tgindex
Последний пост
11 июл.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
889
−1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
457
21 постов
Вовлечённость
51,4%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 11 июл.1504из wollo_amana_business

    ቅጥር ና ደሞዝ ቅጥር እስር ቤት ነው። ደሞዝም ሕልምህን እንድትረሳ የሚሰጥህ ማደንዘዣ ነው። ትልቅ ደሞዝ ደግሞ ትልቅ እስር ቤት ነው። እንዳትሞት ያበላሃል፣ ያጠጣሃል፤ እንዳትድን ግን መድኃኒቱን ይነፍግሃል። ቀን በቀንም እንደ አውሬ እየሸራረፈ ይበላሃል። ለዚህ ብቸኛ መፍትሄው የኑሮ ስትራቴጂህን ከመትረፍ ወደ መትረፍረፍ ቀይረህ የራስህን ቢዝነስ መጀመር ነው። ስታስበው ውስጥህ ይፈራብህ ይሆናል፣ የሚፈራው ታስሮ ስለኖረ እንጂ ቢዝነስ አስፈሪ ስለሆነ አይደለም። የደሞዝን ኑሮ ከተቋቋምክ የቢዝነስን ልፋት መቋቋም አይከበድህም። https://t.me/wollo_amana_bussines_group

  • 10 июл.174из wollo_amana_business

    ቢዝነስ በአንድ ጀምበር አይመጣም! ​ብዙዎቻችን ያደጉና ስኬታማ የሆኑ ታላላቅ ቢዝነሶችን ስናይ የዛሬ ስኬታቸውን እንጂ ትናንት የነበሩበትን ውድቀትና እና ያሳለፈቱን ፈተና አንመለከትም። ​ ማንኛውም ትልቅ ደረጃ ላይ የደረሰ ቢዝነስ ፣ መጀመሪያ ላይ በትናንሽ እርምጃዎች ፣ በብዙ ኪሳራዎች እና ፈተናዎች ውስጥ አልፎ የመጣ ነው። ትናንት በጭቃ ውስጥ ተቦክቶ ዛሬ እሳት ላይ እንደሚጸናው ሸክላ ቢዝነስም በትግል ውስጥ አልፎ ነው ጠንካራ የሚሆነው። ​https://t.me/wollo_amana_bussines_group

  • Channel photo removed

  • አላህ በጀነቱ ይቀበላቸው ! ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ወደ አኼራ ሄደዋል:: ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን ! ! !

  • ከሐማስ ወታደራዊ ብርጌድ የተሰጠ መግለጫ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው በህዝባችን ላይ የሚደረገውን የዘር ማጥፋት ፍጅቱን ለማስቆም በሸረም አሽ-ሸይኽ የተደረገውን ድርድር አስመልክቶ በሐማስና በፍልስጤም ተቃዋሚ ሃይሎች መካከል ኃላፊነት ከተሞላበት ውይይት በኋላ ወራሪዋ ጋዛን ለቃ እንድትወጣ ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ሰርጡ እንዲገባና የእስረኞች ልውውጥ እንዲደረግ ተስማምተናል። የኳታር፣ የግብፅ እና የቱርክ ወንድሞቻችን ያደረጉትን ጥረት እናደንቃለን። ጦርነቱን ወደ ፍጻሜ ለማምጣትና ወራሪዋን ከጋዛ ሰርጥ ሙሉ ለሙሉ ለማስወጣት በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሚደረገውን ጥረትም እንዲሁ እናደንቃለን። ለስምምነቱ ዋስትናና ኃላፊነት የወሰዱ ትራምፕ፣ የዐረብና ኢስላማዊ ሀገራት እንዲሁም አለምአቀፍ ተቋማት ወራሪዋ የስምምነቱን መስፈርቶች ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንድታደርግና መሸሽም ሆነ መዘግየት ሳይኖር በፍጥነት ተፈፃሚ ይሆን ዘንድ እንዲከታተሉ እንጠይቃለን። በጋዛ ሰርጥ፣ በእየሩሳሌም እና በዌስት ባንክ በአገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ላላችሁ ህዝቦቻችን፣ ወደር የለሽ ጀግንነትና ክብር ላሳያችሁ፣ የፋሺሽቱን የወረራ እቅድ ላከሸፋችሁ፣ መብቶቻችሁን ለማስከበር ለተጋፈጣችሁ ሁሉ ሰላምታችን በያላችሁበት ይድረሳችሁ። እኚህ የገዘፉ መስዋዕቶችና ፅኑ አቋሞቻችሁ የወራሪዋ እስራኤልን የግዳጅ አገዛዝና የማፈናቀል እቅድ አጨናግፈውታል። የሕዝባችን መስዋዕትነት ከንቱ እንደማይሆን፣ ለቃል ኪዳናችን ታማኝ ሆነን እንደምንቀጥል፣ እስከ ድል ደጃፍና የራስ ገዝ አስተዳደር እስኪሰፍን የሕዝባችንን ብሄራዊ መብት አሳልፈን እንደማንሰጥ ልናረጋግጥ እንወዳለን። ኢስላማዊ ንቅናቄ - ሐማስ ሐሙስ ረቢዑል አኺር 17-1447 ሂጅሪያ ኦክቶበር 9 - 2025 ኦፊሴላዊ የሃማስ ንቅናቄ ድረ-ገጽ

