- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 19
- Всего постов
- 34
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 338
- 1/48двое суток
- 1 582
- 1/72трое суток
- 1 706
Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.
Посты
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
ነብያዊው አስተምህሮ እንዲህ የሚል ነው። . ~ ተደሣች ሰው ለሰዎች ደስታ ራሱን አሳልፎ የሠጠው ነው። ~ እዝነትና ልስላሴ የገባበት ነገር ሁሉ ዉብ ነው። ~ ሻካራነትና ከርዳዳነት ዉጤቱ መጥፎ ነው። ~ አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ሥራ በአንድ ፍጡሩ ቀልብ ዉስጥ ደስታን ለማስረጽ የምታደርገው መፍጨርጨር ነው። ችግርህ ይወገድልህ ዘንድ ... ~ ችግረኛን ከችግሩ አስተንፍስ፣ ~ የራበውን መግብ፣ ~ የታረዘውን አልብስ፣ ~ የየቲምን ራስ አብስ፣ ~ ዘመድ ጎረቤትህን አስታውስ፣ ~ ዕዳ ለከበደው ሰርዝ፣ አላስተዋልንም እንጅ ~ በዕዳ ምክንያት ከሰል የመሰሉ ፊቶች አሉ። ~ በችግር የተነሣ መተንፈስ የከበዳቸው ነፍሦች አሉ። ምሽቱ የሚደምቀው በሰለዋት ነው። ጁምዓ ሙባረክ ! https://t.me/MuhammedSeidAbx
ለኔ ከስጦዎች ሁሉ የላቀ ስጦታ መጽሐፍ ነው። አመሰግናለሁ ።
ሦስት ነገሮች ያለ ቀጠሮ ነው የሚመጡት። ሲሳይ፣ ሞት፣ እና ቀደር። ሲሳይ /ሪዝቅ፥ ሲሳይህን ሰማይ ይሁን ምድር አንተ ቦታዉን አታውቀዉም፤ ድንገት ከተፍ ሊል ይችላል። ይመጣል ብለህ ማሰብ ነው። ሞት /አጀል፥ የሞት ቀንህ አልተነገረህም ፤ ድንገት ደርሶ ሊይዝህ ይችላል ። ጣጣህን ጨርሰህ ዝግጁ ሆነህ መጠበቅ ነው። ዕጣፈንታ/ቀደር ፥ በቀን ይሁን በማታ ዉስጥ አላህ ምን እንደወሰንልህ አታውቅም ፤ ድንገት ያላሰብከው ነገር ሊፈጠር ይችላል ። እሱ ሁሌም ሥራ ላይ ነው። ጥሩ ይሁን መጥፎ እሱ የለቀቀልህን መውደድ ነው። ሰባሐል ኸይር https://t.me/MuhammedSeidAbx
የዑምራ ጉዞዬ ትዝታ ክፍል ሦስት ምነው አይናፍቁ *** የጂዳን ኤርፖርት ፍተሻ ጥብቅ ሆኖ አላገኘሁትም፡፡ በዋናነት ከሻንጣ ዕቃዎች ይልቅ ሳይ ዶክመንትና የሰውዬው ማንነት ላይ ያተኩራሉ መሠለኝ፡፡ የዐይን አሻራ ሠጥተን ወደ ውስጥ ገባን፡፡ ይህ እንግዲህ የሳዑዲን ምድር የረገጥንበት የመጀመሪያው ቀን መሆኑ ነው፡፡ ዕቃዎቻችንን እስክንወስድ እና ለቀጣይ ጉዞ እስክንዘጋጃጅ ድረስ ትንሽ ሰዓት ወሰደብን፡፡ ከተርሚናሉ ውጭ ከጉዞ ወኪላችን ጋር ስምምነት ያላቸው አውቶቡሶች ቆመው እየጠበቁን ነው፡፡ ወደዚያው ሄድንና ከተመደብኩበት ከአንዱ አውቶቡስ ውስጥ ገባሁ፡፡ 11 ሰዓት ሲል አውቶቡሶቹ መንቀሳቀስ ጀመሩ፡፡ ጉዞ ወደ መዲና፡፡ አውቶቡሶቹ ቀይ ባህርን ወደ ግራ ትተው አፍንጫቸውን ወደ ሰሜን ምሥራቅ አድርገው ፍጥነታቸውን ጨመሩ፡፡ ጂዳ ብዙ ረጃጅም ሕንፃ የላትም ። መሬት ላይ ግን ሰፊ ከተማ ናት፡፡ በትንሹ ሀያ ደቂቃ ያህል ከተጓዝን በኋላ ከከተማዋ ወጣን፡፡ ቀጥሎ ጫፉ የማይታይ ለጥ ያለ ሜዳ ውስጥ ገባን፡፡ ቅልጥ ያለ የአሸዋ በረሀ ባህር፡፡ ለእርሻም ሆነ ለኑሮ የሚታሰብ አገር አይደለም፡፡ ሰፊውን በረሀ እያየሁ የሀሳብ ባህር ውስጥ ገባሁ፡፡ ከአሸዋማ በረሀ አልፎ የተቃጠሉ የሚመስሉ ጥቋቁር ሹል ድንጋዮች ማዶ ላይ ይታዩኛል፡፡ በአገሬ የዚህ ዓይነት አስፈሪ ድንጋይ አይቼ አላውቅም፡፡ ያላስተዋልነው ነገር ቢኖር እስልምና በዚህ የድንጋይ እና አሸዋ እሣት ውስጥ አልፎ ወደኛ መምጣቱን ነው፡፡ ሰዓቱ ከ11 በኋላ ቢሆንም መስኮቱ ትንሽ ሲከፈት ከውጭ የሚጋረፈው ወላፈን ያስደነግጣል፡፡ የአውቶቡሱ ኤሲ ያለማቋረጥ ቀዝቃዛ ንፋስ ይረጫል፡፡ መንገዱ ሰፊ እና ምቹ ነው፡፡ መንገድ ላይ በብዛት የሚታዩትም ምቹ አውቶቡሶች የቱሪስት የሚመስሉ ናቸው፡፡ የሚከንፉ እንጂ መሬት ላይ የሚሄዱ አይመስሉም፡፡ የኛው ሾፌር በሰዓት ከ100 በታች ፍጥነት የነዳበትን ጊዜ አላስታውስም፡፡ ከ1400 ዓመታት በላይ ወደኋላ ነጎድኩ፡፡ በዚህ ምድር ላይ ተወዳጁ ነቢያች (ሰ.ዐ.ወ.) እና ባልደረቦቻቸው ተመላልሰውበታል፡፡ በትግልም፣ በመልዕክትም ተንቀሳቅሰውበታል፡፡ አጥንታቸው ተከስክሷል፤ ደማቸው ፈሶበታል፡፡ ስደት፣ መከራ፣ እንግልቱን ሁሉ አይተውበታል፡፡ መሬቱ ሁሉ እነርሱን እነርሱን ሸተተኝ፡፡ አየሩና ጋራ ሸንተረሩ እነርሱን ሁሉ እነርሱን አወደኝ፡፡ የምንሄደው ወደ ብርሃናማዋ የረሱል ከተማ መዲና ቢሆንም፤ ወደ ከተማዋ ሳይሆን ቀጥታ ወደርሣቸው የምሄድ መስሎ ታየኝ፡፡ ሳስበው የሆነ ፍርሃት ወረረኝ፣ አመነታሁም፡፡ የኔ ዓይነቱ ተራና ርካሽ ሰው እንዴት የርሣቸው ክቡር ገላ ባረፈበት ከተማ ይገኛል!! አውቶቡሱ ለጉድ ይከንፋል፤ እኔም በመስኮት አሻግሬ ያን ጭው ያለ በረሀ አያለሁ፡፡ የርሣቸው ሂጅራ ትዝ አለኝ፡፡ በስደት ከመካ ወደ መዲና ሲወጡ ሙሽሪኮች ዱካቸውን እንዳያገኙ ብለው ወደ ደቡብ አቅጣጫ ከሄዱ በኋላ እንደገና የባህር ዳርቻውን መስመር ተከትለው ነበር ወደ ሰሜናይቱ መዲና ያቀኑት፡፡ በዚህ ስደት ነቢ ከባልደረባቸው አቡበክር ጋር በመሆን ለስምንት አድካሚ ጉዞ አድርገዋል፡፡ አቤት ሐቢቢ እኮ በኛ ላይ ያላቸው ውለታ፡፡ እያንዳንዱ ነገር ለማሰብ ሞከርኩ፡፡ የከፈሉልኝ ዋጋ እጅግ ገዝፎ ታየኝ፡፡ ወዲህ ያንን ጉዞ አስባለሁ፡፡ ወዲያ ደግሞ መዲነተ ረሱልንም የማየት ናፍቆት ያዞረኛል ….. ያች ነቢ ያረፉባትን ብርሃናማ ከተማ እንዴት ትቀበለኝ ይሆን!!! ድንገት ሳላስበው እንባዬ መጥቶ ዐይኔ ውስጥ ግጥም አለ፡፡ የኔ ዓይነቱ ውዳቂ ሰው ምን ብሎ ነው የርሣቸው ክቡር ገላ ያረፈበትን ከተማ ለማየት የሚሄደው … አውቶቡሱ ጉዞውን እንደደቀጠለ ነው፡፡ እኔም ወዴት እንደምሄድ አሳምሬ አውቃለሁ፡፡ ለአፍታም ቢሆን የመዲና ጉዳይ ከውስጤ አልጠፋም፡፡ መዲና ሲባል ነቢዩ፤ ነቢዩ ሲጠሩ መዲና ሁሌም የሚታሰብ ነው፡፡ እርሳቸውን ለመዘየር መንገድ የጀመረ ሰው ሰለዋት ያብዛ ይላሉ ኢማም ነወዊ ወረሕመቱላህ ዐለይሂ። እኔም ከጂዳ ከተነሳሁበት ጊዜ ጀምሮ ምላሴ ከሰለዋት አላረፈም። አልፉ ሶላቲ ወሰላሙ ዐለይከ ያ ሰይዲ ያ ረሱለላህ! አልፉ ሶላቲ ወሰላሙ ዐለይከ ያ ሐቢቢ ያ ረሱለላህ! አልፉ ሶላቲ ወሰላሙ ዐለይከ ያ ሸፊዒ ያ ነቢየላህ! አልፉ ሶላቲ ወሰላሙ ዐለይከ ያ ኸይረ ኸልቂላህ …. በዚህ አገር እንደ አገራችን ከተሞች ተቀራርበው አይገኙም፤ ከትላልቅ ከተሞች በስተቀር ትናንሽ ከተሞችም ብዙ የሉም፡፡ መግሪብ ሲደርስ ከአንዲት አነስተኛ ከተማ ወረድን፤ የሚቀማመሰውን ከቀማመስን በኋላ እንደገና ጉዞ ጀመርን፡፡ ሰዓቱ እየመሸ ቢሆንም መንገዱ ገና ነው፡፡ ጉጉታችን ጣርያ ቢነካም ከሰዓቱ መቅደም አይታሰብም፡፡ ከጂዳ መዲና ርቀቱ 410 ኪ.ሜ ነው፡፡ በፈጣን አውቶቡስም አራት ሰዓት ከምናምን ያስኬዳል፡፡ ምሽቱ ከዒሻ በኋላ ወደ መዲና ተቃረብን፡፡ ከሩቅም የመዲናን ዳርቻዎች ተመለከትን፡፡ የመዲና ከተማዋ እንደ ስሟ ታበራለች፡፡ ዘንባባዎቿ ከሩቅ ይታያሉ፡፡ በዚህ ጊዜ የኢማም ነወዊን ንግግር አስታወስኩ፡፡ ይላሉ፣ ለነቢ ዚያራ የወጣ ሰው ገና ከሩቅ ዐይኑ የመዲናን ዛፎች፣ የሷን የተከበረ ክልል አሊያም እሷ በምትታወቅበት ነገር ላይ ካረፈ በርሣቸው ላይ ሶላትና ሰላም ማውረዱን ይበልጥ መጨመር፤ አላህም በርሣቸው ዚያራ ተጠቃሚ የሚሆን እንዲያደርገው፤ እንዲሁም በሁለቱም ዓለም ስኬትን የሚጎናፀፍ ያደርገው ዘንድ መለመን ይኖርበታል፡፡ እንዲህም ይበል፥ ‹አልላሁምመ-ፍተሕ ሊ አብዋበ ረሕመቲ ወርዙቅኒ ፊ ዚያረቲ ቀብሪ ነቢይይከ ማ ረዘቅተሁ አውሊያአከ ወአህሊ ጧዐቲከ ወግፊር ሊ ወርሐምኒ ያ ኸይረ መስኡል፡፡› ትርጉሙ -/አላህ ሆይ! የእዝነትህን በሮች ክፈትልኝ፡፡ የነቢይህ ሰ.ዐ.ወ ቀብር በመዘየርም ለነዚያ ለወዳጆችህ እና ለታዛዦችህ የለገስከውን (መልካም ነገር ሁሉ) ለግሠኝ፡፡ ማረኝ፣ እዘንልኝ፡፡ ከተለማኞች ሁሉ በላጭ የሆንክ ሆይ!፡፡/ ቀስ እያልን ወደዚያች ሞገሷ ከፍ ወዳለው፣ ስክነት ወደሚነበብባት የነቢ መናገሻ ገባን። ሰዓቱም ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ከምናምን ነው። በክፍል አራት እንቀጥላለን ኢንሻአላህ https://t.me/MuhammedSeidAbx
без подписи
ቀናችሁን ለእዝነት አድርጉ *** አድራሻ፡ [📍አዲስ አበባ ከፒያሳ ወደ አዲሱ ገቢያ በሚወስደው መንገድ አዲስ አበባ ፖሊስ አለፍ ብሎ ከውሃ ልማት ፊት ለፊት ባለው ቅያስ 40 ሜትር ገባ ብሎ ከፒያሳ ሆቴል ፊትለፊት ] "የአምስት ዓመት የፅናት ጉዞ፤ የአዲስ ዘመን ተስፋ ብስራት" ድርጅቱን ለመደገፍ፦ የባንክ አካውንት _ 1000393427438 - የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 7917839551711 - ዳሽን ባንክ 014171061825600 - አዋሽ ባንክ 1002708080001 - ሂጅራ ባንክ 0043738210301 - ዘምዘም ባንክ 1543261300001 - ኦሮምያ ኢንተርናሽናል ባንክኀ 7000056815185 - ንብ ባንክ 8800001026246 - አማራ ባንክ 1013300076554 - ኦሮምያ ህብረት ስራ ባንክ 1016582315401 - ወጋገን ባንክ 182727059 - አቢሲንያ ባንክ 1004614042 - ፀሀይ ባንክ 6029813564594017 - ህብረት ባንክ አጭር የባንክ አካውንት 270808 (ለንግድ ባንክና ሂጅራ ባንክ ይሰራል) ለበለጠ መረጃ Mobile፦+251 906200020 Mobile፦ +251907404111 Safaricom ፦ +2517688650 office ፦ +251 118126811 እዝነት የእናትነት ተምሳሌት ! #Eznet_cerebral_palsy_care_Center_in_Ethiopia🇪🇹 #Eznet #CerebralPalsyAwareness #Ethiopia #5thAnniversary #SomethingNew #እዝነት #ሰረብራልፓልሲ
без подписи
ባለውለታዎቼ ናቸው ብዬ ከማስባቸው ሰዎች መካከል ጽሑፌን ቆም ብለው በማስተንተንና በመረዳትና የሚያነቡት ናቸው። አንዳንድ ሰዎች በጥረትህ ነፍስ እየዘሩ ምንዳህን ያበዛሉ። ይህን ሰው ልኮልኝ ነው። ሰባሐል ኸይር ! ከነቢዩ ሰ.ዐ.ወ. መልእክቶች መጽሐፍ https://t.me/MuhammedSeidAbx
የዑምራ ትዝታዬ ክፍል ሁለት ባህሩን ማን ባሻገረኝ **** በነጋታው ጠዋት ላይ በቦሌ የውጭ አገር መንገደኞች ተርሚናል ተገኘን፡፡ ከተጓዦች መካከል የቀደመኝ መኖሩን እንጃ። ወደ ግዙፉ ተርሚናል ገባን። የጉዞ ዶክመንቶችን ማሟላታችን ለማረጋገጥ በየመስኮቱ የተቀመጡ አጣሪ ባለሙያዎች ከፓስፖርት እስከ ቪዛና ቲኬት ወረቀቶችን ሁሉ ያመሳክራሉ። በያንዳንዱ መስኮት በሆነ እንከን ይመልሱኝ ይሆን እያልኩ ልቤ ድው ድው ይላል። እንዲሁ እንደፈራሁ ፍተሻዎችን ሁሉ አለፍን። ከሆነ ከባድ ምርመራ እንዳመለጠ ሰው አልሐምዱ ሊላህ! ብዬ በረጅሙ ተነፈስኩ። በቀጣይ ወደ ጂዳ በሚጓዙ የመንገደኞች መሣፈሪያ ቦታ ላይ ተቀመጥን፡፡ ለበረራ ሰዓታችን ገና ሁለት ሰዓት ሙሉ ይቀረዋል። ሰዓቱ አልገፋ ብሎኝ ተቁነጠነጥኩ። በመጨረሻም የበረራ ቁጥራችን ተጠቅሶ ወደ ሳዑዲ የሚበረው አንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ውስጥ ለመግባት በባስ ተሳፈርን፡፡ አሁንም ልቤ አላመነም። የሆነ አካል ና አንተ ተመለስ የሚለኝ እየመሠለኝ አሥሬ ወደኋላ አያለሁ። ከባሱ ወርደን የአውሮፕላኑን ደረጃ ወጣን። ገና እግሬ አውሮፕላኑ ውስጥ እንደገባ የአንድ ወዳጄ ንግግር ትዝ አለኝ፡፡ ዱንያ ምን ያህል አንገላታ እንዳሳደገችኝ የሚያውቅ ሰው ነው። ለአገር ውስጥ በረራ ለመጀመርያ ጊዜ ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ በአውሮፕላን ስሳፈር ያገኘኝ ቀን አጠገቤ መጣና "ከአሁን በኋላ ከአውሮፕላን አትወርድም" አለኝ፡፡ እውነትም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የአገር ውስጥ ረጃጅም ጉዞዎችን በአውሮፕላን እንጂ ሄጄ አላውቅም፡፡ ይህ የመልካም ወዳጄ ምኞት ትልቅ ተፋኡል ነበር፡፡ እግሬን ወደ አውሮፕላኑ እንዳስገባሁ ዛሬም ይኸው ስሜት መጣብኝ፡፡ ገና አውሮፕላኑ ሳይነሳ ካሁን በኋላ ይህን የተባረከ አገር እመላለስበታለሁ ብዬ አሰብኩ፡፡ ዑምራን ትደጋግማለህ፤ ሐጅንም ትሄዳለህ፣ የነቢን አገር ያለአንዳች ከልካይ ትመላለስበታልህ … የሚል ድምፅ ጆሮዬ ላይ ደጋግሞ ደወለብኝ፡፡ ኢንሻአላህ አልጠራጠርም !! በነገራችን ላይ አንድ ሰው ዑምራም ሆነ ሐጅ የሚሄደው ገንዘብ ስላለው ወይም ስለሞላለት አይደለም፡፡ ሁሉም የሚጠብቀው ያን በአጀል የተላለፈው የአላህን ቤት ዚያራ የጥሪ ቀን ነው፡፡ ስንት ሰው አለ ገንዘብ ላይ ተኝቶ የመካና መዲና መስመር ያልተገለጠለት!! ስንት ሰው አለ በአንድ ጊዜ ለመሄድ አቅሙ ስለሌለው ሕይወቱን ሙሉ ለሐጅና ለዚያራ ብሎ ገንዘብ አጠራቅሞ የጥሪውን ቀን በጉጉት የሚጠብቅ!። አሁን አውሮፕላኑ ውስጥ ተደላድዬ ተቀመጥኩ፤ እየሄድኩ እንደሆነም አመንኩ፡፡ በቀጥታ ስልኬን አንስቼ ወደ እናቴ ደወልኩ። የሆነ ፕሮሰስ ጀምሬያለሁ ዱዓ አድርጊ አልኳት እንጂ የዑምራው ጉዳይ እንዳለቀልኝ አልነገርኳትም ነበር ። በመጨረሻም አላህ ፈቅዶ አውሮፕላን ውስጥ እንዳለሁ እና ለበረራ እንደተዘጋጀሁ ነገርኳት። ደስታ ፈነቀላት። ረጅም ዱዓዋን ተቀበልኩ፡፡ ቀጥሎም ለወንድም እህቶቼና ለምቀርባቸው ሰዎች አሳወቅኩ፡፡ ሁሉም ደስ አላቸው። ስኬትና ቅበላን ተመኙልኝ። አባቴ ይህ ከመሆኑ ከስምንት ወራት ወፊት ነበረ ወደ አኺራ የሄደው። በዚህ ጉዞ ለሱም ዑምራ ለማድረግ ሀሳብ አኑሬያለሁ። ከሱ አንፃር ብዙ እንዳጎደልኩ ይሰማኛል። በዚህች ልዩ ቅጽበት ውስጥም ዱዓ አደረግኩ፡፡ የአላህ እዝነት አይለየው፡፡ ከሀብት ሁሉ ትልቁን ሀብት ዲን አስተምሮ አሳድጎኛል። አሁን ያ ግዙፍ ኤርባስ አውሮፕላን እየተንደረደረ ነው። በፍጥነት ከተንደረደረ በኋላም ከመሬትም ከፍ አለ። 333 ሰው ይዞ ወደ ጂዳ አቅጣጫ አመራ፡፡ ብዙዎቹ ተሳፋሪዎች ለሥራ ወደ ዐረብ አገር የሚሄዱ እህቶች ናቸው። ይህ ታሪካዊ ቀን ሐሙስ ነሀሴ 15 ቀን 2017፤ ኦገስት 21 ቀን 2025 ፤ ሶፈር 28 ቀን 1447 ዓ.ሂ ነበር፡፡ አውሮፕላኑ የሰሜን ምሥራቅ አቅጣጫን ይዞ ወደ ሳዑዲት ዐረቢያ በረራውን ቀጠለ፡፡ የብሱን ካቋረጥን በኋላ ቀይ ባህር ደረስን። ወደታች እያየን የኤርትራንና የአፍሪካን ምድር ተሻግረን ከዐረቢያው ምድር ደረስን፡፡ እሱ ጀሊሉ ባለው ቀን ባህሩን ተሻገርን ፡፡ ከ2፡00 ሰዓት በረራ በኋላ ባህር ማዶ ጂዳ ንጉሥ ዐብዱልዐዚዝ የአውሮፕላን ማረፍያ ደርሰን አረፍን፡፡ ኢትዮጲያ ክረምት በመሆኑ ከቦሌ ስንነሳ የቀን ሙቀቱ 16 እና 17 ድግሪ ነበር፡፡ ያኔ የጂዳ ሙቀት ደግሞ 42 ደርሶ ነበር፡፡ መሬቱ የሚፋጅ፣ አየሩ የሚገርፍ እሣት፣ አካባቢው የቂያማ ቀን መስሎ ተቀበለን፡፡ ሰው በዚህ ምድር እንዴት ይኖራል! ብዬ ተገረምኩ፡፡ ኢትዮጵያማ ጀነት ናት አልኩ በሀሳቤ ። ብቻ ጌታ በረሕመቱ ሁሉን ያቻችላል፡፡ አላህ በአንዱ ቢያጎድል በአንዱ ይሞላል፡፡ የአየር ፀባዩ ቢከብድም እዚህ አገር ሀብትን ለቆባቸዋል፤ ከመሬት ሥር የሚወጣውን ነዳጅ ወርቅ አድርጎላቸዋል። ዐረቦቹ የነዳጅ ሀብታቸውን ሽጠው ከቀይ ባህር ውሃ ስበው ተፈጥሮን ለማስተካከልና መሬቱን አረንጓዴ ለማድረግ ይታገላሉ፡፡ ባህሩን በዚህ መልኩ ተሻገርን፤ የመዲና ጉዳይ ነው የቀረን፤ በክፍል ሦስት እንመለስበታለን ኢንሻአላህ ። https://t.me/MuhammedSeidAbx
በምርጥ ሙስሊም ምሁራን ስለ ኢስላም ከተፃፉ ቆየት ካሉና የቅርብ ምርጥ መፃሕፍት መካከል እነኚህን እንጋብዛችሁ፡፡ የቱን አንብባችኋል! 1- ኢስላምን ለመረዳት ፡ ዶ/ር ዩሱፍ አል-ቀረዷዊ - አላህ ይዘንላቸው፣ 2- ኢስላማዊ እሴቶች ፡ በኡስታዝ ሐሰን አዩብ 3- ኢስላም የማኅበራዊ ችግሮች መፍትሄ ፡ በኡስታዝ አቡል አዕላ አል-መውዱዲ 4- የኢስላም ድል አድራጊነት ፡ ዶ/ር ዩሱፍ አል-ቀረዷዊ 5- የኢስላማዊው ሥልጣኔ አንፀባራቂ ገጽታዎች ፡ ዶ/ር ሙስጠፋ ሲባዒ 6- የኢስላም ሁለንተናዊነት ፡ በዶ/ር ዐብደላህ አል-ቀሕጣን (ክፍል አንድ እና ሁለት) 7- ይህ ነው ኢስላም፡ ሸይኸ ዐሊ ጠንጣዊ 8- የኢስላም ጥሪ ፡ በወሒዱ ዲን ኻን 9- ኢስላም የዘመናዊ ሥልጣኔ ፈጣሪ ፡ በወሒዱ ዲን ኻን 10- የኢስላማዊ ጥበብ ውርሣችን ፡ በወሒዱ ዲን ኻን https://t.me/Nejashipp
ምድር ላይ የዕድሜ ልክ ደስታ የለም ፤ የዘላለም መከራና ሐዘንም የለም፤ እንደ ክረምትና በጋ ሁሉ ሁሉም የሚያልፉና የሚያልቁ የሕይወት እርከኖች ናቸው ። ደስታ ሲገኝ በደስታ መቀበል ፤ ሐዘንና መከራ ሲመጣ ደግሞ በትዕግስት እና ተሰፋ መጋፈጥ ግድ ነው። ሰባሐል ኸይር ወዳጆች አማን ዋሉልኝ https://t.me/MuhammedSeidAbx
የዑምራ ትዝታዬ … **** ዓመት ዞሮ መጣ፡፡ የዑምራ ትዝታዬ ተቀሰቀሰብኝና ያኔ ስሄድ ከፃፍኳቸው ማስታወሻዎቼ አንዱን ክፍል አነሳሁ፡፡ አብረን እናንብብ እስቲ የምወዳችሁ … ,,, (በነገራችን ላይ ወደ ንባቡ ከመግባታችን በፊት ለዚህ ዑምራ መሳካት ያገዙኝን ወዳጆች ሁሉ ማመስገን እፈልጋለሁ፤ አላህ ያውቃቸዋል፣ ጌታዬ መልካም በተባለ ነገር ሁሉ ይመንዳቸው፡፡) *** በ2016 ለሐረም ምድር ያለኝን ጉጉት የሚያውቁ የተወሰኑ ወዳጆቼ በሕይወቴ የመጀመርያ የሆነውን ዑምራ መፈፀም እንድችል ቀን ቆርጠው፣ ኬክ አዘጋጅተው ጭምር ሰርፕራይዝ አደረጉኝ፡፡ ያ የዑምራ ሰርፕራይዝ በፓስፖርቴ አለመታደስ ምክንያት ተሰናከለብኝ፡፡ ባለመሳካቱ ኸይር ነው፣ አላህ የሻው ነው፣ እሱ ባለው ጊዜ ይሆናል ብዬ አለፍኩት፡፡ ያኔ የዶክትሬት ትምህርቴን ለማጠናቀቅ ወረቀት ማቅረብ ብቻ ነበር የቀረኝ፡፡ እንደውም በቀጣይ ዓመት ትምህርቴን እንደጨረስኩ ከምረቃ በኋላ ለምስጋናውም ለዚያራውም እሄዳለሁ ብዬ ሀሳቤን አፀናሁ፡፡ ትምህርቱ በሰላም አለቀ፡፡ ብዙ ሳልቆይ ፓስፖርቴን ለአንድ የዑምራ ኤጀንሲ ሰጠሁና ተመዘገብኩ፡፡ ፕሮሰስ መጀመሬን ሰምተው ስለ ጉዳዩ ለሚጠይቁኝ የቅርብ ወዳጆቼ ሁሉ እ .. እህሳ እንዴት ሆነ ሲሉኝ “ቆይ እስቲ እየተሳካ ነው መሠለኝ፡፡” እላለሁ፡፡ የሆነ በተለይ አጓጊ ነገር ስጀምር መጨረሻውን ሳላይ የማላምን ጠርጣራ ሰው ነኝ፡፡ ብዙውን የዱንያ ላይ የሕይወት ፈተናዎችን የማልፈው ከድግግሞሽ በኋላ ነው፡፡ ስለሆነም ጉዳዬን ለብዙ ሰው ሳልነግር ከራሴ ጋር ያዝኩት፡፡ ከመጠነኛ የፕሮሰስ መንገራገጭ በኋላ በመጨረሻም የዑምራ ጉዞዬ ተቀባይነት ማግኘቱን ከጉዞ ወኪሉ ተደወለልኝ፡፡ ነገ እንደምሄድ ተነግሮኝ ዛሬ ከዐስር በኋላ በሽኝት እና ሥልጠና ፕሮግራሙ ላይ ታደምኩ፡፡ የዑምራ አደራረግ ሥልጠናን እንደ አዲስ አፌን ከፍቼ አዳመጥኩ፡፡ በርግጥ በዚሁ ዙርያ መጽሐፍ ጽፌ የነበረ ቢሆንም ነገሩ ሁሉ አዲስ ሆነብኝ፡፡ የጓጉለት ነገር አዲስ ቢሆን አይገርምም፡፡ ከሥልጠናው በኋላ ምሽቱን ወደ ዘመድ አዝማድና ጓደኛ ደዋወልኩ፤ ለደስታውም ለዐፈውታውም ብዬ፡፡ አቤት ዕድለኛነቴ!!! ከሰላምታው እና ከእንኳን ደስ አለህ መልእክት ቀጥሎ የብዙ ሰው አማና “ነቢን ሰልምልኝ” የሚል ነበር፡፡ “ውይ ታድለህ እኮ!!” ያለኝ ሰው አቤት መብዛቱ!! ፡፡ ያኔ ያገኘሁት ፀጋ በርግጥም ከባድ ሆኖ ተሰማኝ፡፡ የአላህ ቤት ከዕባ የሚገኝበትን የተቀደሰ ምድር ፣ የነቢን አገር ከመርገጥና ወደ ነቢ ሰላምታን ከመሸከም በላይ ምን ክብር አለ!! ትልቅ አምባሳደርነት ነው ወላሂ፡፡ ገና ሳስበው አጠገባቸው ያለው ያህል ፍርሃትና አክብሮት ተሰማኝ፡፡ ለርሣቸው ሠላምታ የሠጡኝ ሰዎች ሰልምልኝ ሲሉ ገና ከአፋቸው ሳይጨርሱ ያገኟቸው ያህል ፍንድቅድቅ ይላሉ፡፡ በተለይ በነቢ ከልክ በላይ አፍቃሪነታቸው የማውቃቸው፡፡ ብዙዎቹ በትካዜ ይነጉዳሉ፣ የዚያ አገር ነገር ትዝ ባላቸው ቁጥር አህህ … የሚሉ አሉ፡፡ እንባ የቀደማቸው ብዙ ነበሩ፡፡ ከነርሱ መካከል አንዱ ኡስታዝ በድር ነበር፡፡ እንደ ነገ ልሄድ ዋዜማው ላይ ቤተሰብ ሰብሰብ ብሎ ተቀባብሎ ዱዓ አደረገልኝ፡፡ አሁንም እንደ አዲስ ፈነደቅኩ፡፡ እንደ ሕፃን ልጅ ቦረቅኩ፡፡ ህልም እንጂ እውን አልመስልህ አለኝ፡፡ በርግጥም የመመረጥ ስሜት ተሰማኝ፡፡ ሌሊቱን እንቅልፍ አልወስድ ብሎኝ እንዲሁ ስገላበጥ አደርኩ፡፡ ተነስቼ ለማንበብም ለመፃፍም ሞከርኩ፤ አልሆነልኝም፡፡ ሱብሒን በጀማዓ ቅርባችን ካለው መስጊድ ሰግጄ ለመስጊዱ ኢማምና ላገኘኋቸው ሰዎች ሁሉ ዑምራ ጉዞ ማሰቤን ነገርኳቸው፡፡ እነርሱም ከልክ በላይ ተደሰቱልኝ፡፡ በሰላም ሄጄ እንድመለስ፣ አላህም ዑምራዬን ይቀበለኝ ዘንድ ዱዓም አደረጉልኝ፡፡ ቤተሰቤን ተሰናብቼ ለአምስት ሰዓቱ በረራ ጠዋት አንድ ሰዓት ላይ ቦሌ ደረስኩ፡፡ ሀሳቤ ሁሉ ማዶ ነው፡፡ ከሰውነቴ ልቤ ቀድሟል፡፡ ልቤ በፍጥነት ይመታል፡፡ ትንፋሼ ይቆራረጣል፡፡ እራመዳለሁ ግን የለሁም፡፡ አጋጣሚ ሆኖ ያንኑ ሰሞን የሰማሁትን “ባህሩን ማን ባሻገረኝ መዲና ጉዳይ ነበረኝ” የሚለውን ነሺዳ አዜማለሁ፤ ያለማቋረጥ፡፡ የኔ እና የነቢ ጉዳይ ትንሽ ለየት ይላል መሠለኝ፡፡ እንደው ባልናገረው ይሻለኛል፡፡ ሳስባቸው እንባ ይቀድመኛል፡፡ ልዘይራቸው እየሄድኩ መሆኔን ሳስብ ደግሞ አንዳች ነገር ሰውነቴን ሁሉ ወረረው፡፡ ይህን ዜማ በተደጋጋሚ የሰማሁ ባሆንም የሆነ ጊዜ ወንድሜ ሙሐመድ አሕመድ ባቲ ሲነሽደው ከሰማሁ በኋላ ግን ይበልጥ አዲስ ሆኖብኛል፡፡ አንጀቴ ልውስውስ አለ፡፡ ትርጉሙም ስሜቱም በጣም ተለወጠብኝ፡፡ ፍቅራቸውም በብዙ እጥፍ አገረሸብኝ፡፡ ዜማውን ስደጋግም የሰማችኝ ልጄ ጭምር “እንዴ ምን ሆንክ ባባ!” አለችኝ፡፡ እሷ በርግጥ ያለሁበትን ሸውቅ አታውቅም ነበርና ነው፡፡ የነቢ ናፍቆት ከባድ ነው፡፡ ትልቁን እንደ ትንሽ ያረጋል፣ ስቅስቅ አድርጎ ያስለቅሳል፡፡ (ክፍል ሁለት ይቀጥላል ) https://t.me/MuhammedSeidAbx