ዳሩል ሀዲስ ኢንስቲትዩት Darul Hadith institute
Статистикаዳሩል ሀዲስ የዓረብኛ ቋንቋ እና የሸሪዓዊ ትምህርቶች ኢንስቲትዩት ✔ ኢስላማዊ ቤተ መፃህፍት ✔ የቁርአን ሂፍዝ ፕሮግራም ✔ የአረብኛ ቋንቋ እና ሸሪዓዊ ትምህርቶች معهد دار الحديث لتعليم اللغة العربية والعلوم الشرعية (أديس أبابا – تأسيس 1436 هے) «من يرد الله به خيرا يفقهه في الدين» 👍ዳሩል ሀዲስ
- Последний пост
- 2 апр.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
📣የሙሀደራ ግብዣ ለሴቶች "وَالَّذِينَ اهْتَدَوْا زَادَهُمْ هُدًى وَآتَاهُمْ تَقْوَاهُمْ" 🌻ረመዳናችንን አላህ ተቀብሎታል? 🌻ለመቀበሉስ ምልክቶች አሉት? በዕለቱ የዚህን መልስ እና ሌሎች ለእህቶች ጠቃሚ ትምህርቶችን አዘጋጅተን እንጠብቃችሗለን 🗓 እሁድ መጋቢት 27/2018 ⏰ ከ3:00-6:30 "وَلَا تَكُونُوا كَالَّتِي نَقَضَتْ غَزْلَهَا مِنْ بَعْدِ قُوَّةٍ أَنْكَاثًا" ⚠️ መልእክቱን ለእህቶች በማድረስ የዳእዋ ሃላፊነታችንን እንወጣ! 🕌ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ከጦር ሀይሎች ከፍ ብሎ 18 ማዞሪያ አካባቢ https://t.me/darulhadis18
без подписи
📣 ዘካተል ፊጥር ላልሰጣችሁ 🌾ዘካተል ፊጥር መሰብሰቢያ ሰዓት ስላራዘምን ያልሰጣቹ ወንድምና እህቶች ዛሬ እስከ ቀኑ 10:00 ድረስ ገቢ ማድረግ ትችላላችሁ:: ኢብኑ መስዑድ እስላሚክ ሴንተር
📣ዘካተል ፊጥር መሰብሰብ ጀምረናል❗ ▪️ከንባታ ፣ወሊሶ፣ ጉራጌ ዞን፣ ሸገር ሲቲ እና አዲስ አበባ አካባቢ ላሉ ለተቸገሩ ወገኖቻችን ዘካተል ፊጥራችሁን ለናንተ ወኪል ሆነን በጤፍ ወይንም በፉርኖ ዱቄት ለማድረስ ዝግጅታችንን አጠናቀናል:: ▪️የ 1ሰው ተመን በጤፍ 300 ብር በፉርኖ ዱቄት 275 ብር ▪️ገቢ የምታደርጉበት አካውንት ንግድ ባንክ 1000742126386 ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ⚠️ዘካውን በጤፍ ተመን የምታወጡ ያስገባችሁበትን ደረሰኝ በ 0904366666 ላይ በቴሌግራም ላኩልን። ⚠️ዘካችሁን የምንቀበለው እስከ ረቡዕ ረመዳን 29 ከቀኑ 7:00 ድረስ ብቻ ይሆናል። __ 🕌ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር Http://telegram.me/merkezuna
🌙 የጎዳና ኢፍጣር🌙 =============== 🖌 በኢልያስ አሕመድ በቅድሚያ ይህን ፕሮግራም ለማሰናዳት በቅንነት የሚለፉ ግለሰቦችና ድርጅቶችን አላህ የኒያቸውን እንዲሰጣቸው እንለምናለን፤ ከዚህ በታች ያለው አጭር ፅሑፍ የልፋታቸው መሰረት የተስተካከለ እንዲሆን ታስቦ በተቆርቋሪነት የተከተበ ነው። ››››› ‹‹‹‹‹ በህብረት ማፍጠር ሁለት አይነት አፈፃፀሞች ሊኖሩት ይችላል፦ 1ኛ/ ለማፍጠር መሰባሰቡን ዋና ኢላማ ሳያደርጉ በተወሰኑ አጋጣሚዎች በህብረት ማፍጠር ሲሆን ይህም እንደማይወገዝ ግልፅ ነው። ለምሳሌ፦ ለሰላት ወደ መስጂድ የመጣውን ስብስብ ወይም ድሆችን በአንድ ቦታ ለማስፈጠር የሚኖረው መሰባብሰብ ተቃውሞ ሊነሳበት አይችልም። ዘመድና ጓደኛን ጠርቶ በጋራ ማፍጠርም እንደተራ ግብዣ ሊታይ ይችላል። ፆመኛን ማስፈጠርን አስመልክቶ የተወራውን ምንዳ ለማግኘት ከታሰበ ደግሞ እንደ እሳቤው የተወደደ ሊሆን ይችላል። ብዙ ዑለማዎች የፈቀዱትም በዚህኛው ምድብ የሚካተተውን ነው። 