tgindex
ወርቃማው ቢራቢሮ

ወርቃማው ቢራቢሮ

Статистика

ነፃነት ምትፈልገውን ሁሉ ማድረግ ማለት ብቻ ሳይሆን ማትፈልገውንም አለማድረግ ነው!! ቢራቢሮዬ🦋 ለሀሳብ አስተያየትዎ @wordwhisper_bot ይጠቀሙ

Последний пост
13 февр.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
642
+1 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 485
20 постов
Вовлечённость
231,3%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ከሳሽ እና ተከሳሽ እውነቱን ያውቁታል....እየተፈተነ ያለው ዳኛው ነው። @wordwhisper🦋

  • መላመድ ጉልበት እንዳለው የምታውቀው መለያየት ሲመጣ ነው!! @wordwhisper🦋

  • #የማለዳ ስንቅ ራስህን አዝረክርከህ.....ይታዘቡኝ ይሁን? ኩራትህን ጥለህ ለምነህ......ይንቁኝ ይሁን? አላዋቂ ሆነህ ተገኝተህ.......ይጫወቱብኝ ይሁን? ሀሜት ምግቡ ሆነህ........ይሰለቹኝ ይሁን? ውሸትህን እያዘነብክ........ይደርሱብኝ ይሁን? በማለት አትጠመድ......ራስህን ግዛ!!!!! @wordwhisper🦋

  • እወድሻለሁ አልኳት <<አሁን ነው ትንሽ ያገገምኩት ፤ መሳቅ የጀመርኩት ፤ ብቻዬን መሆንን የለመድኩት ። አሁን ነው እንቅልፍ ሳልቸገር መተኛት የጀመርኩት ። አሁን ነው ሰበብ እያደረግኩ ፣ የሆነውን እያስታወስኩ መነፋረቅ ያቆምኩት ። >> እኔ እኮ.. ..አቋረጠችኝ ለቁምነገር ነው የምፈልግሽ ...አከብርሻለሁ ... እወድሻለሁ ...እታመንሻለሁ... አልከዳሽም ....ልትለኝ ነው አይደል ? ሁሉንም ተብያለሁ ተወኝ ትንሽ ብቻዬን መሆንን ላጣጥመው ፤ ትንሽ ማገገሜ ይታወቀኝ ...ተወኝ >> እሺ ...ግን እውነቴን ነው ብሎ እውነተኛም አለ ፣ ኋላ ማየት ኋላ ያስቀርሻል ፣ ህይወት ወደፊትም ነው .....አሁንም አቋረጠቺኝ <እሱንም ተብያለሁ......>> እሺ ..አልኳት ከትላንቱ ጋ የተጣበቀን ሰው ነገን ማሳየት ከባድ ነው © Adhanom Mitiku @wordwhisper🦋

  • ውድና የተከበራቹ የቻናሉ ቤተሰቦች ያው ብቅ ጥልቅ ማለቴ ትዕግስታቹን እየተፈታተነው እንደሆነ ሳልረዳ ቀርቼ አይደለም ግን በአንዳንድ ግላዊ ምክንያት ፅሁፎቼን ወደናንተ ማድረስ እየቻልኩ አይደለም። በቻልኩት መጠን ራህዋን ጨምሮ ሌሎች ፅሁፎችን ወደናንተ ለማድረስ እጥራለው እስከዛው በትዕግስት እንድትጠብቁኝ ስል በትህትና ጠይቃለው። @wordwhisper🦋

  • ምንድነው ዝምታው ሞቅ ሞቅ አርጉት እንጂ leave ለማለት እያሰባቹ ያላቹ አድቡ አድቡ🙄

  • ጥረትህን አይቶ ማንም አይገረምም። ውጤቱ አሪፍ ከሆነ ያደንቁሀል ካልሆነ ይንቁሀል....አላማችንን ማሳካቱ ላይ እናተኩር!! @wordwhisper🦋

  • "ያለ እናንተ መኖር አንችልም ያሉት ከሄዳችሁ ወዲያ መኖር ቀጥለዋል ለእናንተ የተፃፈ የፍቅር ደብዳቤ ከእናንተ በኋላ ለመጡት ተፅፈዋል ለእናንተ ተሰምቶናል ያሏችሁ ስሜቶች ድጋሚ ተሰምቷቸዋል እናንተን በጠሩበት ስም የጠሯቸውም አሉ የለቀቃችሁት መስሪያ ቤት በምትካችሁ አዲስ ሰራተኛ ቀጥረውበታል ምናልባት ከሞታችሁም በኋላ መጉደላችሁ እስከማያስታውቅ ድረስ አድምተው ይኖራሉ እና አሁንም ራሳችሁን አታስቀድሙም?" @wordwhisper🦋

