ሰከላ ዜና(Sekela News)
Статистика- Последний пост
- 29 нояб. 2024 г.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ለአንድ ከተማ ሁለት ከንቲባ ተሾመ ትግራይ ክልል ዓዲግራት ከተማ ሁለት ከንቲባዎች ተሾሙባት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከትላንት በስቲያ አቶ ዓለም አረጋዊ ለዓዲግራት ከተማ “ከንቲባ” አድርጎ የሾመ ሲሆን፣ በዶ.ር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ደግሞ ዛሬ ባካሄደው የምክር ቤት ጉባኤ አቶ ረዳኢ ገብረእግዚኣብሄር ለዓዲግራት ከተማ “ከንቲባ” አድርጎ መሾሙን የአሜሪካ ድምፅ ዘግቧል:: ሁለቱንም ተሿሚዎች VOA አነጋግሯል። በጊዜያዊ አስተዳደሩ የተሾሙት አቶ ዓለም <<ጊዜያዊ አስታዳደሩ በተቋቋመበት ህግ እና አሰራር መሰረት ወደ ስራ ገብቻለሁ አሁን ላይ በፅ/ቤት ስራ ርክክብ እያደረኩ ነው>> ብለዋል። የእነ ዶ/ር ደብረፂዮን ተሿሚ አቶ ረዳኢ ሹመቱን አረጋግጠው <<TPLF ተወዳድሮ በተመረጠበት ትግራይ እስካሁን ያለው የTPLF ም/ቤት አባላት ናቸው ፤ እኔም እንደ TPLF አንድ አካል ተወካይ ሆኜ ነው የቀረብኩት>> ሲሉ ሹመቱ በም/ቤት እንደፀደቀላቸው ለጣቢያው ተናግረዋል። ለበለጠ እንዲሁም ለአዳዲስ እና ትክክለኛ መረጃ telegram ላይ ከስር ባለዉ ማስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ 👇👇 https://t.me/sekelazena
አልጸጸትም ጃዋር መሐመድ የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሐመድ «አልጸጸትም»የሚል መጽሃፍ ማሳተሙ ታውቋል። መጽሃፉ ሕትመቱ ከሳምንት በኋላ በገሃድ ገበያ ላይ ይውላል።በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች፣ በተለይም የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ነጻ ይዞታ ናቸው በሚባሉ አካባቢዎች ጭምር ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ "የሰላም ያለህ" ማለቱን " የሰላም ድርድር ጥሪ የገፋ መንግስት ስለምን ህዝብ ያሰልፋል" በሚል የተቃወመው ጃዋር ያሳተመው መጽሃፍ በኦሮምኛና በአማርኛ መሆኑ ታውቋል። ዜናውን ያጋሩን ወገኖች ጃዋር ለመጽሃፉ «አልጸጸትም» የሚል ርዕስ የመረጥበትን ምክንያት ለጊዜው ግልጽ አላደረጉም። ይሁን እንጂ በከፍተኛ ደረጃ ተከታዮችና አባላት አስከትሎ፣ ከመንግስት ባልተናነሰ በይፋ አገር ቤት ተቀምጦ ሲመራው የነበረውን ትግል አሰበበት ሳያደርስ መቅረቱ ለመጽሃፉ ርዕስ መነሻ ሊሆን እንደሚችል ግምት አለ። ለበለጠ እንዲሁም ለአዳዲስ እና ትክክለኛ መረጃ telegram ላይ ከስር ባለዉ ማስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ 👇👇 https://t.me/sekelazena
በሰሜን ሸዋ ዞን አለልቱ መንገድ ላይ ከባድ የትራፊክ አደጋ መከሰቱ ተሰማ‼️ በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አለልቱ መንገድ ላይ ከባድ የትራፊክ አደጋ መድረሱን አሐዱ የደረሰው መረጃ ያመለክታል፡፡ አደጋው አለልቱ አቅራቢያ ጮሌ ጸበል ጋር የተከሰተ ሲሆን፤ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚጓዝ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሲኖ ትራክ ተሸከርካሪ ጋር በመጋጨቱ መከሰቱን በስፍራው ያሉ ነዋሪዎች ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡ በአደጋው በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውን እንዲሁም ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች ሕይወት ማለፉን የተናገሩት ነዋሪዎቹ፤ የሲኖ ትራክ ተሸከርካሪው ረዳት መኪና ውስጥ ተቀርቅሮ በመቅረቱ እርሱን ለማውጣት ከአንድ ሰዓት በላይ ጥረት ቢደረግም ሕይወቱን ማትረፍ አለመቻሉን ተናግረዋል፡፡ በዚህም ምክንያት መንገዱ ለረጅም ሰዓት መዘጋቱ የተነገረ ሲሆን፤ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ወደሆስፒታል የማድረስ ሥራ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል፡፡ ለበለጠ እንዲሁም ለአዳዲስ እና ትክክለኛ መረጃ telegram ላይ ከስር ባለዉ ማስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ 👇👇 https://t.me/sekelazena
አየር ላይ ህይወቱ አለፈ!! ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ በሚጓዝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሳፋሪ አየር ላይ ህይወቱ አለፈ ባሳለፍነው አርብ November 15 ቀን 2024 ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ፣ በበረራ ቁጥር ET 500 ፣ በAirbus A350 አውሮፕላን ተሳፋሮ የሚመጣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አንድ መንገደኛ አየር ላይ እንዳለ ባጋጠመው ድንገተኛ ህመም ህይወቱ አለፈ። እድሜው ከ45 እስከ 50 ዓመት የሚገመተው ይህ ተሳፋሪ ከእህቱ አጠገብ አብሮ ቁጭ ብሎ በመብረር ላይ እያለ ፣ አውሮፕላኑ ነዳጅ ሞልቶ እና የበረራ ሰራተኞችን ቀፍሮ ከሮም፣ ጣልያን ተነስቶ ወደ አሜሪካ ጉዞ ከጀመረ ከአንድ ሰዓት በኋላ እህቱ ለበረራ አስተናጋጆች ወንድሟ የመተንፈስ ችግር እንዳጋጠመው ትነግራቸዋለች፣ የበረራ አስተናጋጆቹም የህክምና ባለሞያዎች ካላችሁ ለእርዳታ እንፈልጋችኋለን ብለዉ ጥሪ ካቀረቡ በኋላ፣ በበረራው ዉስጥ የነበሩ ወደ 5 የሚጠጉ የህክምና ባለሞያዎች ወደ ግለሰቡ መጥተው ህይወቱን ለማትረፍ ተረባርበው የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ ቢሰጡትም ግለሰቡ አየር ላይ ህይወቱ ሊያልፍ መቻሉን በበረራ ላይ የነበሩ ተሳፋሪዎች ለመዝናኛ ሚዲያ አስታውቀዋል ። ለበለጠ እንዲሁም ለአዳዲስ እና ትክክለኛ መረጃ telegram ላይ ከስር ባለዉ ማስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ 👇👇 https://t.me/sekelazena
ከሀገር እንዳይወጡ በፍርድ ቤት እግድ የተጣለባቸዉ ባለስልጣን ከሀገር መዉጣታቸዉ ተሰማ የኢትዬጲያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አመራር የሆኑት ዶ/ር አሸብር ወልደጊወርጊስ በፍርድ ቤት ከሀገር እንዳይወጡ እግድ ቢጣልባቸዉም ወደ ደቡብ አፍሪካ መሄዳቸዉ ተሰምቶል ፡፡ ከኦሎምፒክ ምርጫ ጋር እና ከፓሪስ ኦሎምፒክ ጉዞ ጋር በተያያዘ በእነ አትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴ እና ገዘሃኝ አበራ ክስ ቀርቦባቸዉ ጉዳያቸዉ በፍርድ ቤት እየታየ እንደነበር ይታወሳል ፡፡ ዶ/ር አሸብር ከሃገር የወጡት የህ/ተ/ም ቤት አባል ስለሆኑ ያለ መከሰስ መብታቸዉን በመጠቀም በምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ፍቃድ ሰጭነት እንደሆነ አንኳር መረጃ ያገኘችዉ መረጃ ያመለክታል ፡፡ ለበለጠ እንዲሁም ለአዳዲስ እና ትክክለኛ መረጃ telegram ላይ ከስር ባለዉ ማስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ 👇👇 https://t.me/sekelazena
አንጋፋው ጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። አንጋፋው ጋዜጠኛ ዜናነህ ፥ በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቭዥን እንዲሁም በዴቼ ቬለ ሬድዮ ለረዥም ዓመታት አገልግሏል። ጋዜጠኛ ዜናነህ ለረዥም ጊዜያት ባደረበት ህመም ህክምናውን ሲከታተል ከነበረበት እስራኤል ቴል አቪቭ ዛሬ ጠዋት ኣፏል። በስልሳ ስምንት ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው አንጋፋው ጋዜጠኛ ዜናነህ አዘዞ ጎንደር ነው የተወለደው። ከ1970ዎቹ እስከ ሰማኒያዎቹ አጋማሽ ድረስ በኢትዮጵያ ራዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት በተለይ በዜና አንባቢነት አገልግሏል። በ1980ዎቹ አጋማሽ ወደ እስራኤል ያቀናው ዜናነህ በህመም ተዳክሞ ከሥራው እስኪርቅ ድረስ በኢየሩሳሌም የዶቼ ቬለ ራዲዮ ዘጋቢ በመሆን ሲያገለግል ቆይቷል። " ይህ ዶቼ ቨለ ነው !! " ከሚለው የዲቼቬለ ሬድዮ ጣቢያ መለያ አንስቶ የተለያዩ ዝግጅቶች መክፈቻም የአንጋፋው ጋዜጠኛ ድምፅ ነው። የዶቼ ቬለ አድማጮች ዜናነህን ከመካከለኛው ምስራቅ በእስራኤል አረብ ግጭት እና ጦርነቶች ብሎም በቀጣናው በሚነሱ ፖለቲካዊ ዘገባዎች ያውቁታል። የዜናነህ መኮንን የቀብር ሰነ ስረዓት ቴል አቪቭ ውስጥ በሚገኝ ፓርክ ያኮም መካነ መቃብር እንደሚፈጸም ልጁ ቢታንያ ዜናነህ ገልጻለች። ዜናነህ ባለትዳር እና የሶስት ሴቶች ልጆች አባት ነበር። ለበለጠ እንዲሁም ለአዳዲስ እና ትክክለኛ መረጃ telegram ላይ ከስር ባለዉ ማስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ 👇👇 https://t.me/sekelazena
без подписи
በሬክተር ስኬል 4.6 የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ አካባቢ መከሰቱ ታውቋል። ንዝረቱም ከአዲስ አበባ እስከ ደብረብርሃን ተሰምቷል። ህዝብ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎችን እያቀረቡ ግንዛቤ መስጠት አለባቸው። ለበለጠ እንዲሁም ለአዳዲስ እና ትክክለኛ መረጃ telegram ላይ ከስር ባለዉ ማስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ 👇👇 https://t.me/sekelazena
መንግሥት፣ ሪል እስቴቶች ከግንባታ በፊት የቤት ሽያጭ እንዳያካሂዱ የሚከለክል ረቂቅ አዋጅ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቅረቡን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ረቂቅ አዋጁ፤ የቤት ግንባታ ለማካሄድ የመሬት የይዞታ ማረጋገጫና የግንባታ ፍቃድ ያላገኙ የሪል ስቴት አልሚዎች የደንበኞች ምዝገባ እንዳያካሂዱና ቅድመ-ክፍያ እንዳይሰበስቡ እንደሚከለክል እንዲሁም ከደንበኞች የሰበስቡትን ገንዘብ በዝግ የባንክ ሒሳብ እንዲያስቀምጡ እንደሚያስገድድም ዘገባው አመልክቷል። የሪል እስቴት አልሚዎች “የብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ” እንዲያወጡም ረቂቁ ያስገድዳል ተብሏል። ረቂቅ አዋጁን ማውጣት ያስፈለገው፣ የሪል እስቴት ልማት ከአገሪቱ የቤት ፍላጎት "በእጅጉ የራቀ" እና በሕገወጥ መንገድ በሚንቀሳቀሱ ደላሎች ተጽዕኖ ሥር የወደቀ በመኾኑ እንደኾነ ተገልጧል። ለበለጠ እንዲሁም ለአዳዲስ እና ትክክለኛ መረጃ telegram ላይ ከስር ባለዉ ማስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ 👇👇 https://t.me/sekelazena
без подписи
без подписи
без подписи
በመሬት ናዳ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ። በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጉባ ቆርቻ እና ሻናን ዱንጎ ወረዳዎች ትላንት ማክሰኞ በጣለው ከባድ ዝናብ የተነሣ በተከሠተው የመሬት መናድ፣ 10 ሰዎች መሞታቸውን ወረዳዎቹ አሳውቀዋል። የጉባ ቆርቻ ወረዳ አስተዳዳር ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ/ም በጃርጃታ ቀበሌ ውስጥ በተከሰተው የመሬት መናድ ምክንያት 4 ሰዎች ሲሞቱ በሌላ ቀበሌ በደረሰው አደጋ ደግሞ አንድ ሰው ሞቷል። በሻናን ዱንጎ ወረዳ በሌሊስቱ ቀበሌ በዚሁ ቀን በተከሰተው ሌላ የመሬት መናድ አደጋ የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው አስተዳዳር ለሬድዮ ጣቢያው ገልጿል። ነፍስ ይማር ! ለበለጠ እንዲሁም ለአዳዲስ እና ትክክለኛ መረጃ telegram ላይ ከስር ባለዉ ማስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ 👇👇 https://t.me/sekelazena
በአዲስ አበባ ዛሬ ረፋድ 4 :00 ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል። ከጎሮ ወደ ኮዬ እየተጓዘ የነበረ ኮድ 3-69867 ቱርቦ የሆነ የጭነት ተሽከርካሪ ከከተማ አውቶቢስ ጋር ተጋጭቶ ነው አደጋ የደረሰው። በዚህም የ4 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 7 ሰዎች ላይ ቀላል እና ከባድ ጉዳት ደርሷል። በአደጋው የሞቱት ሁሉም ሴቶች ናቸው። ዕድሜያቸውም ከ20 እስከ 52 የሚገመቱ ናቸው። 3ቱ ሴቶች የአውቶቢስ ትኬት በመቁረጥ ላይ እያሉ ነው አደጋው የደረሰባቸው። በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በቤጂንግ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው። የአዲስ አበባ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ " አደጋው እጅግ አሰቃቂ ነበር " ብለዋል። የአደጋው ምክንያት እየተጣራ ነው ሲሉ ገልጸዋል። ለበለጠ እንዲሁም ለአዳዲስ እና ትክክለኛ መረጃ telegram ላይ ከስር ባለዉ ማስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ 👇👇 https://t.me/sekelazena
ቤንዚን እና ነጭ ናፍጣ ምን ያህል ጨመረ ? በነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ተደርጎ የነበረው ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር 2016 ዓ/ም ነበር። በወቅቱ ቤንዚን በሊትር 82.60 ብር ፤ ነጭ ናፍጣ በሊትር 83.74 ብር በሊትር ፤ ኬሮሲን በሊትር 83.74 ብር ፤ ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 65.48 ብር እንዲሁም ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 64.22 ብር ተደርጎ ነበር። ከዛ በኃላ ባሉት ወራት የነዳጅ ዋጋ ባለበት ቀጥሏል። ዛሬ ግን ጭማሪ ተደርጓል። በቤንዚን ላይ ከ8 ብር በላይ ጭማሪ ተደርጎ 1 ሊትር ቤንዚን 91 ብር ከ14 ሳንቲም ሆኗል። በነጭ ናፍጣ ላይ ከ6 ብር በላይ ጭማሪ ተደርጎበት አሁን አንዱ ሊትር 90 ብር ከ28 ሳንቲም ገብቷል። (ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ የጀመረው የነዳጅ ዋጋ ከላይ ተያይዟል) ለበለጠ እንዲሁም ለአዳዲስ እና ትክክለኛ መረጃ telegram ላይ ከስር ባለዉ ማስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ 👇👇 https://t.me/sekelazena
እንኳን ለደማቁ የመስቀል በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን መልካም በዓል! ለበለጠ እንዲሁም ለአዳዲስ እና ትክክለኛ መረጃ telegram ላይ ከስር ባለዉ ማስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ 👇👇 https://t.me/sekelazena
በትራፊክ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት አለፈ ከወላይታ ሶዶ ከተማ ወደ ዳውሮ ዞን ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የ28 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ በወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ወልዴ ቢሊሶ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ከሟቾች በተጨማሪ በ29 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡ አደጋው ዛሬ ቀን 7 ሠዓት ላይ በወላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ፈታታ ቀበሌ መከሰቱንም አረጋግጠዋል፡፡ የተከሰተው አደጋ ከባድ መሆኑን ጠቅሰው የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል አመላክተዋል፡፡ ለበለጠ እንዲሁም ለአዳዲስ እና ትክክለኛ መረጃ telegram ላይ ከስር ባለዉ ማስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ 👇👇 https://t.me/sekelazena
ዶላንድ ትራምፕ በቅርብ በሚካሄደው የአሜሪካ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ካሸነፉና ፕሬዜዳንት ከሆኑ ፥ " በአስቸኳይ የስደተኞችን ወረራ አስቆማለሁ፣ ማንኛውም አይነት የህገወጥ ስደተኞችን በረራ እንዲቆም እንዲሁም በማንኛውም መንገድ ወደ አሜሪካ ምድር እንዳይገቡ አደርጋለሁ " ብለዋል። ከዚህ ባለፈ በስልጣን ዘመናቸው በአሜሪካ ታሪክ ትልቅ የተባለ ዲፖርቴሽን (ከሀገር የማስወጣት) ስራ እንደሚሰሩ ከወዲሁ ተናግረዋል። " ከአሜሪካ ምድር ጓዛቸውን አስይዘን ወደ መጡበት እንልካቸዋለን " ያሏቸው ዶክመንት አልባ ህገወጥ ስደተኞችን ነው። በስድተኞች ጉዳይ ላይ ያላቸው አቋም ከዚህ ቀደምም የሚታወቀው ትራምፕ አሁን ስመጣ " አጠነክረዋለሁ " እያሉ ለደጋፊዎቻቸው ቃል በመግባት ላይ ናቸው። " ከተሞቻችን አድንላችኋለሁ " እያሉ ያሉት ትራምፕ ቢያንስ ቢያንስ ከ15 እስከ 20 ሚሊዮን ህገወጥ ስደተኞችን ከአሜሪካ ለማስወጣት እቅድ አላቸው ተብሏል። ምናልባትም ተመርጠው ፕሬዜዳንት ከሆኑ በኃላ ይሄን ሁሉ የሰው ቁጥር እንዴት ከአሜሪካ ዲፖርት እንደሚያደርጉ ለጊዜው በዝርዝር የሚታወቅ ነገር የለም። ለበለጠ እንዲሁም ለአዳዲስ እና ትክክለኛ መረጃ telegram ላይ ከስር ባለዉ ማስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ 👇👇 https://t.me/sekelazena
"ጄኔራል ፃድቃን ከማን ጋር ነው የምንደራደረው ? ብሎናል " ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)‼️ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፤ ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ስልጣን ለመጠቅለል በማቀድና የቆየ ቂም ለመወጣት በሚል ከሰሱ። ቅዳሜ በመቐለ በተካሄደና የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ህወሓትን ለማጥፋት፣ ስልጣን ለመጠቅለል የሚንቀሳቀሱ ተብለው የተገለፁ አመራሮች በስም እየተጠቀሱ ወቀሳ ሲሰነዘርባቸው ተሰምቷል። በዚሁ መድረክ ደብረፅዮን (ዶ/ር) ፥ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝደንት የሆኑት ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤን፥ ስልጣን ለመጠቅለል በማቀድ፣ የቆየ ቂም በመወጣት እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች በማንሳት እንዲሁም ከዚህ በፊት በይፋ ያልተሰሙ መረጃዎች በመግለፅ ሲተቹ ተደምጠዋል። በንግግራቸው እርሳቸው የሚመሩትን ህወሓት ሰላም የማይፈልግ አድርጎ የማቅረብ የተሳሳተ ፍረጃ ከትግራይ ባለስልጣናት በኩል እየቀረበበት መሆኑ ገልጸው " ይህ ውሸት ነው " በማለት አጣጥለዋል። ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፤ " ለምሳሌ በደቡባዊ ዞን በተደረገ መድረክ ጀነራል ጻድቃን እኛ ሰላም እንፈልጋለን፣ እነሱ የሚሹት ጦርነት ነው ሲል ሰምታችሁታል። በጦርነቱ ወቅት ደሴ ተሻግረን ሰሜን ሸዋ ስንጠጋ፥ ድርድር ያስፈልጋል ወይ ሲባል እኔ አዎን ያስፈልጋል ነው ያልኩት። በሰላም ሊፈታ ስለሚገባው። እሱ ግን ከማን ጋር ነው የምንደራደረው፣ ውጊያው አልቋል ሲል የነበረ ነው። አሁን ግን እኔ ሰላም ነኝ እነሱ ጦርነት ናቸው የሚፈልጉ ማለት ጀመረ " ብለዋል። ለበለጠ እንዲሁም ለአዳዲስ እና ትክክለኛ መረጃ telegram ላይ ከስር ባለዉ ማስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ 👇👇 https://t.me/sekelazena
በመስቀል ደመራ በዓል የተከለከሉ ነገሮችን ለብሶም ሆነ ይዞ መምጣት ክልክል ነው የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ሥራ መገባቱን ጥምር የፀጥታ ኃይሉ አስታውቋል፡፡ በዓሉ ወደሚከበርበት ስፍራ ከበዓሉ አከባበር ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ነገሮች ይዞ መምጣት አመፅን የሚቀሰቅሱ እና ተከባብሮ የመኖር እሴትን የሚሸረሽሩ ፅሁፎች ያሉባቸውን አልባሳት ለብሶ መምጣት በአጠቃላይ የተከለከሉ ነገሮችን ይዞ መምጣትና እንዲሁም ደመራ የማብራት ስነ ስርዓት በሚከናወንባቸው የተለያዩ ቦታዎች ላይ ርችት ማፈንዳት ክልክል መሆኑን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ለፀጥታ ሃይሎች ሥራ ተባባሪ እንዲሆን ጥምር የፀጥታ ኃይሉ አሳስቧል፡፡ ለበለጠ እንዲሁም ለአዳዲስ እና ትክክለኛ መረጃ telegram ላይ ከስር ባለዉ ማስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ 👇👇 https://t.me/sekelazena