tgindex
ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ: የህጻናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት እና ረ. ፕሮፌሰር (Ass. Prof. Of Pediatric Surgery)

ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ: የህጻናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት እና ረ. ፕሮፌሰር (Ass. Prof. Of Pediatric Surgery)

Статистика

@ ከ18 አመት በታች ለሆኑ ህፃናትና ታዳጊዎች(0911441651)@Addis Ababa ✅️የኩላሊት እና የሽንት ቱቦ ቀዶ ህክምና ✅️የብልት አፈጣጠር ችግር ✅️የዘር ፍሬ አቀማመጥ ችግር ✅️የግርዛት አገልግሎት ✅️ጠቅላላ የአንጀት ቀዶ ህክምና ✅️የሰገራ መውጫ አፈጣጠር ችግር ሕክምና ✅️ማንኛውንም የህፃናት ቀዶ ህክምና አገልግሎትን እንሰጣለን

Последний пост
29 июл.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
3 796
−3 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 033
21 постов
Вовлечённость
27,2%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
2
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
751
1/48двое суток
860
1/72трое суток
928

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • Dr. Saleamlak Tigabie:     MD, Pediatric Surgeon, FCS-ECSA(at YK12HMC) ,Addis Ababa, Ethiopia   👉ለበለጠ መረጃ ፣ ቀጠሮ ለመያዝ እና ነፃ የምክር አገልግሎት : ከስር ያሉ አድራሻዎችን መጠቀም ይቻላል! 📱0911441651 👉Gmail: saleamlaksati@gmail.com   Telegram: https://t.me/DrSaleamlakT Facebook: https://www.facebook.com/ዶር-ሳለአምላክ-ጥጋቤ-Pediatric-Surgeon-100878625359706/ Tiktok: https://www.tiktok.com/@drsaleamlakpedisurgeon?_r=1&_t=ZM-931jtU5Pk1E YouTube: https://www.youtube.com/@Dr.Salie_Pedisurgeon

