tgindex
Truth Revolution Ministry

Truth Revolution Ministry

Статистика

ለማንኛውም ሀሳብና አስተያየት በውስጥ መስመር ያናግሩን @kirubel_christian

Последний пост
7 янв.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
24
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Instagram (по похожим)
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
7 448
−5 за 3 дн.
Сутки
−4
−0,05%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
5 520
24 постов
Вовлечённость
74,1%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 24
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 7 янв.3 7321774

    #ድንግል_አምላኳን_ወለደችው! ድንግል አምላኳን ወለደችው፤አምላክ ፍፁም ሰው ሆነ።ሰውነትን ገንዘቡ አደረገ። ከዚህ የተነሳ በማመን የሚገኘውን የእግዚአብሔር ልጅነት አገኘን።በአብ ፊት እንደ ባሪያ ሳይሆን እንደ ልጅ የመቅረብን ድፍረት አገኘን።ክብር ሁሉ ተጠቅልሎ ለባለልደቱ ይሁን። “ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።”ዮሐንስ 1፥14 ✍️kirubel 🎄መልካም በዓል ይሁንላችሁ!🎄 @Amen_Maranata   @Amen_Maranata   @Amen_Maranata ❇️Join and Share❇️

  • 26 дек.6 8801714

    ይቅርታ ማድረግ የከበዳችሁ ሰዎች ይህን ቪድዮ ግቡና ተመልከቱ https://vm.tiktok.com/ZMDFWn7NA/

  • 15 дек.4 320207

    እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቃችሁ! https://vm.tiktok.com/ZMDRP8Qck/

  • 4 дек.4 321198

    https://vm.tiktok.com/ZMAoTw1Bb/ የማይታመን እውነተኛ የፍቅር ታሪክ

  • 7 нояб.3 9308127

    አዝ፦ እኔን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ድካም ፡ ይዞኛል ድምጼንም ፡ ላሰማህ ፡ አቅቶኛል ወድቄአለሁኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንሳኝ እባክህ ፡ ሕይወቴን ፡ ለውጥልኝ 1. ቃልህን ፡ ለማንበብ ፡ ዐይኔ ፡ ታወረ ሳልጸልይ ፡ ጉልበቴ ፡ ታሰረ አንተን ፡ እንዳላስብ ፡ አዕምሮዬ ፡ ዛለ እግሬም ፡ ወደ ፡ ጥፋት ፡ ኮበለለ አዝ፦ እኔን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ድካም ፡ ይዞኛል ድምጼንም ፡ ላሰማህ ፡ አቅቶኛል ወድቄአለሁኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንሳኝ እባክህ ፡ ሕይወቴን ፡ ለውጥልኝ 2. ጠፋሁኝ ፡ ጌታ ፡ ካልደረስክልኝ ዓለም ፡ እንደ ፡ ጐርፍ ፡ እንከባለለኝ በኀጢአት ፡ ባሕር ፡ ልሰጥም ፡ ነውና ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ አዝ፦ አትጨክን ፡ ጌታ ፡ በእኔ ፡ በልጅህ አውቃለሁኝና ፡ ጉድለቴን ጌታ ፡ ሆይ ፡ አሁን ፡ ኀጢአቴን ፡ ማረኝ የምመራበትን ፡ ብርሃን ፡ ስጠኝ 3. አየሁ ፡ ጌታዬን ፡ ወዲህ ፡ ሲመጣ እኔን ፡ ከጥፋት ፡ ሊያወጣ እጁን ፡ ላከልኝ ፡ ፍፁም ፡ አዳነኝ ከእንግዲህስ ፡ ከጌታዬ ፡ ጋር ፡ ነኝ አዝ፦ ፍፁም ፡ ቸል ፡ አልልም ፡ እርሱን ፡ ስከተል እኔን ፡ ለመውሰድ ፡ ስለሚያስብ መስቀሉ ፡ ለእኔ ፡ ቢከብደኝ ፡ እንኳ ፍፁም ፡ ለመሸከም ፡ አልቦዝንም   @Amen_Maranata   @Amen_Maranata   @Amen_Maranata ❇️Join and Share❇️

