tgindex
ሜርሲ እና ብዕሯ✍

ሜርሲ እና ብዕሯ✍

Статистика

ለ ሀሳብ አስተያየት t.me/mercy_bbot @Mercyasta

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
13
Всего постов
28
Тип
открытый
Язык
nn
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
19 930
+20 за 4 дн.
Сутки
−8
−0,04%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
347
27 постов
Вовлечённость
1,7%
к подписчикам
Постов в день
1,9
всего 28
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
283
1/48двое суток
324
1/72трое суток
349

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • без подписи

  • ቤተ ክርስቶስ ክፍል#17 "አንቺው ..እስከዛሬ ስንቱን ስትነግሪኝ ሂን ማትነግሪኝ ስምረቴ" ስምረት ምንም ሳትል ዝም ብላ ታያታለች::እጅጉን መገረም የያዛት ወሮ አለም አፏን ይዛ አሰብ ካረገች ቡሃላ "ስምረቴ.." "ወይ እናን..?" "በጣም የሚያሳዝን ልጅ ነው አይደል..?ተዝያ ላይ በጣም ጥሩ ልጅ ነው" አንገቷን በአዎንታ ነቀነቀችላት:: "ታይ ቢመጣ እንደቤተሰብ ማንቀበለው.." "እናና..!" "ስምረቴ..እውነቱን ንገሪኝ ከኸይ ልጅ ጋር ምንም የላችሁም አይ..?" "አይ..የለንም" "ታይ ምን ገዶን ቢመጣ.!ከናቱ ናፍቆት ሽሽትም አይ..? ጓደኛሽ ከሆን አንቺን መሸሻው ማድረጉም አይደል..ተይ ላይ ስንት ነገር አርጎልሽ የኔም ባለወለታዬ ነውይ.." "አቤይ ምን ይላል..?" ... "መውደድ..ይሄኮ ገጠር ነው የኛም ቤት አንተ እንደለመድከው አይነት ቤት አይደለም" "ገጠር ሄጄ ማላውቅ ነው ሚመስልሽ..?" "ኡፍፍ"በረጅሙ ተንፍሳ?"እሺ እንዴት አርገህ ነው ምትመጣው.." "እሺ አልሽኝ ማለት ነው!"የደስታ ድምፅ:: "ለኪዳን ነግሬዋለሁኝ ተሱ ጋር አብሮ ይመጡና ጓደኛው እንደሆን ለአባትሽ እንነግረውዋለን ከዝያ ተዛው እነሱው ጋር ይቆያል"አለች ወ/ሮ አለም:: ... "አይ ኪዳኔ..አንተው ጠፍጠተህ አንተን ራስህኑ ስንል ጥቁር እንግዳ ይዘህ መጣህ አይደል...በሉ ያዙ እየበላችሁ"አቶ ይደርሳል ከፊታቸው ያለውን እንጀራ አንስቶ ወደነሱ አያረገ:: "ነይ ስምረቴ ጠላውን ጨምሪላቸው" "አይ..ጋሼ እኔ አልጠጣም እያወቁ..ባይሆን ለመውደድ ቅጂለት" "ወገኛ..! በይ ነይ እሺ ለእንግዳው ስጪው ለሱ ደሞ እርጎ ስጭ" "እና ምን ያህል ይቆያል ትምህርታችሁ..?" "አንድ ሳምንት..አንድ ሳምንት ቡሃላ ይጀምራል ጋሼ"መውደድ መለሰ:: "ደግ እንግድያ...ኪዳኔ እናትህ እስክትመጣ ስምረቴና አለሜ አሉ እሺ ከባዶ ቤት ይልቅ እንግዳውን ኸኛ ጋር ይዘከው መምጣትህ ጥሩ አርገሃል" ኪዳን ግራ ገብቶት ስምረትን ቀና ብሎ አያት:: አክስቷ ለፀበል ሂዳ ማንም ባለመኖሩ ኪዳን እነሱ ቤት ከጓደኛው ጋር እንደመጣ ለአቶ ይደርሳል ቢነግሩትም ግን ከኪዳን ጋር ሙሉ ዝርዝር ነገሩን አላወሩበትም ነበር:: ስምረት በአንገቷ ንቅናቄ አዎ እንዲል ነገረችው::እንዲሁ በአይን መግባባቱን ለምደውታል:: "አ..አው እሺ ጋሼ ችግር የለውም" ሲያየው ከተሜነቱ ያስታወቀው አቶ ይደርሳል ኪዳንን ለብቻው ጠርተውት ራቅ ብሎ ወዳለው ሰፍር ካለች ለስራ ብለው ሰርተዋልት ከነበረችው አነስተኛ ቤት እንዲወስደው ነገረው:: ኪዳን ግን እነሱ ቤት መቆየት እንደሚሉ አሳምነው:: "ስምረት ምንድነው ያልሽው ቆይ..?ለምን አልነገርሽኝም?"ኪዳን ብቻቸውን ሲሆኑ ጠብቆ:: "ያዩ ለፀበል ስለሄደች ቤትም ማንም እንደሌለና ከብቶቹን እሚጠብቅ ስለሌለ ላንድ ሳምንት ልታይ እንደመጣህ ነው አቤይ ሚያውቀው" "ምን..? ያወቀ እንደሆነስ..? ደሞ እኔ ገና መምጣቴኮ ነው እረፍቱ በሁለት ሳምንቱ አያልቅም ቆይ ለምንድነው..?" "ኪዳኔ ረጅም ታሪክ ነው ሌላ ቀን ነግርሃለው" "ቆይ እቴቴ ይሄን ሁሉ ታውቃለች..? ብዙ ምናወራው ነገር አለ ሰም ቆይ ብቻ..!"እንደ መዛት ብሎ እየሳቀ:: "ስማ ታልቅህ እንደሆንኩ አትርሳ..!" "በዘጠኝ ወር?በይ ይሁንልሽ ግን.." "ኪዳን..!" "እቴቴን ምን ብለሽ እንዳሳመንሻት አላውቅም ግን እኔ አይቻቹዋለው!" "ምንድነው ምትለው ሰው ቢሰማህ ሌላ ነገር ነው ሚመስለው" "እሺ እሺ እንደውም ግልጽ ሆነልኝ በቃ..ግን ከኔ መደበቅ አይጠበቅብሽም ነገ ቤት ይዤው ሄዳለው" እንደማፈር ብላ "ሂድ ከዚህ!"አለች::ኪዳን ከማንም በላይ ታውቀዋለች ያውቃታል:: "አለናፈኩሽም ግን ሰም?" "እናትህ እንዴት ሆነች?" "ክትትል ጀምረውላታል ለቀዶ ጥገናው ትክክለኛ ጊዜ እየጠበቁ ነው ግን ጥያቄዬን መልሺልኝ" "አይ ጥሩ ነው..ከያሲን ጋር ትደውላላችሁ አይደል?" "አው ደና ነው ኃይሌም ጋሼም ደና ናቸው ሌላ ምጠይቂኝ ሰው አለ?" በንግግሩ ፈገግ አለችና "አንተስ?" "ናፍቀሽኛል..በጣም!" ፀጥታ መሃላቸው ሰፈረ:: "የምር ግን ከጠየቅሽኝ..ነፋስ አየር ላይ እንዳቆመው፤መሬትም እንዳልያዘ ተንሳፋፊ፤ ልክ ከሆነ ከፍታ ላይ ስትዘይ መሬት እስክትደርሽበት ባለው አፍታ መሃል የሚሰማሽ ስሜት አለ አይደል..ትንፋሽሽን ሰቅዘሽ ምትይዢበት..ነብስሽ ጥላሽ እየወጣች እያለች ያህል ልብሽን ስልብ የሚያደርግ የአየር ላይ ያለ ስሜት..ልክ እንደዛ..ምንም የምቆምበት ጥግ አጥቼ ትንፋሼን ሰብስቤው አንዱ ጋር እስክደርስ እየጠበኩ ነበር::ሁሉም ጥግ ግን የራቀ ሲመስለኝ በአሁኑ ሰዓት በሕይወቴ አንድ የሚጨበት ነገርና ማርፍበት ትንፋሽ ምወስድበት ቦታ ስለፈልኩ ነው አንቺ ጋር መምጣቴ ስምረት" ምትለው ጠፍቷ ት በዝምታ ተመለከተችው አይኑ ውስጥ የሚለው ነገር ይታይ ነበር:: "ሌላ መሄጃ ስላጣው እንጂ ልክ አለመሆኑ ጠፍቶኝ ወይም ላስጨንቅሽ ብዬ አልነበረም ግን ስለ ተቀበልሽኝ አመስግናለሁ ቤተሰቦችሽ በጣም መልካም ሰዎች ናቸው" "አልተቸገርኩም እኮ መውደድ..ደሞ እንደ ቤተሰብህ ልታየው ትችላለህ ወዳጆች አይደለን ደሞ ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል እሺ ጌታ አለ እንፀልያለን" "አመሰግናለሁ"ይሄ ማለት ለሱ ምን ያህል እንደሆነ እንዴት አድርጎ ቢያሳያት እንደሚችል አያውቅም ግን አጠገቡ መሆኗ ብቻ የሰጠውን እፎይታና ልቡ ላይ የፈጠረው የመደላደል ስሜት በቃል ሚገልጠው አልነበረም:: "እሺ ቀጥሎ ምንድነው ምናደርገው?" "ምን ታደርጋለህ...በሌሊት ተነስታችሁ ከኪዳኔ ጋር ከብቶቹን ይዛችሁ ትወጣላችሁ" "ምን..?" በ ድንጋጤ በሁኔታው ከት ብላ እየሳቀችበት ጥላው ሄደች::ፈገግታዋን ተከትሎ ሳቀ:: በጥዋት ተንስቶ ከኪዳን ጋር ከበቶችን ይዘው ግጦሽ ይወጣል ስምረት ምሳ ታቀብላቸዋለች እንዲ እያሉ ቀጠሉ::አይምሮውን ሚያሳርፍበት ስለነበር የፈለገው ዘወር ማለቱና አዲስ ነገር ማድረጉን ወዶታል በዛ ላይ ስምረትን በየቀኑ ማየት ከምንም በላይ ሚፈለገው ነገር ነበር ልቡ የታደሰ ይመስለዋል:: "አንተ ትናንት አቤን ለማገዝ ብላችሁ ከሱ ጋር እርሻ እንደዋላችሁ ነገረኝ" "አው..በዛ ላይ አባትሽ በጣም ወደውኛል አሁን እሳቸውን በጎን ጠይቄ ሁላ ሊድሩልኝ ይችላሉ" "ቀልደኛ..ትምህርቷን ብሎ ከስንቱ ደብቆ እንደ አይኑ ብሌን የጠበቃትን ልጁን እንዲሁ በቀላሉ አገኛለሁ ብልህ ነው ምታስበው" "እረ..? ይልቅ ግን ልጠይቅሽ..አባትሽ ግን የምር ኦርቶዶክስ ናቸው ነው ያልሽኝ ማለቴ እርግጠኛ ነሻ ግን.." ሊል የፈለገው የገባት ስምረት ፈገግ አለች:: "እረ አባዬ ለመስበክም ሁላ እየጀመረ ነው.ምን ቢለው ይሆን.." ስትል በውስጧ አሰበች:: አንድ ሳምንትንቱ አልቆ ረጅም ጊዜ የተዋወቁ እስኪመስለው የተላመዳቸውን እነስምረት ቤተሰብ ተሰናብቶ ወደ ቤቱ ተመለሰ:: ስምረት አንድ አራት ቀን ቆይታ ተከተለችው:: መምጣቷን ስትነግረው ልክ ለአመታት ያላያት ይመስል ግቢ በፍጥነት ሄዶ ተንስፍስፎ ነበር ያገኛት::ሲያቅፋት ላየ ከሩቅ ሀገር ከርሞ የመጣ እንጂ ከቀናት በፊት የተለያዩ አይመስሉም::አልተቃወመችውም መልሳ አቀፈችው:: በአፋቸው ያላወጡት ፍቅር ከሩቅ እንኳን ለሚያያቸው ሰው ግልጽ መሆን ጀምሮ ነበር::የተቆጣጠረችው ቢመስላትም ግን አልቻለችም ነበር::ምንም ነገር ባታደርግ ግን አንዳንድ ነገሮችን መቃወም ማትችልበት ደረጃ ደርሳለች:: ይቀጥላል.. ✍️ዲቦራ @Arebumenfesawi39

