tgindex
🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

🌺 ለስኬታማ ቤተሰብ 🌺

Статистика

ለስኬታማ ቤተሰብ - نحو الأسرة الناجحة ቤታችንን ኢሰላማዊ በማድረግ ትዉልድን እናድን! ስለ ቻናላችን ያሎትን ሀሳብና አስተያየት በ @nesiha_ouserya_Bot ይላኩልን! እናመሰግናለን! @nesiha_ouserya

Последний пост
2 апр.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 799
0 Са 4 дн.
Сутки
−1
−0,06%
Неделя
—
 
Месяц
—
 
Просмотров на пост
816
20 постов
Вовлечённость
45,4%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всогО 20
УпОПинаниК
0
канаНОв
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
—
1/48двое суток
—
1/72трое суток
—

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 2 апр.6093иС darulhadis18

    📣የሙሀደራ ግብዣ ለሴቶች "وَالَّذِينَ اهْتَدَوْا زَادَهُمْ هُدًى وَآتَاهُمْ تَقْوَاهُمْ" 🌻ረመዳናችንን አላህ ተቀብሎታል? 🌻ለመቀበሉስ ምልክቶች አሉት? በዕለቱ የዚህን መልስ እና ሌሎች ለእህቶች ጠቃሚ ትምህርቶችን አዘጋጅተን እንጠብቃችሗለን 🗓 እሁድ መጋቢት 27/2018 ⏰ ከ3:00-6:30 "وَلَا تَكُونُوا كَالَّتِي نَقَضَتْ غَزْلَهَا مِنْ بَعْدِ قُوَّةٍ أَنْكَاثًا" ⚠️ መልእክቱን ለእህቶች በማድረስ የዳእዋ ሃላፊነታችንን እንወጣ! 🕌ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ከጦር ሀይሎች ከፍ ብሎ 18 ማዞሪያ አካባቢ https://t.me/darulhadis18

  • йоС пОдписи

  • 18 мар.695иС merkezuna

    📣 ዘካተል ፊጥር ላልሰጣችሁ 🌾ዘካተል ፊጥር መሰብሰቢያ ሰዓት ስላራዘምን ያልሰጣቹ ወንድምና እህቶች ዛሬ እስከ ቀኑ 10:00 ድረስ ገቢ ማድረግ ትችላላችሁ:: ኢብኑ መስዑድ እስላሚክ ሴንተር

  • 15 мар.632иС merkezuna

    📣ዘካተል ፊጥር መሰብሰብ ጀምረናል❗ ▪️ከንባታ ፣ወሊሶ፣ ጉራጌ ዞን፣ ሸገር ሲቲ እና አዲስ አበባ አካባቢ ላሉ ለተቸገሩ ወገኖቻችን ዘካተል ፊጥራችሁን ለናንተ ወኪል ሆነን በጤፍ ወይንም በፉርኖ ዱቄት ለማድረስ ዝግጅታችንን አጠናቀናል:: ▪️የ 1ሰው ተመን በጤፍ 300 ብር                            በፉርኖ ዱቄት 275 ብር ▪️ገቢ የምታደርጉበት አካውንት ንግድ ባንክ 1000742126386 ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ⚠️ዘካውን በጤፍ ተመን የምታወጡ ያስገባችሁበትን ደረሰኝ በ 0904366666 ላይ በቴሌግራም  ላኩልን። ⚠️ዘካችሁን የምንቀበለው እስከ ረቡዕ ረመዳን 29 ከቀኑ 7:00 ድረስ ብቻ ይሆናል። __ 🕌ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር Http://telegram.me/merkezuna

  • 14 мар.509иС merkezuna

    📣 አደራችሁን አድርሰናል! አልሃምዱሊላህ ደካሞችን የማስፈጠር ኸይር ስራ ጥሪ ምላሽ የሰጣቹ የመርከዝ ተማሪዎች፣ ሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ያላችሁ እህትና ወንድሞች እንዲሁም ለዚህ ፕሮግራም መሳካት አስተዋጽዖ ያደረጋችሁ ሁሉ አላህ መልካም ስራችሁን ይቀበላችሁ جزاكم الله خيرا ____ 🕌 ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር 📲 t.me/merkezuna

  • 5 мар.5972иС ustazilyas

    🌙 የጎዳና ኢፍጣር🌙 =============== 🖌 በኢልያስ አሕመድ በቅድሚያ ይህን ፕሮግራም ለማሰናዳት በቅንነት የሚለፉ ግለሰቦችና ድርጅቶችን አላህ የኒያቸውን እንዲሰጣቸው እንለምናለን፤ ከዚህ በታች ያለው አጭር ፅሑፍ የልፋታቸው መሰረት የተስተካከለ እንዲሆን ታስቦ በተቆርቋሪነት የተከተበ ነው።               ››››› ‹‹‹‹‹ በህብረት ማፍጠር ሁለት አይነት አፈፃፀሞች ሊኖሩት ይችላል፦ 1ኛ/ ለማፍጠር መሰባሰቡን ዋና ኢላማ ሳያደርጉ በተወሰኑ አጋጣሚዎች በህብረት ማፍጠር ሲሆን ይህም እንደማይወገዝ ግልፅ ነው። ለምሳሌ፦ ለሰላት ወደ መስጂድ የመጣውን ስብስብ ወይም ድሆችን በአንድ ቦታ ለማስፈጠር የሚኖረው መሰባብሰብ ተቃውሞ ሊነሳበት አይችልም። ዘመድና ጓደኛን ጠርቶ በጋራ ማፍጠርም እንደተራ ግብዣ ሊታይ ይችላል። ፆመኛን ማስፈጠርን አስመልክቶ የተወራውን ምንዳ ለማግኘት ከታሰበ ደግሞ እንደ እሳቤው የተወደደ ሊሆን ይችላል። ብዙ ዑለማዎች የፈቀዱትም በዚህኛው ምድብ የሚካተተውን ነው። 2ኛው/ ለኢፍጣር መሰባሰቡ ራሱ እንደ ዋና ግብ ታልሞና ይህንንም በሚያሳብቁ ተግባራት ታጅቦ በስፋት የሚተገበር አፈፃፀም ሲሆን ይህ የቢድዓ መገለጫን ሊላበስ ይችላል። በሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለመደው የጎዳና ኢፍጣር ይህንን ይዘት እንደተላበሰ ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል፦ 👉 እንደ በዓላት የሚጠበቅ ህዝባዊ ኩነት መሆኑ፣ (Grand Iftar 1, 2 እየተባለ ዘንድሮ 4ኛው ላይ ደርሰናል!) 👉 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የበድር ዘመቻ የተካሄደበት የረመዳን 17ኛው እለት ለዚህ አመታዊ መሰባሰቢያ እንዲሆን በተደጋጋሚ መመረጡ፣ 👉 ሰዎች በነቂስ ወጥተው እንዲታደሙ ሰፊ ጥሪ መደረጉ፣ 👉 በታዳሚያን ብዛት ከሌሎች አገራት ጋር ፉክክር ውስጥ የተገባበት መሆኑ፣ እና ሌሎች አባሪ ሂደቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ። የነዚህ ሂደቶች ስብስብ ተግባሩን ራሱን የቻለ አዲስ የሙስሊሞች ይፋዊ ምልክት (ሺዓር) እያደረገው ነው። 📌 ታላቁ ኢማም #ኢብኑ_ተይሚያህ በዲን ውስጥ ስለሚጨመሩ የፈጠራ በዓላት በሚያብራሩበት አውድ ስለ በዓላት ምንነት ሲያስረዱ የሚከተለውን ይላሉ፦ «“ዒድ” (በዓል) በተለመደ መልኩ ለሚደጋገም ሁሉን አቀፍ መሰባሰብ የሚሰጥ ስያሜ ሲሆን በየአመቱ፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩ ወይም በተመሳሳይ ሁኔታ (በውስን ቀናት) የሚመላለስ ነው። በዓል የተወሰኑ ነገሮችን አቅፎ ይይዛል፤ ከነሱ መካከል፦ እንደ ዒድ አል-ፊጥር እና እንደ ጁሙዓ የሚመላለስ ቀን፣ (በቀኑ) መሰባሰብ፣ ይህን ተከትለው የሚመጡ አምልኳዊ ወይም ልማዳዊ ተግባራት ይገኛሉ። በዓል በውስን ቦታ የተገደበ ሊሆን ይችላል፤ ያልተገደበም ሊሆን ይችላል፤ እነዚህ ነገሮች ሁሉ (በነጠላ) ዒድ ሊሰኙ ይችላሉ.... “ዒድ” የሚለው ቃል ለእለቱና በውስጡ ላለው ተግባር ጥምረት የሚሰጥ ስም ሊሆን ይችላል፤ ይህም አብዛኛው (አጠቃቀሙ) ነው።» [“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (1/496 – 497)] 📌 በሌላ ቦታም እንዲህ ብለዋል፦ «ከተደነገጉት መሰባሰቦች ውጪ ሳምንታት፣ ወራት፣ ወይም አመታት በተደጋገሙ ቁጥር የሚደጋገም  መሰባብሰብን በቋሚነት መያዝ ለአምስቱ ሰላቶች፣ ለጁሙዓ፣ ለሁለቱ ዒዶችና ለሐጅ ከመሰባብሰብ ጋር ይመሳሰላል፤ ፈጠራና አዲስ ተግባር ማለት ይህ ነው!)) [“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/140)] 📌 አለፍ ብለውም እንዲህ ይላሉ፦ «ከነዚህ (ከተደነገጉት) መሰባሰቦች ባሻገር የሚለመድ ተጨማሪ መሰባሰብ ከተጀመረ አላህ ከደነገገውና ካፀደቀው ፈለግ ጋር የሚመሳሰል ይሆናል …. - ለብቻው የሆነ ግለሰብ ወይም ውስን ስብስቦች አንዳንዴ ከሚሰሩት በተለየ መልኩ!)) [“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/144)] ይህ ማብራሪያ ሰዎች በየውስን ጊዜ በታወቀ ቀጠሮ የሚፈፅሙት ህዝባዊ ስብስብ እንደ በዓል ባይታቀድ እንኳ በዓላዊ ይዘትን እንደሚላበስ ያሳያል። አንድ ነገር በጥቅሉ የሚፈቀድ፣ ብሎም የሚደነገግ ከመሆኑ ጋር በአፈፃፀሙ ረገድ የሚኖሩ ተጓዳኝ ነገሮች ብይኑ እንዲቀየር ሊያደርጉ ይችላሉ። 📌 ታዋቂው ዓሊም #ኢብኑ_ደቂቅ_አል_ዒድ አንዳንድ ሸሪዓዊ አፈፃፀሞችን ለመተግበር በደካማ የሐዲሥ ዘገባ ላይ ስለመመርኮዝ የሚነሳውን ውዝግብ አስመልክቶ እንዲህ ይላሉ፦ «የ“መውዱዕ” (የተቀነባበረ የውሸት ሐዲሥ) ክልል ውስጥ ያልገባ ደዒፍ (ደካማ) ከሆነ በዲን ላይ አዲስ ይፋዊ ምልክት “ሺዓር” የሚፈጥር ከሆነ ይከለከላል፤ ካልሆነ ደግሞ ምልከታ የሚቸረው ይሆናል...» [“ኢሕካሙ’ል-አሕካም” (1/501)] 👉 አንድን ተግባር እንደ “ሺዓር” ከሚያስቆጥሩት የአፈፃፀም ሂደቶች መካከል ሰዎች ተጠራርተው የሚሰባሰቡበት ኩነት መሆኑ ነው፤ በተለይ እንደ ዒድ ሰላት በጎዳና/በአደባባይ ላይ የሚተገበር ከሆነ! ይህን የሚያብራራ አንድ ምሳሌ እንጥቀስ፦ ሰዎች በተሰባሰቡበት አጋጣሚ አንዳንዴ ዱዓ ማድረግ የሚቻል ከመሆኑ ጋር ይህን በህብረት ለመፈፀም መጠራራትን ብዙ የኢስላም ሊቃውንት አይደግፉም። 📌 #አል_ኢማም_አሕመድ እንዲህ ተብለው ተጠየቁ፦ «ሰዎች ተሰባስበው አላህን መለመናቸውና እጃቸውንም ማንሳታቸው ይጠላል?» እርሳቸውም፦ «مَا أَكْرَهُهُ لِلْإِخْوَانِ إذَا لَمْ يَجْتَمِعُوا عَلَى عَمْدٍ إلَّا أَنْ يَكْثُرُوا» = «ሆን ብለው ካልተሰባሰቡ ለ(ዲን) ወንድማማቾች አልጠላውም – ካልበዙ በስተቀር!» 📌 #አል_ኢማም_ኢስሓቅ ኢብኑ ራሀወይህ ሲጠየቁም ተመሳሳይ መልስ ሰጥተዋል። «ካልበዙ በስተቀር» ሲሉ ልማድ በማድረግ እስካልተበራከቱ ድረስ ማለታቸው እንደሆነ ጠያቂው (ኢስሓቅ ኢብኑ መንሱር) ተናግረዋል! [“መሳኢሉ’ል-ኢማሚ አሕመድ ወኢስሓቅ” (9/4879)፣ “ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/140)]፣ “አል-ኣዳብ አሽ-ሸርዒይ-ያህ” ሊ’ብኒ ሙፍሊሕ (2/103)] 👉 ስለሆነም ነገሩ ከዚህ በላይ ሳያድግ መግታቱ አስፈላጊ ነው። ይህ ከዚህ በፊት የተስተዋሉ የአፈፃፀም ግድፈቶችን ከግምት ሳናስገባ የምንደርስበት መደምደሚያ ሲሆን፤ ያለ በቂ ምክንያት መንገድ መዘጋጋት፣ አግባብ ያልሆነ የወንድና የሴት መቀላቀል፣ የሴቶች ምስል በሚዲያ የሚሰራጭበት ቀረፃ፣ ሴቶች በምሽት መንገላታታቸው፣ በሙዚቃ መሳሪያ የታጀበ "ነሺዳ"፣ የምግብ ብክነት እና መሰል ጥፋቶች የሚታከሉበት ከሆነ ደግሞ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆናል። አዎን! ፕሮግራሙ ከዚህ በፊት ሞራላዊ ጥቅምን አስገኝቶ ሊሆን ይችላል፤  ነገር ግን በውስጡ ከላይ የጠቆምነውን አመዛኝ ጉዳት ማካተቱ ለመታቀብ በቂ እንደሆነ አስባለሁ። አላህ ይበልጥ አዋቂ ነው። ረመዳን 15/1445 ____ @ustazilyas

