tgindex
እግዚአብሔርን ማወቅ

እግዚአብሔርን ማወቅ

Статистика

ሰላምታ በተለዋወጥን ቁጥር ይመስገን ስለምንለው አምላካችንና አባታችን እግዚአብሔር ያለንን ዕውቀት ለማዳበር የሚያግዝ ቻነል ነው፡፡

Последний пост
15 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
24
Всего постов
30
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
949
+6 за 3 дн.
Сутки
+3
+0,32%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
64
28 постов
Вовлечённость
6,7%
к подписчикам
Постов в день
3,4
всего 30
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
65
1/48двое суток
74
1/72трое суток
80

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • የሐዋርያት ሥራ ጥናት :: ክፍል 70 :: ቅዱስ ጳውሎስ በንጉሡ አግሪጳ ፊት መቅረቡ ፡፡   ከክፍል 69 ባጭሩ :: ከጥቂት ቀንም በኋላ ንጉሡ አግሪጳ በርኒቄም ለፊስጦስ ሰላምታ እንዲያቀርቡ ወደ ቂሳርያ ወረዱ። ..ፊስጦስ የጳውሎስን ነገር ለንጉሡ እንዲህ ብሎ ገለጠ። ፊልክስ አስሮ የተወው አንድ ሰው በዚህ አለ፤ ..የካህናት አለቆችና የአይሁድ ሽማግሌዎች እፈርድበት ዘንድ እየለመኑ ስለ እርሱ አመለከቱኝ። ..ከሳሾቹም ..እኔ ያሰብሁትን ክፉ ነገር ክስ ምንም አላመጡበትም፤ ..አግሪጳም ፊስጦስን፡- ያንንስ ሰው እኔ ዳግም እኮ እሰማው ዘንድ እወድ ነበር አለው። እርሱም፡- ነገ ትሰማዋለህ አለው ( የሐዋ 25 ÷ 13 – 22 ) ። -----------/////----------   በነገውም አግሪጳና በርኒቄ በብዙ ግርማ መጥተው ከሻለቆችና ከከተማው ታላላቆች ጋር ወደ ፍርድ ቤት ገቡ፤ ፊስጦስም ባዘዘ ጊዜ ጳውሎስን አመጡት። ፊስጦስም አለ። አግሪጳ ንጉሥ ሆይ እናንተም ከእኛ ጋር ያላችሁ ሰዎች ሁሉ፥ ከእንግዲህ ወዲህ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንዳይገባው እየጮኹ የአይሁድ ሕዝብ ሁሉ በኢየሩሳሌም በዚህም ስለ እርሱ የለመኑኝን ይህን ሰው ታዩታላችሁ። እኔ ግን ሞት የሚገባውን ነገር እንዳላደረገ አስተዋልሁ፥ እርሱም :- ወደ አውግስጦስ ይግባኝ ስላለ እሰደው ዘንድ ቈረጥሁ። ስለ እርሱም ወደ ጌታዬ የምጽፈው እርግጥ ነገር የለኝም፤ ስለዚህ ከተመረመረ በኋላ የምጽፈውን ነገር አገኝ ዘንድ በፊታችሁ ይልቁንም በፊትህ፥ ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፥ አመጣሁት፤ እስረኛ ሲላክ የተከሰሰበትን ምክንያት ደግሞ አለማመልከት ሞኝነት መስሎኛልና ( የሐዋ 25 ÷ 33 – 27 ) ።   ማብራሪያ ቅዱስ ጳውሎስ በእስር ቤት የመሆኑ ምክንያት ስለ ክርስቶስ በመስበኩ ነው፡፡ አገረ ገዢው ፊስጦስ ስለ ጳውሎስ ለንጉሡ አግሪጳ ሲነግረው ጳውሎስን ሊሰማው ፈለገ፡፡ ሲነጋ ንጉሡ አግሪጳ ከብዙ ሰዎች ጋር ወደ ፍርድ ቤት መጣ፡፡ ጳውሎስም እንዲመጣ ታዘዘ፡፡ አገረ ገዢው ፊስጦስ አይሁድ መገደል አለበት የሚሉትን ጳውሎስ ለመገደል የሚያበቃውን ነገር እንዳላደረገ አስረዳ፡፡ ጳውሎስ :- ይግባኝ ማለቱንም ገለጠ፡፡ ጳውሎስ :- ይግባኝ ሲል ወደ ሮም ሄዶ በንጉሠ ነገሥቱ አውግስጦስ ፊት ከአይሁድ ጋር መከራከር ፈልጎ ነው፡፡ አገረ ገዢው ፊስጦስ ጳውሎስን ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ወደ ሮም ሲልከው የታወቀ ነገር ሊኖረው ያስፈልገዋል፡፡ ጳውሎስ ደግሞ ምንም ጥፋት ስላልተገኘበት መፈታት ነበረበት፡፡ አገረ ገዢው ከሚሰሙትና ከንጉሡ አግሪጳ ሀሳብ ለመቀበል ፈልጎ ነው እያወራቸው ያለው፡፡ ጳውሎስ በከሳሾቹ አይሁድ ተከሶ ቢታሰርም ምንም ጥፋት የሌለበት ሆኖ ተገኝቶአል፡፡ በከሳሾቻችን ፊት እንደ ጳውሎስ ምንም ጥፋት ሳይገኝብን ሲቀር ያስደስታል፡፡   በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ቅዳሴ ሲቀደስ የሐዋርያት ሥራ ይነበባል ፡፡ ይቀጥላል፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡፡ አሜን! ✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

  • ✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

  • እግዚአብሔር ድብቅ ጦርን ያስነሣል፡፡   እግዚአብሔርም ኢያሱን፡- አትፍራ፥ አትደንግጥ፤ ሰልፈኞችን ሁሉ ከአንተ ጋር ውሰድ፥ ተነሥተህም ወደ ጋይ ውጣ፤ እይ፥ የጋይን ንጉሥ ሕዝቡንም ከተማውንም ምድሩንም በእጅህ ሰጥቼሃለሁ። በኢያሪኮና በንጉሥዋም እንዳደረግህ እንዲሁ በጋይና በንጉሥዋ ታደርጋለህ፤ .. ከከተማይቱም በስተ ኋላ ድብቅ ጦር አስቀምጥ አለው።  ኢያሱም ሰልፈኞቹም ሁሉ ወደ ጋይ ሊወጡ ተነሡ፤ ኢያሱም ጽኑዓን ኃያላን የሆኑትን ሠላሳ ሺህ ሰዎች መረጠ በሌሊትም ሰደዳቸው፥ እንዲህም ብሎ አዘዛቸው። እነሆ፥ ከከተማይቱ በስተ ኋላ ተደበቁ፤ ከከተማይቱ አትራቁ፥ ሁላችሁም ተዘጋጁ፤ እኔ ከእኔም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ወደ ከተማይቱ እንቀርባለን፤ እኛንም ሊገናኙ ..በወጡ ጊዜ ከፊታቸው እንሸሻለን፤ ..የምንሸሽ ይመስላቸዋልና ከከተማይቱ እስክናርቃቸው ድረስ ወጥተው ይከተሉናል፤ እኛም ከፊታቸው እንሸሻለን። እናንተም ከተደበቃችሁበት ስፍራ ተነሡ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር እርስዋን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣልና ከተማይቱን  ያዙ። በያዛችኋትም ጊዜ ከተማይቱን በእሳት አቃጥሉአት፤ ..ኢያሱም ሰደዳቸው፤ ወደሚደበቁበትም ስፍራ ሄዱ፥ ..ኢያሱ ግን በዚያች ሌሊት በሕዝቡ መካከል አደረ።   ኢያሱም ማልዶ ተነሣ፥ ሕዝቡንም አሰለፈ፤ እርሱም የእስራኤልም ሽማግሌዎች ከሕዝቡ በፊት ወደ ጋይ ወጡ። ከእርሱም ጋር የነበሩ ሰልፈኞች ሁሉ ወጥተው ቀረቡ፥ ወደ ከተማይቱም ፊት ደረሱ፥ ..አምስት ሺህ ያህል ሰዎችንም ወስዶ ..በከተማይቱም በምዕራብ በኩል ደብቆ አስቀመጣቸው። በከተማይቱ በሰሜን በኩል የነበሩትን ሠራዊት ሁሉ በከተማይቱም በምዕራብ በኩል የተደበቁትን ሕዝብ አኖሩ፤ ..የጋይም ንጉሥ ባየ ጊዜ የከተማይቱ ሰዎች ቸኵለው በማለዳ ተነሡ፤ እርሱና ሕዝቡም ሁሉ በተወሰነው ጊዜ ..እስራኤልን በሰልፍ ለመገናኘት ወጡ፤ ከከተማይቱ በስተ ኋላ ግን ድብቅ ጦር እንዳለ አያውቅም ነበር። ኢያሱም እስራኤልም ሁሉ ድል የተነሡ መስለው ከፊታቸው በምድረ በዳው መንገድ ሸሹ። በከተማይቱም የነበሩ ሰዎች ሁሉ ሊያሳድዱአቸው ተጠሩ፤ ኢያሱንም አሳደዱት፥ ከከተማይቱም እንዲርቁ አደረጓቸው። ..እስራኤልን ለማሳደድ ያልወጣ ሰው አልነበረም፤ ከተማይቱንም ከፍተው ተዉ፥ እስራኤልንም አሳደዱት።  እግዚአብሔር ኢያሱን፡- ጋይን በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁና በእጅህ ያለውን ጦር በላይዋ ዘርጋ አለው፤ ኢያሱም በእጁ ያለውን ጦር በከተማይቱ ላይ ዘረጋ። የተደበቁትም ፈጥነው ከስፍራቸው ተነሡ፥ ኢያሱም እጁን በዘረጋ ጊዜ ሮጡ፥ ወደ ከተማይቱም ገብተው ያዙአት፤ ፈጥነውም ከተማይቱን በእሳት አቃጠሉአት። የጋይም ሰዎች ወደ ኋላቸው ዞረው የከተማይቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፥ ወዲህና ወዲያም መሸሽ አልቻሉም፤ ወደ ምድረ በዳም የሸሹ ሕዝብ በሚያሳድዱአቸው ላይ ተመለሱ። ኢያሱም እስራኤልም ሁሉ ተደብቀው የነበሩት ከተማይቱን እንደ ያዙ፥ የከተማይቱም ጢስ እንደ ተነሣ ባዩ ጊዜ ወደ ኋላ ተመልሰው የጋይን ሰዎች ገደሉ። ሌሎቹም በላያቸው ከከተማይቱ ወጡ፤ የጋይም ሰዎች በእስራኤል መካከል ሆኑ፥ እስራኤልም ከበቡአቸው፤ አንድ እንኳ ሳይቀር ሳያመልጥም ገደሉአቸው። የጋይንም ንጉሥ ሳይሞት ይዘው ወደ ኢያሱ አመጡት።  ..ኢያሱም በጋይ የሚኖሩትን ሁሉ ፈጽሞ እስኪያጠፋ ድረስ ጦር የዘረጋባትን እጁን አላጠፈም። ..የጋይንም ንጉሥ እስከ ማታ ድረስ በዛፍ ላይ ሰቀለው፤ ፀሐይም በገባች ጊዜ ኢያሱ አዘዘ፥ ሬሳውንም ከዛፍ አወረዱት፥ በከተማይቱም በር አደባባይ ጣሉት፥ በላዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩበት ( ኢያሱ 8 ÷ 1 – 29 ) ።    ማብራሪያ እግዚአብሔር ለኢያሱና ለእስራኤል ሕዝብ ዙሪያዋን ቅጥር ያላትን የኢያሪኮን ከተማ ቅጥርዋ እንዲወድቅ አድርጎ በኢያሪኮ ንጉሥና በሕዝብዋ ላይ ድልን አቀዳጅቶአቸው ነበር፡፡ ማነው ባለሳምንት ካላችሁኝ ደግሞ ጋይና ንጉሥዋ ናቸው፡፡ ኢያሱና የእስራኤል ጦር ጋይን የሚወጉ መስለው ወደ ጋይ ከተማ መጡ፡፡ የጋይ ሰዎች ከከተማቸው ጀርባ የተደበቀ የእስራኤል ድብቅ ጦር እንዳለ አላወቁም፡፡ የጋይ ንጉሥና ሕዝቡ እስራኤላውያን ወደ ከተማቸው እየመጡ መሆናቸውን ሲያዩ ሊወጉአቸው ተነሡ፡፡ ኢያሱና ሕዝቡ የፈሩ መስለው ሸሹ፡፡ የጋይ ሕዝብ ግልብጥ ብሎ ከከተማቸው ኢያሱንና እስራኤልን ለማሳደድ ወጡ፡፡ ግቢያችን የገባን ሌባ ለማሳዳድ የግቢያችንን በር ክፍት አድርገን ትተን ሌባውን ለማሳደድ ብንወጣ መንገድ አላፊ ዘው ብሎ መግባት እንደሚችል የጋይ ሕዝብ ከከተማው ተነቅለው እስራኤልን ለማሳደድ ሲወጡ የተደበቁት የእስራኤል ድብቅ ጦር ወደ ከተማይቱ ገቡና ከተማይቱን በእሳት አቃጠሉአት፡፡ የጋይ ሰዎች ወደ ኃላቸው ዞረው ሲመለከቱ ከተማቸው ተቃጥላ ጢሱ ወደ ሰማይ ደርሶ አዩ፡፡ የሸሹ የመሰሉትም ኢያሱና ሕዝቡ በኢያሱ በኩል እግዚአብሔር መሸሻቸውን ትተው መዋጋት እንዲጀምሩ ውጊያውን አስጀምሮአቸው ነበርና መሸሹን ትተው የጋይን ሰዎች ከፊት ለፊት መውጋት ጀምረው ነበር፡፡ ከተማይቱን ያቃጠሉት ድብቅ ጦር ደግሞ ከኋላ ውጊያውን ተቀላቀሉ፡፡ የጋይ ሰዎች ከፊትም ከኋላም በእስራኤል ጦር ተከበው እንደ ሳንዱች ሆኑ ፡፡ አንድም የጋይ ሰው ሳያመልጥ ሁሉም ተገደሉ፡፡ የጋይንም ንጉሥ ይዘው ሰቅለው ገደሉት፡፡ ኢያሱና እስራኤል ድል ሊነሡ የቻሉት የድብቁን ጦር ስልት በመቀየሳቸው ነበር፡፡ የድብቁን ጦር ስልት ለኢያሱ የነገረው ደግሞ የእስራኤል የጦር መሪ ብንለው አይበዛበትም ቢያንስበት እንጂ እግዚአብሔር ነበር፡፡ ከመነሻው ኢያሱን፡- አይዞህ አትፍራ ብሎ ያበረታታ እግዚአብሔር በሚመጣብን ሰልፍ እንዳንፈራ የሚያበረታታ የጦር መሪ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚመጣፈብንን ተግዳሮት እንዴት ማሸነፍ እንዳለብን ስልትን ጭምር በመቀየስ የሚነግረን አምላክ ነው፡፡ ድብቅ ጦር በሚያስፈልግ ግዜ ድብቅ ጦርን የሚያስነሣልን አምላክ ነው፡፡ እንደ ሳንዱች አድርጎ ጠላትን ድል ከማድረግ በላይ የሚያስደስት ነገር ምን አለ? ወደኛ የሚመጣ ማንኛውም ክፉ ነገርን በሙሉ እንዲህ አድርጎ መቋጫ ያበጅለታል፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ከእግዚአብሔር ጋር መኖር ታዲያ ደስ አይልም! እግዚአብሔርን እያመለኩና እየታዘዙ መኖር ታላቅ ጥቅም አለው፡፡ እንዲህ ብለን ልንገልጸው የማንችለው ትልቅ ጥቅም፡፡ በችግራችን ፣ በሀዘናችን፣ በመከራችን ፣ ሰልፍ በበዛብን ጊዜ ወ.ዘ.ተ የማይለይ አምላክ እኮ ነው፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሁሌም የምጽፍላችሁ ወድጄ አይደለም፡፡ የምናመልከው እግዚአብሔር ድንቅ አምላክ በመሆኑ ሁሌም ድንቁን እየሰማንና እያነበብን በፈቀደልን ዘመን እንድንኖር ነው፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡ አሜን! ✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

  • ✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

  • የሐዋርያት ሥራ ጥናት ፡፡ ክፍል 69 ፡፡ ንጉሡ አግሪጳ ጳውሎስን ሊሰማው መፈለጉ ፡፡   ከክፍል 68 ባጭሩ ፡፡ ጳውሎስ.. ፡- ..ወደ ቄሣር ይግባኝ ብዬአለሁ አለ። በዚያን ጊዜ ፊስጦስ ከአማካሪዎቹ ጋር ተማክሮ፡- ወደ ቄሣር ይግባኝ ብለሃል፤ ወደ ቄሣር ትሄዳለህ ብሎ መለሰለት ( የሐዋ 25 ÷ 1 – 12 ) ። -----------/////----------   ከጥቂት ቀንም በኋላ ንጉሡ አግሪጳ በርኒቄም ለፊስጦስ ሰላምታ እንዲያቀርቡ ወደ ቂሳርያ ወረዱ። በዚያውም ብዙ ቀን ስለተቀመጡ ፊስጦስ የጳውሎስን ነገር ለንጉሡ እንዲህ ብሎ ገለጠ። ፊልክስ አስሮ የተወው አንድ ሰው በዚህ አለ፤ በኢየሩሳሌምም ሳለሁ የካህናት አለቆችና የአይሁድ ሽማግሌዎች እፈርድበት ዘንድ እየለመኑ ስለ እርሱ አመለከቱኝ። እኔም፡- ተከሳሹ በከሳሾቹ ፊት ለፊት ሳይቆም ለተከሰሰበትም መልስ ይሰጥ ዘንድ ፈንታ ሳያገኝ፥ ማንንም ቢሆን አሳልፎ መስጠት የሮማውያን ሥርዓት አይደለም ብዬ መለስሁላቸው። ስለዚህም በዚህ በተሰበሰቡ ጊዜ፥ ሳልዘገይ በማግሥቱ በፍርድ ወንበር ተቀምጬ ያንን ሰው ያመጡት ዘንድ አዘዝሁ። ከሳሾቹም በቆሙ ጊዜ እኔ ያሰብሁትን ክፉ ነገር ክስ ምንም አላመጡበትም፤ ነገር ግን ስለ ገዛ ሃይማኖታቸውና ጳውሎስ፡- ሕያው ነው ስለሚለው ስለ ሞተው ኢየሱስ ስለ ተባለው ከእርሱ ጋር ይከራከሩ ነበር። እኔም ይህን ነገር እንዴት እንድመረምር አመንትቼ፡- ወደ ኢየሩሳሌም ሄደህ በዚህ ነገር ከዚያ ልትፋረድ ትወዳለህን? አልሁት። ጳውሎስ ግን አውግስጦስ ቄሣር እስኪቈርጥ ድረስ እንዲጠበቅ ፡- ይግባኝ ባለ ጊዜ፥ ወደ ቄሣር እስክሰደው ድረስ ይጠበቅ ዘንድ አዘዝሁ። አግሪጳም ፊስጦስን፡- ያንንስ ሰው እኔ ዳግም እኮ እሰማው ዘንድ እወድ ነበር አለው። እርሱም፡- ነገ ትሰማዋለህ አለው ( የሐዋ 25 ÷ 13 – 22 ) ።   ማብራሪያ ፊስጦስ ጳውሎስን በእስር ቤት እንዲቆይ ያደረገው፡- ወደ ኢየሩሳሌም ሄደህ ተከራከር ቢለው  ስላልፈለገና ቄሣር ተብሎ በሚጠራው በሮም መንግሥት ፊት መከራከር መርጦ፡- ይግባኝ በማለቱ ነው፡፡ ወደ ሮም መሄዱም የማይቀር ነው፡፡ ንጉሡ አግሪጳ ከሌሎች ሰዎች ጋር ወደ አገረ ገዢው ፊስጦስ በመጣ ሰዓት ስለ ጳውሎስ ነገረው፡፡ ከሳሾቹ አይሁድ የሚከሰቱትም ምንም ክፉ ነገር አግኝተውበት ሳይሆን ከሞት ተነሥቶአል ብሎ ስለሚሰብከው ስለ ኢየሱስ እንደ ሆነ አስረዳው፡፡ ንጉሡ አግሪጳ ለፊስጦስ ጳውሎስን ሊሰማው እንደሚፈልግ ገለጠለት፡፡ ለነገም ቀጠሮ ተያዘ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ውሎ አዳሩ በእስር ቤት ከሆነ በትንሹ ሁለት ዓመት ሆኖታል፡፡ መከራውን እንደ ሙሉ ደስታ የቆጠረ ሰው ነው፡፡ በሕይወታችን መከራ ሲገጥመን ከቅዱስ ጳውሎስ መማር ይኖርብናል፡፡ የቅዱሳንን ሕይወት ማወቅ ጠቀሚታው ለዚህ ነው፡፡ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን ቅዳሴ ሲቀደስ የሐዋርያት ሥራ ይነበባል ፡፡ ይቀጥላል፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡፡ አሜን! ✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

  • ✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

  • የበደልነው እያለ ያልበደልናቸው ኃጢአታችንን ሲመዙ ፡፡   ከፈሪሳውያንም አንድ ከእርሱ ጋር ይበላ ዘንድ ለመነው፤ በፈሪሳዊው ቤትም ገብቶ በማዕድ ተቀመጠ። እነሆም በዚያች ከተማ ኃጢአተኛ የነበረች አንዲት ሴት፤ በፈሪሳዊው ቤት በማዕድ እንደ ተቀመጠ ባወቀች ጊዜ፥ ሽቱ የሞላበት የአልባስጥሮስ ቢልቃጥ አመጣች። በስተ ኋላውም በእግሩ አጠገብ ቆማ እያለቀሰች በእንባዋ እግሩን ታርስ ጀመረች፥ በራስ ጠጕርዋም ታብሰው እግሩንም ትስመው ሽቱም ትቀባው ነበረች። የጠራው ፈሪሳዊም አይቶ፡- ይህስ ነቢይ ቢሆን፥ ይህች የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች እንዴትስ እንደ ነበረች ባወቀ ነበር፥ ኃጢአተኛ ናትና ብሎ በልቡ አሰበ። ኢየሱስም መልሶ፡- ስምዖን ሆይ፥ የምነግርህ ነገር አለኝ አለው። እርሱም። መምህር ሆይ፥ ተናገር አለ። ለአንድ አበዳሪ ሁለት ተበዳሪዎች ነበሩት በአንዱ አምስት መቶ ዲናር ነበረበት በሁለተኛውም አምሳ። የሚከፍሉትም ቢያጡ ለሁለቱም ተወላቸው። እንግዲህ ከእነርሱ አብልጦ የሚወደው ማንኛው ነው? ስምዖንም መልሶ፡- ብዙ የተወለቱ ይመስለኛል አለ። እርሱም፡- በእውነት ፈረድህ አለው። ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው። ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፥ ውኃ ስንኳ ለእግሬ አላቀረብህልኝም፤ እርስዋ ግን በእንባዋ እግሬን አራሰች በጠጕርዋም አበሰች። አንተ አልሳምኸኝም፤ እርስዋ ግን ከገባሁ ጀምራ እግሬን ከመሳም አላቋረጠችም። አንተ ራሴን ዘይት አልቀባኸኝም፤ እርስዋ ግን እግሬን ሽቱ ቀባች። ስለዚህ እልሃለሁ፥ እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ኃጢአትዋ ተሰርዮላታል፤ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል። እርስዋንም፡- ኃጢአትሽ ተሰርዮልሻል አላት። ከእርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጠው የነበሩት በልባቸው፡- ኃጢአትን እንኳ የሚያስተሰርይ ይህ ማን ነው? ይሉ ጀመር። ሴቲቱንም፡- እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ አላት ( ሉቃ 7 ÷ 36 - 50 ) ።   ማብራሪያ ፈሪሳውያን ራሳቸውን ጻድቃን አድርገው በመቁጠር ሌሎችን የሚንቁ ናቸው፡፡ ስምዖን  ሳይጠራት በቤቱ የተገኘችው ሴት እሱ እንደሚያውቃት በከተማው የታወቀች ኃጢአተኛ ነበረች፤ ኃጢአተኛ ሆና መኖር ሰልችቷት በደልዋ እንደ አደፈ ልብስ ከላይዋ እንዲገፈፍላት የመጣች ሴት ነበረች፡፡ ሁሌ እየበደለች መኖር ሰልችቷት ይቅር እንድትባል ብትመጣም ስምዖን  ግን በትናንትናና በድሮ ማንነቷ እያሰባት ነበር፡፡ እርሱን ሳይሆን ጌታችን ኢየሱስን ለዳሰሰችው ተጸየፋት፡፡ ምን ፈልጋ እንደመጣች ባይረዳም ኃጢአቷ አስጨንቋት ይቅር እንድትባል እያለቀሰች ስታነባ የሚፈሳትን እንባ እንኳን አይቶ አልራራላትም ፡፡ ስምዖን ራሱ ኃጢአተኛ ነበር፡፡ ስሞዖን የሴቲቱን ኃጢአት እንዳየ፣ ጌታችን ኢየሱስ የስምዖንን ቢያይ ኖሮ ቤቱ እንዲመጣለት ባልተገባው ነበር፡፡ ስሞዖን እንደ ሴቲቱ ኃጢአተኛ ሆኖ ሳለ ጌታችን ኢየሱስ ወደ ቤቱ ቢገባለት እርሱ ግን ሴቲቱ ስትዳስሰው የማይገባት አድርጎ ቆጠራት፡፡ ሰው ኃጢአተኛ መሆኑ እየተሰማው በእግዚአብሔር ፊት መቅረብ ፈልጎ ከብዶት ሲተው ሴቲቱ ግን ከመቅረት ወደ ኋላ ያላለች፣ ሸክም በዝቶባት ይቅርታ ፈልጋ የሄደች ነበረች፡፡ ክርስቶስ ሴቲቲ ማን እንደሆነች ያውቅ ነበር፡፡ አውቆም ነው እንድትዳስሰው የፈቀደላት ፡፡ ነቢይ ቢሆን ግን የምትዳስሰው ማን እንደ ሆነች ባወቀ ነበር ብሎ በልቡ ለተናገረው ቃል መልስ ተሰጠው፡፡ ኢየሱስ ሴቲቱ ያደረገችውን ነገር በስምዖን ፊት አንድ በአንድ በመጥቀስ ያበጀ ሥራ እንደ ሠራች መሰከረላት፡፡ በእንባዋ እግሩን ያራሰችውን ፣ በጠጉሯም ያበሰችውን በማንሣት ስምዖን ግን ውኃ ለእግሩ እንዳላቀረበለት ነገረው፡፡ እርሷ እግሩን ስትስመው ስምዖን ግን እንዳልሳመው አስረዳው፡፡ ስምዖን ያመጣችውን ሽቶ ከቁብ ባይቆጥረውም ኢየሱስ ግን በሽቶ እርሷ እግሩን ስትቀባው ስምዖን ግን ራሱን ዘይት እንዳልቀባው ነገረው፡፡ ስምዖን ያላደረገለትን ሴቲቱ እንዳደረገችለት ከነገረው በኋላ ስምዖን ፡- ኃጢአተኛ ናት ያላትን ሴት ኃጢአትዋ ተሰርዮላታል አለው፡፡ ስምዖን ለመውቀስ ኃጢአተኛነቷን ሲያነሣ ክርስቶስ ግን ኃጢአተኛነቷን ያነሣው ተሰርዮልሻል ለማለት ነበር፡፡ በክርስትናችን ከሚገጥሙን ተግዳሮት አንዱ እንደ ስምዖን ባሉ ሰዎች መከሰስ ነው፡፡ የራሳቸውን ድካም ትተው ( ረስተው ) በሰዎች ድካም ላይ ዓይናቸውን የሚጥሉ ይቅርታ ሲያጡ፣ የራሳቸውን ግን የሚያዩ ይቅርታ ያገኛሉ፡፡ የልባችንን የሚያውቅ እኛን ይቅር ሲለን፣ የልባችንን የማያውቁ እነርሱ በከሳሽ ወንበር ተቀምጠው ይቅርታ ሳይሰጣቸው ይቀራሉ፡፡ ሰዎች ስለኛ ደካሞቹ ሲያስቡ ሁሌም ኃጢአት ለመሥራት የምንፈልግ ቢመስላቸውም የእኛ ግን መሻታችን ለበደልነው ፡- ይቅር ተብለን  በቀጣይ ደግሞ ላለመበደል ነው፡፡  ምክንያቱም ሁሌ እየበደሉ መኖር ይሰለቻል ፡፡ ዕዳን ሳይጨርሱ በመበደር ሌላ ዕዳን እንደ መጨመር ነውና፡፡ እንደ ስምዖን ያሉ ከሳሾችን ትተን መሐሪውን ኢየሱስን ብቻ እናስብ፡፡ የከሳሾቻችንን መላስ የሚዘጋ የአምላካችን ቃል እስኪመጣ ድረስ የሚሉንን ወደ ጎን በመተው ሁሌ ፊቱን መፈለጋችንን አንተው፡፡ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ የመጣው ደካማነታቸውን አውቀው ለሚሹት ነው፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡፡ አሜን! ✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

  • ✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

  • የሐዋርያት ሥራ ጥናት :: ክፍል 68 :: አይሁድ ይረቱት ዘንድ በጳውሎስ ላይ ብዙ ክስ ማቅረባቸው ፡፡   ከክፍል 67 ባጭሩ :: ሁለት ዓመትም ከሞላ በኋላ ..ፊስጦስ በፊልክስ ፈንታ ተተካ። ፊልክስም አይሁድን ደስ ያሰኝ ዘንድ ወዶ ጳውሎስን እንደ ታሰረ ተወው  ( የሐዋ 24 ÷ 23 – 27 ) ፡፡ -----------/////----------   ፊስጦስም ወደ አውራጃው ገብቶ ከሦስት ቀን በኋላ ከቂሣርያ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። የካህናቱ አለቆችና የአይሁድም ታላላቆች በጳውሎስ ላይ አመለከቱ፥ ጳውሎስንም ሲቃወም እንዲያደላላቸው እየለመኑ፥ በመንገድ ሸምቀው ይገድሉት ዘንድ አስበው ወደ ኢየሩሳሌም እንዲያስመጣው ማለዱት። ፊስጦስ ግን ጳውሎስ በቂሳርያ እንዲጠበቅ እርሱም ራሱ ወደዚያ ፈጥኖ ይሄድ ዘንድ እንዳለው መለሰላቸው፤ እንግዲህ በዚህ ሰው ክፋት ቢሆን ከእናንተ ዘንድ ያሉት ባለ ስልጣኖች ከእኔ ጋር ወርደው ይክሰሱት አላቸው። በእነርሱም ዘንድ ከስምንት ወይም ከአስር የማይበልጥ ቀን ተቀምጦ ወደ ቂሳርያ ወረደ፤ በነገውም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ጳውሎስን ያመጡት ዘንድ አዘዘ። በቀረበም ጊዜ ከኢየሩሳሌም የወረዱት አይሁድ ከበውት ቆሙ፥ ይረቱበትም ዘንድ የማይችሉትን ብዙና ከባድ ክስ አነሡበት፤ ጳውሎስም ሲምዋገት፡- የአይሁድን ሕግ ቢሆን መቅደስንም ቢሆን ቄሣርንም ቢሆን አንዳች ስንኳ አልበደልሁም አለ። ፊስጦስ ግን አይሁድን ደስ ያሰኝ ዘንድ ወዶ ጳውሎስን፡- ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተህ ስለዚህ ነገር ከዚያው በፊቴ ትፋረድ ዘንድ ትወዳለህን? ብሎ መለሰለት። ጳውሎስ ግን፡- እፋረድበት ዘንድ በሚገባኝ በቄሳር ፍርድ ወንበር ፊት ቆሜአለሁ። አንተው ደግሞ ፈጽመህ እንደምታውቅ አይሁድን ምንም አልበደልሁም። እንግዲህ በድዬ ወይም ሞት የሚገባውን ነገር አድርጌ እንደ ሆነ ከሞት ልዳን አልልም፤ እነዚህ የሚከሱኝ ክስ ከንቱ እንደሆነ ግን ለእነርሱ አሳልፎ ይሰጠኝ ዘንድ ማንም አይችልም፤ ወደ ቄሣር ይግባኝ ብዬአለሁ አለ። በዚያን ጊዜ ፊስጦስ ከአማካሪዎቹ ጋር ተማክሮ፡- ወደ ቄሣር ይግባኝ ብለሃል፤ ወደ ቄሣር ትሄዳለህ ብሎ መለሰለት ( የሐዋ 25 ÷ 1 – 12 ) ።   ማብራሪያ አገረ ገዢው ፊልክስ ጳውሎስን እንደ ታሰረ ተወው፡፡ በእርሱ ፋንታ ለተተካው ፊስጦስ አይሁድ በጳውሎስ ላይ ያላቸውን ክሳቸውን አነሡ፡፡ እንዲያደላላቸውም ለመኑት፡፡ ጳውሎስ የታሰረው ቂሳርያ ነበርና ወደ ኢየሩሳሌም እንዲያመጣውና አድብተውም ሊገድሉት ፈለጉ፡፡ አገረ ገዢው ፊስጦስ ወደ ቂሳርያ ወረደ ፡፡ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ ሳለ ጳውሎስን እንዲያመጡት አዘዘ፡፡ አይሁድ በጳውሎስ ላይ ብዙና ከባድ ክስ አቀረቡበት ፡፡ መርታት ግን አልቻሉም፡፡ ጳውሎስም በቀረበበት ክስ ዝም ሳይል ምንም እንዳልበደለ አስረዳ፡፡ አይሁድን ደስ ለማሰኘት ፈልጎ፡-  ወደ ኢየሩሳሌም ሄደህ መከራከር ትፈልጋለህን? ብሎ አገረ ገዢው ለጠየቀው ጥያቄ አለመፈለጉን ገለጠ፡፡ ወደ ቄሣርም ይግባኝ አለ፡፡ ቄሣር ማለት የሮም መንግሥት የሚጠራበት ስም ነው፡፡ አይሁድ በወቅቱ በሮማውያን ቅኝ ግዛት የተያዙበት ጊዜ ነበር፡፡ ጳውሎስ ወደ ሮም ሄዶ በንጉሡ ፊት መከራከር መረጠ፡፡ ወደ ፍርድ ቤት መሄድ ጥሩ ባይሆንም ጉዳያችን የግድ ማለቅ ያለበት በፍርድ ቤት ከሆነ ግን በፍርድ ቤት መከራከር ኃጢአት አይደለም፡፡ ጳውሎስ ታስሮ ከአይሁድ ጋር እየተከራከረ ያለው ጥፋት ተገኝቶበት ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስን በመስበኩ ነበር፡፡ አይሁድ እየከሰሱት ያሉት ያለ ጥፋቱ ነው፡፡ ያለ ጥፋታችንን ስንከሰስ ቢሆን  መከራ ሲገጥመን የገጠመንን ክስና መከራ ከጳውሎስ ጋር ስናስተያየው እዚህ ግባ የማይባል መሆኑን ተረድተን ልንጽናናና ልንበረታ ያስፈልጋል፡፡ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን በሰኔ 15 ቅዳሴ ሲቀደስ ከበላይ የጠቀስኩት ክፍል ይነበባል ( መጽሐፈ ግጻዌ) ፡፡ ይቀጥላል፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡፡ አሜን! ✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie

  • ✍ ዘማሪ ዲያቆን ንጉሤ ጥላሁን ( ወንጌል ሰባኪ ) በተጨማሪም የንድፍና የኮምፒዩተር ባለሙያ ▶️ ስብከቶቼንና መዝሙሮቼን በዩቱቤ ቻናል  ማግኘት ትችላላችሁ https://youtube.com/channel/UC5CXetEDzzsnMHbPAT-b_0w ▶️ ቴሌግራም ቻናል https://t.me/EMaweq ▶️ ፌስቡክ fb.me/yeglie