tgindex
Christian tweet

Christian tweet

Статистика
@christians_Tweetанглийский

በዚህ ቻናል በየቀኑ ለ ➜ #Profile_picture ➜ #Instagram_story ➜ #Facebook ➜ #Telegram_story የሚሆኑ #መንፈሳዊ_ጥቅሶች በዚህ ቻናል ያገኛሉ Buy ads: https://telega.io/c/Christians_tweet ⒸSince 5-11-2015

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
12 780
+34 за 4 дн.
Сутки
−11
−0,09%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 393
21 постов
Вовлечённость
10,9%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всего 21
Упоминаний
17
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
68
1/48двое суток
77
1/72трое суток
84

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 📲በቀላሉ በስልካችን የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን በማንኛውም ሰዓት የሚያደርሱን 💁🏻‍♀የቴሌግራም ቻናሎችን ልጦቁማቹ የምትፈልጉትን አገልግሎት መርጣቹ ተቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇

  • 11 авг.4 900удалён 14 авг.

    🌧በዚህ ክረምት መንፈሳዊ ህይወታችንን የሚያሳድጉ ዝግጅቶች። የፈለጋቹትን መርጣቹ ተቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇

  • ለተቀበሉትና በስሙ ላመኑት ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን መብት ሰጣቸው። እነዚህም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ፣ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም። ዮሐንስ 1:12-13 የምንኖረው የግለ ሰብ መብቶችን ሰዎች አክርረው በሚይዙበት ዘመን እና ባህል ውስጥ ነው "____ መብቴ ነው።" ባዶውን ቦታ ሙሉት። ነገር ግን ማናችንም ብንሆን በራሳችን ብቃት ወይንም ደረጃ የእግዚአብሔር ልጅ የመሆን መብት የለንም። ይህንን መብት የሰጠን የእግዚአብሔር ጸጋ ነው። ይህ መብት ደግሞ ወደ እኛ የመጣው እግዚአብሔርን ትልቅ ዋጋ አስከፍሎ ነው። ኢየሱስ ወደ ምድር መጣ፣ ኖረ፣ ሞተ ከሙታንም ተነሣ። ይህንን ጸጋ ደግሞ በእምነት በኩል ተቀበልን(ኤፌሶን 2፥8-10)። ኢየሱስን እንደ ጌታችን አድርገን ስንቀበለውና ስናምነው እግዚአብሔር ዳግም ውልደትን ይሰጠናል (ሮሜ 10፥9-10)። በመንፈስ ቅዱስ ኀይል የእግዚአብሔር ልጆች ሆነን ዳግም ተወልደናል(ዮሐንስ 3፥3-7፤ ገላትያ 3፥26-29፤ ቲቶ 3፥3-7)። ከእግዚአብሔር መወለድ፣ ከላይ መወለድ፣ "ዳግም" መወለድ (ዮሐንስ 3፥3-7) ማለት ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አብረን ወራሾች ሆነን ወደ እግዚአብሔር ቤተ ሰብ ተቀላቅለናል ማለት ነው (ሮሜ 8፥14-17፤ ገላትያ 4፥1-7)። @Christians_Tweet @Christians_Tweet

  • አላምናቸው ወዳጆቼን ጓደኛዎች ዘመዶቼን ያጋልጡኛል ጠብቀው አይችሉትም ጉዴን ተሸክመው....ወረት አያውቀው ጌታዬ ዘላለም ሚስጥረኛዬ የልቤን አጫውተዋለው ገመናዬን አሳየዋለሁ😊

  • ከድስት በታች እንደሚቃጠል እሾህ ድምፅ የሰነፍ ሳቅ እንዲሁ ነው፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው። መክብብ 7:6 @Christians_Tweet @Christians_Tweet

  • አረጋዊውን ሰው እንደ አባትህ ቈጥረህ ምከረው እንጂ በኀይለ ቃል አትናገረው። ወጣት ወንዶችን እንደ ወንድሞች ተቀበላቸው 1 ጢሞቴዎስ 5:1 ከወጣትነት ጋር ጉጉት፣ ለነገሮች ጠንካራ ፍላጎትና ግልጽ የሆነ ዐላማ አብረው ይሄዳሉ። ወጣትነትን አንዳንድ ዕድሜያቸው ከፍ ያሉ ሰዎች ጠንካራ እና ለነገሮች ምላሽ ለመስጠት ችኩል የሚኮንበት ጊዜ እንደ ሆነ ይናገራሉ። እነዚህ ደግሞ በጊዜ ውስጥ ይፈተናሉ። ወጣቶች ደግሞ በእድሜ የገፉትን ሰዎች ጊዜው ያለፈባቸው፣ ተገማች የሆነ ሕይወት ያላቸውና የማይንቀሳቀሱ እንደ ሆኑ ይገልጻሉ። ይህ በመካከላቸው ያለው ልዩነት ውጥረትና ግጭትን ቢፈጥርም አንዳቸው ከሌላኛቸው የሚማሩት ነገር አለ። በዕድሜ የገፉ ክርስቲያኖች ምንም ያኽል ቢሳሳቱ በእምነት የተፈተነ ሕይወት ስላላቸው በአክብሮት ልንቀርባቸው ይገባል። ነገር ግን በእድሜ የገፉ ክርስቲያኖች ከወጣቶች በተለይም ለታላላቆቹ ፍቅር እና አክብሮት ካለው ወጣት በጸሎትና በትሕትና የመጣን እርማትን ለመቀበል ፈቃደኞች መሆን አለባቸው። ከሁሉም በላይ በምንም የዕድሜ ክልል ውስጥ ብንሆን ለኢየሱስ ለመኖር እርስ በርስ ልንረዳዳ ይገባል። @Christians_Tweet @Christians_Tweet

  • 4 июл.1 108152

    ክርስቶስ ነጻ ያወጣን በነጻነት እንድንኖር ነው። ስለዚህ ጸንታችሁ ቁሙ፤ ዳግመኛም በባርነት ቀንበር አትጠመዱ። ገላትያ 5:1 ነፃ ወጥተናል! ኢየሱስ ክርስቶስ በጸጋና በእርሱ ላይ ባለን እምነት በኩል ከሕግ፣ ከኀጢአትና ከሞት ነፃ አውጥቶናል(ሮሜ 8፥1-4)። ሕጉን በመጠበቅ ለመጽደቅ ከመሞከር ነፃ ወጥተናል። አሁን እግዚአብሔርን የምናገለግለው ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ድነትን በላያችን ላይ ስላፈሰሰልንና ለእርሱ ጸጋ ካለን ምሥጋና የተነሣ ነው(ቲቶ 3፥3-7)። ስለዚህ ይህንን ነፃነት እንዴት መጠቀም እንችላለን? ለኀጢአት ወይም ሕግን ለመጠበቅ "ዳግመኛ በባርነት ቀንበር" ለመጠመድ መፍቀድ የለብንም! ይልቁንም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ተለውጠን ይበልጥ ክርስቶስን እንምሰል(2 ቆሮንቶስ 3፥18፣ ገላቲያ 5፥22-25)። "በሥጋ ሳይሆን በመንፈስ ስንመላለስ" "ሕጉ የሚጠይቀውን ጽድቅ" እናሟላለን (ሮሜ 8፥4)። @Christians_Tweet @Christians_Tweet

  • 18 июн.1 378253

    እግዚአብሔር ሆይ፤ የሰው ሕይወት በራሱ እጅ እንዳልሆነች፣ አካሄዱንም በራሱ አቃንቶ ሊመራ እንደማይችል ዐውቃለሁ። ኤርምያስ 10:23 ምንም እንኳ ልናሳካቸው የምንፈልጋቸው ግቦች እና ተልዕኮዎች ቢኖሩንም የወደፊት ሕይወታችንን ግን መወሰን ለእኛ አልተሰጠም። ማቀድ እንችላለን። ነገር ግን ይህንን የምናደርገው ጌታን ለማክበርና በእኛ ያለውን ዐላማ ለመፈጸም እንደ ሆነ መገንዘብ አለብን። እናቅዳለን፣ ነገር ግን የምንኖረው በእግዚአብሔር ፈቃድ ሥር ነው። @Christians_Tweet @Christians_Tweet