  • አዲስ ልቦለድ ይጀመር ዎይይይይ??? ማሳሰቢያ፦ማንኛውንም አይነት reaction እንደ አዎ ነው ምወስደው😁

  • የሆነን ነገር <<ኧረ በፍፁም አላደርገውም >>ከማለት ይልቅ <<አምላኬ የምገደድበት ሁኔታ ውስጥ አይክተተኝ>> ማለት የተሻለ ነው......አትሻብኝ ይላል ሀበሻ። @wordwhisper🦋

  • እሳትን እፍ ማለት አንድም ለማጥፋት አንድም ለማቀጣጠል....ተግባራችንን እየተጠነቀቅን!! @wordwhisper🦋

  • <<ጉዳዩን ለጊዜ ተወው። የመዓት ጉድ ይሰራል። አንዳንድ ገፆች በፈገግታህ ብቻ እንዴት እንደሚጠቀለሉ ፣ የማታልፈው የመሰለህን ጉዳይ እንዴት በቀዝቃዛ ልብ እንዳለፍከው ፣ የተወሰኑ ህልሞችህን በፍቃድህ እንዴት እንደተሰናበትካቸው ትመለከታለህ። አንዳንድ ጉዳዮችህ ይሞቱና ሌሎች አዳዲስ ጉዳዮችህ ሲወለዱም ታያለህ።......ዘመን።>> @wordwhisper🦋

  • ይቅርታ አርጉላቸው......ስለሚገባቸው ሳይሆን አዕምሯቹ ከነሱ ነፃ መሆን ስላለበት... @wordwhisper🦋

  • "መነፅር ስላረክ ብቻ ሁሉም ነገር ጥርት ብሎ እኔጋ ይደርሳል ብለህ አታስብ አንዳንዴም መነፅሩ መፅዳት እንዳለበት አትዘንጋ!" @wordwhisper🦋