  • ሰላም ዶክተር የ3 ዓመት ልጄ የአንጀት ነርቭ ችግር(Hirshsprung Disease) እንዳለበት ተረጋገጠ እና "Pull through " የሚባል ቀዶ ጥገና እንደሚያስፈልገው ተነገረኝ። ህክምናው ከባድ እንደሆነ እና ተያያዥ ችግሮች እንዳሉት ሊያስረዱኝ ሞክረዋል! እባክህ ስለዚህ ጉዳይ ብታስረዳኝ? (የወላጅ ጥያቄ) 🌡ውድ ጠያቂያችን ስለ ጥያቄው በጣም እናመሰግናለን! 🌡ይህ ጥያቄ የብዙ ወላጆች እና በዬ ቀኑ የምንጠዬቀው ጥያቄ ስለሆነ ወላጆች ሊረዱት በሚችሉት ቋንቋ ለማብራራት እንሞክራለን! 🌡የአንጀት ጡንቻ ነርቭ ችግር( Hirshsprung Disease) ማለት ህጻናት ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ የሚከሰት ችግር ሲሆን አንጀት በተለይ የትልቁ አንጀት (Colon) ክፍል መደበኛ የነርቭ ሴሎች(Ganglion Cells)  በማይኖሩበት ጊዜ የሚከሰት ችግር ነው። 🌡እነዚህ የነርቭ ሴሎች አንጀትን ዘና ለማድረግ እና ሰገራን ወደፊት ለመግፋት የሚረዱ ናቸው። 🌡ያለእነሱ ችግር ያለበት የአንጀት ክፍል በመጥበቅ ዝግ ሆኖ ይቆያል! 🌡 ይህም የሚከተሉትን ምልክቶች  ያስከትላል፡ 💊💊የመጀመሪያው ካካ መዘግዬት 💊💊ሥር የሰደደ የሆድ ድርቀት 💊💊ቀስ እያለ የሚጨምር የሆድ መነፋት 💊💊ሰገራ ለመጠቀም መቸገር እና ማማጥ 💊💊ተደጋጋሚ የአንጀት ኢንፌክሽን እና ሎሌች ችግሮችን ያስከትላል! 🩺ስለዚህ የመጎተት ቀዶ ጥገናው( Pull through) ችግር ያለበትን  የአንጀት ክፍል(Aganglionic Segment) በማስወገድ ጤናማውን የአንጀት ክፍል  ከፊንጢጣ ጋር ማገናኘት ሲሆን በዚህም ልጅዎ ሰገራውን በተለመደው መንገድ ማሳለፍ እንዲችል የሚደረግ ህክምና ነው። ✍ጥያቄ -1 ፡- ቀዶ ጥገናው ለምን ያስፈልጋል? በመድሃኒት መስተካከል አይችልም ወይ? 🌡እነዚህ ነርቮች በመድሃኒት ሊተኩ የሚችሉ አይደሉም። 🌡ብቸኛው ዘላቂ ሕክምና የተጎዳውን ክፍል በቀዶ ጥገና ማስወገድ እና በጤነኛው መተካት ነው። 🌡ያለ ቀዶ ጥገና የምንጠብቃቸው ከሆነ ልጆች እንደ የአንጀት ኢንፌክሽን (Enterocolitis)፣ ከባድ የሆድ ድርቀት እና ደካማ እድገት ያሉ ከባባድ ችግሮች ሊያጋጥሟቸው ይችላሉ። ✍ጥያቄ- 2፡- በቀዶ ጥገናው ጊዜ ምንድነው የሚደረገው? ትንሽ ብታብራራልኝ? 🌡በቀዶ ጥገናው ወቅት የሚከናወኑት ዋና ዋና ነገሮች: 1. ችግር ያለበት የአንጀት ክፍል ይወገዳል። 2. ጤናማው አንጀት ከመደበኛ የነርቭ ሴሎች ጋር ይጎተታል። 