  • 26 февр.6374иС darulhadis18

    ⚘️ የረመዳን የሙሃደራ ግብዣ ለእህቶች ⭐ ረመዳን የለውጥ ወር ⭐ ተከታታይ 2 የረመዳን እሁድ ጠዋቶችን ከኛ ጋር በማሳለፍ ኢማንሽን የምታድሺበት ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ላይ ተሳታፊ እንድትሆኝ ተጋብዘሻል! ◽የካቲት 22 እና 29/2018 ◽ከጠዋቱ 3:00-6:30 ኢብኑ መስ ዑድ እስላሚክ ሴንተር ከጦር ሃይሎች ከፍ ብሎ 18 ማዞሪያ አካባቢ ⚠️ጥሪውን ለእህቶች በማድረስ የምንዳ ተካፋይ እንሁን https://t.me/darulhadis18

  • 19 февр.7045иС darulhadis18

    🌙 ረመዳን ሙባረክ ልዩ የሙሃደራ ግብዣ ለሴቶች ⭐ የረመዳን ጾምን የተመለከቱ ድንጋጌዎች ⭐ በአላህ ማመን ⭐ ወደ አላህ ምህረት እንሽቀዳደም ✔️የካቲት 15/ 2018 ✔️ጠዋት 3:00 18 በሚገኘው ኢብኑ መስዑድ እስላሚክ ሴንተር https://t.me/darulhadis18

  • йоС пОдписи

  • йоС пОдписи

  • йоС пОдписи

  • 7 февр.7481иС nesihatv

    የነገ ቀጠሮዎ የት ነው...?       🕌 ጦር ሀይሎች ረያን መስጂድ እንገናኝ ።        ⏱ ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ #3ኛው የነሲሓ ኮንፈረስ ============================= ነሲሓ ቲቪ ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም! 📡 Ethiosat  /11545 / H / 45000

  • 2 февр.7654иС nesihatv

    ነሲሓ ኮንፈረስ 3 كُنْتُمْ خَيْرَ أُمَّةٍ " ምርጥ ህዝቦች ! " ⏱ እሁድ የካቲት 1 🕌 በረያን መስጅድ ( ጦር ሀይሎች) =============================== ነሲሓ ቲቪ ኢስላማዊ እውቀት ለሁሉም! 📡 Ethiosat  /11545 / H / 45000

  • 23 янв.824иС merkezuna

    🌙 ከፊታችን እየመጣ ያለውን የእዝነት ወር በመተዛዘን እናሳልፈው! በዚያ የመልካም ስራ ምንዳዎች እጥፍ ድርብ በሚሆንበት የረመዳን ወር ለተቸገሩ ቤተሰቦች አስቤዛ በማቅረብ እንዲያፈጥሩና እንዲመገቡ በማድረግ ለአኼራዎ ይሰንቁ! 💰 የ1 ቤተሰብ ማስፈጠሪያ ብር 6000 📌 ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ንግድ ባንክ 1000742126386 ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿وَالصَّدَقَةُ تُطْفِئُ الْخَطِيئَةَ كَمَا يُطْفِئُ الْمَاءُ النَّارَ﴾ “ሰደቃ (ምፅዋት) ወንጀልን ታጠፋለች (ታሰርዛለች) ልክ ውሃ እሳትን እንደሚያጠፋው።” ቲርሚዚ በህይወት የሌሉ ቅርብ ቤተሰቦቻችንን ሰደቃ በማውጣት እናስታውሳቸው! __ 🕌በኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር Http://telegram.me/merkezuna

  • 19 янв.9235иС darulhadis18

    📢ልዩ  ስንቅ ለታዳጊዎች የመጪው ጊዜ የኢስላም ተረካቢዎች! ⭐️ውድ ለሆኑት ትውልዶች! ለታዳጊ ተማሪዎች የተዘጋጀ  ለ 3 ቀናት የሚቆይ ድንቅ ኮርስ! ኮርሱ በአላህ ፈቃድ የሚመጥናቸውን ወሳኝና ወቅታዊ ትምህርቶች የሚያገኙበት ይሆናል።   ▫️እድሜ   ከ10- 18                  🗓 ከጥር 26- 28፣2018 🕘ጠዋት ከ3:00-6:30 1⃣ 18 ማዞሪያ የሚገኘው መርከዝ ኢብኑ መስዑድ 👇በዚህ ማስፈንጠሪያ ይመዝገቡ https://forms.gle/7cHjHhBLNc4Wxo4KA   +251904366666 2⃣ ቤተል ቅርንጫፍ 👇በዚህ ማስፈንጠሪያ ይመዝገቡ https://forms.gle/dEdoFKzh2ayncn9k9 +251929749160 ⚠️ወላጆች ልጆችዎን ወደዚህ ድንቅ ዝግጅት በመላክ የህይወት ስንቅን ያውርሱ። ✔️መልዕክቱን ሼር በማድረግ የምንዳ ተካፋይ እንሁን! https://t.me/darulhadis18

  • 30 док.9527иС abdurezaq27

    🔍የመደነቅና የመለከፍ ጥማት🔥 "Attention-seeking behavior" የሚባለው በተለይም በሴቶች ላይ ስጋዊ ማንነትን መሰረት አድርጎ ሲከሰት ከፍተኛ የሆነ መንፈሳዊ እና ስነ-ልቦናዊ ቀውስ ያስከትላል። ይህን አባዜ በተለያዩ አቅጣጫዎች ሰፋ አድርገን እንመልከተው 🎯​1. የአድናቆት ሱሰኝነት (Dopamine Loop) ​ትኩረት መፈለግ ልክ እንደ አደንዛዥ ዕፅ ሱሰኝነት ነው። አንዲት ሴት በለካፊዎች ወይም በአድናቂዎች ቃላት ስትደሰት፣ በአንጎሏ ውስጥ "ዶፓሚን" የተባለ የደስታ ሆርሞን ይረጫል። ይህ ስሜት ጊዜያዊ በመሆኑ፣ ልክ ስሜቱ ሲጠፋ ሌላ ተጨማሪ አድናቆት ትራባለች። ይህ ጥማት ደግሞ ቀስ በቀስ ድንበሮችን እንድትጥስ፣ ይበልጥ ሰውነቷን እንድትገልጥ እና ክብሯን ለገበያ እንድታቀርብ ያደርጋታል። 🎯​2. የ"እኔነት" መጥፋት እና የ"ቁስ" ማንነት መተካት ​ይህ በሽታ ያለባት ሴት ራሷን የምትመዝነው በሌሎች ሰዎች አይን ነው። የራሷ የሆነ ውስጣዊ እርካታ ስለሌላት "ዛሬ ስንት ሰው አየኝ? ስንት ሰው ተከተለኝ? ስንት ሰው አመሰገነኝ?" በሚሉ ጥያቄዎች ትወጠራለች። በዚህ ጊዜ የሰው ልጅነቷ (ሰብዕናዋ፣ እውቀቷ፣ ቅንነቷ) ዋጋ ያጣና "ስጋዊ ማንነቷ" ብቻ ትልቁ ሀብቷ እንደሆነ ታስባለች። ይህ ደግሞ እድሜ ሲገፋ ወይም ውበት ሲቀንስ ለከፍተኛ ጭንቀትና ለራስ ጥላቻ (Self-loathing) ይዳርጋል። 🎯​3. የማህበራዊ ትስስር መርከስ ​ለመለከፍና ለስጋዊ አድናቆት የምትቋምጥ ሴት፣ ወንዶችን የምታየው እንደ "አድናቂ" እንጂ እንደ "ሰው" አይደለም። በተመሳሳይ መልኩ ወንዶችም እሷን የሚያዩዋት እንደ "ዕቃ" ወይም "መዝናኛ" ነው። እንዲህ ያለ ስሜት ባለበት ቦታ እውነተኛ ፍቅር፣ መከባበርና ጥልቅ የሆነ የትዳር ግንኙነት ሊገነባ አይችልም። ምክንያቱም ግንኙነቱ የተመሰረተው በማያቋርጥ "ትኩረት ሰጪ" እና "ትኩረት ፈላጊ" ሚና ላይ ብቻ ስለሆነ ነው። 🎯​4. ከኢስላማዊ እሴትና ከ"ሀያእ" አንጻር ​ኢስላም ሴት ልጅን እንደ "መክኑን" (እንደተሸፈነ ዕንቁ) ነው የሚመለከታት። ዕንቁ ውድ የሆነው በቀላሉ ስለማይገኝና ስለሚጠበቅ ነው። አንዲት ሴት ስጋዊ ማንነቷን ለሁሉም አይን ስታጋልጥና በለካፊዎች ስትደሰት "ሀያእ" (ሀፍረት) የተባለውን ትልቅ መከላከያዋን ትጥላለች። ሀያእ ደግሞ የኢማን (የእምነት) በር ነው። ይህ በር ሲሰበር፣ የሰው ልጅ ነፍስያዋን መቆጣጠር ያቅታታል፤ በሰይጣን ውሸትም ትታለላለች። ሰይጣን "ትኩረት ማግኘት ስልጣን ነው" ብሎ ቢነግራትም፣ እውነታው ግን ራስን ማርከስ ነው። 🎯​5. የሱስ ምልክቶችና መዘዞች ​ይህ አባዜ የተጠናወታቸው ሴቶች ብዙውን ጊዜ የሚከተሉት ምልክቶች ይታዩባቸዋል፡- ​ከልክ ያለፈ ጭንቀት፦ መስታወት ፊት ለረጅም ሰዓት መቆምና በትንሽ የሰውነት ለውጥ መበሳጨት። ​ቅናት፦ ሌላ ትኩረት የሚስብ አካል ሲያዩ ከፍተኛ የሆነ የቅናትና የጥላቻ ስሜት ማሳደር። ​ባዶነት፦ ማንም ያላያት ወይም ያላደነቃት ቀን እንደ ከንቱ ቀን ተቆጥሮ በትልቅ ሐዘን መዋጥ። 🎯​6. የመውጫ መንገዱ (መፍትሄው) ​ይህን በሽታ ለማከም በመጀመሪያ ደረጃ "ዋጋዬ ያለው ከአላህ ዘንድ እንጂ ከሰዎች አይደለም" የሚለውን እምነት ማጽናት ያስፈልጋል። ➖​ራስን ማወቅ፦ የሰው ልጅ ከቆዳና ከስጋ በላይ መሆኑን፣ የመጣነውም አላህን ልናመልክ እንጂ ሰዎችን ልናዝናና አለመሆኑን መረዳት። ➖​ልብን ማከም፦ በቁርኣንና በዚክር ልብን ማረጋጋት። ልብ በአላህ ፍቅር ከረካች የሰዎችን "ላይክ" እና አድናቆት አትለምንም። ➖​አካባቢን ማጽዳት፦ ትኩረት መስጠትን እንደ ትልቅ ነገር የሚያዩ ጓደኞችንና ማህበራዊ ሚዲያዎችን መራቅ። ​በአጠቃላይ፣ ይህ አባዜ ሴትን ልጅ አቅም የሚያሳጣና በሰው ሰራሽ እስር ቤት ውስጥ የሚቆልፍባት ሰንሰለት ነው። ከዚህ ሰንሰለት መውጣት የሚቻለው ደግሞ ወደ ውስጣዊ ማንነት በመመለስና እውነተኛውን የሴትነት ክብር በመረዳት ብቻ ነው። ​ 🛫https://t.me/abdurezaq27

  • 24 окт.1 0742иС darulhadis18

    📣 የምርቃትና የዳእዋ ፕሮግራም ⭐️እሁድ ጥቅምት 23፣2018 🔘ከጠዋቱ 3:00-6:30 ⚡️ስቴድየም አካባቢ በሚገኘው ኦሮሞ ባህል ማእከል አዳራሽ ⭐️⭐️ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ዳሩል ሀዲስ ኢንስቲትዩት ⚠️ጥሪውን ተደራሽ በማድረግ የአጅር ተካፋይ ይሁኑ! @darulhadis18

  • 9 окт. 2025 Đł.1 1241иС darulhadis18

    📌 ሳምንታዊ የቅዳሜ የዲን ትምህርት ፕሮግራም ለሴቶች 📢 ታላቅ የምስራች በስራ እና በትምህርት ምክንያት በመደበኛ ቀን የዲን ትምህርት ለመማር ላልተመቻችሁ እህቶች  ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ዳሩል ሀዲስ ቤተል ቅርንጫፍ ዘወትር ቅዳሜ ከሰአት ሳምንታዊ የዲን ኮርስ ለመጀመር ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል። 👌 የተማሪዎች የቅበላ መስፈርት ▪️እድሜ ከ 12 አመት በላይ የሆነች ⏱የትምህርት ሰዐት  ከ8:00-11:00 🏢 አድራሻ ፦ ቤተል አደባባይ ንግድ ባንክ ያለበት ህንፃ 4ኛ ፎቅ ✔️ትምህርቱ የሚጀመረው በአላህ ፈቃድ የፊታችን ቅዳሜ ጥቅምት 1፣2018 ይሆናል። ☎️ ለበለጠ መረጃ፦ 👇    ▪️911062499 ▪️911692377 ⚠️መልእክቱን ሼር በማድረግ የአጅር ተካፋይ እንሁን! @darulhadis18

  • 9 окт. 2025 Đł.940иС darulhadis18

    йоС пОдписи

  • 6 сент. 2025 Đł.1 380иС darulhadis18

    💐ነገን ከእኛ ጋር!