  • በግራ ገባኝ!    ቀኝ ልቤ፦ ቅኔ የሚያነብ ሰው አለ?    ግራ ልቤ፦ አዎ አለ።     ቀኝ ልቤ፦ የሚፈታስ?  ....     ግራ ልቤ፦  እንደአማርኛህ...     ቀኝ ልቤ፦ እንዴት "እንደአማርኛህ"?     ቀኝ ልቤ፦ ሆሆ ምን እንዴት አለው ታድያ አማርኛህ #የታሰረው በሰው ከሆነ ሁሉም ሰው ይፈታልሃል     ግራ ልቤ፦ ስለምን መታሰር ነው ምታወራኝ... ደሞ ሰው ስትል ምን ማለትህ ነው?     ቀኝ ልቤ፦ አንተ አይደለህ እንዴ የሚፈታ ያልከው... ታድያ ታስሮ መሠለኝ... ማለቴማ ሰው ተቸግሮ ፣ ሰው አለፈለት ሰው ተጠንፍሮ ፣ ሰው ተረፈለት ብለህ ብትል "ንፍሮ" ሚል ቃል ይፈጥሩልሃል (NON EXPECT) ወላ ተራ ቅልል ቃልህን ፤ ቁልል ያደርጉልሃል ነው ምልህ...     ግራ ልቤ፦ እየቀለድክ ነው ያላልኩትን? እንዴት ሳላወራ ይሰማሉ?     ቀኝ ልቤ፦ ነገርኩህ እኮ ፈቃዳቸውን ፣ ራሳቸውን ነው ሚሰሙት እንጂ አንተ ምንም አልክ ጉዳያቸው አይደለህም!! አይ የ20ኛው sencheri ሰው ዘመኑን አታውቀውም መሠል... ግራ ልቤ፦ ቆይ ታድያ ካንተ ሰማን ተብሎ የተከታይ ጋጋታስ?    ቀኝ ልቤ፦ አይገባህም መሠል? "በቃ ገጠር ግባ" የሰሙህ ስለመሠለህ ነው እንጂ የሰሙት የውስጥ ምኞቸውን ነው!!     ግራ ልቤ፦ ደነቀኝ!! ታድያ እንደ አማርኛህ መታሰር ስትለኝ.....በሰው ከማለትህ ጋር ልትነግረኝ የፈለከው ነገር ነበር ማለት ነው!?     ቀኝ ልቤ፦በሚገባ እንጂ!     ግራ ልቤ፦ ምንድነው!?     ቀኝ ልቤ፦ ልትሸከመው አትችልም። በጊዜው ነግርሃለሁ!! ✍#ናትናኤል_አበበ | @Hiyaw_Kidan

  • 12 авг.2483из menabenbabersprituallitrature

    #የተሰወረ ክፍል 7 (መክሊት) "ወንድም አላት ማለት ነው?" "ምን አልከኝ?" "ዳጊ ወንድም እንዳላት አላውቅም ነበር።" "ታድያ በልጅነት የት ነበር የምታቃት?።" "ቸርች።" "ቸርች? እርግጠኛ ነህ?።" "አዉ ምነዉ?።" "አይ እንዲሁ..።" ከፑል ሳጥኑ ላይ ዱላዉን ዘርግቶ ነጯን ኳስ ወደ ቀይዋ ኳስ ሰዷ አሽከርክሮ ከቀዳዳዉ ከተታትና ለቀጣይ ጨዋታ ዱላዉን መሞረድ ጀመረ። "የሰፈራችን ግሪኖች ጋር ገባዉ በለኛ።" "እነሱ ጋር አደለም በእርግጥ የልጁ ጀለስ ጋር ነዉ።" "ሀዬ። ዳጊሻስ?።" "ተራ።" "አንተስ ቆይ እንዴት ነህ?።" "ደና ነኝ።" "አሁንም ለመናገር ድፍረት አላገኘህማ?።"ዱላዉን አስቀመጠና ከወንበሩ ተቀምጦ ሽቅብ ወደ ላይ እያየዉ። "ጥ..አልቻልኩም ሄና።" "አንተ እኮ ዝም ብለህ ስለምታካብድ ነዉ ዳጊን እኔ አቃታለሁ ቀለል ያለች ልጅ ናት ትረዳሀለች።" "ችግሬ እሱ አደለም አሁንም ድረስ ወንድሜ እያለች ነዉ ምጠራኝ እሷ ልብ ዉስጥ ከወንድምነት የዘለለ ቦታ የለኝም ምናልባት የኔ ስሜት ይሆናል ልክ ያልሆነዉ።" "እሱን አላዉቅም ግን ላይፍን አደለም እንዲ አወሳስበሀት ለራሷ ራሱ ደባሪ ናት። የአራዳ ልጅ ነገር በሆዱ አይዝም የመጣዉ ይምጣ ዘርግፈህ ተገላገል።" "ወይ ሄና አንተ ትቀልዳለሀ....   እኔ ልሂድ አሁን ለማዘሯም አልነገርኮትም።" "ሀዬ ሂድ በቃ።" አቶ አንተነህ ከቤት አንስቶ ስራ ቦታቸዉ ካደረሳቸዉ መኪና ወረዱና ወደ ትልቁ ፎቅ ገቡ። "መዉረጃሽ ይሄ ነዉ እህት?።" "እ አዉ ስንት ነዉ?።". "ሶስት መቶ።"ገንዘቡን ከፍላ ከመኪናዉ ወረደችና ወደ ድርጅቱ አቀናች።"! "ዳጊ?።"እየሄደች ካለበት ጥሪዉ አስቆማት ዞር ብላ አየችዉ። "እዚ ምን ትሰሪያለሽ?።" "እ...ስራ እየፈለኩ አንተስ?።" ""እኔማ....ያባቴ ድርጅት ነዉ።" "አረ ።" "ግን ስራሽ ምን ሆነ ማለቴ መኪናዉስ።" "ከባሉካዉ ጋር ትንሽ ተቦቀስንና ወሰደዉ።" "ምን?።" "ተባረርኩ።" "እንዴ ለምን?።" "ረጅም ታሪክ ነዉ በቃ አላስቁምህ ግባ።" "አይ የኔ በኋላ ይደርሳል ነይ ገብተን እንጠይቅ።" አንገታቸዉን ደፍተዉ አፍጠዉ ከሚያዩት ፋይል ላይ በሩ ሲንቆረቆር ቀና አሉና። "ይግቡ።" "ግዜ ይኖርሀል አባዬ።" "እንዴ ግባ የኔ ልጅ መጣህ።" "አዉ አንድ ሰዉ ይዤ ነዉ የመጣሁት።" "ማንን?።" "ስራ ፈላጊናት በሹፍርና ።" "ኦ በእርግጥ አሁን ላይ ሹፌር አያስፈልገንም ግን ምናልባት የሰራተኞች ባስ አለ ፍቃደኛ ከሆነች።".ቢኒያም ዞሮ ሲያያት ግዜ።አንገቷን በአዎንታ ነቀነቀችለት። "ታዲያ ስምሽ ማነዉ?።" "ዳግማዊት።"ከሰማይ አንዳች ነገር ተሰብሮ የወደቀበት ይመስል ደርቆ ቀረ። "አባዬ!።" "እ እ ማን አልሽኝ?።" "ዳግማዊት!።" "አይ አይሆንም ተሳስቼ ነው ስራዉ ተይዟል።" "እንዴ አባዬ አሁን አለ አላልክም አንዴ!?።" "አይ ተሳስቼ ነዉ ባለፈዉ ነዉ የቀጠርነዉ ረስቼዉ ነዉ።"ዳግማዊት እያየችዉ ፈገግ አለችና። "ከተያዘ ምን ይደረጋል በቃ ሌላ ቦታ ፈልጋለሁ አመሰግናለሁ።"ቢኒያም ተሸማቆ አንዴ አባቱን አንዴ እሷን አየ እና ዳግማዊት በሩን ከፍታ ስትወጣ። "ለአንድ ግዜ እንኳን ሰብዓዊ ዜጋ መሆን አትችልም አደል ታሳፍራለህ በእዉነት።" "አንተ ልጅ.....።"ሊያወራ ያለዉን ሳያስጨርሰዉ በሩን ከፍቶ ወጣ። "ዳጊ!...ዳጊ!።" "ወይ።" "ይቅርታ።" "ለምኑ?።" "አባቴ....።" "ስራ መጥፋቱ የማንም ጥፋት አደለም ያንተ አባት ጋር ባይገኝ ሌላ ሰዉ ጋር ይገኛል።" "ለምን እኔ ጋር አትቀጠሪም።" "ምን?።" "የግል ሹፌሬ ሁኚ።ያልሽዉን ያህል ከፍልሻለሁ።" "ከልብህ ነዉ?።" "አዉ።" ይቀጥላል..... @menabenbabersprituallitrature

  • ሜርሲ እና ብዕሯ✍ pinned «ለአዳዲስ ቤተሰቦች:-   ከዚህ ቀደም በዚህ ቻናል የተፃፉ ናቸው።# ጉን በመንካት this chat በሚለው ላይ ከክፍል አንድ ጀምራችሁ የፈለጋችሁትን ማንበብ ትችላላችሁ። #አኬልዳማ #እንዳልጠፋ #ከረፈደ #የውስጥ ጩሀት #የመውጊያው በትር #ሎዛ #ራማ #አረሜን #ነጥብ #የተጋረደ #ሶምበር #የሞት_መንገድ #ሁለት ገፅታ #ከስሜ በፊት #ካልተፈቱ_እሥራቶች #ስውር_ህልም #ነፍሰ_መና #ኤማሁስ #ሻካር…»

  • 11 авг.252из christians_Tweet

    🌧በዚህ ክረምት መንፈሳዊ ህይወታችንን የሚያሳድጉ ዝግጅቶች። የፈለጋቹትን መርጣቹ ተቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇

  • ለአዳዲስ ቤተሰቦች:-   ከዚህ ቀደም በዚህ ቻናል የተፃፉ ናቸው።# ጉን በመንካት this chat በሚለው ላይ ከክፍል አንድ ጀምራችሁ የፈለጋችሁትን ማንበብ ትችላላችሁ። #አኬልዳማ #እንዳልጠፋ #ከረፈደ #የውስጥ ጩሀት #የመውጊያው በትር #ሎዛ #ራማ #አረሜን #ነጥብ #የተጋረደ #ሶምበር #የሞት_መንገድ #ሁለት ገፅታ #ከስሜ በፊት #ካልተፈቱ_እሥራቶች #ስውር_ህልም #ነፍሰ_መና #ኤማሁስ #ሻካር #በመንገዴ #ሁለት_ሰይፍ #ቀጠሮ የረሳሁት ካለ አስታውሱኝ። ሰናይ ጊዜ❤ @Mercy_ena_berua✍