  • 💫ራህዋ💫 #ክፍል 3⃣0⃣ በቢራቢሮዬ          "ኡፍፍፍፍ እንዴት አባሽ ነው ምታምሪው እ ምናይነት የመልዐክ ፊት ነው ይሄ??  ባልጎዳሽ ምንኛ ደስ ባለኝ ዓለም ነበር ለኔ እንዴት እንደማፈቅርሽ ቢገባሽ ግን እያፈቀርኩሽም ቢሆን ዛሬ ማታ ከህይወቴ ላባርርሽ እገደዳለው። እንዲ ስል ካንቺ መራቁ ሚያስደስተኝ አልመስልም?ጉዳቴን የማውቀው እኔ ነኝ። ከኔ ጉዳት በላይ አንቺን መጉዳቴ፤ ያንቺን እንባ ማየቴ፤ ለማገገም ጊዜ እንደሚወስድብሽ ማሰቤ ይሰብረኛል። ሲጀመር እኔኮ መጥፎ ሰው ነኝ አልገባሽም እንደኔ አይነቱ ላንቺ አይገባም....ግን አሁን ለራሴ ምንም ማድረግ አልችልም ትከሻዬ ላይ እናቴ አደራ ያለቺኝ ሴት አለች....እህቴ። በምን መጥፎ ቀን ተገናኝታቹ ለጠላትነት እንደበቃቹ....የኔ ህይወት ምስቅልቅሉ ወጣኮ..." ይኼን ብሎ ሳይጨርስ ራህዋ <<ረመኀይ??>> አለችው.....ሲያወራ የነበረው በሆዱ ስለነበር ምንም ልትሰማው አልቻለችም። "ንግስት ሆይ እንቅልፍ ያበዙ አልመሰለዎትም.....መቼስ ቤት አራት አምስት ቦታ ሚበታተኑትን ሰራተኞችሽን ተማምነሽ ነዋ እንዲ ምተኚው እ ረመኀይን እነሱ ሰርተው ያበሉታል ብለሽ" <<አረረረረረ እኔ ጋ እንደዚ አይነት ቀልድ የለም የራስህን ምግብ ራስህ ሰርተህ ትበላ እና የኔን ደግሞ አግባብ ባለው መንገድ ጥፍጥ አርገህ ትሰራልኛለህ። የሰራተኛማ አልበላም አንተ እያለህ>>......ፊቷን ለጉድ አመናቅራ አየችው። "ምን ምን ምንንንን...ጆሮዬ ነው? ድገሚው እስቲ አልሰማሁሽም.....አይይ 21ኛው ክፍለዘመን ጭራሽ 'አንተ እያለህ' ጉድኮ ነው ሌላ ፈልጌ ማግባት ነው እንጂ 'ፍቅሬ ተነስ ቁርስ ደርሷል' ብላ እየሳመች ምትቀሰቅሰኝን ካንቺ ጋማ አልቀጥልም..." ተርሳው የቆየችውን ትራስ ወርውራ ንግግሩን አቋረጠችው። <<ደግመህ እንደዚ አይነት የጅል ወሬ ስታወራ እንዳልሰማ!!>>....ፊቷ እሳት ሲለብስ ታየው። ያለችበት የቅናት መንፈስ ስላስደሰተው ከት ብሎ ሳቀ። <<ምናባህ ያስገለፍጥሀል?? ያማረብህ መስሎሀል አሁን>> "ተይ በናትሽ አሁን እየቀናሽ መሆኑ ነው??" ሳቁን ደገመው። <<እድልህ ይረገም አቦ....ዞር በልልኝ አሁን>> በእጆቿ ገፍትራ ከራሷ አራቀችው። "ትሰሪልኛለሽ አሰሪልኝም እ" በክንዱ አንገቷን ይዞ ወደዚ ወደዚያ ያረጋት ጀመር። በሱ የተጀመረ ልፊያ ክፍሉን እንዳልነበር አድርገው ውጥንቅጡን አወጡት።      <<ፍቅር ሻወር ልውሰድ በቃ>> ብላ ወደ ክፍሉ ባኞ ቤት አመራች። እሱም ተነስቶ ከተጣጠበ በኃላ ልብሷን አንድ በአንድ ያለብሳት ጀመር። <<እንዴት አባህ ነው ባክህ ምታፈቅረኝ?>> "ተቆጥሮ እንደማያልቀው ኮከብ" <<ኮከቦቹ ጥለውት እንደሄዱት ጥቁር ሰማይ አታረገኝማ?>>.....በቀድሞው መልሱ ፈንጥዛ ሌላ የማረጋገጫ ማህተም እንዲመታላት ያስከተለችው ጥያቄ ነበር። እሱ ግን ያለችው ጥቁር ሰማይ ስባሪ ትከሻው ላይ የወደቀ ይመስል ድንጋጤ ዋጠው። <<ፍቅር ምነው ዝም አልክ አትመልስልኝም እንዴ?>> "እ...እ..ምን ም..ን አልሺኝ የኔ ቆንጆ የቀሚሱ ዚፕ እምቢ ብሎኝ እኮ ነው....ደግሞ እኔ ራሴ ሳልዘጋጅ ሰዓቱ ሄደኮ"....ጥድፍ ጥድፍ እያለ ልብሱን መለባበስ ጀመረ።ራህዋ የረመኀይ ሁኔታ ግራ ቢሆንባትም ለጊዜው ትኩረቷ የሚደረግላት እራት ግብዣ ላይ ስለነበር ልታግዘው ወደሱ ተጠጋች። "እውነት ይሄን ማድረጌ ልክ ነው?.....ምን ነካህ ረመኀይ ነገሩን ልትቋጨው የተወሰኑ ሰዓታት እኮ ነው የቀሩህ......ረመኀይ አሁንም እድል አለህ እንዳታጣት እባክህን!!.....ተው ረመኀይ ለአንዲት ሴት ብለህ የእናትህን አደራ ልትበላ ነው?.....ግንኮ...." በነዚ መነሻቸው ከመድረሻቸው በማይለዩ ሀሳቦች የተዋጠው ረመኀይ ራህዋ ሸሚዙን እየቆለፈችለት እንደነበር አላስተዋለም።...... @wordwhisper🦋

  • ጊዜ ፣ ክስተት እና ሰው በራሱ ሌላ ሰው ያደርግሀል። ተስፋ ያልቆረጠብኝ ሰው ይኖር ይሁን?🥺 @wordwhisper🦋

  • ብዙ ጊዜ ምክንያትህ ላንተ መስካሪህ ሲሆን ለሌላው ግን ይግባኝ መጠየቂያ ሰበብ መስሎ ይታየዋል🙃 @wordwhisper🦋

  • አንዳንዴ እኛም ቀበጥ ነን....ህይወታችን ውስጥ እየከፈለ ቢቆይ ማያዋጣ ሰው እኮ ነው እኛነታችንን እየከፈልን ምናቆየው..... @wordwhisper🦋

  • .......አሁን በራልኝ አለች አንዲት ሚስኪን ቤቷን አቃጥላ... @wordwhisper ⚡️⚡️

  • ሆኖልህ በየቀኑ ትተውናለህ። እንዳዲስ ቲያትር ከፊት ሆኜ አይሀለው። አልቆ ላታመሰግነኝ እኔም ላላጨበጭብ..... 3 ኪሎ❤️‍🩹 @wordwhisper🦋