የፀጋ አዳማ መ/ክ አጥቢያ ቤ/ክ የወንጌል አገልግሎት!!
Статистика“ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤”ቲቶ 2፥11
- Последний пост
- 1 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 94
- 1/48двое суток
- 107
- 1/72трое суток
- 116
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
week 4 ከሀምሌ 26-ነሀሴ 2/2018 የሚፀለይላቸው የህዝብ ክፍሎች እንጸልይ ለሶሪያ ሕዝብ ሶሪያ፣ በይፋ የሶሪያ አረብ ሪፐብሊክ፣ በምዕራብ እስያ በምስራቅ ሜዲትራኒያን እና በሌቫንት የሚገኝ አገር ነው። በምዕራብ የሜዲትራኒያን ባህርን፣ ቱርክን በሰሜን እና በሰሜን ምዕራብ፣ ኢራቅን በምስራቅ እና በደቡብ ምስራቅ፣ በደቡብ ዮርዳኖስ፣ በደቡብ ምዕራብ እስራኤል እና ሊባኖስን ይዋሰናል። በጊዜያዊ መንግስት ስር ያለ ሪፐብሊክ ሲሆን 14 ገዥዎችን ያቀፈ ነው። ደማስቆ ዋና ከተማ እና ትልቁ ከተማ ነው። በ185,180 ስኩዌር ኪሎ ሜትር (71,500 ስኩዌር ማይል) ስፋት 26 ሚሊዮን ሕዝብ ያላት፣ በሕዝብ ብዛት 56ኛዋ እና 87ኛዋ ትልቁ አገር ናት። እምነታቸው ምን ይመስላል? ሶሪያ እስልምና የበላይ እምነት የሆነባት የብዙሀኑ የሱኒ አረብ ሕዝብ ተፅዕኖ ፈጣሪ አናሳ ቡድኖች የሚተገብሩባት በሃይማኖት የተለያየች ሀገር ነች። እነዚህ ቁልፍ አናሳ ሙስሊም የፖለቲካ ሃይሎች አላውያን፣በደቡብ የሚገኙት ሚስጥራዊው ድሩዝ እና በሰሜን እና በሰሜን ምዕራብ የሚገኙ አብላጫዎቹ የሱኒ ኩርዶች ይገኙበታል። የእስልምና የበላይነት ቢኖርም ከእነዚህ ቡድኖች ውስጥ ብዙዎቹ፣ የሱኒ አረብ አብላጫውን ጨምሮ፣ ያልተደረሰላቸው የወንጌል መዳረሻ ያላቸው ቡድኖች ተደርገው ይወሰዳሉ። 🤲🏾 የጸሎት ርዕሶች 🤲🏾 👉🏾ከአስራ አራት ዓመታት ጦርነት እና ከከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ወደ ተነሳችው ሶሪያ፣ እግዚአብሔር ሰላሙን እንዲልክላት እንለምን። በዚህ የረመዳን ወር፣ አዲሱ የሽግግር መንግሥት በጥበብ እንዲመራ እና ለሁሉም ሕዝቦች፣ በተለይም ለሚሰደዱ ክርስቲያኖች መጠበቂያ እንዲሆን እንጸልይ። 👉🏾እግዚአብሔር፣ በዚህ የረመዳን ወር ሙስሊሞች በጾም እና በጸሎት ወደ አላህ በሚቀርቡበት ወቅት፣ በሶሪያ የሚገኙትን ያልተደረሱትን ሕዝቦች በምሕረቱ እንዲጎበኛቸው እንጸልይ። ለሱኒ አረብ ብዙሃኑ፣ ሉዐላውያን፣ ለድሩዝ፣ እና ለኩርዶች ኢየሱስ እራሱን እንዲገለጥላቸው። በሕልም፣ በራእይ እንዲገለጥላቸው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት እንዲሆንላችው እንጸልይ። 👉🏾ኢየሱስ ሆይ፣ በሶሪያ ቀደምት ሥር ያደረጉትን የኦርቶዶክስ እና የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናትን፣ እንዲሁም በቁጥራቸው ትንሽ የወንጌላውያን አማኞችን በዚህ ረመዳን ወር አጽናናቸው። በሙስሊም አክራሪነት ዘንድ ፍርሃት እና ስደት በሚጨምርበት ጊዜ፣ መንፈስ ቅዱስህን ልክላቸው ደፋር እና ጥበበኛ እንዲሆኑ ሥራቸው። ከጎረቤቶቻቸው ጋር የክርስቶስን ፍቅር ለማካፈል በር ክፈትላቸው እንጸልይ። 👉🏾የምሕረት አባት ሆይ፣ ግማሽ ያህሉ የተፈናቀለውን የሶሪያ ሕዝብን ተመልከት። በዚህ የረመዳን ወር፣ በሀገር ውስጥ ላሉ እና በስደት ላሉ ሶሪያውያን ተስፋን ስጣቸው። የምግብ፣ የመጠለያ እና የፈውስ ፍላጎታቸውን ለማሟላት የክርስቶስን እጆች የሆኑትን አገልጋዮችህን አስነሳ። በድካማቸው ውስጥ፣ የማይሳነውን የክርስቶስን ፍቅር ይቀበሉ ዘንድ ጸሎታችንን እንጸልይ::