  • #ጥብቅ_መልዕክት! በቦረና ወረዳ መካነሰላም ከተማ በኢሻ ሶላት ወቅት የፋኖ ታጣቂዎች መስጅድ በመግባት የመስጅድ ኢማሞችን፣ የመጅሊስ አመራሮች፣ ኻዲሞችን አሰቃቂ በሆነ መንገድ በመረሸን በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ከፍተኛ በደል ተፈፅሟል። የተገደሉ/ሸሂድ የሆኑ ኡስታዞችን፣ ኢማሞችን፣ የመጅሊስ አመራሮችን ለማሰብ ዱዓ ለማድረግና ህዝበ ሙስሊሙ ሹራ እንዲያደርግ በተጠቀሱት መስጅዶች በተገለፀዉ ሰዓት እንዲትገኙልን ጥሪ እናስተላልፋለን። #ማሳሰቢያ፦ የሰደቃና የሹራ መረሃ ግብሩን ከተገለፁት ከተሞችና መሥጅዶች በተጨማሪ በሌሎች አካባቢዎችም በማድረግ ሸሂዶችን እንዲታስቡ እንጠይቃለን!! የአማራ ክልል ሙስሊሞች ድምፅ #አክሙድ

  • ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ 💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢 በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሰላም ከተማ መስከረም 23፣2018 ዓ.ል በመስጂድ ኑር በኢሻ ሰላት ወቅት ወደ መስጂድ የታጠቁ ኃይሎች በመግባት ሃይማኖታዊ ግዴታቸውን በመወጣት ላይ በነበሩ ፦ 1 የመስጂድ ዋና ኢማምና የወረዳው መጅሊስ ም/ሰብሳቢ 2 የመስጂድ አመራሮች 3 የመስጂድ ኻዲሞችን አሰቃቂ እና አረመኔያዊ በሆነ ሁኔታ መግደላቸውን የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት አረጋግጦልናል። እነሱም ሸሂድ ሆነዋል አላህ ጀነተል ፍርዶስ ይወፍቃቸው ። ጠቅላይ ምክርቤቱ የእምነት ተቋማት የተከበሩ ቦታዎች በመሆናቸው ሊጠበቁ እንጅ እንዲህ አይነት አፀያፊ ተግባር የሚፈፀምባቸው መሆን የለባቸውምና ድርጊቱን በፅኑ ያወግዛል። መላው የሃይማኖት ተቋማትም በእምነት ቦታዎች የሚደረጉ ትንኮሳዎች እና በእምነት ተከታዮች ላይ የተቃጣ መሰል የጅምላ ግድያ ሊያወግዙና ሊያስቆሙ ይገባል። ህዝበ ሙስሊሙ ይህንን በሀይማኖት ተቋማት ላይ የተቃጣ አደጋ ለመከላከል መረጃ በመለዋወጥ የሃይማኖት ተቋማትንና አካባቢውን እንዲጠብቅ ጠቅላይ ምክርቤቱ ጥሪውን ያስተላልፋል። ብዝሃ ሀይማኖት ባለባት ሀገራችን በተለያየ እምነት ውስጥ ያሉ ህዝቦች ለዘመናት ያቆዩተን ሰላማዊ እና መልካም መስተጋብር ሆን ተብሎ ለመናድና ማባሪያ ያጣ ቀውስ ውስጥ እንድንገባ የሚፈልጉ አካላት የፈፀሙት መሆኑን ጠቅላይ ምክርቤቱ ይገነዘባል። በመጨረሻም ሁሉም ሃይማኖት ተቋማትና መሪዎች ይህ ጉዳይ አብሮ የመኖር እሴት እንዳይሸረሽር ብሎም እንዳያጠፋ ድርጊቱን እንድታወግዙ እንዲሁም በፅኑ እንድትቃወሙ እየጠየቅን መንግስትም ይህንን ተግባር በእምነት ቦታዎችና አባቶች ላይ የፈፀሙት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን። መስከረም 24፣2018 ዓ.ል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት

  • አዎ ገና ጭፍጨፋው ሳይፈፀም ጅምሮ ምንም ዓይነት ግጭት እንዳይፈጠር መስጅድ ገብተው የፈለጉትን እንዲያደርጉ ለማግባባት እስከመጨረሻው ተሞክሯል። ግቡ ፣ ፈትሹ፣ የፈለጋችሁትን ውሰዱ ወደ ግጭት የሚያመራ ነገር ግን አታድርጉ ተብለው ተለምነው ነበር!! ሙስሊሙን ከመከላከያም ሆነ ከፋኖ እኩል አርቀት ላይ በማድረግ የተለዬ ውግንናም ሆነ ጥላቻ ለአንድኛው ቡድን ማድረግ እንደማይገባ እና ከየትኛውም ወገን ጋር የትይዩም ሆነ የተቃራኒ አሰላለፍ እንዳይኖር እጅጉን ደክመን ነበር። ግና ምንም ብትሸሸው የልቡን ግብ የማይረሳ ቡድን ነውና መስጅድ ክፍት ተደርጎ «ይሄው በነፃነት ፈትሻችሁ ውጡ ብሎ እየተፈቀደለት የስም ዝርዝር ይዞ፣ የአመራር ክፍተት ለመፍጠር፣ የስነልቦና ልዕልናን ለማግኘት ብቻ  የመካነሰላም ሙስሊም የመጅሊስ አመራሮችን እና የመስጅድ ኢማም ረሽኖ የወጣውን የፋኖ ቡድን እና የቀጠናው ኤጀንቶቹን ሁኔታ ስትመለከት የህይዎት የግብ ትጥቅ አስታጥቆህ ስለሄደ ታመሰግነዋለህ!! በቅንነት ግጭት ለማስቀረት የሄድንበትን ርቀት እና እነሱ ምስኪን የመስጅድ ሰጋጆችን ረሽነው የሄዱበትን የዓላማ ፅናት ስትመለከት፣ የዚያ አካባቢ ተወላጅ የሆኑ ኤጀንቶቻቸውን የዓላማ ትጋት ስትመለከት ትልቅ የህይዎት ግብ ሰጥቶህ ያልፋል!! በሙስሊሙ ሪሶርስ፣ በሙስሊሙ የሰው ሃይል፣ በሙስሊም የብዕር ስም፣ በሙስሊም  ሃይል ክልሉን ከእስላም እያፀዳ   የመስቀል ጦርነት ግቡን በሚገርም እቅድ እየመራ ያለውን ሃይል የተግባር ትጋት አለማድነቅ አይቻልም!! ቁጭት ሆድ ውስጥ ሲሰነብት፣ እልህ በልብ ውስጥ ሲከርም ነውና ጩኸትህን፣ስሜታዊነትህን  ግብታዊ ንጭንጭህን ትተህ መሬት ላይ እንገናኝ!! የህይዎት ኮዝ የሰጠህንማ አመስግነው እንጅ!! ማር ተራ እንገናኝ!! ©️ Abduljelil Sheh Ali Kassa

  • ትላንት ምሸት በመካነ ሰላም ከተማ የተገደሉት ሙስሊሞች ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ! - ሀሩን ሚዲያ፥ መስከረም 24/2018 በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሰላም ከተማ ትላንት ጁመዓ መስከረም 23/2018 ምሽት ላይ፤ በከተማው ቀደምት በሆነው ኑር መስጅድ በታጠቁ አካላት የተገደሉትን የመስጅዱ ኢማምና የቦረና ወረዳ መጅሊስ ምክትል ሰብሳቢ ሸይኽ ጀማል ከማልን ጨምሮ አራት ሰዎች በዛሬው ዕለት በአያሌው ባህሩ የሙስሊም መካነ መቃብር ስርዓተ ቀብራቸው መፈፀሙ ተገልጿል። ሀሩን ሚዲያ ከስፍራው በደረሰው መረጃ መሰረት፤ ትላንት ምሽት የኢሻ ሰላት ተሰግዶ ከተጠናቀቀ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የታጠቁ አካላት ወደ ኑር መስጅድ ዘልቀው በመግባት "የተደበቁ የመንግስት አመራሮች አሉ፣ አውጡ በማለት" ከዚህ ጋር በተያያዘ በመስጅዱ የተደበቀ የመንግስት አመራርም ሆነ ታጣቂ የለም መስጅዳችን አትድፈሩ በማለት የአዛን ጥሪ ሲያሰሙ የነበሩትን የመስጅዱን ኢማምና የቦረና ወረዳ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ም/ል ሰብሳቢ የነበሩትን ሸይኽ ጀማል ከማልን የአዛን ጥሪውን ሳይጨርሱ በተኩስ እሩምታ እንደገደሏቸው ነው የተገለፀው። በተጨማሪ የኑር መስጂድ የረጅም አመት ጥበቃ የነበሩት ሸይኽ ይማም ሙሀመድ፤ የመካነሠላም ከተማ መጅሊስ የወጣት ሰብሳቢ ወጣት አብዱሶመድ ሙሀመድ ፤መስጅድ ኻዳም ወጣት ቃሲም ዳኜ በጥቃቱ መገደላቸው ታውቋል። ከተገደሉት በተጨማሪ የኑር መስጅድ ሙዐዚን ዓሊ ሐሰን በታጣቂዎቹ ታግተው መወሰዳቸውና የሙዓዚኑ ሁኔታ እስካሁን ድረስ አለመታወቁ ተገልጿል። ለሟቾቹ የሁሉም ከተማዋ መስጅድ ኢማሞች በኑር መስጅድ ሶላተልኻኢብ በመስገድ ዱዓ ካደረጉላቸው በኋላ በከተማዋ ቀበሌ 5 በሚገኘው አያሌው ባህሩ የሙስሊም መካነ መቃብር በርካታ የከተማዋ ሙስሊም ነዋሪዎች በተገኙበት ስርዓተ ቀብራቸው ተፈፅሟል። © ሀሩን ሚዲያ

  • ሸሂድነት ሞት አይደም እኛ የምንሞተው ለ እስልምና እንጂ ለ ፖለቲከኞች: ለፅንፈኝነት አይደለም አላሁ አክበር አላሁ አክበር አላሁ አክበር

  • ለመስገድ ወደ መስጅድ የሄዱ ሙስሊሞችን መጨፍጨፍ እጅግ ነውረኛ ተግባር ነው። ጥላቻን ከማስታገስ ውጭ ከዚህ የሚገኝ ኢምንት ትርፍ የለም። የሞቱ ወንድሞቻችን አላህ ይዘንላቸው!

  • без подписи

  • ፋኖ ወሎ መካነሰላም መስጂድ ውስጥ በፈፀመው እልቂት እስካሁን የሞቱት:- ሸኽ ጀማል ዐብዱ ሶመድ (የመስጅዱ ኢማም) ሸኽ ይማማ የምስጅዱ ኻዳሚ ወጣት ዐብዱሶመድ ወጣት ቃሲም ዳኜ አላህ በጀነት ይቀበላቸው ! ! !

  • እንደ ኻሊድ ፍጠን፣ በውሳኔህ ጽና፣ እንደ ዑመር ደግሞ፣ ፍትህን አክብረና

  • በወሎ መካነሰላም መስጂድ ውስጥ ፋኖ በከፈተው ጭፍጨፋ እስካሁን ከመስጂዱ ኢማም ጋር 5 ወንድሞቻችን ሸሂድ ሆነዋል:: አላህ ነፍሳቸውን በጀነት ይቀበል ! ሸሂድነታቸውን ያፅና ! !

  • без подписи

  • без подписи

  • "ተራቁተን ነበር ኢስላም አለበሰን።" አለች እህታችን። አላህ ለሁላችንም እሱን የመፍራት ልብስ ያልብሰን።

  • ወዳጄ ባለ ሙሉ ፀጋ ነህና አልሃምዱሊላህ በል ።

  • без подписи