ወርቃማዎች
Статистика- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 54
- 1/48двое суток
- 61
- 1/72трое суток
- 66
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ውይ ውይ አቤት ቅሌት ቀለልኩላቹ ወላሂ😭💔😂 መንገድ ላይ ከፊት ለፊቴ አንድ ልጅ ሲመጣ አየሁት እቃ የሚያመጣልኝ ከስተመሬ ነው ብዬ ልክ አጠገቤ ሲደርስ "አንተ እዚም እየዞርክ ነው" ብዬ ፈገግ😊 ስል ግራ በተጋባ ሁኔታ በደረቅ ፈገግታ "እሺ ሰላም ነው"🙄 ብሎኝ ሲያልፍ ያመዋል እንዴ ብዬ ልክ አንድ ሁለት እንደተራመድኩ ትዝ ሲለኝ ለካ አንድ ቀን ባንክ ሄጄ የሆነ ነገር አስተካክልልኝ ስለው እኔ አላውቅም ማናጀሩን አናግሪ ሲለኝ "ምናለ ባትጠም ጠማማ" ያልኩት ባንከር ቢሆንስ 😭😭😭 ነገ እንዴት ነው እዛ ባንክ ምሄደው አረ ምን ይሻለኛል💔😭
የአረብ ቀልድ ልንገራቹማ አንድ ግመል ነጋዴ አረብ ሊያጭ ይሄዳል ከዛም የልጅቷ ቤተሰቦች መህር 40ሺ ይሉታል ምን ቢል ጥሩ ነው እነ እንትና ቤት እኮ ከእነ ልጇ በ20ሺ አግኝቻለው 😂😂😂😂
በአንድ ወቅት እጅግ ተጫዋች፣ ፈጣንና በደስታ የተሞላችሁ ሰው የነበራችሁበት ጊዜ ነበር...ዛሬ ግን ዝምታን፣ ብቸኝነትንና መረጋጋትን ልትመርጡ ትችላላችሁ።🙌 ይህ ማለት ማንነታችሁን አጣችሁ ማለት አይደለም፤ ህይወት ያስተማረቻችሁ ትምህርት፣ ያለፋችሁበት ፈተና እና የገጠማችሁ ድካም የፈጠረው ተፈጥሯዊ የጥበቃ መንገድ (Self-protection) ነው። ጸጥ ማለታችሁ ድካም ቢመስልም፣ የውስጥ ሰላማችሁን ለመጠበቅ ያበጀችሁት ወሰን ሊሆን ይችላል።🤝 ዝም ማለታችሁ ወይም ድካም መሰማቱ የተሰበራችሁ ያደርጋችኋል ማለት አይደለም። አንዳንዴ አእምሮአችን ራሱን ለማደስ (Recharge) ለማድረግ ጊዜ ይፈልጋል። ለራሳችሁ እረፍትና ፍቅር ስጡ።🤌 Silence isn't always a sign of defeat; sometimes it's your soul's way of resting and rebuilding. Be gentle with yourself.🔥 ቀድሞ ከነበራችሁበት ተጫዋችነት ወደ ዝምታ እንድትቀየሩ ያደረጋችሁ የህይወት አጋጣሚ አለ? በርቱ! አመሰግናለሁ 🙂
አሁን የገጠመኝ አብነት ጋር ታክሲ ውስጥ ..ታክሲው ገና እየጫነ እያለ ሁለት ተሳፋሪዎች አጠገቤ ፀብ ጀመሩ! ከዛ አንዱ ሽጉጥ አወጣ ልጁ ሽጉጥ ስለያዝክ ምሰማህ መሰለህ እንዴ? እያለ በboክስ ላጥ ላጥ ደም በdም አደረገው። ስንት አይነት ጀግና ወንድ አለ እኔ እዳይተኩስ ወይ እንዳይባርቅበት ደንግጬ ዘልዬ ውርድ ! ለራሴ አራት ሚስት የማግባት እቅድ ያለኝ ሰው ነኝ በጊዜ ሊቋጨኝ ብዬ😀 ልጁም ወርዶ ሮጠ ሰውዬው ወደ ላይ ተኮሰ ።የታክሲውን ሰው አትወርዱም ብሎ ያዛቸው እኔ የናቴ ዱዐ ጠበቀኝ ሌላ ታክሲ ይዤ ወደ ቤቴ😌
በነገራችን ላይ የሆነ ወቅት ላይ ተቸግረህ ስለደረሰልህ ብቻ እንደ ኢሉምናቲ ማንነትህን እንድትገብርለት የሚፈልግ ሰው ነፍ ነው። ምክንያቱም የሆነቀን የቆመበት እንደሚከዳው ስለሚያውቅ ለዛች ቀን የሚሆነውን ስንቅ ዛሬ ላይ ነው በችግር ጎንህ መጥቶ የሚቋጥረው። ከዛ የዚህን ሰው አደገኛነት መቼ መሰለህ የምታየው ልክ መንሸራተት ሲጀምር ነው። ይመጣና ደግፈኝንጂ ይልሀል። በራሱ ደንባራ አረማመድ እራሱላይ ያመጣውን ውድቀት ብቻውን መጋፈጥ አይፈልግም። የሆነ ቀን ተቸግረህ ያደረገልህን እያስታወሰ ዛሬላይ ህልውናህን አሳልፈህ እንድትሰጠው ይጠይቅሀል። አይ ያኔ እገዛህን ስቀበል ራሴን አልሸጥኩልህም ባመንኩበት ጉዳይ ብቻ ነው የማግዝህ ስትለው ልፈፋውን ይጀምራል። ያኔ እንዲ አርጌለት እሱግን ዛሬ አላግዝ አለኝ ጲሪሪም ጳራራም ምናምን... ውለታን መቁጠር የጀመርክ ሰአት ነው ውለታነቱ የሚያበቃው! ሲጀመር ውለታ ከተቆጠረ manipulation ነው
ሀኪሙ ታማሚዎችን እየጎበኘ አንዱ ታማሚ ግርግዳውን በቴስተ ሲመታ አየው ''ምን ሆኖ ነው?'' አለ "አንድ ልጅ እሱን ትታ ሌላ አግብታ ነው" አሉት የሚቀጥለው ክፍል ሲገባ ሌላኛው ታማሚ ጭንቅላቱን በጫማ ይመታል "ይሄስ ምን ሁኖ ነው?" "ያቺን ልጅ ያገባት እሱ ነው"🚶
የህግ ተማሪዎችን 4 ከ Square root እንዴት ይወጣል ስትላቸው... ( በዋስ )
"ጌታህም ለባሮቹ በዳይ አይደለም::"💙🤍
ከአንዳንድ ፕሮግራም በኋላ ምሳ በልተን ስንጨርስ ጫት ያዝ ሲሉኝ 😊
አይስክሬም ሻጩን የሚጎዳው ተመሳሳይ ዝናብ...ለጃንጥላ ሻጩ ደግሞ ትልቅ እድልና በረከት ነው። እያንዳንዱ ቀን ለእኛ ብቻ ይመች ዘንድ አልተፈጠረም! and that's okay.🙌 ህይወት የሁልጊዜ ደስታና ስኬት ብቻ አይደለችም። ለእኛ ፈተናና መጥፎ አጋጣሚ የሚመስለን ነገር፣ ለሌላው ሰው ደግሞ በረከትና አዲስ እድል ሊሆን ይችላል።🤷♀️ ሁሉም ቀን ለእኛ ተመችቶ አይውልም፤ የህይወት ውበቷም ያለው በዚህ ሚዛን ውስጥ ነው። ነገሮች እንደፈለግነው ባልሄዱ ቁጥር ከመበሳጨት ይልቅ፣ የሂደቱ አካል መሆኑን አምኖ መቀበል ትልቁ የአእምሮ እረፍት ነው። ✨ ሁልጊዜ አየር ሁኔታው ወይም ሁኔታዎች ለእናንተ ብቻ እንዲመቹ አትጠብቁ! በህይወታችን ውስጥ የምናልፍባቸው አስቸጋሪ ቀናት የራሳቸው የሆነ ዓላማ አላቸው!🔥 ~አንድ ነገር ለእኛ አልሳካ ማለቱ ዓለም አበቃች ማለት አይደለም፤ ይልቁንም የህይወት ሚዛን መጠበቂያ መንገድ ነው። ~ዛሬ ዝናቡ የእናንተን መንገድ ቢያስተጓጉል እንኳ፣ ነገ ደግሞ ፀሐይ ለእናንተ ትወጣለች። ቀናትን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር አለመሞከር የአእምሮ ሰላም ይሰጣል።😍 Not every storm comes to disrupt your life; some come to balance it. Trust the timing and accept that not every day is meant to be yours.🌧️🧠✨ በርቱ! አመሰግናለሁ🙂 @WERKAMAA
"አንዳንዴ... ከእንክርዳድ መሃል ይገኛል ስንዴ!!" የተባለልሽ 🥰🙌
ከማግባቴ በፊት ቀድሞኝ ያገባ ጉአደኛዬ ስለ ትዳር እና የትዳር ጨዋታ ሲያወጋን የባለቤቱን ቢክራ ለመውሰድ 3 ተከታታይ የስራ ቀናትን እንደወሰደበት ነግሮኝ ነበር! ከዚያም ላገባ ስል ምጠነቀቀው እና እንዳይነሳ ምፈልገው ርዕስ ይሄ የቢክራ ጉዳይ ነበር! ምክንያቱም ከጉአደኛዬ ልምድ አንፃር እንደዚ አድካሚ ነገር ከሆነ ባይኖር ነው ሚሻለው የሚል ሃሳብ ውስጤ ተፈጥሮ ነበር, ግማሽ ልቤ ደሞ መኖር አለበት ይለኛል! እና ከራሴ ጋር ያልተስማማውበትን ጉዳይ ከወደፊት ሚስቴ ጋር ማውራት ያስፈራኝ ነበር! ከዚያም ተጋባን እና ጊዜው ሲደርስ እንዳልነበረች አወኩኝ, እንዴት ስላት ልጅነት አታሎኝ, ስሜት አሸንፎኝ ብላ እውነተኛ ታሪኩን በዝርዝር ነገረችኝ! እውነቱን ስትነግረኝ ይበልጥ ለሷ ያለኝ ክብር እና ፍቅር ጨመረ! በዚህ ዘመን ከሴቶቻችን አብዛኞቹ ለመናገር በማይመች እና በማይቻል የሕይወት መጥፎ አጋጣሚ የቅርብ ዘመድ በሚሏቸው ወንዶች ገና ቢክራ ምን እንደሆነ ከማወቃቸው በፊት ቢክራቸውን ያጡታል! በኔ እይታ አሁን ላይ ቢክራ መሆን የትዳር ዋነኛ መስፈርት ከሚሆን ይልቅ መተማመን እና መዋደድን ዋነኛ መስፈርት ብናደርግ ብዙ ትዳሮች ፀንተው ይቆይ ነበር! ታሪኩ እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ እና ይበልጥ ሃሳብ እና እይታዬን እንዲያንፀባርቅ ተደርጎ የተፃፈ ነው! እርሶስ በዚህ ዘመን ስላለው የ ቢክራነት አረዳድ ምን ሃሳብ አሎት? @anwarahmeed
በሬንኳን ቀንበር መሸከም በተወበት ዘመን የ PC bag ተሸክመን ትከሻችንን ማውለቅ ምን ይሉታል? እምቧ ማለት ነውኮ የቀረኝ
በታሪክ መዛግብት ፥ ለሴት የተሠዋ ወንድ'ይ ለወንድ ብለው የሚሠው ሴቶች አልገጠሙኝም ። ይሞታሉስ ብለህ ነው ? አምስት ቀን በተከታታይ ደም ፈሷት የማትሞት ልጅ ፤ ይታይህ ፥ በአንተ ፍቅር ስትሞት °°°
ያማረ እና የተባረከ ቤተሰብ የሚጀመረው ከጥሩ ወንድ ነው።🙌 አንድ ወንድ ለባለቤቱ ደግና መልካም ሲሆን ያ መልካምነት ወደ ልጆቹ ይፈሳል መላው ቤተሰብም የተባረከ ይሆናል። ምክንያቱም ጥበቃ፣ ፍቅር እና የደህንነት ስሜት የሚሰማት ሴት በቤቷ ማዕዘን ሁሉ ሙቀትና ፍቅርን ትገነባለች።🥱 የእሷ ሰላም የልጆቹ ሰላም ይሆናል። የእሷ ደስታ የቤቱ መሰረት ይሆናል፤ ይህ ሁሉ ደግሞ የሚጀመረው በቅንነት በታማኝነት እና በበጎ አሳብ ከሚመራ ወንድ ነው!🤝 ወንድ ስላቹህ ሚስቱን መውደድ ለቤተሰቡ ሊሰጠው የሚችለው ትልቁ ስጦታ መሆኑን ከሚረዳ አስተዋይ ወንድ። ልክ እንዴ አባቴ አይነት!!😍 "Happy wife, happy life"የሚለውን የተለመደ አባባል ተውት it’s deeper than that: እንክብካቤና ፍቅር ያገኘች ሴት የሰላማዊ ቤት መረጋጋትና መሰረት ትሆናለች! እሷን የሚወድ አባት ደግሞ ለልጆቹ በዓለም ላይ ትልቁን የተጠበቅ የደህንነት ስሜት ይሰጣቸዋል።Because a happy home always begins with a man who knows how to love.🔥 በርቱ! አመሰግናለሁ🙂
አድስ አበባ ላይ ከ KG እስከ 4ኛ ክፍል 2.7 ሚሊዮን ብር፣ ለሃይስኩል ተማሪዎች ደግሞ ከ 6_7 ሚሊዮን ብር በዓመት የሚያስከፍል ትምህርት ቤት አለ አሉ እናንተ። እኔ ዛሬ ብዙ ሽህ ብሮች ለተርም ከፍዬ ፀጉሬ በራሱ መርገፍ ጀምራል። አሁን መገናኛ ላይ ብቻዬ እያወራሁ ራሴን አገኘሁት ደግሞ 😂
አንተ በረካ የለህም ማለት - በረካ የለም ማለት አይደለም !
ዜብራው የተሰራው ለመኪናው መሻገሪያነት ነው ወይ? እኛ እግረኞች መኪኖችን እንዳንገጫቸው ነው ወይ?ለምንድነው አሽከርካሪዎቹ ልክ ዜብራውን እንዳዩ ከሰው ቀድመው ለማለፍ የሚሮጡት ተሳቀቅነ 😭
ሰው በጣም በሚያስፈልግህ ወቅት ላይ የሆነ የምትፈልገው ሰው ድንገት ስታገኘው መላኢካ የተላከልህ ይመስልሃል::
አታጠኑም የሚባልበት ጊዜ አለፈና አታገቡም የምንባልበት ግዜ መጣ