3. ከፊንጢጣ ጋር ይያያዛል ወይም ይሰፋል። 🌡እንደ ሁኔታው ​​​​ቀዶ ጥገናው እንደሚከተለው ሊሆን ይችላል- 💊💊በአንድ ደረጃ ሆድ ሳከፈት በፊንጢጣ ብቻ ሊከናወን ይችላል ወይም 💊💊በሁለት ደረጃዎች  (ጊዜያዊ ኮሎስቶሚ መጀመሪያ ይሰራል፣ ከዚያም ከተወሰነ ጊዜ  በኋላ ዋና ቀዶ ህክምና ይሰራል)። ✍ጥያቄ- 3 ፡- ቀዶ ጥገናው ደህንነቱ የተጠበቀ ነው ማለት ይቻላል? 🌡አዎ! 🌡በተለይ በሰለጠኑ እና ልምድ ባላቸው  የሕፃናት የቀዶ ጥገና ባለሙያወች ቢሰራ በደንብ የተረጋገጠ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ህክምና  ነው። 🌡አብዛኛዎቹ ልጆች በጥሩ ሁኔታ ያገግማሉ፣ ከዚያ በኋላ በከፍተኛ ሁኔታ ጤናቸው በመልካም ደህንነት ይቀጥላሉ። ✍ጥያቄ- 4 ፡- ከቀዶ ህክምና ጋር የተያያዘ ምን አይነት ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ? 🌡ልክ እንደ ሌሎች ቀዶ ጥገናዎች ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮች ይኖራሉ። 🌡እነዚህም የሚከተሉትን ያካትታሉ፡ 💊ቀደም ብለው ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮች፡- 🩺የደም መፍሰስ( Bleeding) 🩺ኢንፌክሽን 🩺ከተያያዘበት ቦታ ላይ ማፍሰስ (anastomotic leak) 🩺በቀዶ ጥገና ቦታ ላይ ጥበት( Anastomotic stenosis) እና ሌሎች ችግሮች ሲሆኑ 💊ዘግይተው ሊከሰቱ የሚችሉት ደግሞ፡- 🩺ከችግሩ ጋር የተያያዝ ከባድ የአንጀት ኢንፌክሽን( HSD associated Enterocolitis) 🌡🌡ምልክቶች፡ ትኩሳት፣ የሆድ መነፋት፣ ተቅማጥ፣ መልፈስፈስ 🩺የሆድ ድርቀት በአንዳንድ ልጆች ላይ ሊቀጥል ይችላል 🩺ከቀዶ ጥገና በኋላ ለተወሰነ ጊዜ የሰገራ ማምለጥ(Soiling) 🩺የፊንጢጣ መጥበብ 🩺አልፎ አልፎ ቢሆን ድጋሜ መከሰት  ወይም የአንጀት መዘጋት 🌡አብዛኛዎቹ ችግሮች በክትትል  የህክምና እርዳታ ሊስተካከሉ የሚችሉ ናቸው። 🌡አልፎ አልፎም ቢሆን ድጋሜ ቀዶ ጥገና ሊያስፈልግ ይችላል! ✍ጥያቄ - 5 ፡ ልጄ ከቀዶ ጥገናው በኋላ ሰገራውን በተለምዶ መጠቀም ይችላል ማለት ነው? 🌡ብዙ ልጆች ቀዶ ጥገናውን ከሰራንላቸው በኃላ የሰገራ አጠቃቀማቸው በከፍተኛ ሁኔታ ይሻሻላል። 🌡ሆኖም ግን፡- 🩺🩺የአንጀት ልማዶች( Bowel Habits) ወደ መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ ጊዜ ሊወስዱ ይችላሉ። 