tgindex
Bethel primary school

Bethel primary school

Статистика

Bethel primary school discussion group

Последний пост
7 мая
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
419
+1 за 2 дн.
Сутки
+1
+0,24%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 249
21 постов
Вовлечённость
298,1%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 7 мая6683из STEMwithMurad

    ጥቆማ‼ ====== (ልጆቻችሁን ቶሎ አስመዝግቡ። እንዲህ አይነት ነገር ስጠቁማችሁ አታንቀላፉ!) || ✍️ የ2018 ኢመደአ ሰመር ካምፕ የምዝገባ መስፈርቶች – INSA Cyber Talent Challenge 2026 • ምዝገባ በብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ይደረጋል (ከውጪ ዜጎች በስተቀር) • በብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ከተመዘገቡ/ማራጋገጫ ከጨረሱ ቡሀላ ወደዋናዉ የምዝገባ ፖርታል ገብተዉ ፎርሙን መሙላት እንዳይረሱ • ከ11 ዓመት ጀምሮ ያለ ማንኛውም ታለንት ያለው ኢትዮጵያዊ መሳተፍ ይችላል - ምዝገባው የሚቆየው እስከ ግንቦት 8 • ሰመር ካምፑ በ6 ዩኒቨርሲቲዎች ይካሄዳል፡ 1) አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 2) ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ 3) ሀረሚያ ዩኒቨርሲቲ 4) ጅማ ዩኒቨርሲቲ 5) ደብረብርሀን ዩኒቨርሲቲ 6) ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ • በሳይበር ደህንነት፣ ዴቨሎፕመንት፣ ኢምቤድድ ሲስተም፣ ኤሮስፔስ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ላይ ፍላጎት እና ተሰጥኦ (Talent with passion) ያላቸው • የተቋሙን ፈተና/ቻሌንጅ ማለፍ የሚችሉ • አዲስ ነገር የመማር ፍላጎት እና ተግባራዊ ስራ ላይ የመሳተፍ ፈቃደኝነት/ዝግጁነት • ችግር ፈቺ እና በራስ የመስራት/የመማር ማይንድሴት ያላቸው • የስነ-ምግባር ችግር የሌለባቸዉ የስልጠና ዘርፎች • ሳይበር ደህንነት • ሶፍትዌር ልማት • Embedded Systems • Aerospace • Emerging Technologies በምዝገባዉ መሳተፍ የማይችሉ/የማይመለከታቸዉ 1. በሳይበር ደህንነት እና ተዛማጅ ዘርፎች ላይ ፍላጎት እና ታለንት የሌላቸዉ 2. በኢመደአ የ4ዙር የሰመር ካምፕ/ፕሮግራም የተሳተፉ ድጋሜ መመዝገብ አይቻልም ⚠️ ማሳሰቢያ፡ ፎርሙ ስትሞሉ ሙሉ በሙሉ በAI የተፃፈ ይዘት መጠቀም አይፈቀድም። ከአንድ ጊዜ በላይ መሞከር ከምዝገባዉ ሊታገዱ ስለሚችሉ። 🎯 ተሳታፊዎች በINSA የመስራት እድል ፣ የስታርታፕ እድል እና ሌሎች ተጨማሪ እድሎች ተጠቃሚ ይሆናሉ 👉 ለመመዝገብ: https://ctc.insa.gov.et/registration 📌 Registration Requirements – INSA Cyber Talent Challenge 2026 • Registration must be completed using a National ID (except for foreign nationals). • After completing National ID verification/registration, applicants must proceed to the main portal and complete the application form. • Any Ethiopian citizen aged 11 years and above with talent and passion is eligible to apply. . Registration Deadline ⏰ May 17 • The summer camp will be hosted at the following universities: 1. Addis Ababa Science and Technology University 2. Bahir Dar University 3. Haramaya University  4. Jimma University 5. Debre Berhan University 6. Wolaita Sodo University Preferred Fields/Streams Applicants should demonstrate interest, talent, and passion in areas such as: • Cybersecurity • Software Development • Embedded Systems • Aerospace • Emerging Technologies Selection Criteria Applicants should: • Successfully pass the INSA’s selection test/challenge • Be willing and ready to learn new skills and participate in practical activities • Have strong problem-solving ability and self-learning discipline • Maintain good ethical behavior and discipline ❌ Individuals Not Eligible for Registration 1. Applicants who do not have genuine interest, passion, and talent in Cybersecurity and related technology fields. 2. Individuals who previously participated in the 4-round INSA summer camp/program are not eligible to register again. ⚠️ Important Notice: Submitting fully AI-generated responses in the application form is strictly prohibited. The system only provides a one-time warning and will not tolerate repeated attempts. Continued violations may result in automatic disqualification from the registration process. 🎯 Benefits for Participants Selected participants may gain access to: • Employment opportunities at INSA • Startup and innovation opportunities • Additional training and career development benefits 👉 Registration Portal: https://ctc.insa.gov.et/registration ©: INSA

  • видео или голосовое, без подписи

  • 7 мая5131из tikvahethiopia

    የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የማስተማር ስነ-ዘዴ ስልጠና ላልጨረሱ መምህራን የደረጃ እድገት እንዲሰጥ ፈቀደ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ፣ የማስተማር ሙያ ስልጠና (PGDT) ባለመውሰዳቸው ወይም ባለማጠናቀቃቸው ምክንያት የደረጃ እድገታቸው ተቋርጦ ለቆዩ መምህራን፣ ከጥር 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የደረጃ እድገት እንዲሰጥ መወሰኑን አስታወቀ። ቢሮው ለሁሉም ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች በጻፈው ደብዳቤ እንደገለጸው፤ የትምህርትን ጥራት ለማረጋገጥ መምህራን በሙያ ስልጠና መታገዝ ቢኖርባቸውም፣ በተለያዩ ምክንያቶች ስልጠናውን ሳይወስዱ በመቆየታቸው የደረጃ እድገታቸው ተቋርጦ መቆየቱን ገልጿል። ቢሮው የትምህርት ሴክተሩ ለየትምህርት ደረጃው የተዘጋጀውን ፕሮፋይል እና ብቃት የሚያሟሉ መምህራንን በማፍራት ለዜጎች ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት የተለያዩ ስልጠና መርሃ-ግብሮችን በመቅረጽ እየተገበረ መሆኑ ገልጿል። ከነዚህም መካከል በቅድመ ሥራ እና በሥራ ላይ የሚሰጥ የማስተማር ስነ-ዘዴ ስልጠና (PGDT) ሲሆን የስልጠናውን አሰጣጥ ከመምህራን ደረጃ እድገት ጋር ተያይዞ በተለያዩ ምክንያቶች መዘግየቱን ጠቅሷል። በእዚህም ምክንያት ያልሰለጠኑ መምህራን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄድ እንዲሁም ስልጠናው ከተጀመረበት ጊዜ በኋላ የደረጃ እድገት ጊዜያቸው እና ስልጠናው የሚፈጀው ጊዜ አለመጣጣም መፍጠሩን በደብዳቤው ተገልጿል። በዚህ አዲስ መመሪያ መሠረት የደረጃ እድገት ተጠቃሚ የሚሆኑት መምህራን በአራት ዋና ዋና ዘርፎች ተከፍለዋል ፡- 1. በዲግሪ ተመርቀው በስራ ላይ እያሉ የማስተማር ስነ-ዘዴ (PGDT) ስልጠና ያልጀመሩ ወይም ያላጠናቀቁ መምህራን። 2. በመጀመሪያ ዲግሪ እያስተማሩ ነገር ግን በዲፕሎማ የሙያ ማረጋገጫ ያላቸው መምህራን። 3. በማንኛውም የትምህርት አይነት ተመርቀው በስራና ተግባር ትምህርት ላይ የተሰማሩና በዲፕሎማ የማስተማር ሙያ የሰለጠኑ። 4. በአፕላይድ ሳይንስ ቀጥታ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው በማስተማር ሙያ ስልጠና ያልወሰዱ ሆነው በተከታታይ ዓመታት በማስተማር ሙያ ላይ የነበሩና የቀጣይ የደረጃ እድገት የሚጠባበቁ መምህራን ናቸው። ቢሮው አክሎም፣ እነዚህ መምህራን ከጥር 2018 ዓ.ም ጀምሮ የደረጃ እድገት እንዲሰጣቸው ቢወሰንም፤ በቀጣይ የሚኖራቸው የደረጃ እድገት ግን የግድ የPGDT ስልጠናን ወይም ተመጣጣኝ የሙያ ስልጠናን ማጠናቀቅ ላይ የተመሰረተ እንደሚሆን አሳስቧል። የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አሊ ከማል መሐመድ በፈረሙበት በዚህ ደብዳቤ ላይ፤ አፈጻጸሙ በተጠቀሱትን መስፈርቶች፣ የአገልግሎት ዘመን እና የስራ አፈጻጸም ውጤት መሠረት ያደረገ መሆን እንዳለበት ተገልጿል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ሚያዚያ 29 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

  • видео или голосовое, без подписи

  • 10 авг. 2025 г.1 440из tikvahethiopia

    የ2018 ዓ/ም የትምህርት ጊዜ ሰሌዳ ምን ይመስላል ? የትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ የ2018 ዓ/ም የትምህርት የጊዜ ሰሌዳን ለክልል ትምህርት ቢሮዎች አሳውቋል። ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተገኘው መረጃ ትምህርት ሚኒስቴር በላከው የዓመቱ የትምህርት ካላደር ፦ - እስከ ነሐሴ 30/2017 ዓ/ም የአዲስ እና ነባር ተማሪዎች ምዝገባ ይካሄዳል። - መምህራን በትምህርት ቤታቸው ተገኝተው ሪፖርት የሚያደርጉበት ጊዜ ነሐሴ 19/2017 ዓ/ም ነው። - መስከረም 5/2018 ዓ/ም የመጀመሪያው ቀን የመጀመሪያ መደበኛ ትምህርት ክፍለ ጊዜ (day one class one) የሚጀምርበት ቀን ነው። - ከጥር 18 እስከ ጥር 22 / 2018 ዓ/ም የአንደኛ ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና የሚሰጥበት ነው። ከጥር 25 እስከ 29 ትምህርት ቤቶች ዝግ ይሆናሉ። - የካቲት 2/2018 ዓ/ም የሁለተኛ ሴሚስተር መደበኛ ትምህርት ይጀምራል። - ከሰኔ 1 እስከ 5/2018 ዓ/ም የ6ኛ ክፍል የአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ክልላዊ ፈተና ይሰጣል። - ከሰኔ 8 እስከ 12/2018 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል የመካከለኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና ይሰጣል። - የሁለተኛ ሴሚስተር ፈተና ከሰኔ 15 እስከ 19/2018 ዓ/ም ድረስ ይሰጣል። - የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 15 እስከ ሰኔ 26/2018 ዓ/ም ድረስ ለመስጠት ታቅዷል። (የ2018 ዓ/ም የትምህርት ጊዜ ሰሌዳ ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ) #TikvahEthiopiaFamily @tikvahethiopia

  • የተፈታኞች መብትና ግዴታ ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብና ሥርዓት  አከባበር እንዲሁም የመልስ ወረቀት አጠቋቆርና   ተዛማጅ ሁኔታዎችን አስመልክቶ በሚሰጡ ገለፃዎች ላይ የመሣተፍ ግዴታ አለበት። ተፈታኙ በገለፃው ላይ ባለመሳተፉ ምክንያት በፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ለሚያጋጥመው ችግር ኃላፊነቱን ይወስዳል። ተፈታኙ/ኟ የሰራበትን የመልስ ወረቀት ለፈታኙ በመስጠት  የጥያቄ ወረቀቱን ይዞ መውጣት ይችላል ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ጥያቄዎቹን መስራት ከመጀመሩ በፊት በፈተና የመልስ መስጫ ወረቀት ላይ የግል መለያ መረጃዎችን በሙሉ ግልፅ በሆነ ሁኔታ በቅደም ተከተል ጽፍ ማጥቆር ይኖርበታል (በተለይ የመለያ ቁጥር እና የትምህርት አይነት ኮድ)። ማንኛውም ተፈታኝ የራሱን ችሎታና ዕውቀት ተጠቅሞ መስራት ይጠበቅበታል፡፡ የሚሠራባቸው የጥያቄና የመልስ መስጫ ወረቀቶች ለሌሎች ተፈታኞች ዕይታ የተጋለጡ እንዳይሆኑ ሸፍኖ መስራት ይኖርበታል ማንኛውም ተፈታኝ ሞባይል፣ ካልኩሌተርና የመሳሰሉ ማንኛውንም ዓይነት  የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ይዞ ወደ ፈተና ክፍል መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው ። እያንዳንዱ ተፈታኝ ይህንን አውቆ በቅድሚያ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ። ይህንን ባለማድረጉ ምክንያት በፈተና አሰጣጥ ዙሪያ ለሚያጋጥመው ችግር ተፈታኙ  ራሱ ኃላፊነቱን ይወስዳል። ማንኛውም ተፈታኝ በመፈተን ላይ እያለ ፈተናውን እንዳይሠራ የሚያውኩ ሁኔታዎች ቢያጋጥመው በፈታኙ ሲፈቀደለት ችግሩን በመግለጽ አስፈላጊውን እርዳታ ማግኘት ይችላል ይሁንና በማንኛውም ምክንያት ለባከነ ጊዜ ተጨማሪ ሰዓት አይፈቀድም ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ከሚጀመርበት ጊዜ ተኩል ሰዓት /30 ደቂቃ/ ቀደም ብለው ከመፈታኛው ቦታ በመገኘት መቀመጫቸውን መያዝ አለባቸው። ፈተናው ከተጀመረ ከ15 ደቂቃ በኋላ የሚመጣ ተፈታኝ ወደ ፈተናው አዳራሽ መግባት አይፈቀድለትም። ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ፈተናውን ሠርቶ ቢያጠናቅቅም እንዲወጣ አይፈቀድለትም። ይሁን እንጂ ፈተናው ከተጀመረ ከ45 ደቂቃ በኋላ ከፈተና አዳራሹ ለመውጣት   እንዲፈቀድለት ሲጠይቅ የመልስ ወረቀቱን ለፈታኙ አስረክቦ በጸጥታ እንዲወጣ ይፈቀድለታል። ፈተናው ሊጠናቀቅ ከ10 ደቂቃ ያነሰ ጊዜ ሲቀረው የሚጨርስ ተፈታኝ የሁሉም ተፈታኞች የመልስ ወረቀቶች እስኪሰበሰቡና ለፈተናው የተፈቀደው የጊዜ ገደብ አብቅቶ እስኪደወል ድረስ በቦታው ተቀምጦ እንዲቆይ ይደረጋል። ፈተናው በሚሰጥበት ጊዜ ማንኛውም ተፈታኝ ትክክለኛ ያልሆነ የተቀደደ ወይም የተበላሸ የፈተና ጥያቄ ጥራዝ ከገጠመው ወይም የተሰጠው የመልስ ወረቀት የተበላሸ ከሆነ ወይም በራሱ እጅ ቢበላሽበት እጁን አንስቶ በመጠየቅ ሲፈቀድለት ሊያስቀይር ይችላል። ለተፈታኞች የተፈቀዱ እርሳስ የቀን ተማሪዎች የደንብ ልብስ (UNIFORM) ADMISSION CARD ላጲስ፣ መቅረጫና ማስመሪያ ለተፈታኞች የተከለከሉ ስልክ ይዞ መግባት አይቻልም ካልኩሌተር የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ሰዓት በሀኪም ከታዘዘ ውጪ የሆኑ መነጽሮች የሚነበቡ ጽሁፎች በሙሉ የፈተና ኦረንቴሽን ቀን የ8ኛ ክፍል በ2/10/2017 እና የ6ኛ ክፍል በ9/10/2017 ዓ፣ም ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ 8ኛ ክፍል ሰኔ 3 እና 4 /2017 ዓ.ም 6ኛ ክፍል ከሰኔ10-12/2017 ዓ/ም ይሆናል

  • የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ መልስ መስጫ ወረቀት አጠቃቀም መመሪያ ለተማሪዎች፣ ➊ የተማሪዎች መለያ ቁጥር እና የትምህርት ዓይነት መለያ ቁጥር ለእያንዳንዳቸው በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ከላይ ወደ ታች መፃፍ አለበት፡፡ ❷ በተፃፈው መለያ ቁጥር ፊት ለፊት የተፃፈውን ቁጥር የያዘውን አራት ማዕዘን ቅንፍ (Square Bracket) ብቻ ማጥቆር አለበት፡፡ ➌ ተማሪዎች የመረጡትን መልስ ትይዩ በተሰጠው አራት ማዕዘን ቅንፍ (Square Bracket) ላይ በትክክል ማጥቆር አለባቸው፡፡ ❹ ተማሪዎች ያጠቆሩትን መልስ መቀየር ቢፈልጉ መጀመሪያ ያጠቆሩትን የአራት ማዕዘን ቅንፍ (Square Bracket) በደንብ ማጥፋት አለባቸው፡፡ ❺ በአንድ ረድፍ ከአንድ በላይ መልስ (የአራት ማዕዘን ቅንፍ/Square Bracket) ማጥቆር የተከለከለ ነው፡፡ ❻ ለመፃፍ እና ለማጥቆር ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ምንም አይነት ፅሁፍም ሆነ ጭረት ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡ ❼ ለመፃፍ ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ተፅፎ ወይም ትንሽ ጭረት እና ነጥብ ከተገኘ የመልስ መስጫ ወረቀቱ ሙሉ  በሙሉ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ❽ መልስ በሚጠቆርበት ጊዜ እርሳሱ ከተሰጠው አራት ማዕዘን ቅንፍ (Square Bracket) መውጣት የለበትም። ከወጣም በማጥፊያ ማጥፋት ይጠበቅባችኋል። ❾ መልስ መስጫ ኮርነር ላይ ያሉትን አራት ጠርዞች መንካትም ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡ ➓ ተፈታኞች የመልስ መስጫ ወረቀታቸውን በንፅህና መያዝ አለባቸው ማለትም እንዳይቆሽሽ፣ እርጥበት  እንዳይነካው፤ እንዳይቀደድ እና እንዳይታጠፍ መጠንቀቅና ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው፡፡ ⓫ በእስክሪብቶ መፃፍ አይፈቀድም። ስለዚህ እርሳስ፣ ላጲስ እና መቅረጫ አይለያችሁ ⓬ ፈተና ጨረስኩ ብሎ አላስፈላጊ የሆነ ነገር፤ ስዕል ወይም ሌላ ከጀርባም ይሁን ከፊት አይፃፍበትም። ⓭ በጣም የተቀረፀ ሹል እርሳስ በምንጠቀም ወቅት ወረቀቱ እንዳይቀደድ መጠንቀቅ አለብን።

  • የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥና የአቻ ግመታ ለማግኘት ከሙያ ብቃት ምዘና የተያያዙ መረጃዎችን ግልፅ አድርጓል። ➻ እስከ 2009 ዓ.ም መጨረሻ ባለው ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያ ዲግሪዎን ተምረው የጨረሱ ከሆነ ያለ ብቃት ምዘና የትምህርት ማስረጃዎን ማረጋገጥ ይችላሉ። ➻ በ2008 ዓ.ም የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርትዎን የጀመሩ ከሆነ፥ ዲግሪዎን ከማረጋገጥዎ በፊት የደረጃ አራት የሙያ ምዘና ማቅረብ ይኖርብዎታል። በመማር ላይ እያሉ ያገኙት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት/COC/ ተቀባይነት ይኖረዋል። ➻ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ የሚቀርቡ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬቶች ተማሪው የመጀመሪያ ዲግሪውን ለመማር ከመመዝገቡ በፊት የተጠናቀቁ መሆን አለባቸው፡፡ #ETA

  • видео или голосовое, без подписи

  • 27 мая 2025 г.8762из tikvahethiopia

    " ከቤት ኪራይ እና ከዕለት ፍጆታ ተርፎ ቤት ለማግኘት 25 በመቶ መቆጠብ አንችልም " - መምህራን 🔴 " ዘጠኝ እና አስር ዓመት የስራ ልምድ ያለው መምህር 10 ሺህ ብር ገደማ ደመወዝ ነው የሚከፈለው ! " ➡️ " መቆጥብ ለማይችሉት የኪራይ ቤት ገንብቶ ለመስጠት እየተሰራ ነው " - ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንግድ ባንክ ጋር መምህራንን ጨምሮ በከተማዋ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞችን የቤት ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለ ስምምነት ተፈራርመው ነበር። ስምምነቱ በአነስተኛ የወለድ መጠን በ25/75 የብድር መርሐ ግብር የሚከናወን ሲሆን 25 በመቶውን መንግሥት ሰራተኛ ይቆጥባል 75 በመቶ የባንክ ብድር ይቀርባል። ብድሩ በ20 ዓመታት የሚከፈል ነው። ንግድ ባንክ 120 ቢሊዮን ብድር እንደሚያቀርብም ተገልጾ ነበር። ፕሮጀክቱ 3  ዓመት የግንባታ ጊዜ አንድ አመት የብድር መክፈያ እፎይታ አለው ነው የተባለው። ነገር ግን መምህራን ይህ የተባለውን 25 በመቶ ቁጠባ የመቆጠብ አቅም እንደሌላቸው ተናግረዋል። በአዲስ አበባ የመምህራን ስብሰባ ላይ የተገኙ መምህራን " የተፈራረመው የመምህራን የቤት ቁጠባና ብድር አገልግሎት ጥሩ ቢሆንም በስምምነቱ መሰረት 25 በመቶ ቁጠባ የመቆጠብ አቅም የለንም " ብለዋል። መምህራኑ " በኑሮ ጫና ምክንያት 25 በመቶ መቆጠብ አንችልም " ሲሉ ተናግረዋል። " ዘጠኝ እና አስር ዓመት የስራ ልምድ ያለው መምህር 10 ሺህ ብር ገደማ ደመወዝ ነው የሚከፈለው ፤ ከዚህ ደመወዝ ላይ ለቤት መሥሪያ የሚሆን 25 በመቶ ሊቆጥብ አይችልም ፤ ሌላ አማራጭ ሊዘረጋ ይገባል " ሲሉ ጠይቀዋል። መምህራኑ ከቤት ኪራይና ከዕለት ፍጆታ ተርፎ  ቤት ለማግኘት 25 በመቶ የመቆጠብ አቅም እንደሌላቸው ገልጸው " ሌላ መፍትሄ ይፈለግልን " ብለዋ። ለመምህራኑ ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፥ " መምህራን ያነሷቸ የቤት ጥያቄዎች ትክክልና ተገቢ ናቸው " ብለዋል።  " መምህራን ከዚህ በፊት በነበረ ስብሰባ ያነሱት ጥያቄ ' ለቤት ግንባታ የሚውል በነፃ መሬት ስጡን ' የሚል ነበር ፤ በተጨማሪም ' የብድር አገልግሎት አመቻቹልን ' የሚል ጥያቄ ነበር በዚህም ብድሩ ተመቻችቷል " ሲሉ አብራርተዋል። " 25 በመቶ መቆጠብ የሚችሉ እንዲቆጥቡ እና 75 በመቶ የብድር አገልግሎት እንዲያገኙ የማድረግ ዕድል ተመቻችቷል " ያሉት ከንቲባዋ " መቆጥብ ለማይችሉት የኪራይ ቤት ገንብቶ ለመስጠት እየተሰራ ነው " ሲሉ ተናግረዋል። #ኢፕድ #መምህራን @tikvahethiopia

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • በኬኒያ ሀገር የሚኖር አንድ ሰውዬ ለመታከም ወደ መንግስት ሆስፒታል አቅንቶ 'X-ray' ከተነሳ በኋላ በጥሩ ጤንነት ላይ ያለች በረሮ ልቡ ውስጥ እንዳለች ይነገረዋል። ወደ ሲንጋፖር ሄዶም መታከም እንዳለበት ይነግሩታል። ታማሚውም ሪፈሩን ወደ ሲንጋፖር ሄዶ ሲታይ የታየው በረሮ ልቡ ውስጥ ሳይሆን 'X-ray' ከሚያነሳው ማሽን ውስጥ የተገኘ መሆኑን ያስረዱታል። ከዚህ ምን እንማራለን? ብዙ ግዜ የምናይበትን ነገር ሳናፀዳ፣ አሊያም የምንመለከትበት መስታወት ሳናነፃ የሌላውን እድፍ ለመናገር መቸኮል እንደሌለብን። እድፉ እኛ የምንለው ነገር ሳይሆን አስተሳሰባችን ወይም የምናይበት መነፅር መሆኑ ነው። አመሰግናለሁ!!

  • видео или голосовое, без подписи

  • በአዲስ አበባ በኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሰላም በር ትምህርት ቤት የ2ኛ ክፍል ተማሪዋን ለምን የቤት ስራ አልሰራሽም ብላ፣ልጅቷን በተማሪዎች እጇን አስይዛ ሽንቷ እስኪያመልጣት ድረስ ከፍተኛ ድብደባ የፈፀመችባት መምህር በቁጥጥር ስር የዋለች ሲሆን ከትምህርት ቤት ትባረራለች ተብሏል። "አስተማሪ ልጄን ተቆጣብኝ: ተናገረብኝ"የሚሉ ወላጆች ደጋፊ ባልሆንም፣አስተማሪ እንደሁለተኛ ወላጅ ስለሆነ የሚታየው ተማሪን መስመር የማስያዝ ግዴታ አለበት። ነገር ግን አስተማሪም ቅጥ ሊኖረው ይገባል ተማሪ እልህ እና ቁጣ መወጫ አይደለም።  እንደዚህ ያለ ከፍተኛ ድብደባ መፈፀም ነውር፣የስነልቦና ጉዳቱም ቀላል አይደለም።

  • видео или голосовое, без подписи

  • " ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ስልክ ይዘው እንዳይሄዱ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል " - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ስልክ የሚባል ነገር ይዘው እንዳይገቡ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ። የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በሚመሩት የትምህርት ዘርፍ ላይ ስለአፈጻጻምና ስለታቀዱ እቅዶች ማብራሪያ ሰጥተዋል። በሰጡት ማብራሪያም በሚቀጥለው ሳምንት ከትምህርት ቢሮዎች ጋር ውይይት እንደሚካሄድ ጠቁመዋል። በዚህም ወቅት ተማሪዎች ስልክ ትምህርት ቤት ይዘው እንዳይገቡ ለማድረግ ስለሚደረገው እንቅስቃሴ እንደሚመከር ገልጸዋል። " የጋራ ስምምነት ላይ ከደረስን ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ገብተው ትምህርት መከታተል ነው እንጂ ከስልክ ጋር የሚጫወቱበት ሁኔታ እንዳይፈጠር ይደረጋል " ብለዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia

Bethel primary school — tgindex