2ኛው/ ለኢፍጣር መሰባሰቡ ራሱ እንደ ዋና ግብ ታልሞና ይህንንም በሚያሳብቁ ተግባራት ታጅቦ በስፋት የሚተገበር አፈፃፀም ሲሆን ይህ የቢድዓ መገለጫን ሊላበስ ይችላል። በሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለመደው የጎዳና ኢፍጣር ይህንን ይዘት እንደተላበሰ ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል፦ 👉 እንደ በዓላት የሚጠበቅ ህዝባዊ ኩነት መሆኑ፣ (Grand Iftar 1, 2 እየተባለ ዘንድሮ 4ኛው ላይ ደርሰናል!) 👉 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የበድር ዘመቻ የተካሄደበት የረመዳን 17ኛው እለት ለዚህ አመታዊ መሰባሰቢያ እንዲሆን በተደጋጋሚ መመረጡ፣ 👉 ሰዎች በነቂስ ወጥተው እንዲታደሙ ሰፊ ጥሪ መደረጉ፣ 👉 በታዳሚያን ብዛት ከሌሎች አገራት ጋር ፉክክር ውስጥ የተገባበት መሆኑ፣ እና ሌሎች አባሪ ሂደቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ። የነዚህ ሂደቶች ስብስብ ተግባሩን ራሱን የቻለ አዲስ የሙስሊሞች ይፋዊ ምልክት (ሺዓር) እያደረገው ነው። 📌 ታላቁ ኢማም #ኢብኑ_ተይሚያህ በዲን ውስጥ ስለሚጨመሩ የፈጠራ በዓላት በሚያብራሩበት አውድ ስለ በዓላት ምንነት ሲያስረዱ የሚከተለውን ይላሉ፦ «“ዒድ” (በዓል) በተለመደ መልኩ ለሚደጋገም ሁሉን አቀፍ መሰባሰብ የሚሰጥ ስያሜ ሲሆን በየአመቱ፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩ ወይም በተመሳሳይ ሁኔታ (በውስን ቀናት) የሚመላለስ ነው። በዓል የተወሰኑ ነገሮችን አቅፎ ይይዛል፤ ከነሱ መካከል፦ እንደ ዒድ አል-ፊጥር እና እንደ ጁሙዓ የሚመላለስ ቀን፣ (በቀኑ) መሰባሰብ፣ ይህን ተከትለው የሚመጡ አምልኳዊ ወይም ልማዳዊ ተግባራት ይገኛሉ። በዓል በውስን ቦታ የተገደበ ሊሆን ይችላል፤ ያልተገደበም ሊሆን ይችላል፤ እነዚህ ነገሮች ሁሉ (በነጠላ) ዒድ ሊሰኙ ይችላሉ.... “ዒድ” የሚለው ቃል ለእለቱና በውስጡ ላለው ተግባር ጥምረት የሚሰጥ ስም ሊሆን ይችላል፤ ይህም አብዛኛው (አጠቃቀሙ) ነው።» [“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (1/496 – 497)] 📌 በሌላ ቦታም እንዲህ ብለዋል፦ «ከተደነገጉት መሰባሰቦች ውጪ ሳምንታት፣ ወራት፣ ወይም አመታት በተደጋገሙ ቁጥር የሚደጋገም መሰባብሰብን በቋሚነት መያዝ ለአምስቱ ሰላቶች፣ ለጁሙዓ፣ ለሁለቱ ዒዶችና ለሐጅ ከመሰባብሰብ ጋር ይመሳሰላል፤ ፈጠራና አዲስ ተግባር ማለት ይህ ነው!)) [“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/140)] 