  • 5 нояб.3 7924213

    “አምላካችንስ በላይ በሰማይ ነው፤ በሰማይም በምድርም የፈቀደውን ሁሉ አደረገ።”    መዝሙር 115፥3   @Amen_Maranata   @Amen_Maranata   @Amen_Maranata ❇️Join and Share❇️

  • 31 окт.4 0234953

    አምላኬ ታማኝ ነው በመንገዱ (4) በሐሩር ያሸዋ በረሃ ወይን አቆጠቆጠ ጌታ በቃሉ ያለው ተፈፀመ ቃሉ አይደክምምና በታላቁ ክንዱ ይሠራል ለበረሃው ልብህ ፍሬ ይሰጣል አዝ… የሞተው ሁሉ ሲነሣ የማይሞት አካል ለብሶ መበስበስ ላያይ ዳግም ተመልሶ በዕድሜው ያፈራውን ሰው ሁሉ ያንኑ ያቀርባለ ለጌታ የሚሆን ምን መከራ ይዘሃል አዝ… ከሥጋህ ነው ያጨድከው ወይስ ከርሱ ቅዱስ መንፈስ ለሕይወት ይሆን ወይስ ለመበስበስ መንገድህን አሁን ቀይር ፍሬህም አይቅር መና የምሕረት ጊዜ አላለቀምና አዝ… ቢመስልህ ላንተ የተነፈገህ ደሞዝህ ዛሬ ለድካምህ መኖ ለለቅሶህ ፍሬ ታገል አትፍራ በርታ ጌታ አምላክህ ይረዳሃል ለድካምህ አንድ ቀን አክሊል ይሰጣል አዝ… @Amen_Maranata   @Amen_Maranata   @Amen_Maranata ❇️Join and Share❇️

  • 24 окт.8 36018219

    #ቅዱስ_አውግስጢኖስ_በፍትወትና_በዝሙት_ተዘፍቆ_ስለ_ነበረበት_ሁናቴ_ምን_ጻፈ? *               *                * “አሁን ያለፈውን አሳፋሪ ተግባሬን እና የነፍሴን ሥጋዊ ርኩሰት ማስታወስ እፈልጋለሁ።” (2.1.1) “በዓለማዊ ነገሮች ለመርካት ተጣጥሬአለሁ እናም በተለያዩ ስኬቶች ሰክሬ በአላፊ ፍቅር መዳራትን ደፈርሁ፤ ነፍሴም አጠጠች።” (2.1.1) “በንጹሕ መውደድ እና በረከሰ ምኞት መሀል ያለውን ልዩነት ማመዛዘን እስኪሳነኝ ድረስ፣ የጨለማው የሥጋ ፍትወት እና የጉርምስና ምናባዊ የቀን ሕልም፣ ልቤን ነስቶኝ ማስተዋሌን ነጥቆኛል። የመሻት ጭጋግም ውጦኛል። ሁለቱም በውስጤ በመፍላት ግራ ያጋቡኛል። ያልተገራውንም ወጣትነቴን ወደ ጎርበጥባጣ የዝሙት ምኞቶች ስበው ይወስዱታል፤ በርኩሰት አዝቅት ውስጥም ያሰጥሙታል።” (2.2.2) “በአንተ ሕግ የተነቀፈ ቢሆንም እንኳን በአሥራ ስድስት ዓመቴ ሕይወተ-ሥጋ ፍትወት በእብደት አቅሌን ነስቶኝ ነበር።” (2.2.4) “የፍትወት እሾህ-ቁጥቋጦ ራሴን አናውዞት፣ ከውስጤ ሰንኮፉን ነቅሎ የሚጥልልኝ አንዳች ኀይል አልነበረም።” (2.3.6) “እነሆ እነዚህን መሰል ከሆኑ አጋሮቼ ጋር በባቢሎን ጎዳና ተምነሸነሽኩ! በተክፋፋ ርክሰቱም፣ በከበረ ሽቶ እና በቀረፋ መዓዛ በታጠነ አልጋ እንደሚንፈላሰስ ተንከባለልኩበት።” (2.3.8 ) “ማፍቀርና መፈቀር ያስደስተኝ ነበር፤ ከምንም በላይ ግን ባፈቀርሁት ሰው ሰውነት መደሰት ከቻልሁማ አቤት እንደዚያ የሚያስደስተኝ ነገር የለም ነበር። በዚህ መልክ የወዳጅነትን ንጹሕ ምንጭ በሚከረፋ ፍትወት እበክለዋለሁ፤ ጸዳሉንም በፍትወት ጽልመት አጨልመዋለሁ።” (3.1.1) “ማስተዋል ወደ ጎደላት፣ አሳብ የለሽና አላዋቂ ወደሆነችው በቤት ደጃፍ ተቀምጣ የሰለሞንን እንቆቆልሽ ወደምታጣቅስ ‘የስርቆት ውሃ ይጣፍጣል፤ የተሸሸገም እንጀራ ደስ ያሰኛል’ ወደምትለው ሴት ፈቀቅ አልሁ። ይህች ሴት አማለለችኝ፤ ምክንያቱም በሥጋዬ ሕዋሳቶች ዘንድ ተቀምጣ በእነዚህም አካላዊ ህውስታዎች በኩል የዋጠቸውን ምግብ ስታመነዥግ ነፍሴ ከደጃፍ አግኝታታለችና።” (3.6.11) “እንግዲህ ከአሥራ ዘጠኝ እስከ ሃያ ስምንት ዓመቴ ድረስ በእነዚህ ዘጠኝ ዐመታት ጊዜ ውስጥና እኔም ራሴ ማልዬ፣ ሌሎችንም አማልዬ ነበር። ተታልዬ በብዙ ፍትወቶችም ሌሎችን ሳታልልም ነበር።” (4.1.1) “በሴት ካልታቀፍሁ ራሴን የተጎሳቆልሁ አድርጌ አስብ ነበር።” (6.11.20) "በፍጥነት ትዳር ልንይዝ አልፈለግንም። ነገር ግን እኔ ተሠቃየሁበት። አንደኛውን ባሪያው አድርጎኝ ስለ ነበር በማይገራ ፍትወት ራሴን የማርካት ልማድ ነበረኝ።" (6.12.22) "እኔ ግን ኀጢአት እየባሰብኝ እየባሰብኝ ይሄድ ነበር። አብራኝ ትኖር የነበረችው ወዳጄ ለጋብቻዬ ዕንቅፋት እንዳትሆን ከእኔ ተለየች። እርሷን ያለው ልቤ ግን ተቀጣ፤ እስኪደማም ድረስ ቆሰለ። እርሷም የወለደችልኝን ልጅ ጥላልኝ፣ ዳግም ሌላ ወንድ ላታውቅ ላንተ ምላ ወደ አፍሪካ ተመለሰች። ... ጋብቻም አፍቃሪ ሳልሆን የፍትወት ባሪያ እንደ መሆኔ . . . ሌላ አገኘሁ፤ ሚስት ባትሆንም ሌላ የሴት ወዳጅ። (6.15.25) “ንጽሕናን፣ ራስንም መግዛት ስጠኝ፤ ግን አሁን አይደለም።” (8.7.17) *               *                * (ጥቅሶቹን የወሰድሁት በዘካርያስ ደበበ ከተተረጎመው የአውግስጢኖስ ኑዛዜ መጽሐፍ ነው።) #ጸሀፊ_ጳውሎስ_ፈቃዱ @Amen_Maranata   @Amen_Maranata   @Amen_Maranata ❇️Join and Share❇️

  • #ልዩ_የውይይትና_የምክክር_ጊዜ ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር ከነገ ወዲያ ቅዳሜ ቀን በአያት መሰረተክርስቶስ ቤ/ክ ከ 10:00 ጀምሮ "የማህበራዊ ድህረገጽ(social media) አዎንታዊና አሉታዊ ተፅዕኖ በወጣቶች ህይወት" በሚል ርዕሰ የውይይትና የምክክር ጊዜ ስለሚኖረን የምትችሉ ሁሉ እንድትገኙ ይሁን።ተባረኩ አድራሻ:ከአያት ወደ ጣፎ በሚወስደው መንገድ ምዕራፍ አካዳሚ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ +251977535185

  • ይህን ፀሎት ከመተኛታችሁ በፊት ስሙት “ቸር ነውና፥ ምህረቱም ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ።” 1 ዜና 16፥34

  • 14 июн. 2025 г.11,7 тыс43426

    “እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።” መዝሙር 27፥4 እግዚአብሔር እስከመጨረሻው በቤቱ ያፅናቹ!

  • አንተ የምህረት አምላክ በሰላም እንዳዋልከን እንዲሁ በሰላም አሳድረን! ምሽታችሁ የተባረከ ይሁን

  • ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ህይወት ነው!

  • እግዚአብሔር ይመስገን!

  • ኢየሱስ ከሙታን ካልተነሳ፦ 1⃣ ስብከታችን ዋጋ ቢስ ነው 2⃣ እምነታችን ከንቱ ነው 3⃣ እስከ አሁን በኃጢአታችን አለን 4⃣ በክርስቶስ ያንቀላፉ ጠፍተዋል 5⃣ ከሰው ሁሉ ይልቅ ከንቱ ነን አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል።" 1ኛ ቆሮ 15፥20 እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ! መልካም በዓል! @Amen_Maranata   @Amen_Maranata   @Amen_Maranata ❇️Join and Share❇️

  • без подписи

  • እግዚአብሔር ፍቅር ነው! ፍቅሩ አይቀዘቅዝ ወረት አያውቀው እንደ ጌታ ያለ የትም አይገኝም የተናገረውን ቃሉን ይፈፅማል ተናግሮ ማድረግን እርሱ ብቻ ያውቃል @Amen_Maranata   @Amen_Maranata   @Amen_Maranata ❇️Join and Share❇️

  • እግዚአብሔር የምህረት አምላክ ነው!

  • በመንፈሳዊ ህይወቴ ደክሜያለው ምን ላድርግ? #ከሙሉ_ትምህርት_ተቆርጦ_የተወሰደ አታውቅምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፣የምድር ዳርቻ ፈጣሪ ነው።አይደክምም፤ አይታክትም፤ ማስተዋሉም በማንም አይመረመርም።ለደከመው ብርታት ይሰጣል፤ለዛለው ጒልበት ይጨምራል።ኢሳ 40:28-29 @Amen_Maranata   @Amen_Maranata   @Amen_Maranata ❇️Join and Share❇️

  • #የጴንጤቆስጤአዊነት_ችግር! በዘመናችን Pentecostal እንቅስቃሴ የሚመሩ አብያተክርስቲያናት ችግራቸው እንቅስቅሴው ራሱ ሳይሆን እንቅስቃሴውን ከዶክትሪን ማስቀደማቸው ይመስለኛል። ማንኛውም ልምምድ ከመሰረታዊ አስተምህሮዎች ሊቀድም አይገባውም፤ ዶክትሪን ችላ ከተባለ ልምምዶች የሐሰተኞች መደበቂያ እየሆነና ኢየሱስን እየገፋ ይሄዳል። ስለዚህ እኛ ጴንጤዎች ቢያንስ ወደ  ፕሮቴስታንቲዝም Essential doctrines ማተኮርና የጣልነውን በማንሳት Reform ማድረግ ይኖርብናል! ✍ ቃለአብ @Amen_Maranata   @Amen_Maranata   @Amen_Maranata ❇️Join and Share❇️