Addis Ababa Health Bureau
СтатистикаThis is the official telegram channel for City Government of Addis Ababa. ☎️ +251 11 833 2493 🔗 http://www.aahb.gov.et 📧 aacahb.covid@gmail.com Addis Ababa, Ethiopia @AAHealthBureau @MoHEthiopia
- Последний пост
- 3 июн. 2024 г.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ቆልማማ እግር በፈጣሪ ቁጣ ወይም በዘር የሚከሰት አይደለም! #clubfootawareness 📱 www.moh.gov.et 📱 @MoHEthiopia 📱 Ministry of Health,Ethiopia 📱 twitter.com/FMoHealth 📱 YouTube.com/FMoHealthEthiopia
በህፃናት ላይ በተፈጥሮ የሚከሰተው ቆልማማ እግር በወቅቱ ከታከመ መዳን እንደሚችል ያውቃሉ? #clubfootawareness 📱 www.moh.gov.et 📱 @MoHEthiopia 📱 Ministry of Health,Ethiopia 📱 twitter.com/FMoHealth 📱 YouTube.com/FMoHealthEthiopia
የኩላሊት ጠጠር (Nephrolithiasis) ምንድን ነው? ብዙዎቻችን ውሀን የመጠጣት ባህላችን በጣም ዝቅ ያለ ነው። ይህ ልምድ ደሞ ብዙ መዘዝን ይዞብን መምጣቱ አይቀሬ ነው። አንድ ወንድማችን "ኩላሊቴ በጠጠር ምክንያት ፈሳሽን ሙሉ ለሙሉ ማስወገድ አልቻለም እና ሀኪሞቹ አሁን መውጣት አይችልም ፣ ገና ነው የሚል መልስ ነው የሰጡኝ ፣ እና ለምንድን ነው" የሚል ጥያቄ አንስቶልኝ ነበር። የኩላሊት ጠጠር በአብዛኛው ጊዜ 80% በውስጡ ካልሺየም ኦግዛሌት (calcium oxalete) የተቀሩት ደግሞ ከካልሺየም ፍስፌት (calcium phosphate) ፣ ዩሪክ አሲድ (uric acid) ፣ ሲስቲን (cystine) ሊሰሩ ይችላሉ። የኩላሊት ጠጠር በአብዛኛው በአንድ ኩላሊት በኩል ይታያል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በሁለቱም ኩላሊት ሊኖር ይችላል። ለኩላሊት ጠጠር የሚያጋልጡን ነገሮችስ? ለኩላሊት ጠጠር የመጋለጥ እድላችን የሚወሰነው ሽንት በተሰራበት (composition) ለምሳሌ በካልሼየም ኦግዛሌት የተሰራ ጠጠር ከሆነ በሽንት ወስጥ የሚገኝ ከፍተኛ መጠን ካልሺየም እና ኦግዛሌት ሲኖር እንዲሁም ዝቅተኛ ካልሽየም እና ፖታሺየም መውሰድ እና ፈሳሽ ነገር ያላቸው ምግቦች አለማዘውተር እንዲሁም ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከስኳር የተሰሩ ጣፋጭ መጠጦች ተጋላጭነተን ይጨምረዋል ተብሎ ይታሰባል። ሌሎች አጋላጭ ምክንያቶች ለምሳሌ አንድ ሰው ከዚህ በፊት የኩላሊት ጠጠር ከነበረበት ድጋሚ የመመለስ እድል ሊኖረው ይችላል። ከዚህ በተጨማሪ በዘር (በቤተሰብ) ወስጥ ጠጠር ያለበት ካለ ፣ በተደጋጋሚ የላይኛው የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ተጠቂ መሆን ፣ መድሀኒቶች ለምሳሌ Idinavir, Acyclovir, Sulfadiazine፣ መድሀኒቶችን ከሚገባው መጠን በላይ መውሰድ፣ ከመጠን በላይ ውፍረት፣ ከመጠን በላይ በፕሮቲን እና Vitamin C የበለፀጉ ምግቦች መመገብ ፣ ከከመጠን በላይ የሰውነት እንቅስቃሴ ለምሳሌ የማራቶን ሯጮች ፣ ደም ግፊት ፣ ስኳር ፣ ሪህ ችግር ያለባቸው ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ። ምልክቶቹስ? - በአብዛኛው ከ20-60 ደቂቃ ሄድ መጣ የሚል ህመም በጎናችን አካባቢ ሊሰማን ይችላል። ህመሙ በጣም ሀይለኛ ውጋት ፣ ቁርጠት ስለሆነ ህመምተኛው የመንቆራጠጥ ነገር ሊያሳይ ይችላል። አንዳንዴም ህመሙ እስከ ሽንት ፌኛ አካባቢ ሊደርስ ይችላል። ይህም አንደ ጠጠሩ ያለበት ቦታ ይወሰናል። ከዚህ በተጨማሪ የሽንት ቀለም ወደቀይነት (ደም) መቀላቀል ፣ ማቅለሽለሽ ፣ ማስመለስ ፣ ሽንት ማጥ ፣ ሽንት ማጣደፍ ሊኖር ይችላል። ምርምራዎቹስ? - ከላይ የጠቀስኳቸውን ምልክቶች በምናይበት ግዜ ቶሎ ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ተገቢውን ምርመራ ማድረግ ይጠበቅብናል። የጤና ባለሙያውም እንደ አስፈላጊነቱ የተለያዩ ምርመራዎችን ለምሳሌ የሽንት ምርመራ ፣ የሆድ አልትራሳውንድ ፣ የሆድ x ray ፣ የሆድ ሲቲ ስካን ፣ ሊያዝልን ይችላል ነፍሰ ጡር እናት ላይ ምርመራዎችን ስናዝ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅብናል። ምክንያቱም ከx-ray ፣ እና ሲቲ ስካን የሚወጣው ጨረር በተለይ ፅንሱን ሊጎዳው ስለሚችል ነው። ስለዚህ በዚህ ጊዜ አልትራሳውንድ ተመራጭ ይሆናል። የሚያመጣውስ ችግር? -የኩላሊት ጠጠር ካልታከመ ለኢንፌክሽን ፣ ደጋሚ ተመልሶ የመምጣት ችግር (recurrence) ፣ የሽንት ቱቦ መዘጋት ፣ ኩላሊትን ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ እስከማድረስ ሊደርስ ይችላል። ህክምናውስ? - አመጋገባችንን ማስተካከል - ጠጠሩን ያመጣብን ችግር ከታወቀ ማከም - የህመም ስሜት ላላቸው ታካሚዎች እንደ አስፈላጊነቱ የህመም ማስታገሻ ሊሰጥ ይችላል። - ማንኛውም የኩላሊት ጠጠር በቀዶ ጥገና ይወጣል ማለት አይደለም። ይህም የሚወሰነው እነደ ጠጠሩ መጠን ሲሆን የጠጠሩ መጠን እስከ 10 ሚሊ ሜትር ከሆነ በሽንት እንዲወጣ ነው የሚመከረው። በዚህ ጊዜ ታካሚው ዉሀ በብዛት እንዲጠጣ ይመከራል መጠናቸው ከ10 ሚሊሜትር በላይ ከሆነ የመውጣት እድላቸው ጠባብ ስለሆነ ሌሎች አማራጮችን መጠቀም ሊጠበቅን ይችላል። ለምሳሌ በድምፅ እና በጨረር በመታገዝ ጠጠሩ እንዲሰባበር በማድረግ ከዛም ውሀ በመጠጠት በሽንት እንዲወጣ ይደረጋል አንዳንድ ጊዜም በቀዶ ጥገና መውጣት ሊያስፈልግ ይችላል። የህክምና አማራጮቹ የሚወሰኑት በባለሙያው ስለሆነ ከባለሙያ የሚሰጡንን ምክሮች ማክበር ተገቢ ነው። NB. ንፁህ ውሀ በብዛት መጠጣት ተነገሮ ከማያልቁት ጥቅሞች አንዱ በሰውነታችን ውስጥ ያሉ አላስፈላጊ ቆሻሻዎችን ባሉበት ተቀምጠው ጉዳት እንዳያስከትሉ እና ለማስወገድ እጅግ ጠቃሚ ስለሆነ ውሀ የመጠጣት ልምዳችንን ብናዳብር መልካም ነው። ለወዳጅዎ ያጋሩ ጤና ይብዛሎ! ዶ/ር ኤርሚያስ ማሞ @AAHealthBureau @MoHEthiopia
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የኩላሊት ጠጠር (Nephrolithiasis) ምንድን ነው?