📌 አለፍ ብለውም እንዲህ ይላሉ፦ «ከነዚህ (ከተደነገጉት) መሰባሰቦች ባሻገር የሚለመድ ተጨማሪ መሰባሰብ ከተጀመረ አላህ ከደነገገውና ካፀደቀው ፈለግ ጋር የሚመሳሰል ይሆናል …. - ለብቻው የሆነ ግለሰብ ወይም ውስን ስብስቦች አንዳንዴ ከሚሰሩት በተለየ መልኩ!)) [“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/144)] ይህ ማብራሪያ ሰዎች በየውስን ጊዜ በታወቀ ቀጠሮ የሚፈፅሙት ህዝባዊ ስብስብ እንደ በዓል ባይታቀድ እንኳ በዓላዊ ይዘትን እንደሚላበስ ያሳያል። አንድ ነገር በጥቅሉ የሚፈቀድ፣ ብሎም የሚደነገግ ከመሆኑ ጋር በአፈፃፀሙ ረገድ የሚኖሩ ተጓዳኝ ነገሮች ብይኑ እንዲቀየር ሊያደርጉ ይችላሉ። 📌 ታዋቂው ዓሊም #ኢብኑ_ደቂቅ_አል_ዒድ አንዳንድ ሸሪዓዊ አፈፃፀሞችን ለመተግበር በደካማ የሐዲሥ ዘገባ ላይ ስለመመርኮዝ የሚነሳውን ውዝግብ አስመልክቶ እንዲህ ይላሉ፦ «የ“መውዱዕ” (የተቀነባበረ የውሸት ሐዲሥ) ክልል ውስጥ ያልገባ ደዒፍ (ደካማ) ከሆነ በዲን ላይ አዲስ ይፋዊ ምልክት “ሺዓር” የሚፈጥር ከሆነ ይከለከላል፤ ካልሆነ ደግሞ ምልከታ የሚቸረው ይሆናል...» [“ኢሕካሙ’ል-አሕካም” (1/501)] 👉 አንድን ተግባር እንደ “ሺዓር” ከሚያስቆጥሩት የአፈፃፀም ሂደቶች መካከል ሰዎች ተጠራርተው የሚሰባሰቡበት ኩነት መሆኑ ነው፤ በተለይ እንደ ዒድ ሰላት በጎዳና/በአደባባይ ላይ የሚተገበር ከሆነ! ይህን የሚያብራራ አንድ ምሳሌ እንጥቀስ፦ ሰዎች በተሰባሰቡበት አጋጣሚ አንዳንዴ ዱዓ ማድረግ የሚቻል ከመሆኑ ጋር ይህን በህብረት ለመፈፀም መጠራራትን ብዙ የኢስላም ሊቃውንት አይደግፉም። 📌 #አል_ኢማም_አሕመድ እንዲህ ተብለው ተጠየቁ፦ «ሰዎች ተሰባስበው አላህን መለመናቸውና እጃቸውንም ማንሳታቸው ይጠላል?» እርሳቸውም፦ «مَا أَكْرَهُهُ لِلْإِخْوَانِ إذَا لَمْ يَجْتَمِعُوا عَلَى عَمْدٍ إلَّا أَنْ يَكْثُرُوا» = «ሆን ብለው ካልተሰባሰቡ ለ(ዲን) ወንድማማቾች አልጠላውም – ካልበዙ በስተቀር!» 📌 #አል_ኢማም_ኢስሓቅ ኢብኑ ራሀወይህ ሲጠየቁም ተመሳሳይ መልስ ሰጥተዋል። «ካልበዙ በስተቀር» ሲሉ ልማድ በማድረግ እስካልተበራከቱ ድረስ ማለታቸው እንደሆነ ጠያቂው (ኢስሓቅ ኢብኑ መንሱር) ተናግረዋል! [“መሳኢሉ’ል-ኢማሚ አሕመድ ወኢስሓቅ” (9/4879)፣ “ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/140)]፣ “አል-ኣዳብ አሽ-ሸርዒይ-ያህ” ሊ’ብኒ ሙፍሊሕ (2/103)] 👉 ስለሆነም ነገሩ ከዚህ በላይ ሳያድግ መግታቱ አስፈላጊ ነው። ይህ ከዚህ በፊት የተስተዋሉ የአፈፃፀም ግድፈቶችን ከግምት ሳናስገባ የምንደርስበት መደምደሚያ ሲሆን፤ ያለ በቂ ምክንያት መንገድ መዘጋጋት፣ አግባብ ያልሆነ የወንድና የሴት መቀላቀል፣ የሴቶች ምስል በሚዲያ የሚሰራጭበት ቀረፃ፣ ሴቶች በምሽት መንገላታታቸው፣ በሙዚቃ መሳሪያ የታጀበ "ነሺዳ"፣ የምግብ ብክነት እና መሰል ጥፋቶች የሚታከሉበት ከሆነ ደግሞ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆናል። አዎን! ፕሮግራሙ ከዚህ በፊት ሞራላዊ ጥቅምን አስገኝቶ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን በውስጡ ከላይ የጠቆምነውን አመዛኝ ጉዳት ማካተቱ ለመታቀብ በቂ እንደሆነ አስባለሁ። አላህ ይበልጥ አዋቂ ነው። ረመዳን 15/1445 ____ @ustazilyas
⚘️ የረመዳን የሙሃደራ ግብዣ ለእህቶች ⭐ ረመዳን የለውጥ ወር ⭐ ተከታታይ 2 የረመዳን እሁድ ጠዋቶችን ከኛ ጋር በማሳለፍ ኢማንሽን የምታድሺበት ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ላይ ተሳታፊ እንድትሆኝ ተጋብዘሻል! ◽የካቲት 22 እና 29/2018 ◽ከጠዋቱ 3:00-6:30 ኢብኑ መስ ዑድ እስላሚክ ሴንተር ከጦር ሃይሎች ከፍ ብሎ 18 ማዞሪያ አካባቢ ⚠️ጥሪውን ለእህቶች በማድረስ የምንዳ ተካፋይ እንሁን https://t.me/darulhadis18
🌙 ረመዳን ሙባረክ ልዩ የሙሃደራ ግብዣ ለሴቶች ⭐ የረመዳን ጾምን የተመለከቱ ድንጋጌዎች ⭐ በአላህ ማመን ⭐ ወደ አላህ ምህረት እንሽቀዳደም ✔️የካቲት 15/ 2018 ✔️ጠዋት 3:00 18 በሚገኘው ኢብኑ መስዑድ እስላሚክ ሴንተር https://t.me/darulhadis18
без подписи
без подписи
без подписи
የነገ ቀጠሮዎ የት ነው...? 🕌 ጦር ሀይሎች ረያን መስጂድ እንገናኝ ። ⏱ ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ #3ኛው የነሲሓ ኮንፈረስ ============================= ነሲሓ ቲቪ ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም! 📡 Ethiosat /11545 / H / 45000
ነሲሓ ኮንፈረስ 3 كُنْتُمْ خَيْرَ أُمَّةٍ " ምርጥ ህዝቦች ! " ⏱ እሁድ የካቲት 1 🕌 በረያን መስጅድ ( ጦር ሀይሎች) =============================== ነሲሓ ቲቪ ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም! 📡 Ethiosat /11545 / H / 45000
📢ልዩ ስንቅ ለሴት ታዳጊዎችና ወጣቶች የመጪው ጊዜ የኢስላም ተረካቢዎች! 🗓 ከጥር 26- 28፣2018 🕘ጠዋት ከ3:00-6:30 1⃣ 18 ማዞሪያ የሚገኘው መርከዝ ኢብኑ መስዑድ 👇በዚህ ማስፈንጠሪያ ይመዝገቡ https://forms.gle/7cHjHhBLNc4Wxo4KA +251904366666 2⃣ ቤተል ቅርንጫፍ 👇በዚህ ማስፈንጠሪያ ይመዝገቡ https://forms.gle/dEdoFKzh2ayncn9k9 +251929749160 ⚠️ወላጆች ልጆችዎን ወደዚህ ድንቅ ዝግጅት በመላክ የህይወት ስንቅን ያውርሱ። https://t.me/darulhadis18