🩺🩺አንዳንድ ልጆች መጀመሪያ ላይ በተደጋጋሚ ሰገራ( Frequent stools) ሊኖራቸው ይችላል። 🩺🩺አንዳንዶቹ የአመጋገብ(Dietary management)! ወይም የአንጀት ስልጠና(Bowel training) ሊያስፈልጋቸው ይችላል። 💊ከጊዜ በኋላ አብዛኛዎቹ ልጆች ጥሩ የአንጀት መቆጣጠር እና አጠቃቀም ያዳብራሉ። ✍ጥያቄ - 6፡- ይህ ህክምና  እድገቱ እና የወደፊት ሕይወቱ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ይኖረው ይሆን? 🌡ከተሳካ ቀዶ ጥገና እና ተገቢ ክትትል በኋላ አብዛኛዎቹ ልጆች፡- 🩺🩺በመደበኛነት ያድጋሉ 🩺🩺በመደበኛነት ትምህርታቸውን ይከታተላሉ 🩺🩺ጤናማ ህይወት ይኖራሉ 💊ነገር ግን አዘውትሮ መከታተል እና የህክምና ክትትል ማድረግ  በጣም አስፈላጊ ነገር  ነው። ✍ጥያቄ -7 ፡- ከቀዶ ጥገና በኋላ ምን ምን ማስተዋል ይኖርብኝ ይሆን? 🌡የሚከተሉትን ችግሮች ካስተዋሉ የሕክምና እርዳታ ሊያስፈግ ይችላል: 🩺🩺ትኩሳት 🩺🩺የሆድ መነፋት 🩺🩺መጥፎ ሽታ ያለው ተቅማጥ 🩺🩺ከባድ የሆድ ድርቀት 🩺🩺ማስታወክ 🩺🩺ደካማ አመጋገብ 💊እነዚህ ችግሮች ከፍተኛ የአንጀት ኢንፌክሽን  ወይም የአንጀት መዘጋት ምልክቶች ሊሆኑ ስለሚችሉ ወዲያውኑ ህክምናው ወደ ተሰጠበት ህክምና ተቋም መውሰድ ያስፈልጋል። ✍በመጨረሻም✍ 🌡የአንጀት ነርቭ ችግር ሊታከም የሚችል ችግር ነው። 🌡Pull Through  ቀዶ ጥገና የተለመደ እና ዘላቂ ሕክምና ነው። 🌡አብዛኛዎቹ ልጆች ተገቢውን እንክብካቤ እና ክትትል በማድረግ በጣም ጥሩ ውጤት ይኖራቸዋል። 💊ስለዚህ ውድ ጠያቂያችን በቂ ምላሽ እንዳገኙ ተስፋ እናደርጋለን! ❤️ ጠቃሚ መረጃ ነው ብለው ካሰቡ ለሌሎችም ወላጆች እንዲደርስ በ ቅንነት #share ያድርጉት ‼️🙏 📘በዚህ ጉዳይ ተጨማሪ ጥያቄ መጠየቅ ከፈለጉ ወይም  በሌሎች ጉዳዬች  በማንኛውም ጊዜ ማንኛውንም ጥያቄ ለመጠየቅ ከስር ያለውን አድራሻ መጠቀም ይቻላል። 👇👇👇👇👇👇 📲+251911441651 🌡🙏ሌሎች መረጃዎች ሲለቀቁ እንዲደርሷችሁ የtelegram አድራሻችንን ይቀላቀሉ! http://t.me/DrSaleamlakT ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን!!!   አዘጋጅ :-    ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ:      የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር ( YK12HMC)

