አዲስ ሪፖርተር - NEWS
описание
🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው ! => በቻናሉ 📌 ፈጣን ፥ 📌 ትኩስ ፥ 📌 ወቅታዊ እና 📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል ! 🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል ! For promotion @Addisreporter_bot #ADDIS ABABA, ETHIOPIA
35 818
подписчиков
Охват к подписчикам
8,8%
ERR
Реакции к просмотрам
0,65%
1 280 на 50 постов
Пересылки к просмотрам
0,13%
256
Постов в день
9,9
всего 131
Где отзываются чаще
доля реакций к просмотрам- 13 авг.የአውሮፓ ረጅሙ የድንግል ማርያም ሐውልት ሊመረቅ ነው። በአንድ የፖላንድ ቢሊየነር ወጪው የተሸፈነው 182 ጫማ ቁመት ያለው የድንግል ማርያም ሐውልት ግንባታ ተጠናቆ በነሐሴ ወር መጨረሻ ለምረቃ እንደሚበቃ ተገለፀ። ይህ ሐውልት በአውሮፓ አህጉር ትልቁና ረጅሙ የድንግል ማርያም ሐውልት ያደርገዋል። የግንባታውን ወጪ ሙሉ በሙሉ የሸፈኑት ታዋቂው የፖላንድ ባለሀብት ሮማን ካርኮሲክ እና ባለቤታቸው ግራዚና መሆናቸው ታውቋል። ፕሮጀክቱ ላለፉት አራት ዓመታት ሲያከናውኑ መቆየታቸው ነው የተገለፀው። ይህ መንፈሳዊ ሀውልት በሀብትና በስልጣን ላይ ትኩረት በሚደረግበት በዚህ አለም ውስጥ የሰዎችን አእምሮ ወደ ላቀ መንፈሳዊ እሴትና እምነት የሚያነሳሳ አርማ እንደሆነ አስተያየት ሰጪዎች ገልጸዋል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter3,07%
- 13 авг.በአዲስአበባ ጉዳይ ተወሰነ አከራካሪ የነበረው የአዲስ አበባ ጉዳይ ስምምነት እንደተደረሰበት ተገለጸ በተመካካሪዎች ዘንድ በሰፊው አከራካሪ ከነበሩ አጀንዳዎች መካከል የፌደራል ከተሞች፡- የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ጉዳይ ዋነኛው ሲሆን፣ በዛሬው የምክክር ውሎ በአጀንዳው ላይ ስምምነት ላይ እንደተደረሰ ተገልጿል። ከሐምሌ 8/2018 ዓ.ም. ጀምሮ በይፋ በተጀመረው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 4 ሺህ ተመካካሪዎች በተመረጡ 8 አጀንዳዎች ላይ ሲመክሩ መቆየታቸው ይታወቃል። በዛሬው የምክክር ጉባኤ ውሎ በተመካካሪዎች ዘንድ በሰፊው አከራካሪ የነበረው የፌደራል ከተሞች፡- የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ጉዳይ አጀንዳ ስምምነት እንደተደረሰበት ታውቋል። በዚህ መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ የፌደራል እና የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ እንድትሆን 500 አባላት ያሉት የተመካካሪዎች ቡድን ተስማምተዋል። ልዩ ጥቅምን በተመለከተ ዝርዝር ጉዳዮች በቀጣይ በሰፊው እንደሚመከርባቸው ተገልጿል። የአዲስ አበባ ጉዳይ በተመካካሪዎች ዘንድ በሁለት ጎራ፤ «የኦሮሚያ ክልል አካል እና ዋና መቀመጫ ትሁን» በሚል እና «የፌደራል ከተማ ዋና መቀመጫ ትሁን» በሚል በተመካካሪዎች ዘንድ ለቀናት ሲያጨቃጭቅ መቆየቱ የሚታወስ ነው። @Addis_Reporter @Addis_Reporter2,32%
