Ethiopia Check
Статистикаኢትዮጵያ ቼክ በማህበራዊ ሚድያ እና በመደበኛ ሚድያዎች የሚቀርቡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማጣራት ስራዎቹን ለተከታታዮቹ ያቀርባል።
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 67
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 2 671
- 1/48двое суток
- 3 060
- 1/72трое суток
- 3 301
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
#FactCheck በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቦራ ወረዳ ወደቀ ስለተባለው ጄት እየተሰራጩ ያሉ ትክክለኛ እና አሳሳች መረጃዎች /ኢትዮጵያ ቼክ/- ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቦራ ወረዳ ጎራ ለመን ቀበሌ ወደቀ ስለተባለ የጦር ጄት የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰጡ ቆይተዋል። የጄቱ ስብርባሪ አካል ብቻውን እንዲሁም የታጠቁ ሰዎች በስብርባሪው ላይ ቆመው የሚያሳዩ ምስሎች እና ቪዲዮዎችም እየተጋሩ ይገኛሉ። አንዳንዶች የጦር ጄቱ በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (ኦነሠ) ታጣቂዎች ተመቶ መውደቁን በመጥቀስ ምስሎቹን ያጋሩ ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ ምስሎቹ እና ቪዲዮዎቹ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰሩ እንደሆኑ የጻፉም አሉ። በተጨማሪም ምስሉ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ጄትን እንደማያሳይ በመጥቀስ መረጃው ሀሰተኛ እንደሆነ የጻፉም አሉ። ከነዚህ መካከልም ‘Demeke Negassa Kube’ የሚል ስም እና ከ500 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ ይገኝበታል። ገጹ “የወያኔ ቋሚ ተላላኪዎች እያሰራጩ ያለው ዜና በፍጹም ውሸት ነው ።ጀግናው አየር ኃይላችን እንደዚህ ጨጨባ (ስብርባሪ) ጄት የለውም።ይህንን ስብርባሪ ለራሣችሁ አውሉት።በመንደር ሽፍታ ቀርቶ በሌላም በቀላሉ የሚመታ ጄት የለውም” ሲል በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋሩ ስለሚገኙ ምስሎች እና ቪዲዮ ጽፏል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሎቹ እና ቪዲዮ ላይ ባደረገው ማጣራት ምስሎቹም ሆነ ቪዲዮ በሰው ሰራሽ አስተውሎት እንዲሁም በቅንብር የተሰሩ እንዳልሆኑ አረጋግጧል። በተጨማሪም ምስሎቹ እና ቪዲዮ ከዚህ በፊት በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተጋርተው እንደማያውቁም ተመልክቷል። የጦር ጄቱም ኤሮ L-39 አልባትሮስ (Aero L-39 Albatros) በመባል የሚታወቅ ሲሆን የቼክ ሪፐብሊክ ስሪት ነው። ይህ ጄት በስፋት ለስልጠና አገልግሎት የሚውል ሲሆን ለአየር ላይ ውጊያ፤ የመሬት ላይ ኢላማዎችን ለማጥቃት እንዲሁም ለስለላ አገልግሎትም መዋል ይችላል። የኢትዮጵያ አየር ኃይልም ይህን ጄት ለስልጠና እንደሚጠቀም ከዚህ በፊት የተጠቀሰ ሲሆን ጄቱ የዛሬ ስድስት ወር ገደማ በተከበረው የአየር ኃይል 90ኛ አመት ክብረ በዓል ላይ ትርዒት ካሳዩ ጄቶች መካከል አንዱ ነበር። በእለቱም የተወሰኑ የአየር ኃይሉ L-39 አልባትሮስ ጄቶች ትርዒት ያሳዩ ሲሆን የጄቶቹ ትርዒት EBC በእለቱ ባሰራጨው ቀጥታ ስርጭት ቪዲዮ 1፡03፡00 ጀምሮ ይታያል፡ https://www.youtube.com/live/Ib4t9boBZxg?si=uqGOCD92DKVMGo30 በዚህ የEBC ቪዲዮ ውስጥ 5፡30 ደቂቃ ላይ ደግሞ ጄቶቹ በረድፍ ቆመው ይታያሉ፡ https://youtu.be/969VaWBL9EY?si=cJFbiSKI6zBvBFBg በተጨማሪም ኢትዮጵያ ቼክ የተከሰከሰውን ጄት ስብርባሪና በክብረ በዓሉ ላይ ትርዒት ያሳዩ L-39 አልባትሮስ ጄቶችን በማነጻጸርም ተመልክቷል። በዚሁ መሰረት የተከሰከሰው እና በትርዒቱ ላይ የተሳተፉት ጄቶች ተመሳሳይ የቀለም ስብጥር እንዳላቸው አረጋግጧል። ከነዚህ መካከልም ጄቶቹ ሆድ ስር የሚገኘው ሰማያዊ ቀለም፤ ክንፎቹ ጫፍ ላይ ያሉት ቀይ እና ቢጫ ቀለማት እንዲሁም የጄቶቹ ጅራት ጫፍ ላይ የሚገኘው ቢጫ ቀለም ቅብ ይገኙበታል። ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች እንዲሁም በጄቱ ስብርባሪ ምስል ላይ የሚታየውና ጄቱ እንደወደቀ የተገለጸበት ስፍራ መሬት አቀማመጥ መመሳሰል ጄቱ ከጥርጣሬ በላይ የኢትዮጵያ አየር ኃይል መሆኑን የሚያመላክቱ ናቸው። ይሁን እንጂ ጄቱ ተመቶ ወይስ በቴክኒክ ችግር ምክንያት ነው የወደቀው የሚለው ጥያቄ በማስረጃ ያልተመለሰ ሲሆን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊትም ሆነ የኢትዮጵያ መንግስትም ስለ ጉዳዩ በግልጽ ያሉት ነገር የለም። ኢትዮጵያ ቼክ
#FactCheck በሸረሪና የተማረኩ 'የህወሓት ኃይሎች እና ጦር መሳሪያዎች' በሚል እየተሰራጩ የሚገኙት ምስሎች የቆዩ ናቸው /ኢትዮጵያ ቼክ/- ሰሞኑን በፌደራል ሠራዊት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ሸረሪና አካባቢ ግጭት መቀስቀሱ ተሰምቷል። ይህን ግጭት መነሻ በማድረግም በፌደራል ሠራዊት የተማረኩ ‘የትግራይ ኃይሎች’ አባላት እና ጦር መሳሪያዎችን ያሳያሉ በሚል በርከት ያሉ ምስሎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋሩ ይገኛሉ። እነዚህን ምስሎች ካጋሩ የፌስቡክ ገጾች መካከልም ‘አውደ ሀገር’ የሚል ስም እና ከ107 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ ይገኝበታል። በዚህ ገጽ የተጋራውን የምስል እና ጽሁፍ መረጃ 19 የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰው ሲያጋሩት በርከት ያሉ አስተያየቶችም ተሰጥቶበታል። በተጨማሪም ‘Mimi Jarso’ የሚል ስም እና ከ170 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ ተመሳሳይ መረጃን አጋርቷል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ በምስሎቹ ላይ ባደረገው ማጣራት ምስሎቹ ሰሞኑን ሸረሪና አከባቢ በተከሰተው ግጭት የተማረኩ የትግራይ ኃይሎች አባላትን እና ጦር መሳሪያዎችን እንደማያሳዩ አረጋግጧል። ምስልን በምልሰት መፈለጊያ ድረ-ገጾችን በመጠቀም ባደረግነው ማጣራት ምስሎቹ ከወራት በፊት በአማራ ክልል ውስጥ የተነሱ መሆናቸውን አረጋግጠናል። በዚሁ መሰረት ምስሎቹ እኤአ ታህሳስ 15፣ 2025 “በምስራቅ ደምቢያ እና በቆላድባ ከተማ አካባቢ ታጥቀዉ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂ ሃይሎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለዉ ገቡ” በሚል ርዕስ በአማራ ክልል ፕሬዘዳንት ጽ/ቤት የተረጋገጠ የፌስቡክ ገጽ የተጋሩ ናቸው፡ https://www.facebook.com/share/14hssp5abfn/?mibextid=wwXIfr ስለዚህም ምስሎቹ ከአውድ ውጭ የተጋሩ እና አሳሳች መሆናቸውን አረጋግጠናል። በተለይ በግጭት ወቅት ከአውድ ውጭ እና አሳሳች በሆነ መልኩ የሚጋሩ ምስሎች ለሀሰተኛና አሳሳች መረጃ ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማጋራታን እንዲሁም ከማመናችን በፊት ተገቢውን ማጣራት እናድርግ። ኢትዮጵያ ቼክ
#FactCheck የአሜሪካው ፕሬዚዳንት አማካሪ ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ላይ አቋም ወስደዋል ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሐሰተኛ ነው /ኢትዮጵያ ቼክ/- የአሜሪካው ፕሬዚዳንት የመካከለኛው ምሥራቅ፣ የአረብ አገራት እና የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ማሳድ ቡሎስ አገራቸው በፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ላይ የጠነከረ እርምጃ ትወስዳለች ብለው ተናግረዋል ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ መሠረት የሌለውና ሐሰተኛ መሆኑን ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት አረጋግጧል። ከ193 ሺህ በላይ ተከተዮች ያሉት «ጌትነት አልማው ጥሩነህ» የተባለው የፌስቡክ ገፅ ይህ ከፍተኛ የአሜሪካ መንግሥት ኃላፊ «ፀረ-ኢትዮጵያ አደረጃጀቶች ላይ አሜሪካ እርምጃ እንደምትወስድ ተናግረዋል» በሚል የተሳሳተ መረጃ አጋርቷል። ይህ የፌስቡክ ገፅ ያሰራጨው መረጃ አሳሳች መሆኑ ሳይታወቅ በበርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መልሶ እንዲሰራጭ እና የህዝብን ትኩረት እንዲስብ ተደርጓል። ኢትዮጵያ ቼክ ያደረገው ጥልቅ ማጣራት እንደሚያሳየው ማሳድ ቡሎስ በይፋዊ የኤክስ (X) ገፃቸው ላይ ባጋሩት መግለጫ አሜሪካ የተባለውን ዓይነት እርምጃ ትወስዳለች የሚል ንግግር አላደረጉም። ማሳድ ቡሎስ በሰጡት ቀጥተኛ ማብራሪያ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ያተኮረው የአሜሪካ ዲፕሎማሲ «ፀረ-ኢትዮጵያ ጥምረትን ለማጠናከር እየሞከረ ነው» ተብለው በየቦታው የቀረቡት ዘገባዎች ሙሉ በሙሉ ውሸት አሳሳችና ህዝብን የሚያሳስቱ መሆናቸውን በግልጽ አስረድተዋል። በተጨማሪም አሜሪካ ከኢትዮጵያ እንዲሁም ከሌሎች የአፍሪካ ቀንድና የሰፊው ቀይ ባሕር ቀጣና አገሮች ጋር በጋራ የልማት፣ የሰላምና የደህንነት ጉዳዮች ላይ በቅርበትና በትብብር እየሰራች እንደምትገኝ ገልጸዋል። የአሜሪካ ዲፕሎማሲ ዋነኛ አላማ ተፎካካሪ ጎራዎችን መፍጠር ወይም የቀጣናውን ቅራኔዎች ማጥበቅ ሳይሆን ግጭቶችን በማስቀረት ዘላቂ ሰላምና ደህንነትን ማረጋገጥ እንደሆነ አብራርተዋል። በሌላ በኩል መቀመጫውን ፓሪስ ያደረገው «አፍሪካ ሪፖርት» (The Africa Report) የተባለው የዜና ምንጭ በቅርቡ ባወጣው የትንታኔ ዘገባ የአሜሪካ ዲፕሎማሲ በግብፅ-ሶማሊያ-ኤርትራ ምህዋር በኩል እና በኢትዮጵያ-ሶማሊላንድ-እስራኤል ምህዋር በኩል ባለው አህጉራዊ ፖለቲካዊ ውጥረት መካከል ሊወጠር እንደሚችል አመላክቷል። ይህ የትንታኔ ዘገባ የቀጣናውን ፖለቲካዊ ሁኔታ የሚያስረዳ እንጂ ማሳድ ቡሎስ እርምጃ እወስዳለሁ ብለው የተናገሩትን የሚያረጋግጥ አይደለም። በፖለቲከኞች፣ በዲፕሎማቶች እና በታዋቂ ሰዎች ስም ያልተናገሩትን ንግግር እንደተናገሩ አስመስሎ ማሰራጨት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሰፊ ተቀባይነት ለማግኘት የሚደረግ የተለመደ የሐሰተኛ መረጃ (Disinformation) ስልት ነው። ስለሆነም የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንደዚህ ያሉ አጠራጣሪና የፖለቲካ ትኩሳት ያላቸውን መረጃዎች በሚያነቡበት ጊዜ፣ መረጃው የወጣበትን ድረ-ገፅ ታማኝነትና ትክክለኛነት አስቀድመው እንዲያረጋግጡ እና ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማጋራት እንዲቆጠቡ ይመከራል። ኢትዮጵያ ቼክ!
#FactCheck በአሜሪካ የአማራ ማህበር ስም የተሰራጨው መግለጫ ሐሰተኛ መሆኑን ተቋሙ አስታወቀ /ኢትዮጵያ ቼክ/- በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ ከሰሞኑ በስፋት ሲሰራጭ የነበረውንና በአሜሪካ አማራ ማህበርን (AAA) የደብዳቤ ቅርፅ እና አርማ የያዘውን መግለጫ አስመልክቶ ማህበሩ በዛሬው ዕለት ለኢትዮጵያ ቼክ መረጃ አጋርቷል። በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚል ቀን የተጻፈበትና የአሜሪካ አማራ ማህበርን ህጋዊ አርማ የያዘ የአቋም መግለጫ በሰፊው ሲያሰራጩ ቆይተዋል። ይህ በስፋት የተሰራጨው መግለጫ ስለ አማራ ሕዝብ የትግል አቅጣጫና የወቅቱ የፖለቲካ ሁኔታዎች ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ሀሳቦችን ያካተተ ነው ተብሎ ነበር። ነገር ግን መረጃው በስፋት መሰራጨቱን ተከትሎ የአሜሪካ አማራ ማህበር በጉዳዩ ላይ አስቸኳይ ይፋዊ ማብራሪያና ማሳሰቢያ ሰጥቷል። ማህበሩ በላከው መግለጫ መሰረት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዘዋወረ ያለው ሰነድ በማህበሩ ያልተዘጋጀና ሙሉ በሙሉ የተፈበረከ ሐሰተኛ መረጃ መሆኑን ጠቁሟል። ድርጅቱ ምስሉ ላይ ትልቅ የቀይ “FAKE” (ሐሰተኛ) የሚል ማህተም በማስቀመጥ ደጋፊዎቹ እና የሕዝብ አባላት በተሳሳተ መረጃ እንዳይደናገሩ አሳስቧል። እንደ ማህበሩ ገለጻ ከሆነ ይህ የተቀናበረ ሐሰተኛ መግለጫ የመነጨውና መጀመሪያ የተሰራጨው ከመንግስት ጋር ግንኙነት ካላቸው አካላት ወይም "የገዥው አካል አፈቀላጤዎች ገጽ ላይ ነው" ብሏል። በተጨማሪም በአሜሪካ የአማራ ማህበር ማንኛውም አይነት ይፋዊ መግለጫ፣ መረጃና አቋም የሚለቀቀው በድርጅቱ ህጋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች እና በኦፊሴላዊ ድረ-ገጹ ላይ ብቻ መሆኑን አብራርቷል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሰራጭ የነበረውና የማህበሩ አርማ ያለበት መግለጫ ሙሉ በሙሉ የተፈበረከ መሆኑን ድርጅቱ በመግለፁ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲቆጠቡና መረጃዎችን ከተቋማቱ ህጋዊ ገጾች ብቻ እንዲከታተሉ ይመከራል። ኢትዮጵያ ቼክ!
#FactCheck በጮቄ ሰንሰላታማ ተራራ የተማረኩ ጦር መሳሪያዎች በሚል በሰበር መልኩ እየተጋሩ ያሉ ምስሎች በሰው-ሰራሽ አስተውሎት የተፈበረኩ ናቸው /ኢትዮጵያ ቼክ/- ‘በጮቄ ሰንሰላታማ ተራራ የተማረኩ የጦር መሳሪያዎችን ያሳያሉ’ የተባሉ ምስሎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተጋሩ ይገኛሉ። በምስሎቹ በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል መሀመድ ተሰማ ከሌሎች ሁለት ግለሰቦች ጋር ቆመው ከፊታቸው ደግሞ በርከት ያሉ የጦር መሳሪያዎች ተደርድረው ይታያሉ። ምስሎቹን “ሰበር መረጃ” በማለት ካጋሩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች መካከል ‘ዲጂታል ኢትዮጵያ’ የሚል ስም ያለው የፌስቡክ ገጽ ይገኝበታል። ይህ ገጽ “ከጮቄ ሰንሰለታማ ተራራ ዛሬ ብቻ 75 ክላሽ 1ዲሽቃ 2 ብሬን ጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ተረክቧል” የሚል ጽሁፍም ከምስሎቹ ጋር አጋርቷል። በተመሳሳይ መልኩ 'ሀገሬ ሚዲያ’ የሚል ስም ያለው የፌስቡክ ገጽም ምስሎቹን እና የጽሁፍ መረጃውን ያጋራ ሲሆን 35 የፌስቡክ ተጠቃሚዎች በገጹ የተጋራዉን መረጃ መልሰው አጋርተዉታል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቼክ የጉግል ምርት የሆነውና በሰው-ሰራሽ አስተውሎት የተፈበረኩ ምስሎች፣ ቪዲዮ እና ድምጾችን ለማጣራት በሚረዳው ‘SynthID Detector’ በመጠቀም ምስሎቹን መርምሯል። በዚሁ መሰረት ምስሎቹ ጉግል ኤአይ (Google AI) በመጠቀም የተፈበረኩ መሆኑን ተመልክተናል። በተጨማሪም ምስሎቹን በምልሰት በመፈለግ (reverse image search) ባደረግነው ማጣራት አንዳንዶቹ ምስሎች ትክክለኛ የሌተናል ጀነራል መሀመድ ተሰማ ምስልን ይዘት በመቀየር የተሰሩ መሆናቸዉን አረጋግጠናል። ትክክለኛው የጀነራሉ ምስል በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ትክክለኛና የተረጋገጠ የፌስቡክ ገጽ ከሁለት ቀናት በፊት የተጋራ ሲሆን በአማራ ክልል የተደረገን ኦፕሬሽን በማስመልከት የተጋራም ነበር፡ https://www.facebook.com/share/p/1BuimH7V2p/?mibextid=wwXIfr የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ከምስሉ ጋር ባጋራው የጽሁፍ 'ምስራቅ ዕዝ በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጣናዎች ባደረገው ፀረ-ሽምቅ ስምሪት ፈረስ ቤት ፣ ዋሸራ ፣ ጫት ዋርካ ፣ ሐሙስ ገበያ ፣ ሰከላ እና ሌሎች ቀጣናዎች የነበረው ፅንፈኛ ተደምስሷል’ ብሏል። የሰው-ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም የሚፈበረኩ እና ከአውድ ውጭ የሚጋሩ ምስል እና ቪዲዮዎች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጣራት እናድርግ። ኢትዮጵያ ቼክ
#Explainer ድምጽ ማቸገን (voice cloning) ምንድ ነው? ጉዳቱስ? እንዴት መከላከል እንችላለን? የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂዎች ፈጣንና የማያቋርጥ እድገት ለሰው ልጆች በርከት ያሉ ዕድሎችን ይዘው ስለመምጣታቸው በተደጋጋሚ ሰምተናል፣ በአንጻሩ ቀላል የማይባሉ ጉዳቶችን እያስከተሉ ስለመሆናቸውም አድምጠናል። ለምሳሌም በእነዚህ ቴክኖሎጂዎች የሚፈበረኩ ምስሎች፣ ቪዲዮዎች እና ጽሁፎች የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን በማባባስ ረገድ በመጫዎት ላይ ያሉትን አሉታዊ ሚና መጥቀስ ይቻላል። ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopiacheck.org/home/disinformation-threats-posed-by-voice-clones-and-how-to-combat-them/