  • ቤተ ክርስቶስ ክፍል#16 ተማሪው ቀጣይ የግቢ ቆይታና የሕይወቱን አቅጣጫ የሚወስንለትን የመጀመሪያ ሰሚስተር ፈተና ለመውሰድ ዝግጅቱን ጨርሶ በተጠንቀቅ እንደተባለ ወታደር ትንፋሹን ሰብሰቦ የቀረውን ደቂቃ ያነበበውን ለመጨረሻ ጊዜ ደጋግሞ በአይምሮ ያሰላስላል::ግማሹ ከወዲህ ወድያ እያለ ከሌሎች አገኝ ያለውን ቃርምያ የቃርማል:: ስምረት ጥግ ላይ ደብተሯን ይዛ ቁጭ ብትልም አይኗን በየደቂቃው ሌላኛው መውጫ ጫፍ ከያሲን ጋር ቆሞ እየተጠያየቀ ሚስቀውን መውደድ ማየቷ አልቀረም:: ስትገባ ትናንት በሸኛት አይነት ፈገግታ ፈገግ ብሎ"ደና አድረሽ ስምረት..በድንብ ተዘጋጀሽ?"ከማለት ውጭ ሌላ ምንም ቃል አልተለዋወጡም:: ልቧ ላይ ምቾት አልተሰማትም::ባለፈው አስርት ደቂቃዎች ውስጥ እሷ ይሄን ያክል ጊዜ ስታየው አንዴም ዞሮ አላያትም::ስታየው ደስተኛ ነው የሚመስለው::ለምን እንደሆነ ባታውቀውም ግን ከፋት:: "ቅድም ሳልጠይቅህ መውደድ..እነ ጋሼ እንዴት ሆኑ.."ፈተናው አልቆ በር ላይ እንደወጡ ጠብቃ:: "ህም ታውቂ ነበር..?ደና ገብተዋል እግዚአብሔር ይመስገን..ፈተናው እንዴት ነበር..?" "ምንም አይል አንተጋስ..?" "አሪፍ ነው" ለቀናት ከዚህ ያለፈ ሌላ ንግግር ሳያደርጉ ፈተናው መገባደጃው ደርሶ የፈተና ውጥረቱም ቀንሶ መጨረሻ ቀን ደረሰ:: ልታወራው ብትፈልግም ግን መራቁን ራሷው ፈልጋለው መልሶ መቆስቆሱ ጤናማ አልመስልሽ አላት:: ፈተናው እንደጨረሱ ወደ ቤት መሄዷን እያሰበች ግን ልቧ ለሁለት ይከፈላል:: "ቆይ ይሄን አልነበር ፈልጌው የነበረው..? ምን እየሆንኩ ነው!"ራሷን ትገፅፃለች:: "ወደ ቤት ትሄጃለሽ አይደል..?"የመጨረሻ ፈተና ወስደው ሲወጡ ጠየቃት:: "አው" "ጥሩ.."ውስጧ ማውራቱን እንዲቀጥል እየተመኘ ምንም ሳይላት ሄደ:: ቅር እንዳላት ዶርም ገብታ አረፍ አለች::ትንሽ እንደ ቆየች ወደ ሎከሯ ሄዳ ከሰጣት አንዴም ሳትከፍተው ያስቀመጠችውን ስልክ አይታ ፈገግ አለች:: ከፍታ ውስጡን ማየት ስትጀምር ሙሉ መዝሙር እንደነበረው አይታ ይበልጥ በመገመረም ፈገገች:: "ተመስገን ፈጣሪዬ ኡፍፍፍ.."ሱዛን በሩን ከፍታ ገባች:: "ፈተና አለቀ እኮ ሰም" "ልትሄጂ ነዋ..?"ስምረት ቀዝቀዝ ብላ አልጋዋ ላይ ራሷን የወረወረችውን ሱዛን እያየች:: ሱዛን መልስ ሳሰጣት ከተንጋለለችበት ቀና ብላ አየቻት:: "ዝውውሩ ካለቀ ተመልሰሽ አትመጭም አይደል..?" "እንዴ እመጣለሁ የኔ ቆንጆ ማነው እንደዛ ያለው በዛው አልቀርም ደሞ እንገናኛለን.." ስምረትን ምቾት እንዲሰማት ለማድረግ ሞከረች:: "መገናኘት አለብን ሱዝ.."እጇን ያዘቻት:: "ግድ የለም አንቺ ባታገኚኝ እንኳን እኔ ራሴ ከየትም ብዬ አገኝሻለው እንዲ በቀላሉማ አንለያይም"መልሳ እጇን የያዘውን እጇን በሁለት እጇ እየያዘች:: "እወድሻለሁ.."አቀፈቻት "እኔም" በዚህ መሃል የስምረት ስልክ ጠራ መውደድ ነበር ሚለው ባለማመን ወደ ሱዛን ዞራ "መውደድ!" አለቻት:: "አንሺው አንሺው"አለቻት ሱዛን:: አንስታ "ሄለው" አለች ድምፅዋ እንደሆነ ነገር እየሆነባት:: "ሄለው ሰም..እኔ ምልሽ..መቼ ነው ምትሄጂው?" "እንጃ ምናልባት ነገ ብዬ ነበር ያሰብኩት" "ለኃይሌ እኮ እንደጨረስን ነግሬው እንደምትሄጂ ጠይቆኝ ነበር..እናም ከመሄድሽ በፊት ፍቃደኛ ከሆንሽ ሆቴል እንድትመጪ ይፈልጋል ከሱዚ ጋር" ስምረት ቀና ብላ ሱዚን አየቻት:: እሺ በይ በሚል በአይኗ አወራቻት:: "እ..መወደድ እስኪ ቆይ አሳውቅሀለው" "እሺ ባትቀሪ ግን ደስ ይለኛል እንደጓደኛ ወይንም እንደ ቤተሰብ ግብዣ ልትቀበይው ትችያለሽ" "እሺ ገብቶኛል" "ነገ ሰባት ሰዓት መጥቼ ልወስዳችሁ እችላለሁ" ስልኩን ዘግታ ወደ ሱዛን ተመልሰች:: "ሰም እንቢ ማለት ነውር ነው እነዚህ ሰዎች እኮ ላንቺ ብቻ አይደለም ለኔም ብዙ ነገር አድርገውልኛል ኃይሌ ሁለት ቀን እዛ በቆየሁበት ጊዜ እንደ አባት እንደታላቅ ወንድም ነበር የሆነልኝ ስለዚህ በዚህ መልኩ አስቢው እባክሽ እንዳታወሳስቢው እ..?" ምንም ማለት አልቻለችም ቢሆንም ግን መውደድ እሷ ጋር መደወሉን በራሱ ወዳዋለች:: ... ቀኑና ሰዓቱ ደርሶ ይቅርብኝ እያለቻት ሱዛን ለረጅም ሰዓት አንዴ ልብሷን አንዴ ፀጉሯን ከወዲህ ወድያ ስታደርግ ቆይታ ዝግጅታቸውን ጨርሱ:: "ሰም ትንሽ ብቻ..ከንፈርሽን ብቻ እኮ ነው ምነካው እሱ ደሞ ሜካፕ አይባልም.."በልምምጥ:: "እይኝ እስኪ ሱዚ ይሄ ራሱኮ በጣም ተካብዷል ሰርግ ነው እንዴ ምንሄደው..?" "ግብዣ አይደል እንዴ..ሰም ደግሞ ሁሉንም ነገር አክብደሽ ትችያለሽ!"ብዙ ብትላትም ግን ምንም አይነት ሜካፕ አሻፈረኝ እንዳለች ቀረች:: "ዛሬ መመለሳችሁንም እንጃ..!" ሰላም "ከፈራሽ ፀልይልና...!"ስምረት "ሆ...ለራሴ ፀልዬ ማላውቅ ሴትዮ..!" "አየሽ ሳፀልይ እንኳን ሴጣን ፈርቶሽ የምትኖሪ ዜጋ እኮ ነሽ ሰሉ"ሱዛን እየቀለደችባት ሁሉንም ፈገግ አስባለ:: "አንቺ እንዴት ነው ያማረበት እይው..!"ሱዛን ጥቁር ቀይ ሸሚዝ በጨርቅ ሱሪ ለብሶ ነጭ መኪናውን ላይ ተደገፎ ስልኩ ላይ ያቀረቀረውን መውደድ ጠቆመቻት:: መውደድ በበኩሉ ድንገት ቀና ሲል ካያት ስምረት ላይ በቀላሉ አይኑን መመለስ አልቻለም ነበር::ልቡ ላይ እንደአዲስ የሆነ ነገር ሲቀጣጠል ተሰማው::ልክ መጀመርያ ቀን አይቷት እንዳስደነገጠችው አይነት፤ ልክ ሀይቁ ላይ ሲያያት ልቡ ላይ እንደበራበት አይነት፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ፈገግታዋን አይቶ ብልጭ እንዳለው አይነት:: ራስ ሆቴል ደርሰው ወደ ተዘጋጀላቸው ልዩ ቦታ ካደረሳቸው ቡሃላ ኃይሌ ሲቀበላቸው እሱ ዞር አለ::ግብዣው ላይ እሱ እንደማይኖር ስታይ ቅር አላት::ነገር ግን ከሰላሳ ደቂቃዎች ቡሃላ ያሲንን ይዞት ሲመለስ ውስጧ ፈነደቀ::ያሲን ሙሉ ድባቡን ቀየረው ሲጫወቱና ሲስቁ ቆዩ:: ስምረትና መውደድ ሲቀሩ ሌሎቹ መጠጥ ያዙ::ለሷ ምቾት ለመስጠት ብሎ እንጂ ማይጠጣ ሆኖ ግን አልነበረም:: "ስለመጣሽ አመሰግናለሁ..!" "የኃይሌ ግብዣ መስሎኝ..? "አው ልክ ነሽ ግን ቢሆንም.." አፉ ባይላትም ግን አይኖቹ ቆንጅተሻል የሚል መልዕክት እያስተላለፉላት:: "እኔ ነኝ እኮ ማመስገን ያለብኝ!" "ቢያንስ ጥሩ ጓደኛሞች ነን አይደል..?" "በጣም ጥሩ!" ... መንገዷን ሙሉ ይሄንን እና ያሳለፈችው ሰሚስተር እንደትሪዕት በመስታወቱ ውስጥ እየታያት ሰዓታትን ተጉዛ ወደናፈቀችው ቀዬ ደረሰች:: ለአንድ ሳምንት ጎረቤት ዘመዱን እርሻና ግጦሹ ሳይቀራት ከእረኞች ጋር ስትዞር ሰላም ስትል ከረመች::ለእናቷ አውርታና ተርካ አልጠግብም ያለችው ነገር ቢኖር ስለ ቸርችና ፈሎ ነበር:: ከመውደድ ጋር የነበረው ነገር ቀለል ብሎ ስለነበር አልፎ አልፎ ይደዋወላሉ:: በሆነኛው ቀን ድንገት "ልመጣ ነው"አላት "ምን..!የት ነው ምትመጣው..?" "ጎንደር ነዋ እናንተ ጋር!" "መውደድ አብደሃል እንዴ..? እንዴት ነው እዚህ ምትመጣው..?" "ምን ችግር አለው ለአንድ ሳምንት እኮ ነው ጋሼና እማ የሉም እዚህ በጣም እየደበረኝ ነው" "ማነው እሱ..ኪዳኔ ነው..?"ያላየቻት እናቷ ድምፅ ከኋላዋ:: ስምረት ደንግጣ ዞረች:: ይቀጥላል.. ✍️ዲቦራ እኔ 5ሺ ፊደል 5ሺ ጊዜ typ አደረጋለሁ እናንተ ግን አንድ like ይደክማችኋል አይደል ..?? https://t.me/Arebumenfesawi39