  • 19 июл.1 3597

    ትንሽዬ እባጭ ብታዩ ቸላ መባል የለበትም! https://youtube.com/watch?v=E0i-sK211Is&si=NliNUbLsyUwIrkYx

  • 18 июл.1 28314

    እባካችሁ ወላጆች ልጆቻችንን እያየን! ያልወረደ የዘር ፍሬ- Undescended testicle https://youtube.com/watch?v=y6perg-m3dI&si=wkKlMOl1F0u8YCfl

  • 16 июл.1 421122

    ሰላም ዶክተር ልጄ ከተወለደች ገና 3 ቀኗ ነው። በእርግዝና ወቅት በደረቷ እና በሆዷ መካከል ችግር አለ ብለውኝ ይህ ህክምና ወደሚሰጥበት ሆስፒታል በሪፈር ተላኩ! አሁን ከተወለደች ጀምሮ የመተንፈሻ ማሽን ላይ ነች። ችግሩን ስጠይቃቸው "ዲያፍራማቲክ ሄርኒያ" ነው አሉኝ! በጣም ጨንቆኛል ካላስቸገርኩ ስለዚህ ጉዳይ ማብራሪያ ብትሰጡኝ! (የወላጅ ጥያቄ) 👉ውድ ጠያቂያችን ይህን ጥያቄ ስለጠቁን በጣም እናመሰግናለን! 👉እንደ እርሶ አገላለጽ ከሆነ ልጅዎ ያለባት ችግር በህክምና አጠራር " Congenital Diaphragmatic Hernia" ይባላል! 👉ለሌሎችም ያስተምራል ብለን ስላሰብን ለወላጆች በሚመች መልኩ ለማስረዳት እንሞክራለን! ✍ጥያቄ - 1 : Congenital Diaphragmatic Hernia (CDH) ምንድን ነው? 🌡Congenital Diaphragmatic Hernia(CDH) ማለት  ደረትን ከሆድ እቃ  የሚለየው ጡንቻ(Diaphragm) በአፈጣጠር ችግር ምክንያት  ክፍተት  ሲኖረው የሚፈጠር ችግር ነው። 🌡 በዚህ ክፍተት  የሆድ ዕቃ አካላት (እንደ ጨጓራ፣ አንጀት፣ ጉበት ፣ ቆሽት ወይም ኩላሊት ያሉ አካላት) ወደ ደረት   ውስጥ ይገባሉ። 🌡ይህም ሳንባን በትክክል እንዳያድግ እና እንዳይጎለብት ያደርጋል። 🌡 ይህም በህክምና አጠራር pulmonary hypoplasia (ትንሽ ሳንባ) የመፈጠር እድሉን ይጨምራል! 🌡 ከዚህም በተጨማሪ በሳንባ ውስጥ ያሉ የደም ስሮች ግፊታቸው እንዲጨምር ያደርጋል። 🌡ይህም በህክምና አጠራር pulmonary hypertension እንለዋለን! ✍ጥያቄ-2፡ ይህ ችግር ምን ያህል የተለመደ ነው? 🌡ከ2,500-4,000 በህይወት ከሚወለዱ ህጻናት መካከል በአንዱ የመከሰት እድል አለው። 🌡ይህ ማለት በሐገራችን 100,000 ህጻናት በአንድ ቀን ቢወለዱ 25 ህጻናት ይህ ችግር ይኖርባቸዋል ማለት ነው። ✍ጥያቄ-3፡  መንስኤው ምን ሊሆን ይችላል? 🩺 ትክክለኛው መንስኤ ሙሉ በሙሉ አይታወቅም። 🩺በእርግዝና መጀመሪያ ሳምንታት ላይ Diaphragm በትክክል ሳይዘጋ ሲቀር የሚፈጠር ችግር ነው። 🌡በአብዛኛው ያለምንም የሚታወቅ ምክንያት የሚከሰት ችግር ነው። 🌡በአንዳንድ ጊዜ ከዘረመል እክሎች  ወይም ከሌሎች የአፈጣጠር ችግሮች ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል። 💊ማስተዋል ያለብን ነገር በእርግዝና ወቅት  እናቶች ከሚያደርጉት ወይም ከማያደርጉት  ነገር ጋር የሚገናኝ ችግር አይደለም። ✍ጥያቄ-4: ይህ ችግር ያለባቸው  ሕፃናት  ምን አይነት ምልክት ያሳያሉ? 🌡ይህ ችግር ያለባቸው ሕፃናት ብዙውን ጊዜ ከተወለዱ በኋላ ወዲያውኑ ከስር የተዘረዘሩት ችግሮች ያጋጥሟቸዋል። 🌡 ከእነዚህም ውስጥ፡- 📍📍ከባድ የአተነፋፈስ ችግር (Severe respiratory Distress) 📍📍በዝቅተኛ ኦክስጅን ምክንያት የቆዳ መጥቆር ወይም ሰማያዊ መሆን(Cyanosis) 📍📍ፈጣን አተነፋፈስ እና ለመተንፈስ መቸገር 📍📍ወደ ውስጥ የሰመጠ ሆድ(Scaphoid Abdomen ) - ይህም የሆድ ዕቃ አካላት ወደ ደረት ስለሚገቡ ሆድ እቃ  ባዶ ይሆናል! 📍📍ችግሩ ባለበት ጎን ላይ የትንፋሽ ድምጽ መቀነስ ፣ አንዳንድ ጊዜ የልብ ድምፆች ወደ ተቃራኒው ጎን መሸሸት ✍ጥያቄ-5፡ ችግሩ መኖሩ እንዴት ማረጋገጥ ይቻላል? 🌡በእርግዝና ወቅት  በአልትራሳውንድ ምርመራ የመታወቅ እድል አለው። 🌡ከተወለደ በኋላ በደረት ራጅ(Chest X Ray) በደረት ውስጥ አንጀት እና ሌሎች የሆድ እቃ አካላት ሊታዩ ይችላሉ! 