  • 29 мая1 965183

    አሮን ወደ መቅደሱ በሚገባበት ጊዜ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ለዘላለም መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የእስራኤልን ልጆች ስሞች በፍርድ መስጫው ደረት ኪስ በልቡ ላይ ይሸከም ዘፀአት 28:29 ተምሳሌታዊ በሆነ መልኩ፣ ሊቀ ካህናቱ ወደ መቅደሱ ሲገባ ሁሉንም እስራኤላውያን "በልቡ ላይ" ተሸክሞ ነበር። ታላቁ ካህን ኢየሱስ ወደ መስቀል የሄደው፣ ኀጢአታችንን በጀርባው ተሸክሞና ይቅርታችንን ደግሞ በልቡ ይዞ ነበር! ኢየሱስ እግዚአብሔር ለዓለም ያዘጋጀው አዳኝ ነው። እኛንም ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርበን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መሥዋዕትን ያቀረበ ካህናችን ነው(ዕብራዊያን 7፥23-27፣ 9፥24-28፣ 10፥8-10)። . @Christians_Tweet @Christians_Tweet

  • 24 мая1 67919

    ፍትሕን በታማኝነት(የእግዚአብሔር አገልጋይ) ያመጣል። ፍትሕን በምድር እስኪያመጣ ድረስ፣ አይደክምም፤ ተስፋም አይቈርጥም፤ ደሴቶች በሕጉ ይታመናሉ።” ኢሳይያስ 42:3-4 እግዚአብሔር አይወድቅም! በፍቅር ላይ የተመሠረተ ፍትሕ በምድር ላይ ኢምንት በሆነ መልኩ ቢኖርም ሰማያዊ ፍትሕ ግን በመጨረሻ እንደሚነግሥ እግዚአብሔር ብቸኛና ፍጹም ማረጋገጫችን ነው። ይህ የምድር እና የሕዝብ ሁሉ ተስፋ ደግሞ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው። ዳግም ሊመለስና የእግዚአብሔርን እውነትና ፍቅርን መሠረት ያደርገ ፍትሕን ይዞልን ሊመጣ ተስፋ ሰጥቶናል፣ ማራናታ(1ቆሮንቶስ 16፥22) ጌታ ሆይ ና! @christians_Tweet @christians_Tweet

  • 5 мая2 089221

    በእኔ ላይ የፈጸማችሁትን በደል ሁሉ ወደ ኋላ ጣሉት፤ አዲስ ልብና አዲስ መንፈስ ይኑራችሁ... ወደ እኔ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ! ሕዝቅኤል 18:31-32 እግዚአብሔር ከራሳችን መንገድ በንሰሓ እንድንመለስ ያዘናል። ወደ እርሱ እንድንመለስና ፈቃዱን ለመከተል እንድንሻ ይለምናል። ይህንን ካልተቀበልን ግን እየሄድንበት ያለው መንገድ መዳረሻው ሞት እንደ ሆነ እንወቅ። እግዚአብሔር ዳግም ሊወልደንና ሊያድሰን ይፈልጋል። ነገር ግን ከጥፋት መንገዳችን ተመልሰን በመንፈስ ቅዱስ አዲስ እንሆን ዘንድ ልባችንን አሳልፈን እንድንሰጠው ይፈልጋል። ንሰሓ ማለት ወደ ጥፋት የሚመራውን መንገድ መተውና ሕይወት፣ ደስታና ድነት ወዳለበት ወደ አብ ቤት የሚመራውን መንገድ መምረጥ ነው። @christians_Tweet @christians_Tweet

  • 30 апр.1 713251

    አምላኬም እንደ ታላቅ ባለጠግነቱ መጠን የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ይሞላባችኋል። ፊልጵስዩስ 4:19 ጳውሎስ ይህንን ተስፋ ለፊልጵስዩስ የሰጣቸው በጥሩና መጥፎ፣ በማግኘትና በማጣት ጊዜያት ውስጥ የጌታን ጸጋ እንዳገኘ አጽንኦት ሰጥቶ ከነገራቸው በኋላ ነው። ለዚህ ተስፋ ቁልፉ ነገር የእግዚአብሔር መግቦትና በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል የሚያስፈልገንን እንደሚሞላን በእርሱ መታመን ነው። በጌታ ለመሞላት፣ እርሱን ለማስደሰት፣ በመገኘቱ ለመባረክና ከሞት በኋላ ስላለው ሕይወት መተማመኛን ከእርሱ ለመቀበል ልባችን አጥብቆ ሲፈልግ ያኔ ለሚያስፈልገን ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር አቅርቦት ላይ መደገፍ እንችላለን። @christians_Tweet @christians_Tweet

  • 27 апр.1 777285

    አንተ ግን መከራንና ሐዘንን ታያለህ፤ በእጅህም ዋጋ ለመክፈል ትመለከታለህ፤ ምስኪኑም ራሱን በአንተ ላይ ይጥላል፤ ለድኻ አደግም ረዳቱ አንተ ነህ። መዝሙር 10:14 እግዚአብሔር እስራኤላውያንን በግብፅ እያሉ መከራቸውን አይቶና ጩኸታቸውን ሰምቶ ሊረዳቸው እንደ ወረደ፣ ዛሬም ጩኸታችንን ያያል ይሰማል። አሁን ደግሞ እግዚአብሔር የሚሰማን ሁሉን ቻይ ስለ ሆነ ብቻ ሳይሆን ልጁ ኢየሱስ በቀኙ ተቀምጦ ስለሚማልድልን ነው። እኛ የነበርንበት ቦታ ኢየሱስ ነበር። የሞትን ሽታ፣ ስቃይን እንግልትንና መዋረድን ያውቃል። በአብ ፊት የኢየሱስ መገኘት እግዚአብሔር ጩኸታችንን ይሰማል ማለት ብቻ ሳይሆን ህመማችንን እንደሚረዳ ያሳያል። ኢየሱስ የመጣውም ለዚህ ነበር። እግዚአብሔር እንደሚረዳን፣ እንደሚጠነቀቅልንና በመጨረሻም እንደሚያድነን ኢየሱስ ማረጋገጫችን ነው። አምላካችን በችግርና በሐዘን ውስጥ ስንሆን ያያል፣ አቅመ ደካሞችን እርሱ ይረዳል። @christians_Tweet @christians_Tweet

  • 19 апр.1 64320

    የሚጠፋው የማይጠፋውን፣ የሚሞተውም የማይሞተውን በሚለብስበት ጊዜ፣ “ሞት በድል ተዋጠ” ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል። 1 ቆሮንቶስ 15:54 እንደ ክርስቲያኖች ሰውነታችን ቢሞትም እኛ ግን አንሞትም! ሥጋዊ ሞት ማለት የማይበሰብሰውን ሰውነት መልበስ ማለት ነው። ኢየሱስ ከሞት አስነሥቶ የማይበሰብሰውን ያለብሰናል። የእግዚአብሔር ልጆች ስለሆንን ሞት በእኛ ላይ ሥልጣን የለውም። ድል የእኛ ነው። የመጨረሻው ሥልጣናዊ ቃል ያለው ሞት ሳይሆን ኢየሱስ ነው፤ "ተነሣ!" ይለዋል። @christians_Tweet @christians_Tweet

