✞ ይታመናል TUBE 🇪🇹✞
Статистикаየዚህ ቻናል ዓላማ:- 👉 የሚታመኑበትን ጌታ በዝማሬ ያመልኩታል። 👉ሌላው አስተማሪ የሆኑ መልክቶች ና ጽሑፎች እንለቃለን። ✦ መዝሙር ለመላክ እና ሀሳብ አስተያየት ለመስጠት በ @yetamenaltube_bot ላይ አድርሱን። 👉አጋር ቻናል የህይወት ዜማ Tube 👉አጋር ቻናል worship God @yetamenaltube
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 3
- Всего постов
- 31
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Музыка (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 83
- 1/48двое суток
- 95
- 1/72трое суток
- 102
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
👉 እ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር አባታችን ሆይ፥ ከሰው ፊት ይልቅ የአንተን ፊት፣ ከሰው እርዳታ ይልቅ የአንተን ረድዔት፤ ከሰው ሞገስ ይልቅ የአንተን ሞገስ ስጠን። በልጅህ በኢየሱስ ስም አሜን!!!
👉 እ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር አስተማሪ ነው። ለዘመናት በሰላሙ መስክ፣ በእረፍቱ ጎዳና እየመራ፣ ያስተማረንን ትምህርት የሚፈትንበት መፈተኛ ጣቢያው መከራ ነው። 👉 አንድ ወታደር በበረሃ ውስጥ ከባድ ልምምዶችን የሚያካሂደው የአገሩ መንግስት ስለጠላው ሳይሆን ብቁ እንዲሆን በማሰቡ ነው። 👉 እ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር-ም እኛን በተለያዩ ችግሮች ውስጥ እያስገባ ነው ህይወታችንን የሚያስተካክለው። መከራ እኛን ወደ እርሱ የሚጎትትበት ገመድ ነው። 👉 እ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር በሕይወታችን ላይ ደስታንም ያምጣ መከራ እርሱ የወደደው ይሁንብን። 👉 ወዳጆቼ፥ በመከራ ውስጥ የምናሳልፈው ስቃይ ቀላል አይደለም፤ እጅግ መራራ ነው፥ ግን ለመብሰል ነውና እግዚአብሔር ይመስገን። እርሱ በስራው አይሳሳትም!!! የተናገረውን የሚፈጽም፣ የሚተጋ አባት ነው። ስሙ ይባረክ!!!
👉 “አንተ ግን ሕይወት ለሚገኝበት ትምህርት የሚገባውን ተናገር።” (ቲቶ 2፥1)
https://youtu.be/EA6C-5uEaIw
👉 እግዚአብሔር የሰይጣን ዉጊያ ሲበረታ እንዳንደክምና እንዳንዝል የሚያበረታን መንፈሱን ልኮልናል። 👉 ንስር ያረጀ አካሉን በአዲስ እንደሚተካ ሁሉ፥ እኛም ዘወትር በእርሱ ቅዱስ መንፈስ እንበረታለን፤ ጉልበታችንንም እናድሳለን። የሚከብደን ነገር አይኖርም!!!
👉 ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና። 👉 እንዲሁ ወደ ዘላለሙ ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋልና። (2ኛ ጴጥሮስ 1፥10-11)
👉 አበቃልኝ አትበሉ!! በእግዚአብሔር እቀጥላለሁ በሉ። ጨልሟል አትበሉ!! እግዚአብሔር ያነጋልኛል በሉ። 👉 ተዘጋ አትበሉ!! እግዚአብሔር ማንም የማይዘጋው በር ይከፍትልኛል በሉ። ተሸንፌያለሁ አትበሉ!! እግዚአብሔር እያስተማረኝ ነው በሉ። 👉 የዛሬ ሃዘናችሁ የነገ ደስታችሁን ሊያዘጋጅ ይችላል። የዛሬ እንባችሁ የነገ ምስክርነታችሁ ሊሆን ይችላል። 👉 ስለዚህ ተስፋ አትቁረጡ። እግዚአብሔር የሰጣችሁን ሕይወት በፍርሃት ሳይሆን በእምነት ኑሩ። 👉 በማጉረምረም ሳይሆን በምስጋና ኑሩ። በተስፋ ተራመዱ፣ በድፍረት ሥሩ፣ በእግዚአብሔር ታመኑ። መልካምና የተባረከ ቀን ይሁንላችሁ!!!
👉 “የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ፥ ተነሥ፥ ተነሥ፥ ኃይልንም ልበስ በቀድሞው ወራትና በጥንቱ ዘመን በነበረው ትውልድ እንደ ሆነው ተነሥ። 👉 ረዓብን የቈራረጥህ ዘንዶውንም የወጋህ አንተ አይደለህምን?" (ኢሳይያስ 51፥9)
# # # “አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፤ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች እንጨትና ውኃ በሌለበት በምድረ በዳ።” (መዝሙር 63፥1) 👉 ያለ እ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር ምቹው ቦታ ምድረ-በዳ ነው። ከ-እ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር ጋር ምድረ-በዳው ገነት ነው። በሕይወታችን ምድረ-በዳዎች የሚገጥሙን እ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር-ን አጥብቀን እንድንፈልገው ነው። 👉 እ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር-ን ለመፈለግ ለማግኘት ምቹ ቦታ ሳይሆን ምቹ ልብ ብቻ ነው የሚያስፈልገው። ዳዊት በምድረ-በዳ እ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር ከፈለገ እኛም በምንም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ብንሆን እ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር-ን ፈልገን ማግኘት እንችላለን።
# # # 1ኛ ቆሮንቶስ 9 👉 ²⁴ በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፥ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ። 👉 ²⁵ የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፥ እኛ ግን የማይጠፋውን። 👉 ²⁶ ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፥ ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም፤ 👉 ²⁷ ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ።
# # # 1ኛ ቆሮንቶስ 2 ✍️¹⁴ ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም። ✍️ ¹⁵ መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል ራሱ ግን በማንም አይመረመርም። ✍️ ¹⁶ እንዲያስተምረው የጌታን ልብ ማን አውቆት ነው? እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።
👉 አቤቱ እ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር አባታችን ሆይ፥ ዓይኖቻችንን ከፍተህ ብሩክ ቀን እንድንመለከት ስለረዳኸን ተመስገን። ምህረትህ የመቆማችን ምስጢር ነውና እ-ና-መ-ሰ-ግ-ን-ሃ-ለ-ን። 👉 ታማኝነትህ እጅግ ብዙ ነው። ሰዎች ሲለዋወጡብን፣ ሁኔታዎች ሲቀየሩብን፣ ዓለም ስትናወጥብን አንተ ግን አልተለወጥህም፤ በብዙ ታማኝነት ደግፈኸናል። ዛሬም በአንተ ላይ ልባችን ይወድቃል። 👉 አንተ ከክፉ ወጥመድ፣ ከማንኛውም ስውር ፈተና፣ ከራሳችንም ጭምር ጠብቀን። ቃልህን ቃላችን አድርግልን። 👉 በሄድንበት ቦታ ሁሉ የአንተን መዓዛ የምናርከፈክፍ ባሪያዎችህ አድርገን። በምትወደው ልጅህ በኢየሱስ ስም። አሜን!!!
🍊 “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፤” (ነሀምያ 2፥20)
💠 ወዳጆቼ፥ ዛሬ ከ-ክ-ር-ስ-ቶ-ስ ኢ-የ-ሱ-ስ ሊለዩን የሚሞክሩ ብዙ ነገሮች አሉ። ኃጢአት፣ የዓለም ፍቅር፣ የገንዘብ ፍላጎት፣ መንፈሳዊ ስንፍና፣ ምቾቶቻችን ሊለዩን ይችላሉ። 💠 ጌታ ግን በእኔ ኑሩ ብሎ ይጠራናል (ዮሐንስ 15፥4)። በእርሱ የሚኖር ሰው ከፈተና ንፁህ ይሆናል ማለት ሳይሆን ፈተናን ድል የሚነሳበት ጥበብ፣ ኃይል ይቀበላል፣ ፈተናውንም ድል ይነሳል ማለት ነው። 💠 ቅርንጫፍ ከግንዱ እስከተጣበቀ ድረስ ብቻ ነው ፍሬ ማፍራት የሚችለው። ቅርንጫፉ ከግንዱ የሚፈለገውን ምግብ እንደሚቀበል ሁሉ እኛም ከ-ክ-ር-ስ-ቶ-ስ ጸጋ፣ ኃይል እንቀበላለን። ብሎም ከ-ክ-ር-ስ-ቶ-ስ ጋር ስንኖር የመንፈስ ፍሬ እናፈራለን። 💠 ይህን ማድረግ የልባችንን በር ለ-ክ-ር-ስ-ቶ-ስ እየከፈትን እርሱ በልባችን ተንሰራፍቶ እንዲኖርበት ያደርገዋል። ክ-ር-ስ-ቶ-ስ በእኛ ውስጥ በመንፈሱ ይኖራል። 💠 እርሱ በእኛ ውስጥ ሲኖር ሕይወታችን ይለወጣል፣ ቁጣችን በትዕግስት፣ ጥላቻችን በፍቅር፣ ፍርሃታችን በእምነት ይለወጣል። ይህ የ-ክ-ር-ስ-ቶ-ስ ሕይወት በእኛ መገለጡ ማሳያ ነው። 💠 ወዳጆቼ፥ ከእኛ የሚጠበቀው ግንዳችን ከሆነው ከ-ክ-ር-ስ-ቶ-ስ ጋር በየቀኑ መጣበቅ፣ ልባችንን በፊቱ በማፍሰስ፣ የ-ክ-ር-ስ-ቶ-ስ-ን ፍቅር በመቀበልና ለሌሎች በማሳየት፣ በእምነት በመታዘዝ፣ በመንፈስ ቅዱስ በመመራት የራሳችንን ፍቃድ ሳይሆን በ-እ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር ፍቃድ በመመላለስ በ-ክ-ር-ስ-ቶ-ስ ውስጥ መኖር እንችላለን። 💠 ከእኛ የሚፈለገው ብዙ ድካም አይደለም። ከእርሱ ጋር የማያቋርጥ ሕብረት፣ ጸሎት፣ ንስሐ፣ ልባችንን ለእርሱ መክፈት ራሳችንንም በእርሱ ላይ መጣል ነው። ጸጋው ይረዳናል!!!
### "የዕለቱ የማለዳ መልዕክት" ### 👉 “ተንኮለኞች ተመካከሩ፥ ምክራቸውም ይፈርሳል፤ ቃል አውጥተው ተናገሩ፥ ቃላቸውም አይጸናም። 👫 ለእኛ ግን ምርኮ ፈጠነ፥ ብዝበዛ ቸኰለ እ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር ከእኛ ጋር ነውና።” 👉 እ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር ይሁን ያለው ይሆናል፤ ማንም አያስቆመውም። ድምጽን በድምጽ የሚሽር የበላይ ዳኛ ነው። እርሱ ያለው ከጫፍ እስከ ጫፍ ያለ ከልካይ ይሆናል። አሜን፤ ሃሌ፤ ሉያ!!! ተመስገን። 🙏
👉 ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ # የተሰበረውን ልቤን አከምከው፣ # የተዘጉ ደጆችን ከፈትክልኝ፣ # ያልጠየኩትን ሰጠኸኝ፣ # ያላሰብኩትን ጨመርክልኝ፣ # በረከትህ ቀድሞ ደረሰልኝ፣ # ምህረትህም በፊቴ ሄደ፣ # ጸጋህን እንደ ልብስ አለበስከኝ፣ # አዕምሮዬን ጠበከው፣ # ከብዙ ጉድ አወጣኸኝ፣ # ምህረትህ ከባህር ይሰፋል፣ # ታማኝነትህ ከዘላለም ያልፋል፣ 🙎♂️ ለኔ ያላደረክልኝ ምን አለ??? 🙏 ስለዚህ አመሰግንሃለው ክብር ሁሉ ለአንተ ይሁን!!! አሜን። 🙏
👉 ማንም አይፈልገኝም፣ ሰው ረስቶኛል ለምትሉ ሁሉ፦ # # # “ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም" (ዮሐንስ 14፥18) ይላል የሠራዊት ጌታ እ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር። ✍️ ወዳጆቼ፥ መተው፣ መረሳት የሰው ልጅ ብርቱ ህመም ነው። ላለመረሳት፣ ላለመተው ምንም ዋስትና የለንም። እኛ እንኳን አጠገባችን ያሉ ሰዎችን ይቅርና እ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር-ን የምንረሳ ደፋሮችና ምስኪኖች ነን። ✍️ ዛሬም ይህ ስሜት የሚሰማችሁ አንዳንድ ጊዜ በሕይወታችሁ ብቻችሁን የቀራችሁ ሰዎች ትኖሩ ይሆናል። ✍️ ወዳጆቼ፥ ሰዎች ሊተዉን ይችላሉ፣ ጓደኞች ሊርቁን ይችላሉ፣ ሁኔታዎችም ልባችንን ሊያስጨንቁ ይችላሉ። ነገር ግን ኢየሱስ የሰጠን ተስፋ ከሁሉ በላይ ነው፤ “አ-ል-ተ-ዋ-ች-ሁ-ም” ይለናል። ሁል-ጊዜ ከእኛ ጋር ነው ፈፅሞ ከህይወታችን አይለይም ማለት ነው። ✍️ በደስታችንም ሆነ በሃዘናችን፣ በስኬታችንም ሆነ በፈተናችን እርሱ አይለየንም። እኛ እርሱን ስንፈልገው ይቀርበናል፣ ስንጸልይ ይሰማናል፣ በቃሉም ያበረታታናል። ምንም ዓይነት ችግር ቢኖር እ-ግ-ዚ-አ-ብ-ሔ-ር አይተወንም። ✍️ እርሱ የታመነ አምላክ ነው። ሰው ከጎናችን ቢሆን ጊዜያዊ ነው፤ ጊዜያዊ ያልሆነው አምላክ ለዘላለም ከእኛ ጋር ነው። ለአፍታ እንኳን አይኖቹን ከእኛ ላይ የማይነቅል፣ በምንም ሁኔታ ውስጥ የማይተወን አልተዋችሁም ብሎ ቃል የገባልን ጌታ በዙፋኑ ላይ አለ። ✍️ ወዳጆቼ፥ የመተው፣ የመረሳት ስሜት ሲሰማችሁ ይህን አስታውሱ፥ የማይረሳው ጌታ ከእኔ ጋር ነው በሉ!! የተባረከና የተቀደሰ ይሁንላችሁ!!!
👉 ከጠላታችን ግፍ፣ ከጠላታችን ክፋት ያንተ ፍቅር በልጧልና ጌታችን ኢ-የ-ሱ-ስ ተመስገን።
# # # ቆላስይስ 3 (አዲሱ መ.ት) 👉 ²³ የምታደርጉትን ሁሉ ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉት ቈጥራችሁ በሙሉ ልባችሁ አድርጉት፤ 👉 ²⁴ ከጌታ ዘንድ እንደ ብድራት የምትቀበሉት ርስት እንዳለ ታውቃላችሁና፤ የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስን ነው።
👉 “ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ።” (ፊልጵስዩስ 4፥4)