🌡Echocardiography (የልብ አልትራሳውንድ) : ይህ ምርመራ የሚደረገው የሳንባ የደም ግፊት መኖር አለመኖሩን ለማአቅና  እና ተያያዥ የልብ አፈጣጠር ችግሮችን  ለማወቅ ይረዳል፣። 🌡ሌላው እንዳይስፈላጊነቱ የደረት ሲቲ ስካን( Chest CT) ሊታዘዝ ይችላል! ✍ጥያቄ-6: የህክምና አሰጣጡ ምን ይመስላል? 👉ህክምናው የራሱ የሆነ የአሰራር ሒደት አለው! 🩻1. አፋጣኝ የሆነ  የማረጋጋት ህክምና(Immediate Stabilization) 💉ይህ ችግር ያለባቸው ህፃናት ከባድ የሆነ የአተነፋፈስ ችግር ካላቸው በማሽን(Mechanical Ventilator) በመታገዝ እንዲተነፍሱ ይደረጋል 💉 በአንዳንድ ሁኔታዎች ከሰውነት ውጭ ኦክስጅን እንዲያገኙ ይደረጋል ። ይህም በህክምና አጠራር ECMO (extracorporeal membrane oxygenation) ይባላል። 🩻2. በመድኃኒት የሚደረግ ድጋፍ(Medical Support) 🌡የpulmonary hypertension ለመቆጣጠር የሚረዱ መድሃኒቶች ሊሰጡ ይችላሉ። 🌡 በመርፌ  የሚሰጥ ምግብ ሊያስፈልጋቸው ይችላል። 🩻3. ቀዶ ህክምና( Surgery)- 💉ይህ ዋናው የህክምናው አይነት ሲሆን ከላይ በተዘረዘሩት ህክምናዎች የአተነፋፈሳቸ ሁኔታ ሲስተካከል የሚሰራ ህክምና ነው። 💉 ይህም  ወደ ደረት ውስጥ የገቡ የሆድ እቃ አካላትን  በመመለስ ዲያፍራም ላይ ያለውን ክፍተት መዝጋት ነው። 🩻4. ከቀዶ ጥገና በኋላ የሚደረጉ ህክምናወች 🌡 Surgery ከተሰራ በኋላ  ከፍተኛ ክትትል፣  የአተነፋፈስ ድጋፍ ፣ ቀስ በቀስ ደግሞ ምግብ መስጠት ያስፈልጋል። 🌡ዕድገታቸውንም ረዘም ላለ ጊዜ መከታተል ያስፈልጋል። ✍ጥያቄ-7፡ ምን አይነት ውጤት ይጠበቃል? 🌡 ይህ ችግር በጣም ከባድ እና ለሕይወት አስጊ የሆነ ችግር ነው። 🌡 የህክምናውን ውጤት የሚወሰኑ ብዙ ምክንያቶች አሉ: 💊💊የሳንባው መጠን እና ተግባር (Degree of pulmonary hypoplasia ) 💊💊የሳንባ ደም ስሮች ግፊት ክብደት( Severity of pulmonary hypertension) 💊💊ሌሎች ተያያዥ የአፈጣጠር ችግሮች መኖር አለመኖራቸው 💊💊ለህክምናው የሚሰጡት ምላሽ 💊💊ህክምናው የሚሰጥበት ቦታ! 💊💊ህክምናውን የሚሰጡት ባለሙያዎች ልምድ እና ብቃት 👉አሁን በደረስንበት ዘመናዊ የህክምና አሰጣጥ ይህ ችግር ያለባቸው ህጻናት ከህክምና በኋላ የመትረፍ እድላቸው ወደ 70-80% ተሻሽሏል። 🩺ሆኖም አንዳንድ ልጆች እንደሚከተሉት ያሉ ቀጣይ ችግሮች ሊኖራቸው ይችላል፡- 🌡🌡ቀጣይነት ያለው የአተነፋፈስ ችግር (Chronic Lung Disease- Asthma like symptoms) 🌡🌡የአመጋገብ ችግር ( Feeding Difficulties) 🌡🌡ቅርሻ ( Reflux) 🌡🌡የእድገት ውስንነት(Growth and Development Delays) 👁ስለዚህ ውድ ጠያቂያችን ልጅዎ የሚቻለውን ሁሉ ህክምና እያገኘች እንደሆን ተስፋ እናደርጋለን። 👁ሙሉ በሙሉ አገግማ ከሆስፒታል እንድትወጣ ምኞታችን ነው። 👁 በዚህ ጉዳይ ወይም በሌሎች ጉዳዬች  በማንኛውም ጊዜ ማንኛውንም ጥያቄ ለመጠየቅ ከስር ያለውን አድራሻ መጠቀም ይቻላል። 👇👇👇👇👇👇 📲+251911441651 💻ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት የtelegram ቻናላችንን ይቀላቀሉ: 👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/DrSaleamlakT ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን!!! እናመሰግናለን አዘጋጅ: ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ: የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም እና ረዳት ፕሮፌሰር Dr. Saleamlak Tigabie: MD, Consultant Pediatric Surgeon, FCS-ECSA