без подписи
без подписи
ነገ 1:00 ላይ ተገናኝተን ወንጌል እየሰበክን እና ትራክት እየሰጠን ወደ ወጣቶች ማዕከል እንሄዳለን።ስፖርት ለጤንነት ወንጌል ለህይወት !! 2:00 ላይ ፀጋ አዳማ መ/ክ/ቤ/ክ vs ገንደጋራ ሙሉ ወንጌል የምድብ አንድ ሁለተኛ ጨዋታ
ከዚህ በፊት በተለያዩ አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ ባሳወቅናችሁ መሰረት 2 ኛ ሚሽነሪ ወደ አፋር ክልል የምንልክ መሆኑን ስንገልፅ ቆይተናል እግዚአብሔር ፈቅዶ ከ ሐምሌ 21/2018 ጀምሮ ሚሽነሪ ኖህ ጳውሎስ ወደ አፋር ክልል ሚሽነሪ በመሆን ወደ ስፍራው ልከናል።ይሄም ድንቅ ለሆነው ለተልዕኮ ጉዞ የተሳካው በእናንተ የወንጌል ማህበርተኛ መዋጮ መሆኑን እየገለፅን የወንጌልን ብስራት ሰዎች እዲሰሙ ብዙዎች በመትጋት ላይ መሆናቸው ግልፅ ነው።ያላለቀው መከር ብዛት ግን ዛሬም በርካታ በመሆኑ ምክንያት የወንጌል ማህበርተኛ መዋጮ የምታዋጡ በዚሁ ቀጥሉ ያቋረጣችሁም ድጋፋችሁን ቀጥሉ ከዚህ በፊት የወንጌል ማህበርተኛ ያልሆናችሁ ማህበርተኛ በመሆን ወንጌልን ያገልግሉ ኢየሱስ ሁላችሁንም ይባርካችሁ።
የ 2019 week 2 ከ ሀምሌ 12-18/2018 ድረስ የሚፀለይላቸው የህዝብ ክፍሎች በየመፅሀፍ ቅዱስ ቡድኑ !! 🙏የጸሎት ርዕሶች🙏 👉 እግዚአብሔር በሃባኒያ ባግጋራ የሕዝብ ክፍል መካከልስሙ እንዲቀድስ እንጸልይ። 👉 መፅሐፍ ቅዱስ በቋንቋቸው ሙሉ ለሙሉ እንዲተረጎም እንጸልይ ። 👉 አማኞች እንዲበዙ እንዲብዛዙ ደቀመዛሙርት ሌሎችን ደቀመዝሙር እንዲያደርጉ እንጸልይ።
<ንባብን ለተልዕኮ> በፀጋ አዳማ መሰረተ ክርስቶስ ቤ/ክ የወንጌል ምክንያታዊ ያልሆነ የኢንተርኔት አጠቃቀም አንዱ እና ዋነኞቹ የሱስ ዝርዝር ውስጥ ተካቷል ።ቲክ ቶክ እና አጫጭር ቪድዮዎች Short Mimory እንዲኖረን ለማድረግ እና ያልደከምንበትን እና ዋጋ ያልከፈልንበትን ሀብት በቀላሉ እንደምናገኝ በስፋት በማውራት በውሸት ትርክታቸው በርዘውናል በቀቢፀ ተስፋም ሞልተውናል።ተረጋግቶ ማሰብ፣ረጅም የሆነ ትምህርት አዘል ቪድዬዎችን ተመልክቶ መጨረስ፣መፅሀፍቶችን እና መፅሀፍ ቅዱስን በጥልቀት ማጥናን፣የስልክ ቀፎዎቻችን ከኪሳችን🕺እና ከቦርሳችን 💃ሳናወጣ ቁጭ ብሎ መወያየትና አንዱ የአንዱን ሸክም በመጋራት የመፍትሄ ሀሳብ ላይ በጋራ መድረስ ከእያንዳንዳችን ማንነት ላይ ጓዙን ጠቅልሎ እየወጣ ይገኛል።አዲሱ ትውልድ ደግሞ ከእነዚህ ክፉ ከሆኑ የልማድ ጠንቆች በመላቀቅ ክረምቱን ስለመንፈሳዊ ህይወቱ፣ስለ ህግና መመሪያዎች፣አእምሮውን ለማልማት፣ስለ ሀገሩ እና ሌሎች ታሪኮች ለማወቅ፣መረጃዎችንም ለማግኘት እና ለመሳሰሉት ጥቅሞች መፅሀፍትን እንዲያነብ ይበረታታሉ በዚህ እሳቤ መሰረት ክረምቱን መፅሀፍ በማንበብ ተልዕኮውንም አብራችሁ እንድትወጡ በማሰብ <ንባብን ለተልዕኮ> በሚል መሪ ቃል መሰረት እኛ የመረጣችሁትን መፅሀፎችን ጠይቁን እናንተ ደግሞ በተሰጣችሁ ቀናት ውስጥ ጨርሳችሁ መልሱ ይሄን ስታደርጉ ግን በቀን አምስት ብር ይቆጥራል። ይሄ ማለት ከወሰዳችሁበት ቀን እስከምትመልሱበት ቀን ውስጥ ሁሉ አምስት ብሮች ይኖራሉ አንብባችሁ ስትጨርሱ በቀናቱ መጠን ልክ ድምር አምስት ብሮችን በማምጣት ደረሰኝ አስቆርጡ።ልብ በሉ እነዚህ ብሮች ለወንጌል ተልዕኮ አላማ ይውላሉ።
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи