tgindex
EthioTube
@ethiotubeВидеоанглийский

ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ። Follow us on other our social media networks: Facebook.com/EthioTube Twitter.com/EthioTube Youtube.com/EthioTube Instagram.com/EthioTube

Последний пост
12 авг.
Последнее чтение
14:42
Постов за неделю
3
Всего постов
197
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Видео
В каталоге с
12 авг.
Подписчики
8 181
−15 за 4 дн.
Сутки
−11
−0,13%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 896
40 постов
Вовлечённость
23,2%
к подписчикам
Постов в день
0,4
всего 197
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
948
1/48двое суток
1 086
1/72трое суток
1 171

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • በግልገል በለስ ከተማ ንጹኃን ላይ በደረሰ ጥቃት ቢያንስ 8 ሰዎች ሲገደሉ ከ 20 በላይ መቁሰላቸው ተገለጸ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ ንጹኃን ላይ በደረሰ ጥቃት ቢያንስ 8 ሰዎች ሲገደሉ ከ 20 በላይ መቁሰላቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ለኢትዮቲዩብ ተናግረዋል። የዞኑ አስተዳደር ትላንት ነሐሴ 5/2018 ባወጣው መግለጫ ‘የጉምዝ ኃይል እና የፋኖ ታጣቂዎች” ጥቃት በመክፈት ወደ ከተማው ለመግባት ሞክረዋል ሲል መወንጀሉ ይታወሳል። መግለጫው በጥቃቱ በንጹኃን ሰዎች ላይ ጉዳት ስለመድረሱ ሳይገልጽ ቀርቷል። በዚህ ጉዳይ ላይ ያነጋገርናቸው ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የከተማው ነዋሪዎች በበኩላቸው በትላንቱ ጥቃት ቢያንስ 8 ንጹኃን ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል። ሟቾችቹ ግልገል በለስ መናኸሪያ ውስጥ የነበሩ ሲሆኑ ሁሉም ወንዶች መሆናቸውን ገልጸዋል። ንጹኃን ዜጎቹ የተገደሉት በተከፈተባቸው “የተኩስ እሩምታ” ሳይሆን ከርቀት በተተኮሰ “የሞርታር ፍንጥርጣሪ” መሆኑን አንድ የዓይን እማኝ ለኢትዮ ቲዩብ አስረድተዋል። “ከግልገል በለስ ከተማ ወደ ማንዱራ፣ ቻይና ካምፕ ተብሎ የሚጠራ የመከላከያ ወታደር ካምፕ አለ። ጥቃቱን የጀመሩት ከእሱ ነው። ቁጥራቸው በሰፊው የታየው የጉምዝ ብሔር ተወላጆች ናቸው” ሲሉ ተናግረዋል። የዞኑ ኮምኒኬሽን “ጽንፈኛ” ሲል የጠራቸው የፋኖ ታጣቂዎች በጥቃቱ ተሳትፈዋል መባሉን እኒህ የዓይን እማኝ እንደማይቀበሉት አክለዋል። በመተከል ዞን ከ 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ማንነት ላይ ያተኮረ ጥቃት በተደጋጋሚ እንደሚፈጸም የሚገልጹት የግልገለስ በለስ ከተማ ነዋሪው የትላንቱ ጥቃት በተመሳሳይ መልኩ "በጉምዝ ኃይሎች" የተፈጽመና የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ያተኮረ ነው በማለት የዞኑ አስተዳደር ያወጣውን መግለጫ አጣጥለዋል።

  • ‎ራሳቸውን የጉሙዝ ኃይል ብለው የሚጠሩና የፋኖ ታጣቂዎች በለስ ከተማ ለመግባት ሞክረው ነበር ተባለ 👉በዛሬው ጥቃት ከአስር በላይ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ ዛሬ ነሐሴ 5/2018 ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ገደማ “ራሳቸውን የጉሙዝ ኃይል ብለው የሚጠሩና በጫካ የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ከጽንፈኛው ፋኖ ጋር በመሆን ወደ ከተማ ለመግባት እና በዜጎች ላይ ጉዳት ለማድረስ ሙከራ ማድረጋቸውን” የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ። ‌‎አስተዳደሩ “ጽንፈኛ” ሲል በጠራው የፋኖ ቡድን ላይ በተወሰደ የተቀናጀ “ከባድ እርምጃ ሙትና ቁስለኛ ሆኖ ተመልሷል” ብሏል። በአሁኑ ሰዓት በከተማዋ ያለውን ፍጹም ሰላምና መረጋጋት ለማስቀጠል የሁሉም የፀጥታ ኃይል ዝግጅቱን ማጠናከሩንም አክሏል። የጀርመን ድምጽ ራዲዮ በዚህ ጉዳይ ላይ በሠራው ዘገባ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ከአስር በላይ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የአይን ምስክሮች ነግረውኛል ብሏል።‎ ዘገባው ሰላማዊ ዜጎቹን ስለገደለ አካል በይፋ አልገለፀም። #Ethiopia #BenshangulGumuz #GumuzForce #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa

  • 11 авг.1 1551

    "4 ኪሎ ሰው የለም ቢባል ፋኖ ይሁን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አንዳቸውም አይመጡም አቅም የላቸውም" በኬኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ጄነራል ባጫ ደበሌ አምባሳደር ባጫ ደበሌ ከሰሞኑ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅታዊ ሀገራዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮችን በተመለከተ አነጋጋሪ ሀሳቦችን አንስተዋል። አምባሳደሩ በዚህ ቃለመጥይቅ ምን አሉ? 👉ህወሓት የኢትዮጵያን መንግሥት ለመጣል ደብረ ሲና ድረስ ደርሶ ነበር። በኢትዮጵያ መንግሥት በሠራዊት እና በሕዝቡ ያ እንዳይሆን ከሽፎ ወደ ትግራይ እንዲመለስ ተብሏል። ህወሓት ከደብረ ሲና ሲመለስ እኮ ሙሉ በሙሉ ህወሓት የሚባል ነገር ሁለተኛ እንዳይነሳ አድርጎ መጨረስ ይቻል ነበር። መቀለ መግባት ይቻል ነበር። እስከ መረብ ድረስ ድንበራችንን መዝጋት እንችል ነበር 👉ህወሓት አዲስ ውጊያ ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ ነው። ግን ልዩነት አለው ባለፈው ጊዜ ህወሓት ራሱ ነው ለመዋጋት ይፈልግ የነበረው አሁን ግን ቀጣናዊ ሆኗል ከሶማሌ እስከ ካርቱም ድረስ ነው ያለው። 👉 ህወሓት ገዳዮቻችን ናቸው፣ዘራፊዎቻችን ናቸው፣ሴቶቻችንን ደፋሪዎች ናቸው አሰቃቂ በሆነ መንገድ ብለው ከከሰሷቸው ሻዕቢያ ጋር ጽምዶ ፈጥረው ወይም ቅንጅት ወይም አንጃ ፈጥረው የኢትዮጵያን መንግሥት እንጥላለን ብለው እንደገና ለውጊያ ተደራጁ 👉ቲ.ፒ.ኤል.ኤፍ (TPLF) ያኔ [በጦርነቱ ወቅት] እንደተባለው 270 ሺህ [ተዋጊ] ሊኖረው ይችላል። አሁን እኮ 30 ሺህ የለውም። አሁን እኮ ሕዝብ አይደግፈውም ነገር ግን የገንዘብ ምንጫቸው የግብፅ መንግሥት ነው። 👉ፕሬዝደንት ኢሳያስ ግብጽ እኛን ስትረዳ የነበረው ኤርትራ ነጻነቷን አግኝታ መንግሥት እንድትመሰርት ሳይሆን ኢትዮጵያ መረጋጋት እንድታጣ ለማድረግ ነበረ [ብሏል] በአፉ ነው የተናገረው። #Ethiopia

  • 5 авг.1 8911

    በቁጥጥር ሥር የዋሉት የኢሕአፓ ሁለት አባላት እና የፓርቲው ጠበቃ ከ “ጽምዶ” ጋር በተያያዘ ውንጀላ ቀረበባቸው ከትላንት በስቲያ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት ሁለት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) አባላት እና የፓርቲው ጠበቃ፤ “የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል” የሚል ውንጀላ ቀረበባቸው። ፖለቲከኞቹ እና ጠበቃው ከህዝባዊ ወያነ ሓርነት (ህወሓት)፣ “ከሌሎች ጸረ- ሰላም ኃይሎች” እና “ጽምዶ” ተብሎ ከሚጠራው ኃይል ጋር “በመቀናጀት” በአዲስ አበባ ከተማ አባላትን “በመመልመል” እና “በማደራጀት” ተጠርጥረዋል። የፌደራልፖሊስ እነዚህን ውንጀላዎች ያቀረበው፤ በአቶ አበበ አካሉ፣ አቶ ይስሀቅ ወልዳይ እና አቶ አበራ ንጉስ ላይ ነው። የኢሕአፓ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ይስሀቅ እና የሕግ ባለሙያው አቶ አበራ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት፤ ከትላንት በስቲያ ሰኞ ሐምሌ 27 እንደሆነ ፓርቲያቸው በወቅቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ሶስቱ ተጠርጣሪዎች ዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 29/ 2018 በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት መቅረባቸውን የፓርቲው ዋና ጸሐፊ ምስጢረ ሥላሴ ታምራት እና ጠበቃቸው አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጠዋል። በዛሬው የችሎት ውሎ የፌደራል ፖሊስ የ14 ቀናት የምርመራ የጊዜ ቀጠሮ መጠየቁን አቶ ሰለሞን ተናግረዋል። ጠርጣሪዎቹ “ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲን እንደ ሽፋን በመጠቀም ከፓርቲው ህግ እና አላማ ውጪ ስልጣን በኃይል ለመያዝ በማሰብ ተንቀሳቅሰዋል” በሚል ተወንጅለዋል። ግለሰቦቹ ይህንኑ ሃሳባቸውን ለማሳካት ሃሳብ ከ“ኢትዮጵያ የውስጥ እና የውጭ ታሪካዊ ጠላቶች” መቀናጀታቸውም በማመልከቻው ላይ ተጠቅሷል። #Ethiopia

  • 4 авг.1 7641

    በፃድቃኔ ማርያም ገዳም ውስጥ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ 14 ሰዎች ሞቱ በሰሜን ሸዋ ዞን፣ በሞጃ እና ወደራ ወረዳ በምትገኘው የጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም ውስጥ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ 14 ሰዎች ሞቱ። ሌሊቱን የክረምት ዝናብ ሲወርድ እንዳደረ እና ይህም ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 27/2018 ዓ. ም. ጠዋት 12 ሰዓት አካባቢ "የዋሻ ናዳ" ማስከተሉን የአካባቢው ባለሥልጣን ገልጸዋል። መሬት መንሸራተቱ በተከሰተበት ጊዜ በቤተ ክርስቲያኑ ዋሻው በር ላይ ፀሎት ሲደረጉ የነበሩ ምዕመናን ላይ ጉዳቱ መድረሱንም የሞጃ እና ወደራ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዳኛቸው አዝብጤ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አምስት ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ደብረአብ ሪፈራል ሆስፒታል እንደተወሰዱ እና ሁለት ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው በሰላ ድንጋይ ጤና ጣቢያ እየታከሙ እንደሚገኙ ኃላፊው አስረድተዋል። ተጨማሪ አደጋን ለመከላከል "አሁን አካባቢውን ከልለናል። ስጋት ሊኖር ስለሚችል ግን ምዕመናል በአካባቢው የሉም" ብለዋል። በገዳሙ ፀበል ስላለ እና የፍልሰታ ፆም እየገባም ስለሆነ ምዕመናን በሥፍራው እንደሚገኙ አቶ ዳኛቸው ጠቅሰዋል። #Ethiopia #TsadqaneMariam #ፃድቃኔማርያም #Landslide #መሬትመንሸራተት #EthiopiaNews #የኢትዮጵያዜና #ኢትዮጵያ

  • 29 июл.2 3583

    ወደ ስዊድን ያቀኑ 20 የእግርኳስ ቡድን አባላት መጥፋታቸው ተሰማ ወደ ስዊድን ያቀኑ ዕድሜያቸው ከ 14 እስከ 17 የሚገመት 20 ታዳጊ የእግርኳስ ተጫዋቾች ከ መሪያቸው ጋር መጥፋታቸውን ስዊድን ሄራልድ ዘግቧል። "ጎቲያካፕ" ለተሰኘ የእግር ኳስ ውድድር ከኢትዮጵያ የሔዱት ታዳጊዎች ካረፉበት ትምሕርት ቤት ሳያሳውቁ በመውጣት መሰወራቸውን የስዊድን ፖሊስ አስታውቋል። እግር ኳስ ተጫዋቾቹ ወደ ኢትዮጵያ እንዳልተመለሱ ያረጋገጠው ፖሊስ፤ በራሳቸው ፍላጎት ጠፍተው ሊሆን እንደሚችል አመላክቷል። #Ethiopia #EthiopianFootball #EFF #Sweden #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa

  • 28 июл.2 0331

    በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ውስጥ ባለፉት አራት ዓመታት 458 ሰዎች መገደላቸውን ኢሰመጉ አስታወቀ በጥቃቱ የሰባት ወር ሕጻንን ጨምሮ የ67 ሰዎች ፎቶግራፍም ይፋ ተደርጓል የኢትዮጵያሰብአዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ውስጥ ባለፉት አራት ዓመታት በተፈጸሙ ጥቃቶች 458 ሰዎች መገደላቸውን በጉዳዩ ላይ ባወጣው ሪፖርት አስታወቀ። 7 ገጽያለው ሪፖርት፣ ከ2014 እስከ እስካ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም. በዞኑ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን የዳሰሰ ነው። በአካባቢው የሚገኙ የታጠቁ ቡድኖች የአካባቢውማኅበረሰብ ላይ ሃይማኖትን መሠረት ባደረገ መልኩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ላይ" ጉዳት ማድረሳቸውን ሪፖርቱ ላይ ሰፍሯል። "ከፍተኛ የሆነ ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመት፣ አስገድዶ መሰወር፣ እገታ" ተፈጽሟል። "አብያተ ክርስቲያናት ላይዝርፊያ" መድረሱን እንዲሁም ታጣቂዎቹ "በርካታ ቤቶችን ማቃጠላቸውን" አክሏል። ኢሰመጉ ታግተው ያሉበት ሁኔታ የማይታወቅ"በሚል የተገለጹ 38 ሰዎች ስም ዝርዝር ሪፖርቱ ውስጥ አካትቷል። #Ethiopia #Oromia #HumanRights #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa

  • 26 июл.2 1193

    በትግራይ ክልል በውስጣዊ አቅም የሚሸፈን የ 65 ቢሊዮን ብር በጀት ጸደቀ የትግራይ ክልል ምክር ቤት በክልሉ ውስጣዊ አቅም የሚሸፈን ነው ያለውን 65 ቢሊዮን 296 ሚሊዮን 756 ሺህ 634 ብር በጀት አጸደቀ። ለ2019 ዓ.ም. ይውላል ተብሎ የተገለጸው በጀት፤ “በትግራይ ሕዝብና መንግስት መተማመንን በማጠናከር ከክልሉ ውስጣዊ አቅሞች የሚሰበሰብ ገቢ ነው” ተብሏል። በአሁን ወቅት በትግራይ ክልል እና በፌደል መንግሥት መካከል ያለው ውጥረት እንደተባባሰ ይገለጻል። ክልሉን እያስተዳደረ የሚገኘው ህወሓት “የኢትዮጵያ መንግሥት በጀት፣ ነዳጅ እና ሌሎች ምርቶች ወደ ትግራይ እንዳይገባ ከልክሏል” በማለት ክስ እያቀረበ ይገኛል። የፌደራል መንግሥት በበኩሉ “ለክልሉ የተመደበው በጀት ለወታደራዊ አገልግሎቶች እየዋለ ነው” የሚል የሚቀርብበትን ክስ ውድቅ ያደርጋል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ከስድስት ዓመታት በኋላ በቅርቡ በድጋሚ ወደ ኃላፊነት የተመለሰው የትግራይ ክልል ምክር ቤት በ 2019 ዓ.ም. ከፌደራል መንግሥት የምንጠብቀው በጀት የለም በማለት ትግራይ ክልል የራሷን በጀት በራሷ ውስጣዊ አቅም ትሸፍናለች ብሏል። #Ethiopia #Tigray #TPLF #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa

  • በአማራ ክልል በሚገኝ ገዳም ላይ በተጣለ ድሮን መነኮሳት መገደላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አሳወቀች በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የሚገኝ ገዳም ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ሁለት መነኮሳት መገደላቸውን እና 13 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል። በዞኑ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሀገረ ስብከት አርብ ሐምሌ 17 ባወጣው መግለጫ የተፈጸመውን ጥቃት "ዘግናኝ እና አሰቃቂ ድርጊት" በማለት ገልጾታል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ጥቃቱን አስመልክቶ ባወጣችው መግለጫ “የሚያሳፍር ድርጊት” ስትል ኮንነዋለች። “መስቀልን በተሸከሙ፣ጸሎትን መከታ ባደረጉ፣ ለፍጥረት ሁሉ ምህረትን በሚለምኑ ራሳቸውን ለመከላከል ምንም ዓይነት ቁሳዊ ዝግጅት በሌላቸው መናኒያን ላይ እጅን ማንሳት ዘንድ የተከለከለ በእግዚአብሔር በታሪክ ፊትም የሚያሳፍር ድርጊት ነው” ብላለች። ሐምሌ 15/2018 ተፈጸመ በተባለው የድሮን ጥቃት በርካታ መናኒያን መቁሰላቸውን ቤተክርስትያኗ አሳውቃለች። #Ethiopia #Amhara #EOTC #EthiopianOrthodoxTewahedoChurch #DroneStrike #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa

  • ጄኤ ፍኤም 106.7 ለስድስት ወራት ታገደ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ጄኤፍኤም ለስድስት ወራት ከስርጭት ማገዱን አስታውቋል። ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ሬዲዮ ጣቢያውን አስመልክቶ ባደረገዉ የይዘት ክትትልና በአካል ተገኝቶ ባከናወነዉ የኢንስፔክሽን ምልከታ፤ ጣቢያው ሀገራዊ ይዘቶችን የማካተት ግዴታ ከሳምንታዊ የስርጭት ጊዜው 60 በመቶውን ፈቃድ ለወሰደበት አካባቢ የሚመለከት ሲሆን ቀሪውን ጊዜ ለሀገራዊ፣ ክልላዊና ሌሎች ፕሮግራሞች ማዋል እንደሚገባ ቢደነግግም ይህንኑ ተግባራዊ አለማድረጉ ተገልጿል። ሕዝብን የሚያስተምር፣ የሚያሳውቅና የሚያዝናና ፕሮግራሞችን ባለማቅረብ፣ ለፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲሁም በህገ መንግስቱና በሌሎች የሕዝብ ጥቅምና የጋራ ሀገራዊ እሴቶች እንዲጠናከሩ አስተዋፅኦ የሚያደርግ የብሮድካስት አገልግሎት የመስጠት ግዴታን አለማክበሩ ተመላክቷል። በተጨማሪ በፈቃድ የዉል ስምምነት መሰረት ያለመስራት የሚሉ ዋና ዋና ክፍተቶች በመስተዋላቸዉ በተደጋጋሚ ግብረ መልስ፣ የቃልና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያዎች ቢሰጡትም መሻሻሎች ሊታዩ አልቻሉም ሲል ባለሥልጣኑ ወቅሷል። በመሆኑም በፈቃድ ዉሉ የተዘረዘሩ ግዴታዎች ሙሉ ለሙሉ ተሟልተዉ ተግባረዊ እስኪደረጉ ድረስ የሬድዮ ጣቢያዉ ከረቡዕ ሐምሌ 01/2018 በጀት ዓመት ጀምሮ ታሳቢ የሚደረግ ለቀጣይ 6 ወራት ከስርጭት ሙሉ ለሙሉ ታግዶ እንዲቆይ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በኩል ተወስኗል። #Ethiopia #EthiopianPress #EthiopianMedia #AddisAbaba #JFM1067 #JFM #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa

  • 22 июл.1 8381

    “የትግራይ ሕዝብ ከህወሓት ጋር እያደረገ ያለውን ትግል ያለቅድመ-ሁኔታ እደግፋለሁ” የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (#አብን) ሐምሌ 13/2018 ዓ.ም. ባወጣው አጭር መግለጫ፤ “የትግራይ ህዝብ የህወሐትን አውዳሚ እና ጸረ ህዝብ ስርዓት በመለወጥ ሰላሙን ለማረጋገጥ እና ሁለንተናዊ ነጻነቱን ለመቀዳጀት የሚያደርጋቸውን የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴዎች ያለቅድመ-ሁኔታ እንደሚደግፍ” አስታውቋል። የፖለቲካ ፓርቲው “ህወሐት በኢትዮጵያ ሕዝብ እና በሀገሪቱ ብሄራዊ ጥቅሞች ላይ አደጋ የጋረጠ ቡድን መሆኑን” ገልጿል። የትግራይ ሕዝብ እየደረሰበት ያለውን ሰቆቃ ለአፍታም ዘንግተነው አናውቅም ያለው በኢሮብ፣ በእንደርታ እና በኩናማ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ በሚገባ እገነዘባለሁ ብሏል በመግለጫው። የአማራ ሕዝብ በወንድሙ የትግራይ ሕዝብ ማለትም በትግራይ፣ ስር የሰደደ በደል እንዲቆምም ቁርጠኛ አቋም ስናራምድ መቆየታችን ማስታወስ እንወዳለን ብሏል። #Ethiopia #Tigray #Amhara #Nama #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa

  • ስፔን የአለም ሻምፒዮን #WorldCup #FIFAWorldCup #WorldCup2026 #Argentina #Spain #Football

  • ዛሬ ማን ያሸንፋል? የአለም ዋንጫ ፍፃሜ #WorldCup #FIFAWorldCup #WorldCup2026 #Argentina #Spain #Football

  • 19 июл.2 0881

    ኳስ አበደች እንግሊዝ 6-4 ፈረንሳይ #WorldCup #FIFAWorldCup #WorldCup2026 #England #France #Football

  • 18 июл.1 8923

    видео или голосовое, без подписи

  • 18 июл.2 6083

    видео или голосовое, без подписи

  • 18 июл.1 4203

    የሱዳኑ መሪ ጄነራል አብዱል ፋታ አልቡርሃን አስመራ መግባታቸው ታውቋል። ጄነራሉ በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፤ ሁለቱ ሀገራት በቃጠናቂ፣ በዓለም አቀፋዊ እና በጋራ ጉዳዮቻቸው ላይ እንደሚወያዩ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል በ ኤክስ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። ሁለቱ ሀገራት በአሁኑ ወቅት ከኢትዮጵያ ጋር ቅራኔ ውስጥ መግባታቸው ተደጋግሞ ይነሳል። ኢትዮጵያ በሁለቱ ሀገራት ላይ ከምታቀርባቸው ክሶች መካከል “የተለያዩ ቡድኖችን እያስታጠቁ እና በሀገሪቱ ውስጣዊ ጉዳዮች ላይ እጃቸውን እያስገቡ ነው” የሚለው ይገኝበታል። #Eritrea #Sudan #HornAfrica #EthiopianNews #AmharicNews #EthioTube #Africa

  • አርጀንቲና እንግሊዝን ጥላ ወደ ፍፃሜ ዋንጫው የስፔን ነው የአርጀንቲና? #WorldCup #FIFAWorldCup #WorldCup2026 #Argentina #Spain #Football

  • የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ "ዘረኛ መልእክት" አሰተላልፈዋል ሲሉ ወቀሱ የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአማራ ክልል ደብረ ማርቆስ ከተማ ተገኝተው "ዘረኛ መልእክት" አሰተላልፈዋል ሲሉ ወቀሱ ዐቢይ የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ ባስመረቁበት ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ *"ይህ ህዝብ በአፄ ዮሃንስ ጊዜ በነበረው ሁኔታ ምን እንደደረሰበት ያውቃል፣* በጣልያን ጊዜ ምን እንደደረሰበት ያውቃል" ማለታቸው ይታወሳል። ዐቢይ አክለውም "የማያግባቡን ጉዳዮች ካሉ በሰላማዊ፣ በሰለጠነ የፖለቲካ አግባብ መነጋገር ይቻላል። ​ከዛ ውጪ ያለው አማራጭ ኢትዮጵያን አይጠቅምም፣ አማራን አይጠቅምም፣ ጎጃምን አይጠቅምም፣ ምስራቅ ጎጃምን አይጠቅም" ሲሉ በዝግጅቱ ላይ ተናግረዋል። ይህን ገለፃቸውን ተከትሎ በአሁን ወቅት ትግራይ ክልልን እየመሩ የሚገኙት ደብረፂዮን፤ "በህዝቦች መካከል ግጭትና አለመተማመን መፍጠር እንደ ቁልፍ የፖለቲካ መሳሪያ በመጠቀም በስልጣን ለመቆየት የተጉ አካላት፣ ባለፉት አመታት የአማራና የትግራይ ህዝቦችን በማያበራ ግጭትና ቁርሾ ውስጥ ለማስገባት ያልተደረገ ጥረት ሆነ ያልተፈነቀለም ድንጋይ የለም" ብለዋል። በባህልና በታሪክ የተሳሰሩ ወንድማማች ህዝቦች፣ ሁሉንም ውስብስብ የከፋፋዮች ሴራ በማክሸፍ ወንድማዊ ትስስራቸውን አስቀጥለዋል ያሉት የህወሓት ሊቀመንበር፤ "እነዚህ ህዝቦችን በማጋጨት የስልጣን ዘመናቸውን ለማርዘም የሚጥሩ አካላት፣ በጊዜያቸው ታላቅ ገድል በመፈፀም የህዝባቸውንና ሀገራቸውን ክብርና ህልውና ያስቀጠሉ የቀድሞ የትግራይ ጅግኖች አመራርን ስም እያጎደፉ መሆኑን ተናግረዋል። #Ethiopia

  • የብዙዎች ግምት የተሰጣት ፈረንሳይ በስፔን 2ለ0 ተረታች ስፔን የእንግሊዝ እና አርጀንቲና አሸናፊን በእሁዱ ፍፃሜ የምትገጥም ይሆናል ዋንጫው የማን ነው? #WorldCup #FIFAWorldCup #WorldCup2026 #France #Spain #Football

EthioTube — tgindex