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 12 июл.1 4344

    ሰላም ዶክተር ለጄ ከተወለደ 8 ወሩ ነው በአንደኛው ኩላሊቱ ውሀ የቋጠረ ነገር አለ  ሰርጀሪ መደረግ አለበት አሉኝ :: በእርግዝና ወቅትም ጠቁመውኝ ነበር አሁን በጣም ጨነቀኝ። ከሙያ አንፃር ትንሽ በታብራራልኝ አመሰግናለሁ: :(የወላጅ ጥያቄ) 🌡🌡ውድ ጠያቂያችን  ለጥያቄዎ በጣም  እናመሰግናለን። 🌡🌡 ልጅዎ የኩላሊት ህመም እንዳለበት ማወቅ እና ቀዶ ጥገና እንደሚያስፈልገው ሲነግርዎ ማሰብና መጨነቅ ፍጹም ተፈጥሯዊ ነው። 🌡🌡ይህ መረጃ ለሌሎች ወላጆችም ጠቃሚ መስሎ ስለታዬን ለወላጆች ተስማሚ በሆነ እይታ ሁሉንም ነገር ደረጃ በደረጃ ለማስረዳት እንሞክራለን። ✍ጥያቄ 1: ኩላሊት ውሃ መቋጠር (Hydronephrosis)  ምንድን ነው? 🌡Hydronephrosis አንድ ወይም ሁለቱም ኩላሊቶች በሽንት ምክንያት ሲያብጡ የሚከሰት  ችግር ነው። 🌡 ሽንት የሚመነጨው በኩላሊት ሲሆን ureter በተባለ ትንሽ ቱቦ ውስጥ ይወርዳል እና ከሰውነት ከመውጣቱ በፊት ወደ ፊኛ ውስጥ ይከማቻል። 🌡 የሽንት ፍሰትን የሚዘጋ ወይም እንዲዘገይ ወይም ሽንት ወደ ኋላ እንዲመለስ የሚያደርግ ማንኛውም ችግር  ሽንት በኩላሊቱ ውስጥ እንዲከማች ያደርጋል። 🌡ይህም Hydronephrosis ይባላል። 💊በጊዜ ሂደት ይህ ግፊት ካልታከመ ኩላሊቱን ሊዘረጋ እና ሊጎዳ ይችላል። ✍ጥያቄ 2: ይህ ችግር ለምን ይከሰታል? 🌡የኩላሊት ውሃ የመቋጠር ችግር ብዙ ጊዜ የተለመደ ነው። 🌡 ማለትም ከመወለዱ በፊት ህጻኑ ገና በማህፀን ውስጥ እያለ የሚከሰት ችግር ነውና 🌡እንደ እውነቱ ከሆነ በእርግዝና ወቅት ብዙ ሕፃናት በultrasound ምርመራ ሲያደርጉ የመታየት እድል አለው። 🌡ይህም ቅድመ ወሊድ Hydronephrosis(Antenatal) ይባላል። 🌡በጣም የተለመደው ምክንያት ኩላሊቱ ከሽንት ቱቦ ጋር የሚገናኝበት ቦታ ላይ መጥበብ ወይም መዘጋት ሲሆን ይህም Pelvi-Ureteric Junction Obstruction (PUJO) ይባላል። 🌡ይህ በእርግዝና ወቅት ሊከላከሉት የሚችሉት ነገር አይደለም። 🌡 በጽንስ እድገት ጊዜ የሚከሰት እና ያልተለመደ ችግር ነው። ✍ጥያቄ 3:  ይህ ችግር አደገኛ ነው ወይ? 💊እንደ ከባድነቱ ይወሰናል፡-የራሱ የደረጃ አሰጣጥ ሒደት አለው! 🌡ቀላል ከሆ ህጻኑ እያደገ ሲሄድ ችግሩ ​​በራሱ ሊስተካከል ይችላል። 🌡እነዚህ በአብዛኛው በመደበኛ አልትራሳውንድ ክትትል ይደረግላቸዋል። 🌡ከመካከለኛ እስከ ከባድ በሆኑ ሁኔታዎች የቱቦ መዘጋቱ ሽንት እንዲመለስ፣ የኩላሊት እብጠት እንዲባባስ እና የኩላሊት ስራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲቀንስ ያደርጋል። 🌡ብዙውን ጊዜ ቀዶ ጥገና የሚያስፈልግባቸው ሁኔታዎች እነዚህ ናቸው። ✍ጥያቄ 4: ቀዶ ጥገና ለምን ይመከራል? 💊የቀዶ ጥገና ሕክምናን ያስፈልገዋል የምንለው ብዙውን ጊዜ የሚከተሉትን ሲያሟላ ነው: 💉እብጠቱ እየባሰ ሲሔድ 💉ሽንት በትክክል እየፈሰሰ ካልሆነ 💉በተለያዩ ምርመራዎች (እንደ MAG3 ወይም DTPA የኩላሊት ምርመራ) የኩላሊት ተግባር መቀነስ ካሳዬ 💉ህፃኑ በተደጋጋሚ የሽንት ቱቦ ኢንፌክሽን (UTIs) ወይም ህመም ህመም ካጋጠመውና 💉ሌሎች ተጨማሪ ምክንያቶች ካሉ ቀዶ ጥገና ያስፈልገዋል እንላለን! 💊የቀዶ ጥገናው ዓላማ የዘጋውን ክፍል ማስወገድ እና ሽንት ከኩላሊት ወደ ፊኛ በነፃነት እንዲፈስ ማድረግ ሲሆን ይህም ኩላሊት እንዳይጎዳ ይከላከላል። ✍ጥያቄ 5: ቀዶ ጥገናው ምንን ያካትታል? 💊ቀዶ ጥገና Pyeloplasty ይባላል። 💊የሚከተሉትን ያጠቃልላል: 💉💉የጠበበውን ክፍል በማስወገድ 💉💉ሰፊ መጋጠሚያ ለመፍጠር ጤናማ የሆኑትን ጫፎች እንደገና ማገናኘት 💉💉አንዳንድ ጊዜ ሽንት እንዲፈስ ለመርዳት ትንሽ የውስጥ ቱቦ (ስቴንት ተብሎ የሚጠራው) ለጊዜው ይቀመጣል። 💊ምናልባት ዘግይተው ከመጡና ከላሊት መሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሲሆን ሙሉ ኩላሊቱ ማውጣት ሊያስፈልግ ይችላል! ከምስሉ እንደሚታየው! ✍ጥያቄ 6: ከቀዶ ጥገና በኋላ ምን ይሆናል? 🌡አብዛኞቹ ሕፃናት በደንብ ይድናሉ። 🌡የክትትል ወቅት የUltrasound እና ሌሎች ምርመራዎች የኩላሊት ሁኔታ እና ተግባርን ለመፈተሽ ሊያስፈልጉ ይችላሉ። 🌡በአብዛኛዎቹ ሁኔታዎች የኩላሊት ተግባር ይሻሻላል። 🌡አልፎ አልፎ ምልክቶቹ ከቀጠሉ ሁለተኛ ቀዶ ጥገና ሊያስፈልግ ይችላል! ✍ጥያቄ 7: በረጅም ጊዜ ውጤቱ ምን ይመስላል? 🌡በወቅቱ ህክምና ከተደረገ አብዛኛዎቹ ልጆች ጤነኛ እና ስራውን የሚያከናውን ኩላሊት ይኖራቸዋል። 🌡 የPUJO ቀዶ ጥገና በጣም ከፍተኛ የስኬት መጠን (ከ95% በላይ) ያለው የቀዶ ህክምና አይነት ነው። 🩺ስለዚህ ጠያቂያችን ይህ ጊዜ ለእርስዎ አስጨናቂ እንደሆነ እንረዳለን። 🩺እባኮትን ይህ ሊታከም የሚችል ህመም መሆኑን እርግጠኛ ይሁኑ 🩺እናም እያንዳንዱን ነገር ከሚሰራው ሐኪም  በመነጋገር አስፈላጊውን ነገር ያድርጉ። እናመሰግናለን!!! ህፃናት በሁሉም ቦታ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ እንሰራለን!!! አዘጋጅ ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ:     የህፃናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር Dr. Saleamlak Tigabie:     MD, Pediatric Surgeon, assist. Prof of Pediatric Surgery @YK12HMC, FCS-ECSA   ለማንኛውም መረጃ እና ነፃ የምክር አገልግሎት : 📱0911441651 https://t.me/DrSaleamlakT https://www.facebook.com/ዶር-ሳለአምላክ-ጥጋቤ-Pediatric-Surgeon-100878625359706/

ዶ/ር ሳለአምላክ ጥጋቤ: የህጻናት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት እና ረ. ፕሮፌሰር (Ass. Prof. Of Pediatric Surgery) — tgindex