🌙 ከፊታችን እየመጣ ያለውን የእዝነት ወር በመተዛዘን እናሳልፈው! በዚያ የመልካም ስራ ምንዳዎች እጥፍ ድርብ በሚሆንበት የረመዳን ወር ለተቸገሩ ቤተሰቦች አስቤዛ በማቅረብ እንዲያፈጥሩና እንዲመገቡ በማድረግ ለአኼራዎ ይሰንቁ! 💰 የ1 ቤተሰብ ማስፈጠሪያ ብር 6000 📌 ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ንግድ ባንክ 1000742126386 ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿وَالصَّدَقَةُ تُطْفِئُ الْخَطِيئَةَ كَمَا يُطْفِئُ الْمَاءُ النَّارَ﴾ “ሰደቃ (ምፅዋት) ወንጀልን ታጠፋለች (ታሰርዛለች) ልክ ውሃ እሳትን እንደሚያጠፋው።” ቲርሚዚ በህይወት የሌሉ ቅርብ ቤተሰቦቻችንን ሰደቃ በማውጣት እናስታውሳቸው! __ 🕌በኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር Http://telegram.me/merkezuna
📢ልዩ ስንቅ ለታዳጊዎች የመጪው ጊዜ የኢስላም ተረካቢዎች! ⭐️ውድ ለሆኑት ትውልዶች! ለታዳጊ ተማሪዎች የተዘጋጀ ለ 3 ቀናት የሚቆይ ድንቅ ኮርስ! ኮርሱ በአላህ ፈቃድ የሚመጥናቸውን ወሳኝና ወቅታዊ ትምህርቶች የሚያገኙበት ይሆናል። ▫️እድሜ ከ10- 18 🗓 ከጥር 26- 28፣2018 🕘ጠዋት ከ3:00-6:30 1⃣ 18 ማዞሪያ የሚገኘው መርከዝ ኢብኑ መስዑድ 👇በዚህ ማስፈንጠሪያ ይመዝገቡ https://forms.gle/7cHjHhBLNc4Wxo4KA +251904366666 2⃣ ቤተል ቅርንጫፍ 👇በዚህ ማስፈንጠሪያ ይመዝገቡ https://forms.gle/dEdoFKzh2ayncn9k9 +251929749160 ⚠️ወላጆች ልጆችዎን ወደዚህ ድንቅ ዝግጅት በመላክ የህይወት ስንቅን ያውርሱ። ✔️መልዕክቱን ሼር በማድረግ የምንዳ ተካፋይ እንሁን! https://t.me/darulhadis18
без подписи
📣 ነገ ተጋብዛችኋል
📣 የምርቃትና የዳእዋ ፕሮግራም ⭐️እሁድ ጥቅምት 23፣2018 🔘ከጠዋቱ 3:00-6:30 ⚡️ስቴድየም አካባቢ በሚገኘው ኦሮሞ ባህል ማእከል አዳራሽ ⭐️⭐️ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ዳሩል ሀዲስ ኢንስቲትዩት ⚠️ጥሪውን ተደራሽ በማድረግ የአጅር ተካፋይ ይሁኑ! @darulhadis18
📣የሙሐደራ ግብዣ ለሴቶች 💎ስለ እምነትሽና ስለ ሂጃብሽ የምንመካከርበት መድረክ ▫️እሁድ ጥቅምት 9፣ 2018 ▫️ከጠዋቱ 3:00-6:00 ⭐️ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር @darulhadis18
📌 ሳምንታዊ የቅዳሜ የዲን ትምህርት ፕሮግራም ለሴቶች 📢 ታላቅ የምስራች በስራ እና በትምህርት ምክንያት በመደበኛ ቀን የዲን ትምህርት ለመማር ላልተመቻችሁ እህቶች ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ዳሩል ሀዲስ ቤተል ቅርንጫፍ ዘወትር ቅዳሜ ከሰአት ሳምንታዊ የዲን ኮርስ ለመጀመር ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል። 👌 የተማሪዎች የቅበላ መስፈርት ▪️እድሜ ከ 12 አመት በላይ የሆነች ⏱የትምህርት ሰዐት ከ8:00-11:00 🏢 አድራሻ ፦ ቤተል አደባባይ ንግድ ባንክ ያለበት ህንፃ 4ኛ ፎቅ ✔️ትምህርቱ የሚጀመረው በአላህ ፈቃድ የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 1፣2018 ይሆናል። ☎️ ለበለጠ መረጃ፦ 👇 ▪️911062499 ▪️911692377 ⚠️መልእክቱን ሼር በማድረግ የአጅር ተካፋይ እንሁን! @darulhadis18