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የአጥንት ቀዶ ህክምና እና የመገጣጠሚያ ቅየራ ከፍተኛ ቀዶ ህክምና በይፋ አገልግሎት መሰጠት ጀመረ ። የአጥንት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት እና የመገጣጠሚያ ቅየራ እንዲሁም የአርትሮስኮፒ ህክምና ሠብ ስፔሻሊስት ሃኪም በሆኑት ዶ/ር ሰኢድ መሐመድ የሚመራው የሙሉ ዳሌ እና ጉልበት መገጣጠሚያዎች ቅየራ ከፍተኛ ቀዶ ህክምና በተቋማችን የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በይፋ አገልግሎት መሰጠት ጀምሯል ። ይህ አገልግሎት በሃገራችን የፕራይቬት ዊንግ ህክምና ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሠጥ ሲሆን ፣ በርካታ የችግሩ ሰለባ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ይጠቀሙበታል ተብሏል። ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጁ በሚሰጠው ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለመሆን ኘራይቬት ዊንግ ከፍቶ በተመጣጣኝ ዋጋ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ ለማቅረብ በሰፊው እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። @AAHealthBureau @MoHEthiopia
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም የጤና እና የመተሳሰብ እንዲሆን እየተመኘን በበሉ ወቅት ለጤናዎ ይበልጥ ጥንቃቄ በማድረግ በተለይም ቅባቶችን በብዛት ከመመገብ እና ምግብን በደንብ ሳያበስሉ በመመገብ የጤና እክል እንዳይገጥመን ፣ ቅባቶችን መጥኖ በመመገብ እንዲሁም ምግብን በደንብ አብስሎ በመመገብ ጤናዎን እንዲጠብቁ እያሳሰብን ለሚገጥማችሁ ማንኛውም የጤና እክል ጤና ተቋማቶቻችን እንደሁልጊዜው እናንተን ለማገልገል 24 ሰዓት አገልግሎት ላይ መሆናቸውን ለመግለጽ እንወዳለን መልካም የትንሳዔ በዓል ይሁን! የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ !! @AAHealthBureau @MoHEthiopia
በአዲስ አበባ ከተማ በዘንድሮዉ ዓመት የሚከበረዉን የትንሳኤ በአል አስመልክቶ ህብረተሰቡ በየቤቱ በእርድ መልክ የሚጠቀመዉን እና በየአካባቢዉ የቁም እንስሳትን ቅርጫ በማረድ የሚከፋፈለዉን ተከልክሏል በሚል በማህበራዊ ሚዲያዉ ሀሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ ይገኛል። በመሆኑም ከዚህ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ክልከላ ያልተደረገ ሲሆን በየአካባቢዉ በህገ ወጥ መንገድ እርድ በመፈፀም ለሆቴሎች እና ለስጋ ቤቶች በማከፋፈል ተግባር ላይ የሚገኙ አካላት የቁም እንስሳቱ ጤንነት ባልተረጋገ ጠበት ሁኔታ የከተማዉን ነዋሪ ጤንነት ላይ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል። የከተማችን ነዋሪ በአላትን ሽፋን በማድረግ ጤንነቱ ያልተረጋገጠ እንስሳት አርዶ ማከፋፈል በጤና ላይ የሚያደርሰዉን ጉዳት ግምት ዉስጥ በማስገባት በህገወጥ እርድ የሚሰማሩ አካላት በሚደረገዉ ቁጥጥር ተባባሪ እንዲሆን መልክታችንን እናስተላልፋለን። @AAHealthBureau @MoHEthiopia
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ስቅለቱ በሰላም አደረሳችሁ! #መልካም_በዓል! @MoHEthiopia
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1444ኛው የዒድ አል አድሃ በዓል አደረሳችሁ! #eiduladha @MoHEthiopia
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи