tgindex

Werabe university muslim students union

описание

This is the official telegram channel of wrumsu. Email: wrumsu12@gmail.com twitter: http://twitter.com/wrumsu Telegram: @wrumsu

1 435
подписчиков
Охват к подписчикам
92,7%
ERR
Реакции к просмотрам
0,66%
259 на 29 постов
Пересылки к просмотрам
0,37%
144
Постов в день
0,1
всего 29

Где отзываются чаще

доля реакций к просмотрам
  • 28 июн.🏆 الله أكبر 🏆 ልክ እንደ አምናው ሁሉ የጊቢያችን ዋንጫ በሙስሊም ተመራቂ እጅ ገብቷል! 🎓🥇 ወንድማችን ጃፈር ሙሀመድ ከጤና ሳይንስ ኮሌጅ ነርሲንግ ዲፓርትመንት 3.98 CGPA በማምጣት የወራቤ ዩንቨርስቲ የዋንጫ ተሸላሚ እና የማዕረግ ተመራቂ በመሆን አጠናቋል:: "وَمَن جَدَّ وَجَدَ" “የጣረ ያገኛል” እንኳን ደስ አለህ!!! 🏆 ألف مبروك 🏆 ✨3,80%
  • 9 авг.﷽ ⭐ ትላንት ከተማርነው መካከል⭐ 👉ነብዩ ﷺ ለ ሁለተኛ ጊዜ ወደ ሻም ያደረጉት ጉዞ እድሚያቸው ሃያ አምስት ሲሞላ ለንግድ ወደ ሻም ሂደዋል እመቤት ኸዲጃ ሃብታም እና ምትከበር ሴት ነበረች በገንዘብ ሰው ቀጥራ ታሰራ ነበር እና ነብዩን ﷺ እውነተኝነት አደራ ጠባቂነት እና ጥሩ ስነ ምግባራቸው ስትሰማ እሳቸውን መረጠች እና ተስማምተው መይሰራ ከሚባለው አገልጋይዋ ጋር ለሳቸው ለመነገድ ወደ ሻም ተጓዙ እና ሁለት ወር ቆይተው በጣም ብዙ ትርፍ አትርፈው ተመለሱ. 👉ነብዩ ﷺ እመቤት ኸዲጃ ስለ ማግባታቸው ከ ሻም ከተመለሱ ቡሃላ ኸዲጃ በ ገንዘቧ ላይ ልዩ በረካ ባየችሰዓት እና የነብዩን ﷺ ባህሪ ከ አገልጋይዋ መይሰራ በነገራት ጊዜ ምንም እንኳን የ መካ ሹማምንት ጠይቀዋት እምቢ ብትልም ነብዩን ﷺ ግን እራሳቸው ጠይቀው አገባቻቸው. 👉እመቤት ኸዲጃም ከሳቸው በፊት አቢ ሃለህ ሚባል ሰው አግብታ ነበር. በትዳር ሃያ አምስት ዓመት አሳልፈዋል እሳቸው በሕይወት እያሉ ሌላ ሴት አላገቡም ነበር 👉ከ ኸዲጃ ቡሃላ ያገቧቸው ባለቤቶቻቸው 2..ሰውዳ ቢንት ዘምአ 3.አኢሻ ቢንት አቢበክር 4..ሃፍሳ ቢንት ዑመር 5.ዘይነብ ቢንት ኹዘይመህ 6.ረምላ ቢንት አቢ ሱፍያን 7.ጁወይሪያ ቢንት ሃሪሳ 8.መይሙና ቢንት ሃሪሳ 9.ሰፍያ ቢንት ሁየይ 10.ዘይነብ ቢንት ጀህሽ 11.ኡሙ ሰለማ 👉የወለዷቸው ልጆች ቃሲም. አብዱላህ. ዘይነብ. ኡሙ ኩልሱም. ፋጢማ. ሩቅያ(ከኸዲጃ) እና ኢብራህም(የ ማሪየቱል ቂብጥያ ልጅ ነዉ)ናቸው 👉ነብዩ በሃጀረል አስወድ ምክንያት በቁረይሽ መሃከል ስለመፍረዳቸው ነብዩ ሙሐመድ ﷺ እድሜያቸው ሰላሳአምስት ላይ እያሉ ነብይነት የካዕባ ሕንፃ በጎርፍ በመፍረሱ ምክንያት የቁረይሽ ጎሳዎች መልሰው ገነቡት ነገር ግን የተቀደሰውን ሐጀረል አስወድን ቦታው ላይ የመመለስ ሰዓት ሲደርስ የትኛው ጎሳ ይህንን ትልቅ ክብር ያግኝ በሚል በጎሳዎቹ መካከል ከፍተኛ አለመግባባትና ጭቅጭቅ ተፈጠረ ​በመጨረሻም በካዕባ በር መጀመሪያ የሚገባው ሰው ይፍረደን ብለው ተስማሙ በበሩ የመጀመሪያ ሆኖ የገቡት ነብዩ ﷺ ነበሩ እርሳቸውንም ሲያዩት ሁሉም በደስታ ታማኙ (አል-አሚን) መጣ በእርሱ ፍርድ እንስማማለን አሉ ​ነብዩም ﷺ የሚከተለውን ብልህና ፍትሐዊ መፍትሔ ሰጡ ​አንድ ኩታ(ጋቢ)እንዲመጣ አዘዙ ​ሐጀረል አስወድን በገዛ እጃቸው አንስተው ጨርቁ መሃል አደረጉት ​የእያንዳንዱ ጎሳ መሪዎች የጨርቁን ጫፍ እንዲይዙና በአንድነት ወደ ላይ እንዲያነሱት አደረጉ ​ድንጋዩ ወደ ተፈለገበት ቦታ ከተቃረበ በኋላ ነብዩ ﷺ በገዛ እጃቸው አንስተው ቦታው ላይ አስቀመጡት ​በዚህ ፍርድ ምክንያት ሁሉም ተደሰቱ. ❤️صلي الله عليه وسلم❤️1,57%
  • 27 июн.🌙 ከወራቤ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ዋና አሚር ✍️ አብዱልሀኪም ሙሰማ ለ2018 ዓ.ል ተመራቂ ተማሪዎች የተላለፈ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት 📜 በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እና ሩህሩህ በሆነው አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ። ክቡራን ተመራቂ ተማሪዎች:- በዚህ ታላቅ እና ደማቅ ቀን ላይ በወራቤ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ስም እና በራሴ ስም ለሁላችሁም ከልብ የመነጨ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ። ዛሬ የተመረቃችሁት የትምህርት ደረጃ ብቻ አይደለም፤ የስነምግባር፣ የትዕግስት፣ የእምነት እና የትግል ውጤት ነው። በብዙ ፈተናዎች ውስጥ አላህን ታግሳችሁ፣ በዱዓ ተጠናክራችሁ እና በጥረታችሁ ዛሬ ወደዚህ ክብር ደርሳችኋል። አልሐምዱሊላህ! ውድ ተመራቂዎች፤ እስልምና ለሰው ልጅ የሕይወት ስርዓት ነው። ከመስጂድ ውስጥ የሚቀር ሀይማኖት ብቻ ሳይሆን ማህበረሰብን፣ ፍትሕን፣ እውቀትን፣ አመራርን እና ሰብዓዊነትን የሚመራ ሙሉ ስርዓት ነው። ዛሬ ዓለም በብዙ ችግሮች ውስጥ እየተዘፈቀች ነው፤ ፍትሕ ጠፍቷል፣ ሙስና በዝቷል፣ ወጣቶች ተስፋ እያጡ ነው። ይህን ሁሉ የሚያስተካክለው ግን ከእውቀት ጋር የተጣመረ ኢማን ነው። እናንተ ዛሬ የተመረቃችሁ ወጣቶች የኡማው ተስፋ ናችሁ። እስልምናን በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር የምታሳዩ ትውልድ መሆን አለባችሁ። የሙስሊም ወጣት ሲማር ለራሱ ስራ ብቻ አይዘጋጅም፤ ለዑማው ጥቅም፣ ለፍትሕ እና ለአላህ ደስታ ይዘጋጃል። ዛሬ የሙስሊሙ ዓለም ከብዙ አቅጣጫ ጫና ውስጥ ነው። በብዙ ቦታዎች ሙስሊሞች ፍትሕ እየተነፈጉ ነው፣ ወጣቶች ከዲናቸው ለማራቅ ብዙ ፈተናዎች እየተፈጠሩ ነው። ነገር ግን የተማረ፣ ዲኑን የጠበቀ እና ለእውነት የቆመ ወጣት ማንኛውንም ፈተና ማሸነፍ ይችላል። እኛ ሙስሊሞች ከምንም በፊት የምናስቀድመው ዲናችንን ነው። ከዘር በፊት እስልምናችንን ነው። ከግል ጥቅም በፊት የኡማውን ጥቅም ነው። እስልምና የፍትሕ ዲን ነው፤ ማንንም መበደል አያስተምርም፣ ማንንም መጥላት አያዝዝም። ነገር ግን በእውነት ላይ መቆምን፣ ለሐቅ መናገርን እና ፍትሕን መጠበቅን ያስተምራል። ዉድ ተመራቂዎች፤ ዛሬ የምትወጡት ወደ ቀላል ዓለም አይደለም። ግን አላህን የፈራ ሰው መንገዱ አይጠፋዉም። እውቀታችሁን ከተቅዋ ጋር አጣምሩ፣ ስኬታችሁን ከስነምግባር ጋር አስተሳስሩ፣ የተማራችሁትንም ለኡማው እና ለሀገራችሁ ጥቅም አውሉ። ነቢዩ ﷺ “ከሰዎች ሁሉ በላጩ ለሰዎች የሚጠቅም ነው” ብለዋል። ስለዚህ እውቀታችሁ ለማህበረሰብ ብርሃን ይሁን፣ ተግባራችሁ የእስልምና ውበት ይሁን። በመጨረሻ፤ ይህን ቀን እንድትደርሱ ዱዓ ላደረጉላችሁ ወላጆቻችሁ፣ በእውቀት ላሳደጉአችሁ መምህራን እና ከጎናችሁ ለነበሩ ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል። አላህ እውቀታችሁን የሚጠቅም ያድርግላችሁ፣ ዲናችሁን ያጽናላችሁ፣ ለኡማው ክብር እና ለሀገራችሁ በረከት ያድርጋችሁ። እንኳን ደስ አላችሁ! አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱህ። ✍️አብዱልሀኪም ሙሰማ የወራቤ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ዋና አሚር1,37%
  • 27 июн.🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓 السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🎉🎉🎉الف الف مليار مبروك احبابي في الله 🎉🎉🎉 🎓📚ከውዷ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ላጠናቀቃችሁ ውድ ተመራቂ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ከብዙ ቻሌንጅ ጀርባ ህልማችሁንና የኡማውን አደራ ጠብቃችሁ Exit Exam ን ጨምሮ ብዙ ፈተናዎችን በብቃት አልፋችሁ ለምርቃት ለደረሳችሁልን ሁሉ ከአመታት ልፋት በኋላ በጉጉት ለምትጠብቁት የምርቃት ቀን እንኳን አላህ በሰላም አደረሳችሁ። 💯ኢንሻአላህ ቀሪ ዘመናችሁም በመልካም ስራ: በስኬትና በደስታ የተሞላ እንዲሆን ምኞቴ ነው። እንኳን ደስ አላችሁ 🎓🎓🎓🎓 🎈🎈 🎉 🎊🎊هنيئا لكم🎓🎓🎓🎓 Congratulations!! 🎉🎉🎉🎈🎁 ቦሄ ደስ ባረናሁም🎓🎓🎓🎓 ሀበይ ተስ ባለሙ🎉🎉🎉🎈🎁🎓🎓🎓 Congratulation Baga gammaddan🎈🎁🎓🎓🎓 የቀድሞ ተመራቂ ወንድም ዐ/ዐዚዝ ሙሐመድ 🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟1,29%
  • 2 авг.⭐ዛሬ ከተማርነው ትምህርት መካከል ⭐ ⭐የእናታቸው አሚና መሞት ነቢዩ (ﷺ) የ6 ዓመት ልጅ እያሉ እናታቸው አሚና ከመዲና(የ አባታቸውን ቀብር ለማየት ሂደው)ከ ጉዟቸው ወደ መካ ሲመለሱ በአብዋእ በተባለ ስፍራ አረፉ. ከዚያ በኋላ ከ አያታቸው አብዱል ሙጠሊብ እና ሞግዚታቸው ኡሙ አይመን ጋር በመሆን ወደ መካ በመመለስ ከ አያታቸው ጋር አደጉ. ⭐የአያታቸው አብዱልሙጥጠሊብ መሞት 👉 እናታቸው ካረፉ በኋላ አያታቸው አብዱል ሙጠሊብ የልጅ ልጃቸውን ከ ልጆቻቻው አስበልጠው በመውደድ በመንከባከብ እና ፍቅር በመስጠት እጅግ የተለየ ቦታ ሰጡዋቸው። 👉 ነቢዩ ﷺ የ8 ዓመት ልጅ እያሉ አያታቸው አብዱልሙጠሊብ አረፉ ይህም ለነቢዩ ﷺ ሌላኛው የሀዘን ምዕራፍ ነበር አያታቸው ከመሞታቸው በፊት ልጃቸውን አቡ-ጧሊብን ነቢዩን ﷺ እንዲንከባከብ በውክልና አስረከቡት. ይህ የታሪክ ክፍል የነቢዩን ﷺ የልጅነት ፈተናዎች አላህ ለሚወደው ነገር እያዘጋጀውን እንደነበር ያሳያል. أَلَمۡ يَجِدۡكَ يَتِيمٗا فَـَٔاوَىٰ የቲም ሆነህ አላገኘህምና አላስጠጋህምን? (አስጠግቶሃል) 👉ፍየል ስለ መጠበቃቸው እና የመጀመሪያ ወደ ሻም ጉዞ ነብዩ ﷺበልጅነታቸው ለመካ ሰዎች ፍየልን ይጠብቁ እንደነበር እና በዚያ በሚያገኙት ገንዘብ አጎታቸውን በ ኢኮኖሚ ያግዙ ነበር. ከዛም እንድሜያቸው 9 ወይም 12 ሲሆን ለ መጀመሪያ ጊዜ ወደ ሻም ለንግድ እየተጓዙ እያለ. ቡስራ ሚባል አካባቢ ሲደርሱ በሂራ ሚባል መነኩሴ(ቄስ) ነብዩን አይቷቸው የ ወደፊት ነብይ መሆናቸውን ለ አጎታቸው ነግሯቸው እሳቸውን ካገኝዋቸው ሊገሏቸው ሚፈልጉ ሰዎች እንዳሉ እና ወደ መጡበት ሀገር እንዲመለሱ ነግሯቸዋል.1,23%
  • 2 авг.ዛሬ በነበረው የ online ቂርዓት ላይ ለነበረው መቆራረጥ ታላቅ አፍወታን እንጠይቃለን.1,12%
  • 28 июн.ታላቁ የቲክቶክ መድረክ ነገ ሰኞ ከምሽቱ 3:00 ላይ ነው! ስለሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥያቄ ታሪካዊ ዳራ፤ ሕጋዊ መሠረት እና አሁናዊ ሁኔታ ከመፍትሔ ጋር በጥልቀት ይዳሰሳል። የድምፃችን ይሰማው ታጋይ ሙባረክ አደም፤ ጠበቃው ሙስጠፋ ሺፋ፤ የንፅፅር መምህሩ የሕያ ኢብኑ ኑሕ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ፀሐፊው ሁሴን ዩሱፍ በመድረኩ ላይ ሀሳቦቻቸውን ያንፀባርቃል። ፨ ፖስተሩን በስቶሪዎቻችን ላይ እናጋራ፤ ፕሮፋይልም እናድርግ ፨ የዩኒቨርስቲ ጀመዓዎች በቻናሎቻችሁ ላይ አጋሩ ፨ የሀይስኩል ጀመዓዎች መልዕክቱን አድርሱ ፨ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ያላችሁ ተፅዕኖ ፈጣሪ ስብዕናዎች፤ ኡስታዞች እና ዳዒዎች መልዕክቱን ለሁሉም አድርሱ ሁሉም ተጋባዥ ነው። አጀንዳው የሁሉም ነውና ሁሉም ይገኝ። ተማሪ፣ የተማሪ ወላጅ፣ መምህር፣ የመንግስት ሰራተኛ ወዘተ ... ማንም እንዳይቀር። 🗓 ቀን፡ ሰኞ፣ ሰኔ 22 (Monday, 29 June) ⏰ ሰዓት፡ ከምሽቱ 03፡00 ሰዓት እውቀትን መፈለግ መብት ነው፤ እምነትንም በክብር መተግበር እንዲሁ! የቲክቶክ ገፃችንን Follow በማድረግ ዝግጅቱን ይጠብቁ፦ https://www.tiktok.com/@aaumsu ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ! ! ! @EHEMSU1,12%
  • 29 окт. 2024 г.без подписи0,98%
  • 21 июл.✨የክረምት የኢልም ጉዞ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማዓ ✨ السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ​ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ እንዴት ናችሁ? ​ክረምት ሲመጣ ብዙ ጊዜ ጊዜያችንን እንዴት እንደምናሳልፍ ግራ ይገባናል። አንዳንዴም ጊዜያችን በከንቱ ያልፋል። በዚህ ጊዜ ግን አብረን እንድንጠቀምበት እና የነቢዩን ﷺ ሕይወት በቅርበት እያየን ኢማናችንን የምናድስበት የonline የደርስ ፕሮግራም አዘጋጅተናል።🎉 ​በዚህ ክረምት «ዅላሰቱ ኑሪል የቂን» የተሰኘውን የሲራ ኪታብ አብረን እንቀራለን። አላማችን የነቢዩን ﷺ ታሪክ እየቀራን ከሕይወታቸው ትምህርት መውሰድ፣ ጊዜያችንን በኸይር የምናሳልፍበት መንገድ መፍጠር እና በጀማዓ ሆነን በዲን ላይ መበርታት ነው። ​ለዒልም ስንል የምናሳልፈው ጊዜ የቂያማ ቀን ትልቅ ስንቃችን ነውና፣ ሁላችሁም በዚህ የኸይር ስራ ላይ እንድትሳተፉ በአክብሮት እንጋብዛለን።🎁 ✅ ደርሱ ሐምሌ 18 ይጀመራል! ​ፕሮግራማችን ​📖የኪታቡ ስም ፦ ዅላሰቱ ኑሪል የቂን ( خلاصة نور اليقين في سيرة سيد المرسلين) 📆​ቀናት፦ ቅዳሜ እና እሁድ ⏰​ሰዓት፦ ከመግሪብ (ከ1:10) እስከ ኢሻ ሶላት 📍​ቦታ፦ [https://t.me/wrumsu_discussion] ​📝 ምዝገባ ​የዚህ ፕሮግራም አካል ለመሆን እና አብረን ለመማር፣ መመዝገብ የምትፈልጉ በዚህ ሊንክ/Username አሳውቁን። ​👉 ለመመዝገብ ለሴቶች፦ [@R3Y1NN] ለወንዶች:-@Al_amin_022 ​አላህ የምንማረው እውቀት በተግባር የምንኖርበት ያድርግልን። ​የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማዓ የዳዕዋ እና ኢርሻድ እስትራክቸር0,79%
  • 1 авг.﷽ ⭐ነብያችን ﷺ ማናቸው? እሳቸው ለዓለማት እዝነት ተደርገው የተላኩት የመጨረሻው የአላህ ነብይ የነብያት ዲን የሆነውን እስልምና ይዘው የመጡ የመልእክተኞች አውራ ናቸው የዘር ሐረጋቸው ቁረይሽይ ሲሆኑ ከነቢዩላህ ኢስማዒል ዓለይሒሰላም ይዛመዳሉ. 👉 የዘር ሐረጋቸው እና የአባታቸው መሞት 🎯 ነቢዩና ሙሐመድ (ﷺ) ቢን ዓብዱላህ - ቢን ዓብዱል ሙጥጠሊብ ( ስማቸው ሸይባ)- ቢን ሐሺም (የእሳቸው ስም ዓምር) - ቢን ዐብዲልመናፍ - ቢን ቁሰይ - ቢን ኪላብ - ቢን ሙራህ - ቢን ከዕብ - ቢን ሉአይ - ቢን ጋሊብ - ቢን ፊህር - ቢን ማሊክ - ቢን ነድር - ቢን ኪናናህ - ቢን ኹዘይማህ - ቢን ሙድሪካህ - ቢን ኢልያስ - ቢን ሙደር - ቢን ኒዛር - ቢን መዓድ- ቢን ዓድናን። ከ እናታቸው አሚነህ ጋር በ አምስተኛው አያታቸው (ኪላብ) ጋር ይዛመዳሉ 🎯 አባታቸው ዐብዲላህ ነቢዩ ﷺ ከመወለዳቸው በፊት (አመዛኙ) በንግድ ጉዞ ላይ እያሉ መዲና ውስጥ አርፈዋል 👉ውልደታቸው 🎯 ውልደት የተወለዱት ጊዜ በዓመተ ፊል (የዝሆን ዓመት) በመካ ከተማ ነው የተወለዱበት እለት ሰኞ ለመሆኑም ሰሒህ ሀዲስ መጥቶበታል ቀኑ ምን ቀን ነበር የሚለው ላይ ልዩነቶች አሉ ረቢዓል አወል 3ተኛ 8ተኛ 10ኛ 12ተኛ ተብሏል ግን በእርግጠኝነት አይታወቅም. 👉የጥቢ እናቶቻቸው 🎯 የነቢያችን(ﷺ) የጥቢ እናቶች ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው :- እናታቸው አሚና ቢንት ወህብ ሱወይበቱል አስለሚያህ እና ሃሊመቱ ሰዓድያህ አጥብተዋቸዋል .0,77%
  • 8 авг.السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ዛሬ የአላህ ፍቃድ ከሆነ ዘወትር ቅዳሜ እና እሁድ በonline ከ መግሪብ ሰላት ቡሃላ (1:20) ሚቀራው የነብዩ ﷺ ታሪክ ኪታብ (خلاصة نور اليقين) ቂርዐታችን ዛሬም ይቀጥላል ኢንሻ አላህ .0,75%
  • 26 июл.አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ በ online ምንቀራው ቂርዓት ዛሬም ይቀጥላል ትላንትና የቀራነው አብዛኛው ተማሪ ስላላዳመጠ ከ መጀመሪያ ጀምረን እንቀራለን ኢንሻ አላህ.0,74%