#FactCheck የገቢዎች ሚኒስቴር ዴኤታዋ "በዚህ አመት ከእገታ አምስት ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል" ብለዋል በሚል ማህበራዊ ሚድያ ላይ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ ነው /ኢትዮጵያ ቼክ/- በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በርካታ ተከታዮች ባሏቸው ገጾች እና ግለሰቦች ዘንድ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ በቴሌቪዥን መስኮት ቀርበው "በዚህ አመት ከእገታ አምስት ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል" ብለዋል የሚል ጽሁፍ (Caption) የተለጠፈበት ምስል በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል። ይህ እየተሰራጨ ያለው ምስል የፎቶ ማቀናበሪያ መተግበሪያዎችን በመጠቀም የተቀነባበረ እና ሀሰተኛ መረጃን ለማስተላለፍ ሆን ተብሎ የተሰራ መሆኑን አረጋግጠናል። ትክክለኛው እና ያልተቆረጠው ምስል የተወሰደው የገቢዎች ሚኒስቴር ሚያዚያ 01 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ ካጋራው መረጃ ላይ ነው። ዋናው መረጃ የሚያወራው የዩናይትድ ኪንግደም የግብር፣ የክፍያ እና የጉምሩክ ባለሥልጣን (HMRC) በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ሲያካሂደው የነበረውን የታክስ ትራንፎርሜሽን ፕሮግራም ድጋፍ (Tax Transformation Program) ማጠናቀቁን በሚመለከት ነው (ሊንክ: https://www.facebook.com/share/p/1A2mhcT8s1/) በዚህ መድረክ ላይ የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ ተገኝተው ውይይት ያደረጉ ሲሆን የተሰራጨው ሀሰተኛ ምስል ከዚሁ እውነተኛ የፎቶ ስብስብ ላይ ተቆርጦ የተወሰደ ነው። ቅንብሩን የሰሩት አካላይ ይህንን ትክክለኛ ምስል በመውሰድ፣ የቴሌቪዥን ዜና እይታውን ትክክለኛ በማስመሰል እና ከስሩ "በዚህ አመት ከእገታ አምስት ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል" የሚል የሀሰት የሆነ ጽሁፍ በማስገባት አሰራጭተውታል። ማህበረሰቡ ይህ ምስል የተጭበረበረ እና ከእውነተኛ መረጃ ላይ ተቆርጦ የተወሰደ መሆኑን ተገንዝቦ እንዲህ አይነቱን ሀሰተኛ መረጃ ከማመን እና ከማጋራት እንዲቆጠብ ኢትዮጵያ ቼክ ይመክራል። ኢትዮጵያ ቼክ! @EthiopiaCheck
видео или голосовое, без подписи
#FactCheck የአርሰናል ደጋፊዎች ‘የዶ/ር ዐቢይ ታማኝ ደጋፊ ነን’ የሚል መልዕክት የያዘ ባነር ይዘዉ የተነሱት ፎቶ በሚል እየተጋራ የሚገኝ ምስል በቅንብር የተሰራ ነው /ኢትዮጵያ ቼክ/- ባለፉት ቀናት አርሰናል የ2025/2026 ውድድር ዘመን የእንግሊዙ አርሰናል የእግር ኳስ ክለብ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ መሆኑን በማስመልከት የተለያዩ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ከተማ ተካሂደዋል። በዝግጅቶቹም የክለቡ የቀድሞ ተጫዋች ኢማኑኤል ኢቦዬን ጨምሮ የAFTV ሚዲያ አባላት ከክለቡ ደጋፊዎች ጋር ተገናኝተዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም አንድ በቤተመንግስት ሙዝየም ውስጥ የተነሳ ምስል የበርካቶችን ቀልብ የሳበ ሲሆን መነጋገሪያም ሆኗል። ይህ ምስል ኢማኑኤል ኢቦዬን፤ የAFTV ሚዲያ አባላት እና ሌሎች ግለሰቦች/ የቡድኑ ደጋፊዎች “ለመሪያችን ዶ/ር ዐቢይና ለክለባችን አርሰናል ታማኝ ደጋፊ ነን” የሚል ባነር ጀርባ ቆመዉ ይታያል። ምስሉን ካጋሩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች መካከል ‘Wollo Addis’ የተሰኘ የፌስቡክ ገጽ የሚገኝ ሲሆን ገጹ ያጋራውን ምስል ከ50 በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰዉ አጋርተዉታል፣ ከ2 ሸህ በላይ አስተያቶችም ተሰጥተዉበታል። ኢትዮጵያ ቼክ የዚህን ምስል ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የተለያዩ መገልገያዎችን ተጠቅሟል፣ እንዲሁም በምስሉ ላይ ጥልቅ ምልከታ እና የማመሳከር ስራ ሰርቷል። በቅድሚያ የተነካኩና ይዘታቸው የተቀየረ ምስሎችን ለመመርመር የሚረዳዉን ፎቶ ፎረንሲክስ ድረ-ገጽ በመጠቀም ባደረግነዉ ማጣራት በምስሉ ዉስጥ የሚገኘውና “ለመሪያችን ዶ/ር ዐቢይና ለክለባችን አርሰናል ታማኝ ደጋፊ ነን” የሚል ጽሁፍ የያዘው ባነር በቅንብር የተካተተ መሆኑን የሚያሳይ ትንተና አግኝተናል። በተጨማሪ ‘illuminarty.ai’ የተሰኘዉን ድረ-ገጽ በመጠቀም በባነሩ ላይ ባደረግነዉ ምርመራ ባነሩ በሰው-ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተሰራ መሆኑን (88%) የሚያሳይ መረጃ አግኝተናል። በሌላ በኩል ምስሉን በማግዘፍ ባደረግነው ጥልቅ ምርመራ ባነሩን ይዘው የሚታዩ እጆች ቅርጻቸው የተዛባ እና ትክክለኛ ያልሆኑ መሆናቸውን ተመልክተናል። በተጨማሪም በምስሉ በስተቀኝ ዳር ላይ የቆመ ግለሰብ የእጅ ጌጥ ምስሉ በመነካካቱ ይዘቱ የተቀየረ መሆኑን ተመልክተናል። ኢትዮጵያ ቼክ በእለቱ የተነሱ እና የተቀረጹ ምስሎች እና ቪዲዮችን በመመልከትም የማመሳከር ስራ ሰርቷል። በቤተመንግስት ሙዝየም የተነሳውና ትክክለኛ ፎቶ ላይ በስተግራ ጥግ የሚገኝ ግለሰብ የታችኛው የእግር ክፍል ‘I love Addis Ababa’ በሚለው የፎቶ ፍሬም የተደበቀ ነው። ነገር ግን “ለመሪያችን ዶ/ር ዐቢይና ለክለባችን አርሰናል ታማኝ ደጋፊ ነን” የሚል ጽሁፍ የያዘው ባነር ላይ ግለሰቡ ጥቁር ቆዳ መሳይ ጫማ ተጫምቶ ይታያል። ኢትዮጵያ ቼክ የግለሰቡን የእለቱን እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ምስሎች እና ቪዲዮዎች የተመለከተ ሲሆን ግለሰቡ በእለቱ የተለያዩ ቀለማት ያለው ስኒከር ጫማ ተጫምቶ እንደነበር ተመልክቷል። ይህም ባነሩ ያለበት ምስል ከትክክለኛው ምስል ላይ ‘I love Addis Ababa’ ሚለውን የፎቶ ፍሬም በማጥፋት በምትኩ የግለሰቡ የታችኛው የእግር ክፍል ላይ በሰው-ሰራሽ ክህሎት ሀሰተኛ ጫማ የተካተተ መሆኑን አረጋግጠናል። በዚሁ መሰረት ከላይ የተዘረሩትን ቴክኖሎጂን እና የባለሙያ ምልከታን በመጠቀም ባደረግነዉ ማጣራት “ለመሪያችን ዶ/ር ዐቢይና ለክለባችን አርሰናል ታማኝ ደጋፊ ነን” የሚል ጽሁፍ የያዘው ባነር ትክክለኛ ያለሆነ እና በቅንብር የተካተተ መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል። ትክክለኛ ምስሎች ላይ የተፈበረኩ ይዘቶችን በመጨመር የሚጋሩ መልዕክቶች ለሀሰተኛ እና የተሳሳተ መረጃ ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ከማመናችን እና መልሰን ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጣራት እናድርግ። ኢትዮጵያ ቼክ @EthiopiaCheck
видео или голосовое, без подписи
#FactCheck በረቀቀ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቅንብር ተሰርቶ ማህበራዊ ሚድያ ላይ እየተጋራ የሚገኘው ቪዲዮ ምንነት /ኢትዮጵያ ቼክ/- አንድ የፋኖ አባል ለመንግስት እጅ እንደሰጠ የሚጠቁም የጽሁፍ እና የቪዲዮ መረጃ በማህበራዊ ትስስር ገጾች በስፋት እየተጋራ ይገኛል። ይህ የተሰራጨው የጽሁፍ መረጃ “የዘመነ ካሴ አብሮ አደግ እና የዘመነ ካሴ ቀኝ እጅ ቴዎድሮስ የደሜ የሚመራውን ታጣቂ አሰልፎ ወደ ሰላም መጥቷል” የሚል መልዕክት ያዘለ ነው። በተጨማሪም በቪዲዮው ላይ የሚታየዉ ግለሰብ “እኔና ጓደኞቼ ከመንግስት ጋር በመስማማት እጃችንን የሰጠን ሲሆን ከሻብያ ተላላኪዉ ዘመነ ካሴ ጋር የነበረን ግንኙነት በዚ አብቅቷል” ሲል በግልጽ ይደመጣል። ይህን የጽሁፍ እና የቪዲዮ መረጃ በስፋት ካጋሩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች መካከል ‘የፍቅር መንገድ’ እና ‘ዲጂታል ኢትዮጵያ’ የሚባሉ የፌስቡክ ገጾች በዋነኝነት ይገኙበታል። በተለይም ‘የፍቅር መንገድ’ በተሰኘዉ ገጽ የተጋራዉን ይኸንን የጽሁፍ እና የቪዲዮ መረጃ ከመቶ አርባ በላይ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መልሰው ለሌሎች ያጋሩት ሲሆን በርካታ አስተያየቶችም ተሰጥተዉበታል። ይህንን ጉዳይ ተከትሎ ኢትዮጵያ ቼክ መረጃውን ለማረጋገጥ ባደረገው ጥልቅ ምርመራ ቪዲዮው ፈጽሞ እውነተኛ እንዳልሆነ አረጋግጧል። ኢትዮጵያ ቼክ የጉግል ምርት የሆነዉን ‘ሲንዝ አይዲ ዲቴክተር’ (SynthID Detector) የተባለውን ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መተግበሪያ በመጠቀም በቪዲዮው ላይ ባደረገዉ ማጣራት የተሰራጨው ምስል ትክክለኛ ሰውን እንደማያሳይ ደርሶበታል። በዚሁ የምርመራ ውጤት መሰረት በቪዲዮው ውስጥ የሚታየው ምስልም ሆነ የሚሰማው ድምጽ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቴክኖሎጂ አማካኝነት ሙሉ በሙሉ የተቀነባበረ የፈጠራ ውጤት መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል። በቪዲዮው ላይ የሚታየው የከንፈር እንቅስቃሴ፣ የፊት ገጽታ እና የድምጽ ቅንብር አንድን ትክክለኛ ሰው አስመስሎ በኮምፒውተር ፕሮግራም የተሰራ እንጂ በገሃዱ ዓለም የተፈጠረን ክስተት የሚያንጸባርቅ አይደለም። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚፈበረኩ መሰል የዲፕፌክ (Deepfake) ቪዲዮዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ በጣም እየተበራከቱ እና በርካታ ሰዎችን ለተሳሳተ መረጃ እያጋለጡ ይገኛሉ። አጥፊ እና አሳሳች መረጃ አሰራጪ አካላት እነዚህን እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመጠቀም እውነተኛ የሚመስሉ ነገር ግን ፈጽሞ ያልተፈጠሩ ክስተቶችን በመፍጠር ህብረተሰቡን በማሳሳት ላይ ይገኛሉ። ይህ አይነቱ ቴክኖሎጂ የፖለቲካ ውዥንብር ለመፍጠር፣ የተሳሳቱ ትርክቶችን ለማራመድ፣ እና የሰዎችን ስነልቦና ለመጉዳት ሆን ተብሎ የሚሰራጭ አደገኛ የሀሰተኛ መረጃ (Disinformation) መሳሪያ ሆኗል። በተለይም አሁን ባለንበት ወቅት የፖለቲካ እና የጸጥታ ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግ ግለሰቦች ያልተናገሩትን እንደተናገሩ አድርጎ በማቅረብ ህብረተሰቡ የተዛባ መረጃን አምኖ እንዲቀበል ማድረግ የተለመደ የማጭበርበር ስልት ሆኖ ብቅ ብሏል። ሰዎች እውነተኛ ቪዲዮ እየተመለከቱ እንደሆነ በማሰብ እንዲታለሉ እና የተዛባ መረጃን ለሌሎች በማጋራት በማህበረሰቡ ውስጥ አለመተማመንን መፍጠር የዚህ አይነቱ ተግባር ዋና አላማ ነው። ስለሆነም የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ይህንን እያደገ የመጣውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት አደጋ በሚገባ ተገንዝበው ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እንመክራለን። ማንኛውም አጠራጣሪ እና ተአማኒ ባልሆኑ የመረጃ ምንጮች ወይም ግለሰቦች የሚጋሩ የምስል እና የቪዲዮ መረጃዎችን ልክ እንዳዩት ከማመናችን እና መልሰን ለሌሎች ከማጋራታችን በፊት ተገቢዉን ማጣራት ማድረግ አለብን። ቪዲዮዎች ያልተለመደ የዓይን ብልጭታ፣ ከድምጽ ጋር የማይሄድ የከንፈር እንቅስቃሴ ወይም ኢተፈጥሮአዊ የሆነ የቆዳ ገጽታ ካላቸው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውጤቶች ሊሆኑ ስለሚችሉ በጥሞና መመርመር ያስፈልጋል። ኢትዮጵያ ቼክ! @EthiopiaCheck
видео или голосовое, без подписи
#MediaMonitoring ጄነራል ታደሰ ወረደ ታገቱ በሚል የተሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ለኢትዮጵያ ቼክ ተናገሩ /ኢትዮጵያ ቼክ/- የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት የነበሩት ጄነራል ታደሰ ወረደ መታገታቸውን ወይም የቁም እስረኛ መደረጋቸውን አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጠዋል። ይህ መረጃ ባለፉት ጥቂት ቀናት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮች ባፈሩ የፌስቡክ ገጾች እና ግለሰቦች አማካኝነት በከፍተኛ ሁኔታ ሲጋራ ቆይቷል። ከመረጃው ዋነኛ አሰራጮች መካከል ወደ 480 ሺህ የሚጠጉ ተከታዮች ያሉት "አንዳፍታ" የተሰኘው የፌስቡክ ገጽ እና ከ507 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት "አባይ ሚዲያ" የፌስቡክ ገጽ ይገኙበታል። በተጨማሪም ከ161 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት "ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ" የተባለው ግለሰብ የፌስቡክ ገጽ ጄነራል ታደሰ የቁም እስረኛ እንደሆኑ የሚገልጽ ተመሳሳይ ዘገባ ከሌላ ገፅ ወስዶ አጋርቷል። ኢትዮጵያ ቼክ ጉዳዩ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ መሆኑን ተከትሎ እውነተኝነቱን ለማረጋገጥ በቀጥታ ከጄነራል ታደሰ ወረደ ጋር በስልክ ተገናኝቶ የጠየቀ ሲሆን በማጣራቱም ጄነራሉ እንዳልታገቱና የቁም እስረኛም እንዳልተደረጉ ምላሽ ሰጥተዋል። በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ለዘገባቸው ዋቢ ያደረጉት «አፍሪካ ኢንተለጀንስ» (Africa Intelligence) የተሰኘው የዜና ተቋም መሆኑን ቢጠቅሱም ተቋሙ ባወጣው ዘገባ ላይ እሳቸው ስለመታገታቸውም ሆነ የቁም እስረኛ ስለመሆናቸው የጠቀሰው ነገር እንደሌለ አብራርተዋል፣ ይህንን ኢትዮጵያ ቼክም አረጋግጧል። ጄነራል ታደሰ ወረደ ለኢትዮጵያ ቼክ በሰጡት የቀጥታ ምላሽ "ታግተሃል አልያም የቁም እስረኛ ሆነሃል ለሚለው አሁን እያናገርከኝ ነው፤ እኔ አልታገትኩም፣ የቁም እስረኛም አልተደረግኩም፤ የAfrica Intelligence ያወጣው ዘገባ ላይም እኔ እንደታገትኩም አልያም የቁም እስረኛ እንደሆንኩ አልገለጸም" ብለዋል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የታዋቂ ሰዎችን እና የፖለቲካ መሪዎችን ስም በመጠቀም ያልተናገሩትን እንደተናገሩ፣ ያልሆኑትን እንደሆኑ አድርጎ ማሰራጨት የተለመደ የሀሰተኛ መረጃ ስልት መሆኑ ይታወቃል። የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መሰል አጠራጣሪ እና የፖለቲካ ትኩሳት ያላቸውን መረጃዎች ሲያነቡ መረጃው የወጣበትን ድረ-ገጽ ታማኝነት እንዲያረጋግጡ እና ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማጋራት እንዲቆጠቡ እንመክራለን። ኢትዮጵያ ቼክ! @EthiopiaCheck
видео или голосовое, без подписи
#FactCheck፡ ዶ/ር አርከበ እቁባይ 'African Pulse' ለተባለ ሚዲያ ሰጡት ተብሎ በስፋት የተሰራጨው ጽሑፍ እና ቃለ-ምልልስ በሀሰት የተፈበረከ መሆኑ ተረጋገጠ /ኢትዮጵያ ቼክ/ -- የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ የነበሩት ዶ/ር አርከበ እቁባይ “አፍሪካን ፐልስ” (African Pulse) ለተባለ ድረ-ገጽ ሰጡት የተባለው እና በማህበራዊ ሚዲያ በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ ያለው ፖለቲካዊ ትንታኔ እና አስተያየት ከእሳቸው ያልወጣ እና በሀሰት የተፈበረከ መሆኑን ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጠዋል። 'African Pulse' በተሰኘው ድረ-ገጽ ላይ “ስትራቴጂካዊ ራስን ማጥፋት - ዶ/ር አርከበ እቁባይ የህወሓትን አመራር አምርረው ተቹ” በሚል ርዕስ የተጻፈ ጽሑፍ በዛሬው ዕለት ወጥቷል። ይህ የፈጠራ ጽሑፍ ዶ/ር አርከበን በማስመሰል በርካታ ከባድ የፖለቲካ ትችቶችን የቀድሞ ድርጅታቸው ህወሓት ላይ እንደሰነዘሩ አድርጎ ያቀርባል። ጽሑፉን ይበልጥ እውነተኛ ለማስመሰልም ዶ/ር አርከበ ስለ ጦርነቱ አጀማመር፣ ስለ ፖለቲካዊ ስህተቶች እና ስለ ድርጅቱ መጻኢ ዕጣ ፈንታ ተናግረዋል ያላቸውን የሀሰት ሀሳቦች አካቷል። በዚህም የቀድሞ የትግል ጓዶቻቸው በስትራቴጂካዊ ድክመት እና በፖለቲካዊ እልህ ውስጥ ወድቀው የትግራይን ህዝብ ህልውና አደጋ ላይ እንደጣሉ እና ጦርነቱ የተጀመረው በስሜት እንጂ በፖለቲካዊ ስሌት እና በበቂ ዝግጅት እንዳልነበረ በጽሑፉ ላይ ተጠቅሷል። በተጨማሪም አመራሩ የፌደራል መንግስቱን እና የሌሎች ኃይሎችን ጥምረት መገመት አለመቻሉን እንደተቹ፣ እንዲሁም የድርጅቱ አመራሮች ለለውጥ ዝግጁ እንዳልሆኑ እና አሁን ባለበት የዲፕሎማሲ እና የኢኮኖሚ ውድቀት ውስጥ ሆኖ ዳግም ስለ ጦርነት ማሰብ የድርጅቱን ህልውና ሙሉ በሙሉ የሚያጠፋ እንደሆነ አድርጎ አስነብቧል። ይህ ዶ/ር አርከበ ሰጡት የተባለው የፈጠራ ጽሑፍ በዋናነት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተከታዮች ባፈሩ የፌስቡክ ገጾች እና ግለሰቦች አማካኝነት በስፋት ተጋርቷል። ከእነዚህም መካከል ወደ 186 ሺህ የሚጠጉ ተከታዮች ያሉት ጄዚራ አፍሪካ የተባለ ገፅ ይህንኑ ሀሰተኛ መረጃ አጋርቷል። በተመሳሳይ ከ91 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ቬነስ ዜና የተሰኘ የፌስቡክ ገፅ ጽሑፉን ያሰራጨ ሲሆን ከ33 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት Nebyat Alemu የተባለ ገፅም ይህንኑ መረጃ ተቀብሎ ለተከታዮቹ አጋርቷል። እነዚህ ገጾች በአጠቃላይ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮች ያሏቸው በመሆኑ ይህ ሀሰተኛ መረጃ ብዙሃን ዘንድ እንዲደርስ እና በአንባቢዎች ዘንድ ከፍተኛ ብዥታ እንዲፈጥር ምክንያት ሆኗል። ኢትዮጵያ ቼክ ይህ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ መሆኑን ተከትሎ የጉዳዩን እውነተኛነት ለማረጋገጥ በቀጥታ ዶ/ር አርከበ እቁባይን ጠይቋል። በማጣራቱም ዶ/ር አርከበ 'African Pulse.org' ለሚባለው ድረ-ገጽ ምንም ዓይነት ቃለ-ምልልስም ሆነ የጽሑፍ አስተያየት አለመስጠታቸውን አረጋግጠዋል። ዶ/ር አርከበ ለኢትዮጵያ ቼክ በላኩት ቀጥተኛ ምላሽ ላይ ለ Pulse.org ቃለ-ምልልስ ሰጥተው እንደሆነ ተጠይቀው እንደነበር ገልጸው ምንም አይነት ቃለ-ምልልስ አለመስጠታቸውን አስረግጠው ተናግረዋል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ታዋቂ ሰዎችን እና የፖለቲካ ሰዎችን ስም በመጠቀም ያልተናገሩትን እንደተናገሩ አድርጎ ማሰራጨት የተለመደ የሀሰተኛ መረጃ ስልት ነው። የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንደዚህ አይነት አጠራጣሪ እና የፖለቲካ ትኩሳት ያላቸውን መረጃዎች ሲያነቡ መረጃው የወጣበትን ድረ-ገጽ ታማኝነት እንዲያረጋግጡ እና ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማጋራት እንዲቆጠቡ እንመክራለን። ኢትዮጵያ ቼክ! @EthiopiaCheck
видео или голосовое, без подписи
#EthiopiaCheck "በወልቃይት ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ለቀረበ ጥያቄ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የተሰጠ መልስ እንደሆነ በመጥቀስ እየተጋራ የሚገኝ ደብዳቤ ሀሰተኛ ነው" —አቶ አገኘሁ ተሻገር /ኢትዮጵያ ቼክ/- የፌዴሬሽን ምክር ቤት በወልቃይት ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ለቀረበለት ጥያቄ የሰጠዉን መልስ የያዘ እንደሆነ የተገለጸ ደብዳቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች እየተዘዋወረ ይገኛል። ይህ ደብዳቤ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር ስም የሰፈረበት ሲሆን ግንቦት 12፣ 2018 ወጪ የተደረገ እንደሆነም በደብዳቤዉ ተጠቅሷል። የደብዳቤዉ ዋና ይዘት ደግሞ ‘በወልቃይት ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ የቀረበዉ የማንነትና ራስ ገዝነት አስተዳደር ውሳኔ ጥያቄ ተቀባይነት የሌለዉ እና ሙሉ በሙሉ ውድቅ የተደረገ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት በጥብቅ ያሳውቃል” የሚል ነው። ይህን ደብዳቤ ካጋሩ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች መካከል ‘ደጀን ግራካሕሱ ሚዲያ ኔትዎርክ’ እና ‘ቤት ፅሕፈት ህወሓት ከተማ ኮረም’ የሚሉ የፌስቡክ ገጾች ይገኙበታል። ይሁን እንጂ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በተረጋገጠ የፌስቡክ ገጻቸው ባጋሩት ጽሁፍ ደብዳቤው ሀሰተኛ መሆኑን ገልጸዋል። አፈ ጉባዔው “የፌዴሬሽን ምክር ቤት በወልቃይት ጉዳይ ያወጣው መግለጫ በሚል በማኀበራዊ ሚዲያ የሚዟዟረው ደብዳቤ ፍጹም ሐሰትና በቅንብር ፎቶ የተሰራ መሆኑን እየገለፅኩ ይህን የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩት እነማን እንደሆኑ አጣርተን ለህግ የምናቀርብ መሆኑን እንገልፃለን” ብለዋል። አፈ ጉባዔው በፌስቡክ ገጻቸው ያጋሩት መረጃ በዚህ ማስፈንጠሪያ ይገኛል፡ https://www.facebook.com/share/p/14h6RpnEwNE/?mibextid=wwXIfr ኢትዮጵያ ቼክ @EthiopiaCheck
#FakeAccountAlert በሸዊት ውዳሴ ስም የተከፈቱ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገፆች ማሳሰቢያ /ኢትዮጵያ ቼክ/- በመምህር እና የፖለቲካ ተንታኝ ሸዊት ውዳሴ ስም እና ምስል የተከፈቱ በርካታ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገጾች መኖራቸውን ደርሰንበታል። እነዚህ ገጾች የግለሰቡን ማንነት በመጠቀም የተለያዩ መረጃዎችን እያጋሩ የሚገኙ ሲሆን አንዳንዶቹም ህዝብን የሚያሳስቱ ይዘቶች እንዳሏቸው ተመልክተናል። መምህር ሸዊት በሀገራዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በሚሰጣቸው ትንታኔዎች እና በትምህርት ዘርፍ ባለው ተሳትፎ የሚታወቅ ግለሰብ ነው። ሸዊት ውዳሴ ለኢትዮጵያ ቼክ እንዳረጋገጠው የእሱ ብቸኛው እና ትክክለኛው የፌስቡክ ገጽ https://www.facebook.com/share/18iYLyc8Yu/ ነው። ይህ ገጽ በአሁኑ ወቅት ከ72 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ሲሆን ግለሰቡ ትክክለኛ መረጃዎችን እና የራሱን ሐሳቦች የሚያጋራበት ዋነኛ መድረክ ነው። ከዚህ ትክክለኛ ገጽ በተጨማሪ ከ5 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት እንዲሁም ሌላ ከ2 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ተመሳሳይ ስም እና ምስል የሚጠቀሙ ገጾች ተለይተዋል። እነዚህ ገጾች የሸዊት ውዳሴ እንዳልሆኑ ተረጋግጧል። የታዋቂ ግለሰቦችን፣ የመንግስት ባለስልጣናትን ወይም የተቋማትን ስም እና አርማ በመጠቀም የሚከፈቱ ገጾች አሳሳች መረጃዎችን በማሰራጨት በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ጫና ሲፈጥሩ ይታያል። ስለሆነም ማንኛውንም መረጃ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ከመጋራታችን ወይም ከመቀበላችን በፊት የገጹን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ተገቢ ነው። ሀሰተኛ እና ተመሳስለው የሚከፈቱ አካውንቶችን፣ ገጾችን እና ቻናሎችን በቀላሉ ለመለየት የሚረዱን ጠቋሚ ምልክቶችን ለማወቅ ኢትዮጵያ ቼክ ያዘጋጀውን አጭር እና አስተማሪ ቪዲዮ በዚህ ሊንክ መመልከት ትችላላችሁ፦ https://t.me/ethiopiacheck/1344 ኢትዮጵያ ቼክ @EthiopiaCheck
видео или голосовое, без подписи
#FactCheck የኢትዮጵያ የስንዴ ምርት መረጃ እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ሪፖርቶች ንጽጽር /ኢትዮጵያ ቼክ/- ሰሞኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ሰሉልታ አካባቢ የሚገኝ የስንዴ ማሳን በጎበኙበት ወቅት ኢትዮጵያ በዘንድሮው የምርት ዘመን ያስመዘገበችውን ውጤት በተመለከተ የሰጡት መግለጫ አነጋጋሪ ሆኗል። በመግለጫቸውም ሀገሪቱ በዚህ በጀት ዓመት ከ330 ሚሊዮን ኩንታል (33 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን) በላይ ስንዴ ማምረት መቻሏንና ይህም ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚዋ ስንዴ አምራች ሀገር እንደሚያደርጋት ገልጸዋል። ይሁን እንጂ ይህ በመንግስት በኩል የቀረበው አሀዝ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የግብርና እና የኢኮኖሚ መረጃ ተንታኝ ተቋማት ሪፖርቶች ጋር ሲነጻጸር እጅግ ከፍተኛ ልዩነት ይታይበታል። የአሜሪካ የእርሻ ዲፓርትመንት (USDA) የውጭ እርሻ አገልግሎት (FAS) እ.ኤ.አ በኤፕሪል 2024 እና በሜይ 2025 ባወጣቸው ተከታታይ ሪፖርቶች መሰረት የኢትዮጵያ ዓመታዊ የስንዴ ምርት በ6.5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን አካባቢ እንደሚገኝ ተገምቷል። ምንም እንኳን ተቋሙ በኢትዮጵያ የመስኖ ስንዴ ልማት እና የክላስተር ግብርና ምርታማነትን እየጨመረ መሆኑን ቢገልጽም የተመዘገበው ጭማሪ በመንግስት ከተጠቀሰው 33 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ጋር ሲነጻጸር በአምስት እጥፍ ገደማ ያነሰ ነው። ከዚህ በተጨማሪ የሳተላይት ምስሎችን እና የመሬት ላይ መረጃዎችን መሰረት ያደረጉ የUSDA ትንታኔዎች እንደሚጠቁሙት በኢትዮጵያ ለእርሻ የዋለው መሬት ስፋት እና የተገኘው ምርት መጠን መንግስት እንደሚለው "በአራት እጥፍ" አድጓል የሚለውን መረጃ አያረጋግጡም። በተመሳሳይ እንደ FAO (የዓለም የምግብ እና ግብርና ድርጅት) ያሉ ተቋማት መረጃዎችም የኢትዮጵያን ምርት ከ7 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ አያደርሱትም። ኢትዮጵያ "ግብፅን በሶስት እጥፍ በመብለጥ ከአፍሪካ አንደኛ ሆናለች" የሚለውን መግለጫ በተመለከተ ዓለም አቀፍ የንግድ እና የግብርና መረጃዎች የተለየ ምስል ያሳያሉ። የUSDA እና የኢንዴክስ ቦክስ (IndexBox) የ2024/25 ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ግብፅ በ9.2 እስከ 9.7 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ዓመታዊ ምርት አሁንም ከአፍሪካ ቀዳሚነቱን እንደያዘች ነው። ኢትዮጵያ በ6.5 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ምርቷ ከግብፅ ቀጥላ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። መንግስት ኢትዮጵያ ስንዴ ወደ ውጭ መላክ ጀምራለች ቢልም የዓለም አቀፍ የንግድ መረጃዎች (እንደ OEC ያሉ) ግን ኢትዮጵያ አሁንም ከፍተኛ መጠን ያለው ስንዴ ከውጭ እንደምታስገባ ያሳያሉ። ለምሳሌ እ.ኤ.አ በ2024 እና 2025 መጀመሪያ ላይ ኢትዮጵያ ከኬንያ፣ ሮማኒያ እና ቱርክ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር የሚያወጣ ስንዴ ገዝታለች። በተቃራኒው ወደ ውጭ የተላከው የምርት መጠን እጅግ ዝቅተኛ መሆኑ ተመዝግቧል። እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና በዓለም ባንክ የወጡ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት፤ በሀገር ውስጥ ገበያ ላይ የታየው የስንዴ ዋጋ ንረት (በአንድ ዓመት ውስጥ የ28% ጭማሪ) እና በምግብ እርዳታ ላይ የሚገኙ ዜጎች ቁጥር አለመቀነስ፣ ሀገሪቱ "ትርፍ ምርት አምርታለች" ከሚለው መግለጫ ጋር የሚጋጩ ተጨባጭ እውነታዎች ናቸው። በአጠቃላይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበው የ33 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የምርት ሪፖርት ከገለልተኛ ዓለም አቀፍ ተቋማት ግምቶች (ከ5.5 - 7 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን) ጋር እጅግ ሰፊ ልዩነት ያለው ሲሆን የሀገሪቱ የገቢ ንግድ መረጃ እና የገበያ ዋጋም የቀረበውን "ትርፍ ምርት" አያረጋግጡም። ኢትዮጵያ ቼክ @EthiopiaCheck