  • 13 апр.1 949227

    ሰው እንደ እስትንፋስ ነው፤ ዘመኑም ፈጥኖ እንደሚያልፍ ጥላ ነው። መዝሙር 144:4 ጊዜ እጅግ ውድ ነው። ከቤተ ሰብ ጋር፣ ከልጆች ጋር፣ ከጓደኞች ጋር፣ በክርስቶስ ካገኘናቸው ወንድሞች እና እኅቶች ጋር የምናሳልፈው ጊዜ እጅግ ውድ ነው። ጊዜያችሁን እንዴት እየተጠቀማችሁ ነው? የምታጠፉትስ በምንድን ነው? ጊዜያችን ከምናጠፋው ገንዘብ ይልቅ ውድ እንደ ሆነ ታውቃላችሁ? የአሁኑ ጊዜ እና ይዞ የሚመጣቸው ዕድሎች ካለፉ በኋላ እንደ ገና ማግኘት አይቻልም። ስለዚህ እያንዳንዱን ቀን ስትጀምሩ "ጊዜን መረዳት" እንድትችሉና ለበለጠው መልካም ነገር ማዋል ትችሉ ዘንድ እግዚአብሔርን ጠይቁ። ጊዜ ፈጥኖ ያልፋል፣ እንደ ምሽት ጥላ ነው፤ ብዙም ሳይቆይ በሌሊቱ ጨለማ ይዋጣል። @christians_Tweet @christians_Tweet

  • 11 апр.1 633433

    ብወድህ ታድያ ምን ይገርማል?

  • 28 мар.1 926286

    ‎ያለ ምስክር ያለ ማስረጃ እንዳመነህ እንደ አብርሃም ‎የኔም ልብ ባንተ ላይ እንደዚያው ፀንቷል ‎ ይልቁንም በእምነቱ በመጽናት ለእግዚአብሔር ክብርን ሰጠ እንጂ፣ የእግዚአብሔርን ተስፋ አልተጠራጠረም፤ ሮሜ 4፥20 @christians_Tweet @christians_Tweet

  • 28 мар.1 876205

    አንድ እግዚአብሔር አለና፤ ደግሞም በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል አንድ አስታራቂ አለ፤ እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ ራሱንም ለሰዎች ሁሉ ቤዛ አድርጎ ሰጠ፤ ይህም በትክክለኛው ጊዜ ተመስክሮለታል። 1 ጢሞቴዎስ 2:5-6 ምንም ያኽል ኀያል፣ የተለየ ሰው ቢሆን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ የሚማልድ ሌላ ሰው አያስፈልገንም። እንደ ልጆቹ በነጻነት ወደ እርሱ መቅረብ እንችላለን። ምክንያቱም እግዚአብሔር ራሱ በእኛ እና በእርሱ መሐል ፍጹም አስታራቂን አኑሯል። ይህ አስታራቂ ብቻውን ስለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት ሊቀ ካህናት ሆኖ የሚቀርብና የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው። ስሙም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ ጌታችን፣ አዳኛችን እና ወንድማችን ነው። @christians_Tweet @christians_Tweet

  • 28 мар.1 414234

    ኦሪት ዘዳግም 33:26-29 (AMH) •••••••••• ²⁶ ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥  በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ  እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም። ²⁷ መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው፥  የዘላለምም ክንዶች ከአንተ በታች ናቸው፤  ጠላትህን ከፊትህ አውጥቶ።  አጥፋው ይላል። ²⁸ እስራኤልም ተማምኖ፥  የያዕቆብም ምንጭ ብቻውን፥  እህልና የወይን ጠጅ ባለባት ምድር ይኖራል፤  ሰማያቱም ጠልን ያንጠባጥባሉ። ²⁹ እስራኤል ሆይ፥ ምስጉን ነህ፤  በእግዚአብሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን ነው?  እርሱ የረድኤትህ ጋሻ፥  የከፍተኛነትህም ሰይፍ ነው።  ጠላቶችህም ይገዙልሃል፤  አንተም ከፍታቸውን ትረግጣለህ። @christians_Tweet @christians_Tweet

  • 25 мар.1 40329

    አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ!