tgindex
መጽሐፍ ቤት Bookstores

መጽሐፍ ቤት Bookstores

Статистика
@BookstoresAZанглийский

Ask any materials @Books_storebot @Books_storebot

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
2
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
3 982
+11 за 4 дн.
Сутки
+6
+0,15%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 716
22 постов
Вовлечённость
43,1%
к подписчикам
Постов в день
0,3
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
396
1/48двое суток
453
1/72трое суток
489

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ፍቅር በአንድ ጀምበር አይሞትም። እንደ ሻማ እየቀለጠ በዝግታ ይደክማል፤ እሳቱ እያለ ብርሃኑ ይደበዝዛል። ሳራ ከባሏ ጋር ከተጋቡ ሰባት ዓመታት አልፈዋል። የመጀመሪያዎቹ ዓመታት እንደ ጸደይ ነበሩ፤ ትንሽ ቤታቸው በሳቅ፣ በህልምና በተስፋ የተሞላ ነበር። ዛሬ ግን ልባቸው ተራርቋል። ለእራት ሲቀመጡ ውይይታቸው ከሁለት አሊያም ሦስት ሐረጎች አያልፍም። "ውሃ አቀብዪኝ" "እሺ።" "ማታ አመሻለሁ።" "እሺ።" ከዚያ ዝምታ። ሳራ ሙዚቃን ትወዳለች። ሙዚቃ የልቧ ቋንቋ ነው። ስትደሰት ትዘፍናለች፣ ስታዝን ዘፈን ታዳምጣለች። ባሏ ሙዚቃ አይወድም። "ይህ ጫጫታ ምንድነው?" ይላል ሙዚቃ ሲሰማ መጀመሪያ ሳራ ተቆጣች፤ ከዚያ ለመልመድ ሞከረች። በመጨረሻ ግን ሙዚቃዋን በጆሮ ማዳመጫ ብቻ መስማት ጀመረች። እንደ ሌሎች ስሜቶቿ ሁሉ ሙዚቃንም በድብቅ.... ከቅዳሜዎች በአንዱ ከሥራ ባልደረባዋ ጋር ወደ ሙዚቃ ዝግጅት ሄደች። መካከለኛ ሬስቶራንት ነበር። የቡና ሽታ፣ የፒያኖ ድምፅ እና ዝቅተኛ ብርሃን የተቀላቀሉበት። በዚያ ሳሚን አየችው። ሳሚ በመድረኩ ላይ አልነበረም፤ ጠረጴዛ ተደግፎ ዓይኑን ጨፍኖ ሙዚቃውን ያጣጥማል። ዘፈኑ ሲያልቅ ከሁሉም ዘግይቶ በቀስታ አጨበጨበ። የሳሚ ተግባር የተለየ ምክንያት አልነበረውም፤ ነገር ግን ሳራ አስተዋለችው። ከዝግጅቱ በኋላ በቡና ማዘዣው ፊት ተገናኙ። "ይህን ዘፈን ትወጂዋለሽ?" ሳሚ ጠየቃት። "በጣም።" "እኔም። ግጥሙ ከዜማው ይልቅ ይመስጠኛል።" ሳራ በፈገግታ ተመለከተችው። ሳሚ ሳቀ። ሳራ ልቧ ደነሰ። ከረጅም ጊዜ በኋላ በጥልቀት የምታወራውን ሰው እንዳገኘች ታውቋታል። ከዚያ ምሽት በኋላ ሳሚና ሳራ አልተለያዩም፤ ይሁን እንጂ በየቀኑ የሚገናኙ ጓደኞችም አልሆኑም። የሚያገናኛቸው መንገድ ያልታሰበ ነበር። አንድ ዘፈን፣ አንድ ዘፈኑን የሚመለከት የጽሑፍ መልዕክት። "ይህን ግጥም ስሰማው አንቺን አስታወሰኝ" ሳራ መልእክቱን አነበበች። ከዚያም ዘፈኑን አዳመጠች። በግጥሙ ውስጥ ራሷን አገኘች። ... መጀመሪያ ስለ ሙዚቃ፣ ቀጥሎ ስለ መጻሕፍት፣ ከዚያ ስለ ልጅነታቸው፣ በመጨረሻም ስለ ልባቸው አወሩ.... "ምን እያነበብሽ ነው?" ባሏ ጠየቀ። "የሥራ ጉዳይ ነው።" ቃሉ ከአፏ አፈተለከ፤ ልቧ ደነገጠ። ያ የመጀመሪያዋ ውሸት ነበር። ትንሽ ውሸት። የምታነበው የሳሚን የጽሑፍ መልክት ነበር። "እንገናኝ?" ሳሚ አጭር የጽሁፍ መልዕክት ላከለት። ልቧ "አዎ" ይላል፤ ሕሊናዋ "አይ" ይላል።.... ጣቶቿ ልቧን መረጡ። "እሺ" ብላ ፃፈች። ተገናኙ! ሰው የማይበዛበት መናፈሻ መርጠው ተገናኙ! "ለምን ፈራሽ?" እንደተገናኙ ሳሚ ጠየቃት። ሳራ ሳቀች፤ ዓይኖቿ ግን አልሳቁም። ከንፈሯ ሲስቅ አይኗ ተከዘ። "ሳራ...ባለትዳር መሆንሽን አልረሳሁም።" "እኔም አልረሳሁትም።" "ታዲያ ለምን መጣሽ?" ሳራ መልስ አላገኘችም። የሳራ ሕይወት በሁለት ተከፍሏል። አንደኛው የቤቷ ሕይወት ነበር፤ ዝምታ፣ የተለመደ ኑሮ ፣ የተለመደ ግዴታ። ሁለተኛው የሳሚ ዓለም ነበር፤ ሙዚቃ፣ ውይይት፣ ሳቅ፣ እና ያልተነገረ ፍቅር። መሽቷል ፤ እየዘነበ ነበር። "ዛሬ አትሂጂ..." አለ ሳሚ በቀስታ። ሳራ ፊቱን ተመለከተች። በዓይኖቹ ውስጥ የታፈነ ስሜት ነበር። ያንኑ ስሜት እሷም ተሰማት። ቀስ ብሎ እጇን ያዘ። ሳራ እጇን አልሰበሰበችም።... ጥሳው የምትሻገረው መስመር ምን እንደሆነ ታውቃለች። ነገር ግን ከአንዳንድ መስመሮች በፊት ልብ ይራመዳል፤ አእምሮ ደግሞ ከኋላ ይከተላል። ያቺ ምሽት የሕይወታቸውን አቅጣጫ ቀየረች። ውጭ አላደሩም፥ ነገር ግን በሳሚ መኪና ውስጥ ከንፈር ለከንፈር ተጎራረሱ። ቀሚሷን ገለበ፥ ቀበቶውን ፈታችለት። ጡት ማስያዣዋን ሲያላላው አገዘችው... ከዚያ ምሽት በኋላ ሳራ እንቅልፍ ማግኘት አቃታት። የሳሚ እጅ አሁንም በመዳፏ ላይ ያለ ይመስላት ነበር። "ምን እያደረግሁ ነው?" ብላ ራሷን ትጠይቃለች። ቀናት መደበኛ ጉዟቸውን ቀጠሉ። ከሳሚ ጋር ሲሆን የምትስቀው ሳራ ፥ ከባሏ ጋር ሲሆን ግን የምታወራው ቃል እያነሰ ሄደ። በባሏ ፊት ጭምት በሳሚ ፊት ተጫዋች ሆነች። "ሳራ… ደስተኛ ነሽ?" ባሏ ድንገት ጠየቃት። ጥያቄው እንደ መብረቅ መታት። "ለምን ጠየቅከኝ?" "አካልሽ ከእኔጋ ነው፤ ልብሽ ግን ሌላ ቦታ ይመስላል" ሳራ ዓይኖቿን ዝቅ አደረገች። ለመጀመሪያ ጊዜ ባሏ የልቧን ርቀት አስተውሎ ነበር። በሳምንቱ መጨረሻ ሳሚን አገኘችው። "አንቺ ተለዋዋጭ ነሽ" አለ ሳሚ "ምን ማለትህ ነው?" "ከእኔ ደስታን ታገኛለሽ፤ ከዚያ ደግሞ ጥፋተኝነት ይሰማሻል። ይህ ለሁለታችንም ከባድ ነው።" "አንተን ማጣት አልፈልግም።" ሳሚ ፈገግ አለ፤ ግን በፈገግታው ውስጥ ሀዘን ነበር። "እኔም አንቺን ማጣት አልፈልግም። ግን እራስሽን እያጣሽ እኔን እንድታገኚ አልፈልግም።" መሽቶ ባሏ ወደ ቤት ሲመጣ ትንሽ የሙዚቃ ማጫወቻ አመጣላት። "ይህ ለአንቺ ነው።" "አንተ… ሙዚቃ አትወድም እኮ።" "አንቺ እንደምትወጂ አውቃለሁ" የሳራ ጉሮሮ ደረቀ። የሳራ ልብ በሁለት አቅጣጫዎች ይጎተት ጀመር። Via ተስፋአብ ተሾመ

  • ጎዳና አዳሪ ነበርኩ። አስፓልት ጥግ ከቦይ አጠገብ ማዳበሪያ ለብሼ ተኝቻለሁ፤ መንገድ ዳር ኖሬያለሁ። ብድግ ብዬ ከቤት ወጣሁ። እግሬ እንደ መራኝ በዘፈቀደ ሄድኩ። በ14 አመቴ የቤተሰቦቼን ቤት ትቼ ተሰደድኩ። ከቤት የወጣሁባት የመጀመሪያ ቀን የዘላለም ያህል ረጅም ነበረች። ከተማውን ሳካልል ዋልኩ። ሲመሽ አስፓልት ጥግ ተቀመጥኩ። የለበስኳት ነጭ ትሽረት በአንድ ቀን ነተበች። ብርዱ አጥንቴን ሰረሰረው። ጥርሶቼ ተፏጩ ፥ ሰውነቴ ተንቀጠቀጠ። "ያዝ" አለኝ አስፈሪ ገፅ ያለው ጎረምሳ። ቀና ብዬ አየሁት። ማዳበሪያ አቀበለኝ። ማዳበሪያውን ይዤ ፈዘዝኩ። "ልበሰው" አለኝ። ልታዘዘው ሞከርኩ። ነገር ግን አቃተኝ። ማዳበሪያ እንዴት እንደሚለበስ ግራ ገባኝ። እየሳቀ አስተካክሎ አለበሰኝ። "ምግብ በልተሃል?" "አይ" ትራፊ ሰጠኝ። ምግቡን ብፀየፍም ረሃቡ በለጠብኝ። እየፈራሁ ጥቂት ቀመስኩ፣ ሲያቅለሸልሸኝ ተውኩት። ሲጃራ አቀበለኝ "አልፈልግም" አልኩ። ማስቲሽ ሰጠኝ እሱንም አልፈልግም አልኩ። "ትለምደዋለህ። ከሳምንት በኋላ ሱሰኛ መሆንህ አይቀርም" አለኝ እየሳቀ። ማዳበሪያው ብርዱን አላሸነፈውም። ሰውነቴ ወባ እንደያዘው ሰው ይንቀጠቀጣል። "ከቤት ተጣልተህ ነው?" አለኝ እየሳቀ። እንባዬ ገነፈለ። ተንሰቅስቄ አለቀስኩ። ያለቀስኩት በረሃብና ብርዱ ምክኒያት ነበረ። "ምን ሆነሃል?" አለኝ ቤተሰቦቼ እንዴት እንደበደሉኝ ነገርኩት። ጨካኝ አባትና እናት እንዳለኝ ተረኩለት። ሲሰማኝ ከቆየ በኋላ "አይዞህ፥ አሁን ተኛ" ብሎኝ ሄደ። የሚከረፋ ቦይ አጠገብ ማዳበሪያ ለብሼ ተኛሁ። "ወላጆቼ ክፉ ናቸው" ብዬው ነበር። 15 ቀናት በጎዳና ስኖር ላገኘኋቸው የጎዳና ጓደኞቼ ቤተሰብ ያደረሰብኝ በደል ተረኩላቸው... እያስተዛዘንኩ ነገርኳቸው። ከንፈር መጠጡልኝ። እውነታው ሌላ ነበር። ከቤት ያስወጣኝ ልጅነት ነበር። ያስኮበለለኝ ጥጋብ ነበር። የሸፈትኩት በእብሪት ነበር። ነገር ግን ጥፋቴን ማመን ከበደኝ። የገዛ ጥፋቴን ከምቀበል ውሸት መፍጠሩ ቀለለኝ። ጥፋት የሌለባቸውን ወላጆቼን በሀሰት ወነጀልኩ። ሃላፊነት መውሰድ ከባድ ነው። "አጥፍቻለሁ" ማለት ቀላል አይደለም። "ብስለት ጎድሎኝ የተሳሳተ ውሳኔ ወሰንኩ" ብሎ መናገር ይተናነቃል። ሌላውን መወንጀል ቀላል ነው። ተበድያለሁ ማለት ቀላል ነው። ሃላፊነትን ማሸሽ ቀላል ነው። እንዲያ ነው... አንዳንዴ የገዛ ስህተታችንን ላለመቀበል ሌሎችን እንወነጅላለን። የውሳኔ ስህተት መስራታችንን ላለማመን ሌሎች ሰዎችን እናጠለሻለን። አንዳንዴ እንዲያ ነው..... ተስፋአብ ተሾመ

  • ስላመንኩት፥ ለሰጠኝ ፍቅር ዋጋ ስለሰጠሁ፥ እየተመቸኝ አልችልም ስለማልል፥ ስለሚወዱኝና ደጅ ስለሚጠኑ ወንዶች አያወራሁ ስለማልመጻደቅበት ... እኔን የማግኘት መጓጓቱ ቀነሰ ጥፋቱ ላይ ስለማላተኩር፥ ቅሬታዬን ስለማላሳየው፥ በልቤ ከሌሎች ጋ ስለማላወዳድረው...የማይገባኝ መሰለው! ቅር ይለዋል ብዬ የማስበውን ስለማላደርግ፥ ቅድሚያ ስለምሰጠው፥ ስለምወደው ዋጋዬ አልገባውም። እየተወኝ ሁኔታው ሁሉ ውለታ እንደዋለ ነው። እየበደለ ውለታ ዋልኩ እንደሚል ሰው ክፉ የለም! ክፉ አለመሆኔን እንዴት እንዳለማወቅ መቁጠር ተቻለው?! ረስቶት ነው..!? እንዴት አድርጎ ቀልቤን ለመግዛት እንደደከመ። ረስቶት ነው እንዴት አድርጎ ደጅ ጠንቶ እንደቀረበኝ። ረስቶት ነው እንዴት አንቆለጳጵሶ እጁ እንዳስገባኝ... ሲያገኘኝ እና ሳገኘው የነበረውን ሁኔታውን ሁሉ ዘንግቶታል! ሰነፍ እንዲህ ነው....በእጁ የያዘው ውድ አይመስለውም !! ሰነፍ እንዲህ ነው ... የሚደረግለት ካልተነገረው አይገባውም !! ሰነፍ እንዲህ ነው ... ሲቆጠርበት አያይም !! ሰነፍ አንዲህ ነው ... የሚፈልገውን ሲይዘው ያንስበታል !! ሰነፍ እንዲህ ነው ... መከተል እንጂ ማስከተል አይችልበትም !! ሰነፍ እንዲህ ነው ... ደስታው ያለው ሽምያ ውስጥ ነው !! እኔ እና ልቤ ግን ታዝበነዋል!! © Adhanom Mitiku

  • 24 июл.1 502214

    “ምነው አምና በሞትኩ፥ እንዲያ እንዳማረብኝ!?” ዝምታ  ይረብሸኛል። ለዚያም ነው፥ መንገድ ስሔድ መጽሐፍ ይዤ  የምዞረው፣ ሁሌም ጆሮዬ ውስጥ ‘ኤርፎን’ የምወትፈው፣ ልተኛ ስል፥ ያለችውን ፀጥታ እንኳን ላለማስተናገድ፥ የኾነ ነገር ከፍቼ ነው የምተኛው ... በዝምታ ውስጥ ከመኾን፥ ዝም ብሎ ከሚቀደደው ቱሪናፋው ከቤ ጋር ብውል እመርጣለሁ። ዝምታ ሽሽት የማልደውልበት፣ የማላነበው፣ የማልሰማው ዜና የለም። ዝምታ እፈራለሁ! መንገድ ስሔድ… ስቀመጥ! የማነበው መጽሐፍ ካልያዝኩ፣ ስራመድ የምሰማበት ኤርፎን ካልወተፍኩ…. ፖሊሶች አቻኩለው ከቤት አስወጥተውኝ ነው የሚሆነው! ዝምታ እፈራለሁ! አስታውሳለሁ፤ 12ኛ  ክፍል ነበርኩ። ሙዚቃ ከፍቼ እያጠናሁ፥ የአጎቴን የለቅሶ ሳግ ሰምቼ ደንግጬ “ምነው አመመህ?”  አልኩት፤ እሱ ሙዚቃ እየተጫወተበት ያለውን ‘ቴፕ’ ዐየት አድርጎ፥ ወደ ጣርያው አፍጥጦ፣  እምባው ቁልቁል ወረደ! አሞት መስሎኝ ነበር… ከዚህ በፊት ሲያመው ያቃስታል፤ ሲብስበትም ማስታገሻ ይውጣል እንጂ አያለቅስም ነበር። አጎቴ ጥቁር ነው፤ ፊቱ ክስክስ ያለ… ሲያወራ ግን እንደሚታየው ኮስተር ያለ ማንነት  እንደሌለው የሚያስታውቅበት፥ ቁጥብ፣ ደስ የሚል ሰው ነው። ልጅ እያለሁ የገዛልኝን ቼኮሌት እና ብስኩት፥ ታሞ አልጋ ሲይዝ ሲጋራ እያመጣሁ ክሼዋለሁ ። ቤቢ፥ “ያቺን ነገር አትገዛልኝም?” ይላል፤ እገዛለታለሁ። ሲጋራውን በእጁ እያገላበጠ ካያት በኃላ፥ አፉ ላይ እንዳለ እለኩሰለታለሁ። ዐብሮን ማንም በሌለበት ጊዜ ሁሉ፥ “አትብላ” የተባለውን፣ “አትንካ” የተባለውን ሁሉ እሰጠው ነበር። እያጠናሁ ስለነበረ፣ ሲያለቅስ አይቼው ስለማላውቅ፣ ደንግጬ ስለነበረ፣… ዘፋኟን ባውቃትም ግጥሙን አላጤንኩትም ነበር፤ ዘፈኑ እንደረበሸው ሲገባኝ፥ ወተት እንደገነፈለበት ሰው፥ ስበር ሔጄ የቴፑን ሶኬት ነቀልኩለት ። የማባብልበት መንገድ ስለጠፋኝ፥ “ምግብ ላምጣልህ?”፤ “ውሃ ላምጣ”  አልኩት። ጣርያ ጣርያ ዕያየ ዝም ሲለኝ  ከፊቱ ዞር አልኩለት። በዚያው ሰሞን፣ ሲብስበት ሐኪም-ቤት ደግመው አስገቡት፤  አልቆየም፤  ሞተ! የኾነ ቀን ... አባቴ፥ ስለወንድሙ ቸርነት፣ ዘናጭነት፣ ስፖርተኛነት፣ ሰው ወዳድነት፣ አለኝታነት፣ ስለጓደኞቹ ብዛት፣… ሲተርክልኝ ያስለቀሰቺው ዘፋኝ፥ የዝና ነጋሽ ትዝ አለቺኝ። ያስለቀሰውን  የዘፈን ካሴት ከፈትኩት፤ ሆዱን ያባባው “ገዳሙ” ዘፈን  ጋ ደረስኩ።   እስክስታ ሚያስመታ ‘ሪትም’ ያለው ዘፈን ነው “.........አሆዬ እኔ ላንተ ብዬ፣ መጣሁኝ ጠቅልዬ አዬዬ፥ እኔ ላንቺ ብዬ፥ መጣሁኝ ጠቅልዬ “እሀሀ ገዳሙ፥ አሀሀ ገዳሙ እሀሀ ገዳሙ፥ አሀሀ ገዳሙ “አላስኬድ፣ አላስኬድ አለኝ፥ ይሄ ጫማ እኔም ልበቢስ ነኝ፥ ቢመክሩኝ አልሰማ “እሾህ ብቻ ኾኖ፥ እግሬን ብዳብሰው እንዴት መራመጃ፥ መሔጃ ያጣል ሰው? “ኧረግ እናናዬ፣ አረግ እናናዬ ኧረግ እናናዬ፣ አረግ እናናዬ “አሄ አሄ አሄ አሄ አሄ ኡሁ “ይወዘውዘኛል፥ ይወዝውዝ አባቱ እህል አሸክሞኝ አርጎኝ ጎረቤቱ አሞኝ፣ አሞኝ ውሎ፥ አሞኝ ሊያድር ነወይ? እህል ሰርቶ መብላት፥ ጤና ላይሆን ነወይ? “ምነው አምና በሞትኩ፥ እንዲያ እንዳማረብኝ መለየት በሽታ፥ እንዲ ሳይጠናብኝ “ያመኝ የነበረው፥ አያመኝም ተውኩት ያስታማሚ ነገር ሲቸግር አየሁት “እህህህ ገዳሙ ጠይሙ፣ ጠይሙ..........” ይላል ከዛ ቀን በኋላ፥ ተረጋግቼ ሥራዬ ብዬ ሰምቼው ዐላውቅም፤ ነገር ግን ሁሉም ስንኞች ልቤ ውስጥ በአግባቡ  ከመሰነድ አላዳነኝም ድንገት ከተከፈተ፥ የሚረብሸኝ ዘፈን ኾነ .... “ድል ስቀዳጅ፣ ደስ ብሎኝ ስጠጣ፣ እንዳማረብኝ ግደለኝ አስታማሚ ሳታሳየኝ!” ማለት ጀመርኩ። “ያደረ የዋለ በሽታ አትሰጠኝ” እለው ጀመር “ይህ ዘፈን ምን ያህል ይረብሽሃል?” ስባል “ከዝምታ በላይ!” ማለት ጀመርኩ። የግጥሙ ኀይል ነው፥ ወይስ የአጎቴ ኹኔታ ሕይወትን እንድፈራት ያደረገኝ? ሕይወትን ምን ያህል ባካብዳት ነው፥  እያሸነፍኩ እንኳን “ምነው አምና በሞትኩ፥ እንዲያ እንዳማረብኝ…”  የምትል ስንኝ  የምታሳድደኝ? ፈሪ ሰው እንዲህ ነው፤  ከ ጠ’መንጃ በላይ ፥ ቃል ያሳድደዋል! ©  Adhanom Mitiku

  • 23 июл.1 1306

    ወጣቶች ነበርን በእውቀቱ ስዩም ጊዜ ሲራመድ ኮቴው ድምጥ አልባ ከየት ተነስቶ ወደ የት ገባ ከየት ተነስቶ ወዴት ደረሰ ጠጉር መንጥሮ፣ ፊት እያረሰ፤ ወጣቶች ነበርን ቅጽር የሰራን ፤ አምባ የሰበርን ኮካ ኮላውን ባሲድ በርዘን ብንጎነጨው፤ የማይመርዘን፤ በራዱን ያጋልን፣ ሙት ልብ ያስነሳን ግራዋ በልተን ፤ ሎሚ ያገሳን፤ ተስፋችን ብዙ፤ እድሚያችን ለጋ ስንሰማራ፣ ትርጉም ፍለጋ ገላችን አይፈዝ፣ ጭቃ ቢለሰን የማናስቀይም፤ ቡትቶ ለብሰን ገጻችን ብሩህ፤ ልባችን ሽፍታ ስንመነጠቅ፤ ወደ ከፍታ የስኬት ገነት፣ ደጃፏን ከፍታ ምትቀበለን ፣ እየመሰለን ከቁመታችን በላይ፣ የዘለልን፤ ወጣቶች ነበርን ዛሬ እንደዋዛ ዘንድሮን ምሰን፤ ታችአምናን ቀበርን፤

  • 18 июл.1 48884

    "ለምንድነው ድንገት የተውከኝ አለቺኝ ?" "እኔ'ንጃ ምን አልባት ፈርቼሽ ይሆናል"። በአይኗ እየተቅለሰለሰች "ምኔ አስፈራህ ትባ'ላለች አሉህ ወይ " ጥቁረቷ የዐይኗን ውበት ጨምሮታል ጥቁረቷ ጥርሷን ጥርሰ በረዶ ናት እንድትባል ያደረጋት ይመስለኛል። ስታምር ! ትክ ብዬ እያየኋት "የመወደድ ርኃብ ያለብሽ ይመስላል "አልኳት ምን ማለት ነው ?? "የሚወደኝ አጥቼ ማለት ነው? " ሳቀች አሳሳቋ ፌዝ አዝሏል አይምሰልሽ የአንዳንድ ርሃብ ምንጭ እኮ የአቅርቦት እጥረት አይደለም የአስተዳደግ ጠባሳም ሊሆን ይችላል። ቀጠሮ ኖርበት የክት ልብሱን አጥቦ ፀሃይን እንደሚጠብቅ ሰው ነው ቀልብሽ ቆሌሽ ሁሉ ነገርሽ መወደድሽን የሚጠብቀው .... እመኚኝ ቲጂ ማስከተል ለምደሻል ... ፍላጎት አምጠሽ ፣አስወልደሽ ፣አሳድገሽ እንዳላወቀ ድንግጥ ብለሽ እንዴት እንደዚህ ሊሰማ ቻለ !? ብለሽ መካድ ለምደሻል ! . ለመወደድ ምቹ ሆኖ ጠዋት ማታ ከለፉ በኃላ በዚህ መንገድ አላሰብኩም ብለው ከሚያለግጡት ውስጥ ነሽ ከልብ ያሆነ ፈገግታ ፊቷ ላይ ብርት ብሎ ጠፋ ....."ያንተ ጠላት አንተ ነህ መታገስ ሲያቅትህ ለመሸሽ የሰጠህኸው ሰበብ ነው ግርማ እመነኝ የማጣት ፍርሃት አለብህ ...." አይ ቲጂ እኔ የማቃጥለው ትርፍ ግዜ የለኝም !! የመታኝን አይነት እንቅፋት እንዳየሁት ነው የማውቀው ከነ ህመሙ ነው የማስታውሰው እኔ የሰው trauma ማከም አቅም ላይ አይደለሁም ...! አሁን ባላሁበት ሁኔታ አልችልሽም ያሸሸኝ የአቅም ጉዳይ ነው ... መንገድሽን ዞር ብለሽ እይው ሲርቁሽ የምትከትየው እና ሲቀርቡሽ የምትርቂው ርቀት ተመሳሳይ ይመስለኛል ፈራሁሽ !! እንዳንቺ አይነት ሰዎች እንደተወደዱ ካረጋገጡ በኋላ ቀስስ ብለው ከሪትሙ ይወጣሉ ለመወደድ ያደረጉት የከፈቱትን ሁሉ ዝግትግት ያደርጋሉ ... Look ... መጀመርያ ሰሞን እምቶኝልኝ ነገር ሁሉ እንደእጮኛሽ ነው ፣ የመጀመርያ ሰሞን የምታወሪበት ድምፅት እንኳን የለም ። እንክብካቤሽ፣ መንገድ ስንሄድ ሽጉጥ የምትይብኝ ፣መውድድሽ በየምክንያቱ ማክበርሽን በየስበቡ የምታሳይኝ ነገር ሁሉ ራሱን አጥፍቷል። የመንገደኛን ኮቴ መከተል አልችለም ትኩረቴን የሚሻ ህልም አለኝ የኔን ግዜ የሚፈልግ ሌላ ትግል አለኝ። "በኔ አታሳብ ግርምሽ ቶሎ መወደድ ለምደህ ነው!! ሳጠይቅ ማግኘት አበላሽቶህ ነው!! ሳትበረታ ላጣኸው ሁሉ ያንተ ጥፋት እንዳልሆነ ለጭንቅላትህ መንገር ለምደህ ነው ።ድክመቱን ሁሉ የሰው ችግር አድርጎ እንደሚተነትን የሚያሳዝነኝ የለም ።" ቲጂዬ እውነትሽን ነው አቅም ስለሌለኝ ነው የሸሸሁት። ከማልችለው ጋ ምን አታገለኝ ብዬ ነው !! አንቺ ደሞ ሁኔታሽ ሁሉ እንደወፍ ነው ሲከተሉሽ ትበርያለሽ ስረጋጋ ስቆም መጥተሽ አናቴ ላይ ትወጫለሽ ደስታ ሊያስደንሰኝ ሲጀምር ትበርያለሽ ... እንደቅድሙ አልሳቀችም .... "ዳንስ መቼ ትችል እና ...ይልቅ ግርምሽ ሪስክ የማይወስድ ሰው አልወድም ፣ የተበላሸ ነገር ለመስራት የማያቅድ ወንድ ፤ የተሰራ ነገር የሚያሳድድ ሰው ያሳዝነኛል በተለይ ወንድ ...." ካንቺ ባላቅም ....! ጀግና የሚያተርፈውን ሳያሰላ አይታገልም ። ጀግና ሁኔታን እና ዋጋን አስልቶም ይሸሻል እስከማውቀው .... አለም ላይ የመወደድ ርሃብ ካለበት ሰው ጋ እንደተጣበሰ ፣ እንደተጋባ የሚያሳዝነኝ የለም ... ጠዋት ማታ ሥራ አለበት፥ ማባልል አለበት፥ ውድድር አለበት ኑሮ ሁሉ ሪሲሊንግ በይው...ዋንጫ ሜዳልያ የማይበላበት ሪሲሊንግ "ማንም እንዲ ብሎኝ የትኛውም ወንድ አንተ ባልከው መንገድ ተረድቶኝ አያውቅም !" ይሆናል .....እኔ ግን አንተ ብቻ ነህ ያመለጥከኝ እንዳልሺኝ ነው የምቆጥረው !! © Adhanom Mitiku

  • 12 июл.1 5548

    "እናቴ ሦስቴ አግብታ ሦስቴ ፈታለች። ከእህቴ እና ከወንድሜ ጋር አባት እንደማንጋራ ታውቂያለሽ። እናቴ አዲስ ሕይወት በጀመረች ቁጥር በትዳሯ እንደምትፀና የምትወራረድ ቢሆንም፣ አዲሱ ሕይወት ብዙም ሳይቆይ መዝመም ይጀምርና የመጠገን እድልን ሳያገኝ ይፈርሳል።ይህ እንዴት ሆነ?›› ‹‹እርግማን ላይሆን ይችላል›› ‹‹ወንድሜ ለትዳር ምንም አይነት መጓጓት እንዳልነበረው ታውቂያለሽ... እማማና ዘመዶቿ ወትውተውት ካገባ በኋላ በሦስት ዓመቱ ተፋታ። ከትዳሩ መፍረስ በኋላ ለገዛ ልጁ እንኳን ግድ የለሽ ሆኖ የተገለለ ኑሮ እየገፋ እንደሆነ ታውቂያለሽ።... ይህ እርግማን አይደለም?›› ‹‹እርግማን ላይሆን ይችላል›› ‹‹እህቴ ቁጥብ እና በራስ መተማመን ያላት ሴት እንደነበረች መመስከር እንደምትችይ አውቃለሁ። ስለ መልኳ ሁሉም ሰው ይናገራል። መብራት ከተማ ውስጥ የእህቴን ያህል ቆንጆ ማግኘት እንደማይቻል እወራረዳለሁ፡፡ ትዳር ከመሠረተች በኋላ ግን ሕይወቷ ተመሳቀለ። የወለደችው ልጅ ጡት ሳይጥል ትዳሯ ፈረሰ። በዚህ የተነሳ ማንንም ማመን የማትችል፣ በራስ መተማመኗን ያጣች ሆናለች። በሃዘኗ ብርታት የተነሳ ውበቷ ከድቷታል። የተሰበረች ሴት ነች... ይህ እርግማን አይደለም?›› ‹‹እርግማን ላይሆን ይችላል›› ‹‹የእኔን ታሪክ ታውቂዋለሽ። የፍቅር ሕይወቴ በመለየት ይደመደማል። ጀመርኩ ስል ይቋረጣል። የገነባው ሲመስለኝ ይፈርሳል። አንዴ አይደለም። በተደጋጋሚ እንጂ!.... ይህ እርግማን አይደለም?›› ‹‹እርግማን ላይሆን ይችላል›› ‹‹ስለ አያቴ የትዳር ሕይወት ነግሬሽ አውቃለሁ?›› ‹‹ነግረሽኝ አታውቂም›› ‹‹የእማዬ እናት አራቴ አግብታ አራቴ ፈታለች›› ‹‹ይህን አላውቅም ነበር›› ‹‹የእናቴ ታናሽ እህት ሁለት ጊዜ ትዳር መስርታ ሁለት ጊዜ ትዳሯ ፈርሷል፡፡ ሁለቱ ልጆቿ ከሁለት ባሎች የተገኙ ናቸው፡፡ ይሄ ያለጥርጥር የዘር እርግማን ነው›› ‹‹እርግማን ላይሆን ይችላል›› ‹‹ከአያቴ ጀምሮ እስከ እኔ ድረስ ታሪካችን ተመሳሳይ የሆነው በአጋጣሚ አይደለም። በእርግጠኝነት ከዘር የሚተላለፍ የቤተሰብ እርግማን አለብን›› ‹‹እርግማን ላይሆን ይችላል›› ‹‹ገደል ግቢ›› ‹‹ንፁህ ሙች እርግማን አይደለም›› ‹‹ገደል ግቢ አልኩኮ›› ከ #የዙፋን_ልፊያ መጽሐፍ የተወሰደ ደራሲ ተስፋአብ ተሾመ አሳታሚና አከፋፋይ ጃፈር መጽሐፍት

  • 11 июл.1 4662310

    ኦሮማን (በእውቀቱ ስዩም) ሰሞኑን እንደ አዲስ አስቴር አወቀን ሳደምጥ፣ በአሉ ግርማ ትዝ አለኝ፤ የበአሉን ኦሮማይ ታስታውሱታላችሁ ? ፀጋየ ሀይለማርያም ጋዜጠኛ ነው፤ ሮማን የተባለች ውብ ኩሩ እጮኛ አለችው፤ ሊጋቡ ጥቂት ወራት ሲቀራቸው በቀይ ኮከብ ጥሪ አስመራ ለግዳጅ ተላከ፤ በዚያም በዘመቻው መሀል ፊያሜታ የተባለች ያስመራ ሴት ተዋወቀ፤ ከባድ ፎንቃ ገባለት፤ ባስመራይቱና በሸገሪቱ ሴቶች ፍቅር መሀል ተወጥሮ በታሪካዊው ዘመቻ ላይ ተሳተፈ ፤ በመጨረሻ ሮማን አስመራ መጥታ ከሌላ ሴት ጋር ፍቅር አንደያዘው ተረዳች፤ ፊያሜታ ለሱ ብላ ህይወትዋን ትሰጣለች፤ በመጨረሻም ፊያሜታን በሞት ሮማንን በቅያሜ አጥቶ አጥቶ ብቻውን ሲቀር ልቦለዱ ይጠናቀቃል፤ ሮማን አዲስአበባ ሆና የአስቴር አወቀን ክር ካሴት ልካለት ነበር፤፤ ፊያሜታ ሮማን የላከችውን ካሴት ሰባብራ ክሩን ጎልጉላ ፊቱ ላይ የምትነበትንበት ትእይንት አይረሳኝም፤ አሁን ድንገት ጉደኛ ሀሳብ ብልጭ አለልኝ ፤ ኦሮማይን የደረሰው ስብሀት ቢሆን ኖሮ ብየ አሰብሁ፤ አንዲህ ነበር የሚሆነው፤ ሮማን እና ፊያሜታ አስመራ ተገናኝተው እየተጨዋወቱ ነው፤ -ስትገናኙ እጮኛው መሆኔን ነግሮሽ ነበር ? “አለች ሮማን ፊያሜታ ራስዋን በአዎንታ ነቀነቀች፤ “እና እጮኛ አንዳለው እያወቅሽ አፈቀርሽው?” ፊያሜታ ጸጉሯን ነስንሳ “አዝናለሁ፤ ነገሩ እዚህ ይደርሳል ብየ አላሰብኩም ነበር፤ ሕይወት አንደ ደራሽ ውሀ ገፍቶ የት አንደሚያደርሰን አናውቅም’ አለችና በስፕራይት ጠርሙስ የተቀዳ ቢራዋን ተጎነጨች፤ የቢራ ጠርሙሶች ተለቅመው ለምሽግ መስርያ ወደ ናቅፋ ስለተወሰዱ አስመራ ውስጥ የቢራ ጠርሙስ እጥረት ሰፍኑዋል፤ ለጥቂት ሰከንዶች በዝምታ ተዋጡ፤ “ ጸግሽ ነገ ወደ ግንባር ይሄዳል” አለች ሮማን፤ “ አውቃለሁ “ መለሰች ፊያሜታ፤ “ በወጣበት ይቀራል የሚል ስጋት አለኝ ‘ አለች ሮማን እንባ ባቀረረ አይን የናቅፋ ተራራ ወዳለበት አቅጣጫ እየተመለከተች” “ አትስጊ፣ ሻእቢያ ጋዜጠኛ አይገድልም” አለች ፊያሜታ በውስጥ አዋቂ ስሜት ; “አይምሰልሽ፤ ሻቢያ ከመድፍ በላይ ብእር፣ ወረቀትና ካሜራ ያሰጋዋል፤ ጠመንጃቸውን የሚያሙዋሹት ፀግሽን በመግደል ይሆናል” ፊያሜታ ዝም አለች፤ ሮማንም በጸጥታ ስታስብ ከቆየች በሁዋላ፤ “የምታግዥኝ ከሆነ ለጸግሽ አንድ የመጨረሻ ስጦታ ልሰጠው አስቢያለሁ” “ምን ?” አለች ፊያሜታ፤ ‘ ጸግሽ አንችንም እኔንም እኩል አንደሚያፈቅር አውቃለሁ፤ ለሚያፈቅራቸው ሴቶች አንደ ሞት ማበላለጥ አያውቅም፤ስለዚህ በህይወቱ የመጨረሻዋን ሌሊት አብረነው አንድናሳልፍ እፈልጋለሁ፤ “የምርሽን ነው?” ፊያሜታ በግርምት ጠየቀች፤ “አንድ ጀግና ለብዙሀን ህይወቱን መስጠቱ አግባብ ከሆነ ፣ ብዙሀን ላንድ ጀግና እቅፋቸውን መስጠታቸው ተገቢ ነው” አለች ሮማን ፍርጥም ብላ፤ ያን እለት ማታ፣ ፀጋየ በሮማንና በፊያሜታ መሀል ፣ባራት ጡቶች መሀል፣ አንደተንጋለለ በልቡ አንዲህ አለ፤ “ ይገርማል ! ሻእቢያና ደርግ ስልጣንን እንዲህ መጋራት ቢያውቁ ኖሮ ባፍሪቃ ቀንድ ለዘላለም ሰላም ይነግስ ነበር”

  • 18 июн.2 202254

    አንድ ልጅ አጣብሰኝ እስቲ አለችኝ ። ያን ወቅት አንድ ልጅ አጣብሰኝ ሲለኝ ስለነበር እና ማች ያደርጋሉ ስላልኩ ። አገናኘዋቸው ። ከመሃል ወጣው ። እሱ እንድወጣ አልፈለገም መሰለኝ ያሰበውን ሁሉ ይነግረኛል በተለይ ያደረጉትን ሲነግረኝ ልጎመጅ ይዳዳኛል .... "ምን አይነት አበባ ....ምን አይነት ቀሽት ልጅ ነው ያጣበስከኝ እንዴት እንደ ምትጣፍጥ .....ደሞ ሰውነቷ ደሞ ፍቅር ላይ አኳኃኗ " በሌላ ቀን ... "I think አስተዳደጓ ነው መሰለኝ ነፃ ነች ክላስ ይዛ ተሽሞንሙና ትጠብቀኛለች ...ደሞ ዋዛ እንዳመስልህ...ትሽከረከረዋለች ....OMG" በሌላ ቀን "አንተ እቺን መረቅ ልጅ አገናኝተኸኝ እኮ በቃ ኑሮዬ ሰመረ ....እንማጠጠዋለን ....OMG "ይላል I think ፀፀት ሊጀምረኝ ነው 😄 Adhanom Mitiku

  • 12 июн.2 240177

    በአፍላነቴ በተፈጥሮ አስገዳጅነት ጭምር ብርቱ የሆነ የተቃራኒ ጾታ ፍላጎት የተፈጠረብኝ ቢሆንም 'ሰይጣን አለባት' በሚል ተልካሻ ምክንያት የሚንቁኝና የሚያገሉኝ በዙ፡፡ በተገፋሁ ቁጥር ፍላጎቴ በእጥፍ አደገ፡፡ 'አንድ ወንድ አፈቅርሻለሁ ካለኝ ሳላቅማማ እኔም አፈቅርሃለሁ እለዋለሁ' ብዬ የነበረ ቢሆንም የፍቅር ጥያቄ የሚያቀርብልኝ ጠፋ፡፡ያኔ ለራሴ የፍቅር ደብዳቤ ፃፍኩ፡፡ ‹‹ጫሊ ጉድ ሰማሽ?›› አልኳት የክፍላችንን ፍልቅልቅ ተማሪ ‹‹የምን ጉድ?›› ‹‹ደብዳቤ ተፃፈልኝ›› ‹‹ከማን?›› ‹‹አላውቅም›› ‹‹እንዴት አታውቂም?›› ‹‹ስም የለውም፡፡ ግን ከዚህ በፊትም ጽፎልኝ ያውቃል›› ደብዳቤውን ከደብተሬ ውስጥ አውጥቼ ሰጠኋት፡፡ ወሬው ተናፈሰ፡፡ የሆነ ሰው ማንነቱን ሳይገልፅልኝ ደብዳቤ እንደሚጽፍልኝ ተወራ፡፡ የክፍሌ ሴቶች በየቀኑ 'የሚጽፍልሽን ወንድ አወቅሽው?' በሚል ጥያቄ ያዋክቡኝ ጀመር። የሆነ ወንድ እንደሚያፈቅረኝ ተረጋገጠ፡፡ ተፈቃሪነቴ በተማሪ ቤቱ በተወራ ወቅት አንድ ብጣሽ ወረቀት ደብተሬ ስር ተቀምጠ፤ ልቤ ዘለለች፡፡ 'እኔም እንደ እኩዮቼ አፍቃሪ አገኘሁ' ብዬ በደስታ ተሞላሁ፡፡ ተፈላጊ የመሆን ስሜት ሀሴትን ፈጠረብኝ፡፡ በደስታ ውስጥ ሆኜ አንድ አንቀጽ ጽሑፍ ብቻ ያለውን ደብዳቤ ማንበብ ጀመርኩ. . . ‹‹ላንቺ የፍቅር ጥያቄ የሚፅፍልሽ ማን እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ የሚያፈቅርሽ ሰይጣን ነው፡፡ አንቺ ሴት ሰይጣን ነሽ፡፡ ወንዱ ሰይጣን ደግሞ ያፈቅርሻል፡፡ እሺ ካልሽው መውደቅሽ ይቆማል›› ይላል ደብዳቤው። ሰውነቴ እየተንቀጠቀጠ አለቀስኩ.... #ክራራዊ_ህይወት ደራሲ ተስፋኣብ ተሾመ አሳታሚና አከፋፋይ ጃፈር መጽሐፍት

  • 11 июн.1 88091

    ምንገድ ላይ (በእውቀቱ ስዩም) በቀደም ከሆነ ቦታ ተነስቼ ወደ አልሆነ ቦታ ስራመድ ኡራኤል ፊትለፊት ካለው አስፋልት ላይ ስደርስ የሚገርም ነገር ተከሰተ፤ አንድ የጎዳና ተዳዳሪ ቡሌ በፌስታል, ሸክፎ አስፋልት እያቁዋረጠ ሳለ አንድ ሞተረኛ ከላይ ሲንደርደር መጥቶ ደንብቆ ጣለው ፤ የሸገር ሞተረኞች ለምን እንደሚካልቡ አይገባኝም፤ አለምን ከጥፋት የሚታደግ መልክት ለማድረስ የሚነዱ እንጂ የጠወለገ በለጨ የጫኑ አይመስሉም፤ ሞተረኛው ከሞተሩ ተስፈንጥሮ አስፋልቱ ዳር ተዘረረ ፤ ሞተሩ ግን በራሱ ፈቃድ እየበረረ ሂዶ ባቅራቢያው ከሚገኝ ጋራጅ ውስጥ ገብቶ ተሰወረ፤ የጎዳናው ሰውየ ተሽቀንጥሮ መንገዱ ጠርዝ ላይ ተገኘ፤ ወድያው ባካባቢው የነበረው ህዝብ ሞተረኛውን እና የጎዳናውን ሰውየ ተካፍለው ከበብ ከበብ አድርገው ቆሙ፤ ብብዙዎች ፊት ላይ ሀዘን በግልፅ ይነበባል ፤ ቢያንስ ከሁለት አንዱ አለመሞታቸው ብዙዎችን ያስደበረ ይመስለኛል ፤ እኔ ሁሌም ከተጎጂው ጎን መሰለፍ ስለሚያስደስተኝ ፣ ከጎዳና ተዳዳሪው አጠገብ ቆምኩ፤ ተጎጂው ቀና ብሎ አየኝ፤ መላከ ሞትን ያባረረ ኡራኤል መስየ ታይቸው ይሆንን ብየ ራሴን ሸነገልሁ፤ የጎዳናው ሰውየ የፈራሁትን ያህል አልተጎዳም፤ ደጋግሞ የመገጨት ልምድ ያካበተ ይመስላል፤ የቀኝ እግሩ መሀል አገዳ ላይ ብቻ የመድማትና የመጫጫር ምልክት አየሁ፤ -አይዞህ ወንድም ጥላ! በዚች እግርህን ታይበት ‘ አልሁና ከቦርሳየ ውስጥ ሁለት መቶ ብር በማውጣት ዘረጋሁለት፤ በልግስናየ ልቡ ተነክቶ ተጠምጥሞብኝ ያለቅሳል የሚል ግምት ነበረኝ፤ ‘እናትህ ትጎዳ ! (በትክክል ያለኝ እንኩዋ ከ-ትጎዳ-ይከፋል )፤ በሁለት መቶ ብር ምንላቀቅ መስሎሀል?’ አለና እጅጌየን ጥቅጥቅ አርጎ ያዘኝ; ክፉኛ አንደዞረበት ተገለጠልኝ፤ ‘አይዞህ ዠለሳዊ ! በዚህ ደግሞ ጭንቅላትህን ታይበት’ አልሁና ቸክ ፈርሜለት ጉዞየን ቀጠልሁ፤

  • 9 июн.1 778163

    ቻይናዊው ሻወር እየወሰደ እያለ፣ ድንገት ቤቱ በእሳት ይያያዛል... ራቁቱን በመስኮት ዘሎ ይወጣል። ትንሽ እንደተረጋጋ ሚስቱ የሚቃጠለው ቤት ውስጥ መቅረቷን ያስታውሳል፤ ነገር ግን "እንግዲህ ቀኗ ካልደረሰ መውጣቷ አይቀርም" ብሎ ችላ ይላታል። ወዲያው ግን አንድ በጣም አስደንጋጭ ነገር ትዝ ይለውና፣ በአስደናቂ ጀግንነት ድጋሚ ዘሎ ወደሚቃጠለው ቤት ይገባል። ሚስቱንም አንከብክቦ ይዟት ይወጣል። ​በኋላ ላይ ጋዜጠኞች ተሰብስበው፦ "እንዴት በዚህ ድፍረት ወደሚቃጠለው ቤት ገብተህ ሚስትህን ልታተርፋት ቻልክ? ስታገኛትስ በምን ሁኔታ ላይ ነበረች?" ብለው ጠየቁት። ​ስሜቱን በራሱ ቋንቋ እንስማው... ​我不能把手机和妻子单独留在家里。我一直担心她会拿起我的手机偷看信息。当我急匆匆地冲进家门时,果然不出所料,她正一边被浓烟包围着剧烈咳嗽,一边在翻看我的手机。最终,我把她和手机一起救了出来。 ​አቻ ትርጉም ከትንሽ ቅመም ጋር ​"ስልኬንና ሚስቴን ብቻቸውን እቤት ውስጥ መተው ፈጽሞ አልችልም! 'የተላላኩትን መልዕክት እያነበበች ይሆን?' የሚለው ስጋት እረፍት ነሳኝ። ​ዘልዬ እቤት ውስጥ ስገባ ልክ እንደፈራሁት፤ በጭስ ተከባ የቀሚሷ ጫፍ በእሳት እየተቀጣጠለና እያሳለች ስልኬን ስትፈትሽ አገኘኋት! በጨዋነት ስልኬን ተቀብየ ልወጣ  ስሞክር  'ዢዋን ማናት? ለምንስ የልብ ኢሞጂ ላክህላት?' እያለች በዚያ ጭስ ውስጥ መጨቃጨቅ ጀመረች። ሌላ አማራጭ ስላልነበረኝ፣ ከነስልኩ አንጠልጥዬ ይዣት ወጣሁ።" ​ክፉ ጊዜ ላይ ነን እ? 😁 Alex Abraham

  • 6 июн.1 820111

    "የአስራ ሰባት አመት ወንድም እንዳለኝ ነግሬሽ አውቃለሁ?" "አላስታውስም" "የአስራ ሰባት አመት ወንድም አለኝ" "ምን ሆነ?" "ዘመቷል" "መዝመት ማለት?.... ወደ ጦርነቱ?" ጮኸች። በቡናቤቱ የነበሩ ሌሎች ሰዎች በሙዚቃውና በግል ወሬያቸው ተይዘው ባይሆን ድንጋጤ ያዘለ ድምጿ ያስደነግጣቸው ነበር። ወንድሜ እንደዘመተ የሰማኹ ቀን 'ወደ ጦርነቱ ነው የዘመተው?' ብዬ እንደተደናበርኩ እሷም ተደናበረች "አዎ። ወደ ጦርነቱ ነው የዘመተው" "ቤተሰብ እንዴት ፈቀደ?" "በቤተሰብ ፈቃድ አይደለም" "ታፍሶ ነው?" "አልታፈሰም። ስለ ጦርነቱ እንደ አቅሙ መረጃ ይሰበስብ ነበር። ነሸጠውና ተመዘገበ። ነገር ግን ወደ ስልጠና ከገባ በኋላ ስልክ አግኝቶ ደውሎልኝ እንደፈራ ነገረኝ" "እኔን" ደረቷን መታች "እኔን" ደረት መነረቱን ደገመች "እሱ ከሄደ በኋላ እናቴ ደህና አይደለችም። 'አዳዲሶቹ ጥይት ማብረጃ ይሆናሉ' ሲባል ሰምታለች። ወንድሜ ፈንጂ አምካኝ አልያም ጥይት ማብረጃ ሆኖ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደሞተ እርግጠኛ ናት" "የኔ እናት" ደረት መድቃቱን ሰለሰች "አይኗን ማየቱ ያስጨንቃል፥ ምግብ በመከራ ነው የምትበላው፥ለሊት ትቃዣለች" "እኔ ልሰቃይላት" "መሄድ የነበረብኝ እኔ ነበርኩ። እኔ የሱን እጥፍ እድሜ ኖሬያለሁ፥ ሰላሳ አምስት አመቴ ነው። ከሱ በተሻለ ህይወትን አጣጥሜያለሁ። እርሱ ግን ልጅ ነው" "አንተስ ምን በወጣህ?" "ከሱ በተሻለ ኖሬያለሁኝ" "ገና በ ሰላሳ አምስት?" "ከ አስራ ሰባት አይሻልም? እሱ እኮ ምንም አልኖረም" እንባዋ የመናገር ፍላጎትቴን አናረው። ለቅሶዋ በእናቴ ፊት የምሸሽገውን የታፈነ ስሜቴን እንድዘረግፍ ምክኒያት ሆነኝ። "በጦርነት የሞተ ወንድም እንዳለኝ ነግሬሻለሁ?" "አልነገርከኝም" "ታላቅ ወንድሜ በባድመ ጦርነት ወቅት 'ጠላት የአገራችንን ድንበር ሊደፍር አይገባም' ብሎ ከሻቢያ ጋር ለመፋለም ሄዶ መስዋዕት ሆነ። መሞቱን መርዶ ተነገረን እንጂ አስክሬኑን የመቅበር እድል አላገኘንም" "እኔን" ሌላ ደረት መድቃት "ታናሽ ወንድሜ ደግሞ በ ዘጠና ሰባት ነው የሞተው" "እንዴ....?" "ተባራሪ ጥይት ነው የበላለው። ከምርጫ ጋር በተያያዘ ጉዳይ አገር ስትታመስ ከመንግሥት ሰራዊት ለተቃዋሚዎች የተተኮሰች ጥይት ወንድሜን በላችው" "ምን ጉድ ነው?" እንባ የተቀላቀለበት ደረት መድቃት ያጀበው ንግግር "ምን የሚሉት መኣት ነው? እንዴት ያለ መራራ እድል ነው?" ስታለቅስ አብሬያት አለቀስኩ። "እናቴ ግማሽ አእምሮዋን አጥተዋለች" "ለእኔ ያድርገው" እንባና ደረት መድቃት አልተለያትም "ተስፋ ቆርጫለሁ። አዲስ ህይወት የማልሞክረው፥ እንደ ህፃን ከእናቴ ቤት መውጣትን የምፈራው 'ለማን ትቼያት እሄዳለሁ?' በሚል ስጋት ነው። አራት ወንዶችን ወልዳ ሁለቱ የጥይት ሲሳይ የሆኑባት እናቴ ስለምታሳዝነኝ ከአጠገቧ መራቅ ያስጨንቀኛል" ከ #ነገን_ፍለጋ መፅሐፍ የተወሰደ ደራሲ ተስፋአብ ተሾመ

  • 5 июн.1 606162

    ‹‹እማዬ ስራ ስይዝ ሀበሻ ቀሚስ እገዛልሻለሁ›› ‹‹ለማን?›› ‹‹ላንቺ ነዋ›› ‹‹ምን ላደርገው?›› ‹‹እንድትለብሺው›› ‹‹እኔው?›› ከንፈሯን እንደ አሽሙረኛ ሴት ታጣምመዋለች ‹‹አትፈልጊም?›› ‹‹ጽድቁ ቀርቶብኝ በወጉ በተኮነንኩ›› ‹‹ምን ማለት ነው?›› ‹‹ይልቅ ለራስሽ አስቢ። እኔ ረፍዶብኛል። ከዚህ በኃላ ማጌጥ አልፈልግም። አንቺ ሰው ከሆንሽ ለእኔ ከበቂ በላይ ነው›› ‹‹ሰው ከሆንኩ በኃላስ?›› ‹‹ከዛማ ምን እፈልጋለሁ?›› ‹‹እንደ ሌሎች እናቶች መሆን አትፈልጊም?›› ‹‹እኔ አሁን ከስሜያለሁ። ለማጌጥ ረፍዶብኛል፣ ለመዋብ ብሞክር አያምርብኝም›› ሁሉም ነገር ከእጇ ያመለጠ ይመስላታል፡፡ መጎሳቆልን እጣፋንታዋ አድርጋ ስለተቀበለች የተሻለ ነገር አትመኝም፡፡ መዋረድን ስለተለማመደች ከሰው እኩል መሆን ቅንጦት ይመስላታል፡፡ መድመቅ የተፈቀደላት አድርጋ ስለማትቆጥር መክሰሟን በፀጋ ተቀብላለች፡፡ ቀና የማለት መብት እንዳላት ስለማታውቅ በመጉበጧ ተቃውሞ የላትም፡፡ ማንን ትቃወማለች? ለማን አቤት ትላለች? ‹‹የኔ ልጅ ትምህርትሽን በርትተሽ ተማሪ፣ እንደ እኔ እንዳትሆኚ›› ‹‹እሺ›› ‹‹ባክኜ የቀረሁት ያልተማርኩ ደን^ቆሮ ስለሆንኩ ነው›› ‹‹እሺ›› 'እሺ' ከማለት በቀር ምን እላታለሁ? ደ^ንቆሮ መሆኗን ስትመሰክር 'ደን^ቆሮ አይደለሽም' ብላት ደስ ይለኛል፡፡ ነገር ግን የድን^ቁርና ልከኛ ትርጓሜና መለኪያ ሚዛኑ ምን እንደሆነ ስለማይገባኝ እሺ እላታለሁ፡፡ እሺ ብቻ ‹‹ህልሜ የምትመረቂበትን ቀን ማየት ነው፡፡ የምርቃትሽን ቀን አይቼ በማግስቱ ብሞት ግድ አይሰጠኝም›› እናቴ የምትጓጓለት የምርቃት ቀኔ ሲደርስ በመመረቂያ ስፍራው አልተገኘችም፡፡ አባቴና ጥቂት ጓደኞቼ ስጦታ ይዘውልኝ እንኳን ደስ አለሽ ሲሉኝ እናቴ በስፍራው አልነበረችም፡፡ ‹‹ለምን ቀረሽ?›› አልኳት ቤት ከመግባቴ ‹‹ፈርቼ›› ‹‹ምን ያስፈራሻል?›› ‹‹እንዲህ ያለ ቦታ በምን አቅሜ እገኛለሁ?›› ‹‹አቅም ያስፈልጋል ያለሽ ማነው?›› ‹‹በዛ ሁሉ ሰው መካከል እንደኔ አይነት ተራ ሰው ይገኛል?›› ‹‹ሁሉም'ኮ ተራ ሰው ነው›› ‹‹እንደዛስ አይሆንም›› ‹‹የተለዩ ሰዎች ቢኖሩ እንኳን ጥቂት ናቸው›› ‹‹የኔ ግን ይለያል›› ‹‹የምርቃቴ ቀን ያጓጓሽ አልነበረም?›› ‹‹ነበር›› ‹‹ታዲያ ለዓመታት ስትመኚው በነበረው ቀን በስፍራው መገኘት አልነበረብሽም? እኔ እንደሌሎች ሩቅ ቦታ አልተመደብኩም፡፡ እዚሁ አዲስ አበባ ነው የተማርኩኩት፡፡ በአንድ ታክሲ መምጣት እየቻልሽ መቅረትሽ ምን ይባላል?›› ‹‹አስፈራኝ፡፡ የልጅነት ቃልሽን ጠብቀሽ የገዛሽልኝን ሀበሻ ቀሚስ ለብሼ ስሞክረው አፈርኩኝ፡፡ ከኔ ሰውነት ጋር የሚሄድ አልመስልሽ ሲለኝ የለመድኩት ቡቱቶ ይሻለኛል አልኩ፡፡ እድሜዬን ሁሉ በጭስ ስጨናበስ ኖሬ የገዛሽልኝን ሽቶ መላመዱ ከበደኝ፡፡ ምርቃትሽ ቦታ ብገኝ የሰው ሁሉ አይን እኔ ላይ የሚያርፍ ስለመሰለኝ መቅረትን መረጥኩ፡፡ ከሰው እኩል በመሆንሽና ህልሜ ስለተሳካ ደስታ አስለቅሶኛል፡፡ ታዲያ እንባዬ የደስታ ብቻ አልነበረም፡፡ ሆድ ብሶኛል፡፡ በብቸኛ ልጄ የደስታ ቀን ባለመገኘቴ ሆድ ባሰኝ፡፡ እድሜዬን ሳስብ ከፋኝ፡፡ ደስታና ሀዘን አስለቀሰኝ› ተደብቄያት አለቀስኩ፡፡ #ክራራዊ_ህይወት ደራሲ ተስፋአብ ተሾመ አከፋፋይ ጃፈር መጽሐፍት

  • 2 июн.1 867236

    ፈገግታ ይሸውደኛል ። መንገዴ ላይ ያጠቃኝ ሁሉ ፈገግታውን ተጠቅሞ ነው የጣለኝ። የጎዳኝ ሁሉ ከጀርባዬ ሰንዝሮ ነው። ፈገግታ ስስ ጎኔ ነው !! ቤተሰቦቼ ቀጥተኛ ነበሩ አጥፍቼ የሚስቅልኝ አልነበረም፤ ወድቄ ፈገግ ብሎ አባብሎኝ የሚያውቅ ኖሮ አያውቅም። ፈገግ እያለ የሚታገል ይጥለኛል ። ፈገግታ ካየሁ ትግሉ የምር አይመስለኝም። አቅፎ ሰላም የሚለኝ ልቡ የሚወደኝ ይመስለኛል። ልቡ ላይ በመጥፎ ያስቀመጠኝ ሰው ጥርሱ ፈገግ የሚልለት እና እጁ አጥብቆ የሚያቅፍለት አይመስለኝም ነበር። እናት እና አባቴ ተደባብረው ፈገግ ብለው ሲጨዋወቱ አይቼ አላውቅም። ወንድም እና እህቴ አታለው ይዘው ቀጥተውኝ አያውቁም። ቤተሰቦቼ ቀጥተኛ ነበሩ ! ፀባቸው ፊት ለፊት ነው። ቅሬታቸው ፊታቸው ላይ ይነበባል ። ከተሰማቸው ስሜት ርቀው አያስመስሉም! አይወደኝም የምለው ሰው ቀረብ ብሎ ለስለስ ብሎ ካዋራኝ ጋሻዬን ጦሬን እጥላለሁ። ስልት ያለው ጥላቻ አይገባኝም አባቴ አጥፍቼ እንዳይመታኝ ከተማፀንኩት ይቅርታ አደረጎልኝ፥ አረሳስቶ መቶኝ አያውቅም ። የተጣላሁት ሰው ፈግግ ብሎ ካወራኝ ይቅር ብሎኝ ነው የሚመስለኝ። ፈገግ እያሉ ክፋት የሚጎነጎኑ ሰዎች ሳይጥሉኝ ቀርተው አያውቁም። በርግጥ የሰው ልጅ መሸነፍያ ሰፍራ አያጣም!! ©Adhanom Mitiku

  • 28 мая1 999163

    የቆሰለ ነገር ፣የከሳ ፣የኮሰመነ እንሰሳ እሚያድን አውሬ ያስጠላኛል ምቹ ግዜ እየጠበቀ ድምፁን እና ሁኔታውን የሚቀያይር ሰው ግን ያስፈራኛል። ስዩም ፦ ጓደኛው ነኝ ጓደኛዬ ግን አይደለም። ብዙኅ አሳልፈናል ። ቢሰማብኝ የማፍረውን ነገር ወይ ቢሰማብኝ ጉድ የሚያደርግብኝን ነገር አልነግረውም ። እፈራዋለሁ። ቋሚ ወዳጅ ስለሌለው እና ዋሉልኝ ያለቸውን ሰዎች ሁሉ በየምክንያቱ ስለሚተዋቸው እፈራዋለሁ ። ከጓደኞቹ X ስር ስለማይጠፋ ስሜቱን ሁሉ የተሰማው ሰዓት ስለማያንፀባርቅ አብሬው ሆኜ አይጥ ለመያዝ ትክ ብላ እንደምታደባ ድመት ነው የማየው። እሱ እንደድመቷ ትኩረት ሲያደርግ ሁኔታው እንደድመቷ አይነት አይደለም አያስታውቅበትም ። ዘና እያለ እየሳቀ ሚስጥር እየነገረ ነው ሚስጥር የሚያስወጣው ። ስዩምን እፈራው ነበረ .....! ችግር ገጠመኝ ከሁሉም በላይ አብሮኝ ሆነ ያለውን ሁሉ ሰጠኝ አሰጣጡ ስሙልኝ እዩልኝ ያለው አልነበረም በችግሬ አብረውኝ ያልነበሩትን ስወቅሳቸው እያገዘ አላባባሰብኝም... "ተዋቸው አልሞላ ብሎቸው ነው" አለኝ ....ከነሱ ጋ ሆኜ ያጣጣልኩት ስዩም አብሮኝ ቆመ .... ተፀፀትኩ ...! ከብዙ ግዜያት በኋላ ስዩምን በየወሬው እንደዚ አትመስለኝም ነበር እያልኩ እሱ ላይ ያለኝን አቋም ተናዘዝኩ አልተናደደም ሳቀ ስልከው እና ሲላከኝ እንደኩያ አይደለም እንደታናሽ ነው ሲተማመንብኝ እንደታላቅ ነው ...! እሚያግዘን እና የሚኮራብን ወዳጅ የኛ ሲሆን የሚሰማውን ምቾት አሰማኝ ከጥቂት ግዜ በኃላ ... ስራ በዛብኝ ብዬ የሰጠሁንት ላግዝ ብሎ የወሰደውን ሙሉ ውክልና ተጠቅሞ መኪናዬን ሸጦ አውሮፓ መግባቱን ከሳምንት በሆላ ሰማሁኝ ... ስስቅ ላየኝ ሰው ተታልዬ አልመስልም ነበር ... ማመን ከመጠራጠር በላይ ዋጋ ያስከፍላል ማለት ነው ?? መፍራት ከመድፈር በላይ አቅም አለው ማለት ነው ?? ኮቴ በሰማን ቁጥር እየባነንን የት ድረስ እንሄዳለን ?? የሄድንበትን መንገድ እየጠየቅን መሄድ የሰውነት እጣ ፈንታ ነው ??.... በርግጥ የግዜ ጉዳይ እንጂ ከተካደ ሰው የከዳ ሰው ያሳዝናል!! © Adhanom Mitiku

  • 26 мая1 864247

    እናንተ ከድካማቹ የበረታቹ ሆይ እንዴት ከባድ ግዜያችሁን አለፈላቹ ? እንዴት የተሰበረ ልባችሁን ጠገናችሁ? የአፈሰ እጃችሁ ባዶ ሆኖ ስታገኙት ..... ድንጋጤ እንዴት አደረጋቹ ? . . እናንተ ከድካማቹ የበረታቹ ሆይ ስትታመሙ ስታጡ ቤት ስትውሉ መረሳት እንዴት ሳይሰብራችሁ ቀረ ? .... ያልፍልኛል ብላችሁ የሄዳችሁበት መንገድ አባጣው ጎርባጣው አተርፍ ባይ አጉዳይ ሲደርጋቹ ምን አላችሁ?? . . እናንተ የበረታችሁ ድንገተኛ ሃዘን ጎጃቹ ሲገባ፣ ያተርፋል ያላችሁት ሲያከስር ፣ መከዳት ልባችሁን ሲያርደው ......እንዴት ጨለማው ነጋላችሁ? ተስፋችሁ የተሟጠጠ ማድጋችሁ የጎደለ ኪሳቹ የተራቆተ እለት ........ ጭንቀት እንዴት ድል ሆነላቹ . . እናንተ የበረታቹ ሆይ መውለድ እምቢ ሲላችሁ ፣ ልጃችሁ ሲታመም፣ ጤናችሁ ሲጓደል .....ተስፋ የለም ስትባሉ ልባቹ እንዴት ተስፋ አየ ??? . . መፅሃፍ ቅዱስ የበረቱ ሰዎችን የአንበሳን አፍ ከዘጉ ፣ከሰይፍ ስለት ካመለጡ፣ የእሳትን ሃይል ካጠፉ፣ የባእድ ጭፍሮችን ካባረሩ ፣በጦርነት ሃይለኛ ከሆኑ ሰዎች እኩል ከድካማቸው የበረቱትን ያወሳል ከድካም መበርታት ቀላል አይደለም ! ቅዱስ ዳዊት ልጁ አቤሰሎም ሲያሳድደው የሚያስጨንቁኝ እንዴት በዙ! ብዙዎች በእኔ ላይ ተነሡ። ብሏል ትግስተኛው እዮብ መከራ ሲሸከም ድካሙ ሲበረታበት ስለ ምን ከማህፀን አልሞትሁም ብሏል . . የሰው ልጅ ሃያል ነው ከድካሙ ይበረታል አይነጋም ያለው ይነጋል . . እናንተ የበረታችሁ ሆይ እናንተ ግን እንዴት እንዴት በረታቹ ??? © Adhanom Mitiku

  • 7 апр.2 8562611

    ቻርለስ ቡኮውስኪ ቀጭን ሲጋራውን እየማገ ኢንተርቪው ለሚያደርጉት ሰዎች አንድ ጥያቄ ይጠይቃል፦ ‹‹ማንም ጠዋት ሳይቀስቅሰን ስንነሳ፤ ማታ ደግሞ ማንንም ሳንጠብቅ ስንተኛ፣ የፈለግነውን ማድረግ ስንችል። ምን ብለን እንፈርጀዋለን፤ ነፃነት ወይስ ብቸኝነት?›› መልሱን በዚህ መልኩ አስቀምጬዋለሁ..               ከረጅም ከባድ ቀን በኋላ ወደ ቤት እንገባለን። እዛ የሚጠብቀን ማንም የለም። ድመት እንኳን አላሳደግንም። ወደቤት እንደገባን ቁልፉን ጠረጴዛ ላይ እናስቀምጣለን። ይህ የእለት ተእለት ተግባራችን ነው። በህይወታችን ውስጥ የቀረው ብቸኛው ቁጥጥሮሽ ቁልፉን ጠረቤዛው ላይ ማስቀመጥ ነው። ጫማችንን እናወልቃለን።  “የት ነበራችሁ?” ብሎ የሚጠይቀን የለም፤ “ውሎህ እንዴት ነበር?” የሚለን አይኖርም። ወደ ኩሽና እንገባለን ፍሪጁን ከፍተን ግማሽ ጠርሙስ ውሃ እና መች እንዳስቀመጥነው የማናውቀውን እርጎ እናወጣለን። ቀጥሎ የረሳነውን የለውዝ ቅቤ በማንሳት በደረቀው ዳቦ ላይ እንለውሳለን። ከዛ ብዙም መጠበብ እና መጨናነቅ በሌለው መልኩ የፍሪጁን በር ወርውረን እንዘጋዋለን። እናም ሶፋችን ላይ ተቀምጠን ስልካችንን እንመለከታለን፤ ምንም አዲስ መልእክት አልተላከም። የለቀቅነውን ፎቶ ማንም ላይክ አላደረገውም። አለም እኛን ችላ ብላናለች። ስለዚህ ካየነው የቆየ “shutter island” የሚለውን ፊልም እንደገና እንገርባለን። ምክንያቱም ድግግሞሽ ከአዲስ ክስተት የተሻለ አስተማማኝ ነው የሚል አስተሳሰብ ስላለን። በዙርያችን የሚበጠብጥ ድምፅ የለም፤ ሙዚቃ የለም፣ ሳቅ የለም፤ ስለአስቤዛ የሚከራከረን የለም፤ ሁሉም በዝምታ ውስጥ ተውጧል። ማንም አያቋርጠንም ማንም ደግሞ ሙዳችንን አይቀይረውም። ከእኛ ጋር አልጋ የሚጋራን ስለሌለ አልጋው ላይ በነጻነት ተዘረጋግተን እንቀመጣለን። ቀዝቃዛ ድባብ ነገር ግን ምንም ማስመሰል የሌለበት እውነተኛ ስሜት። ብቻን መኖር ማለት የዚህ ሁሉ ባዶነት ፍፁም አለቃ ነን ማለት ነው። የቀዘቀዘውን ወጥ ሳናሞቅ አልጋችን ላይ መብላት እንችላለን። ያለምንም መረበሽ ቀኑን ሙሉ ተኝተን መዋል እንችላለን። ሳና ሳምንቱን ሙሉ መጥፋት እንችላለን። ማንም የእኛን ማብራሪያ አይጠብቅም፤ የትኛውም ሰው በቀስታ እየጠፋን እንደሆነ አይገነዝብም!። ሰዎች ብቻን መሆን ማለት ብቸኝነት ይመስላቸዋል። ነገር ግን ይህ የስነ ልቦና ኢኮኖሚካሊ ዘዴ ነው። ሌሎች ላይ ኢንቨስት ማድረግ አቁሙ ምክንያቱም በምላሹ የምታገኙት ደካማ ውጤት ነው። በስተመጨረሻ መብራታችንን አጥፍተን በቀዝቃዛ አልጋችን ላይ እንተኛለን። እናም ሚስጥራዊ ምቾት ይሰማናል። ማንም አይወደንም ማንም አይጠላንም፤ እና ማንም አይፈልገንም። ይህ ደግሞ በጣም ዘና የሚያደርግ ነፃነት ነው።       @Imagination_officially

  • 1 апр.2 729249

    የጠንቋይ ልጅ! (አሌክስ አብርሃም) የሰርግ ፎቷችን ያለበት ቦርድ እየዞረ ተጋባዥ እንግዶች ሁሉ ይፈርሙና መልካም ምኞታቸውን ያሰፍሩ ነበር። ቆይቶ አንድ ጽሁፍ አየሁ፤ "መልካም ድህነት" ይላል። ብልግና አይደል? ጽሁፉን ጠንቅቄ አውቀዋለሁ፤ የእርሱ ነው። ለዓመታት ፍቅረኛዬ የነበረው የያሬድ እጅ ጽሁፍ! "ምነው ፀባዩ እንደ እጅ ጽሁፉ ቢያምር ኖሮ!" እላለሁ። አፈቅረው ነበር፤ እርሱም ያፈቅረኝ ነበር (ወይም ይመስለኛል)። "የሱቄ ጠባቂ ናት" የሚላት ሴት ጋር ተኛ። እዛ መገናኛ የልብስ ሱቅ አለው። ይቅርታ ላደርግለት ሰበብ ፈለግኩ። ጎበዝ ነው፤ በጥረቱ ኑሮን ያሸነፈ፣ እንዴት እዚህ ደረስክ ቢባል አንድ ሁለት ብሎ ደረጃውን የሚያስቆጥር። ደስ የሚል ሕይወት ያለው፣ ሀብታም የሆንኩ መስሎ እንዲሰማኝ ያደረገ። ሰበብ ፈለኩ ክህደቱን የሚመጥን.... ​"ታፈቅራታለህ?" "አላፈቅራትም!" "ጠጥተህ ሰክረህ ነበር?" "አረ! መጠጥ የሚባል አላሸተትኩም፣ እንኳን ልጠጣ!" "ሰልችቸሃለሁ?" " መቸም አትሰለችኝም፣ መቸም" "እና ለምን...?" "እኔጃ! በቃ አላውቅም!" አለ እንባ እየተናነቀው። ​የሰጠኝን ቀለበት ወርውሬለት ሄድኩ። ስድስት ወር ለመነኝ፣ አስለመነኝ፤ በጭራሽ አልኩ። ቆይቶ አንድ ልጅ ጋር ተዋወቅኩ። ጎረቤታችን የተከራየ የመንግሥት ሠራተኛ። ያሬድ ጋር በተለያየን ሰሞን፣ በቅንጡ መኪና የተመላለስኩበትን የሰፈሬን ኮብልስቶን መንገድ በእግሬ ስኳትን ያገኘሁት ሰው ነው። አብሮ በመኳተን ፀባዩና ትህትናው ማረከኝ። አቀርቅሮ የተማረ፣ ስልጡን ትሁት ነፍስ። ቅርርባችን ወደ ፍቅር አደገ። ሻይ ቡና ጀመርን። የኪራይ ቤቱ ጎራ ማለት ጀመርኩ። እሾህን በእሾህ ነው ብየ ከአመት አካባቢ በኋላ ቅልብጭ ባለች ሰርግ ተጋባን። አንዳንዱ እሾህ ሲያመረቅዝ ይኖራል። ያ ለካፊ እንደመጣ እንኳን ሳላየው፣ "መልካም ድህነት" ብሎ ቦርዱ ላይ ጻፈ። ሟርተኛ! ​ልክ ነበር፤ ገና ባገባሁ በሁለተኛ ዓመቴ ፀጉር የሚያቆም ድህነት ጋር ተፋጠጥኩ። የጠንቋይ ልጅ! ሀብቱንስ ያገኘው ጅብ ጋልቦ እንደሆነ ምናባቱ ይታወቃል? ይህን ሳስብ ነበር ደግሞ ነፍሴም በድህነት ቡጢ እየተጠናገረች መሆኑ የገባኝ። ድህነት ቃላትንም ቅላፄንም እሾህ ያደርጋል። ኑሮ ምቾት ሲነሳኝ በያሬድ ምቾት በቅናት ተቃጠልኩ። እርሱ በተልከሰከሰ እኔ ዋጋ መክፈል ነበረብኝ? ለምቾቴስ ብየ እንዳላየሁ ማለፍ ነበረብኝ? የአገራችን ሕይወት ለኩራትም ለይቅርታም አይመችም። ብር ብር ብቻ አልሆነም! "ጎልድ ዲገር" ባዮ ሁሉ ወርቁ ቢገኝ እስከምድር ወገብ ሊቆፍር ዶማውን ይዞ የሚዞር ነው። በዚህ ዘመን ማንም ቢያሟርት ደሃ ላይ ይደርሳል። ነብይ መሆን አይጠይቅም። ​በቀደም ታዲያ መንገድ ላይ ፀሐይ ሲከካኝ አገኘኝና መኪናውን አቁሞ "ግቢ" አለኝ። ኩራት እየተናነቀኝ፣ ግን ደግሞ መሃል አናቴን እንደጌሾ ያኮሸለለው ፀሐይ ገፍቶኝ ገብቼ ተቀመጥኩ። ምናልባትም የወሬ ጉጉት! መኪና ከትዳር ይመቻል። ደግሞ ቅዝቃዜው! ደግሞም ደስ የሚል ሽታው። የእራሴ ላብ ጠረን መኪናውን የሞላው እስኪመስለኝ የመቆሸሽ ስሜት ተሰማኝ። ​"ደህና ነሽ?" አለኝ። "አይመለከትህም፤ እንደውም ወራጅ!" እንደእብድ አደረገኝ። ​ወሬዬ ሁሉ የደሃ ሆኗል፤ "ወራጅ" የታክሲ ቋንቋ ነው። አላቆመም። እኔም እንደገና "ወራጅ"ን አልደገምኳትም። ነገር ነገር አለኝ፤ ይሄን ምቾት፣ ይሄን ሰላም፣ ይሄ ጎኔ የተቀመጠው ሰው የነጠቀኝ መስሎ ተሰማኝ። "እሱ ሰጠ፣ እሱ ነሳ፤ የሰው ነገር የሰው ነው" ብዬ ማለፍ አልቻልኩም። ነገር አማረኝ፤ አፌን መክፈት አማረኝ... ​"ፍቅሬን፣ እምነቴን ያለምንም ምክንያት ረጋግጠህ አንዲት ዱርዬ ጋር ተጋደምክ!" አልኩት። መንገዳችን ላይ አይኔን ተክየ። ለታክሲ የተሰለፈ ፀሐይ ያደረቀው ህዝብ፣ በዓል ሰሞን ነውና በጎች፣ በሬ መንገዱ ላይ ይርመሰመሳል። እንደዛ በግ፣ እንደዛ የኔ ቢጤ፣ እንደነዛ ተሰላፊወች ነኝ ከዚህ ሲመለከቱኝ። ተበሳጨሁ። ​እንደተረጋጋ "ልክ ነሽ፤ እንደ እንስሳ ራሴን መቆጣጠር ተስኖኝ የማይሆን ነገር ሠራሁ" አለና መሪውን በመዳፉ መታው። መሪው ምን ያርግ ዘዋሪው እንጅ መጠርቀም ያለበት። ​"እንደ እንስሳ አይደለም፣ እንደ ውሻ ነው የተልከሰከስከው!" አልኩት። "ውሻም እንስሳ ነው" አላለኝም። ​"አዎ፤ እንደ ውሻም፣ እንደ አህያም! ልክስክስና ደደብ ሆኜ አንድ ቀን የማይሆን ነገር ሰራሁ። አንድ የተረገመ ቀን! አንቺ ግን የልብ ይቅርታዬን ወርውረሽ፣ በትዳር ስም እኔ የሠራሁትን ለዘላለም ልትሰሪው ወሰንሽ" ​መኪናውን አቆመ፤ ሰፈሬ አድርሶኝ ነበር። እንዴት ሰፈሬን አወቀው? ምንም ሳልናገር ወርጄ ሄድኩ። "በትዳር ስም የማመነዝር ነው የሚመስለው?" አዘገምኩ፤ ወደምኖርበት ከከተማ የወጣ ኮንዶሚኒየም፣ አራተኛ ፎቅ ላይ ባለቤቴ ጋር ወደምኖርበት ድህነት። የጠንቋይ ልጅ! ቀና ብየ ህንፃውን ሳየው ጧት አስጥቻቸው የሄድኩት የባሌ ሁለት ሸሚዞች ህዝቡ ተሰዶ ባዶውን እንደቀረ አገር ባንዲራ በግዴለሽነት ይወዛወዛሉ። በትዳር ስም የማመነዝር መሠለኝ! ዞር ብየ ተመለከትኩ የአዲስ አበባ መብራት ፏ ብሏል። ስንት ያየሁባት ከተማየ እንደምራቅ የተፋችኝ መሠለኝ። የተሰደድኩ መሰለኝ...ሱዳን፣ ሊቢያ ቁሜ አዲስ አበባን በትዝታ የማያት!

  • 26 мар.2 5261712

    ፪ ታውቃለህ ? ሕይወት ለሴት ሌላ ናት… ጨካኝ ናት። ስነቃ ዙሪያዬ በእርጉዝ፣ ዙሪያዬ በሰርግ፣ ዙሪያዬ በ“ቆመሽ ቀረሽ” ምክር ታጅቦአል። አንተ እንደ መጀመሪያው አፍላ ፍቅር፣ አፍላ ጭቅጭቅ፣ አፍላ መውደድ ላይ ነህ። ኩርፌያዬ፣ ስጋቴ፣ ጭቅጭቄ ውስጥህ አልዘልቅም አለ። ቁም ነገር የሌለው ፍቅር፣ ያልበሰለ ፍቅር፣ ነገ የሌለው ፍቅር፤ 'አቤት እዚ ጋ ነኝ' የማይሉት ፍቅር ከወንድ በላይ ለሴት ምቾት አይሰጥም። የማይታገል ወንድ፣ ሃላፊነት የማይሸከም ወንድ፣ “እከለልበታለሁ” የማይሉትን ወንድ፣ “አለልኝ” የማይባል ወንድን ባል ማድረግ ያስፈራል። አስቴር አወቀ “ጠይም ዘለግ ያለ፣ የሰፋው ደረቱ ፍቅር ሃላፊ ነው ባረገኝ እህቱ…” እንዳለችው ነው። ፍቅር ሃላፊ እንደሆነ አስተዳደጌ ነግሮኛል ... አያያዛችን ... ፍቅሩ ሲያልፍ፣ የኑሮን ቀንበር ስንሸከም፣ ሲያንገዳግደን፣ ሃላፊነት ሲወጥረን፣ ልጆች ሲመጡ ....... ጫንቃችን “አልተዘጋጀም” አልኩኝ። እንዳላጠናክርህ የምለው አይገባህም፤ እንዳታጠናክረኝ አልጠነከርክም። ልቤ እየወደደህ አልረጋ አለ… “የት ነሽ?” ስባል “እዚ ጋ” ማለት ተሳነኝ፤ ልቤ ሸሸክ… ሄድኩኝ። የተለየውህ እንደ ዋዛ አልነበረም፤ ሌት ቀን አስቤ "ያልበሰለ ሰው ፍቅር አያሻግረም ብዬ እያዘንኩኝ ነው " © Adhanom Mitiku