- 13 авг.ሌብነት ክፉ ሥር ነው፣ እየሰረቁ ሀገር ማልማት አይቻልም ፤ ሌቦች ልነግራችሁ የምፈልገው ነገር ብር ታከማቻላችሁ እንጂ አትበሉትም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) Via FBC @Addis_Reporter @Addis_Reporter1,84%
- 14 авг.ከጥርስ ቡርሽ እስከ ማንችስተር ሲቲ! የያቡ አርትስ አስደናቂ ድል በጥርስ ቡርሽ ታዋቂ ተጫዋቾችን በመሳል የሚታወቀው ኢትዮጵያዊው ወጣት ባለጥበብ ያብ አርትስ (Yabu Arts)፣ የማንችስተር ሲቲውን ክንፍ ጀርሚ ዶኩን በልዩ ጥበብ ስሎ አቅርቧል። ከ60 ሚሊዮን በላይ ተከታይ ያለው የማንችስተር ሲቲ ኦፊሴላዊ የፌስቡክ ገፅም በስራው በመደመም ቪዲዮውን በገፁ ላይ አጋርቶታል። ይህ ድንቅ ስራ የአለም አቀፍ እውቅናን ያተረፈ ሲሆን ለኢትዮጵያዊው ወጣት ትልቅ ኩራት ሆኗል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter1,80%
- 15 авг.без подписи1,77%
- 15 авг.без подписи1,43%
- 13 авг.ክልሉ ግድያውን አስተባብሏል‼️ ተመስገን ጌታቸው፣ ይታገሱ አሰግደው እና ግዛው ግርማዬ የተባሉ ሶስት ግልሰቦች ከተሳፈሩበት የሕዝብ ማጓጓዣ መኪና ላይ “ፋኖ ናችሁ” በሚል ውንጀላ ተገደው እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ መገደላቸው ይታወሳል። ይህንን አስመልክቶ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ መግለጫ የሰጠ ሲሆን 'እርምጃ የተወሰደባቸው ግለሰቦች የጦር መሳሪያ በመታጠቅ በግድያ ላይ የተሰማሩ እና በመንግሥት ፀጥታ አካላት ላይ ጭምር ጉዳት ያደረሱ አካላት እንደነበሩ እና በትክክል የተረጋገጠባቸው ሽፍታዎች ናቸው ብለዋል። በመሆኑም በቅንጅት በተሰሩ ስራዎች የመንግስትን የሰላም አማራጮችን አንቀበልም ባሉ ሽፍታዎች ላይ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ነው ያሉት። የሚዲያዎች ሀሰተኛ መረጃ በማስረጃ ያልተደገፈ እንዲሁም ክልሉን የማይመጥን እና የህዝቦችን የእርስበርስ አንድነትን የሚሸረሽር እንደሆነም ገልፀዋል። መንግስት የህዝብን ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚወስደው እርምጃ ብሔር ተለይቶ የሚወሰድ እርምጃ ተብሎ በሀሰተኛ ሚዲያዎች የሚሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ እንደሆነም ገልፀዋል። እነዚህ ሽፍታዎች የጦር መሳሪያ በመታጠቅ በግድያ ላይ የተሰማሩ እና በመንግሥት ፀጥታ አካላት ላይ ጭምር ጉዳት ያደረሱ አካላት እንደነበሩ እና በትክክል የተረጋገጠባቸው ሽፍታዎች ናቸው'ብለዋል። ግለሰቦቹ ወንጀል ሰርተው ቢያዙ እንኳን በአደባባይ ረሽኑ የሚል የህግ ማዕቀፍ አለ? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው። @Addis_Reporter @Addis_Reporter1,39%
- 14 авг.ባንዳ ለሆዱ ሲሞት እኛ ለሀገር ሉዓላዊነት ለህዝቦች ክብርና አንድነት እንሞታለን-ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ‼️ ሻዕቢያ ከጅምሩ ኢትዮጵያን ከባህር በር ለማራቅ ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር ፅምዶ ፈጥሮ ኢትዮጵያ ላይ ደባ የሰራ ሃይል ነው ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ህወሃትም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፎ የሸጠና ለ27 አመታት ስልጣን ይዞ ኢትዮጵያ የባህር በር እንድታጣ አጠንክሮ የሰራ ቅጥረኛ የገዛ አገሩን ሠራዊት ያጠቃ የክህደት ሃይል ነው ብለዋል ። ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ በሕወሃት ክህደት የተፈተነች ነገር ግን ፀንታ የቆመች የልዩ ዘመቻ ሠራዊት መሰል ጠንካራ አርበኛ ልጆች ያሏት አገር ስለሆነች ጉዞዋን ቀጥላለች ብለዋል። የጥፋት ሃይሎች በባዕዳን ስትራቴጂ ሥር ተሰልፈው ኢትዮጵያን የማዳከምና የማፍረስ ፅምዶ የተባለ ጥምረት ቀርፀው ሕዝባችንን ለስቃይና መከራ በመዳረግ ደካማ ኢትዮጵያን ለማየት ጓጉተው ቢሠሩም ይህ ፍላጎታቸው መቼም ሊሳካ እንደማይችል አሳይተናቸዋል ብለዋል። ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ በመከፋፈል እርስ በእርሱ እንዳይተማመን ያደርግ እንደነበረ አውስተው የትግራይን ህዝብ ደግሞ የኢትዮጵያ ልጆች እየመጡብህና እየከበቡህ ነው እያለ ከወንድም የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በጠላትነት እንዲተያይ ሲሰራ የኖረ እኩይ ፖለቲካ አራማጅ ፀረ አገር ሃይል ነው ብለዋል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter1,37%
- 13 авг.ኢትዮጵያ በፕሬዚዳንት እንድትመራ ተመካካሪዎች ሙሉ በሙሉ መግባባት መደረሳቸው ተሰማ ፕሬዚዳንቱ በሕዝብ ይመረጥ ወይስ በፓርላማ በሚለው ጉዳይ ስምምነት ላይ አለመደረሱ ተነግሯል ኢትዮጵያ በጠ/ሚኒስትር ቀርቶ በፕሬዚዳንት እንድትመራ፣ የመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ፣ እንዲሁም የፖለቲካ ሥርዓት፣ የፖለቲካ ውክልናና የምርጫ ሥርዓት አጀንዳ ላይ የ500 ቡድን ተመካካሪዎች ሙሉ በሙሉ በምክረ-ሐሳብ ደረጃ መግባባት ላይ መደረሳቸው ተሰማ በዚሁ አጀንዳ ላይ ተወያይ የነበሩ ተመካካሪዎች ለሪፖርተር በሰጡት አስተያየት፣ በቀረቡት አብዛኞቹ ምክረሐሳቦች መግባባት ላይ መደረሱን ሆኖም ያላግባቡና ወደ ቀጣይ የተሻገሩ ጉዳዮች መኖራቸውንም ገልጸዋል። በዚህም የ500 ቡድን ተመካካሪዎች የአገሪቱ አስተዳደር ሥርዓት ፓርላሜንታሪ ሆኖ እንዲቀጥል፣ የአገሪቱ መሪ ፕሬዚዳንት እንዲሆን፣ አዲሱ ተመራጭ ፕሬዚዳንትም የጠቅላይ ሚኒስትሩና የፕሬዚዳንቱ ሥልጣንና ተግባርን ጠቅልሎ እንዲወጣ በምክረሐሳብ ደረጃ ከመግባባት ላይ መደረሱን፣ ይህም ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲቀር የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል። የአገሪቱ መሪ የሥልጣን ዘመን 6 ዓመት ሆኖ ለሁለት ዙር እንዲደረግ፣ የክልል መሪዎችም ከፌዴራሉ ጋር ተመሳሳይ እንዲሆን በምክረሐሳብ ደረጃ ከመግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል። የሕገመንግሥት ጉዳዮች ተርጓሚ ፍርድ ቤት እንዲቋቋም፣ አሁን ያለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አሠራር ያልመለሳቸው የማንነትና የራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄዎች “ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ኮሚሽን" የሚል ሥያሜ ያለው ገለልተኛ ተቋም በአስቸኳይ ተቋቁሞ በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ እንዲሰጥባቸው ለዚህም ይረዳ ዘንድ ልዩ የባለሙያዎች ቡድን እንዲቋቋም በምክረሐሳብ ደረጃ ከመግባባት ላይ መደረሱ ታውቋል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter1,27%
- 13 авг.በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ሱሌማን ደደፎ በኤክስ ገጻቸው ባወጡት ጽሑፍ፣ ሕወሓትን ከውድቀት ለማዳን በድርድር ስም አዲስ ሩጫ እየተጀመረ መሆኑን በማንሳት መንግሥት ከቡድኑ ጋር ምንም ዓይነት ድርድር እንዳያደርግ አሳስበዋል። ፖለቲከኛው ባጋሩት መልዕክት፣ ሕወሓት በሚለኩሰው የጦርነት እሳት እየተሸነፈና ግብዓተ መሬቱ ሲቃረብ ሁልጊዜም በድርድር ስም እንደሚያመልጥ ገልጸዋል። በዚህም ዳግም በመደራጀት የኢትዮጵያ ሕዝብ ላልተገባ መስዋዕትነት እየከፈለ እንዲኖር ማድረጉን አስገንዝበዋል። በአሁኑ ወቅትም መንግሥትን አፍርሶ አገርን ለመበተን ጀምሮት የነበረው ጦርነት ገና ሳይጀመር እንደማይሳካለት ሲረዳ፣ በድርድር ስም የድረሱልኝ ልመና እያሰማ መሆኑን እና ደጋፊዎቹም ቡድኑ ፋታ እንዲያገኝ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን አብራርተዋል። ሕወሓት በታሪኩ በድርድር የፈታው ልዩነት ታይቶ እንደማያውቅ ያስታወሱት ሱሌማን ደደፎ፣ አሁንም ይህንን ቡድን በትኖ መሪዎቹን ለፍርድ ከማቅረብ በስተቀር ምንም ዓይነት ድርድር ሊታሰብ እንደማይገባ በአጽንዖት ተናግረዋል። የትግራይ ሕዝብ እንደሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ ልጅ ወልዶ የማሳደግ፣ እህል አርሶ በነጻነት የመጠቀም፣ እንዲሁም ላለፉት አምስት አሥርተ ዓመታት ከታገተበት አፈና ነፃ የመውጣት መብት ሊረጋገጥለት እንደሚገባ በመግለጽ አቋማቸውን አንጸባርቀዋል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter1,17%
- 14 авг.በርካሽ ድሮን ሚሊዮን ዶላር ማሳጣት‼️ ኢራን የአሜሪካን የአየር መከላከያ አቅም ለማዳከም ርካሽ ድሮኖችን እየተጠቀመች መሆኑ ተገለጸ❗❗ ኢራን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ርካሽ የ«ሻሄድ» (Shahed) አይነት አጥቂ ድሮኖች ከባለስቲክ ሚሳይሎች ጋር በማቀናጀት የአሜሪካን እና አጋሮቿን የአየር መከላከያ ስርአት በመፈታተን ላይ እንደሆነ ተዘገበ። የኢራን ስትራቴጂ ዋና ዓላማ በእያንዳንዱ ድሮን ኢላማን መምታት ሳይሆን፣ በተደጋጋሚ በሚላኩ የድሮን ማዕበሎች የአሜሪካን የመከላከያ አቅም ማድከም ነው። ይህ አካሄድ የአሜሪካን ውድ ሚሳይሎች (ኢንተርሴፕተሮች) በዝቅተኛ ዋጋ በሚገመቱ የኢራን ድሮኖች ላይ እንዲባክኑ በማድረግ፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል የኢኮኖሚ እና የመከላከያ አቅም ሚዛን መዛባትን እንዲፈጠር እያደረገ መሆኑን ወታደራዊ ተንታኞች ይገልጻሉ። @Addis_Reporter @Addis_Reporter1,12%
- 15 авг.без подписи1,03%