዓ.ዩ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል። የመቐለ 70 እንደርታን የማሸነፊያ ግቦች ሙሉጌታ ወ/ጊዮርጊስ እና ሰለሞን ሀብቴ ሲያስቆጥሩ ለወልዋሎ ዓ.ዩ ናትናኤል ሰለሞን ከመረብ አሳርፏል። በሌላ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከመቻል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ በሽመክት ጉግሳ ግብ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል። የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ? 9️⃣ መቻል :- 44 ነጥብ 1️⃣1️⃣ ፋሲል ከነማ :- 42 ነጥብ 1️⃣2️⃣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ :- 41 ነጥብ 1️⃣3️⃣ መቐለ 70 እንደርታ :- 41 ነጥብ 1️⃣6️⃣ አዳማ ከተማ :- 39 ነጥብ 1️⃣8️⃣ ወልዋሎ ዓ.ዩ :- 19 ነጥብ

  • ኤቨርተን ላይ ያለ ዋንጫ ክብር ኖረውበት ሄደዋል ። KDB የሚመራው የቤልጂየም ወርቃማ ትውልድ ላይም አንድም ነገር ሳያሸንፉ  ቀልደዋል ። ከውጤት ዕድለኝነት ይቀናቸዋል ይባላሉ ። ምክንያት ምንም ሳይሰሩ ሌላኛውን የፖሩቱጋል ወርቃማ ትውልድ ሊያመክኑ ሊዝበን ከደረሱ ሁለት ዓመት ሆናቸው  ። አንድ አውሮፓ ዋንጫ ሞክረዋል ወፍ የለም ። ክርስትያኖን ጨምሮ አጭሩ የመሃል ሜዳ ጂኒየስ ቪቲኒያ የማንቸስተሩ ታማኝ ተፅእኖ ፈጣሪ  ኮኮብ  ቡሩኖ ፈርናዴዝ በርናንዶ ሲልቫ ኮንሴሳዎ ሩቢን ዲያዝ  የመሳሰሉ ድንቆችን የያዘው ቡድንን ዕድለኛው አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቴኔዝ  በቀጣዩ የዓለም ዋንጫ ምን እንደሚያደርጉት ይጠበቃል ። ሰውየው  ፖሩቱጋል ከደረሱ በኋላ መልካም ስራ ፈፀሙ የሚባለው  ታላቁ ኮኮብ ክርስትያኖ ሮናልዶን ካለፈው አሰልጣኝ በተሻለ መንገድ  በብሄራዊ ቡድኑ የያዙበት ነው ። ይህም ለእራሳቸው እንጀራ መረጋጋት ሲባል እንደሆነ ብዙዎች ይጠቅሳሉ ። ማርቲኔዝ  ትናንትም በኔሽን ሊግ semi final ቪቲኒያን ተጠባባቂ አድርገው ታላቁን ድፍረት ፈፅመዋል ። በዚህ ወቅት የትም የማይገኘው ማስተሩ የመሃል ሜዳ የፔዤ ማጂሺያን ቪቲኒያን ከዕረፍት መልስ ቀይረው ካስገቡ ደቂቃዎች በኋላ በCR-7 የማድየራው ልዕል በተገኘች ጎል ፖሩቱጋል ጀርመንን 2ለ1 አሸንፏ ለኔሽን ሊግ ዋንጫ ፍፃሜ ደርሳለች ። የላሚን ያማል ስፔን ወይስ የኪሊያን ምፓፔ ፈረንሳይ የፖሩቱጋል የፍፃሜ ተፋላሚ ይሆናሉ ??? አጓጊው ጥያቄ ዛሬ ይመለሳል ።  ደፋሩ ዕድለኛው አሰልጣኝ የቤልጂየም ወርቃማ ትውልድ ዋና ብክነት ሚስጥር ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ግን የፓሬዚያኑ  የወቅቱ የመሃል ሜዳ  የኳሰ ጨዋታ ቀመረኛ አጭሩ ቪቲኒያን ተጠባባቂ አድርገው ታላቁን ድፍረት አለፍ ሲል የእግር ኳስ  ወንጀል ትናንት ምሽት ቢፈፅሙም ፖሩቱጋል አሸንፏ የፍፃሜ ተፋላሚዋን ትጠብቃለች ። ስፔን ወይስ  ፈረንሳይ ታላቁ ፍጥጫ ዛሬ ምሽት ይካሄዳል::

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи