- Последний пост
- 10 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 150
- 1/48двое суток
- 171
- 1/72трое суток
- 185
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
አንድ እቅፍ አንድ እቅፍ… ወደ እራስህ ጠጋ አድርጎ፣በሁለት እጆች ጠበቅ አድርጎ፣ ለአፍታ ከዓለም ለይቶ ወደ ልብ ብቻ የሚያደርስ መንገድ። ከልብ ወዳጅነት የተወለደ፣ ከናፍቆት የተሞላ፣ ከፍቅር የሚፈስ ያ ረጅም እቅፍ… በእቅፉ ውስጥ ሰምጠህ፣ የሌላውን የልብ ምት እየሰማህ፣ የራስህን ጭንቀት ለአፍታ ትረሳለህ። አንድ እቅፍ ሺህ የደከሙ ሕዋሶችን ያነቃል፣ ሺህ ጭንቀቶችን ይቀንሳል፤ ከዚያም… ደስታን በደም ሥሮች ውስጥ ይረጫል፤ ሰላምን በደረት ውስጥ ያሰፍራል፤ የነበረውን ድካም በረጋ ስሜት ይተካል። አንድ እቅፍ እኮ ናት… ግና ዓለምን ታስረሳለች፣ ልብን ታድሳለች፤ ስክነትን እና እዝነትን ታላብሳለች፤ የተዘጋ ልብን በቀስታ ትከፍታለች፤ የተሰበረ ልብን ምንም ሳትናገር ትጠግናለች። እና እቅፉ ሲያበቃ… ልብ ግን አይለይም........ያ ሙቀት ይቀራል፤ ያ የልብ ምት በሰውነት ውስጥ ሂወትን ይዘራል፤ እና ያ አንድ እቅፍ የነገን ሌላ እቅፍ ያስናፍቃል። ምክንያቱም… አንድ እቅፍ ናት እኮ፤ ግና ዓለምን ታስረሳለች። አንድ እቅፍ ናት እኮ፤ ግና ልብን እንደገና ታስጀምራለች። አንድ እቅፍ ናት እኮ… አቃፊያቹን ፈልጉ... ✍️Mewla @with_apen @with_apen
የሰው ልጅ አእምሮ ከሚያጋጥመው ነገር ውስጥ አንዱ Compassion Fatigue ወይም የርህራሄ ድካም ተብሎ የሚጠራ የተፈጥሮ ክስተት አለ። በግሌ ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ ከሚያጋጥሙኝ ክስተቶች አንዱ ነው፤ ማለትም ይደጋገምብኛል። አእምሮዬም ብዙ ኢሞሽን ለሚጠይቁ ነገሮች ቶሎ Shutdown ያደርጋል። እዚህ በመፖሰቴ ምን እና ማንን እንደሚጠቅም ባላውቅም፣ በተጨማሪም ሴቶችን ለተመለከቱ ጥቃቶች aggressive ባልሆን እንኳን (cuz of my emotional numbness) #ትሰማ ማለት እፈልጋለሁ። ©glex @with_apen @with_apen
ሙላ ነስሩዲን ፍርድ ቤት ቀረበ። ሙላ፦ ክቡር ፍርድ ቤት፣ ይህ ሰው ሰድቦኛል! ዳኛ፦ ምን ብሎ ሰደበህ? ሙላ፦ “እናትህን” ብሎኛል። ዳኛው ወደ ተከሳሹ ዞር ብለው፦ ለምን ሰደብከው? ተከሳሹ፦ እኔ አልሰደብኩትም። “እናትህን እና” ነው ያልኩት። “እናትህን እና” ማለት ደግሞ ስድብ አይደለም። ዳኛውም ነገሩን አመዛዝነው ከተመለከቱ በኋላ፦ ዳኛ፦ “እናትህን እና” ብቻውን ስድብ አይደለም። ነጻ ነህ! ሙላ፦ ክብር ፍርድ ቤት እናትህን እና ስድብ አይደለም? ዳኛ፦ አዎ። ሙላ፦ በቃ...... ክብር ዳኛ.. እርስዎም “እናቶትን...” 😄 ✍️Mewla @with_apen @with_apen
👨🔬 ስሚማ አሁን ይሄ ሁሉ የዚ ሬስቶራንት ተጠቃሚ እንደዚ የሚያፈጥብን ምን የሚያፈጥብን እላለሁ የሚያፈጥብኝ ይሄ አመዳም አህያ ፀጉር አጭር (መሬት ለመሬት) የሰው በትር ቆዳ ቅብ የደሀ ብርቅ ከዚች የውበት ፈርጥ ከዚች ልዕልት ጋር ምን ያደርጋል....እያሉ ይሆናል እኮ ቀና ብላ አየቻቸው እና 🧕ወንዶች ቆንጆ ስታዩ እንደዛ ነው የምትሉት ...? አዎ ...እኛኮ ሲጀመር ከቆንጆ ሴት ጋር ወንድ ብናይ አይመጥናትም ነው የምንለው። 🧕እና ማነው የሚመጥናት እንደነዚ የሚያፈጡብኝ ወንዶች ነዋ ... 🧕አንተም እንደዛው ነው የምታስበው... አይ እኔ ብዙ ወንድ የሚፈልጋት ቺክ አትመቸኝም 🧕እና እኔ አልመችህም... ዝም...... 🧕ደሞ ስለ ምትፈልገው አደለም የጠየኩህ ስለ ምታስበው ነው..😡? ምንድን ነው ነገር ነገር እያለሽ ነው እንዴ ወሬዎቼን በጥያቄ አሳደድሻቸው.. ...? 🧕በነገራችን ላይ አንተ ባረፈድክበት ሰዐት ከነዚ ውስጥ አራቱ ስልኬን ተቀብለውኛል.....🙄 እና የተመቸሽ የለም...? 🧕ማለት ? ስልክሽን ሰጠሻቸው...ወይ..? 🧕ያንተን 🙄እኔ ደላላሽ ነኝ ወይስ ማኔጄርሽ...? 🧕እንሄድም ወይ...? ደሞ በአላፊው በአግዳሚው ልታማ .... 🧕ምነው ታፍርብኛለህ ... አዎ በውበትሽ .... 🧕ቀውስ ስርዐት ያዢ እህቴ እንጂ ጌታዬ አደለሽም...አሳምተሽኝም ...ተሳድበሽም ..ወንድምነቱ ያንሰኛል ✍️Mewla @with_apen @with_apen
ሁሌ የሚመስለኝ... ሳምፀው የዋልኩት እኔ በመተኛት አመፄን እዘነጋው እና ጀሊልም የረሳልኝ ይመስለኛል... ✍️Mewla @with_apen @with_apen
ተወው .... (ድካም) የደከመው ሰው መጀመርያ መናገር ይተዋል አይወድም መተ:ውን ቀስ እያለ ለምዶ... ራሱንም ትቷል ኧረ እሱ ኮ ብለው ሼም እያስያዙት ....ሀሳቡን ይተዋል ይፈልጋል እኮ እባክህ ተብሎ...... ድርሻውን ይተዋል። የደከመው ሰው ሰዎችን ይተዋል ፤ ራሱን ይተዋል ፤ ነገንም ይተዋል መኖር እስከሚተው መፈለግ ይተዋል። መ:ተውም መተው:ም ... ልማዱ ይሆናል። መተው ምን ይከብዳል .....? ከሁሉ የሚያሳዝነው ግን ይህ ነው፤ ሰው መኖርን ራሱ እስኪተው ድረስ መፈለግን ይተዋል። ስለዚህ የደከመውን ሰው አትፍረድበት ዝምታው ትዕቢት ላይሆን ይችላል፤ መተዉም ግዴለሽነት ላይሆን ይችላል። ምናልባት የተዋቸው ነገሮች ብዙ ስለሆኑ፣ ከእንግዲህ የሚተወው ራሱ ብቻ ቀርቶት ይሆናል። እና ያን ጊዜ የሚያስፈልገው ፍርድ አይደለም፤ መረዳት ነው። ወቀሳ አይደለም፤ አንድ የሚያዳምጥ ልብ ነው። ምክንያቱም አንዳንድ ሰዎች መተውን የመረጡት ሕይወትን ስለጠሉ ሳይሆን፣ ሕይወት እነሱን በብዙ ጊዜ ስለተወቻቸው ነው። ✍️Mewla @with_apen @with_apen
ያዙኝ… ልሂድ እንዳትተዉኝ… ዞር በሉልኝ እየጠሉ… ለመውደድ መላላጥ እየተገፉ… እቅፍን አለመልቀቅ አልጠገብኩም ግን… በቃኝ አይነት ተለያይተናል ግን… እንገናኛለን ሞቷል ግን… እስትንፋሱ አለ መሞት አልፈልግም ግን… ቅበሩኝ አይነት። ነውር ነው ግን… ትንሽ ልባልግ ጀነት እፈልጋለሁ ግን… ጀሀነምን ባየው ከእንደዚህና ከእንደዚያ አይነት ነገሮች አውጥተህ፣ "ለዚህ ነው" ብለን እንዳፌዝንባቸው፤ ቀደምት ችግሮቻችን አሁን ያለንበትንም ሆነ ወደፊት የሚመጣብንን ሁሉ የምንቋቋምበትን አቅም ስጠን። አሚን። 🤲 ✍️Mewla @with_apen @with_apen
ዳሩል አርቀም የበጎ አድራጎት ማህበር የ follow ዘመቻ ላይ ይገኛል ። ማህበሩ ብዙ ኸይር ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ ሲሆን አብሽሩ ኪሳችሁን አንነካም ዝም ብላችሁ follow ብቻ አርጉና ኸይር ስራ ስሩ ይሏቹሀል ። https://www.tiktok.com/@darularkemislamicjemaa?_r=1&_t=ZM-934EacdfaY4
ዳሩል አርቀም የበጎ አድራጎት ማህበር የ follow ዘመቻ ላይ ይገኛል ። ማህበሩ ብዙ ኸይር ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ ሲሆን አብሽሩ ኪሳችሁን አንነካም ዝም ብላችሁ follow ብቻ አርጉና ኸይር ስራ ስሩ ይሏቹሀል ። https://www.tiktok.com/@darularkemislamicjemaa?_r=1&_t=ZM-934EacdfaY4
ከልቤ በቦረቅኩባቸው ቀናቶች የደስታዬን ስር መሰረት ለኔ ምን ማለት እንደሆነ የምታውቀው አንተ ብቻ ሆነህ መጋራት አለመቻል እንዴት እንደሚያም...ደሞ እንደዚህ የወረደ ስሜት ውስጥ ስሆን የማይጨበጥ ነገር ሳወራበት የሚያደምጠኝን ሰው መራቅ እንዴት እንደሚያደማ። አልነግርህም እንጂ. . .እቺ አሁን ያልኩህ ህመሜ ጠና ስትልብኝ ራስ ወዳድ መሆን....የማውቀውን እውነት ከአይንህ የማነበውን ከወንድምነት የዘለለ ስሜት መካድ ያምረኛል። ግን ከህመሜ...ከብቸኝነት ስሜቴ በላይ የሆነ እሴት አለኝ መሰለኝ ልመጣ አልቻልኩም። ከወንድምነት...ከንፁህ ጓደኝነት ባሻገር ያለ ፍቅር በልባቸው እንደጠነሰሱ እያወቁ ምቾታቸውን ለመጠበቅ ችላ ብለው እዛው ክበብ ውስጥ ለመቆየት እንደሚመርጡ ሴቶች መሆን አልችልም። ያ የምትጠባበቀው ፆታዊ ፍላጎት እኔ ጋር እንደማይመጣ እያወኩ ተስፋን ማቀበል አይሆንልኝም። አልክድም። በአንድ በኩል ውስጤ መስመሬን እንድስት ምቾቴን እንዳስቀድም ይጎተጉተኛል። በሌላ በኩል አጉል ህሊና የሚባል ተፈጥሮዬ ስሜትህ መቀየሩን ካወኩ ጀምሮ ወዳንተ የማደርጋቸው እርምጃዎች ወደፊትህን እየረገጥኩ እንደመመጣ፣ ተስፋህን በባዶ እንደማስቀጥል ያስታውሰኛል። በማደግ ከከፈልኩት ሁሉ የአንተ ሰማዕትነት ያስጠላኛል። ሳዝን ተወው መሳቄን ተካፋይ ነው ያሳጣኝ። Glamor : @with_apen @with_apen
« ልንገናኝ እንለያያለን፣ ልንለያይም እንገናኛለን። እስቲ ደግሞ መግራት የፈለግነውን ከገራን ወዲህ፣ ለማድረግ እጅጉን የሚከብደን የሚመስለንን ነገር አድርገን ከልባችን ጋር ከተያየን በኋላ፣ አጉል እንዳንዘም የአደብ ልጓማችንን መያዝ መቻልን ከተለማመድንበት፣ ምንም ነገር ከሰላማችን እንደማይበልጥ ከተዋወስንበት፣ አበቃ የምንለው ቀደር ይዞ የሚመጣውን አለማወቃችን መሆንን ከተገነዘብንበት፣ በጊዜ ውስጥም…
« ልንገናኝ እንለያያለን፣ ልንለያይም እንገናኛለን። እስቲ ደግሞ መግራት የፈለግነውን ከገራን ወዲህ፣ ለማድረግ እጅጉን የሚከብደን የሚመስለንን ነገር አድርገን ከልባችን ጋር ከተያየን በኋላ፣ አጉል እንዳንዘም የአደብ ልጓማችንን መያዝ መቻልን ከተለማመድንበት፣ ምንም ነገር ከሰላማችን እንደማይበልጥ ከተዋወስንበት፣ አበቃ የምንለው ቀደር ይዞ የሚመጣውን አለማወቃችን መሆንን ከተገነዘብንበት፣ በጊዜ ውስጥም የምንማረውን ከተማርን በኋላ ዳግም የመገናኘትን ፍቃድ ለሰጠን አዛኝ አመስግነን እንደ ቀድሞው ቀለማችን እንጀምር። ሰላም ለሁላችሁም! » [ አብዱልሀኪም ሰፋ ] : @Venuee13 @Venuee13
ኒቃብ ያንቺን ታዛዥነት ወዶታል ረበና ከላይሽ ልቀቂው ላንቺም ለኔም ጤና። ...ተቀበል... የውበትሽ ድምቀት ሀላልሽ ይናገር ብትገላለጪ ጨረቃና ፀሀይ ይሸሸጉ ነበር። ✍️Mewla @with_apen @with_apen
ውስጤም የሚለኝ ከበደ ሚካኤል እንዳለው ነው። ጽድቅ እና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም። : @with_apen @with_apen
ኒቃብ ከኒቃብ የሚሻል ልብስ የለም ባንቺ ላይ ውብ የሚያደርገሽ ከከዋክብት በላይ። ✍️Mewla @with_apen @with_apen
ኒቃብ እኔን ለመጠበቅ ኒቃብ አጥልቀሻል ውዷ የኔ እህት በልቤ ገዝፈሻል። ✍️Mewla @with_apen @with_apen
«አንቺን መውደድ እንደሚደክመኝ አታይም? ምናለበት እንድወድሽ ሙሉ ፍቃድ ብትሰጪኝ። ተከራክሬሽ እዚው መሆኔን...አኩርፌሽ ተመልሼ ማዋራቴን ብቻ አትዪ ውስጤ እየደቀቀ ነው። አለሽ ብዬ እንዳልፅናና ታደርጊኛለሽ። እንዲህ ናት የምልሽ ነገር ያልኖረኝ ነኝ ስላንቺ! ወደ አለምሽ ስመጣ ስለሚመቸኝ ምክኒያቱን ሳላውቀው ስለምዝናና ሌላ ሰው ስለምሆን ነው ያለሁት እንጂ የለሁም። ትልቅ ሰው ነኝ የልጅነት አፍላ እድሜ ላይ ልክ ነው ብለን የምንለው አለም 'እርግጠኛ አለመሆን' 'ሚስጥራዊነት' ላይ ትጨምሪኛለሽ። የበሰለ ሰው ፍቅር ግልፅነት እርግጠኝነት ላይ የተመሰረተ ነው።» አለኝ የምወደውን ወተት በትኩስ በትኩሱ ጠጥቼ እስክጨርስ ጠብቆ! ወተት ከፈላ በኋላ ማስቀመጥ እንደማልወድ ያውቃል። ትክ ብዬ አየሁት። እሱ በሚመለከተው ነገር ውስጥ ምን እንደሚያነብብኝ አላውቅም እኔ ግን እሺ ብቻ በማለት ንግግራችንን እንዳልዘጋበትም ብዙ እንድለውም እንደፈለገ ሁለቱም መልሴ እንዳስፈራው ታይቶኛል። "ምን ላድርግ" አልኩት። "በንግግርህ ብገረም እንዲህ ስባል የመጀመሪያዬ ቢሆን ደስ ይለኝ ነበር እንዳደገ ሰው ካንተ እድገት ጋር አለመግጠሜ የማልታገለው ግን የማዝንበት ጉዳዬ ነው የሚሆነው። በመጠፋፋት አላምንም በመንገድ በጉዞዬ ገንብቼ ያመጣሁት አለም አለኝ። ሰባራ ሳንቲም ያህል እንደምትወደኝ አልጠራጠርም። ጥንቃቄህን አጠባበቅህን አየዋለው። ትታየኛለህ። ግን ደሞ የትኛውም የሂሳብ ቀመር የትኛውም ሳይንስ አንተ በገነባኸው አለም ውስጥ ፍቅር እንደማይበቃኝ የምናገርበትን ፍልስፍና አያብራራልህም። ግራ መጋባትህን ጥያቄ ውስጥ አላስገባም ባይገባህ አልደነግጥም።" ብዬ ዝምታ ወረሰኝ። «እፈራለው» አለ።«የምትወጃቸው ነገሮች ያስፈሩኛል። ስትለቂም ስትይዢም ተመሳሳይ መሆንሽ አለመቀየርሽ ያስፈራኛል። እንዲህ ቁጭ ብለን ስላንቺ እያማረርኩ አንቺን ላንቺ ሳማልሽ የምትሰጪኝ ነፃነት ያስፈራኛል። በቃ እፈራለው ፍላጎቴና ስላንቺ ያለኝ እውቀት አለመግጠም ያስፈራኛል።» " እውነቱን ለመናገር ሁሌም እንዲህ ነህ በንግግርህ በኔ እርግጠኛ ካለመሆንህ በላይ ያየሁት መቦረቁን መቋቋም ካልቻለው ቁምነገረኛ ማንነትህ ጋር ትግል እንደገጠምክ ነው።" የሚል ቃል ወጣኝ ጨከን ያልኩበት ለውሳኔ እንዲመቸው እንዲደላው እንጂ የሰዎችን ዩቶጵያም ሆነ የሚፈራውን ህፃንነታቸውን ማጋለጥ ወይ መሟገት አልወድም። "የምወዳቸውን ነገሮች ታውቃለህ ወደኔ እንድትሳብም መንገድ ከፍተውልሀል አካልህ እንዲሆኑ ንብረቴ እንድትላቸው ግን እነሱ ነገሮች እንዲቀረፉ ካንተ እንዲመሳሰሉ ትጠብቃለህ። ሰውን የምታወራውን ነገር ሳታቅድ መጥተህ ጥፍት ብሎ ሌላ አለም ላይ ራስን ማግኘትን መቀበል ከብዶሀል። የወደድከው ከሆነ ከኔ ጋር መሆኑን ሌላ አለም ውስጥ ካስገባህ እየተላተምክ ያለኸው እዛው ለራስህ ከሰጠኸው ምስል ጋር መሆኑን እወቅ። ዘመንሽን የመጣሽበትን መንገድ ትተሽ አንድ ሁኚ ማለት አትችልም ብዙ ገፅታ መኖር አካሌ ነው።" በማለት ጨርሼ ተራ ለቀቅኩለት። . . . . . . (ዝም ብሎ ዘለግ ላለ ጊዜ ከተመለከተኝ በኋላ) . . «ልቀቂኝ» አለ። ©Glamor : @with_apen @with_apen
без подписи
አጭርዬ ከኢስላም የሚበልጥ ልቤ ውስጥ ታጣ ኢስላሜ ነሽ አልኩሽ የኔ የጀነት ዕጣ። ✍️Mewla @with_apen @with_apen
እየጠበኩ ነው እየጠበኩ ነው ሄጃለሁ እስከትይኝ ሽማግሌም መጣ ብለሽ እንስክትነግሪኝ። እየጠበኩ ነው እንደማትመለሽ ቁርጡን እስክትነግሪኝ ላገባ ነው በለሽ ካርድ እስክትልኪልኝ። እየጠበኩ ነው የኔ ና ያንተ ነገር እዚጋ አበቃ ብለሽ እስክትይኝ። እየጠበኩ ነው በራሴ ላይ ተስፋ ስለሌለኝ እየጠበኩ ነው ሄጃለሁ እስክትይኝ። ✍️Mewla @with_apen @with_apen