  • ቤተ ክርስቶስ ክፍል#15 ልብ ስሌት አይገባውም! ምክንያት እና ውጤት ለአእምሮ እንጂ የልብ ጉዳዩች አይደሉም::ሚገርመው ግን ከአይምሮዋችን ይልቅ እኛ ላይ ጉልበት ያለው እሱ ነው::ልባችንን እኛ አናዝበትም አንዴ ያመነበትን ነገር ካመነ ቡሃላ ተው ብንለውም አይሰማም::ለዚህ ነው ቀድመን ከልባችን መማከር እና በአይምሮዋችን ያሰላነውን ነገር ቀስ ብለን በመንገር መሄድ ያለበትን አቅጣጫ እንዲወስን ማደረግ ሚገባን::ካለሆነ ግን ብቻውን ያለ ልጓም እንደፈለገው ሚያስብና ሚመርጥልን ከሆነ መቼና የቱ ጋር እንደተሸነፍን እንኳን ሳናውቅ እጅ ሰተን ወድቀን አቅመ ቢስ ከሆንን ቡሃላ ነው ድንገት ራሳችንን ምናገኘው:: ለልብ ስሌት አይገባውም::የት ወስዶ እንደሚጥለን አናውቀውም::ለዚህ ነው መፅሐፍ ልብህ ጠብቅ የሕይወት መውጫ በእርሱ ነውና የሚለን:: ለሰዓታት ካቀረቀረችበት ንባብ ቀና ብላ ዙሪያዋን አየች::ማታ ስትገባ ላይብረሪውን አጨናንቆት የነበረው ተማሪ ተመናምኖ እሷና በጣት የሚቆጠሩ ዘርዘር ብለው የተቀመጡ ተማሪዎች ብቻ ቀርተዋል::ወደ ኋላ ሳብ ብላ ሰውነቷን ካፍታታች ቡሃላ ሰዓቷን ለማየት የዘጋችውን ስልኳን ከፈተች:: 11:29 ይላል::ለአይን ያዝ ቢያደርግም ግን ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ተማሪዎች እንቅስቃሴ ስለሚጀምሩ ብቻዋን ወደ ዶርም መግባት ምትችልበት ሰዓት ነው:: ወድያው መልዕክት ገባላት: "መውደድ በር ላይ ተቀምጦ አይቼው ነበር ቀን ላይብረሪ እንደምታመሺ ስለነገርኩ ት ምናልባት አንቺን እየጠበቀ ሊሆን ይቻላል"ይላል ከሱዛን ነበር:: የተላከበትን ሰዓት አየችው አምስት ሰዓት ይላል::ብዙ ሰዓት ስለሆነው ችላ በማለት በቀስታ ተነስታ መፅሐፏን መልሳ ወደ በሩ አቀናች:: ደረጃውን ጨርሳ ዞር ስትል ኮሪደሩ ላይ አንድ እግሩን አጥፎ ግድግዳውን ተደግፎ እንቅልፍ ከወሰደው መወደድ ጋር ተገጣጠመች:: ብርዱ ከውስጥ ለወጣችው እሷ እንኳን ይጋረፋል ጭጋግና ጉም አከባቢውን ሸፍኖታል:: ጠጋ ብላ እሱ መሆኑን ለማረጋገጠ ሞከረች:: "በኢየሱስ ስም..!ጌታ ሆይ ድረስኝ መውደድ..!" ያደረገችውን ስካርፕ ከላይዋ ገፋ እየደረበችለት:: መውደድ ቀስ ብሎ አይኑን ገለጠ "ሰም..መጣሽ እን.."ሳይጨርሰው ሳል ቀደመው "ወይኔ መከራዬ..መውደድ ተንስ እባክህ ብርድ መቶሀል..በጣም ቀዝቅዘሀል እኮ "እጁን ይዛ እንደ መደገፍ እያለች ለማስነሳት ሞከረች:: ሳሉ እንደያዘው ለመቆም ሞከረ ግን አጥፎት የተቀመጠበት እግሩ በቀላሉ አልዘረጋ ብሎት ክፉኛ ሲያመው አቃሰተ:: "እኔን እኔን..አይዞክ ቀስ እያልክ"እጁን ትክሻዋ ላይ አድርጋ አንዱን እጇን በወገቡ አሳልፋ ደገፈችው::እንደምንም አነክሶ ቆመና ትክሻዋ ላይ ያደረገችውን እጁን ተጠቅሞ ወደራሱ ሳብ አድርጎ አቀፋት:: "ለምድነው ጥለሺኝ የጠፋሽው ሰም...?" ስሩ ሽጉጥ እንዳለች ኬት መጣ ስትል እንባ ፊቷን አራሰው:: "የት ነው ቆይ የሄድሽው..ለምን..?" "ሁለተኛ ጥዬህ አልጠፋም..!"ሁለቱንም እጆቿን በወገቡ አሳልፋ ጥምጥም ብላ ይበልጥ ስሩ ገባች::ድምጽ ሳታወጣ ተንሰቀሰቀች እንደ ተቃቀፉ ደቂቃ አለፈ:: "አሁን ወደ ክሊኒኩ መሄድ አለብን.." "ችግር የለውም አሁን ደና ነኝ ጠዋት ይደርሳል" አንክስ እያለ ለመራመድ ሞከረ:: እንደዛ ከሆነ ወደ ዶርም ላድርስህ" "ችግር የለውም ሰም ይኸው እየተራመድኩ እኮ ነው ትንሽ ብቻ ደንዝዞኝ ነው" "መቼም አትሰማኝም በቃ?" "እሺ በቃ" ዝም ተባብለው እንደደገፈችው መንገድ ቀጠሉ:: አንድ ቦታ ላይ ሲደርሱ ዝምታውን ሰብሮ "ሰም እዚህ ጋር ቁጭ ብለን ትንሽ ማውራት እንችላለን?"አላት በልምምጥ "አሞሃል እኮ ከዚህ ብርድ ቶሎ መግባት አለብህ ሌላ ጊዜ አይደርስም"አሁንም ዝምታ:: "ግን ለምን እንዲህ ማድረግ አስፈለገህ..?"ከደቂቃዎች ቡሃላ ራሷ ጠየቀች:: "አንቺን ልጠይቅሽ ለምን እንዲህ ማድረግ ፈለግሽ?"ጥያቄዋን በጥያቄ መለሰላት ዝም አለችው::ለደቂቃዎች ጠበቃት መልስ የለም::ፊት ለፊቷ ቀድሞ ቆመና አስኮቆማት "የምር ግን ለምድነው ከኔ የሸሸሽው ስምረት ንገሪኝ ምንድነው የፈራሽው?"በሁለት እጁ ትክሻዋን ይዞ አይኑን አይኖቿ ላይ ተክሎ መልስ መጠበቅ ጀመረ:: "ምክንያቱም ልክ ያልሆነ ነገር ስላለ"አይኗን ከሱ አሸሸች:: "ፍቅር ነው ልክ ያልሆነው ነገር..? ወይስ እመነታችን?" "የፈለከውን በለው ግን እንደዛ አይነት ነገር መሃላችን መፈጠር የለበትም ከጓደኝነት ወይም ከንፁህ ወንድምነት በዘለለ ምንም መሆን አንችልም" "ለምን እንደዛ ብለሽ ደመደምሽ..ፍቅርን ማሸነፍ የሚችል ኃይል ያለ ይመስልሻል..? እኔም እንዳንቺ አስቤ ነበር ሰም ግን ያ ሊያስፈራን የሚገባ ነገር አይደለም" "ላንተ ሊሆን ይችላል ግን መውደድ እኔ ጋር መሆን አይችልም!" እጁን ከትክሻዋ ላይ አንስቶ "እሺ..አንቺ ሳትፈልጊ ምንም ነገር አይሆንም ምንም ነገር አይፈጠርም" አለ ፈገግ እንደማለት ብሎ ያልጠበቀችው ስለነበር በምላሹ ግራ እንደ መጋባትም እንደ መክፋትም አላት:: "ደርሻለሁ አሁን መሄድ ትችያለሽ ግቢ በቃ" እስካርቧን በእጁ እያቀበላት:: ተቀብላው ከሩጫ ባልተናነሰ እርምጃ ወደ ዶሮሟ ሄደች:: መውደድ በበኩሉ ፈገግ እንዳለ ከአይኑ እስክትሰወር ቆሞ አያት:: ምን አይነት ግራ መጋባትና ፍርሃት ውስጥ እንዳለችና በትክክል ምን ሊሰማት ልታስብ እንደምትችል ተረድቷል::ምክንያቱም ይሄ ስሜት እሱንም ገጥሞት ነበር::ግን ተስፋ አልቆረጠም ለብቻው ጊዜ ወስዶ በድፍረት ወስኖ ተመለሰበት::ምክንያቱም ፍቅርን የሃይማኖት ልዩነት እንደማይገድበው ከጓደኛው ያሲን፤ላፈቀሩት ሰው እስከመጨረሻው መታገልንና መፅናትን ደግሞ እንደ ማገጠባት እያወቀች እንኳን በይቅርታና በፍቅር ስትቀጥል ካያት እናቱ አይቷል::ስለዚህ ይሄን እሱም ማለፍ እንደሚችል በልበሙሉነት አምኖበትና ሊያስከፍለው ለሚችለው ማንኛውም ነገር ተዘጋጅቶበት ነበር የቀጠለው:: አሁን ስምረት የሚያስፈልጋት ያቺ እሱ የወሰዳትን ጊዜ ያህል መወሰድ እንድሆነ እርግጠኛ ስለሆነ ነበር ምንም ያላላት:: ... ዶርም ስትደርስ ሁሉም ጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ ነበር::እንዳይሰማ አፏን በእጇ ይዛ በሩ ላይ እንደቆመች ተንሰቀሰቀች:: ቀስ ብላ ወደ አልጋዋ ጫፍ ሄዳ ለመንበርከክ አመነታች:: ትታው ቁጭ አለችና"ለምን ጌታ ሆይ?"አለች:: መውደድን"አግኘው"ብላ እንዲድን ለመፀለይ ስለወደደችው እንጂ የምር ከልቧ ለነብሱም አስባም ይሆን ለወንጌል ቀንታ እንዳልሆነ ይልቅ ከራስ ወዳድነት የመነጨ የስጋ ፀሎት መስሎ ይታያትና ውስጧ ይወቅሳታል:: ለሱ ወንጌል ለመመስከር ስታስብ በጣም እንደረፈደ አቅሙን እንዳጣች ይሰማታል፤ጌታን ፍቀድልኝ እንዳትለው ፍቃዱ እንዳልሆነ ታውቃለች፤ እንዳትተወው ቀላል አልሆንላት ብሏት በነብስና ልቧ መሃል ሰፋሪ ሆና ቀርታለች::አሁን ደሞ ከራሷ ህመም አልፎ እሱ ያለበትን ስቃይ ስታይ አልቻለም::ከሱ መራቅ ራሷን ብቻ ሳይሆን መውደድን ይበልጥ እንደሚጎዳው አይታለች::ነገሮች እንዲህ ባይሆኑ ብላ ተመኘች::ግን አሁን ላይ ከማልቀስ ውጭ ሌላ ምንም ማድረግ ምትችለው ነገር የለም:: ምኑን ከየት ወዴት ማድረግ እንዳለባት ግራ ገብቷታል::ልቧ ጠዋት ማታ መውደድ ይላታል እሱ ሕይወቷ ውስጥ እንዳልተፈጠረ አድርጎ ለመርሳት ለቀናት ያደረገችው ጥረት ግን ከብዙ ስቃይና ከዚህ ቀን በላይ አልሄደም ነበር:: ፀሎት እየከበዳት ከሄደ ቆየ::እንዲ ተደብቃ በምታለቅስባቸው የብቻ ጊዜ ወደ ላይ ቀና ብሎ "ጌታ ሆይ እባክህ አግዘኝ"ከማለት ውጭ ፀልያ አታውቅም:: ይቀጥላል ✍️ዲቦራ @Arebumenfesawi39

  • #ኤማሁስ ክፍል 16(ሜርሲ) "የዚህ ዙር የአምልኮ ምሽት መዝሙሮችን የመረጣችሁትን አይቻለሁ።በጣም አሪፍ ናቸው።ግን ያልገባኝ ለምን ይሄ መዝሙር እንደገባ ነው::" "የቱ?" አለች አንዷ ከመሃከላቸው። "የኤማሁስ መንገደኞች።ይሄ መዝሙር ለአምልኮ የሚሆን አልመሰለኝም።መኪናችን ውስጥ፣ቤት ላይ የምንሰማው መዝሙር ነው።" "ማነው እንደዛ ያለው?" ሩሃማ ግራ በመጋባት ጠየቀችው። ወደ እሷ ፊቱን አዙሮ:- "ምን አይነት ጥያቄ ነው።ይሀው አሁን እኔ እያልኩ እኮ ነው።" "ብሩክ መዝሙሩ መድረክ ላይ በሌሎች አልተዘመረም ማለት ለመድረክ አይሆንም ማለት አይደለም።ለመድረክ አይሆን ይሆናል የምለውንም ይሀው ከአን። እየሰማሁ ነው።ምን አይነት ክፍፍል ነው?" "ሩሃማ ስለ አምልኮ፣ዝማሬ እዚህ ቲም ከመግባትሽ በፊት ስልጠና አልሰጡሽም ነው?...በምን አይነት ሪትም ልንዘምረው ነው ይሄን መዝሙሩ።" "ብሩክ ይሄ ስለ ሪትም አይደለም ስለ መልዕክቱ ነው።ስንት መዝሙር ዘምረን አይተነው የለ?..ዛሬ እንዴት ነው አዲስ የሆነብህ?...ወይስ ወረቀቱ ላይ ከመዝሙሩ ጎን የእኔ ስም ስላለበት ነው።" "ቅዱሳን...አረ እየተረጋጋን።ምን አይነት ክርክር ነው ይሄ።ይሄ መዝሙር እስከዛሬ መድረክ ላይ አለመዘመሩ ያስቆጨኝ ሩ ስለዚህ መዝሙር ጥልቀት ስታወራን ነው።ምን አልባት አንተ ባለፈው ስላልመጣህ ስላልሰማሀው ይሆናል።ስትሰማው ሃሳቡን ትቀይራለህ። ከቲማቸው በዕድሜ ትንሹ ያቤፅ ይሄን ብሎ ሲቀመጥ ብሩክ ወደ ሩሃማ ዞረ። * * * "ምንድነው ዴቭ ፈዘህ ቀረህ እኮ።" ዴቭ ቀለበቱን ከኪሱ ውስጥ ከተተው። "ልሂድ..." "ከመሸ ወዴት ነው?" "አየር ልውሰድ ባክህ።" "አብሬህ ልምጣ?" "አይ።" ጃኬቱን አንስቶ ከክፍሉ ወጣ። "የዚህ ድራማ መቋጨው የቱ ጋር ነው?...ፈጣሪዬ።" መጋረጃውን ከፍቶ ዴቪድን ሲወጣ ተመለከተው። "ተመልሳ ቢሆንስ?..." "ማናት የተመለሰችው?" "አሃ.."ልቡን ይዞ ደንግጦ ዞሮ ተመለከታት። "ኮቴ የለሽም እንዴ አንቺ ልጅ?" "የትኛው ኮቴ?" ዝቅ ብላ የዊልቸሩን ጎማ ተመለከተች። "ፈጣሪዬ...በእግርሽ እየሄድሽ እንኳ እንደዚህ አልተዘዋወርሽም።አሁን የቀረሽ ደረጃው እኮ ነው።" ደረጃው ቢሆንስ?...እወጣት።" ንዴቱን እረስቶ ፈገግ አለ። "የት ልትሄጂ ነው እሺ ሜካፕ የተቀባሽው?" "ጓደኞቼ ይመጣሉ።" "ጓደኞቼ?" "አዎ።በእርግጥ የቸርች ልጆች ናቸው።የእኔ ሳይሆን የቤዚ።" "ቤዚ?" "አዎ ካላፀለይኩልሽ ብላ ሙጭጭ አለች።" "ስለዚህ ለፀሎት ሜካፕ ተቀባሽ።" "ማንም ተጎሳቅዬ እንዲያየኝ አልፈልግም።ቅድም ምን ነበር ስትል የሰማሁት?" "ምን አልኩ?" "የሆነ ነገር ብለሃል።ይሄ ሾርት ሚሞሪዬ ይጫወትብኛል።በል ና አግዘኝ።ባዶ ቤት እንዳንቀበላቸው።" * * * "ቅድም መስመር አለፍኩኝ መሰለኝ።" "ቆየህ እኮ መስመር ማለፍ ከጀመርክ ብሩክ።" "ሩ...እየመሸብን ነው እንዳናረፍድባት።" "ወዴት ነው?" "ከፀሎት ቲሞች ጋር ሰው ጥየቃ ልንሄድ ነው።" "ጥየቃ?" "እም::መልካም ምሽት።" ወደ ሚወስዳቸው መኪና ውስጥ ገባች። "ያቤፅ.." ያቤፅ ወደ እሱ ቀረበ። "የምን ጥየቃ ነው?.." "የጓደኛችን ጓደኛ መኪና አደጋ ደርሶባት ነበር እና ልንጠይቃት ልንሄድ ነው።" "ማናት?" "ልጁ ተዋቂ ነገር ነው።እንደውም በሰርጉ ቀን ጥላው የሄደችው ሴት።የእሱ እህት ናት።" "ዴቪድ?" "አዎ ዴቪድ።በቃ እኔ ልሂድ።ሁለት ቲም አገልጋይ ስትሆን እንደዚህ ነው እንግዲህ።ደህና እደር።" "ዴቪድ?" * * * ቤዛ እንዴት አደጋው እንደደረሰባቸው እየነገረቻቸው በሳቅ የታጀበ ቆይታ ካሳለፉ በኋላ ፀሎት ፀልየው የቀረበላቸውን እየበሉ ማውራት ጀመሩ። "ወንድምሽ እንዴት ነው?" አለ ያቤፅ። "እም..ወንድሜ ምን ይሆናል።ደህና ነው።" "ተፈጥሮ የነበረውን ነገር ሁላችንም ሰምተነው ነበር።ስለ እሱ ሰግተን ነበር።" "ወራት አለፉ በጣም።ጊዜ የማይሽረው ቁስል አይኖርም።" "አባባሉስ ልክ ነው።መሬት ላይ ሲወርድ ይስታል እንጂ።እም...ለምን አይዘመርም?" "በጣም ጥሩ ሃሳብ።እዚህ ቤት ጊታር አይቼ አልነበር ፍቅር?" አለች ቤዛ በዓይኗ እየፈለገችው። "የወንድሜ ነው።ዴቪድ ክፉሉ ላይ ታገኚዋለሽ።" ቤዛ ተነስታ ወደ ዴቪድ ክፍል በማምራት እንደከፈተችው ዴቪድን ተቀምጦ ቀለበቱን በእጁ እያሽከረከረ ታገኘዋለች። "ዴቪድ?...ይቅርታ በጣም ያለህ አልመሰለኝም ነበር...መች መጥተህ ነው?" ዴቪድ እየተነሳ:- "አሁን ነው የገባሁት።የምን ፕሮግራም ነው?" "የህብረቴ ልጆች ሊጠይቋት መጥተው ነው።እም ጊታር ፈልጌ ነበር።" "ጊታር..እም...ውሰጂ.." ሄዶ በማንሳት ሰጣት:: "አትመጣም?" "አይ።እዚህ ልሁን።" ቤዛ ወደ ቀለበቱ እየተመለከተች ቆይታ። "በቃ እንዳልክ።አመሰግናለሁ።ጎበዝ ስለሆነች አታበላሽብህም።" "ማናት?" "ናና እያት ከፈለግክ።ሲመስለኝ ትተዋወቃላችሁ።ልሂድ በቃ::" ስትወጣ ግራ በመጋባት ይመለከታታል።እሷ እንደወጣች ዳግም ይገባል። "ምንድነው ነገሩ?" ሮማንም ተከትላ ገባች። "የቸርች ልጆች ሊጠይቋት መጥተው ነው።" "ቸርች?" አለች ሮማን ግራ በመጋባት። የጊታሩ ድምፅ ሲሰማ እርስ በእርስ ተያዪ። * * * "የተስፋን ቃል የሰጣችሁ የታመነ ነውና ከስፍራችሁ ሆናችሁ በፍቅሩ ታገሱና እግዚአብሔር አይጨክንም ያስብላችኋል ኢየሱስ አብሯችሁ አለና እርሱ ይጠግናችኋል..." ዘወር ስትል ከበሩ ዴቪድን ተመለከተችው።ዝቅ ብላ ዓይኗን በመጨፈን መዝሙሩን ቀጠለች። "የኤማሁስ መንገደኞች የጌታ ደቀመዝሙሮች ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ ከሞት ተነስቷል ንጉሱ..." ይቀጥላል.... @Mercy_ena_berua✍ @Mercy_ena_berua✍

  • ኤማሁስ ቀጣይ ክፍል ዛሬ ይለቀቃል። ያው የኤማሁስ ወዳጆች እንዳትተኙ ብዬ ነው😊 i think በጣም ልንረሳው ከማንችለው ልብወለድ ውስጥ አንዱ ይሆናል እዚህ ቤት።

  • 10 авг.364удалён 13 авг.

    ባለፈው ለመመዝገብ የ 6ኛ ክፍል ተማሪ ነኝ ያልሽኝ ልጅ እባክሽን DM አድርጊልኝ።ፈልጌ ላገኝሽ ስላልቻልኩ ነው። ከዚህ እንዳልኳችሁ ሁለት ሰው ወስጃለሁ።

  • ሰላም እንዴት ናችሁ #የተሰወረ #ቤተክርስቶስ እና ሌሎች የእኔ ያልሆኑ ፅሁፎች እዚህ ቤት የሚቆዩት ከዚህ በኋላ ለአጭር ጊዜ ነው።ደጋግሜ እንደምላችሁ እኔ ጋር እየለቀቁ ያሉት promote ለማድረግ እንጂ እዚህ ሆናችሁ እንድታነቡት አይደለም። ከስር በማስቀምጥላችሁ የቴሌግራም ቻናል በመግባት ፅሁፎቻቸውን ተከታተሉ። እና የነ መክሊትን ቻናል እየተቀላቀላችሁ። @scripted_word https://t.me/Arebumenfesawi39 @menabenbabersprituallitrature

  • 10 авг.40012удалён 13 авг.

    ባለፈው እንዳልኳችሁ ለተወሰኑ ተማሪዎች Discount ይኖረኛል።ዋናው ምዝገባ አልቋል። እንዳያችሁ inbox ለምታደርጉልኝ 4 ተማሪዎች 50% discount መመዝገብ ትችላላችሁ። @Mercyasta ላይ አናግሩኝ።

  • 9 авг.4205из menabenbabersprituallitrature

    #የተሰወረ ክፍል 6 (መክሊት) "ደና አደርሽ።" "ደና።"አልፋዉ ወደ በሩ ስትሄድ ሮጥ ብሎ ከፊቷ ቆሞና አስቆማት። "ዉይ ዳጊ ዛሬም አኩርፈሽኝ ልትዉይ ነዉ።" "ንዴቴንና ሀዘኔን የምወጣበት ሰዉ እፈልጋለሁ ግን እሱ ሰዉ አንተ እንድትሆን አልፈልግም።ለዛ ብቻዬን መሆን አለብኝ።" "ለኔ ግን ዝም ከምትይኝ ንዴትሽን ሁሉ እኔ ላይ ብታራግፊ እመርጣለሁ።" "ምንቴ የኔ ችግሮች ማለቂያ የላቸዉም አንተ ደግሞ ከችግሮቼ ጋር እንድትቸገር አልፈልግም።" "እኔ መች ቸገረኝ አልኩሽ አሁን ነይ እንሂድ።"እጇን እየጎተተ ይዟት ወጣና የጋቢናዉን ቦታ ይዞ መኪናዉን አስነሳ። "የኔ ወንድም ዲግሪ እኮ መንጃ ፍቃድ አይሆንም!።" "አየሽ ከዕዉቀት ይልቅ ወረቀት ወዳዶች ስለሆንን ነዉ ካሉት የደሀ ሀገሮች ተርታ የተሰለፍ ነዉ።" "አምስት አመት ለወረቀት ብሎ የተጠገረረ ሰዉ ነዉ ይሄን የሚለዉ? ገራሚ ለዉጥ።"ፈገግ ብሎ አይቷት አይኑን ወደ መንገዱ መለሰ። "ከአንድም ሁለት ትልልቅ ካምፓኒዎች አሉኝ የኔ የሆነዉ ሁሉ ደግሞ ያንተ ነዉ ቆይ አንድ ተራ ድርጅት ዉስጥ ተቀጥሮ መስራት ምን ማለት ነዉ?።" "ማነዉ ተራ ያደረገዉ?።" ""ነጥቤ እሱ እንዳልሆነ ታዉቃለህ።" "ከህግ ትምህርት ቤት ስወጣ ቀኝ እጄን አንስጄ ቃል ገብቻለዉ ከእዉነት ጋር እንጂ ከዉሸት ጋር ላለመቆም ።" "እና ህገ ወጥ ነህ እያልከኝ ነዉ!?።" "ንግግሬ ዉስጥ እንደዛ የሚል ቃል የለም ግን....ነህ እንዴ?።" "መስመርህን ያለፍክ አልመሰለህም!።"ከወንበሩ ተስፈንጥሮ ተነስቶ የምግብ ጠረጴዛዉን በእጁ ደለቀዉ። "የትኛዉን መስመር....የአባትነት እንዳይሆን።"ቁጭ ካለበት አይኑን አንጋጦ እያየ መለሰለት። "ልጄ ምን ሆነሀል አባትህ እኮ ነዉ እንዴት እንደዚህ ትናገራለህ።....እስቲ ተረጋጉ አንተም ተቀመጥ አብነት ቁርሱን በስርዓት እንብላ።". "እኔ ልሂድ ዛሬ ስራ የምጀምርበት ቀን ነዉ መልካም ማዕድ።"ከመቀመጫዉ ተነስቶ ቤቱን ጥሎ ወጣ። "ምንቴ እያየህ!።"ከድምጿ ቷን እኩል ፍሬኑን ይዞ አቆመዉ ግን ከፊቱ ካለዉ ቪትስ ጋር እርቀት ስላልነበረዉ ተጋጨ። "አዪ አይሆንም!።"የተጨማተረዉን የመኪና ክፍል እያየች ተናገረች። "አለቃ ሳላስበዉ ነዉ ይቅርታ።" "ያንቺ ይቅርታ የቀን ገቢ ይሆነኛል!?።" "ያን ያህል አልተጎዳም አሁንም ሰርቼ ገቢዉን አመጣለሁ።" "ለዚህ መኪና ሶስት ነጥብ አምስት ሚሊየን ብር ነዉ ያወጣሁት!ለኔ ልጄ ማለት ነዉ ገባሽ!።" "ታዲያ እዘለዋ።"አጉተመተመች። "ምን አልሽ!?።" "ምንም አንድ ዕድል ስጠኝ አይለመደኝም።" "በይ በይ አምጪ ቁልፌን ስንት ስራ ሚፈልግ ሰዉ አለ አንቺ ተጨማልቀሽ ነዉ።"ቁልፉን በጣቷ አንጠልጥላ ከዘረጋዉ እጁ ጣለችለትና ግቢዉን ለቃ ወጣች። "ምን አለሽ?።" "ይመችህ የእንጀራ ገመዳችንን በአሪፍ ሁኔታ በጥሰኸዋል።"እጇን ከፍ አድርጋ አጨበጨበችና ከድንጋዩ ተቀመጠች። "እንኳን በደና ወደ ስራ ፈት ማህበር ተቀላቀልሽ።" "ጥጥ....ከአንድ ቤት ሁለት ስራ ፈት....።"ስልኳ ሲጠራ ከሱሪ ኪሷ አወጣችና አነሳችዉ። "አቤት....ደና.....አልተመቸዉም ነበር አልሄደም....አረ መጣን በቃ።" "ማነዉ?።" "በይፋ ከማህበሩ ወተሀል።.....ቢኒያም ነዉ።" "እህህህ።" "ተነስ በቃ እንሂድ።" "እ ስራ እንዴት እየሄደልህ ነዉ?።" "ጥሩ ነዉ  ወድጄዋለሁ።" "ቆይ ልጁስ ስራዉን ተዉት እንዴ?።" "አረ እየመጡ ነዉ።"ስልኩ ሲጠራ አየዉና። "ይኸዉ እንደዉም ደወሉ።" "ሄለዉ።" "ደርሰናል።...በር ላይ ነን።" "ወደ ዉስጥ ግቡ እየጠበኮቹ ነዉ።" "በቃ አግኛቸዉ መጣሁ የሆነ መጨረስ ያለብኝ ነገር አለ።" "እሺ።"እሱ እንደሄደ እነሱ ገቡ። "እንኳን ደና መጣቹ።" "እናመሰግናለን።" "የትምህርት ማስረጃህን አይተዉ ደስ ብሏቸዋል ዛሬ ቃለ መጠይቁን ካደረክ ቆሚ አድርገዉ ይቀጥሩሀል።" "እሺ።" "በቃ ና ላሳይህ።አንቺ....።" "እኔ እዚ ጠብቃቹሀለዉ።" "አሳይቼዉ መጣለሁ።" " እሺ።" "በቃ ይሄን እንዳልኩህ አድርገዉ። ፋይሎቹን ደሞ ቢሮዬ አስቀምጥልኝ አየዋለሁ።" "እሺ አለቃ።" "እሺ።"ቀና ሲል  በድርጅቱ ዉስጥ ለእንግዳ ማረፊያ ተብሎ በተሰራዉ ሶፋ ላይ ከተቀመጠችዋ ሴት አይኑ አረፈ።ጥቁር ረጅም ፀጉሯን ወደ ኋላ በረጅሙ አስራዉ ከትከሻዋ ላይ ወድቆል ሁለት እጆቾን በጃኬት ኪሷ ከታ እግሯን ዘርግታ አነባብራዉ ተቀምጣለች ዉር ዉር ከሚለዉ ሰዉ እኩል ጎላ ጎላ ያለ አይኖን አብራ ታዞረዋለች። "ዳግማዊት!።"ሳያስበዉ ድምፁን ጮክ አርጎ ስለነበር ሰምታ ቀና አለች አየችውና ከተቀመጨችበት በድንጋጤ ተነስታ ቆመች። "ዳንኤል?።"እሷ ወዳለችበት አቅጣጫ ሄደና አቀፋት።በሁለት እጁ ትከሻዋን እንደያዘ። "በፈጣሪ እኔ ማመን አልችልም የምር አንቺ ነሽ!?።...ቆይ የት ጠፍተሽ ነዉ ያልፈለኩሽ ቦታ እኮ አልነበረም እቤትም መጥቼ ነበረ ግን እንደወጣቹ ነገሩኝ ቆይ ይሄ ሁሉ ዓመት የት ነበርሽ?።"ያለ እረፍት አወራ። "አለዉ።" "ዳኒ ትተዋወቃላቹ እንዴ?።"ዳንኤል ከጀርባቸዉ ያለዉን ቢንያምን ተመለከተና። "እንዴታ ያዉም በልጅነት።" "የሚገርም አጋጣሚ.....በእኔ ቤትማ ላስተዋዉቅ ነበር እኔ ነኛ መተዋወቅ ያለብኝ።" "የእዉነትም ግሩም አጋጣሚ።"ምንተስኖት ጨርሶ ወጣና ሁሉም ተሰብስበዉ ወዳሉበት ሄደ። "ዳጊ ጨርሻለሁ እንሂድ በቃ።" "ጨረስክ ምን አሉህ።" "ነገ መጀመር ችላለሁ ብለዉኛል አቶ ቢኒያም አመሰግናለሁ።" "ኧረ ምንም አይደል።"ደንግጣ ወደ ቆመችዉ ዳግማዊት እየተመለከተ። "ምነዉ ዳጊ?።" "ምንም ከጨረስክ እንሂድ በቃ።" "እንዴ ዳጊ ከስንት አመት በኋላ አግኝቼሽ!...አብረን ምሳ እንብላ እንጂ።" "አይ ዳኒ ሌላ ቀን ይሻላል እቸኩላለሁ።" "በእዉነት እሺ በቃ ስልክሽን ልያዝና ደዉላለሁ።"ስልኳን ሰታዉ ከድርጅቱ ወጡ። "ማነዉ የቅድሙ ልጅ?።" "እም.... ድሮ ማቀዉ ሰዉ ነው ።" "እኔ የማላቀዉ ድሮ አለሽ እንዴ?።" "እህ.. አዉ ለዛዉም  ድሮ የሚባል አስራ ስድስት አመት።" "ኦ።....እና?።" "እና?።" "ማለቴ ትዉዉቃቹ ምን አይነት ነበር?።" "ጥሩ ጓደኛዬ ነበር።" "ጓደኛ ጥሩ ነዉ።" "በል በቃ እኔም ወደ ተራ ሄጄ ስራ ልፈልግ።" "አሁን እኮ እኔ ስራ ገብቻለሁ አንቺ ማረፍ አለብሽ።" "የማርፈዉ ስሰራ ነዉ።"ትከሻዉን ቸብ ቸብ አርጋ ወደ ታች ሄደች።እሷን ቆሞ እያየ ስልኩ ሲጠራ አዉጥቶ አነሳዉ። "ሄለዉ ሄና።" "የተማረ ትምህርት ተራ ነዉ ሚገኘዉ አሉ።" "ልደዉልልህ ስል የት ነህ?።" "ሰፈር ነኝ ፑል ቤት።" "መጣዉ በቃ።" ይቀጥላል..... @menabenbabersprituallitrature

  • 9 авг.42573из scripted_word

    በአካል ርቀን፣ በልብ እንቀራረብ የሰው ልጅ በአካል መራራቅ፣ በልብ ግን መቀራረብ አለበት ብዬ አምናለሁ። በዚህ ዘመን የጎዳን ነገር አንዱ ይህ ይመስለኛል፤ በአካል እጅግ ተቀራርበን ሳለን፣ የሁላችንም ልብ ቢፈተሽ ግን እጅግ ተራርቀን እርስ በርሳችን ስንጎዳዳ እንገኛለን። እጅግ መተዋወቃችን፣ በአካል ብዙ መቀራረባችን አንዳንድ ጊዜ ያለንን አክብሮት እንድንረሳ ያደርገናል፤ ወደ ንቀትም ይመራናል። የአገሬ ሰው “አወቅኩሽ፣ ናቅኩሽ” ሲል የሚናገረው ከንቱ አይመስለኝም። በብዙ ጊዜ የሰውን ድክመት በቅርብ ስናውቅ፣ የነበረን አክብሮት በቀላሉ ሊለወጥ ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስም፦ “እንዳይሰለችህ እንዳይጠላህም እግርህን ወደ ባልንጀራህ ቤት አታዘውትር።” — ምሳሌ 25፥17 ይህ ማለት ሰዎችን መውደድ እንዳንችል ወይም ከሰዎች እንድንርቅ አይደለም። እኛ ሰዎች ፍጹማን አይደለንም። ሁላችንም ደካሞች ነን፤ እንሳሳታለን፣ እንወድቃለን፣ አንዳንድ ጊዜም ሌሎችን እንጎዳለን። ሆኖም የሰው ልጅ ትዕግሥት ስለሚያጥረው፣ የሌላውን ድክመት በፍጥነት ይፈርድበታል፤ ይወቅሰዋልም። ስለዚህ ራስህን ድክመ ታውቀው የለ፤ የራስህን ገመናህን ሊሸፍንልህ፣ ድክመትህን በምሕረት ሊመለከትልህ የሚችል ከኢየሱስ ውጭ ፍጹም የሆነ ሥጋ ለባሽ የለም። ስለዚህ ገመናህን ለማወቅ ሳይሆን ለመሸፈን፣ ድክመትህን ለመቆጠር ሳይሆን ለመደገፍ ከሚችል እውነተኛ ወዳጅ ጋር በፍቅር ቆይ። ልባችን ግን ከሰው ጋር መቀራረብ አለበት። ከኢየሱስ የተማርነው ፍቅር ሰውን ከሰው ጋር የሚያቀራርብ ነው። ኢየሱስ፦ “አብ እንደ ወደደኝ እኔ ደግሞ ወደድኋችሁ፤ በፍቅሬ ኑሩ።” — ዮሐንስ 15፥9 እንዲሁም፦ “እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት።” — ዮሐንስ 15፥12 ስለዚህ ከሰው አንዳች ሳንጠብቅ፣ በልብ መተሳሰርን እንማር። እኛ ይቅር እንደተባልን ደግሞ ሌሎችን ይቅር እንበል። እኛ እንደተወደድን ሌሎችን እንውደድ። የሌሎችን ድክመት እንደምንመለከት የራሳችንንም ድክመት እንዘክር። ምክንያቱም የእውነተኛ ቅርበት መለኪያ በአካል ስንቀራረብ ሳይሆን፣ በልብ ስንቀራረብ ነው። አንዳንድ ጊዜ በአካል መራቅ ያስፈልጋል፤ ግን በልብ መራቅ የለብንም። ድንበር ሊኖረን ይችላል፤ ግን ፍቅር ሊጎድለን አይገባም። ርቀት ሊኖር ይችላል፤ ግን ይቅርታ እና ምሕረት ከልባችን ሊርቁ አይገባም። በአካል እንራቅ፤ በልብ ግን እንቀራረብ። በአካል ርቀት ይኑር፤ በፍቅር ግን አንራቅ። ምክንያቱም ኢየሱስ ያስተማረን ቅርበት የሰውነት ሳይሆን የልብ ነው። ተባረኩልኝ🥰🙏 Join&share 👇👇👇👇 @scripted_word @scripted_word

  • 9 авг.378удалён 13 авг.

    #የመጨረሻ ቀን ለስነፅሁፍ ፍላጎት ላላችሁ ብቻ። አምና ወደ 30 አከባቢ ተማሪዎችን ስልጠና ሰጥቼ ነበር።ያኔ ስጨርስ ድጋሚ ስልጠናውን አልሰጥም ብዬ ነበር።ከአንድ አንድ ተማሪዎች ባህሪ፣ኔትዎርክ ብዙ ተማሪዎች ይቸገሩ ነበር።አሁን ለዛ መፍትሄ በመስጠት ስልጠናውን ቀደም ብዬ በማዘጋጀት በሰዓቱ ገብታችሁ ትምህርቱን መውሰድ የምትችሉ ይሆናል።ስልጠናው ከአምናው 100% የተለየ ስልጠና ነው።detail information…

  • 9 авг.395удалён 13 авг.

    #የመጨረሻ ቀን ለስነፅሁፍ ፍላጎት ላላችሁ ብቻ። አምና ወደ 30 አከባቢ ተማሪዎችን ስልጠና ሰጥቼ ነበር።ያኔ ስጨርስ ድጋሚ ስልጠናውን አልሰጥም ብዬ ነበር።ከአንድ አንድ ተማሪዎች ባህሪ፣ኔትዎርክ ብዙ ተማሪዎች ይቸገሩ ነበር።አሁን ለዛ መፍትሄ በመስጠት ስልጠናውን ቀደም ብዬ በማዘጋጀት በሰዓቱ ገብታችሁ ትምህርቱን መውሰድ የምትችሉ ይሆናል።ስልጠናው ከአምናው 100% የተለየ ስልጠና ነው።detail information ለመሰልጠን የምትፈልጉ በ @mercyasta ላይ አናግሩኝ።መሰልጠን እፈልጋለሁ የሚል text ሲደርሰኝ ብቻ ነው text የምመልሰው።የአምናው አለመግባባት፤ለማስረዳት መሞከር አይጠበቅብኝም።ፍሬውን እራሳችሁ የተመለከታችሁት በመሆኑ።የተወሰኑ ተማሪዎችን እንደተቀበልኩ ስልጠናውን የምጀምር ይሆናል።እንደአምናው ሁለት ዙር አይኖርም።በአንደኛ ዙር ያልቃል።አምና ሰልጥናችሁ ድጋሚ መሰልጠን ከፈለጋችሁም ይቻላል። ሰናይ ጊዜ❤ @Mercy_ena_berua✍

  • ይሄንን ልብ_ወለድ እያነበባችሁ ያላችሁ ሰዎች..🖐️ ዋናውን channel መቼ join ለማለት አሰባችሁ..??👇👇👇 Join here https://t.me/Arebumenfesawi39